ru
Feedback

Не попадитесь на канал ботавода! Telemetrio находит и помечает такие каналы 👉 Хотите видеть метку — оформите подписку

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

Открыть в Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

Больше
4 444
Подписчики
+1624 часа
+487 дней
+1 15030 дней
Архив постов
አፋብኃ |ቴዎድሮስ ዕዝ በሁለት ግንባሮች ውጊያ አደረገ። የበረኸኛው ጅበላ ሙተራ ብርጌድ  በ 3 አቅጣጫ በመግባት የደብረ ማርቆስ ከተማ በመግባት  ጠላትን ደመሰሰ። ኦፐሬሽኑ በአራት አውደ ግምባሮች ማለትም በሞሰቢት ፣ ኮሌጅ ሲቪል ሰርቪስ ፣ ወንቃና በየቦ መኃል አደባባይ አካባቢ የተደረገ ሲሆን ከሌሊቱ  ጀምሮ እስከ ንጋት በተደረገው ውጊያ በርካታ ቁጥር ያለው የጠላት ኃይል እርምጃ ተወስዶበታል። ውጊያ በተደረገባቸው ሁሉም ቦታዎች ላይ የእጅ በእጅና የቦንብ ጥቃች የተፈጸሙ ሲሆን ዋርድዮችን ጨምሮ በርካታ የጠላት ኃይል ሙትና ቁስለኛ ሆኗል።   አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ ፣አዲስ ተስፋ! አፋብኃ| ቴዎድሮስ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መስከረም 24/2018 ዓ.ም ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን። ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️ https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk ‎

ዘመቻ አርበኛ አደም አሊ (አባ ናደው) የትግላችን አንዱ መርህ "ወደ ህዝብ የሚተኩስ ሠራዊት አያሸንፍም" ነው። ስለሆነም እያሸነፍን ያለነው ወደ ህዝብ ፍቅር እንጂ አፈሙዝ ስላላዞርን ነው፡፡ የአብይ መንግሥት እና የጁላ ሠራዊት ወሎ ላይ እየደረሰበት ያለውን ከባድ ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ ዱላ እና ቅጥቀጣ መቋቋም ሲሳነው አንዴ ህውሓት አንዴ ሻዕቢያ እያለ ቢቀባጥርም አመኔታ ማግኘት ስላልቻለ የመጨረሻ የሚመስለውን የእምነት ጦርነት ለመቀስቀስ የቀረችውን አንድ ካርድ በመካነሰላም ከተማ መዟታል፡፡ ወሎ ላይ ይህ መቼም አይሳካም፡፡ ምክኒያቱም የዘመቻው ስያሜ "የአርበኛ አደም አሊ" መሆኑን ልብ እንበል፡፡ ሳጅን አደም አሊ ለአማራ ህዝብ ክብር ራሱን አሳልፎ የሰጠ የምንግዜም ጀግና ሙስሊም ጓድ ነበረ፡፡ ሌሎችም እልፎች አሉ፡፡ አደም በስሙ የተሰየመን ዘመቻ የሚያረክስ ጅል ሠራዊትም ተቋምም አልገነባንም፡፡ ሌላው ወሎ ላይ ክርስቲያን ሙስሊሙን ይጠላል ብሎ ማሰብ ራሱ ወንድም እና እህት እናት እና ልጅ ባል እና ሚስት አጎትና አክስት ሰልፍ ለይተው ይጠላላሉ ብሎ ማሰብ ነው። ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል? አባት እንዴት ልጁን ሊጠላ ይችላል? እናትስ ብትሆን? ወንድም ወንድሙን በምን ሂሳብ? በፍፁም አይሆንም፡፡ አለም ሲሰለጥን ወሎዬን ይመስላል የሚባለው ሁሉም እምነቶች እና ባህሎች ፍፁም ተዋደው ተጋምደው እና ተከባብረው በጋራ በሰላም የሚኖሩበት ድንቅ የአለም ምድር በመሆኑ ነው። ነገም ይቀጥላል ሼሁም አበጋሩም ቄሱም ደረሳውም  ዲያቆኑም ኡስታዙም  አዛኑም ቅዳሴውም ፀሎቱም ዱአውም በአንድ ቅጥር ግቢ ውስጥ ባይደረግም በአንድ አካባቢ ተከባብረው ለዘመናት ኖረዋል አሁንም እየኖሩ ነው ወደ ፊትም ይኖራሉ፡፡ በመካነ ሰላም አገዛዙ የመዘዘውን ካርድ ሰርጎ ገቦችን በመጠቀም በተለያየ ቦታ ሊያሳይ ስለሚችል ሙስሊም ክርስቲያኑ እርስበራሳችን እንድንጠባበቅ እና የአጥፊዎችን ሴራ እንድናከሽፍ ሲል ኮሩ ጥሪውን ያቀርባል። ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! የአፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ልጅ እያሱ ኮር! መስከረም 24 ቀን 2018 ዓ.ም ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን። ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️ https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk ‎

AMHARA DAILY(AD)🟩🟨🟥🐅: አንዱ የአሕመድን ጀበል  "ኢማም" የቦረና ወረዳ ሰላምና ደህንነት ጽ/ቤት ኃላፊው አቶ ቃሲም ዳኜ መሆኑ ተረጋግጧል። ሰበር አዲስ ቅዳም‼️ የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ ጎጃም አገዉ ምድር ክ/ጦር የአስር ዓለቃ ኤፍሬም አጥናፉ ብርጌድ አናብስቶች አዲስ ቅዳም ከተማ ላይ የሰላም አስከባሪ ሃላፊዉን ጨምሮ በርካታ አጥቦ አይለብሴ ሚሊሻና አድማ ብተና አባለትን ሙት እና ቁስለኛ አድርገዉታል። ዘመቻ ሃምሳ  ዓለቃ አይሸሽም ተክሌ ብለዉ አዉጀዉ አዲስ ቅዳም ከተማ በመግባት  ከንጋቱ 12:00 ስዓት _4:40 ድረስ  በፈጀዉ የከተማ ዉጊያ በርካታ አጥቦ አይለብሴ ሚሊሻና አድማ ብተና ወደ ላይኛዉ ሲላክ _21 አጥቦ አይለብሴ ሚሊሻና አድማ ብተና ወደ ላይኛዉ ሲላክ _ከ32 በላይ ቁስለኛ በመሆን እንጅባራ ሆስፒታል የገባ _5 ክላሽ የተማረከ _1 የቃታ መሳሪያ የተማረከ _523 ፍሬ የክላሽ ተተኳሽ የተማረከ _52.000 ብር ከጠላት የተማረከ ፋኖነት አሸናፊነት የቴዎድሮስ ዕዝ ጎጃም አገዉ ምድር ክ/ጦር የህ/ግንኙነት ሃላፊ ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን። ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️ https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk ‎

መርጠን የምንተወዉም ሆነ መርጠን እርምጃ የምንወስድበት ጠላት የለም! በዘመቻ 'አደም አሊ' ታይቶ የማይታወቅ ኪሳራ የደረሰበት የኦህዴድ ብልፅግና 'አሽከርና ሎሌ' የሆነዉ ብአዴን ብልፅግና የሚይዘው የሚጨብጠው በማጣቱ የአማራ ህዝብን ለማፋጀት በማለም ሀይማኖታዊ አጀንዳ ፈብርኳል። ለፀረ-አማራዉ አገዛዝ አስፈፃሚ የሆነ ሁሉ የትኛውንም ሀይማኖት ይከተል በፋኖ ይጠርጋል። ትግላችን የአማራ ህዝብ ህልዉና ጉዳይ ነዉ። ከማሳያዎቹ መካከል ደግሞ 'ወላሂ ሁለተኛ አማራ አልሆንም፣ አትግደሉኝ' እያለች እየተማፀነች በአማራነቷ ምክንያት በግፍ የተገደለችውን 'ህፃን አንሻ'ን እናስታዉሳችሁ። ይህ ዘመቻም የእስልምና ኃይማኖት ተከታይ የሆነው እንቁ የአማራ ሰማዕት አርበኛ 'አደም አሊ' የተሰየመ መሆኑን አትዘንጉ። አገዛዙም/የኦህዴድ ሰራዊት አጋጣሚውን በመጠቀም በዚህ ወቅት 'ለኤሬቻ መባዕ' ይሆነው ዘንድ አማራን እርስበርስ ለማጫረስ በማሴር መካነሰላም ላይ በተሰራ ኦፕሬሽን በአገዛዙ የፀጥታ ዘርፍ፣ የሚሊሻ፣ የፖሊስ አመራር የነበሩ ሙስሊም ባንዳዎች የተወሰደውን እርምጃ ሀይማኖታዊ አጀንዳ አድርጎታል። የአጀንዳው ዋና ዓላማ ፋኖ ሙስሊም ጠል እንደሆነ ለማስመሰል እና ነባር እስልምና ኃይማኖት ተከታዮችን እና የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ክርስትና አማኞችን እርስበርስ ለማጋጨት ታስቦ ነው። ነገር ግን ጠቢቡ የአማራ ህዝብ ከምንጊዜውም በላይ ስለነቃ እንደወትሮው ሁሉ ይህንም ያከሽፈዋል። ያም ሆነ ይህ የፋኖ ትግል ክርስትናም  ይሁን እስልምና ኃይማኖት የሚከተሉ የአገዛዙ አስፈፃሚዎችን በሚገባቸው ልክ እየቀጣ መጥቷል። ነገም ይቀጥላል። ሲኖር የአገዛዙ አመራር፣ ሲሞት ሙስሊም የሚሆን ጠላት ገና ይጠርጋል። ለክርስትና ኃይማኖት ተከታይ አመራሮችም እንደዛው። በተያያዘ የአማራ ህልውና ታጋይ ሙስሊም አማራ ፋኖዎች በወንድማቸው 'አርበኛ አደም አሊ' ስም በተሰየመው 'ዘመቻ አባ ናደዉ' አማራ በመሆኗ ብቻ በግፍ የተገደለችውን የእህታቸውን የሰባት አመት ህፃን 'አንሻ ሙሃመድ'ን እና ሌሎች በአማራዊ ማንነታቸዉ ምክንያት የተጠቁ ሙስሊም አማሮችን ደም እየመለሱ ይገኛል። ሁለንታዊ አደጋ የተጋረጠበት የአማራ ህዝብ ኃይማኖት፣ እድሜ፣ ፆታ ወዘተ ወዘተ... ልዩነት ሳይገድበዉ በፋኖ ትግል ተፈጥሮአዊ ራስን የመከላከል መብት ተጠቅሞ ራሱን እየተከላከለና 'አማራዊ ማንነቱ' እንዳይጠፋ እየመከተ ቀጥሏል። አማራነት ይለምልም! አርበኛ ሞገስ አባራው የአፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ም/የፖለቲካ መምሪያ ኃላፊ ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን። ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️ https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk ‎

#MB_ለበዛባችሁ‼️ ከትግል ሚዳ መልክት ይድርሳችሁ ዘንድ ሸር አድርጉል!! #ብልፅግና_ሊመዝ_የሞከረው_የኃይማኖት_ግጭት‼️ በዘመቻ አርበኛ አደም አሊ (አባ ናደው) ሙሉ ቤተ-አማራ ላይ ከባድ ሽንፈት የገጠመው ፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና መካነሰላም ላይ የሃይማኖት ግጭት ለመፍጠር የመዘዘውን ካርድ አስመልክቶ የንጉስ ሚካኤል አሊ ኮር ህዝብ ግንኙነት አርበኛ አምሳ አለቃ ሁሴን ኡመር ዛሬ መስከረም 24/2018 ዓ.ም ከቦታው መልዕክት አስተላልፏል። የአርበኛው መልዕክት ሼርርርርር ይደረግ!!! 24/ዐ1/2018 ዓ.ም

Audio from Dave Dawit

በላይ ዕዝ 5ኛ ኮር ወንድማማቾች ብርጌድ ክልል እየሱስ የአድማ ብተና ካምኘ ላይ ጥቃት በመሰንዘር የጠላትን ኃይል ሙትና ቁስለኛ እንዲሁም እንዲበተን ማድረጋቸው ታወቀ።     ትላንት  መስከረም 23 ቀን /2018 ዓ.ም አመሻሽ ላይ የአፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ እዝ ዳግማዊ ቴዎድሮስ 5ኛ ኮር ታድሎ ብርሃን ክ/ጦር ወንድማማቾች ብርጌድ አዘዞ ክልል እየሱስ ልዩ ስሙ ጉምብሪት በተባለው የአድማ ብተና ካምኘን ሰብሮ በመግባት በብልጽግና ተላላኪ የአድማ ብተና አባላት ላይ የማያዳግም እርምጃ ተወስዶባቸዋል።     በእርምጃው የጠላት ኃይል 12 ሙት ፣ 20 ቁስለኛ ሲሆኑ በጥቃቱ  በርካቶች ተበትነው እግራቸው ወዳመራቸው አቅጣጫ ተበትነዋል።    ጉምብሪት የአድማ ብተና ካምኘ ላይ ጥቃት መድረሱን ያረጋገጠው ጠላት በቅርብ ርቀት ላይ ከሚገኘው አዘዞ የጦር ካምኘ ተጨማሪ አጋዥ ሰራዊት ይዞ የደረሰ ቢሆንም ሰራዊቱን ከሞትና ከመበታተን ሊታደገው ግን አልቻለም።       ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!! አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ እዝ መስከረም 24/ 2018 ዓ.ም ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን። ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️ https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk ‎

ትዉልዱ ለነፃነቱ ሲል ልዩነቱን እየተወ አንድነቱን እያጠናከረ ድርጂታችንን እየተቀላቀለ ይገኛል። አፋብኃ 9ኛ ክ/ጦር አረንዛዉ ጎንቻ ብርጌድ ከዚህ ቀደም በተለያዩ ምክንያቶች ከትግሉ እራሳቸዉን አግለዉ የነበሩ አባላትን ሰብስቦ አወያይቷል። ብርጌዱ ከዚህ ቀደም ባጋጠመዉ ውስጥ ችግር ምክንያት እና በተለያዩ ጉዳዮች እራሳቸዉን አግለዉ የቆዩት የፋኖ አባላት ከአመራሮች ጋር ዉይይት አድርገዋል። ብርጌዱ በዉስጡ ያጋጠሙትን ችግሮች በዘላቂነት በመፍታቱ እና በተሻለ ቁመና ላይ እንደሚገኝ እና በርካታ ጀብዶችን እየፈፀመ የተሻለ ቁመና ላይ መሆኑን የተረዱት የቀድሞ የፋኖ አባላት በቆይታቸዉ ባሉበት ቦታ በግዳጂ ሰዓት ከፋኖ ጎን ሆነዉ ጠላትን ሲፋለሙ የቆዩ ሲሆን በተናጠል የሚመጣ ለዉጥ ስለሌለ ሙሉ ትጥቃቸዉን ይዘዉ ከ50 በላይ አባላት አረንዛዉ ጎንቻ ብርጌድን ተቀላቅለዋል። የክ/ጦሩ እና የብርጌዱ አመራር በጋራ በመሆን ትግሉን ለተቀላቀሉ አባላት የፓለቲካ እና የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጥተዋል ብርጌዱን የተቀላቀሉ አባላትም በሻለቃ መዋቀሮች ተካተዉ  ለግዳጂ ዝግጁ ሆነዋል። በሌላ ዜና አባይ ሸለቆ ብርጌድ በሚያስተዳድራቸው የተለያዩ ቀበሌዎች ህዝባዊ ውይይቶች ተጠናክረው ቀጥለዋል ከእነብሴ ሳርምድር ወረዳ ምጥና ይማች ቀበሌ ማህበረሰብ ጋር ፍሬያማ ውይይት በማድረግ የተጓደሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመፍታት የጊዜያዊ አስተዳደር የነበሩ ችግሮችን በመፍታት ያልተሟሉ አመራሮችን በማሟላት ፤ ስኬታማ ዉይይቶች አድርገዋል። ነፍተኛ የሆነዉ ህዝባችን ነፍጡን ወልዉሎ በየቀበሌዎች ለማይቀረዉ የነፃነት ትግል እራሱን ለግዳጂ ዝግጁ አድርጎ እየጠበቀ ይገኛል። መስከረም 24/2018 ዓ.ም 9ኛ ሳሙኤል አወቀ ክ/ጦር ህ/ግንኙነት ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን። ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️ https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk ‎

ጀግኖቹ የበረኸኞቹ ጅበላ ሙተራ ብርጌድ ፋኖዎች በደብረ ማርቆስ ከተማ አስደናቂ ኦፐሬሽን ሰርተዋል። መስከረም 24/2018 ዓ.ም ጀግናው የበረኸኛው ጅበላ ሙተራ ብርጌድ በ 3 አቅጣጫ በመግባት የደብረ
ጀግኖቹ የበረኸኞቹ ጅበላ ሙተራ ብርጌድ ፋኖዎች በደብረ ማርቆስ ከተማ አስደናቂ ኦፐሬሽን ሰርተዋል። መስከረም 24/2018 ዓ.ም ጀግናው የበረኸኛው ጅበላ ሙተራ ብርጌድ  በ 3 አቅጣጫ በመግባት የደብረ ማርቆስን ከተማ ሲያደባየው አድሯል! ኦፐሬሽኑ በአራት አውደ ግምባሮች ማለትም በሞሰቢት ፣ ኮሌጅ ሲቪል ሰርቪስ ፣ ወንቃና በየቦ መኃል አደባባይ አካባቢ የተደረገ ሲሆን ከሌሊቱ 7:00 ገደማ እስከ ንጋት በተደረገው ውጊያ በርካታ ቁጥር ያለው የጠላት ኃይል እርምጃ ተወስዶበታል። ውጊያ በተደረገባቸው ሁሉም ቦታዎች ላይ የእጅ በእጅና የቦንብ ጥቃች የተፈጸሙ ሲሆን ዋርድዮችን ጨምሮ በርካታ የጠላት ኃይል ሙትና ቁስለኛ ሆኗል። ድል ለአማራ ፋኖ! አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ! ፋኖ ዘመን ባሳዝነው

ሰበር ዜና! የጎንደሬ በጋሻው ክ/ጦር አመራሮችን ለማፈን ከማክሰኝትና ከደጎማ የመጣው ኃይል ክፋኛ መመታቱ ታወቀ።           መስከረም 23 ለ24 /2018 ዓ.ም ከሌሊቱ 7:00 ላይ ጨረቃዋን በመጠቀም ከማክሰኝትና ከደጎማ ሃይሉን በማውጣጣት ድንዛዝ ከተባለው ቀበሌ ላይ ደፈጣ በመድፈጥ አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ እዝ ዳግማዊ ቴዎድሮስ 5ኛ ኮር የጎንደሬ በጋሻው ክ/ጦር አመራሮችንና የጥቁር አንበሳ ክ/ጦር አባላትን ለማፈን ከበባ ፈጽሞ አድሯል።     ጠላት በሌሊቱ ተጉዞ መድፈጡን መረጃ የደረሳቸው የክ/ጦሩ አመራሮች በቆራጥነት የሚመሩትን ጦር ከፊት ሆኖ በመምራትና በማዋጋት የብልጽግናን ወንበር አስጠባቂ ኃይል          13  ያህሉን በመግደልና          9ኙን ክፋኛ በማቁሰል ከበባውን ሰብረው መውጣት ችለዋል። እስካሁንም ድረስ የጠላት ኃይል ከደጎላ እስከ ፋና ጊዮርጊስ ከፍተኛ ቦታዎች ሰፍሮ እንደሚገኝም ለማወቅ ተችሏል።            ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!! @አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ እዝ ዳግ/ቴዎ/5ኛ ኮር ህ/ግን/ኃላፊ አርበኛ አብነት ሞላ ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን። ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️ https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk ‎

አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 3ኛ ክፍለጦር ፲ አለቃ ኤፍሬም አጥናፉ ብርጌድ  አዲስ ቅዳምን ከተማ ላይ የተሳካ ጥቃት በመፈፀም በርካታ ጠላት በመደምሰስ መሳሪያና ተተኳሽ ማርኳል። አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ ፣አዲስ ተስፋ! አፋብኃ|ቴዎድሮስ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ መስከረም 24/2018 ዓ.ም ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን። ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️ https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk ‎

መካነ ሰላም የተፈጠረው ምንድን ነው ? አርበኛ ሁሴን ዑመር የንጉስ ሚካኤል ኮር ህዝብ ግንኙነት ማብራሪያ ሰጥቷል ! አርበኛ አደም አሊ ሲመራቸው ከነበሩ ክፍለጦሮች መካከል 1.ሸዋን ግዛው ክፍለ ጦር ፋኖዎች 95% 2.ሸህ ሁሴን ጅብሪል ክፍለ ጦር ፋኖዎች 99% የእስልምና እምነት ተከታዮች ናቸው ዝርዝሩን አዳምጡት ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን። ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️ https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk ‎

ሰበር- ከመካነ ሰላም ፋኖ ማብራርያ ሰጠ https://youtu.be/KfSVDb1rXh8?si=GF--KMWaZgl5cyWw

የብልፅግናዉ ቁልፍ ሰዉ መስከረም 24/2018 የብልፅግና ታማኝ አገልጋይ እና ዋና የመንግስት የገቢ ምንጭ የነበረዉ ማህበረሰቡንም ካቅም በላይ ግብር በማስከፈል የሚታወቀዉ የእነብሴ ሳር ምድር ወረዳ
የብልፅግናዉ ቁልፍ ሰዉ መስከረም 24/2018 የብልፅግና ታማኝ አገልጋይ እና ዋና የመንግስት የገቢ ምንጭ የነበረዉ ማህበረሰቡንም ካቅም በላይ ግብር በማስከፈል የሚታወቀዉ የእነብሴ ሳር ምድር ወረዳ አመራር አቶ መልካም ደሴ ስርዓቱ አማራ ጠል መሆኑን ሲረዳ በቀኘ መዋቀር ዉስጥ አርበኛ በመሆን ከሶስት ወር በላይ ፋኖን ሲያግዝና በዉስጥ የመንግስት መዋቀር እንዲፈራርስ ስራ ሲሰራ ከቆየ በኋላ ግዳጁን ሲጨርስ አረመኔዉን ተሰናብቶ ለሌላ ግዳጂ ዝግጁ ሆኗል። ወንድማችን እስካሁን ላደረክልን መልካም ትብብር እያመሰገን ሌሎችም ቀኘ የዉስጥ አርበኞች ስራቹሁን በሚፈለገዉ ልክ እንድትሰሩና ለማይቀረዉ ድል በጋራ እንድንሰለፍ ማለት እንወዳለን። ሌሎችም ይሄን አረመኔ መንግስት ከማገዝና የህዝባቹሁን መከራ እና ስቃይ ከማብዛት በዉስጥ ባሉ የቀኘ አደረጃጀቶች ባስቸኳይ እንድትቀላቀሉ ማለት እንወዳለን። ክብር ለአማራ ህዝብ ሲሉ የህይወት ዋጋ ለከፈሉ ጎዶቻችን Zelalem Desta የዘጠነኛ ክፍለ ጦር ቃል አቀባይ

አብይ አህመድ በአማራ ህዝብ ላይ ያልሰራው ሲራ የለም!! በደቡብ ወሎ መከነሰላም ከተማ በኑር መስጅድ ውስጥ የተካሄደውን ሴራ በቪድዬ በተደገፈ መረጃ ለህዝብ ይፋ የምናደርግ ሲሆን አሁንም በድጋሜ የፖለቲካ ሴራን ልንረዳ ልናውቅ ይገባል። ብልፅግና አይደለም እንደዚህ አይነት ሴራ ተሳክቶለት ይቅርና ሰሞኑን ሜድያውን ያጥለቀለቀው በሙስሊም ስም በተደራጀ የሶሻል ሜድያ ስራዊት እንደነበር አይዘነጋም ስለዚህ ሁላችንም ጥንቃቄ በተሞላባት እየተንቀሳቀስን የብልፅግና የሀይማኖት ሴራውን አሁን ሳይሆን በፊትም የነበረች የሴራ ካርድ ናት ። ስለዚህ አሁን በድጋሜ ጥንቃቄ አይለየን እላለሁ ምክንያቱም ዘመቻው አሁንም ይቀጥላል ። ይህ ዘመቻ ግቡ ብልፅግናንን እና ህዝባችንን ለሁለት አመት ሲያሰቃዩ የነበሩ በግሩፕ የተደራጁ የብልፅግና ታጣቂዋችን ሳይቀር ማፅዳት እና ህዝባችንን ከስቆቃ በማውጣት  በራሱ ልጆች እያደራጀን መሄድ ነው ። ትግሉ ይቀጥላል ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን። ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️ https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk ‎

ታምረኛው ምስራቅ አማራ ፋኖ ዛሬም በምርኮ አንበሽብሾናል፡፡ ይህንን ጥቃት ለመሸፍንና የሙስሊሙን ድጋፍ ለማሳጣት የተበላበትንና ያረጀ ሴራ ተጥቅሞ ንፁህ ሙስሊሞችን ጨፍጭፎ አድሯል፡፡ ፋኖ ራሱ ሙስሊም ነው ፣ወገኖችን ሊያድን እንጅ ሊገል ፋኖ አልሆነም፡፡ዘመቻው የሙስሊሙ የአባ ናደው መሆኑን አትርሱት፡፡ ተዋዶ የሚኖረው ሙስሊም ክርስቲያኑ ተዘነጋሽ እንዲ ኢትዮጵያ መሆኑ ኢትዮጵያ ስትነሳ አማራ ትዝ እንደሚልህ አትርሳ!! ዘመቻው የህፃን አይሻ መሆኑን አትርሱት፡፡ ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን። ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️ https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk ‎

አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ ሐዲስ አለማየሁ 7ኛ ክፍለ ጦር አዋበል ወረዳ መብረቁ ብርጌድ የአገዛዙ አሽከር የሆነው አጥቦ አይለብሴው ሚሊሻ በአዋበል ወረዳ ዱቄ እስጢፋኖስ ቀበሌ ላይ በቀን 23/01/2018 ዓ.ም ከምሽቱ 2:00 ሰዓት ገደማ እርስ በርሱ ሲታኮስ አምሽቷል በዚህም የተነሳ በርካታ ሙትና ቁስለኛ ሆኗል።ከሟቾች መካከል የቆየ ታደለ የተባለ የስኩት እነጋትራ ቀበሌ ተወላጅ የሆነው የበፊት የልዩሀይል ምልስ አባል የነበረ አሁን የአብይ ቅጥረኛ ተለላኪ ቱልቱላ ላይመለስ ተሸኝቷል። የፋኖን ምት መቆቋም ያቃተው ሚሊሻ እርስ በርስ መገዳደል ጀምሯል ፣የፀቡ መነሻም የስርዓቱን የመጨረሻ ዉድቀት በመረዳት አፈሙዝ በማዞር እርስ በእርሱ መቀናደሽ ጀምሯል። አሁንም ጊዜዉ አልረፈደምና ይህን ገዳይ አረመኔ ስርዓተ ቀብሩን ለማፋጠን ከወገናቹህ ጎን ትቆሙ ዘንድ ጥሪ እናስተላልፋለን።💪💪💪💪💪💪💪💪 ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን አዲስ ትዉልድ አዲስ አስተሳሰብ አዲስ ተስፋ መስከረም 24 /01/ 2018 ዓ.ም ፋኖ ወንድምነህ ሠውነት የአዋ/ወ/መብረቁ ብርጌድ የህ/ግንኙነት ኃላፊ።

ከአማራ ፋኖ በወለጋ የተሰጠ የሀዘን መግለጫ ሚዚያ 08/1985ዓ.ም ከአባቱ ከአቶ ጌትነት ይርዳውና ከእናቱ እናትሰው ይርዳው ተገኘ   ምስራቅ ወለጋ ዞን ጊዳ አያና ወረዳ አንዶዴ ዲቾ ቀበሌ ሻሾበር ከተማ ተወልዶ እድሜው ለትምህርት ሲደርስ እንደማንኛውም አካባቢው ተወላጆች እዛው ሻሾበር ከተማ አንዶዴ ዲቾ  አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ትምህረቱን የጀመረው  አመለ ሸገው ወንድማችን በትምህርቱ ብዙም ሳይገፋ አካባቢው የምርት አካባቢ ከመሆኑ አንጻር ሂዎቱን በአርሶ አደርነት የጀመረው ወንድማችን በ2008ዓ.ም የትዳር አጋር በመያዝ 2010ዓ.ም ላይ የአንድ ወንድ ልጅ አባት ለመሆን በቅቶ ነበር። ወለጋ ምድር ላይ  በዬ አቅጣጫው የአማራው ማህበረሰብ መሳደድ፣መጨፍጨፍና ንብረት መዘረፍ ሲጀምር ወለጋ ምድር ላይ ነፍጥ ማንሳት አይደለም ሽመል ይዞ መንቀሳቀስ በሚያስፈራበት በዛ ዛመን እሱ ግን ወገኔ ሲሳደድ፣ ሲጨፈጨፍና ንብረቱ ሲዘረፍ ቁሜ ከማይ ሞቴን እመርጣለሁ በማለት 2012ላይ ነፍጥ አንስቶ ጫካ በመግባት የጊዳያና የሊሙ ገሊላ ወረዳ ነገደ አማራውያንን በማንቃትና በማደራጀት እራሳቸውን ከኦነግ እንዲከላከሉ በማድረግ እንዲሁም በሊሙ ገሊላ ወረዳ በኩል ወደ ጊዳ አያና ወረዳና ወደ ሊሙ ገሊላ ወረዳ አማራ የሚኖርባቸው ቀበሌውች ማለትም ወደ ዋጃ፣ ፊጤቦቆ እንዲሁም ወደ አርቁንቢ ቀበሌዎች የሚሰነዘሩ የኦነግ ሸኔ ጥቃቶች 2013እና 2014 ላይ ከትግል ጓዶቹ ጋር በመሆን የመራውን ጦርነት በሙሉ በአሸናፊት በማጠናቀቅ ማህበረሳባችንን ከመጨፍጨፍ፣ከመሳደድና ንብረት ከመዘረፍ በመታደጉ በማህረቡ ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነትን አገኘ። 2015 መጀመርያዎቹ ወራቶች ላይ የኦሮሚያ ልዩ ሀይል ምስራቅ ወለጋ ዞን ኪረሙ ወረዳ ሀሮ አዲስ አለም ከተማና አባካባቢዋ ከኦነግ ሸኔ እራሳቸውን እዬተከላከሉ የሚኖሩ ነገደ አማራውያን ላይ ተደጋጋሚ ጥቃት እዬከፈተ ከፍተኛ ጉዳት ማስተናገዱን ተከትሎ ከመላው የክልሉ ከተሞየች ጊዳ አያና ወረዳን እያቆራረጠ ወደ ኪረሙ ወረዳ እያስገባ ባለበት ስዓት ህዳር 24/2015 መላው ህዝባችን በማስተባበርና ክተት በማወጀ አንገር ጉትን ከተማ ላይ ወደ ኪረሙ ወረዳ የሚግተለተለውን የኦሮሚያ ልዩ ሀይል ድባቅ በመምታት 4የክልሉ ፖሊስ ፓትሮል 2ድሽቃ 4ብሬን 8ስናይፐር ቁጥሩ ይኸነው የማይባል ክላሽ ኮፍ እንዲሁም ቅጥቅጥ መኪኖች እንዲማረኩና የኪረሙ ወረዳን አማራ ለመጨፍጨፍ ሲግተለትል የነበረን ወራሪ ሰራዊት ምንገድ ላይ ታሪክ አድርገው ካስቀሩ ወጣቶች ግንባር ቀደሙን ይወስዳል ብንል ማጋነን አይሆንብንም። እንዲሁም አማራ ክልል ላይ አቢዎቱ ከፈነዳ በኋላ ውስን ጓዶቹን ይዞ ወደ አማራ ክልል ይዞ በመሻገር 2016ዓ.ም ከመጋቢት እስከ ንሐሴ በቆዬባቸው ወራቶች ሽንዲ ወንበርማ፣አዮ እሁዲት እስከ ሶሪት እንዲሁም ደጋ ዳሞት ግንባሮች ላይ ቀመሳተፍ አመርቂ ውጤቶችን አስመዘግቦ ታሪክን በደማቅ በእጁ ጽፏል። 2017 መጀመርያዎቹ ወራቶች ላይ ከትግል ጓዶቹ ጋር በመሆን ጊዳ አያና ወረዳ ላይ አንገር ጉትን ብርጌድን ሲመሰርቱ ካስመዘገባቸው የግንባር ጀብዶች አንጻር የብርጌዱ ወታደራዊ አዛዥ ሁኖ ተመረጠ።ሌት ተቀን ደከመኝ ሰለቼኝ የማያውቀው በማህበረሰቡ ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነት ያለው ፋኖ መልካሙ ጌትነት ጦርት ሲገባ እንደ ሌላው አዋጊ ከኋላ ሁኖ ሳይሆን የሚያዋጋው ጥላትን አንገት ለአንገት ተናንቆ ነበር ተዋጋቶ የሚያዋጋው። ፋኖ መልካሙ ጌትነትና ጓድቹ ጊዳ አያና ወረዳ ላይ የተመሰረትችውና በፋኖ መልካሙ ጌትነት ጦር አዛዥነት የምትመራው አንገር ጉትን ብርጌድ ምስረታዋ ጊዳ አያና ይሁን እንጅ የመላው ወለጋ ህዝብ ዘብ ብንላት ማጋነን አይሆንብንም። ጥላት ከዞኑ ዋና ከተማ ወደ ኪረሙ ወረዳ እንቅስቃሴ ሲያደርግ በፋኖ መልካሙ ጌትነት እዬተመራች ዲቾ ተራራ እዬጠበቀች ከአፈር የምትቀላቅለው እንዲሁም ጊዳ አያና ወረዳ በመነሳት በብርሃን ፍጥነት ኪረሙ ወረዳና አቤ ደንጎሮ ወረዳዎች በመግባት ጥላትን ቁም ስቅሉን የምታሳየው በአሁኑ ስዓት ካለው የሰው ሀይልና መሳርያ ብዛት አንጻር ወደ ክፍለጦር ያደገችው የፋኖ መልካሙ ጌትነት የእጅ ስሬት የሆነችው አንገር ጉትን ብርጌድ ነበረች። መስከረም 21/2018ዓ.ም ከስዓት የአገዛዙ ጥም ጦር ከአንዶዴና ከአንገር ጉትን ከተሞች ያለ የሌለ ሀይሉን አሰባስቦ እነ መልካሙ ይገኙበበታል ወደተባለው አሊ ቀበሌ ለከበባ ሲንቀሳቀስና አሊ ቀበሌ ላይ ሀይለኛ ጦርነት ሲጀመር ፋኖ መልካሙ ጌትነት ውስን አባሎቹን በመያዝ በቆረጣ አንዶዴ ከተማ  ያለው የአገዛዙ ሰራዊት ካምፕ ላይ በወሰደው መብረቃዊ ጥቃት  ካምፑን ሙሉ በሙሉ በመቆጣጠር አብዛኞቹ ወታደሮች ወደ ተራራ ሩጠው ሲወጡ ካምፑ ውስጥ የነበረውን ሙሉ ሎጅስቲክ ማለትም ከነፍስወከፍ እስከ ቡድን መሳርያ እንዲሁም የዲሽቃ የብሬንና ብዛት ያላቸው የክላሽ ተተኳሾች ማርኮ ወደ ውጭ በማውጣት ወደ ተራራ የሸሹት ወታደሮች በእጅ ለመያዝ ጦሩን ከፊት ሁኖ እዬመራ ተዋግቶ እያዋጋ ባለበት ስዓት ከጥላት በተተኮሰ ጥይት ታሪክን በደማቅ እጁ ጽፎ አልፏል። ፋኖ መልካሙ ጌትነት አንተን ማጣት ለኛ ከባድ ቢሆንም ብዙ መልካሙዎችን አፍርተህ አልፈሀልና እናመሰግናለን ለመላው የወለጋ ህዝብና ነገደ አማራውያን እንዲሁም ወዳጅ ዘመድቹ መጽናናትን እንመኛለን። ነፍሱን በአጸደገነት ከደጋጎቹ ጎን ያስቀምጥልን። መስከረም 24/2018ዓ.ም    የአማራ ፋኖ በወለጋ