ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea
Ir al canal en Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
Mostrar más3 208
Suscriptores
+18224 horas
+2627 días
+63730 días
Archivo de publicaciones
ሁለት ክላሽ ከአራት መቶ (400)የክላሽ ተተኳሽ ጋር በመያዝ ተቀላቅለውናል ።
የአብይ አህመድ እና ብርሀኑ ጁላ ጦር ከምስራቅ ዕዝ ፣303ኛ ኮር፣99ኛ ክፍለ ጦር 3ሬጅመንት አባል የነበሩት ጽዮን ደምሴ እና ተሻገር ሚልኪያስ አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮርን 33ኛ ክፍለ ጦርን ተቀላቅለዋል ።
ብልፅግና ጎንጅ ቆለላ ላይ የተደሠሰሰበትን ሀይል ይተኩልኛል ብሎ ከዳንግላ ካንፕ ወደጎንጅ በቅርቡ ያመጣቸው እንደሆኑ የሚናገሩት ወታደሮቹ ከመደምሰሳችን በፊት እንዲያተርፉን የተማፀንናቸው አካላት አትርፈውናል ሲሉ ከጭንቀት መውጣታቸውን አረጋግጠዋል ። አክለውም ብልፅግና የኢትዮጵያን ወጣት ህይወት ከማስቀዘፍ ውጭ ሊያሳከካው የሚችል ግብ ያለው እና ለዛም አቅም ያለው መንግስት አይደለም ሲሉ ስርአቱን ጀንበሩ እንደጠለቀችበት አስረድተዋል ።
▶️አዲስ ትውልድ
▶️አዲስ አስተሳሰብ
▶️አዳስ ተስፋ
የ102ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
አገዛዙ በንፁሃን እና በህዝብ መገልገያ ተቋማት ላይ የድሮን ጥቃት እንደሚፈፅም ከዚህ በታች ባለው የተጎጅ የድጋፍ ደብዳቤ አረጋግጧል።
የስልጠና ጥሪ‼️
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ(አፋብን) ምዕራብ አማራ ቀጠና የቴዎድሮስ ዕዝ የ105ኛ ኮር 66ኛ ክ/ጦር አዳዲስ ምልምል የፋኖ አባላት ማሰልጠን ይፈልጋል።
በመሆኑም ከታች ያለውን መስፈርት የምታሟሉ ሰልጣኞች በተጠቀሰው ቀንና ቦታ ተገኝታችሁ ምዝገባውን እንድታከናውኑ ጥሪ ቀርቧል።
➡️የመመዝገቢ ቀን ፦ከሚያዚያ 15-30 ; 2018 ዓ.ም
➡️የመመዝገቢያ ቦታ፦ስዋታም፣ፊልፊል እና ሲሚዳ
@አበጀ በለው ገርዬ
@@ህዝባዊ መድረኮች እየተካሔዱ ነው@@
በ24ኛ ክ/ጦር የስናን ወረዳ ጊዜያዊ የመንግስት አስተዳድር በሚያስተዳድራቸው ቀበሌዎች በመንቀሳቀስ የሚፈጠሩ ችግሮችን እየፈታ ይገኛል።
ሚያዚያ፦ 16/2018 ዓ.ም
በአፋብን ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴወድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር 24ኛ ክ/ጦር ስር የሚገኘው የስናን ወረዳ ጊዜያዊ የመንግስት አስተዳደር ከሚያስተዳድራቸው ቀበሌዎች መካከል አንዱ በሆነው በዋሻ ሚካኤል ቀበሌ ከቤተክርስቲያን እና ከአማጋ ጋር ተያይዞ ሲነሳ የነበረውንና የህዝብ ቅሬታ ሆኖ የቆየውን ጉዳይ ከሚመለከታቸው አካላት እና ከማህበረሰቡ ጋር በተደረገ ሰፊ ውይይት በሰላማዊ መንገድ መፍታት ተችሏል።
ላለፉት ጊዜያት በቤተክርስቲያን ጉዳይ በተለያዩ ምክንያቶች አለመግባባቶች ሲነሱ የቆዩ ቢሆንም ይህ ሁኔታ በአካባቢው ማህበረሰብ እንቅስቃሴ ላይ ተጽዕኖ ከማሳደሩ አስቀድሞ ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት የቀበሌው አመራሮች፣ የሃይማኖት አባቶች ፣ የሀገር ሽማግሌዎች ፣ የደብሩ አስተዳዳሪዎች እና የቀበሌውን ማህበረሰብ በማሳተፍ ተሳታፊዎች ሀሳባቸውን በነፃነት እንዲያንጸባርቁ ከተደረገ በኋላ፣ የጋራ መግባባት ላይ መድረስ ተችሏል።
የደብሩ ተገልጋዬች ችግሩ በዚህ መልኩ በመፈታቱ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው በቀጣይም መሰል ጥያቄዎችን በውይይትና በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ቁርጠኛ መሆናቸውን በመግለጽ በተሰራው ስራ መደሰታቸውን እና በማነኛውም መንገድ እየተደረገ ላለው የህልውና ትግል ለትግሉ እንቅፋት እንደማይሆኑና ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል።
በውይይቱ መጨረሻ ሀሳባቸውን የሰጡት የውይይቱ ተሳታፊዎችም ፋኖ በትግል ላይ ሆኖ በየቀበሌው እየተንቀሳቀሰ በሚሰራው አፋጣኝ ፍትህ መስጠቱን አመስግነው የሚሰጠው ፍትህ መንግስት ነኝ እያለ ሲታልለን አና ሲገፋን ከቆየው የብልፅግና ሰርዓት የተሻለ እና ፈጣን መሆኑን ገልፀዋል።
የስናን ወረዳ ጊዜያዊ መንግሰት ሚዲያ እና ግንኙት
አዲስ ሀሳብ፣
አዲስ አስተሳስብ፣
አዲስ ተስፋ፣
📌የመሬት ማቃጠል ፖሊሲ በአማራ ላይ:- የህልውና ትግልን በረሃብና በውድመት የመቀልበስ ስልታዊ ጥፋት
በጦርነት ታሪክ ውስጥ "የመሬት መቃጠል ፖሊሲ" (Scorched Earth Policy) የሚባለው ስልት፣ አንድ አምባገነን ሥርዓት የጠላቱን ኃይል መቋቋም ሲያቅተው፣ ተዋጊውን ከሕዝቡ ለመነጠልና ሕዝቡን ለተቃውሞ እንዳይነሳ ለማድረግ የሚጠቀምበት የመጨረሻውና እጅግ ዘግናኝ የጥፋት መንገድ ነው። ዛሬ በኢትዮጵያ፣ በተለይም በአማራ ላይ ውስጥ እየታየ ያለው እውነታ ከዚህ የተለየ አይደለም። የብልጽግና ሥርዓት በሕዝባዊው የፋኖ ትግል ፊት የፖለቲካም ሆነ የወታደራዊ የበላይነት ማግኘት ሲሳነው፣ ፊቱን ወደ ሕዝቡ መሠረታዊ የህልውና ምንጮች በማዞር መሬቱን በማቃጠል ሕዝብን የማንበርከክ ስልታዊ ጥቃት እያካሄደ ይገኛል።
ይህ ፖሊሲ በዋናነት የሚገለጠው በአርሶ አደሩ የኢኮኖሚ አቅም ላይ በሚሰነዘር ስልታዊ ውድመት ነው። በአማራ ላይ የሚታየው የሰብል መቃጠል፣ የእርሻ መሣሪያዎች መውደም እና ምርት ለገበያ እንዳይቀርብ የሚደረገው ዕገዳ፣ እንዲሁ በጦርነት መሃል የሚፈጠር "አጋጣሚ" ሳይሆን፣ ሆን ተብሎ ሕዝቡን በረሃብ ለመቅጣትና ለፋኖ ኃይል ደጋፊ እንዳይሆን ለማድረግ የታለመ የወንጀል ድርጊት ነው። አርሶ አደሩ በአንድ በኩል በከፍተኛ ዋጋ ማዳበሪያ እንዳያገኝ ይደረጋል፤ በሌላ በኩል ደግሞ የለፋበት ምርት ገና ከማሳው ሳይነሳ በከባድ መሣሪያና በእሳት እንዲጋይ ይደረጋል። ይህ ድርጊት "ሆድን በመምታት" ሕዝብን የማንበርከክ የከሳሪዎች ስልት ከመሆን ባለፈ፣ ሀገርን ወደማይወጣ የረሃብ አዘቅት ውስጥ የሚከት አደገኛ አካሄድ ነው።
ከኢኮኖሚ ውድመቱ ባሻገር፣ የተቋማትና የመሠረተ ልማት ዝርፊያና ውድመት ሌላኛው የመሬት መቃጠል ፖሊሲ መገለጫ ነው። በትምህርት ቤቶች፣ በጤና ተቋማትና በሕዝብ መገልገያ ድርጅቶች ላይ የሚፈጸመው ጥቃት ዓላማው ግልጽ ነው፦ ማኅበራዊ ትስስርን ማላላትና ሕዝቡን ለዘመናት ወደኋላ እንዲቀር ማድረግ። ሕክምና በማጣት የሚሞቱ እናቶች፣ ትምህርት በማቋረጣቸው ተስፋቸው የሚጨልም ወጣቶች እና መኖሪያ ቤታቸው የፈረሰባቸው ዜጎች ቁጥር እየጨመረ የመጣው፣ ሥርዓቱ "እኔ ካልገዛሁት ይህ ሕዝብ መኖር የለበትም" የሚል የጥፋት አባዜ ስለተጠናወተው ነው። ይህ ስልት በአማራ ሕዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለ ታሪካዊ ስርጭት ያለው ግፍ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል።
በተጨማሪም፣ ይህ ፖሊሲ በከባድ መሣሪያና በድሮን የሚፈጸሙ የሲቪል ጥቃቶችን ያካትታል። በገበያ ቦታዎች፣ በሃይማኖት ተቋማትና በመኖሪያ መንደሮች ላይ የሚዘነቡ ጥይቶች ዓላማቸው ወታደራዊ ግብን መምታት ሳይሆን፣ በሕዝቡ ውስጥ ፍርሃትንና ሽብርን መዝራት ነው። ሕዝቡ በገዛ መሬቱ ላይ ሰላም አጥቶ እንዲሰደድና እንዲበታተን በማድረግ፣ የተቃውሞ ድምፁን ለማዳፈን የሚደረገው ጥረት የሥርዓቱን የሞራል ውድቀትና የፖለቲካ ክስረት ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። መሬቱ ለአማራ ሕዝብ ርስቱ ብቻ ሳይሆን ማንነቱም በመሆኑ፣ ያንን መሬት የመኖሪያ አውድማ እንዳይሆን የማድረግ ሴራ፣ በታሪክ የዘር ማጥፋት እና በሰብዓዊነት ላይ የሚፈጸም ወንጀል ተብሎ የሚፈረጅ ነው።
ሆኖም ግን፣ የብልጽግና ሥርዓት ሊረዳው የሚገባው ትልቅ እውነት ቢኖር፣ የመሬት መቃጠል ፖሊሲ ታሪክ ውስጥ ሠርቶ የሚያውቀው ለጊዜው እንጂ ለዘላቂ ድል አለመሆኑን ነው። መሬትን በማቃጠል፣ ሰብልን በማውደም እና ሕዝብን በማፈናቀል የሚገኝ ሥልጣን የለም። ይልቁንም እንዲህ ዓይነቱ ጭካኔ የሕዝብን ብሶትና ቁጣ በማባባስ፣ የህልውና ትግሉን ይበልጥ እንዲጸናና እንዲመረር ያደርገዋል። ሕዝብ የኢኮኖሚና የማኅበራዊ መሠረቱን ሊያጣ ይችላል፤ ነገር ግን ነፃነቱንና ክብሩን ለማስመለስ የገባውን ቃል ኪዳን በመሣሪያ ኃይልና በረሃብ ማስለወጥ አይቻልም።
በአማራ ሕዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለው ይህ አረመኒያዊ ውድመት ዓለም አቀፍ ማኅበረሰብና የሀገር ውስጥ ታዛቢዎች በዝምታ ሊመለከቱት የማይገባ ታሪካዊ ወንጀል ነው። መሬትን በማቃጠል የሚመጣ "ብልጽግና" የለም፤ ያለው የሀገር ውድቀትና የታሪክ ተጠያቂነት ብቻ ነው። ይህንን የጥፋት ፖሊሲ የሚያስተባብሩና የሚያስፈጽሙ አካላት ሁሉ፣ ዛሬ በፈጸሙት እያንዳንዱ ድርጊት ነገ በሕዝብና በታሪክ ፊት መቆማቸው አይቀሬ ነው። የሕዝብ ትግል በጭስና በአመድ የሚዳፈን ሳይሆን፣ ከእሳቱ ውስጥ ይበልጥ ጠንክሮ የሚወጣ የብረት ፅናት መሆኑን ጊዜው ይመሰክራል።
ድል ለአማራ ሕዝብ!
+3
የአገዛዙ ወታደሮች ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ፋኖን መቀላቀላቸውን ቀጥለዋል!
"ፀረ ሕዝብ የሆነ የአገዛዝ ስርዓትን ማገልገል ይብቃን" ያሉ ሐብታሙ ዳግም፣ እዮብ ቀለቡ እንዲሁም ጀምበሩ ጫኔ የተባሉ አድማ ብተና አባላት በአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር 34ኛ ክ/ጦርን መቀላቀላቸውን መረብ ሚዲያ ለማረጋገጥ ችሏል።
ጀምበሩ ጫኔ የተባለው የአድማ ብተና አባል ሁለት ክላሽንኮቭ በመያዝ በደጀን ወረዳ ጉበያ ከተማ ከሚገኘው የጠላት ካምፕ በመውጣት 34ኛ ክ/ጦርን የተቀላቀለ ሲሆን፡ ሐብታሙ ዳግም እና እዮብ ቀለቡ የተባሉት ደግሞ ከኮርክ ከተማ በመውጣት በተመሳሳይ 34ኛ ክ/ጦርን ተቀላቅለዋል።
ከውጊያ ጎን ለጎን የስቦ ማስከዳት ስራ በሰፊው እየሰራ የሚገኘው 34ኛ ክ/ጦ፡ በዚህ ድርጊቱ የጠላት ኃይልን ብትንትኑን በማውጣት ማፍረክረኩን ቀጥሏል ሲል ክ/ጦሩ በህዝብ ግንኙነት ክፍሉ ነው
የቀጣይ ዙር የሰዴን ወረዳ ህዝብ ለማስፈጀት ቃል የገቡ ተሿሚዎችን ላስተዋውቃችሁ።
^^^^^^^^^^^^^^^^^^^>>>>>>>>>>
ካድሬነት = ቢጭኑት አህ*ያ ቢጋልቡት ፈ*ረ*ስ
ሚያ16/2018ዓ.ም
ከመከራ ያልተማሩ በምንስ ልታስተምራቸው ትችላለህ??
^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^
#ምስራቅ_ጎጃም_ሰዴ ወረዳ የመሸገውን የስርዓቱን አረመኔ ሰራዊትና የሂደት አመራርን አፋብን በቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮርና 206ኛ ኮር የተደመሰሰና የተማረከ መሆኑን መጋቢት 30/2018ዓ.ም መግለፃችን ይታወሳል።
አሁን ደሞ ጭራሽ ተስፋ አልቆርጥ ያለው ብልፅ(ግ)ና ሰዴ ላይ በቆጆች ቀምሶ ከወደቀ በኋላ
ነፍስ ዘርቶ ለመንቀሣቀሥ እየሞከረ እና አዲሥ የስርዓቱ የሂደት ካድሬ መድቧል።
ይኸውም
1.ሰፊነው ካሴ አስተዳዳሪ
2. ደሴ ጤና ኃላፊ የነበረ ብልፅግና ፅ/ቤት ኃላፊ ሆኖ በተማረከ የተተካ
3. ተሾመ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን የነበረ አደረጃጀት ዘርፍ ሁኖ በተማረከ የተተካ
4. አዲሱ ዓለሜ ገቢዎች ጽ/ቤት የነበረ ፖለቲካ ዘርፍ በተደመሰሰ የተተካ ማነህ ባለተራ ነግረን ያላደረግነው በዓላማችን መሀል የለምና ጊዜ ደጉ ብለናል።
ህዝባችንን ይዘን ታሪካችንን በጣታችንና አሻራችንን በደማችን እንፅፋለን
አማራነት ያሸንፋል!!
አዲስ ትውልድ!!
አዲስ አስተሳሰብ አዲስ ተስፋ!!
የብልፅግናው ወታደሮች አገዛዙን በመክዳት ዛሬም ጀግናው የአማራ ፋኖን ሲቀላቀሉ ሰራዊታችን ድል ተቀዳጅቷል።
ሚያዚያ 16/2018ዓ.ም
በአማራ ህዝብ ላይ የተደቀነውን የህልውና አደጋ ለመቀልበስ እንደ ህዝብ እያታገለ በፊትአውራሪነት የተሰለፈውን የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) አታጋይ ድርጅት መመስረቱን ተከትሎ በርካታ የአገዛዙ ወታደሮች በሁሉም የአማራ ግዛቶች በየቀኑ ፋኖን እየተቀላቀሉ ይገኛሉ።
ዛሬን ጨምሮ በተከታታይ ሁለት ቀናት ውስጥ ስድስት የአገዛዙ ሰራዊት ከነ ሙሉ ትጥቃቸው የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝን ተቀላቅለዋል።
በዚሕ መሰረት አራት (4) የመከላከያ ሰራዊት አባላት የአፄ አምደ ፅዮን ኮር አፄ ዳዊት ክፍለጦርን ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ከተቀላቀሉት ውስጥ:-
✅ከ101ኛ አየር ወለድ ክ/ጦር 1 አባል
✅ከ105ኛ ክፍለጦር 1 አባል
✅ከ15ኛ ክፍለጦር 2 የመከላከያ ሰራዊት አባላት ሲሆኑ የኮሩ አሃድ የሆነውን የ7ለ70 ክፍለጦርን አንድ የ103ኛ አየር ወለድ ክፍለ ጦር አባል ከነ ሙሉ ትጥቁ ተቀላቅሏል።
በተመሳሳይ መረጃ ከብልፅግናው 104ኛ ልዩ ዘመቻ አየር ወለድ ኮመንዶ ክፍለጦር አንድ የሰራዊቱ አባል የመሐመድ ቢሆነኝ ኮር አስቴ ጉማ ተራራ ክፍለጦርን ከነ ሙሉ ትጥቁ ተቀላቅሏል።
በሌላ የአውደ ግንባር መረጃ በትላንትናው ዕለት ሬሽን በማቀበል ላይ በነበሩ የአገዛዙ ወታደሮች በነበልባሉ የሰራዊታችን ክንድ ክፉኛ መመታቱን መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን ፣የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ከሰም ፪ኛ ኮር በቡልጋ ክፍለጦር በፋኖ ሰራዊት ከፍተኛ ጉዳት ያስተናገደው የአገዛዙ ወራሪ ሀይል ከምሽቱ 11:30 ላይ የኮሩ አካል በሆኑት በነበልባል ክፍለጦር ቃኝና መሃንዲስ ነብሮ ሻለቃ ልዩ ቦታው ከሰም ወንዝ ተብሎ ከሚጠራው ስፍራ በጀግኖቹ በተፈፀመ መብረቃዊ ጥቃት የምርኮኛው ብርሀኑ ጁላ ሰራዊት ከፍተኛ ጉዳት ማስተናገዱን ዕዙ በመረጃው አረጋግጧል።
''ክብር ለትግሉ ሰማዕታት''
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን
የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ የህዝብ ግንኙነት መምሪያ
ሚያዚያ 16/2018ዓ.ም
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ 106ኛ ኮር 34ኛ ክፍለ ጦር በጋዞ ወረዳ የጥላትን ሰራዊት ዶግ አመድ በማድረግ ድል አስመዘገቡ::
ከሚያዚያ 15/2018 ዓ/ም እስከ ሚያዚያ 16/2018 ዓ/ም ለተከታታይ ሁለት ቀናቶችን ያስቆጠረው አውደ ውጊያ በ34ኛ ክፍለ ጦር አናብስቶች የአገዛዙ ሰራዊት ከፍተኛ ምት ተፈፅሞበታል። ውጊያው ቀጥሎ ያለ ሲሆን ጥላት እስካሁን ሙትና ቁስለኛውን እያነሳ ላይዋጋበት የቆፈረውን ምሽጉን እየለቀቀ እየፈረጠጠ ይገኛል።
የፋኖዎች የድል ግስጋሴ የጋዞ ወረዳ ዋና ከተማ የእስታይሽ ከተማን ግማሽ አካልና ፖሊስ ጣቢያ በፋኖዎች ቁጥጥር ስር ውሏል። በዚህ የድል ግስጋሴ በብዙ ደርዘን የሁለት ቀን ቁስለኛና ሙቱን አገዛዙ ተሸክሞ ወደ ኋላ እግሬ አውጭኝ እያለ እየፈረጠጠ ይገኛል።
በዚህ ሰዓት የእስታይሽ ሆስፒታል በቁስለኞች የተሞሉ ሲሆን የጤና ጣቢያ እና የጤና ኬላን ባለሞያዎችን አገዛዙ በግድ ካላከማችሁ እየተባሉ በየ ስራ ቦታቸው እየታፈሱ መወሰዳቸውን የአይን እማኞች ገልፀዋል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!!!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ 106ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት ክፍል
ሚያዚያ 16/2018 ዓ.ም
ሰበር ዜና!!!
አፋብን ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ የ102ኛ ኮር 49ኛ ክፍለ ጦር የሰራዊት ተሃድሶና የአልባሳት መረሀ-ግብር በደማቅ ሁኔታ አካሔደ።
የ102ኛ ኮር አካል የሆነው የ49ኛ ክ/ጦር ከግዳጅ ጎን ለጎን የሰራዊት ተሀድሶና የአልባሳት ፕሮግራም በማድረግ ለወደ ፊት ለሚደረጉ ግዳጆች ዝግጁ መሆናቸውን የክፍለጦር አመራሮች ገልፀዋል።
በመርሀ ግብሩ ከተከናውኑት ሁነቶች መካከል በ49ኛ ክ/ጦር የሰልፍ ትሪኢት፣ በግዳጅ የተሻለ አፈፃፀም የነበራቸውን የሻለቃ አመራር፣ የክ/ጦር አመራር፣ የድርጅት አመራርን በመሸለምና ተወዳጅ የሆነውን የአማራ ፋኖ መዝሙር በጣዕመ ዜማ ቀርቧል።
የተሀድሶ ፕሮግራሙን የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የ102ኛ ኮር ዋና ሰብሳቢ አርበኛ ቀኝ አዝማች ረዳ ውበቱ ሲሆን ለ49ኛ ክ/ጦር የሰራዊት አባላት የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ሰብሳቢው አያይዘው እንደገለፁት የአማራን ህዝብ በሀይል ለማንበርከክ የመጣውን ነውረኛ አገዛዝ ለማስወገድ ከመቸውም ጊዜ በላይ ሰራዊቱ ዝግጁ እንድሆን ገለፁ።
በምርጫ ስም በህዝባችን ላይ ህገ-መንግስታዊና መዋቅራዊ በደል ለማስቀጠል እንድሁም የዳር ተመልካች ለማድረግ የመጣውን የብልፅግና አገዛዝ በቀላሉ ለማስወገድ በሰሞኑ በወሰድንበት ጠንካራ ምት የተብረከረከ በመሆኑ በኮራችን ለሚገኙ ክፍለጦሮች ከመቸውም ጊዜ በላይ ዝግጁ እንዲሆኑ ትዕዛዝ አስተላልፈዋል።
በመቀጠል ንግግር ያደረጉት የ102ኛ ኮር ዋና ወታደራዊ አዛዥ አርበኛ ጌታቸው መልኩ ለ49ኛ ክፍለ ጦር የሰራዊት አባላት የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አሰተላልፈዋል።
ወታደራዊ አዛዡ አያይዘው እንደተናገሩት ከሆነ የአብይ አህመድን ጨፍጫፊ አገዛዝ በአጭር ጊዜ ለማስወገድ ከመቸውም ጊዜ በላይ የሰራዊታቸውን ወትሮ ዝግጁነት እንደሚተማመኑበት ጠንከር ያለ ሀሳብ አስተላልፈዋል።
በተጨማሪም ንግግር ያደረጉት የአሁኑ 49ኛ ክ/ጦር የቀድሞው የከላኮርማ ክፍለ ጦር መስራችና የ102ኛ ኮር ም/ወታደራዊ አዛዥ አርበኛ ዘውዱ ዳርጌ ለሰራዊት አባሉ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ወታደራዊ አዛዡ ለሰራዊቱ ካስተላለፉት መካከል ስለ አላማ ፅናትና የትግል ባህሪያት በመግለፅ ማንም የአማራ ፋኖ ታጋይ የአማራ ብሔርተኝነትን ተላብሶ በህዝባችን ላይ በግደታ የተጫነበትን ቀንበር ከትክሻው ለማስወገድ ዝግጁ እንድሆን መልዕክት አስተላልፈዋል።
እንድሁም የ102ኛ ኮር የስልጠና መምሪያ ሀላፊ መቶ አለቃ ሲሳይ መንግስቴና የኮሩ የሰው ሀይልና የመስክ ስልጠና መምሪያ ሃላፊ አምሳ አለቃ ያብቃል ቢተው የተሀድሶውን የሰልፍ ትሪኢትና የአልባሳት ፕሮግራም በመምራት ዝግጅቱ እንድያምር የራሳቸውን አሻራ ጥለዋል።
በአፋብን ምኒልክ ዕዝ ወሎ ቤተ-አማራ ም/የአደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ አርበኛ አሰፋ መሰለ /አሳምነው/ በዝግጅቱ በመገኘት ለ49ኛ ክፍለ ጦር አመራርና የሰራዊት አባላት እንኳን ደስ ያላችሁ መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል።
የአረጃጀት ዘርፍ ሀላፊው አያይዘው ለሰራዊቱ ጨፍጫፊውንና አምባገነኑን አገዛዝ ለመፋለምና ህዝባቸውን ከገባበት ቅርቃር ውስጥ ለማውጣት ዝግጁ እንድሆን መልዕክት አስተላልፈዋል።
በመጨረሻም 102ኛ ኮር ዋና የፖለቲካ መምሪያ ሀላፊ አርበኛ ሻምበል አሌ ለ49ኛ ክፍለ ጦር አመራር የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
አያይዘው እንደተናገሩት የአማራ ህዝብ የፍትህ፣ የነፃነትና የህገ-መንግስት ጥያቄ ስላለው በወርድና በቁመቱ ልክ የፖለቲካ ውክልና እስኪኖረው ድረስ ጠንካራ ታጋይ እንድፈጠር ሲሉ አበክረው ገልፀዋል።
እንድሁም የ102ኛ ኮር የፖለቲካ መሪው እንደገለፁት ያለጦርነት መኖር ከማይፈልገው የአብይ አህመድ አገዛዝ የአማራን ህዝብ ነፃ ለማውጣት አመራራችንና የሰራዊት አባላችን በሙሉ በምናስተዳድራቸውና አድስ በተቆጣጠርናቸው አካባቢዎች ለህግና ስርዓት ተገዥ እንድሆን ጠንካራ መልዕክት አስተላልፈዋል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ወሎ-ቤተ አማራ ምኒልክ ዕዝ የ102ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
ሚያዚያ 16/2018 ዓ.ም
+1
በደብረወርቅ ከተማ አማራ በመሆናቸው ብቻ ተመርጠው ስርአቱ የእራሱ የሚሊሻ አመራሮቾን በመለየት ረሸኗቸው።
=============================
........ሚያዚያ 16/2018 ዓ.ም
በተደጋጋሚ ስርአቱ አየተናደ በመምጣት በብልፅግና ቤት ከባድ የሆነ ድንጋጤ የፈጠረ ሲሆን በቀን ሚያዚያ 15/2018 ዓ.ም ተቋሙ ውስጥ የነበሩ የሚሊሻ አመራሮች እርስ በእርስ የተገዳደሉ ሲሆን ከእነዚህም መካከል ፦
1.ሸጋው ምናሉ ፈንታ የሚሊሻ ጠርናፊ
2.ሸጋየ ታጠቅ....መረጃ እና ደህንነቱ 3. አሻግሬ ቢሌ....ሚላሻወች ሲሆኑ ስርአቱ በአደባባይ መሀል ከተማ ላይ በአመራሮች እርምጃ የተወሰደባቸው ከ10በላይ ሚሊሻወችም በእስር ላይ መሆናቸውን የ74ክ/ጦር ህ/ግንኙነት መረጃውን ያደረሰን ሲሆን
አሁንም ቢሆን መተኪያ የሌለው ህይወታቹህን ለአብይ አህመድ ወንበር ለማስጠበቅ ብላቹህ መርጦ ገዳይ ከሆነው ስርአት በመውጣት ወደ ወገኖቻቹህ እንድትቀላቀሉ በማለት እንጠዮቃለን።
የአፋብን ቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
አይበገሬው 64ኛ ክፍለ ጦር በጠላት ኃይል ላይ ደፈጣ በመጣል ጉዳት አደረሱ!!
64ኛ ክ/ጦር ሚያዚያ 16/2018 ዓ.ም
ሚያዚያ 15/2018 ዓ.ም በሸበል በረንታ የዕዱውኃ ከተማ በመነሳት ወደ ደጀን ከተማ በጉዞ ላይ የነበር የአገዛዙ ቅጥረኛ ሚኒሻ ላይ በጣሉት ደፈጣ በየዕዱውኃ አካባቢ የምጥጭ ጎጥ ላይ #አበዛው ደምል እስከ ወዳኛው ሲሸኝ ስማቸውን በውል ያላወቅናቸው የአገዛዙ ሰራዊት አባላት ሙትና ቁስለኛ ሆነዋል።
በሸበል በረንታ የዕድውኃ አካባቢው በተጣለው ደፈጣ ጉዳት ያስተናገደው የአገዛዙ ቅጥረኛ ሚኒሻ በየምጥች ጎጥ:-
1ኛ. ማሙሽ ይበልጣል የተባለ ንፁሃን አርሶ አደር በግፍ እረሽኗል።
2ኛ. አቶ አንዳርጌ ጫኔ የድውኃ ነዋሪ 1 በሬ ፣5 ከረጢት የህል ማዳበሪያ፣ የቤት እቃ በሙሉ ወድሟል።
3ኛ.አቶ ዳምጤ ጫኔ ሙሉ ንብረት የቤት እቃ አውድሟል
4ኛ. ጌታሰው ዳምጤ የተባለ ግለሰብ እና በሰረግ ላይ የነበረ የሙሽራ ቤተሰቦች እየደበደቡ አስረዋል። በየምጥች ጎጥ ላይ የሚኖሩ የማህበረሰብ ክፍል በመደብደብ የአካል ጉዳት አድርሰዋል።
በሌላ መረጃ ሚያዚያ 13/2018 ዓ.ም በእነማይ ቀሸምሽ ቀበሌ በአገዛዙ ዘራፊ ሰራዊት ከተዘረፈባቸው ንፁሀን መካከል:-
1ኛ. ፋኖ ሀብቴ ቢሴ 3 ኩንታል ሽንብራ፣ 2 ማዳበረያ ድቄት፣ ፋራሽ
2ኛ. ፋኖ ካሳሁን ዳኜ 20 ኩንታል ጤፍ፣10 ኩንታል ስንዴ እና ሙሉ የቤት ዕቃ
3ኛ. 1 ሞተር ዘረፈዋል።
4ኛ. በቀሸምሽ ቀበሌ የንፁሀን አርሶ አደሮችን ቤት በመግባት ሌጥ እና ዱቄት ሳይቀር ደፍተዋል። በቤት ውስጥ የሚገኙ ቁሳቁሶችንና መገልገያ እቃዎችን አውድመዋል። ከዚህ ጋር ተያይዞ የአፋብን ቴዎድሮስ 201ኛ ኮር 64ኛ ክፍለ ጦር በእነማይ ወረዳ ቀሸምሽ ቀበሌ የገባው የጠላት ኃይል ለማስወጣት በጠልማ ቀበሌ ከሚገኘው የአገዛዙ ሰራዊት ላይ ውጊያ በመክፈት በቀሸምሽ ቀበሌ ለዝርፊያ የገባውን የአገዛዙ ሰራዊት አስወጥቷል።
አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ!!
ሚያዚያ 16/2018 ዓ.ም
አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክፍለ ጦር ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ
አይበገሬው 64ኛ ክፍለ ጦር በጠላት ኃይል ላይ ደፈጣ በመጣል ጉዳት አደረሱ!!
64ኛ ክ/ጦር ሚያዚያ 16/2018 ዓ.ም
ሚያዚያ 15/2018 ዓ.ም በሸበል በረንታ የዕዱውኃ ከተማ በመነሳት ወደ ደጀን ከተማ በጉዞ ላይ የነበር የአገዛዙ ቅጥረኛ ሚኒሻ ላይ በጣሉት ደፈጣ በየዕዱውኃ አካባቢ የምጥጭ ጎጥ ላይ #አበዛው ደምል እስከ ወዳኛው ሲሸኝ ስማቸውን በውል ያላወቅናቸው የአገዛዙ ሰራዊት አባላት ሙትና ቁስለኛ ሆነዋል።
በሸበል በረንታ የዕድውኃ አካባቢው በተጣለው ደፈጣ ጉዳት ያስተናገደው የአገዛዙ ቅጥረኛ ሚኒሻ በየምጥች ጎጥ:-
1ኛ. ማሙሽ ይበልጣል የተባለ ንፁሃን አርሶ አደር በግፍ እረሽኗል።
2ኛ. አቶ አንዳርጌ ጫኔ የድውኃ ነዋሪ 1 በሬ ፣5 ከረጢት የህል ማዳበሪያ፣ የቤት እቃ በሙሉ ወድሟል።
3ኛ.አቶ ዳምጤ ጫኔ ሙሉ ንብረት የቤት እቃ አውድሟል
4ኛ. ጌታሰው ዳምጤ የተባለ ግለሰብ እና በሰረግ ላይ የነበረ የሙሽራ ቤተሰቦች እየደበደቡ አስረዋል። በየምጥች ጎጥ ላይ የሚኖሩ የማህበረሰብ ክፍል በመደብደብ የአካል ጉዳት አድርሰዋል።
በሌላ መረጃ ሚያዚያ 13/2018 ዓ.ም በእነማይ ቀሸምሽ ቀበሌ በአገዛዙ ዘራፊ ሰራዊት ከተዘረፈባቸው ንፁሀን መካከል:-
1ኛ. ፋኖ ሀብቴ ቢሴ 3 ኩንታል ሽንብራ፣ 2 ማዳበረያ ድቄት፣ ፋራሽ
2ኛ. ፋኖ ካሳሁን ዳኜ 20 ኩንታል ጤፍ፣10 ኩንታል ስንዴ እና ሙሉ የቤት ዕቃ
3ኛ. 1 ሞተር ዘረፈዋል።
4ኛ. በቀሸምሽ ቀበሌ የንፁሀን አርሶ አደሮችን ቤት በመግባት ሌጥ እና ዱቄት ሳይቀር ደፍተዋል። በቤት ውስጥ የሚገኙ ቁሳቁሶችንና መገልገያ እቃዎችን አውድመዋል። ከዚህ ጋር ተያይዞ የአፋብን ቴዎድሮስ 201ኛ ኮር 64ኛ ክፍለ ጦር በእነማይ ወረዳ ቀሸምሽ ቀበሌ የገባው የጠላት ኃይል ለማስወጣት በጠልማ ቀበሌ ከሚገኘው የአገዛዙ ሰራዊት ላይ ውጊያ በመክፈት በቀሸምሽ ቀበሌ ለዝርፊያ የገባውን የአገዛዙ ሰራዊት አስወጥቷል።
አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ!!
ሚያዚያ 16/2018 ዓ.ም
አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክፍለ ጦር ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ
