ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)
Kanalga Telegram’da o‘tish
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
Ko'proq ko'rsatish4 443
Obunachilar
+824 soatlar
+657 kun
+91030 kun
Postlar arxiv
ሰላም እንዴት ናችሁ የሰባት ለሰባ የትግል ደጋፊዎቻችን እንደምን አላችሁ አገዛዙ አማራ ጠሉ አብይ አህመድ በአዋቀራቸው የሳይበር ባለሙያዎች የፊስቡክ ፒጅ አካውንት ዋርንግ እየሰጡኝ ስለሆነ ከዛሬ ጀምሮ በዚህ በአዲሱ ፒጅ የምታገኙኝ መሆኑን አሳውቃለሁ
አማራ ታዘዘ የአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ አፄ ዘራያዕቆብ አንደኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=122097734487055237&substory_index=1332254055079849&id=61581657125998
+1
ጨ#አጋልጥ‼️
ትናንት መስከረም 23/2018 ዓ/ም መካነሰላም ከተማ ላይ በተደረገ ውጊያ የተገደለው የቦረና ወረዳ ሰላምና ደህንነት ፅህፈት ቤት ኃላፊ ሃምሳ አለቃ ቃሲም ዳኜ!
👉 የአፋህድ ኃይሎች ምንዝሮ ላይ ሹፌሮችን ማገታቸው ታወቀ።
አፋህድ ሰሞኑን ባወጣው መግለጫው ዘራፊዎችን በማጥፋት ለህዝባትን እፎይታን እንሰጣለን በማለት ከዛሬ 24/2018 ዓ.ም ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ ያልዘሩትን እያጨዱ እና በህልም እሩጫቸዉ እሳቤ የትራንስፖርት እገዳ መጣላቸውን በመግለጫቸው አሳዉቀዋል። ነገር ግን ቤታቸውን ሳያጸዱ ውጩን ለማጽዳት እውነተኛ ታጋዮች ሁነው ለመታየት እያደረጉት ያለው መጋጋጥ "በሃምሳ ገዝቶ በሃምሳ መሸጥ" መሆኑን እንመራዋለን የሚሉት መንጋ ሰራዊታቸው ከፈጸመው ነውረኛ ድርጊት ማረጋገጥ ተችሏል።
በጎንደር ዙሪያ ወረዳ ከባህሪ ግንብ እስከ ምንዝሮ ቀበሌ ድረስ 20 በላይ የሚሆኑ የነዳጅ መጫኛ ረጅም ተሽከርካሪ ሹፌሮችን በማገት ወደ አልታወቀ ስፍራ ወስደዋቸዋል።
ተሽከርካሪዎችም በዋናው መንገድ ላይ እንዲቆሙ ተደርገዋል።
ይህ ሌባ ቡድን የጠላትን ተልእኮ ተሸካሚ በመሆን በህዝባችን ላይ አረመኔያዊ ድርጊት እየፈፀመ ለመሆኑ የምንዝሮው የእገታ ድርጊት ዋና ምስክር ነው።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በምስራቅ ደንቢያ ወረዳ በተለያዩ ቀበሌዎች የሚኖሩ አርሶ አደሮችን በማሰር ፣ ጠመንጃቸውን በመንጠቅ ፣ ሃብት ንብረታቸውን በመዝረፍና በመደብደብ ሰሞኑን መባዘናቸውን ማወቅ ችለናል። በርካቶች ንጹሃን አርሶ አደሮችና ወጣቶች እስካሁንም እንደታሰሩ ናቸው።
የታሰሩበት ምክንያትም ልጆቻችሁ የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይልን ወግነው ተዋግተውኛል በሚል የበቀልተኝነት ሰበብ ሲሆን አሁንም አፋህድን መጥተው ከተቀላቀሉ የታሰራችሁት ትፈታላችሁ ፤ የተወሰደባችሁ መሳሪያም ይመለስላችኋል የሚል ምላሽ እንደተሰጣቸዉ ከታጋቹቹ ቤተሰብ መረጃ ማግኘት ተችሏል።
ያላረሱትን መዝራት ያልዘሩትን ማጨድ ያላጨዱትን ማምረት እንደማይቻለዉ ሁሉ ባልተዋጉበት የጦር ሜዳ ድል ባልተሰማሩበት ቀጠና ዉጊያ እና የቀጠናዉ አስተዳዳሪ ሁኖ መገኘት ላም አለኝ በሰማይ ወተቷንም አላይ ይሉት አባባል ነዉ።
ስለዚህ መላዉ የተከበረዉ ህዝባችን ይህ ቡድን ለማገት ለመዝረፍ ያመቸዉ ዘንድ ያወጣዉ ማደናገሪያ መግለጫ እንጅ ታጋዩ ለትግሉ የሚጠቅም ሁኖ አግኝቶት ያወጣዉ መግለጫ እንዳልሆነ ማሳወቅ እንፈልጋለን።
ድላችን በተባበረ ክንዳችን!!
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና
በላይ ዘለቀ ዕዝ
መስከረም 24/2018ዓ/ም
ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን።
ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇 ‼️
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
+2
የአፋብኃ ማዕከላዊ ኮማንድ አባል እና የምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ ከፍተኛ አመራሮች ለአባ ኮስትር የብርጌድ አመራሮች እና አባላት የፖለቲካ ትምህርት ሰጥተዋል።
የአፋብኃ ማዕከላዊ ኮማንድ አባል አርበኛ አስረስ ማረ ዳምጤ፣የምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ አርበኛ ማርሸት ፀሀዩ፣አርበኛ ጥላሁን አበጄ፣የፖለቲካ መኮንኖች፣የክፍለ ጦር እና የብርጌድ አመራሮች በተገኙበት የአባ ኮስትር ብርጌድ አመራር እና አባላት ጥልቅ የሆነ የፓለቲካ ትምህርት ተሰጥቷል።
የፖለቲካ ትምህርቱን የሰጡት ከፍተኛ አመራሮች እንደተናገሩት አባ ኮስትር ብርጌድ በሳል እና አስተዋይ አመራሮች ያሉት በድርጅታችን ካሉ ብርጌዶች ውስጥ የሰለጠነ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ጠንካራ ወታደራዊ ኃይል መገንባቱ ለጠላቶቻችን ስጋት ለድርጅታችን ጥንካሬ መሆኑን በመግለፅ ወታደሩ የሚሰጠውን ወታደራዊ ግዳጅ በመወጣት ትግሉን ከጠላፊዎች በመጠበቅ የትግላችን መርህ በማክበር፣የትግላችን ፍትህ አስከባሪዎች በአጠቃላይ የአማራ ህዝብ የህልውና አደጋ ዘቦችና የሀገሪቷ ቀጣይ ተርካቢ ኃይል መሆናቸውን ገልፀዋል።
በመጨረሻም በጀግና ታጋይ እዚህ የደረሰው ውድ እና ቅዱስ የሆነው ትግል መሪዎችን እና ድርጅታችንን በመጠበቅ የአማራን ህዝብ አደራ እንድትወጡ በማለት የፖለቲካ ትምህርቱ ተጠናቋል።
ፋኖ ይበልጣል ጌቴ ምትኩ
የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 8ኛ በላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ
አዲስ ትውልድ፤አዲስ አስተሳሰብ፤አዲስ ተስፋ!
መስከረም 24/2018 ዓ.ም
#ስለመካነሰላም‼️
እኔ የእስልምናሐይማኖት ተከታይ ፋኖ ነኝ። የብልፅግና ቡድን የመጨረሻ ያለውን ካርድ በመምዘዝ ወሎ ቤተአማራ ላይ የሐይማኖት ግጭት ለመቀስቀስ እየሰራ ነው።
በሐይማኖት ሰበብ አድርጋችሁ የፖለቲካዊ አጀንዳችሁን ለማስፈፀም የምትሯሯጡ ሰዎች አደብ ያዙ።
ሕዝባችን ላይ የሚተኩስ ፋኖ የለም።አይኖርም። የተደቀነብን አደጋ በአማራነታችን ነው። ሕልውናችንን እናስከብራለን። እናሸንፋለን! ድል ለአማራ ሕዝብ! ድል ለፋኖ!
አርበኛ መሐመድ ፈንታው (በአፋብኃ ምኒልክ ዕዝ የልጅ እያሱ ኮር ግዢ ክፍል ኃላፊ)
24/ዐ1/2018 ዓ.ም
+2
አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ ሐዲስ አለማየሁ 7ኛ ክፍለ ጦር አዋበል ወረዳ መብረቁ ብርጌድ ሻለቃ 3 ፣ ሻለቃ 4 እንዲሁም የዲሽቃ ምድብ እና የብርጌዱ መቺ ሀይል አመራሮችን የትግላችንን መነሻና መዳረሻ ካለንበት የትግል ሂደት በመነሳት የፓለቲካ ግንዛቤ እና የመሪነት ስልጠና (ኢንተርፕሪነርሽፕ) በመስጠት የትግል ጉዞአችንን ለማፋጠን እያሰለጠን፣እያደራጀን፣እያታገልን ደከመን ሰለቸን ሳንል ባአንድነት በተባበረ ክንዳችን እራያችንን ከግብ እናደርሳለን።
ህልዉናችን በተባበረ ክንዳች
አዲስ ትዉልድ
አዲስ አስተሳሰብ
አዲስ ተስፋ
መስከረም 24 /01/ 2018 ዓ.ም
የአዋበል ወረዳ መብረቁ ብርጌድ ህዝብግንኙነት ኃላፊ ፋኖ ወነድምነህ ሰውነት።
አስቸኳይ መረጃ‼️
24/01/2018
ከመኮድ ባህር ዳር የተነሳ በ21 መኪና fsr iszuu በዲሽቃና በዙ 23 ታጅበው ወደ ጎንደር አቅጣጫ ወጠዋል አስቸኳይ ነው share ይፈልጋል አዛምቱ ለወገን ይድረስ
ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን።
ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
~ ከአፋር ብሔራዊ አንድነት አብዮታዊ ግንባር ለፋኖ ኃይሎች የተሰጠ የአጋርነት መግለጫ!
የተከበራችሁ መላው የአፋር ህዝብና የኢትዮጵያ ብሄረሰቦች በሙሉ እንደምታወቀው የአፋር "ኡጉጉሞ" ነፃነት ግንባር፣ የአፋር ህዝብ ክብርና ጥቅም እንዲሁም ልዑላዊነትና ድህንነት ከየትኛውም የውስጥና የውጭ ጠላት እንዲጠበቅና እንዲከበር ለበርካታ አመታት በደምና በአጥንት ብዙ መስዋዕትነት እየከፈለ የመጣ ግንባር መሆኑ ይታወቃል።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህም ወደመደበኛ የትጥቅ ትግል በመሸጋገር ላይ እንዳለን ይታወቃል።
የአሁኑን ትግላችን ከዚህ ቀደሙ የተለየ ያደረገው፦
አንደኛ፡- የብልፅግና ቡድን የአፋር ህዝብ ልዑላዊ ግዛት ለሌላ አሳልፎ ሊሰጥ በመሆኑ፤
ሁለተኛ፦ ቀይ ባህርን የኢትዮጵያ አካል እናደርጋለን በማለት የብልጽግና አገዛዝ የሚቀሰቅሰው ጦርነት፣ በይበልጥ አፋርና አፋርን ለማጋደል የተጠነሰሰው ሴራ በመሆኑ፤
ሦስተኛ፡- ክልሉን በለውጥ ስም ስልጣን የተቆጣጠረውና ለ7 አመታት እየመራ የሚገኘው የብልፅግና ቡድን በማናለበኝነት የህዝብ ሀብት መበዝበዝና ጎሳን ከጎሳ በማጋጨት ወንጀል እየፈፀመ የሚገኝ በመሆኑ፤
አራተኛ፡- በአፋር መሬት ላይ ለአብይ አህመድና የአገዛዙ ፍላጎት ማስፈፀሚያ እየሰለጠኑ ያሉ የታጠቁ ኃይሎች አፋርን የደም መሬት ሊያደርጉት እየሰሩ በመሆኑ፤
በእነዚህና ሌሎች የትግል መነሻ ምክንያቶች የአፋር ህዝብ ያልተገባ የመስዋዕትነት እንዲከፍሉ ለማድረግ እየተሰራ በመሆኑ የአሁኑን የትጥቅ ትግላችን የተለየ ያደርገዋል።
በአሁኑ ሰዓት በምናደርገው የተደራጀ ትግል የአብይ አህመድ ወኪል፣ አድርጎ ያስቀመጠውን የአወል አርባን አገዛዝ ከውጭም፣ ከውስጥም ሁነን እያፈረስነው እንገኛለን።
በዚህም አመርቂ ውጤቶችን አግኝተንበታል። በዚህም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ይህ አገዛዝ ያንገሸገሻቸው የአወል አርባን ወታደራዊ አመራሮችና ሲቭል አመራሮች እየተቀበልን እንገኛለን።
ከዚህ በፊት በመግለጫችን እንዳስታወቅነው፣ በሶማሌ ክልል እጅ አዙር መሪነትና በጂቡቲ ስፖንሰርነት፣ የተባበሩት የሶማሌ አሸባሪዎች የአፋር ህዝብ ላይ በኢሳ ሽፋን ያወጁት ወረራ ለ7 አመታት በንጹሃን ላይ ጥቃት ሲሰነዝሩ ቆይተዋል።
ከወትሮ በተለዬ የአፋር ህዝብ በገዛ ቤቱ እያሸበሩና እየገደሉ ቢሆንም የአፋር ህዝብ በብርቱ ክንድና በሙሉ ልብ እየመከታቸው ከራሱ አልፎ ኢትዮጲያን ከዚያድ ባሬ ህልምና ቅዠት እየታደጉ አብዛኛው አሸባሪዎችን ወደ መሬት እቀበሩ የተቀሩት ደሞ በመመከት ወደ መጡበት ሀገር እንዲመለሱ ማድረግ ላይ ነው።
ሕዝባችን በራሱ ትግል ክልሉን ከወራሪው ነፃ ያደረገ ቢሆንም በሚያሳዝን መልኩ ይሄንን የተባበሩት ሶማሌ ተስፋፊያን የከፈቱብን ግልፅ ወረራ የፌድራል መንግስት ወራራውን ከማስቆምና ከመከላከል በተቃራኒ የአብይ ቡድን በጂቡቲ ያለውን የሥልጣን ጥቅምና ቀጠናዊ የቡድን ፍላጎት በማስቀደም በአፋር ህዝብ ላይ የሚፈፀም የተባበሩት ሶማሌ ወረራ በግልፅ እየደገፍ ይገኛል።
አፋርን በቴክኒካል ሴራና የእጅ አዙር ተፅዕኖ በማዳከም አሸባሪዎቹን ወደ አፋር ልዑላዊ ግዛት እምብርት ላይ እንዲመለስ ግፊት በማድረግ ላይ ነው። ይህ እንደ ሀገር ክህደት የሚቆጠር ወንጀል ነው።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ ወንድም የሆነውን የኤርትራ ህዝብን ለመውጋትና የሚሰለጥኑ ኃይሎች ለአፋር ሕዝብ ብቻ ሳይሆን ለኢትዮጵያና ለአካባቢው የከፋ አደጋ እንደሚያመጣ ህዝባችን ያምናል።
በትላንትናው ዕለትም የአፋር ሕዝብ ይሄ ነገር መቆም እንዳለበት ተቃውሟውን በተለያዩ መንገድ ገልጿል፣ ይሄ ጉዳይም እስከ ነጻነት ድረስ የሚቀጥል መሆኑን የአፋር ብሔራዊ አንድነት አብዮታዊ ግንባር ያስታውቃል።
የአፋር ብሔራዊ አንድነት አብዮታዊ ግንባር ከሰሞኑ በአማራ ክልል ወሎ ግንባር በአገዛዙና በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ በኩል እየተደረጉ ያሉ ውጊያዎችን በትኩረት እየተከታተለ ይገኛል።
የፋኖ ኃይሎች ከባዶ እጅ በመነሳት ዛሬ ላይ በመካናይዝድ የታገዘ መደበኛ ውጊያ እያደረጉ መሆኑን ተገንዝበናል። የተሰየመው ዘመቻም ዘመቻ አደም አሊ የሚል መሆኑን፣ ዘመቻው የተሰየመለት ፋኖ፣ በትግል ላይ የተሰዋ ሙስሊም ፋኖ መሆኑንም አረጋግጠናል።
ይህ የፋኖ ኃይሎችን የአንድ ኃይማኖት ሰዎች ናቸው፣ የቀድሞውን ሥርዓት ለመመለስ ነው የሚታገሉ የሚለውን የብልጽግና አገዛዝ የሐሰት ፍረጃ፣ እንዲሁም በፍረጃው ለተሳሳቱ ሁሉ ምላሽ የሚሰጥ ሁኖ አግንተነዋል።
የፋኖ ኃይሎች እያደረጉ ላለው ከባድ ትግል እውቅና የምንሰጥ መሆኑን እንገልጻለን።
የአማራ ሕዝብና የአፋር ሕዝብ ከትናንት እስከዛሬ በመከራም፣ በደስታም የጋራ እጣ ፈንታ ያላቸው መሆኑ ይታወቃል። አሁን ላይ በአብይ አህመድ የሚመራው የብልጽግና አገዛዝ በአማራ ሕዝብ ላይ የከፈተው ጦርነት ተቀባይነት የሌለውና ለሀገር ወዳዱ የአማራ ሕዝብም ይሄ የማይገባው መሆኑን መግለጽ እንፈልጋለን።
በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሱ የፋኖ ኃይሎች እያደረጉት ያለው ተጋድሎ ከነሱም መግለጫዎች በተደጋጋሚ እንደተረዳነው የመላው ኢትዮጵያ ብሄረሰቦች ነጻነት እንደሆነ ድርጅታችን ያምናል።
እኛም የአፋር ብሔራዊ አንድነት አብዮታዊ ግንባር በቀጣይ ከፋኖ ኃይሎች ጋር በጋራ በመታገል የአብይ አህመዱን የብልጽግና አገዛዝ ለአንዴና ከመጨረሻ ጊዜ በመጣል በእኩልነት የጋራ አገር ለመገንባት በትብብር እንደምንሰራ ስንገልጽ በደስታ ነው።
በመጨረሻም አፋርን እንደመሸጋገሪያ በማድረግ የአማራ ሕዝብን ለማውድም የሚያደርገውን እንቅስቃሴ መላው የአፋር ሕዝብ እንዲቃወምና እንዲያስቆም የአፋር ብሔራዊ አንድነት አብዮታዊ ግንባር ይጠይቃል፣ እንዲቆም እንደምንሰራ መግለጽ እንፈልጋለን።
መላው የኢትዮጵያ ብሄረሰቦች የትግል መነሻዎቻችን ተረድቶ በሀገራችን ላይ የተደቀነው ብሄራዊ አደጋ በጋራ ትግል እንዲቀለብስ ጥሪ እናቀርባለን።
ግመሎቻችን ጭምር የሚያውቋት የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ እንዳትወድቅ፣ ነፃ ሀገር እንድትኖረን ለትግላችን አስፈላጊውች ትብብር እንዲያደርጉ እንጠይቃለን !
ድልና ድምቀት ለአፋር ኡጉጉሞ!
ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን።
ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
አፋብኃ |ቴዎድሮስ ዕዝ በሁለት ግንባሮች ውጊያ አደረገ።
የበረኸኛው ጅበላ ሙተራ ብርጌድ በ 3 አቅጣጫ በመግባት የደብረ ማርቆስ ከተማ በመግባት ጠላትን ደመሰሰ።
ኦፐሬሽኑ በአራት አውደ ግምባሮች ማለትም በሞሰቢት ፣ ኮሌጅ ሲቪል ሰርቪስ ፣ ወንቃና በየቦ መኃል አደባባይ አካባቢ የተደረገ ሲሆን ከሌሊቱ ጀምሮ እስከ ንጋት በተደረገው ውጊያ በርካታ ቁጥር ያለው የጠላት ኃይል እርምጃ ተወስዶበታል።
ውጊያ በተደረገባቸው ሁሉም ቦታዎች ላይ የእጅ በእጅና የቦንብ ጥቃች የተፈጸሙ ሲሆን ዋርድዮችን ጨምሮ በርካታ የጠላት ኃይል ሙትና ቁስለኛ ሆኗል።
አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ ፣አዲስ ተስፋ!
አፋብኃ| ቴዎድሮስ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መስከረም 24/2018 ዓ.ም
ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን።
ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
ዘመቻ አርበኛ አደም አሊ (አባ ናደው)
የትግላችን አንዱ መርህ "ወደ ህዝብ የሚተኩስ ሠራዊት አያሸንፍም" ነው።
ስለሆነም እያሸነፍን ያለነው ወደ ህዝብ ፍቅር እንጂ አፈሙዝ ስላላዞርን ነው፡፡
የአብይ መንግሥት እና የጁላ ሠራዊት ወሎ ላይ እየደረሰበት ያለውን ከባድ ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ ዱላ እና ቅጥቀጣ መቋቋም ሲሳነው አንዴ ህውሓት አንዴ ሻዕቢያ እያለ ቢቀባጥርም አመኔታ ማግኘት ስላልቻለ የመጨረሻ የሚመስለውን የእምነት ጦርነት ለመቀስቀስ የቀረችውን አንድ ካርድ በመካነሰላም ከተማ መዟታል፡፡ ወሎ ላይ ይህ መቼም አይሳካም፡፡
ምክኒያቱም የዘመቻው ስያሜ "የአርበኛ አደም አሊ" መሆኑን ልብ እንበል፡፡ ሳጅን አደም አሊ ለአማራ ህዝብ ክብር ራሱን አሳልፎ የሰጠ የምንግዜም ጀግና ሙስሊም ጓድ ነበረ፡፡
ሌሎችም እልፎች አሉ፡፡ አደም በስሙ የተሰየመን ዘመቻ የሚያረክስ ጅል ሠራዊትም ተቋምም አልገነባንም፡፡
ሌላው ወሎ ላይ ክርስቲያን ሙስሊሙን ይጠላል ብሎ ማሰብ ራሱ ወንድም እና እህት እናት እና ልጅ ባል እና ሚስት አጎትና አክስት ሰልፍ ለይተው ይጠላላሉ ብሎ ማሰብ ነው።
ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል? አባት እንዴት ልጁን ሊጠላ ይችላል? እናትስ ብትሆን? ወንድም ወንድሙን በምን ሂሳብ? በፍፁም አይሆንም፡፡
አለም ሲሰለጥን ወሎዬን ይመስላል የሚባለው ሁሉም እምነቶች እና ባህሎች ፍፁም ተዋደው ተጋምደው እና ተከባብረው በጋራ በሰላም የሚኖሩበት ድንቅ የአለም ምድር በመሆኑ ነው።
ነገም ይቀጥላል ሼሁም አበጋሩም ቄሱም ደረሳውም ዲያቆኑም ኡስታዙም አዛኑም ቅዳሴውም ፀሎቱም ዱአውም በአንድ ቅጥር ግቢ ውስጥ ባይደረግም በአንድ አካባቢ ተከባብረው ለዘመናት ኖረዋል አሁንም እየኖሩ ነው ወደ ፊትም ይኖራሉ፡፡
በመካነ ሰላም አገዛዙ የመዘዘውን ካርድ ሰርጎ ገቦችን በመጠቀም በተለያየ ቦታ ሊያሳይ ስለሚችል ሙስሊም ክርስቲያኑ እርስበራሳችን እንድንጠባበቅ እና የአጥፊዎችን ሴራ እንድናከሽፍ ሲል ኮሩ ጥሪውን ያቀርባል።
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ልጅ እያሱ ኮር!
መስከረም 24 ቀን 2018 ዓ.ም
ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን።
ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
AMHARA DAILY(AD)🟩🟨🟥🐅:
አንዱ የአሕመድን ጀበል "ኢማም" የቦረና ወረዳ ሰላምና ደህንነት ጽ/ቤት ኃላፊው አቶ ቃሲም ዳኜ መሆኑ ተረጋግጧል።
ሰበር አዲስ ቅዳም‼️
የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ ጎጃም አገዉ ምድር ክ/ጦር የአስር ዓለቃ ኤፍሬም አጥናፉ ብርጌድ አናብስቶች አዲስ ቅዳም ከተማ ላይ የሰላም አስከባሪ ሃላፊዉን ጨምሮ በርካታ አጥቦ አይለብሴ ሚሊሻና አድማ ብተና አባለትን ሙት እና ቁስለኛ አድርገዉታል።
ዘመቻ ሃምሳ ዓለቃ አይሸሽም ተክሌ ብለዉ አዉጀዉ አዲስ ቅዳም ከተማ በመግባት ከንጋቱ 12:00 ስዓት _4:40 ድረስ በፈጀዉ የከተማ ዉጊያ በርካታ አጥቦ አይለብሴ ሚሊሻና አድማ ብተና ወደ ላይኛዉ ሲላክ
_21 አጥቦ አይለብሴ ሚሊሻና አድማ ብተና ወደ ላይኛዉ ሲላክ
_ከ32 በላይ ቁስለኛ በመሆን እንጅባራ ሆስፒታል የገባ
_5 ክላሽ የተማረከ
_1 የቃታ መሳሪያ የተማረከ
_523 ፍሬ የክላሽ ተተኳሽ የተማረከ
_52.000 ብር ከጠላት የተማረከ
ፋኖነት አሸናፊነት
የቴዎድሮስ ዕዝ ጎጃም አገዉ ምድር ክ/ጦር የህ/ግንኙነት ሃላፊ
ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን።
ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
መርጠን የምንተወዉም ሆነ መርጠን እርምጃ የምንወስድበት ጠላት የለም!
በዘመቻ 'አደም አሊ' ታይቶ የማይታወቅ ኪሳራ የደረሰበት የኦህዴድ ብልፅግና 'አሽከርና ሎሌ' የሆነዉ ብአዴን ብልፅግና የሚይዘው የሚጨብጠው በማጣቱ የአማራ ህዝብን ለማፋጀት በማለም ሀይማኖታዊ አጀንዳ ፈብርኳል።
ለፀረ-አማራዉ አገዛዝ አስፈፃሚ የሆነ ሁሉ የትኛውንም ሀይማኖት ይከተል በፋኖ ይጠርጋል።
ትግላችን የአማራ ህዝብ ህልዉና ጉዳይ ነዉ። ከማሳያዎቹ መካከል ደግሞ 'ወላሂ ሁለተኛ አማራ አልሆንም፣ አትግደሉኝ' እያለች እየተማፀነች በአማራነቷ ምክንያት በግፍ የተገደለችውን 'ህፃን አንሻ'ን እናስታዉሳችሁ።
ይህ ዘመቻም የእስልምና ኃይማኖት ተከታይ የሆነው እንቁ የአማራ ሰማዕት አርበኛ 'አደም አሊ' የተሰየመ መሆኑን አትዘንጉ።
አገዛዙም/የኦህዴድ ሰራዊት አጋጣሚውን በመጠቀም በዚህ ወቅት 'ለኤሬቻ መባዕ' ይሆነው ዘንድ አማራን እርስበርስ ለማጫረስ በማሴር መካነሰላም ላይ በተሰራ ኦፕሬሽን በአገዛዙ የፀጥታ ዘርፍ፣ የሚሊሻ፣ የፖሊስ አመራር የነበሩ ሙስሊም ባንዳዎች የተወሰደውን እርምጃ ሀይማኖታዊ አጀንዳ አድርጎታል።
የአጀንዳው ዋና ዓላማ ፋኖ ሙስሊም ጠል እንደሆነ ለማስመሰል እና ነባር እስልምና ኃይማኖት ተከታዮችን እና የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ክርስትና አማኞችን እርስበርስ ለማጋጨት ታስቦ ነው። ነገር ግን ጠቢቡ የአማራ ህዝብ ከምንጊዜውም በላይ ስለነቃ እንደወትሮው ሁሉ ይህንም ያከሽፈዋል።
ያም ሆነ ይህ የፋኖ ትግል ክርስትናም ይሁን እስልምና ኃይማኖት የሚከተሉ የአገዛዙ አስፈፃሚዎችን በሚገባቸው ልክ እየቀጣ መጥቷል። ነገም ይቀጥላል።
ሲኖር የአገዛዙ አመራር፣ ሲሞት ሙስሊም የሚሆን ጠላት ገና ይጠርጋል። ለክርስትና ኃይማኖት ተከታይ አመራሮችም እንደዛው።
በተያያዘ የአማራ ህልውና ታጋይ ሙስሊም አማራ ፋኖዎች በወንድማቸው 'አርበኛ አደም አሊ' ስም በተሰየመው 'ዘመቻ አባ ናደዉ' አማራ በመሆኗ ብቻ በግፍ የተገደለችውን የእህታቸውን የሰባት አመት ህፃን 'አንሻ ሙሃመድ'ን እና ሌሎች በአማራዊ ማንነታቸዉ ምክንያት የተጠቁ ሙስሊም አማሮችን ደም እየመለሱ ይገኛል።
ሁለንታዊ አደጋ የተጋረጠበት የአማራ ህዝብ ኃይማኖት፣ እድሜ፣ ፆታ ወዘተ ወዘተ... ልዩነት ሳይገድበዉ በፋኖ ትግል ተፈጥሮአዊ ራስን የመከላከል መብት ተጠቅሞ ራሱን እየተከላከለና 'አማራዊ ማንነቱ' እንዳይጠፋ እየመከተ ቀጥሏል።
አማራነት ይለምልም!
አርበኛ ሞገስ አባራው
የአፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ም/የፖለቲካ መምሪያ ኃላፊ
ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን።
ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
#MB_ለበዛባችሁ‼️ ከትግል ሚዳ መልክት ይድርሳችሁ ዘንድ ሸር አድርጉል!!
#ብልፅግና_ሊመዝ_የሞከረው_የኃይማኖት_ግጭት‼️
በዘመቻ አርበኛ አደም አሊ (አባ ናደው) ሙሉ ቤተ-አማራ ላይ ከባድ ሽንፈት የገጠመው ፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና መካነሰላም ላይ የሃይማኖት ግጭት ለመፍጠር የመዘዘውን ካርድ አስመልክቶ የንጉስ ሚካኤል አሊ ኮር ህዝብ ግንኙነት አርበኛ አምሳ አለቃ ሁሴን ኡመር ዛሬ መስከረም 24/2018 ዓ.ም ከቦታው መልዕክት አስተላልፏል።
የአርበኛው መልዕክት ሼርርርርር ይደረግ!!!
24/ዐ1/2018 ዓ.ም
በላይ ዕዝ 5ኛ ኮር
ወንድማማቾች ብርጌድ ክልል እየሱስ የአድማ ብተና ካምኘ ላይ ጥቃት በመሰንዘር የጠላትን ኃይል ሙትና ቁስለኛ እንዲሁም እንዲበተን ማድረጋቸው ታወቀ።
ትላንት መስከረም 23 ቀን /2018 ዓ.ም አመሻሽ ላይ የአፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ እዝ ዳግማዊ ቴዎድሮስ 5ኛ ኮር ታድሎ ብርሃን ክ/ጦር ወንድማማቾች ብርጌድ አዘዞ ክልል እየሱስ ልዩ ስሙ ጉምብሪት በተባለው የአድማ ብተና ካምኘን ሰብሮ በመግባት በብልጽግና ተላላኪ የአድማ ብተና አባላት ላይ የማያዳግም እርምጃ ተወስዶባቸዋል።
በእርምጃው የጠላት ኃይል 12 ሙት ፣ 20 ቁስለኛ ሲሆኑ በጥቃቱ በርካቶች ተበትነው እግራቸው ወዳመራቸው አቅጣጫ ተበትነዋል።
ጉምብሪት የአድማ ብተና ካምኘ ላይ ጥቃት መድረሱን ያረጋገጠው ጠላት በቅርብ ርቀት ላይ ከሚገኘው አዘዞ የጦር ካምኘ ተጨማሪ አጋዥ ሰራዊት ይዞ የደረሰ ቢሆንም ሰራዊቱን ከሞትና ከመበታተን ሊታደገው ግን አልቻለም።
ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ እዝ
መስከረም 24/ 2018 ዓ.ም
ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን።
ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
ትዉልዱ ለነፃነቱ ሲል ልዩነቱን እየተወ አንድነቱን እያጠናከረ ድርጂታችንን እየተቀላቀለ ይገኛል።
አፋብኃ 9ኛ ክ/ጦር አረንዛዉ ጎንቻ ብርጌድ ከዚህ ቀደም በተለያዩ ምክንያቶች ከትግሉ እራሳቸዉን አግለዉ የነበሩ አባላትን ሰብስቦ አወያይቷል።
ብርጌዱ ከዚህ ቀደም ባጋጠመዉ ውስጥ ችግር ምክንያት እና በተለያዩ ጉዳዮች እራሳቸዉን አግለዉ የቆዩት የፋኖ አባላት ከአመራሮች ጋር ዉይይት አድርገዋል።
ብርጌዱ በዉስጡ ያጋጠሙትን ችግሮች በዘላቂነት በመፍታቱ እና በተሻለ ቁመና ላይ እንደሚገኝ እና በርካታ ጀብዶችን እየፈፀመ የተሻለ ቁመና ላይ መሆኑን የተረዱት የቀድሞ የፋኖ አባላት በቆይታቸዉ ባሉበት ቦታ በግዳጂ ሰዓት ከፋኖ ጎን ሆነዉ ጠላትን ሲፋለሙ የቆዩ ሲሆን በተናጠል የሚመጣ ለዉጥ ስለሌለ ሙሉ ትጥቃቸዉን ይዘዉ ከ50 በላይ አባላት አረንዛዉ ጎንቻ ብርጌድን ተቀላቅለዋል።
የክ/ጦሩ እና የብርጌዱ አመራር በጋራ በመሆን ትግሉን ለተቀላቀሉ አባላት የፓለቲካ እና የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጥተዋል ብርጌዱን የተቀላቀሉ አባላትም በሻለቃ መዋቀሮች ተካተዉ ለግዳጂ ዝግጁ ሆነዋል።
በሌላ ዜና
አባይ ሸለቆ ብርጌድ በሚያስተዳድራቸው የተለያዩ ቀበሌዎች ህዝባዊ ውይይቶች ተጠናክረው ቀጥለዋል ከእነብሴ ሳርምድር ወረዳ ምጥና ይማች ቀበሌ ማህበረሰብ ጋር ፍሬያማ ውይይት በማድረግ የተጓደሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመፍታት የጊዜያዊ አስተዳደር የነበሩ ችግሮችን በመፍታት ያልተሟሉ አመራሮችን በማሟላት ፤ ስኬታማ ዉይይቶች አድርገዋል።
ነፍተኛ የሆነዉ ህዝባችን ነፍጡን ወልዉሎ በየቀበሌዎች ለማይቀረዉ የነፃነት ትግል እራሱን ለግዳጂ ዝግጁ አድርጎ እየጠበቀ ይገኛል።
መስከረም 24/2018 ዓ.ም
9ኛ ሳሙኤል አወቀ ክ/ጦር
ህ/ግንኙነት
ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን።
ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
ጀግኖቹ የበረኸኞቹ ጅበላ ሙተራ ብርጌድ ፋኖዎች በደብረ ማርቆስ ከተማ አስደናቂ ኦፐሬሽን ሰርተዋል።
መስከረም 24/2018 ዓ.ም
ጀግናው የበረኸኛው ጅበላ ሙተራ ብርጌድ በ 3 አቅጣጫ በመግባት የደብረ ማርቆስን ከተማ ሲያደባየው አድሯል!
ኦፐሬሽኑ በአራት አውደ ግምባሮች ማለትም በሞሰቢት ፣ ኮሌጅ ሲቪል ሰርቪስ ፣ ወንቃና በየቦ መኃል አደባባይ አካባቢ የተደረገ ሲሆን ከሌሊቱ 7:00 ገደማ እስከ ንጋት በተደረገው ውጊያ በርካታ ቁጥር ያለው የጠላት ኃይል እርምጃ ተወስዶበታል።
ውጊያ በተደረገባቸው ሁሉም ቦታዎች ላይ የእጅ በእጅና የቦንብ ጥቃች የተፈጸሙ ሲሆን ዋርድዮችን ጨምሮ በርካታ የጠላት ኃይል ሙትና ቁስለኛ ሆኗል።
ድል ለአማራ ፋኖ!
አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ!
ፋኖ ዘመን ባሳዝነው
ሰበር ዜና!
የጎንደሬ በጋሻው ክ/ጦር አመራሮችን ለማፈን ከማክሰኝትና ከደጎማ የመጣው ኃይል ክፋኛ መመታቱ ታወቀ።
መስከረም 23 ለ24 /2018 ዓ.ም ከሌሊቱ 7:00 ላይ ጨረቃዋን በመጠቀም ከማክሰኝትና ከደጎማ ሃይሉን በማውጣጣት ድንዛዝ ከተባለው ቀበሌ ላይ ደፈጣ በመድፈጥ አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ እዝ ዳግማዊ ቴዎድሮስ 5ኛ ኮር የጎንደሬ በጋሻው ክ/ጦር አመራሮችንና የጥቁር አንበሳ ክ/ጦር አባላትን ለማፈን ከበባ ፈጽሞ አድሯል።
ጠላት በሌሊቱ ተጉዞ መድፈጡን መረጃ የደረሳቸው የክ/ጦሩ አመራሮች በቆራጥነት የሚመሩትን ጦር ከፊት ሆኖ በመምራትና በማዋጋት የብልጽግናን ወንበር አስጠባቂ ኃይል
13 ያህሉን በመግደልና
9ኙን ክፋኛ በማቁሰል ከበባውን ሰብረው መውጣት ችለዋል። እስካሁንም ድረስ የጠላት ኃይል ከደጎላ እስከ ፋና ጊዮርጊስ ከፍተኛ ቦታዎች ሰፍሮ እንደሚገኝም ለማወቅ ተችሏል።
ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!! @አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ እዝ ዳግ/ቴዎ/5ኛ ኮር ህ/ግን/ኃላፊ አርበኛ አብነት ሞላ
ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን።
ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
