🌹قَـــنَـــاةُ بِـــنـــتْ مُـــحَـــمَّـــد 🌹
الذهاب إلى القناة على Telegram
إظهار المزيد
لم يتم تحديد البلدالفئة غير محددة
1 376
المشتركون
+1824 ساعات
+3637 أيام
+64630 أيام
أرشيف المشاركات
ምቀኝነት
ሓቲም አል-አሶም "አሏህ ይዘንላቸዉና" እንዲህ አሉ፦↓
"ሰዎች እርስ በእርሳቸዉ ሲመቀኛኙ አየሁ ከዛም የአሏህን ቃል ተመለከትኩና↓
نَحْنُ قَسَمْنَا بَيْنَهُم مَّعِيشَتَهُمْ فِي الْحَيَاةِ الدُّنْيَا
<እኛ በቅርቢቱ ሕይወት ኑሯቸውን በመካከላቸው አከፋፍለናል።>
ምቀኝነትን ተዉኩኝ ምክኒያቱም ምቀኝነት የአሏህ ክፍፍል መቃወም ነዉና።
📚 مختصر منهاج القاصدين (28)
ዛሬ እንደገና ተነስተናል....
ምን ያህል ነገር ትናንት እንዳሳለፍን አላህ ያውቃል።
ያለቀስነውንም፣ ዝም ብለን የተሸከምነውንም እርሱ ያውቃል።
ነገር ግን ይሄ ጧት ሌላ ዕድል ይዞ መጥቷል።
ልባችን ትንሽ ቢደክምም እንደገና እንጀምር።
የትናንትን ስህተት ዛሬ ላለመድገም እንሞክር፣
ከአላህም የራቅንከሆነ እንደገና ወደ እርሱ እንመለስ።
ምናልባት ዛሬ የምንጠብቀው ዱዓ መልስ ይሆናል።
ምናልባትም የደከመው ልባችን በሰላም ይሞላ ይሆናል።
አላህዬ ዛሬን ከምንጠብቀው በላይ ያሳምርልን።
መልካም ውሎ ይሁንላችሁ።
~እንኳን ያዩን ቀርቶ ስለኛ የሰሙ ቆንጆናት ይላሉ
~ዉበትና ጣፋጭ በእኛ ይመሰላሉ
~ሁሌም ያዩን ለታ የማናት ይላሉ
👉ሑረል ዐይን!
.እኛ ለባሎቻችን ስንስቅ ኮኮቦቹ
.ጨረቃ ወለደች እየተባባሉ
.እኛን ተጠግተዉ ብርሃን ተሞሎ
👉የዱኒያዋ እንስት !
~ቃላት አሳምረዉ
~ ስለናንተ ዉበት አድንቀዉ የፃፉ
~እኛ የመጣን ለት ትተዋችሁ አለፉ
👉 ሑረል ዐይን!
.ዉበት ከእኛ ነዉ ዘንቦ የሚንጠባጠበዉ ቆንጆ ጣፋጭ ዉብና መሳጭ የሚሉ ቃላቶች ሁሉ አይገልፁንም ያዩን ፈዘዉ ቀልባቸዉ ይሰረቃል።
.ጨረቃ ከእኛ ትደበቃለች አይናችን ሳይኳል የተኳለ ዉብ ነዉ። ጡባ ሊመን ኩና ለሁ ወካነ ለና።
👉የዱኒያዋ እንስት
~አይኖቻችንን አይተዉ ከዋክብት አፈሩ
~ድንቄም ብርሀን ሆን ብለዉ ተናገሩ
~ፀሀይዋ ጠለቀች ባለችበት ቦታ
~እኛን ስታይ ጊዜ ተደናግጣ ፈርታ
ዓኢሻ አስከተሉና በአላህ እምላለዉ አሸነፍናቸዉዉዷ እህቴ ሆይ! በጀነት ዉስጥ የሑረል ዐይኖች አለቃ ነሽ እንኳን ደስ አለሸ።
🌸ሁለቱ ዉብ እንስቶች🌸
ሁለት ታላላቅ ብርሀናት ቢያበሩ በምድር
ምድር ያችን ጊዜ እንዴት ትሆን ነበር።
~
t.me/https_Asselfya
🔖የሑረይል ዐይኗና የዱኒያዋ እንስት ተረብ!
👉ሑረል ዐይን!
እናንተ የዱኒያ ሴቶች ሆይ!ቁንጅናችን የሚያፈዝ ፀባያችን የሚማርክ በቁርአንና በሐድስ ተደጋግመን የተወሳን ዉብ እንስቶች ነን።የአላህ መልእክተኛ ስለኛ ያሉትን ስሙ፦
~አንድት የጀነት እንስት ወደ ምድር ብትመለከት ፀሐይንና ጨረቃን ጋርዳ ምድርን በተለየ ብርሃን ባካበበች ነበር።አላህ እዲህ ብሏል፦ፀባየ መልካሞች ፤መልከ ዉብ ሴቶች አሉ(አል-ረህማን.70)
~ጌታችን አላህ ለጀነት ሰዎች ያዘጋጀን ከዉቦች ሁሉ ያስበለጠን ያለ ምክንየት አይደለምና ቆንጆን ለማየት ከፉጋችሁ ወደ እኛ መዞር ብቻ ነዉ ምርጫችሁ
👉 የዱኒያዋ እንስት!
~በቁንጅና ከእናንተ በሰባ(70)እጥፍ እንድንበልጥ ተደርገን ተፈጥረናለ።
ጀነትን የተጎናፀፉ የዱኒያ ሴቶች ዱኒያ ላይ በደከሙት ዒባዳ ምክንያት ከሑረል አይን በ70 እጥፍ የበለጠ ቁንጅና ይኖራቸዋል ተብሎ በረሱል ስለሏሁ አለይሂ ወሰለም አንደበት እንደተነገረን አትዘንጉ።
👉ሑረል ዐይን!
~እኛ በጀነት ዉስጥ እጅ ለእጅ ተያይዘን ፍጥረታት ሰምቶ በማያዉቀዉ ተስረቅራቂ አንደበታችን እንድህ እያልን እንገጥማለን።
.እኛ ሰንስቅ እኮ
.የጨረቃ ገላ እስኪያልቅ ይሸረፋል .ሙሉ ፣ግማሸ ፣ሩብ እያለ ይጠፋል
ከዋክብት እንደ ቅጠል እግር ስር ይረግፋል
👉የዱኒያዋ እንስት!
~የዱኒያ ሴቶች ሆይ!እናታችን ዓኢሻ ሑረል ዓይኖች ይህንን ሲሉ ተገርመዉ እናንተን ወክለዉ የሰጡት ምላሸ አድምጡ ሑረል ዓይኖች እጅ ለእጅ ተያይዘዉ በአንድነት ሲገጥሙ የዱኒያ ሴቶች ተቃቅፈዉ ምላሽ ይሰጣሉ።
~ለጌታችን ሱጁድ ወርደናል
~ፁመናል፣,ሰድቀናል
~ በወዱእ ፊታችንም አብርቷል
~አላገኛችሁም እናንተ ይህን እድል
~እልፍ አዕላፍ አይኖች እኛላይ ያርፋሉ
Repost from አህሉ-ተውሂድ ኢስላሚክ ሴንተር - ሀርቡ
▶️ ግቡ ተጀመረ - 😂😘
አዲስ የኪታብ ደርስ📚ኪታቡ አልቀዋዒዱል ሙስላ 🎤በኡስታዝ አቡ ኢምራን 📔የኪታቡን PDF ለማግኘት https://t.me/sefinetunuh/9009 ደረሱ የሚሰጠዉ 📣በአህሉ-ተውሂድ መስጂድ - - https://t.me/sefinetunuh?livestream=2aa0f105b7a048c75d https://t.me/sefinetunuh?livestream=2aa0f105b7a048c75d
Repost from 𝑹𝙖𝙢𝙖𝙨 𝑨𝑳-𝑯𝒂𝒏𝒂𝒏𝒊 (ራማስ)
✅ ማስታወቂያ
ሶብር የአረብኛ ቋንቋ ትምህርት ቤት አዲስ ምዝገባ ጀምሯል ! 🟢
አረብኛ ቋንቋን ቁርዓንን እንዲሁም የተለያዩ የውጭ ቋንቋዎችን በቀላሉ እና ጥራት ባለው መንገድ መማር ይፈልጋሉ? እንግዲያውስ ሶብር የአረብኛ ቋንቋ ትምህርት ቤት ለእርስዎ በተሻለ ዝግጅት አጠናቆ ተማሪዎችን በመቀበል ላይ ይገኛል! ከጀማሪ እስከ ከፍተኛ ደረጃ ብቁ በሆኑ መምህራን እና ምቹ በሆነ የትምህርት ሰዓት እናስተምራለን።
🌟 የምንሰጣቸው ትምህርቶች 👇
❶ ቃኢደቱ ኑራንያ
❷ አረበኛ ፅሁፍ (ኸጥ)
❸ ቁርዓን ንባብ
❹ ተጅዊድ
❺ አረበኛ መሰረታዊ ንግግር
❻ ሶርፍ
❼ ነህው
❽ በላጋ
❾ መንጢቅ
❿ እንግሊዝኛ
❶❶ የፈረንሳይ ቋንቋ
❶❷ የቱርክ ቋንቋ
📍 ለመመዝገብ ⬇️
@Sobrarabic_bot
✅ ለበለጠ መረጃ ⬇️
@sobrTyake_bot
📱 ቴሌግራም ቻናል ⬇
https://t.me/Sobrarabic
✍ለልባችን ትንሽ ማስታወሻ…
አንዳንድ ቀን በጣም እንጠነክራለን፤
አንዳንድ ቀን ደግሞ እንደክማለን።
ያኔ ግን ራሳችንን አንወቅስ።
የሰው ልብ ሁልጊዜ በአንድ ሁኔታ አይኖርም።
ዛሬ ማድረግ ያልቻልነውን ነገ ለመሞከር እንችላለን።
ዛሬ የወደቅንበትን ነገ ላለመድገም እንችላለን።
ከአላህ ርቀን ብንቆይም ወደ እርሱ የምንመለስበት በር ሁሌም ክፍት ነው።
ስለዚህ ልባችን ቢደክምም ተስፋ አንቁረጥ።
ትንሽ ትንሽ እንመለስ፣
ትንሽ ትንሽ እንሻሻል፣
አላህንም እንደገና እንያዝ።
አላህዬ ያግዘን
Repost from የኒቃብ እና ጅልባብ ባንክ [channel]
የሙሓደራና የኒያ ፕርግራም
~
የፊታችን ማክሰኞ በጅልባብና ኒቃብ ቻናል ላይ በተወዳጅ ኡስታዞችና ወንድሞች ደማቅ ይሙሓደራና የኒያ ፕርግራም ተዘጋጅቶ ይጠብቃችኋል።
በፕሮግራሙ የሚሳተፉ ኡስታዞችና ወንድሞች
❶ ኡስታዝ ሙሐመድ ሰዒድ
❷ ኡስታዝ ተውፊቅ ሙሐመድ
❸ ወንድም አቡ ፋሩቅ ኑረዲን
❹ ወንድም አቡ ሹራ
የፕሮግራሙ መሪ
አቡ ፈውዛን ኸይረዲን
ፕሮግራሙ የሚተላለፍበት ቻናል 👇
https://t.me/NikabJilbab
https://t.me/NikabJilbab
➡️➡️ ሼር አድርጉት
▶️ተጀመረ - 😂😘
አዲስ የኪታብ ደርስ📚ኪታቡ አልቀዋዒዱል ሙስላ 🎙በኡስታዝ አቡ ኢምራን 📔የኪታቡን PDF ለማግኘት https://t.me/sefinetunuh/9009 ደረሱ የሚሰጠዉ 📣በአህሉ-ተውሂድ መስጂድ - - https://t.me/sefinetunuh?livestream=78ecafa74f5f278b8c
Repost from አህሉ-ተውሂድ ኢስላሚክ ሴንተር - ሀርቡ
▶️ተጀመረ - 😂😘
አዲስ የኪታብ ደርስ📚ኪታቡ አልቀዋዒዱል ሙስላ 🎙በኡስታዝ አቡ ኢምራን 📔የኪታቡን PDF ለማግኘት https://t.me/sefinetunuh/9009 ደረሱ የሚሰጠዉ 📣በአህሉ-ተውሂድ መስጂድ - - https://t.me/sefinetunuh?livestream=78ecafa74f5f278b8c
ፈጥኖ ማን ቀድሞ ይመልስ 🚀🚀
ትክክለኛውን መልስ ያገኝ ሰው add የሚለውን በመጫን ስጦታ ያገኛል።
📝 ጥያቄ እውነት ሀሰት በማለት መልሱ ።
ከጀነት በሮች ውስጥ ፆመኞች ብቻ የሚገቡበት ልዩ በር ረያን ይባላል ።
Repost from قناة أبو عمران الخميسي لنشر السنة والتوحيد
💎ምን አይነት ሴት ብያገቡ ይመረጣል?
እንደ ኢስላም ለትዳር ሴት ሲመረጥ ዋናው መስፈርት ዲኗና ባህሪዋ መሆን አለበት።
ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
«تُنْكَحُ الْمَرْأَةُ لِأَرْبَعٍ: لِمَالِهَا، وَلِحَسَبِهَا، وَلِجَمَالِهَا، وَلِدِينِهَا، فَاظْفَرْ بِذَاتِ الدِّينِ تَرِبَتْ يَدَاكَ» “ሴት በንብረቷ፣ በዘርዋ፣ በውበቷ እና በዲኗ ምክንያት ትጋባለች፤ የዲን ባለቤት የሆነችዋን ምረጥ።” — ቡኻሪና ሙስሊምስለዚህ ለትዳር ሴት ስትመርጥ እነዚህን ተመልከት፦ 🔹ዲንና ተቅዋ — አላህን የምትፈራ፣ ሶላትን የምትጠብቅ፣ ከሐራም የምትርቅ። 🔹መልካም ባህሪ — ትሁት፣ ታጋሽ፣ አክባሪ እና በችግር ጊዜ የምትታገስ። 🔹የቤተሰብ አስተዳደር ችሎታ — ትዳርን እንደ ኃላፊነት የምትመለከት። 🔹ከባል ጋር በመልካም መኖር የምትፈልግ፣ ችግርን በውይይት የምትፈታ። 🔹የምትስማማህ — በዲን፣ በእሴቶች፣ በቤተሰብ እቅድና በወደፊት ግቦች ላይ። 🔹ውበትና መሳብ — ይህም እንደ ሚፈቀድ ነገር ይታያል፤ ነገር ግን ከዲንና ከባህሪ በላይ እንዳይሆን። 🔹ቤተሰቧንና አስተዳደጓን መመልከት — ይህ ስለ ባህሪዋ ጥሩ ግንዛቤ ሊሰጥ ይችላል። በተጨማሪም አላህ ﷻ እንዲህ ይላል፦
﴿إِنَّ أَكْرَمَكُمْ عِندَ اللَّهِ أَتْقَاكُمْ﴾ “ከእናንተ አላህ ዘንድ የተከበረው በተቅዋ የበለጠው ነው።” (ሱረቱል ሁጁራት 49፥13)🗣በአጭሩ፦ ቆንጆ መሆኗን ብቻ አትመልከት፤ ሀብታም መሆኗን ብቻም አትመልከት። ዲን፣ ባህሪ፣ የአእምሮ ብስለት እና የትዳር ኃላፊነትን መሸከም ችሎታዋን ቅድሚያ ስጥ። ©https://t.me/Abuimran_alkemisse ©https://t.me/Abuimran_alkemisse
Repost from ABU~MAHI (አቡ_ማሒ)
ልጆቻችን የት ላይ ናቸው?
ዛሬ ባለንበት የቴክኖሎጂ ዘመን፣ የልጆቻችን ዓለም በእጃቸው ባለው ስክሪን መጠን ያህል ጠቦ ወይም ሰፍቶ ይገኛል።
ወላጆች ልጆቻቸው በምቾት ቤት ውስጥ ስለተቀመጡ ብቻ ደህና ቦታ ላይ እንደሆኑ የሚያስቡበት ዘመን አብቅቷል፤ ምክንያቱም በስክሪኑ በኩል ያለው ዓለም ወደ ልጆቻችን አእምሮና ልብ የሚያስገባው ነገር ወላጅ ከሚገምተው በላይ የሰፋ ነው::
ስክሪኑ የሚያስተምረው ትምህርት፡ ልጆቻችን በስልክና በኮምፒውተር የሚያዩት ነገር በቀጥታ የአስተሳሰብ፣ የባህሪና የሥነ-ምግባር መቅረጫቸው እየሆነ ነው።
አልፎ አልፎ የሚታዩት አላስፈላጊና አጥፊ ይዘቶች የልጆችን ንጹህ አእምሮ የሚያበላሹና ከእሴቶቻቸው የሚያወጡ ናቸው።
የወላጅ ተርቢያ ፡ እውነተኛ ተርቢያ ማለት ምግብ፣ አልባሳትና ምቾትን ማቅረብ ብቻ አይደለም። እውነተኛ ተርቢያ ልጆች በሌሉበትና ማንም በማያያቸው ቦታ እንኳን መልካሙን ከክፉው መለየት የሚችሉበትን መንፈሳዊና ስነ-ምግባራዊ ኮምፓስ (መሪ) በልባቸው ውስጥ መትከል ነው።
የዲናዊና የመልካም እሴት አስተዳደግ፡ ልጆችን ገና በለጋ እድሜአቸው ከአላህ መንገድ፣ ከዲናዊ እውቀትና ከታላላቅ ዑለሞች ምክር ጋር ማስተዋወቅ የአእምሮአቸውን ሰላም፣ የስነ-ልቦናቸውን ጥንካሬና የህይወታቸውን ስኬት ያረጋግጣል።
አላስፈላጊ ነገሮችን አይተው አእምሮአቸው ከሚበላሽ፣ መንፈሳዊና አቅጣጫ ጠቋሚ የሆኑ አስተማሪ ነገሮችን እየሰሙ ማደጋቸው ለነገው ማንነታቸው ታላቅ መሰረት ይጥላል::
የዛሬው ጥንቃቄአችንና የምንመግባቸው መንፈሳዊ ምግብ፣ የነገውን ትውልድ ማንነትና የወደፊት አቅጣጫ የሚወስን ትልቅ አደራ ነው።
https://t.me/Abu_Mahi_Ibnu_Idris
https://t.me/Abu_Mahi_Ibnu_IdrisRepost from []سَكِينَةُ الْقُلُوبِ ሰኪነቱል-ቁሉብ[]
ጧት ማለት ፀሐይ መውጣት ብቻ አይደለም…
እንደገና ለመጀመር አላህዬ የሰጠን ሌላ እድል ነው።
ትናንት የተሰበረውን ዛሬ ማስተካከል እንችላለን።
የዘገየውን በዱዓ መጠበቅ እንችላለን።
የደከመውን ልብ በአላህ ቃል ማሳረፍ እንችላለን።
እናም ዛሬ ምንም ቢጠብቀን፣
አንድ ነገር እናስታውስ፦
ያለ አላህ እርዳታ አንድ ቀን እንኳን አንችልም፤
ስለዚህ ቀናችንን በእርሱ ስም እንጀምር።
አላህዬ ይህን ጧት የልባችን ሰላም፣
የዱዓችን መልስ እና
የቀናችን በረከት ያድርገው 🤲
https://t.me/+SpJHRe6JfQQ0NGI0
