uz
Feedback
ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

Kanalga Telegram’da o‘tish

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

Ko'proq ko'rsatish
3 537
Obunachilar
+24824 soatlar
+5847 kun
+97230 kun
Postlar arxiv
206ኛ እና 201ኛ ኮር በመቀናጀት በቁይ ከተማ በአደረጉት እልህ አስጨራሽ ትንቅንቅ 59 የመከላከያ ሰራዊት አባላት ሲደመሰሱ 29 ሚኒሻና ፖሊሶች መገደላቸው ተረጋግጧል። መጋቢት 17/2018 ዓ.ም ======================================= በቴዎድሮስ ዕዝ ዘመቻ መምሪያ ፻ አለቃ አበበ ሰውመሆን መሪነት ከሌሊቱ 10:00 ሰዓት ጀምሮ ቁይ ከተማን በመክበብ ከንጋቱ 11:30 በተጀመረ ውጊያ ቁይ ከተማን ሙሉ ለሙሉ በመቆጣጠር በአረመኔው ሰራዊት ላይ ያነጣጠረ ጥቃት በመክፈት 59 (ሀምሳ ዘጠኝ) የ75ኛ ክ/ጦር 3ኛ ሬጅመንት አባላት በተደረመሱ ምሽጎች ውስጥ ተገድለዋል። በግራሮ፣ በቴ/ሙ/ኮሌጅ፣ በአንደኛ ደረጃ ት/ቤት ፣አሞራ ገደል የነበሩ ተደራራቢ ጠንካራ ምሽጎች በተሰበሩበት አውደ ውጊያ በርካታ ወታደራዊ ድሎች ያስመዘገበው ቴዎድሮስ ዕዝ ጠላት የሚመካበትን የአሰንዳቦ የቁም ምሽግ በመደረማመስ ፦ ብሬን 2 (ሁለት) ስናይፐር 1 (አንድ) ክላሽ 51 (ሀምሳ አንድ) የቃታ መሳሪያ 8 ( ስምንት) ካዘና 13 (አስራ ሶስት) ቦምብ 21፣ቁጥሩ ያልታወቀ ተተኳሽና ወታደራዊ ቁሳቁሶች የተማረኩ ሲሆን፦ 59 የአረመኔ ሰራዊት 25 ሚኒሻ 4 ፖሊስ 2 ካድሬዎች ተገድለዋል። 35 ቁስለኛ አካላቸው በጥይት ሀሩር የተበሳሳ ሲሆን 2 (ሁለት) ፓትሮሎች ተቃጥለዋል። ኢንስፔክተር የፀዳው ወልዴ ወንጀል መከላከል ኃላፊ፣ ነግሬው ሰውነት፣ ካሳ ታምሩ እና ምኔ ሰውነት የተባሉ የአረመኔው ሰራዊት ወታደራዊ አመራሮች ከተገደሉት ውስጥ በፊት አውራሪነት ሲቀመጡ ሁለት መቶ አለቆች ከተገደሉ የጦር መኮንኖች መካከል ይገኙበታል ። በዚህ ጠንካራ ፍልሚያ የ206ኛ ኮር እና የ201ኛ ኮር የጦር አመራሮች የክ/ጦር መሪዎች ጋር በመናበብ ውጊያውን ከጠላት ጋር እየተፋለሙ መርተውታል። አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ! የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት

በሸበል በረንታ መርገጭ ንዑስ ከተማ በርካታ የጠላት ሀይል በመደምሰስ እና በማቁሰል አይበገሬው 64ኛ ክፍለ ጦር ድል ተቀዳጅቷል። ➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺ መጋቢት 17/2018 ዓ.ም የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክ/ጦር ልዩ ኮማንዶ ከማስመረቁ ማግስት ከክፍለ ጦሩ የተሰባሰበ ኃይል ጋር በሸበል በረንታ ወረዳ መርገጭ ንዑስ ከተማ ከአገዛዙ የጠላት ኃይል ጋር ከባድ ውጊያ በማድርግ በርካታ የጠላትን ኃይል በመደምሰስ እና በማቁሰል ዛሬም የደጅ አዝማች በላይ ዘለቀ ልጆች ታሪክ ሰረቷል። ክፍለ ጦር በዛሬው እለት መጋቢት 16/2018 ዓ.ም  በአካሄደው ውጊያ መርገጭ ከተማን ከጥዋቱ 12:00 ሰዓት እስከ 4:00 ሰዓት ድርስ የአገዛዙ ካንፖችን ሙሉ በሙሉ በመቅጣጠር ለአገዛዙ መንገድ መሪ የነበሩ ሚሊሻ፣ አድማ ብተና፣ ፖሊስ እና የአገዛዙ ቅጥርኛ አራጅ የመከላከያ ሰራዊትን ሲደመስስ በርካቶች ቁስለኛ ሆነው በሞት አፋፍ ላይ ይገኛሉ። በሸበል በረንታ መርገጭ ከተማ 64ኛ ክፍለ ጦር በአካሄደው ውጊያ መርገጭ ንፁስ ከተማ መሽጎ የሚገኘውን ካንፕ ለአራት ሰዓታት ሙሉ በሙሉ በመቆጣጠር ከ40 በላይ የአገዛዙ መንገድ መሪ ቅጥርኛ ሰራዊት ሲደመሰስ 20 ከበላይ የጠላት ኃይል ከባድ እና ቀላል ቁስለኛ በማድርግ 10 መሳሪያ ገቢ አድረጓል። በመርገጭ ከተማ በተደረገው ውጊያ ከተደመሰሱት እና ከባድ ቁስለኛ ከሆኑት የአገዛዙ ሰራዊት አባላት ውስጥ:- 1ኛ.ሚሊሻ 10 አለቃ ባየ ገዛኸኝ የሸበል በረንታ ሚሊሻ ፅ/ቤት ቤት ም/ል ኃላፊ           የተወገደ 2ኛ.ፖሊስ አሸናፊ ብሬን ተኳሽ    የተወገደ 3ኛ.ፖሊስ ጀማል                      የተወገደ 4ኛ.ፖሊስ እስማየል                  የተወገደ 5ኛ.ፖሊስ ሞላ መርጃ ደህንነት   የተወገደ 6ኛ.ፖሊስ ሰይድ                      የተወገደ 7ኛ.ሚሊሻ ትልቁ ጠጋነህ ነጠርጌ ቀበሌ   የተወገደ 8ኛ.ሚሊሻ አንለኝ ንጉሴ                          የተወገደ 9ኛ. ሚሊሻ አቃተ መረከቡ የጁ ባይሌ       ምረኮኛ 10ኛ.ሚሊሻ ዝናው ብርሃኑ ውራጌ ቀበሌ     ቁስለኛ 11ኛ.ሚሊሻ ስለሽ አሻግሬ ኃናማሪያም ቀበሌ ከባድ ቁስለኛ 12ኛ.ሚሊሻ ቄስ ፍቃዱ የተባሉ ከባድ ቁስለኛ ሲሆኑ ሌሎች በስም ያልዘረዘናቸው የአገዛዙ መንገድ መሪ ቅጥረኛ ሰራዊት በሸበል በረንታ መርገጭ ጤና ጣብያ እና የዕድውኃ የመጀመርያ ደረጃ ሆሲፒታል ገብተው በሞት አፋፍ ላይ መሆናቸውን አረጋግጠናል። ለግዜው ያልደረሱን ቀሪ መረጃዎችን ይዘን የምንመለስ ይሆናል። ለአማራ ህዝብ የህልውና ትግል ብለው በጀግንነት ለተዋደቁ ሰማዕታት ክብር ይድርስልን🙏🙏🙏 አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ!!             መጋቢት 17/2018 ዓ.ም አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ሕዝብ ግንኙነት

በሸበል በረንታ መርገጭ ንዑስ ከተማ በርካታ የጠላት ሀይል በመደምሰስ እና በማቁሰል አይበገሬው 64ኛ ክፍለ ጦር ድል ተቀዳጅቷል። ➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺ መጋቢት 17/2018 ዓ.ም የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክ/ጦር ልዩ ኮማንዶ ከማስመረቁ ማግስት ከክፍለ ጦሩ የተሰባሰበ ኃይል ጋር በሸበል በረንታ ወረዳ መርገጭ ንዑስ ከተማ ከአገዛዙ የጠላት ኃይል ጋር ከባድ ውጊያ በማድርግ በርካታ የጠላትን ኃይል በመደምሰስ እና በማቁሰል ዛሬም የደጅ አዝማች በላይ ዘለቀ ልጆች ታሪክ ሰረቷል። ክፍለ ጦር በዛሬው እለት መጋቢት 16/2018 ዓ.ም በአካሄደው ውጊያ መርገጭ ከተማን ከጥዋቱ 12:00 ሰዓት እስከ 4:00 ሰዓት ድርስ የአገዛዙ ካንፖችን ሙሉ በሙሉ በመቅጣጠር ለአገዛዙ መንገድ መሪ የነበሩ ሚሊሻ፣ አድማ ብተና፣ ፖሊስ እና የአገዛዙ ቅጥርኛ አራጅ የመከላከያ ሰራዊትን ሲደመስስ በርካቶች ቁስለኛ ሆነው በሞት አፋፍ ላይ ይገኛሉ። በሸበል በረንታ መርገጭ ከተማ 64ኛ ክፍለ ጦር በአካሄደው ውጊያ መርገጭ ንፁስ ከተማ መሽጎ የሚገኘውን ካንፕ ለአራት ሰዓታት ሙሉ በሙሉ በመቆጣጠር ከ40 በላይ የአገዛዙ መንገድ መሪ ቅጥርኛ ሰራዊት ሲደመሰስ 20 ከበላይ የጠላት ኃይል ከባድ እና ቀላል ቁስለኛ በማድርግ 10 መሳሪያ ገቢ አድረጓል። በመርገጭ ከተማ በተደረገው ውጊያ ከተደመሰሱት እና ከባድ ቁስለኛ ከሆኑት የአገዛዙ ሰራዊት አባላት ውስጥ:- 1ኛ.ሚሊሻ 10 አለቃ ባየ ገዛኸኝ የሸበል በረንታ ሚሊሻ ፅ/ቤት ቤት ም/ል ኃላፊ የተወገደ 2ኛ.ፖሊስ አሸናፊ ብሬን ተኳሽ የተወገደ 3ኛ.ፖሊስ ጀማል የተወገደ 4ኛ.ፖሊስ እስማየል የተወገደ 5ኛ.ፖሊስ ሞላ መርጃ ደህንነት የተወገደ 6ኛ.ፖሊስ ሰይድ የተወገደ 7ኛ.ሚሊሻ ትልቁ ጠጋነህ ነጠርጌ ቀበሌ የተወገደ 8ኛ.ሚሊሻ አንለኝ ንጉሴ የተወገደ 9ኛ. ሚሊሻ አቃተ መረከቡ የጁ ባይሌ ምረኮኛ 10ኛ.ሚሊሻ ዝናው ብርሃኑ ውራጌ ቀበሌ ቁስለኛ 11ኛ.ሚሊሻ ስለሽ አሻግሬ ኃናማሪያም ቀበሌ ከባድ ቁስለኛ 12ኛ.ሚሊሻ ቄስ ፍቃዱ የተባሉ ከባድ ቁስለኛ ሲሆኑ ሌሎች በስም ያልዘረዘናቸው የአገዛዙ መንገድ መሪ ቅጥረኛ ሰራዊት በሸበል በረንታ መርገጭ ጤና ጣብያ እና የዕድውኃ የመጀመርያ ደረጃ ሆሲፒታል ገብተው በሞት አፋፍ ላይ መሆናቸውን አረጋግጠናል። ለግዜው ያልደረሱን ቀሪ መረጃዎችን ይዘን የምንመለስ ይሆናል። ለአማራ ህዝብ የህልውና ትግል ብለው በጀግንነት ለተዋደቁ ሰማዕታት ክብር ይድርስልን🙏🙏🙏 አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ!! መጋቢት 17/2018 ዓ.ም አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ሕዝብ ግንኙነት

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ​Amhara Fano National Movement (AFNM) ​የስልጠና ጥሪ፡- ከቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 54ኛ ክ/ጦር የወጣ የስልጠና ማስታወቂያ ​መጋቢት 17/2018 ዓ.ም ​ጉዳዩ፡- ወታደራዊ ልምድና እውቀት የነበራችሁንና ከአማራ ትግል ውጭ ሆናችሁን ይመለከታል። ​ከላይ በጉዳዩ ለመግለጽ እንደተሞከረው የአማራ ህዝብ በቅርብና በሩቅ ምክንያቶች በውጭና በውስጥ ጠላቶች ሴራ ተሰርቶበት በደምና በአጥንቱ በመሰረታት ሀገሩ ሳይቀር ባይተዋር መደረጉ የደባባይ ሀቅ ነው። ለብዙ አስርት ዓመታት በሰላማዊ ትግል ጥያቄዎቹንና ችግሮቹን ቢያቀርብም ጠላቶች ትኩረታቸውን አንድነት ላይ በመስራታቸው ለስቃይ እንዲዳረግ ተደርጎ ቆይቷል። አሁን ግን የጠላቶቹን መረብ ሴራ በጥሶ አዲሱ ትውልድ እንደ አታጋይ ድርጅት (አ.ፋ.ብ.ን) መስርቷል። ድርጅቱ አማራዊ ቀና መምሪያና ስርዓት ያለው አታጋይ ድርጅት ሆኖ ተወልዷል። ይኸውም ድርጅቱ በ54ኛ ክ/ጦር ጥሪ አቅርቧል። ​በ54ኛ ክ/ጦር ስር ባሉ ቀጠናዎች (እነሆ ወረዳ ሞጣ፣ ሰዴ ወረዳ እና ቢቢኝ ወረዳ) ተወላጅ ሆናችሁ በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍል ያላችሁ፦ ​ምልስ የሀገር መከላከያ ​ምልስ የአማራ ልዩ ኃይል ​ምልስ ፖሊስና አድማ ብተና ​ምልስ የአማራ ክልል VIP እጀባ ኮማንዶ ​የምዝገባ ቦታ ወደ 54ኛ ክ/ጦር ማዕከል (ዋበር፣ አስተርዮ ኩርባ) በመምጣት የአማራን የጥቅም ትግል እንድታስቀጥሉ፣ እንድትመዘገቡና አማራዊ ግዴታችሁን እንድትወጡ እናሳስባለን!!! ​አማራነት ያሸንፋል! ​አዲስ ትውልድ!! አዲስ አስተሳሰብ!! አዲስ ተስፋ!! ​የ54ኛ ክ/ጦር ወታደራዊ መምሪያ የምዝገባ ቀን፡ ከመጋቢት 17 - 30/2018 ዓ.ም

#የአገዛዙ_ወታደሮች_በየቀኑ_ፋኖን_እየተቀላቀሉ_ይገኛሉ!    መጋቢት 17 ቀን 2018 ዓ.ም የብልፅግናው ወታደሮች የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ አፄ አምደጽዮን ኮር የራሰ አበበ አረጋይ ክፍለጦርን ተቀላቅለዋል። በዛሬው ዕለት ከፍቸ ሰላሌ ወረዳ  ፍቸ ከተማው ውሰጥ ትምህርት ቤት ላይ መሽጎ  የሚገኘው የዓብይ ዓህመድ ወንበር አሰጠባቂ  የሰሪዊት አባል አበበ ጥጋቡ  የተባለ መሰረታዊ  ወታደር ታዋጊ መሀንዲሰ  4ኛ ሬጅመንት አባል የነበረው የራሱን ዜጋ በድሮን ከሚጨፍጭፍ  ሰርዓት ጋር አልቀጥልም  በማለት በዛሬው ዕለት አፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ አፄ አምደ ፅዮን ኮር የራሰ አበበ አረጋይ ክፍለጦርን ከነሙሉ ትጥቁ ተቀላቅሏል። በተመሳሳይ ዜና በሞረትና ጅሁር ወረዳ  ጅሁር ከተማ ውሰጥ አድማ ብተና ተመድቦ የተቀምጠ  የፋሸሰቱ ዓብይ ዓህመድ ስልጣን ሲያሰጠብቅ የቆየው ያሬድ ሙጩ  የተባለ መሰረታዊ ወታደር የብሬን ተኳሸ ቢሆንም ነገር ግን በቅርብ ያገኝውን ክላሸ በማንሳት  የአፄ አምደ ፅዮን ኮር የራሰ አበበ አረጋይ ክፍለጦርን በሰላም ተቀላቅለዋል፡፡ መረጃው የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ አፄ አምደ ፅዮን ኮር የራስ አበበ አረጋይ ክፍለጦር የህዝብ ግንኙነት ክፍል ነው   መጋቢት 17 /2018 ዓ.ም  

የ55 ዓመቷ አዛውንት በብልፅግና መከላከያ ሰራዊት በህብረት ተደፍራ ህይወቷ አለፈ! መጋቢት 17/2018 ዓ/ም አዛውንቷ በሰሜን ወሎ አስተዳደር ዞን ላስታ ወረዳ 025 ቀበሌ ድብኮ ከተማ ከመኖሪያ ቤቷ መጋቢት 16/2018 ዓ/ም ጧት 12:00 ሰዓት በብልፅግና መከላከያ ሰራዊት ታፍና ከተወሰደች በኋላ እየተፈራረቁ በጋርዮሽ እንደደፈሯት ታውቋል። በምስራቅ አማራ ቀጠና ላስታ ወረዳ 025 ቀበሌ ድብኮ ከተማ ነዋሪ የነበረችው አዛውንት ወይዘሮ የሽዬ ጉቼ በለጠ የሦስት ወንዶች እና የሦስት ሴቶች በድምሩ የስድስት ልጆች እናትና ከባለቤቷ ጋር ቆርባ የምትኖር ትዳሯንና ቤተሰቦቿን ወዳድና አክባሪ አስታራቂ ነበረች። ወይዘሮ የሽዬ ጉቼ በደቡብ ዕዝ 204ኛ ኮር የብልፅግና መከላከያ ሰራዊት አባላት ታፍና ተወስዳ የተደፈረች ሲሆን መጋቢት 16/2018 ዓ/ም አመሻሽ ላይ እስከሬኗን በመኪና አምጥተው ድብኮ ከተማ ከመኖሪያ ቤቷ እንደጣሉት የአይን እማኞች ገልፀዋል። በተያያዘ መረጃ የፋኖ ሚስት ነሽ በሚል ወይዘሮ እማትቀር ተከታይ የምትባልን ግለሰብ አግተው በመውሰድ ሲያንገላቷት እንደዋሉ እና እዚሁ ድብኮ ቀበሌ ላይ ዲያቆን ዘውዱ፣ ማዕረግ ገላው፣ አንደበት መንግስቱና ንጉስ ጌጡ የተባሉ ግለሰቦችን አፍነው በመውሰድ ካንገላቷቸው በኋላ ከአንገት በላይ በደረሰባቸው ከባድ ድብደባ አሁንም ጀሯቸው መስማት እንደማይችል ታውቋል። ወከባና እንግልት የደረሰባቸው ግለሰቦች በላስታ ወረዳ 025 ቀበሌ ድብኮ ከተማ ላይ አሉ የተባሉ አስታራቂ የሐገር ሽማግሌዎች በማህበረሰቡ ዘንድ ተሰሚና ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ሲሆኑ ይህንን የባንዳነት ተግባር የመራውና ያስተባበረው የአካባቢው ተወላጅ የብልፅግና የላስታ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ አዳነ ካሳ እንደሆነ ከአይን እማኞች ባገኘነው መረጃ ተረጋግጧል። በመጨረሻም የአገዛዙ ብልፅግና ወንበር አስጠባቂ መከላከያ ሰራዊት ድብኮ ማርያምና ገብርኤል ቤተ-ክርስቲያን ቅጥር ግቢና ዙሪያውን ምሽግ ሲጭር መዋሉና ማደሩ የታወቀ ሲሆን ለቀጣይም ንፁሃንና የሃይማኖት ተቋማት ኢላማ እንደሆኑ ማሳያ ነው ሲሉ የአይን እማኞች ገልፀዋል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የ303ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ አርበኛ መምህር ቢሆነኝ ቢያበይን መረጃውን አድርሷል! ትግላችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ መጋቢት 17/2018 ዓ.ም

ነፋሱ ከተራራው ጫፍ እየተነሳ በኃይል ይነፍሳል። ያ የደጋው ቅዝቃዜና አጥንት ሰንጣቂ ብርድ ለብዙዎች አስፈሪ ቢሆንም፣ ለእርሱ ግን የነፃነት ሽታ ነው። አርበኛ ኢሳያስ ደመቀ በተራራው አፋፍ ላይ ቆሞ ወደ ታች ሲቃኝ። በዓይኖቹ ውስጥ የሚነበበው ፅናት እንጂ ፍርሃት አይደለም ፍርሃት በአንደበቱ ታሪክ ውስጥ ቦታ የለውምና። ​ኢሳያስ የአንበሳ ልጅ አንበሳ የተባለለት ጅግና በትከሻው ላይ ያንገተው ያ ጥቁር ክላሽ የመኖርና የመከበር ዋስትናው ይመስላል። ቆላውን ወርዶ፣ ደጋውን ወጥቶ፣ ዋሻና ገደሉን ለምዶታል። የአብይ አህመድ ሰራዊት ያስታጠቀውን ያን ጥቁር ብረት እንደ ጌጥ ሳይሆን እንደ ታሪክ መፅሐፍ ይዞታል። ​ አንድ ጥይት ለአንድ ጠላት! የሚለው መፈክር በሸለቆው ውስጥ ሲያስተጋባ፣ የኢሳያስ ቆራጥ ልብ በአዲስ ተስፋ ይመታል። ዛሬም እንደ ትላንቱ ከምስራቅ፣ ከምዕራብ፣ ከደቡብና ከሰሜን ከመጡት ወንድሞቹ ጋር ለአማራ ሕዝብ መኖርና ነፃነት ውድ ዋጋን እየከፈለ ይገኛል። ​በዚህ የነፃነት ጉዞ ላይ ኢሳያስ ብቻውን አልነበረም። በዙሪያው እንደ አጥቅሮት የከበቡት፣ የአንድነት ምሰሶ የሆኑ ታላላቅ አርበኞች አሉ። ​ከፊት መስመር ላይ አርበኛ መከታው ማሙ እንደ አለት የጠነከረ መከታ ሆኖ ይታየዋል። አርበኛ ኢንጅነር ደሳለኝ ሲያስብ ሽዋ ከንጉሶቹ መንደር ከሽዋ ምድር በከፍተኛ ወኔና ጥበብ ተነሥቶ ለአላማው ቁሞለታል። ከምስራቁ አድማስ ደግሞ እንደ ንጋት ኮከብ የሚመሰገነው አርበኛ ፊታውራሪ ድርሳን ብርሃኔ የጀግንነት ታሪኩን በሜዳው ላይ ገድሉን እየፃፈ ይገኛል።​እነዚህ የዘመኑ ሚኒልኮች በአንድነት ሲቆሙ፣ የተራራው ድምፅ ይለወጣል። ዛሬም ሆነ ነገ፣ የነፃነት ምልክት በእነዚህ የአማራ የቁርጥ ቀን ልጆች እጅ ላይ ትገኛለች። ​የአማራ ልጅ የብዙ እውቀት ባለቤት መሆኑን በተግባር እያሳየ ነው። ያ የጥንት የአባቶች ጥበብ ዛሬም በልጆቻቸው ደም ውስጥ ይፈሳል። ኢሳያስና ጓደኞቹ በከፈሉት መስዋዕትነት፣ ተራራውም ሆነ ገደሉ የነፃነትን ዜማ አብሮ መዘመር ጀምሯል። ታሪክ ራሷ ትመሰክራለች ይህ የአርበኝነት ትግል መጨረሻው ድል፣ ትርፉም ነፃነት ነው። Dawit Amhara ከንጉሶች መንደር

ቀን፡17/07/18 ዓ.ም ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) - ቢዛሞ ቀጠና አይሻ ሰይድ ዕዝ የተሰጠ መግለጫ ርዕስ፦ በስማ በለውና በግል ምቀኝነት ላይ የተመሰረተን የሴራ መግለጫ ስለማውገዝ!
+1
ቀን፡17/07/18 ዓ.ም ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) - ቢዛሞ ቀጠና አይሻ ሰይድ ዕዝ የተሰጠ መግለጫ ርዕስ፦ በስማ በለውና በግል ምቀኝነት ላይ የተመሰረተን የሴራ መግለጫ ስለማውገዝ!

አፋብን |ቴዎድሮስ ዕዝ _፩ 13 የጠላት  አባላት የምረት ጥሪውን ተቀብለው  ሙሉ ትጥቅ በመያዝ  ቴዎድሮስ ዕዝን ተቀላቅለዋል። በዛሬው እለት ወደ  201ኛ 74ኛ እና 54  ክፍለ ጦርን ከደ/ወርቅ ከተማ አገዛዙን ሲያገለግሉ  ፓራኮማንዶ አባላት ናችሁ ተብለው የተመረቁ  ሚሊሻዎች በህዝባችን ላይ እየተፈፀመ ያለውን ድርጊት ውስጥ ሆነን መቋቋም ስላልቻልን ቀሪ ጊዜያችን ህዝባችን መካስ አለብን በማለት በዛሬው ዕለት  ከእነ ሙሉ ትጥቃቸው ፋኖን  ተቀላቅለዋል። 1.እያዩ አብየ..... ኮሪያ 2.ብርቁ አስሜ..... ኮሪያ 3.እንዳለው አብየ..... ኮፍ ክላሽ 4.ብርሐኑ አስሜ .....ኮሪያ 5.የጸዳው አረጋ .....ኮሪያ 6.ክንዱ መላኩ .....ኮሪያ 7.ስላባት አዝመራው ....ኮሪያ 8 ደጉ ዳኛቸው  (መርጡለማርያ 9.አሳየ ጋሻው... አብራራው  ከግንደ ወይን 10.ከፋለ አውለኝ.. እስኬስ ከድጎ 54ክ/ጦር 11.ስመኘው ገረመው ..ክላሽ ጎንቻ 54ክ/ጦር የተቀላቀሉ ሲሆን በክፍ ለጦር አመራሮች አቀባበል ተደርጎላቸዋል።በተመሳሳይ 12.አበዉ_አሳየ እና 13.አዲሱ_አሳየ የተባሉ የአድማ ብተና ተወርዋሪ ክፍል አባላት የነበሩ ሁለት ወንድማማቾች ከአዲስ ቅዳም ከተማ የጠላት ካምፕ በመዉጣት ቀጠናዉ ላይ ወደምትገኘዋ የአፋብን ቴዎድሮስ እዝ 105ኛ ኮር 44ኛ ክ/ጦር ፭ኛ ሻለቃ በሰላም ተቀላቅለዋል። ____፪ በጃዊ ፈንድቃ ከተማ እና ደብረማርቆስ ከተማ  የጨረባ ምርጫ ለማስሄድ ሕዝብ ሲያስገድዱ በነበሩ የፀጥታአካላት ላይ እርምጃ ተወሰደ። በደብረ ማርቆስ ከተማ አብማ ክ/ከተማ ልዩ ቦታው ቄስ ሰፈር ተብሎ በሚታወቀው ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን አካባቢ የምርጫ ማስፈፀሚያ መዝገብ ይዘው ማህበረሰቡን በማስገደድ ላይ በነበሩ ፖሊስና ካድሬዎች ላይ 206ኛ ኮር 24ኛ ክ/ጦር ስናን አባጅሜ ሻለቃ በፈፀመችው መብረቃዊ ጥቃት ኮማንደር ቢያልፈው መኮነን የአብማ ክ/ከተማ ሰላምና ደህንነት ኃላፊ ከዚህ በፊት የሸበል በረንታ ወረዳ አስተዳዳሪ የነበረውን ጨምሮ 4ፖሊሶች ሲገደሉ የአብማ ከተማ አስተዳዳሪና ሁለት ፖሊሶች ከባድ ቁስለኛ ሁነው ደብረ ማርቆስ ሆስፒታል ወድቀዋል። በተመሳሳይ  105ኛ ኮር 66ኛ ክ/ጦር ቀጠና በጃዊ ፈንድቃ ከተማ  የምርጫ ቅስቀሳ ለማድረግ ሙከራ ሲያደርጉ የነበሩ የአብይ ተላላኪ ካድሬዎች ላይ ኮልኮሎ ተራ ተብሎ ከሚጠራዉ አካባቢ አዳኞቹ በፈፀሙት የቦምብ ጥቃት የአብይ አህመድን ቅጥረኞች ሙት እና ቁስለኛ ማድረግ ተችሏል። 1.ሸጋዉ የሚባል ፖሊስ 2.ሀይማኖት የሚባል ሚሊሻ ከበድ ቁስለኛ ሆነዉ ሪፈር በመባል ወደ ፓዊ ሆስፒታል የተወሰዱ ሲሆን ኮንስታብል ማርነሽ የተባለች ፖሊስ እና ሌሎች ቁስለኞችም እንዳሉ ማረጋገጥ ተችሏል። አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ ፣አዲስ ተስፋ!         ክፋት ለማንም ፣በጎነት ለሁሉም! አፋብን| ቴወድሮስ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ            መጋቢት 16/2018 ዓ.ም

አንድነትታችን ውበት ብቻ ሳይሆን የአሸናፊነት ፀጋ የተላበሰበት እጅጉን የሚያምር አፋብን ድርጅታችን በውስጡ እንቁ እንቁ ልጆችን ይዞ ወደ ፊት እየገሰገሰ ይገኛል አማራነት ውበት ብቻ አይደለም ማሪያምን አሸነፊነትም ጭምር ነው እናሸንፋለን ፍኖተ አማራ ሚዲያ ከግንባር ሁና የአማራ ፋኖዎችን የትግል እንቅስቃሴ እየሰራች ደጋና ተራራውን አብርን እየሰራን እንገኛለን ይወዳጁን። አርበኛ ወንድማችን በርታልን ፈጣሪ ይጠብቅ መልካም ምኞታችን ነው።