ar
Feedback

لا تقع ضحية للمخادعين! تيليمتريو يكتشف ويُميّز هذه القنوات 👉 إذا كنت تريد رؤية العلامة، اشترك 👈

የአኺራ ተጓዦች☁️

የአኺራ ተጓዦች☁️

الذهاب إلى القناة على Telegram

ኢንሻአላህ በዚህ ቻናል ላይ ሱናን የሚደግፉ የሚያነቃቁ እና አሪፍ አሪፍ የሆኑ ስንቆችን እንለቃለን inshallah የሱና ቻናሎች መገኛ @bahruteka @shakirsultan @alateriqilhaq @abdulham

إظهار المزيد
لم يتم تحديد البلدالفئة غير محددة
982
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
+527 أيام
+18330 أيام
أرشيف المشاركات
እስኪ በብዙ ነገር የደከመን ቀናችንን በቁርአን እናነቃቃው🫀 @nesihetulinisa

🚫 የኢኽዋኖች ጥመት ለህዝቡ መነገር አለበት ! 🔹 እውን የአካዳሚ ትምህርት ዒባዳ ነውን ? ሀገራችን ላይ ስመጥር ከሆኑ የኢኽዋን መሪዮች አንዱ የሆነው የካሚል ሸምሱ ወንድም አቶ ሹዓይብ ሸምሱ የአላህ መልእክተኛ ከሽርክ በማስጠንቀቅ ተውሒድ ባስተማሩበት ሜምበር ላይ ወጥቶ ለጁሙዓ የተሰበሰበውን ሙስሊም የአካዳሚ ትምህርት ዒባዳ ነው ብላችሁ ንያ እንድታደርጉ አደራ እላችኋለሁ ይላል ። በዚህ ብቻ አያቆምም ድሮ እኛ አለማዊና ዲናዊ ትምህርት ብለን የከፋፈልነው የተሳሳተ ግንዛቤ ወደ ልጆቻችን መተላለፍ የለበትም ይላል ።‼ እንዲህ እያለ ፊዚክስና ኬሚስትሪ ወይም ባዮሎጂና ሲቪክ የመሳሰሉ ትምህርቶች ዒባዳ መሆኖቸውን በጁሙዓ ኹጥባ ላይ ያውጃል ። አይደለም ከሚሉት ያስጠነቅቃል ። ወደ ምላሽ መስጠት ከመሄዴ በፊት ንግግሩን ( ኹጥባውን) በሚከተለው ሊንክ ገብታችሁ አዳምጡት : – ⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️ https://drive.google.com/file/d/1G-IAkoIq7rfkXVESogD-_2KJ4jMI8Rob/view?usp=drivesdk ለአቶ ሹዓይብ ሸምሱ የማቀርበው ጥያቄ አንደኛ :— ለመሆኑ መሬት በፀሀይ ዙሪያ ትዞራለች ፀሀይ የማትንቀሳቀስ አካል ነች የሚለውን ፍልስፍና ሲግቱን መሬትን እንደ ኳስ አድርገው በአንድ እጃቸው ይዘው እያሽከረከሩ ፀሀይን በሚያበራ ባትሪ መስለው በሌላ እጃቸው ይዞው መሬት እየተሽከረከረች ብርሀንዋን ከማይንቀሳቀሰው ፀሀይ ታገኛለች ሲሉን የነበረው ኩፍር ነው ወይስ ዒባዳ ? መልሱን ለማገኘት የፀሀይ ጉዞ የሚለውን አጭር ማስታወሻ በሚቀጥለው ሊንክ ገብታችሁ አንብቡ : – 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/bahruteka/1694 ሁለተኛ :— የሰው ልጅ ከዝንጆሮ ነው የመጣው የሚለው የዳርዊን ፍልስፍና ኩፍር ነው ወይስ ዒባዳ ? ይህ አስተሳሰብ ኩፍር ለመሆኑ ቁጥር ስፍር የሌላቸው የቁርኣንና ሐዲስ መረጃዎች ቢኖሩም ለማሳጠር የሚከተሉትን የቁርኣን አንቀፆች ልጠቀስ : – وَلَقَدْ خَلَقْنَا الْإِنسَانَ مِن سُلَالَةٍ مِّن طِينٍ በእርግጥም ሰውን ከነጠረ ጭቃ ፈጠርነው ፡፡ ثُمَّ جَعَلْنَاهُ نُطْفَةً فِي قَرَارٍ مَّكِينٍ ከዚያም በተጠበቀ መርጊያ ውስጥ የፍትወት ጠብታ አደረግነው ፡፡ ثُمَّ خَلَقْنَا النُّطْفَةَ عَلَقَةً فَخَلَقْنَا الْعَلَقَةَ مُضْغَةً فَخَلَقْنَا الْمُضْغَةَ عِظَامًا فَكَسَوْنَا الْعِظَامَ لَحْمًا ثُمَّ أَنشَأْنَاهُ خَلْقًا آخَرَ ۚ فَتَبَارَكَ اللَّهُ أَحْسَنُ الْخَالِقِينَ ከዚያም ጠብታዋን (በአርባ ቀን) የረጋ ደም አድርገን ፈጠርን ፡፡ የረጋውንም ደም ቁራጭ ሥጋ አድርገን ፈጠርን ፡፡ ቁራጯንም ሥጋ አጥንቶች አድርገን ፈጠርን ፡፡ አጥንቶቹንም ሥጋን አለበስናቸው ፡፡ ከዚያም (ነፍስን በመዝራት) ሌላ ፍጥረትን አድርገን አስገኘነው ፡፡ ከሰዓሊዎችም ሁሉ በላጭ የሆነው አላህ ላቀ "፡፡ (12–14) المؤمنون የምእምናን ምእራፍ ከ12 – 14 ሶስተኛ :— ስለሴቶች መብትና የራስን መብት በራስ ስለመወሰንና የመሳሰሉት የሰው ሰራሽ ህጎችን የሚያስተምረው ሲቪክ መማር ዒባዳ ነው ብለህ ነው የምታምውና ሙስሊሞች ዒባዳ ነው ብለው ንያ እንዲያደርጉ አደራ የምትለው ? አራተኛ :— የዚህ አይነቱ ፍልስፍናና መለኮታዊ የህይወት መመሪያ የሆነው የቁርኣንና ሐዲስ አስተምሮ የተለያዩ ናቸው ማለት የተሳሳተ ግንዛቤ ስለሆነ ወደ ልጆቻችን መተላለፍ የለበትም የምትለው የአላህን ቃል አፕሩቭ ማድረግ ከማይቻሉ የሰው ልጆች ፍልስፍና ጋር አንድ ነው ብሎ ማስተማር ዒባዳ ስለሆነ ነው ? እነዚህን የተወሰኑ ነጥቦች ያነሳሁት የወደቀን ነገር የሚያነሳው አያጣም ስለሚባል እንጂ የንግግሩ ውዳቂነት ውድቅ ከማድረግ ያብቃቃ ነበር ። ለማንኛውም ኢኽዋኖች ማለት እነዚህ ናቸው ልብ ያለው ልብ ይበል ። https://t.me/bahruteka

ወይ የወይዘሪት አህባሽ ነገር ለቅሶሽ በዝቶ ሳቅሽ ይነስ እንዲህ አይነቱንም ሞኝ እያየን ነው ! ~ ያ ረብ የተቀበረበቸው የውሸት ተክል ከስሩ አድርቅላቸው ያለወቁትን የልቀመሱትን የተውሒድ ጠአም እሳ
ወይ የወይዘሪት አህባሽ ነገር ለቅሶሽ በዝቶ ሳቅሽ ይነስ እንዲህ አይነቱንም ሞኝ እያየን ነው ! ~ ያ ረብ የተቀበረበቸው የውሸት ተክል ከስሩ አድርቅላቸው ያለወቁትን የልቀመሱትን የተውሒድ ጠአም እሳያቸው ወሏሂ በጣም ያሳዝናሉ መካ ቢባል ምን ሊናገር እንደሚችል አስባችሁታል ። ቆይ በየ ግዜ እየመጣችሁ ወሃቢያ እንትንያ እያላችሁ እትት ግትት የምትሉ ጨጓራችሁን አትፈልጉትም እንዴ ? አሁንስ በዛ ምርር አይላችሁም  ሁልጊዜ ማታ ማታ በህልማችሁ ወሃቢያን ጥርግርግ አደረግን ስትሉ ጠዋት ስተነሱ ልጥጥ ያለ ቅዠት የሚሆነው ነገር ! ወይ የወይዘሪት አህባሽ ነገር ለቅሶሽ በዝቶ ሳቅሽ ይነስ join #telegram ቻናል https://t.me/abuabdurahmen

صباح الخیر ኣላህ ዛሬን እንድናይ በሰላም አድርሶናል። አዲስ ቀን አዲስ እድል ነው። ለኢባዳ፣ለተውባ፣ለመልካም ስራ እና ወደ ኣላህ የመቃረብ እድል ነው። 🌕ቀንሽን በሶላት ጀምሪ 🌕ልብሽን በዚክር አብሪ 🌕አንደበትሽን በመልካም ንግግር አስውቢ 🌕ቀንሽንም በተግባር አሳምሪ ረቡና ዛሬን በበረካ በሂዳያና በራህማ ይሙላልን @nesihetulinisa

ወጣቶች በዲናቹ ወኔ እንዲኖራቹ ከፈለጋቹ የኡስታዝ ባህሩ ተካን እና የኡስታዝ ሻኪር ሱልጣንን ሙሀደራ ኮምኩሙ ©ቻናላቸውን ለማግኘት 👇👇 @bahruteka @shakirsultan

✅   የዓሹራእ ፆም ታሪክና የሑሰይን ሞት አይገናኙም !     ዓሹራእ ነብዩላሂ ሙሳን አላህ ነጃ ያወጣበትና ፊርዐውንን ከነሰራዊቱ ያጠፋበት ቀን ሲሆን ነብዩ ከመላካቸው በፊትም አዩሁዶች ይፆሙት ነበር ። ዓኢሻ ባወራችውና ኢማሙል ቡኻርይ በዘገቡት ሐዲስ ቁረሾችም ነብዩ ከመላካቸው በፊት ይፆሙት እንደነበርና ነብዩ ወደ መዲና ሲሄዱ ራሳቸውም ፁመውት ፁሙት ብለው ያዘዙ መሆኑን ያረጋግጣል ።    ሑሰይን የተገደለው ሙሐረም 10 / 61ኛው አመተ ሂጅሪያ ላይ ነው ። በመሆኑም የሑሰይን መገደል ከዓሹራእ ፆም ጋር የሚያገናኘው ነገር የለም ። ነገር ግን ቢዳዓ ያሳወረው ዐይን ሱናን ማየት አይችልምና ሺዓዎች ነብዩ ሙሐመድ ሙሳንና ተከታዮቹን ነጃ አውጥቶ ፊርዓውንና ሰራዊቱን በማጥፋት ለነብዩላሂ ሙሳ ድል በመስጠቱ አላህን ለማመስገንና በተገኘው ድል ለመደሰት የፆሙትን የዓሹራእ ቀን ከአኼራ በፊት በዱንያ ላይ ራሳቸውን ያሰቃዩበታል ።    ኢስላም አንድ ሰው ሲሞት የእለቱም ቀን ቢሆን ድምፅ ከፍ አድርጎ ማልቀስና ሙሾ ማውረድ እንዲሁም ልብስ መቅደድና ራስን መግረፍን ይከለክላል ። ሺዓዎች ና ብለው አስጠርተው ከመካ እንዲወጣ ካደረጉትና ለዑበዱላሂ ኢብኑ ዚያድ ሰው በላ አሽከሮች አስረክበው ተገሎ ጭንቅላቱ እንዲቆረጥ ካደረጉ በኋላ አዛኝ መስለው እስከ ቂያማ ራሳቸውን እያሰቃዩና እየቀጡ ያለቅሳሉ  ⁉️      በሱና ብርሃን ከቢዳዓ ጨለማ ነጃ ላወጣን አምላካችን ምስጋና ይገባው ። https://t.me/bahruteka

በኡስታዙና ሻኪር ቢን ሱልጣን🎧 @nesihetulinisa

[ ወንድሜ ] ------------\\\\ ማየት አልፈልግም ህይወትህ ቅጥ ሲያጣ፣ ሲመክሩህ ተመከር ምንም ሳትቆጣ፣ ያንንቀን አስታውሰው የቀብርህን ጣጣ፣ ከውሸት ተመለስ ካለህበት ውጣ፣ የሱና ሰው መስለህ ሴቶችን አትቅጣ፣ ጭራሽ ሳትፈራ የአላህን ቁጣ፣ አንዷን ይዘህ ከአንዷ ስዘል እንደጦጣ ኑሮህ ሲበሳቆል ትላለህ የኔ እጣ ፣ አላህን እያመፅክ ደስታህ ከየት ይምጣ፣ ጆሮዬ እየሠማህ ሀዲሡን ስቀራ፣ ተግባርህን ሳየው  የዱርዬ ስራ፣ እንደት ብዬ ልመን አጋባኸኝ ግራ፣ ቃልና ተግባርህ  ርቆ እደተራራ፣ አንዷን በጅህ ይዘህ ስፅፍ ለአንዷ፣ አንዷ ስታምንህ  ዞርክ ወደ አንዷ፣ መዘርዘሬን ተኩት ይቅር አይወራ፣ ወንድሜ ተመከር ታው አላህን ፍራ፣ ሴት ልጅ አታታል ውሸትን አታውራ ጀግና አገኘሁ ብላ ለዲኑ የነቃ፣ አንተኑ እያሠበች ሁሉን ተደብቃ፣ የእሡ ነኝ እያለች ቃልህን ጠብቃ፣ ተግባርህን ሲታይ በወሬህ ተደቃ፣ ውደዱልኝ ብላ ቤተሰብ ጠይቃ፣ ከሷጋ ጨርሰህ ጉዳዩ ካበቃ፣ ያችም ካሰኘችህ ከልብህ ላይ ወድቃ፣ ልቀያይር ካሰብክ ሴትን ልጅ እንደቃ፣ ትታህ ትሄዳለች ላትመለስ ርቃ፣ ውሸት የሞላውን ተግባርህን አውቃ፣ ከሀሳቧ አውጥታ ከልቧላይ ፍቃ፣        ያኔ እሷም በተራዋ ስጥልህ እንደቃ፣ መለደምህ ላይቀር  ስትታይህ ርቃ፣ ዛሬ ላይ ታማኝሁን ማታለልህ ይብቃ፣ አስተውል ወንድሜ ሳትነቃብህ ንቃ፣ አቅሙ ካለህ አግባ በሀላል ተብቃቃ፣ (የሱና ቤት አይጠብም ተቀላቀሉን!) ➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘ https://t.me/menhaj_Aselefiya

صباح الخير 🌕 ከቀልብ 🫴🫀 ወደ ቀልብ🫴🫀 @nesihetulinisa

"ሴቶች ምን ሆነን ነው" ለባላችን ነው ከማንም በላይ ዝንጥ ማለት ያለብን ሆ ውጪ ያለው ምን ያደርግልናል።ሰርግ ቤት ስንሄድ ፏ ከምንለው በላይ ነው ለባላችን ፏ ማለት ያለብን። ባለችን ነገር መዋዋብ ግድ ነው እእ እኮ 🙌 ስረአት ዋ ተናግሬያለው🙌 @nesihetulinisa

🎧🫴🫀 @nesihetulinisa

ስትርትር @nesihetulinisa
ስትርትር @nesihetulinisa

ምክር ቢጤ ለወንድም እህቶቼ አንቺ እህቴ ሆይ! አንድ ወንድ አላህን ፈርቶ ሀራምን ትቶ ወደ ሀላል እንሂድ ሲል እርሱን ወደ ሀራም መጎተት ፍቅር አይደለም ፈተና ነው። እውነተኛ ፍቅር ሰውን ወደ አላህ ያቀርባል እንጂ ከአላህ አያርቀውም። የሚወድሽ ከሆነ ሀላልን ይፈልጋል ሀላልን የማይፈልግ ደግሞ ስሜቱን እንጂ ደህንነትሽን አይፈልግም። 🌷 ሀራም ላይ የተጀመረ ነገር በልብ ላይ ቁስል ያስቀራል ሀላል ላይ የተጀመረ ነገር ደግሞ ሁሌም ደስታን ያመጣል ወንድሜ ሆይ! በሶሻል ሚዲያ ላይ ልብን የሚፈትኑ መንገዶችን መከተል ቀላል ነው ግን ሀላልን በትዕግስት መጠበቅ በአላህ ዘንድ ክብር ነው። ዛሬ ለአላህ ብለህ የተውከውን ነገር ነገ አላህ ከእርሱ የተሻለ በሆነ ነገር ይተካልሃል። قال رسول الله ﷺ: إِنَّكَ لَنْ تَدَعَ شَيْئًا لِلَّهِ عَزَّ وَجَلَّ إِلَّا بَدَّلَكَ اللَّهُ بِهِ مَا هُوَ خَيْرٌ لَكَ مِنْهُ አንተ ለአላህ ብለህ አንድን ነገር አትተውም አላህ ከእርሱ የተሻለን ነገር ካልተካልህ በቀር። 🌷 ሀራም ግንኙነት ጊዜያዊ ደስታ ነው ሀላል ደስታ ግን ሁሌም ዘውታሪ ነው https://t.me/Nasiha_forSelefiyyah https://t.me/Nasiha_forSelefiyyah

ከቀልብ 🫴🫀 ወደ ቀልብ 🫴🫀 አላህ ሆይ ቁርአንን ሰምተው ከሚጠቀሙት አድርገን ያ ረብ🤲 @nesihetulinisa

هلموا ایا اخوتی🎧👌 @nesihetulinisa

🌻🌕ጥዋትሽን በዚክር ጀምሪ ቀንሽን በበረካ ታገኚዋለሽ🌻 @nesihetulinisa
🌻🌕ጥዋትሽን በዚክር ጀምሪ ቀንሽን በበረካ ታገኚዋለሽ🌻 @nesihetulinisa

ለኛ ነው እህቴ 👆 @nesihetulinisa

ቲክቶክ ሰፈር እየዋልሽ ቃሪእ ነውኮ እያልሽ አጅነቢይ ላይ እያፈጠጥሽ ንፅፅር ነው እያልሽ ላይቭ ገብተሽ ከአጅነቢይ ጋር እያወራሽ ቀልድኮ ነው እያልሽ አጅነቢይ እያየሽ ለመዝናናትኮ ነው እያልሽ ካስ
ቲክቶክ ሰፈር እየዋልሽ ቃሪእ ነውኮ እያልሽ አጅነቢይ ላይ እያፈጠጥሽ ንፅፅር ነው እያልሽ ላይቭ ገብተሽ ከአጅነቢይ ጋር እያወራሽ ቀልድኮ ነው እያልሽ አጅነቢይ እያየሽ ለመዝናናትኮ ነው እያልሽ ካስ እያየሽ ያውም አውራቸውን ገልጠው እየተጫወቱ እያየሽ ልክ እንደ ወንድሜኮ ነው ማየው እያልሽ ከአጅነቢይ ጋር እየተጀናጀንሽ ነገኮ ያገባኛል እጮኛዬ ነው እያልሽ በሀራም ፍቅር እየተጨማለቅሽ ዋናው ልብ ነው እያልሽ ኒቃብ ጅልባብን ጠልተሽ በነሺቲ በነሱሪ በነቱርክ ቀሚስ ተገላልጠሽ እየወጣሽ እሺ የቱ ጋር ነው የሙእሚን ሴት ሀያእ እና አደብ ያለሽ? ያ ኢላሂ ሴቶቻችንኮ የአንተን ድንበር በአመፅ በማለፍኮ ጥግ ደርሰዋል። ኢላሂ ሂዳያ ሚፈልጉትን ምራቸው ጥመትን ሚፈልጉትን አቁስላቸው🤲 https://t.me/Abu_Umer1 https://t.me/NasihaLishebab https://t.me/NasihaLishebab

👉 ለፈገግታ ! ሚስት, ባልዋን በእውነት ትወደኛለህ ? ብላ ጠየቀችው ! ባልም, አው እንጂ እወድሻለሁ ! አላት ። ሚስትም, ታዲያ ለምንድነው ብዙ ጊዜ የማታየኝ ? አለችው ! ባልም, ሐኪምች በቀጥታ ወደ ፀሀይ አትመልከቱ ብለው ስለሚመክሩ ነው ብሎ መለሰላት !። http://t.me/bahruteka