🌹قَـــنَـــاةُ بِـــنـــتْ مُـــحَـــمَّـــد 🌹
الذهاب إلى القناة على Telegram
إظهار المزيد
لم يتم تحديد البلدالفئة غير محددة
1 383
المشتركون
+624 ساعات
+3437 أيام
+63530 أيام
أرشيف المشاركات
ጀግና ሴት በሚሰጧት መጥፎ እይታ ቦታ የላትም
እደት መሻሻል እዳለባት ጠንቅቃ የምታውቅ ናት ።
ጀግና ሴት ሁኚ በሁሉም ነገር የማትርታ ያቺን ሴት ሁኚ ጀግናዬ
_• የትልቅ ስኬት መነሻ ጥልቅ ፍላጎት ነው!_
_«ይሄን ሁሌም በአይምሯችን ማሰብ አለብን፤ ብዙም ያልተቀጣጠለ እሳት ብዙ ሙቀት እንደማይሰጠን ሁሉ ደካማ ፍላጎትም ደካማ ውጤት ነው የሚሰጠን። ሁሌም የማይበርድ ፍላጎት የማይቋረጥ ፅኑ መሻት ያስፈልገናል።»_
አድስ ሙሐደራ ደሴ አረብ ገንዳ መስጅድ
💉ስለ ሽርክና ተያያዥ ርዕሶች ምረጥ ምክር
🎙በኡስታዝ አቡ ሒዛም (ሀፊዘሁሏህ)
t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
ምን ላይ ነሽ እህቴ
እያለቀሽ ነው ልብሽ ቁስል ሁኗል?
ድሮ ያሰብሻቸው ህልሞችሽ ጠፍተዋል
ምን ላይነሽ እህቴሀሳብሽ ምንድነው?
ቀርቦ ለማይጠቅምሽ ስለሄደ አዝነሽ ነው
እስኪ እንነጋገር አለሁሽ እያለ ፌዝ ከሚያፌዝብሽ
እርቆሽ ቢሻገር እኮ ነው ሚሻልሽ
መሰበር ይሻላል ወይንስ መገኘት
ልክ እንደ ህፃን ልጅ በቃላት መሞኘት
ሂድበይው,,,,,,,
ግን ደግሞ አልቅሰሽ ተሰብረሽ አይደለም
ፈገግ ብለሽ ሸኝው አይከፋም ግድ የለም
ኑሮ ላልጠቀመሽ ሻንጣ ማዘጋጀት
የሰርቶ ክፍያ የባንክ የለው በጀት
እሱ እንደሰበረሽ ለማሳዬት ብለሽ
እስቶሪሽ ላይ ወተሽ ሞትኩ ሄድኩኝ እያልሽ
ግድ ሐማይሰጠው ኩራት የለገሰሽ
ምነካሽ እህቴ ግድ የለም ተመለሽ
“ልቦችን የምታናውጥና አእምሮን የምትማርክ ምርጥ ቲላዋ”
🎙“በወንድማችን አንዋር ከራያ”
t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
Repost from ስለ ቀልባችን
➲በነገራችን ላይ..በሐራም የተጀመረ ጉዞ ፍጻሜው በረካ የለውም።የዛሬው ዘመን ወጣቶች ትዳር መፍረስ ትልቁና የመጀመሪያው ሰንሰለት የሚቀጠለው ከትዳር በፊት በሚደረጉ ስህተቶች ነው። ምክኒያቱም ጅማሮው በሐራም የፍቅር ግንኙነት ላይ የቆየ፣ በድብቅና በኃጢአት የተገነባ ግንኙነት ፍጻሜው ያምራል ተብሎ አይታሰብም። ጌታችን አላህ በከለከለው መንገድ የተቃረቡ ልቦች፣ በትዳር ጥላ ስር ዘላቂ ሰላምና በረካን ሊያገኙ አይችሉም።
በሐራም ግንኙነት ውስጥ ያለው ውበትና መሳሳብ የሰይጣን አሸብራቂ ስራ በመሆኑ፣ ያ ግንኙነት ወደ ሐላል ትዳር ሲቀየር ያ የውሸት መጋረጃ ይቀደዳል። በሐራም ውስጥ የነበረው የውሸት ናፍቆት በትዳር ውስጥ ወደ መሰላቸትና እርስ በርስ መናናቅ ይለወጣል። ጅማሮው አላህን በማስቆጣት የሆነ ነገር፣ ፍጻሜው ውድመት መሆኑ የማይቀር የእውነት ህግ ነው።
አላህን በመፍራት ላይ ያልተመሰረተ ትዳር አሸዋ ላይ እንደተሰራ ቤት ነው። መሠረቱ የላላ ቤት አውሎ ንፋስ ሲመጣ ፍርክስክሱ እንደሚወጣው ሁሉ፣ ተቅዋ የሌለውም ትዳር በትናንሽ ፈተናዎች ይናዳል።በትዳር ውስጥ አላህን መፍራት ሲኖር እያንዳንዱ አካል የሌላኛውን ሐቅ ያከብራል፤ ባል የሚስቱን ደካማ ጎን በትዕግስት ያልፋል፤ ሚስትም የባሏን ልፋትና ደረጃ ትጠብቃለች። አላህን መፍራት በሌለበት ቤት ውስጥ ግን ኩራት፣ እራስ ወዳድነት፣ አለመቻቻልና ምላሰኝነት ይነግሳሉ። አንደኛው ወገን ለሌላኛው ክብርና እውቅና አይሰጥም። አላህ የሌለበት ቤት የጨለማ ቤት ነው፤ ጭቅጭቅና ሰላም ማጣት አይለየውም።
አላህ ላላገቡት በሐላል ጎዳና የልብ እርካታ የሚሆን መልካም የትዳር አጋርን ይለግሳቸው፤ ያገቡትንም ትዳራቸውን በፍቅር፣ በረካና በተቅዋ አጅቦ እስከ ጀነት የሚያዘልቅ ያድርግላቸው።
~
t.me/Sle_qelbachn1
t.me/Sle_qelbachn1
📚የሠለፍያ ጎዳና ከጥመት ለመዳን ዋና ዋስትና ነው
🎙️ ውዱ ኡስታዛችን፦ ኡስታዝ ኸድር አህመድ አላህ ይጠብቀውና
t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
3ኛው የኪታብ ኮርስ አልቀዋኢዱል ሙስላ ተጀምሯል
በታላቁ ሸይኽ ዐሊይ አራዚህይ ሀፊዘሁሏህ
https://t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy?livestream=144b3a59c732531013
Repost from شـبـاب السـلــفـــيـــيــن
✍️ኢብኑ ሙነወር ሆይ ያለ ድንበር ማለፍ በክብር እንወድሀለን።
በእያንዳንዱ አቋምህ አብረን ስንሰለፍ፡
በመሀይማኖች ምንም ብንዘለፍ፡
#እናከብርሀለን_ያለ_ድንበር_ማለፍ፡
t.me/nuredinal_arebi
t.me/nuredinal_arebi
#እራስሽን እራስሽ እምታክሚባቸው ዘዴዎች
#ስሜትሽ አዛዥሽ አይሁን
ህመም ይሰማሻል እንጂ አንቺ ህመሙ አይደለሽም፡፡
#ባዶነትሽን ሙዪው
በሰዎች የተተወውን ክፍተት በእውቀትና በስራ ሙይው፡፡
#ትውስታሽን ቆልፊ
ወደ ኋላ የሚጎትቱሽን ፎቶዎችና መልእክቶች ያለ ርህራሄ አጥፊ፡፡
#ብቸኝነትሽን ውደጂው
ብቻሽን መሆን መጎዳት ሳይሆን ራስን የማግኘት እድል ነው፡፡
#አዲስ ራዕይ ፅንሺ
*የተሰበረውን ልብሽን አዲስ ህልም እንዲያልም አስገድጂው።*
አድስ ሙሐደራ ደሴ አረብ ገንዳ መስጅድ
💉ስለ ተውሒድና ሽርክ ምረጥ ምክር
🎙በኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር (ሀፊዘሁሏህ)
t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
አጠር መጠን ያለች ኮርስ በኡስታዝ ኢብን ሙነወር ሀፊዘሁሏሁ ወረዓ
ወደ ቻናሉ ለመቀላቀል
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/yedaewachannel
https://t.me/yedaewachannel
👉ወሎ ምድር ኮንቦልቻ ዛሬ ልዩ ፕሮግራም
⭕️«ወሎ በልጆቿ»⭕️
---------------------
የዑለሞች ምድር የብርሀን ማማ፡
የእዝነት የደግነት ውብ የፍቅር ካስማ፡
ደምቃ በልጆቿ ኮንቦልቻ ከተማ፡
በሁሉም አቅጣጫ ደዕዋ እየተሰማ፡
ወጣቱ ከየትም ተጠራርቶ ቀርቧል፡
ወሎ ምድር ዛሬ ልዩ ዝናብ ዘንቧል፡
ዳግም እንደገና ይህ ትውልድ አብቧል፡
ትውልዱ ለእውነት እጁን እየሰጠ፡
ህዝባችን በተውሒድ እየተለወጠ፡
ጠላት እየሟሟ እንደ ጨው ቀለጠ፡
አብሽር የኔ ህዝብ
የታሪክ ሰገነት የሞላበት ምድር፡
የፅናት ተምሳሌት የውብ ጀግኖች ስድር፡
የሸጋዎች ሀገር የውበት አውድማ፡
የአሊሞች መፍለቂያ የደጎች ባድማ፡
የፍቅር ተምሳሌት የመውደድ ውብ አርማ፡
የእስልምና ታሪክ የታላቆች ፊርማ፡
ከትናንት እስካሁን ጀግና እማይጠፋብሽ፡
አሊም የሐቅ ሰው ሰው እሚበቅልብሽ፡
የፍቅር የሰላም ፅናት ነው መረብሽ፡
ተውሒድና ሱናን የሚያስተምሩልሽ፡
ከውስጥሽ ተፈጥረው የሚዘምሩልሽ፡
ሐቅን እየሰሙ የማያቃልሉ፡
ሽርክን ለመፋለም ሁሌ እሚታገሉ፡
እውነተኛ አፍቃሪ ምርጥ ልጆች አሉ፡
ከፊሎቹ ዛሬ ደዕዋ ታድመዋል፡
ስለ እውነት ሊሰሙ ኮንቦልቻ ተመዋል፡
የኔ ቢጤ ደግሞ ሔዷል ባህር ማዶ፡
ከሚወዳት ምድር #ከወሎ ተሰዶ፡
....ተመኘሁ አቦ...!!
ምነው ትንሽ ቅፅበት በሆንኩ አብሬያችሁ!?
ምነው በተገኘሁ ከመካከላችሁ!?
በደስታ ሰክሬ ምነው ባቀፍኳችሁ!?
ወንጀል ይሆን እንደ ከናንተ የለየኝ፡
ባህር ማዶ ወስዶ ናፍቆት ያሰቃየኝ፡
ለነፍሴ እንደዛ ነው ለኔ የሚታየኝ፡
....እውነት ነው!!
እርግጥ ቀንቻለሁ አልቅሻለሁ ዛሬ፡
ግን ደግሞ ለእናንተ የ'እውነት ነው ፍቅሬ፡
ንግግሬን ቆጠብኩ እናንተን አክብሬ፡
👉ለማንኛውም!!
ሰለፍያ አ'ቅ'ፋው በውብ አክናፎቿ፡
ለሐቅ አናብስቶች ተከፍተው ቀሮቿ፡
ሒዝብያን አባረው ተፈፅሞ ፍቿ፡
በደዕዋ ደምቃለች ወሎ በልጆቿ፡
t.me/nuredinal_arebi
t.me/nuredinal_arebi
የጥፋት መንደር ብዙ እህቶች ተምረው እዳልተማሩ የሆኑበት ሰፈር ኮመንት በመፃፍ ለፃፈላቸው ሁሉ መልስ በመመለስ ውድ ግዜያቸውን የሚጨርሱበት የሚራቆቱበት ሰፈር የኢብሊስ መንደር።
አላህ ሆይ ከጥፋት ግዜን በከንቱ ከመጨረስ አንተ ጠብቀን!!
✍አስቸኳይ የእርዳታ ጥሪ
አሰላምአለይኩም ወራህመቱሏሂ ወበረካትሁ
ዉድ ሙስሊም እህቶቸ ይህ በምስሉላይ የምትመለከቱት ወንድም ይማም ሁሴን አህመድ ይባላል
በባጃጅ ስራ የሚተዳደር ወንድማችን ነበር ነገርግን የኢድ ለት ጧት ሰዉ አድርሰን ብለዉት ለሶላት እንድደርስ ብሎ ሊያደርስ ሲሄድ መንገድ ላይ ድንገት ላም ትገባበትና ባጃጁ ይገለበጣል ።
እንደምታዩት ከባድ ጉዳት ደርሶበታል ለህክምና የተጠየቁት ገንዘብ 900 ሺብር ሲሆን ከአቅማቸዉ በላይ ሲሆንባቸዉ ወደኛ ብቅ አድርገዉታል ። ሰበብ እንሁን እራሱ ስለተመታ አልተሰፋም በቅርቡ ታልተሰፋ ለሌላ ህመም የመጋለጥ አቅሙ ሰፊ እንደሆነ ተነግሯቸዋል
እባካችሁ ተባበሩን ስንል በአሏህ ስም እንጠይቃችሁዋለን
አካዉንት 👇1000088439086
ኑሩ ሁሴን
1000331303748
"አህመድ ሁሴን
የግሩብ ሊንክ 👇
https://t.me/+Vp1lW-dOfOkwZjVk
ሁላችንም በገንዘብም በዱአም አድ በማድረግም ሌሎቺን በማስተባበርም እንተባበር
خرج علينا النبي ﷺ فقلنا: يا رسول الله، قد عَلِمْنا الله كيف نُسَلِّمُ عليك؛ فكَيف نُصَلِّي عليك؟ فقال: قولوا: اللَّهُمَّ صَلِّ على محمد وعلى آل محمد؛ كما صَلَّيْتَ على إبراهيم، إنَّك حميد مجيد، وبَارِكْ على محمد وعلى آل محمد؛ كما باركت على إبراهيم، إنَّك حميد مجيد».
ንግግሩ ውብነው ልብን የሚያረጥብ
ላስተነተነው ሰው የነፍስያምግብ
ከላይ የተሰጠን ከሀያሉ ጌታ፡፡
ምስጋናይደባው በጧትም በማታ፡፡
ያአሏህ ቁርአንን እንኳን ትንርጉሙን አውቀን እያስተነተንን ስንቀራው ዝም ብለን ስንሰማው ልብን የሚያረጥብ ነፍስያን የሚያረጋጋ ውብ ቃልኮነው
«
እራሳችሁን ተቀበሉ!
ለወሬ ማድመቅያነት በዘለለ እውነታን እየካዱ ለራስ አጓጉል ነገር መንገር አያበረታም። ተስብርያለሁ፣ ደክምያለሁ፣ ጠንካራ ይደለሁም፣ ተስፋ ቆርጫለሁ ለማለት ሳይሆን ማፈር ያለባችሁ በእነዚህ ስሜቶች ውስጥ ስትሰነብቱ ነው።
በቅጡ ካላለቀስሽ በደንብ መሳቅ እንዴት እንደሆነ ማወቅ ይጠፋሻል። ልክ ሞትን ብንክድ እንኳ መሞታችን እንደማይቀረው ሁሉ ስብራታችሁን ስለካዳችሁ የምትጎናፀፉት ጥንካሬ የለም።
ይገባኛል ይህ መራር እውነት ነው። ነገር ግን ወደዳችሁም ጠላችሁ የምትክዱት እውነታ እያላችሁ ልትበረቱ አይቻላችሁም። ይህን ለመረዳት ረጅም እድሜ መኖር፣ መሸበት አይጠበቅባችሁም ጥቂትን በጥልቀት ለማስተዋል ሞክሩ። ሁሉንም ነገር ዋጋ ከፍላችሁ ለመማር እራሳችሁን አታስገድዱት!
ህመማችሁን በዘላቂነት ሊፈውስላችሁ የሚችልን ነገር ምረጡ እንጂ ህመማችሁን የሚያስታግስላችሁ ማስታገሻ አታሳድዱ! »
የአሏህ መልእክተኛ ሰለላሁአለይሂ ወሰላም እንድህ አሉ
*ሳቅን አታብዙ ብዙ ሳቅ ልብን ይገላል*
_ኢብኑ ማጅህ ዘግበውታል አልባኒ ሶሂህ ብለውታል_
አንድ እናት ለልጇ እንድህ ስትል መከረች
እየውልህ ልጀ ከባድ የሆኑ ነገሮችን ፊትለፊት ተጋፈጣቸው ብዙተማሪወች የቀለላቸውንና የሚያውቁትን ነገር ደጋግመው ማንበብ ይመርጣሉ ምክናየቱም ያንን ሲያነቡ ብዙ ያወቁ ይመስላቸውና እኔኮ ሁሉንም አውቀዋለሁ የሚል በራስ የመተማመን የውሸት ስሜት ይሰጣቸዋል
ነገር ግን ከባድ የሆነውን እና የማይረዱትን ትምህርት ሲያው ስለሚጨንቃቸው ይሸሹታል
እናማ ልጀ የሚከብድህን ነገር ደጋግመህ አድርገው ምክናየቱም እድገትህ የተሸሸገው እዛ እከበደህ ነገር ውስጥ ነው፡፡
ምነኛ ድንቅ የሆነ ምክር ነው ቁርአን ከበደን ብለን ስንቶቻችን ነን ሸሽተን የተውነው ኪታብ ጀምረን ስንቶቻችንን ነን አይገባኝም ብለን በመንገድ የቀረነው
ስንቶቻችን ነን ሙሲባ ሲደርስብን የሙሲባችን አጅር በሶብር ውስጥ ሆኖ ሳለ ሶብርን አተን ከአሏህ ጋር የተጣላነው
መልሱን ከራሳችን ለራሳችን ፡፡
