ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea
Kanalga Telegram’da o‘tish
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
Ko'proq ko'rsatish3 218
Obunachilar
+18224 soatlar
+2627 kun
+63730 kun
Postlar arxiv
አሳዛኝ ዜና!
በሰሜን ወሎ ዞን በራያ ቆቦ ወረዳ ጨፍጫፊውና አምባገነኑ የአብይ አህመድ አገዛዝ የንፁሀንን ህይወት ቀጠፈ።
ዛሬ ሚያዚያ 17/2018 ዓ/ም ጧት 4:30 ላይ የአማራ ፋኖን እርምጃ መቋቋም ባለመቻሉ ቆቦ ከተማ አቅራቢያ መንደፈራ ሆኖ ባስወነጨፈው መድፍ ኮባ 04 ቀበሌ ጦርነቱ የማይመለከታቸው ሁለት የአንድ ቤተሰብ ልጆችና አንድ ከቤቱ የተቀመጠ ሽማግሌ ህይወት ቀጥፏል።
እንደሚታወቀው ያለ ጦርነት መኖር የማይፈልገው አገዛዝ በባለፈው ሳምንት በቆቦና በአድስ ቅኝ በአማራ ፋኖ በወሎ ምኒልክ ዕዝ 102ኛ ኮር በተወሰደበት ከባድ እርምጃ ብስጭት ሁለት ቤተ-ክርስቲያኖች በማውደምና አንድ የ8 አመት ህፃን በመግደል እንዲሁም የቤተ-ክርስቲያን ሰንበት ተማሪዎችን ማቁሰሉ ይታወቃል።
በተጨማሪም በጌታቸው ረዳ የሚመራው ራሱን ሐራ መሬት እያለ የሚጠራው ቡድን እና የአብይ አህመድ ወንበር ጠባቂ ሰራዊት በ05 ቀበሌ ቡኩ፣ ኮረራው መንደር ፣ድንጋይ ቀበሌና 09 ቀበሌ ራማ አካባቢ የሚገኙትን አርሶ አደሮች ሽርጥ፣ ወርቅና ብር በመቀማት ወደ ተራ ዘራፊነት የተቀየረ መሆኑን በተግባር አሳይቷል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ የ102ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት ክፍል
ሚያዚያ 17/2018 ዓ.ም
ሌላኛው የአረጋ ከበደ መንግስት ጉድ።
=========================
✍️ኮማንደር ገበየሁ ካሴ አየነው የተባለ የፖሊስ መኮነን በ2017 ዓ•ም የአንደኛ ሻለቃ አድማ ብተና አመራር ሁኖ ብዙ ሰዎችን አግቶ ገንዘብ ተቀብሏል::
✍️ በርካቶችን ደግሞ ረ*ሽ*ኗል::
✍️ ይህም በማስረጃና መረጃ ተረጋግጧል::
✍️ ኮማንደር ገበየሁ ካሴ አየነው በሶስት ወንጀሎች ለባህርዳርና አካባቢው ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክስ ቀርቦበት ነበር::
✍️ የሶስቱ የክስ መዝገቦች የወንጀሎች አይነትም 👉 👉 ሁለቱ አግቶ ገንዘብ መቀበልና 👉 ሶስተኛው የክስ ፋይል በሰው ድብደባና አካል ማጉደል ነው::
✍️ በአንደኛው የክስ መዝገብ ማለትም ሰውን አግቶ ገንዘብ መቀበል ወንጀል ብር 300,000 መቀበሉ በባህርዳና አካባቢው ከፍተኛ ፍርድቤት ተረጋግጦ ለዚህ ፅፋተኝነቱም #ሶስት (3) አመት ፅኑ እስራት ተቀጣ።
✍️ ዉሳኔው የተሰጠበት ቀን ህዳር 15/2018 ዓ•ም ነው
✍️ የውሳኔው መዝገብ በወ/መ/ቁጥር 0421423 ነው( የፍርድቤት ውሳኔው ተያይዟል)
✍️ ጥፋተኛ ተብሎ 3 አመት ፅኑ እስራት ቢወሰንበትም የአረጋ ከበደ መንግስት ከባህርዳር የአንደኛ ሻለቃ አመራርነት አንስቶ በደቡብ ወሎ ዞን ለምትንቀሳቀሰው #የ21ኛ ሻለቃ አድማ መከላከል ፖሊስ አዛዥ ተደርጎ ተመደበ::
✍️ ወንጀለኛን በአዛዥነት መመደቡ fb ላይ ሲገለፅባቸው የአረጋ መንግስት ቦታ በመቀየር ከእስራት ለማስቀረት ሲባል ሰሞኑን ወደ ደ/ጎንደር ለተንቀሳቀሰችው አድማ ብተና አዛዥ ሁኖ እየሰራ ነው::
✍️ ወቸው ጉድ ያሰኛል የአረጋ ከበደ መንግስት የሚሰራው ስራ
👉 ማለትም አስገድዶ በመሰወር 300ሺ ብር የተቀበለን ሌ*ባ(የተበየነበት ስለሆነ ነው) ያውም በፍርድቤት የተወሰነበትን ግለሰብ ቦታ እየቀያየረሩ በአዛዥነት መመደብና ማሰራት ማለት በእኔ አስተሳስብ በየሄደበት ዜጎች እንዲታገቱና ገንዘብ እንዲከግሉ እንዲሁም እናቶችና ልጃገረዶች እንዲደፈሩ የማድረግ ስልት ነው ብል ስህተት አይሆንም ።
✍️ ኮማንደር ገበየሁ የሚመራቸው የጠጥታ አካላት ከእርሱ ምንድን ነው የሚማሩት?
👉 እገታ? 👉 ድብደባ? 👉 ስርቆት? 👉 አስገድዶ መድድፈር? 👉 ወይስ ህግ ማስከበር?
✍️ ለመሆኑ የህግ ፍርደኛን ህግ ለሚያስከብር የሰራዊት አባላት አዛዥ አድርጋችሁ መድባችሁ ስለፍትህ የማውራት ሞራል ይኖራችሁኃል?
✍️የዜጎችስ ደህንነት እንዴት ሁኖ ሊጠበቅ ይችላል? 👉 ወይስ የህግ የበላይነትን ሳይሆን እኛ ከህግ በላይ ነን የሚለውን ለማስተማር አስባችህ ይሆን? መልሱን ለእናንተ::
ማስታወሻ፦ የፍርድቤቱብን የውሳኔ ወረቀት ያንብቡ
✍️በመረጃና በማስረጃ ላይ ተመስርተን ማጋለጣችን ተጠናክሮ ይቀጥላለ
በቀድሞው የቡሬ ዳሞት ብርጌድ የኮማንዶ ስልጠናውን ያጠናቀቀው ኮማንዶ አበባው አጉማስ፣ የተሰጠውን ተልዕኮ በመፈፀም 109ኛ ኮር 77ኛ ክፍለጦር ተቀላቀለ።
ወደ ጠላት በመግባት መረጃ በማሰባሰብና የጠላትን እንቅስቃሴና ምስጢራዊ መረጃዎች ሲሰጠን ቆይቷል። ተልዕኮውን በስኬት በማጠናቀቅ ጂንፎ ኤስኬስ ከነ ሙሉ ትጥቁን ይዞ በመውጣት፣ የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 77ኛ ክፍለጦር ተቀላቅሏል።
አፋብን ምዕራብ ዐማራ ቀጠና ቴውድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 77ኛ ክፍለ ጦር ህዝብ ግንኙነት
16/08/2018
🛑"ተጠቅሞ መጣል" የውድቀት አዋጅ‼️
በትጥቅ ትግል ታሪክ ውስጥ ትልቁ ድል የጠላት ምሽግን መስበር ሳይሆን፣ በጓዶች መካከል ያለውን መተማመን መጠበቅ ነው። አንድ ታጋይ ወደ ጦር ግንባር የሚገሰግሰው ነገ ቢወድቅ የሚያነሳው፣ ቢሰዋ ቤተሰቡን የሚደግፍ የጸና ወንድማማችነት እንዳለ በማመን ነው። ይህ መንፈሳዊ ትስስር ከላላ ግን ትግሉ የሞራል መሰረቱን ያጣል።
በዚህ ፈታኝ ትግል ውስጥ የታመሙትንና የቆሰሉትን ዞር ብሎ ማየት እንደ ግዴታ ሳይሆን እንደ ትግሉ አካል ሊቆጠር ይገባል። የቆሰለን ታጋይ ጥሎ ማለፍ ወይም የተሰው ቤተሰቦችን ችላ ማለት፣ የትግሉን ዋጋ ዝቅ ያደርገዋል። "አብሮ የበላን አብሮ የሞተን አለመርሳት" የኢትዮጵያዊነት ብቻ ሳይሆን የታጋይነት መመሪያም ነው። ዛሬ በደምና በአጥንታቸው ለቆሙት ዋጋ አለመስጠት፣ ነገ ለሚተካው ትውልድ ተስፋ አስቆራጭ መልእክት ያስተላልፋል።
በቬትናም ትግል ወቅት የቪዬት ኮንግ መሪዎች አንድ መርህ ነበራቸው፦ "አንድም ጓድ ወደኋላ አይቀርም"። የቆሰለን ጥሎ ማለፍ እንደ ትልቅ ወንጀልና የትግል ክህደት ይቆጠር ነበር። ይህ መተሳሰር ነው የአሜሪካን ግዙፍ ጦር እንዲያሸንፉ ያደረጋቸው። በአንጻሩ፣ በታሪክ ብዙዎቹ የደቡብ አሜሪካ ሽምቅ ተዋጊዎች የከሰሙት፣ መሪዎቻቸው ከድል በኋላ ወይም በትግሉ መሀል የታመሙና የደከሙ ጓዶቻቸውን ችላ በማለታቸው የውስጥ መከፋፈልና ተስፋ መቁረጥ ስለነገሰ ነው።
ማንኛውም ሕዝባዊ ትግል "ተጠቅሞ የመጣል" ባህልን ሊጸየፍ ይገባል። በትጥቅ ትግል ታሪክ ውስጥ ብዙዎች የከሸፉት ጠላት በዝቶባቸው ሳይሆን፣ በትግሉ ውስጥ ለቆሰሉና ለደከሙ ጓዶቻቸው የሚሆን ልብ በማጣታቸው ነው። "የቀደመውን ያላከበረ፣ ለሚመጣው አይበጅም" እንደሚባለው፣ ለትላንት መስዋዕትነት እውቅና የማይሰጥ ጉዞ፣ የነገውን ድል የመሸከም አቅም አይኖረውም። አመራርነት ማለት በትከሻው ላይ የወደቁትን ጓዶቹን ተሸክሞ ወደ ድል መጓዝ እንጂ፣ የቆሰሉትን እየረገጡ ፊት መሮጥ አይደለም።
በቁስለኛው ደም ላይ ቆሞ ስለ ድል መስበክ ፍጹም ጀግንነት ሊሆን አይችልም። የቆሰሉትን ጓዶች እንደራስ ቤተሰብ አለመቁጠር በትግሉ ውስጥ ትልቅ ክፍተት ይፈጥራል። አመራሮች ዛሬ ችላ የሚሉት እያንዳንዱ ቁስለኛ፣ ነገ በሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች ወደ ትግሉ እንዳይቀላቀሉ የሚያደርግ 'ሕያው ምስክር' መሆኑን ማጤን ይገባል። ለቆሰለ ጓዱ የማይራራ ልብ፣ ነገ ለሚመራው ሕዝብ ይራራል ብሎ ማሰብ አስቸጋሪ ነው።
ትግሉ ግቡን እንዲመታ ከተፈለገ፣ የቆሰሉትንና የተሰዉትን አለማየት እንደ ትልቅ ውድቀት ሊታይ ይገባል። "ካልተያያዙ አይጸኑ፣ ካልተሳሳቡ አይበዙ" ነውና፣ ትግሉ መካከለኛውን መንገድ መርጦ፣ የደከሙትን ደግፎና የቆሰሉትን አንስቶ መጓዝ ይኖርበታል። ድል የሚገኘው በጠላት ብዛት ሳይሆን፣ በጓዶች መካከል ባለ የማይበጠስ መተሳሰብና የህሊና ንጽህና ነው።
ድል ለአማራ ህዝብ
+8
አፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዕዝ 206ኛ ከፍያለው ደሴ ኮር በጀግናውና ልበሙሉው ፋኖ ሻለቃ አንደበት ክንዳለም የክብር መስዋዕትነት የሽኝት ፕሮግራም ተካሄደ !!!
አርበኛ አንደበት ክንዳለም አንተ ጀግና ነህ ፤አንተ ልዩ ምልክታችን ነህ፤ አንተ የአባቶችህ ልጅ ነህ ፤ አንተ ትንሹ ገብርዬ ነህ ፤ አንተ የዚህ ትውልድ ምርኩዝ የቀጣዩም ልዩ ምልክት ሁነህ ትቀጥላለህ።
የጀግና ሞቱ ክብሩ ነውና በሚወደው በሚያከብረውና እንዳባቶቹ በትህትናና በአክብሮት በሚመለከተው ህዝብ ዘንድ የክብር ሽኝት ተካሂዶለታል። ፋኖ ሻለቃ አንደበት ክንዳለም በህይወት እያለም በህዝብ ዘንድ ተወዳጂ ፣ለፍትህና ለእኩልነት የታገለ ያታገለ የተዋጋና ያዋጋ የጦር ጠበብት ነበር።
ልበቀናው አንደበት ክንዳለም የጠላትን ኃይል አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት ሚያዚያ 13/2018 ዓ.ም ሳሊ ላይ የተሰዋ ሲሆን በኃይማኖት አባቶች የፍትሀት ስነ ስርዓት፣የህይወት ታሪኩ እንዲነበብ ተደርጎ፣ አፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዕዝ 206ኛ ከፍያለው ደሴ ኮርም ዛሬ ሚያዚያ 16/2018 ዓ.ም የጀግና እና የክብር ሽኝት በወታደራዊ ትርኢት አስፈጽሞለታል።
ጀግና ሞቱ የጀግንነት ነው! ትግልህን እንጠብቃለን! ቃልህንም እናከብራለ! ነፍስህን በአፀደ ገነት ያሳርፍልን!!!
አፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዕዝ 206ኛ ከፍያለው ደሴ ኮር ቃል አቀባይ ክፍል !!!
""ሚያዚያ 2016 ዓ.ም በጀግንነት ለአማራ ህዝብ ክብርና ነፃነት ሲል አንድያ ነፍሱን አሳልፎ የሰጠ አርበኛ ያስቀመጠው ለአማራ አርበኞች የአደራ ቃል።"""
እኔ በምድር ላይ በህይዎት የመኖር እድሌ 99% አብቅቷል በህይዎት የመኖር እድሌ ጠባብ እንደሆነ ያረጋገጥኩት ዛሬ ላይ ሳይሆን የአማራ ህዝብ መከራና ግፍ ሲበረታ የህዝቤን ክብርና ነፃነት ለማስመለስ ከትግል ጓዶቸ ጋር ምድራዊ የተደላደለ ኑሮዬን ትቸ ጫካ ዱር ቤት ካልኩበት ዕለት ጀምሮ ነው።እኔ የሚቆጨኝና ሞቼ እንኳ አፅሜ ዕረፍት የማያገኝ እንዲሁም የሞት ሞት የምሞተው የግፈኛውና የመከረኛው ህዝባችንን ነፃነት ሳናረጋግጥ የጀግና አርበኛ አባቶቻችንን ታሪክ ሳንደግም እንዲሁም ታሪክ አስወቃሽ ሆነን የጀመርነውን የህልውና ትግል ከዳር ሳናደርስ ከንቱ የቀረ እንደሁ ነው።ይህ ከሆነ ደግሞ የአማራ ህዝብ የባርነት ቀንበርን ይበልጥ እንደሚያከብደው ምንም ጥርጥር የለውም።አርበኛ መስለው እርስ በርሳችን እንድን በላላና አላማችንን ከግብ እንዳናደር ስ ሽኩቻዎች ሊገጥሙን ይችላሉ ይህ ደግሞ የትግል አንዱ ባህሪ ነው ቀድመን ልናስብበት እና መላ ልንይዝለት ይገባል።ጥበበኞችና አስተዋዮች ካልሆን ግን ትግል በባህሪ የራሱን ሰው የመብላት ሱስ አለበት።ይህ እንዳይሆን ስጋት አለኝ የሆነው ሆኖ ግን ይህ መከረኛ ህዝብ ብሏል አርበኛው በእኛ አጥንትና ደም ነፃነቱንና ክብሩን መልሰን እንዲሁም ከመከራና ግፍ አላቀን ለቀጣይ ተተኪ ትውልድ ማስረከብ አማራዊ ግዴታ አለብን ብሎ ነበር።
ሚያዚያ 4/2018 ዓ.ም ዲማ ጊዮርጊስ ላይ ልክ እንደ አባቶቹ ቃሉን አክብሮ ለአማራ ህዝብ ነፃነት ሲል የክብር መስዋዕትነትን በመክፈል የጀግንነት አክሊሉን የተቀዳጀው አርበኛ ኢንጅነር ተሾመ ለገሰ
አፈሩ ይቅለለው
ተሾመ ይለዋል አባቱ ለገሰ፣
ምናው በጠዋቱ ከሞት ገሰገሰ።
እናም አንባቢያን የአርበኛውን ዕይታ እንዴት አያችሁት? ፍርዱን ለእናንተ ልተው።
ሁለት ክላሽ ከአራት መቶ (400)የክላሽ ተተኳሽ ጋር በመያዝ ተቀላቅለውናል ።
የአብይ አህመድ እና ብርሀኑ ጁላ ጦር ከምስራቅ ዕዝ ፣303ኛ ኮር፣99ኛ ክፍለ ጦር 3ሬጅመንት አባል የነበሩት ጽዮን ደምሴ እና ተሻገር ሚልኪያስ አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮርን 33ኛ ክፍለ ጦርን ተቀላቅለዋል ።
ብልፅግና ጎንጅ ቆለላ ላይ የተደሠሰሰበትን ሀይል ይተኩልኛል ብሎ ከዳንግላ ካንፕ ወደጎንጅ በቅርቡ ያመጣቸው እንደሆኑ የሚናገሩት ወታደሮቹ ከመደምሰሳችን በፊት እንዲያተርፉን የተማፀንናቸው አካላት አትርፈውናል ሲሉ ከጭንቀት መውጣታቸውን አረጋግጠዋል ። አክለውም ብልፅግና የኢትዮጵያን ወጣት ህይወት ከማስቀዘፍ ውጭ ሊያሳከካው የሚችል ግብ ያለው እና ለዛም አቅም ያለው መንግስት አይደለም ሲሉ ስርአቱን ጀንበሩ እንደጠለቀችበት አስረድተዋል ።
▶️አዲስ ትውልድ
▶️አዲስ አስተሳሰብ
▶️አዳስ ተስፋ
የ102ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
አገዛዙ በንፁሃን እና በህዝብ መገልገያ ተቋማት ላይ የድሮን ጥቃት እንደሚፈፅም ከዚህ በታች ባለው የተጎጅ የድጋፍ ደብዳቤ አረጋግጧል።
የስልጠና ጥሪ‼️
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ(አፋብን) ምዕራብ አማራ ቀጠና የቴዎድሮስ ዕዝ የ105ኛ ኮር 66ኛ ክ/ጦር አዳዲስ ምልምል የፋኖ አባላት ማሰልጠን ይፈልጋል።
በመሆኑም ከታች ያለውን መስፈርት የምታሟሉ ሰልጣኞች በተጠቀሰው ቀንና ቦታ ተገኝታችሁ ምዝገባውን እንድታከናውኑ ጥሪ ቀርቧል።
➡️የመመዝገቢ ቀን ፦ከሚያዚያ 15-30 ; 2018 ዓ.ም
➡️የመመዝገቢያ ቦታ፦ስዋታም፣ፊልፊል እና ሲሚዳ
@አበጀ በለው ገርዬ
@@ህዝባዊ መድረኮች እየተካሔዱ ነው@@
በ24ኛ ክ/ጦር የስናን ወረዳ ጊዜያዊ የመንግስት አስተዳድር በሚያስተዳድራቸው ቀበሌዎች በመንቀሳቀስ የሚፈጠሩ ችግሮችን እየፈታ ይገኛል።
ሚያዚያ፦ 16/2018 ዓ.ም
በአፋብን ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴወድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር 24ኛ ክ/ጦር ስር የሚገኘው የስናን ወረዳ ጊዜያዊ የመንግስት አስተዳደር ከሚያስተዳድራቸው ቀበሌዎች መካከል አንዱ በሆነው በዋሻ ሚካኤል ቀበሌ ከቤተክርስቲያን እና ከአማጋ ጋር ተያይዞ ሲነሳ የነበረውንና የህዝብ ቅሬታ ሆኖ የቆየውን ጉዳይ ከሚመለከታቸው አካላት እና ከማህበረሰቡ ጋር በተደረገ ሰፊ ውይይት በሰላማዊ መንገድ መፍታት ተችሏል።
ላለፉት ጊዜያት በቤተክርስቲያን ጉዳይ በተለያዩ ምክንያቶች አለመግባባቶች ሲነሱ የቆዩ ቢሆንም ይህ ሁኔታ በአካባቢው ማህበረሰብ እንቅስቃሴ ላይ ተጽዕኖ ከማሳደሩ አስቀድሞ ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት የቀበሌው አመራሮች፣ የሃይማኖት አባቶች ፣ የሀገር ሽማግሌዎች ፣ የደብሩ አስተዳዳሪዎች እና የቀበሌውን ማህበረሰብ በማሳተፍ ተሳታፊዎች ሀሳባቸውን በነፃነት እንዲያንጸባርቁ ከተደረገ በኋላ፣ የጋራ መግባባት ላይ መድረስ ተችሏል።
የደብሩ ተገልጋዬች ችግሩ በዚህ መልኩ በመፈታቱ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው በቀጣይም መሰል ጥያቄዎችን በውይይትና በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ቁርጠኛ መሆናቸውን በመግለጽ በተሰራው ስራ መደሰታቸውን እና በማነኛውም መንገድ እየተደረገ ላለው የህልውና ትግል ለትግሉ እንቅፋት እንደማይሆኑና ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል።
በውይይቱ መጨረሻ ሀሳባቸውን የሰጡት የውይይቱ ተሳታፊዎችም ፋኖ በትግል ላይ ሆኖ በየቀበሌው እየተንቀሳቀሰ በሚሰራው አፋጣኝ ፍትህ መስጠቱን አመስግነው የሚሰጠው ፍትህ መንግስት ነኝ እያለ ሲታልለን አና ሲገፋን ከቆየው የብልፅግና ሰርዓት የተሻለ እና ፈጣን መሆኑን ገልፀዋል።
የስናን ወረዳ ጊዜያዊ መንግሰት ሚዲያ እና ግንኙት
አዲስ ሀሳብ፣
አዲስ አስተሳስብ፣
አዲስ ተስፋ፣
📌የመሬት ማቃጠል ፖሊሲ በአማራ ላይ:- የህልውና ትግልን በረሃብና በውድመት የመቀልበስ ስልታዊ ጥፋት
በጦርነት ታሪክ ውስጥ "የመሬት መቃጠል ፖሊሲ" (Scorched Earth Policy) የሚባለው ስልት፣ አንድ አምባገነን ሥርዓት የጠላቱን ኃይል መቋቋም ሲያቅተው፣ ተዋጊውን ከሕዝቡ ለመነጠልና ሕዝቡን ለተቃውሞ እንዳይነሳ ለማድረግ የሚጠቀምበት የመጨረሻውና እጅግ ዘግናኝ የጥፋት መንገድ ነው። ዛሬ በኢትዮጵያ፣ በተለይም በአማራ ላይ ውስጥ እየታየ ያለው እውነታ ከዚህ የተለየ አይደለም። የብልጽግና ሥርዓት በሕዝባዊው የፋኖ ትግል ፊት የፖለቲካም ሆነ የወታደራዊ የበላይነት ማግኘት ሲሳነው፣ ፊቱን ወደ ሕዝቡ መሠረታዊ የህልውና ምንጮች በማዞር መሬቱን በማቃጠል ሕዝብን የማንበርከክ ስልታዊ ጥቃት እያካሄደ ይገኛል።
ይህ ፖሊሲ በዋናነት የሚገለጠው በአርሶ አደሩ የኢኮኖሚ አቅም ላይ በሚሰነዘር ስልታዊ ውድመት ነው። በአማራ ላይ የሚታየው የሰብል መቃጠል፣ የእርሻ መሣሪያዎች መውደም እና ምርት ለገበያ እንዳይቀርብ የሚደረገው ዕገዳ፣ እንዲሁ በጦርነት መሃል የሚፈጠር "አጋጣሚ" ሳይሆን፣ ሆን ተብሎ ሕዝቡን በረሃብ ለመቅጣትና ለፋኖ ኃይል ደጋፊ እንዳይሆን ለማድረግ የታለመ የወንጀል ድርጊት ነው። አርሶ አደሩ በአንድ በኩል በከፍተኛ ዋጋ ማዳበሪያ እንዳያገኝ ይደረጋል፤ በሌላ በኩል ደግሞ የለፋበት ምርት ገና ከማሳው ሳይነሳ በከባድ መሣሪያና በእሳት እንዲጋይ ይደረጋል። ይህ ድርጊት "ሆድን በመምታት" ሕዝብን የማንበርከክ የከሳሪዎች ስልት ከመሆን ባለፈ፣ ሀገርን ወደማይወጣ የረሃብ አዘቅት ውስጥ የሚከት አደገኛ አካሄድ ነው።
ከኢኮኖሚ ውድመቱ ባሻገር፣ የተቋማትና የመሠረተ ልማት ዝርፊያና ውድመት ሌላኛው የመሬት መቃጠል ፖሊሲ መገለጫ ነው። በትምህርት ቤቶች፣ በጤና ተቋማትና በሕዝብ መገልገያ ድርጅቶች ላይ የሚፈጸመው ጥቃት ዓላማው ግልጽ ነው፦ ማኅበራዊ ትስስርን ማላላትና ሕዝቡን ለዘመናት ወደኋላ እንዲቀር ማድረግ። ሕክምና በማጣት የሚሞቱ እናቶች፣ ትምህርት በማቋረጣቸው ተስፋቸው የሚጨልም ወጣቶች እና መኖሪያ ቤታቸው የፈረሰባቸው ዜጎች ቁጥር እየጨመረ የመጣው፣ ሥርዓቱ "እኔ ካልገዛሁት ይህ ሕዝብ መኖር የለበትም" የሚል የጥፋት አባዜ ስለተጠናወተው ነው። ይህ ስልት በአማራ ሕዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለ ታሪካዊ ስርጭት ያለው ግፍ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል።
በተጨማሪም፣ ይህ ፖሊሲ በከባድ መሣሪያና በድሮን የሚፈጸሙ የሲቪል ጥቃቶችን ያካትታል። በገበያ ቦታዎች፣ በሃይማኖት ተቋማትና በመኖሪያ መንደሮች ላይ የሚዘነቡ ጥይቶች ዓላማቸው ወታደራዊ ግብን መምታት ሳይሆን፣ በሕዝቡ ውስጥ ፍርሃትንና ሽብርን መዝራት ነው። ሕዝቡ በገዛ መሬቱ ላይ ሰላም አጥቶ እንዲሰደድና እንዲበታተን በማድረግ፣ የተቃውሞ ድምፁን ለማዳፈን የሚደረገው ጥረት የሥርዓቱን የሞራል ውድቀትና የፖለቲካ ክስረት ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። መሬቱ ለአማራ ሕዝብ ርስቱ ብቻ ሳይሆን ማንነቱም በመሆኑ፣ ያንን መሬት የመኖሪያ አውድማ እንዳይሆን የማድረግ ሴራ፣ በታሪክ የዘር ማጥፋት እና በሰብዓዊነት ላይ የሚፈጸም ወንጀል ተብሎ የሚፈረጅ ነው።
ሆኖም ግን፣ የብልጽግና ሥርዓት ሊረዳው የሚገባው ትልቅ እውነት ቢኖር፣ የመሬት መቃጠል ፖሊሲ ታሪክ ውስጥ ሠርቶ የሚያውቀው ለጊዜው እንጂ ለዘላቂ ድል አለመሆኑን ነው። መሬትን በማቃጠል፣ ሰብልን በማውደም እና ሕዝብን በማፈናቀል የሚገኝ ሥልጣን የለም። ይልቁንም እንዲህ ዓይነቱ ጭካኔ የሕዝብን ብሶትና ቁጣ በማባባስ፣ የህልውና ትግሉን ይበልጥ እንዲጸናና እንዲመረር ያደርገዋል። ሕዝብ የኢኮኖሚና የማኅበራዊ መሠረቱን ሊያጣ ይችላል፤ ነገር ግን ነፃነቱንና ክብሩን ለማስመለስ የገባውን ቃል ኪዳን በመሣሪያ ኃይልና በረሃብ ማስለወጥ አይቻልም።
በአማራ ሕዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለው ይህ አረመኒያዊ ውድመት ዓለም አቀፍ ማኅበረሰብና የሀገር ውስጥ ታዛቢዎች በዝምታ ሊመለከቱት የማይገባ ታሪካዊ ወንጀል ነው። መሬትን በማቃጠል የሚመጣ "ብልጽግና" የለም፤ ያለው የሀገር ውድቀትና የታሪክ ተጠያቂነት ብቻ ነው። ይህንን የጥፋት ፖሊሲ የሚያስተባብሩና የሚያስፈጽሙ አካላት ሁሉ፣ ዛሬ በፈጸሙት እያንዳንዱ ድርጊት ነገ በሕዝብና በታሪክ ፊት መቆማቸው አይቀሬ ነው። የሕዝብ ትግል በጭስና በአመድ የሚዳፈን ሳይሆን፣ ከእሳቱ ውስጥ ይበልጥ ጠንክሮ የሚወጣ የብረት ፅናት መሆኑን ጊዜው ይመሰክራል።
ድል ለአማራ ሕዝብ!
+3
የአገዛዙ ወታደሮች ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ፋኖን መቀላቀላቸውን ቀጥለዋል!
"ፀረ ሕዝብ የሆነ የአገዛዝ ስርዓትን ማገልገል ይብቃን" ያሉ ሐብታሙ ዳግም፣ እዮብ ቀለቡ እንዲሁም ጀምበሩ ጫኔ የተባሉ አድማ ብተና አባላት በአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር 34ኛ ክ/ጦርን መቀላቀላቸውን መረብ ሚዲያ ለማረጋገጥ ችሏል።
ጀምበሩ ጫኔ የተባለው የአድማ ብተና አባል ሁለት ክላሽንኮቭ በመያዝ በደጀን ወረዳ ጉበያ ከተማ ከሚገኘው የጠላት ካምፕ በመውጣት 34ኛ ክ/ጦርን የተቀላቀለ ሲሆን፡ ሐብታሙ ዳግም እና እዮብ ቀለቡ የተባሉት ደግሞ ከኮርክ ከተማ በመውጣት በተመሳሳይ 34ኛ ክ/ጦርን ተቀላቅለዋል።
ከውጊያ ጎን ለጎን የስቦ ማስከዳት ስራ በሰፊው እየሰራ የሚገኘው 34ኛ ክ/ጦ፡ በዚህ ድርጊቱ የጠላት ኃይልን ብትንትኑን በማውጣት ማፍረክረኩን ቀጥሏል ሲል ክ/ጦሩ በህዝብ ግንኙነት ክፍሉ ነው
የቀጣይ ዙር የሰዴን ወረዳ ህዝብ ለማስፈጀት ቃል የገቡ ተሿሚዎችን ላስተዋውቃችሁ።
^^^^^^^^^^^^^^^^^^^>>>>>>>>>>
ካድሬነት = ቢጭኑት አህ*ያ ቢጋልቡት ፈ*ረ*ስ
ሚያ16/2018ዓ.ም
ከመከራ ያልተማሩ በምንስ ልታስተምራቸው ትችላለህ??
^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^
#ምስራቅ_ጎጃም_ሰዴ ወረዳ የመሸገውን የስርዓቱን አረመኔ ሰራዊትና የሂደት አመራርን አፋብን በቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮርና 206ኛ ኮር የተደመሰሰና የተማረከ መሆኑን መጋቢት 30/2018ዓ.ም መግለፃችን ይታወሳል።
አሁን ደሞ ጭራሽ ተስፋ አልቆርጥ ያለው ብልፅ(ግ)ና ሰዴ ላይ በቆጆች ቀምሶ ከወደቀ በኋላ
ነፍስ ዘርቶ ለመንቀሣቀሥ እየሞከረ እና አዲሥ የስርዓቱ የሂደት ካድሬ መድቧል።
ይኸውም
1.ሰፊነው ካሴ አስተዳዳሪ
2. ደሴ ጤና ኃላፊ የነበረ ብልፅግና ፅ/ቤት ኃላፊ ሆኖ በተማረከ የተተካ
3. ተሾመ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን የነበረ አደረጃጀት ዘርፍ ሁኖ በተማረከ የተተካ
4. አዲሱ ዓለሜ ገቢዎች ጽ/ቤት የነበረ ፖለቲካ ዘርፍ በተደመሰሰ የተተካ ማነህ ባለተራ ነግረን ያላደረግነው በዓላማችን መሀል የለምና ጊዜ ደጉ ብለናል።
ህዝባችንን ይዘን ታሪካችንን በጣታችንና አሻራችንን በደማችን እንፅፋለን
አማራነት ያሸንፋል!!
አዲስ ትውልድ!!
አዲስ አስተሳሰብ አዲስ ተስፋ!!
የብልፅግናው ወታደሮች አገዛዙን በመክዳት ዛሬም ጀግናው የአማራ ፋኖን ሲቀላቀሉ ሰራዊታችን ድል ተቀዳጅቷል።
ሚያዚያ 16/2018ዓ.ም
በአማራ ህዝብ ላይ የተደቀነውን የህልውና አደጋ ለመቀልበስ እንደ ህዝብ እያታገለ በፊትአውራሪነት የተሰለፈውን የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) አታጋይ ድርጅት መመስረቱን ተከትሎ በርካታ የአገዛዙ ወታደሮች በሁሉም የአማራ ግዛቶች በየቀኑ ፋኖን እየተቀላቀሉ ይገኛሉ።
ዛሬን ጨምሮ በተከታታይ ሁለት ቀናት ውስጥ ስድስት የአገዛዙ ሰራዊት ከነ ሙሉ ትጥቃቸው የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝን ተቀላቅለዋል።
በዚሕ መሰረት አራት (4) የመከላከያ ሰራዊት አባላት የአፄ አምደ ፅዮን ኮር አፄ ዳዊት ክፍለጦርን ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ከተቀላቀሉት ውስጥ:-
✅ከ101ኛ አየር ወለድ ክ/ጦር 1 አባል
✅ከ105ኛ ክፍለጦር 1 አባል
✅ከ15ኛ ክፍለጦር 2 የመከላከያ ሰራዊት አባላት ሲሆኑ የኮሩ አሃድ የሆነውን የ7ለ70 ክፍለጦርን አንድ የ103ኛ አየር ወለድ ክፍለ ጦር አባል ከነ ሙሉ ትጥቁ ተቀላቅሏል።
በተመሳሳይ መረጃ ከብልፅግናው 104ኛ ልዩ ዘመቻ አየር ወለድ ኮመንዶ ክፍለጦር አንድ የሰራዊቱ አባል የመሐመድ ቢሆነኝ ኮር አስቴ ጉማ ተራራ ክፍለጦርን ከነ ሙሉ ትጥቁ ተቀላቅሏል።
በሌላ የአውደ ግንባር መረጃ በትላንትናው ዕለት ሬሽን በማቀበል ላይ በነበሩ የአገዛዙ ወታደሮች በነበልባሉ የሰራዊታችን ክንድ ክፉኛ መመታቱን መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን ፣የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ከሰም ፪ኛ ኮር በቡልጋ ክፍለጦር በፋኖ ሰራዊት ከፍተኛ ጉዳት ያስተናገደው የአገዛዙ ወራሪ ሀይል ከምሽቱ 11:30 ላይ የኮሩ አካል በሆኑት በነበልባል ክፍለጦር ቃኝና መሃንዲስ ነብሮ ሻለቃ ልዩ ቦታው ከሰም ወንዝ ተብሎ ከሚጠራው ስፍራ በጀግኖቹ በተፈፀመ መብረቃዊ ጥቃት የምርኮኛው ብርሀኑ ጁላ ሰራዊት ከፍተኛ ጉዳት ማስተናገዱን ዕዙ በመረጃው አረጋግጧል።
''ክብር ለትግሉ ሰማዕታት''
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን
የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ የህዝብ ግንኙነት መምሪያ
ሚያዚያ 16/2018ዓ.ም
