uz
Feedback

Firibgarlarga uchmang! Telemetrio bunday kanallarni topadi va belgilaydi 👉 Belgini ko‘rmoqchi bo‘lsangiz, obuna bo‘ling 👈

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

Kanalga Telegram’da o‘tish

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

Ko'proq ko'rsatish
4 129
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
+4197 kun
+1 13230 kun
Postlar arxiv
በውስጡ 9 ማህበራትን የያዘው የአማራ ማሕበራት ትብብር ተቋም በአፋብን ምስረታ መደሰቱን እና አብሮ ለመስራት ዝግጁ መሆኑን ገልጿል።
+1
በውስጡ 9 ማህበራትን የያዘው የአማራ ማሕበራት ትብብር ተቋም በአፋብን ምስረታ መደሰቱን እና አብሮ ለመስራት ዝግጁ መሆኑን ገልጿል።

10ሩ ኮማቾች ምን አሉ?😂 '' በአማራ ክልል መንግሥት እና በአማራ Faኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ) መካከል እንደ #አዲስ የሰላም ስምምነት ተካሄደ። የሰላም ስምምነቱን በአዲስ ማካሄድ ያስፈለገው በመጀመሪያው ስምምነት ያልተካተቱ ጉዳዮች በመኖራቸው ነው!'' ከሚለው ዘገባ ስር ከተሰጡ አስተያየቶች መካከል፦👇 ✅'' ባለፈው የተፈራረማችሁት ከቦኮሀራም ጋር ነበር እንዴ?'' ✅'' የአሁኑን ድራማችሁን ተመልካች የሚያሳጣው አፋህድ የሚባል ድርጅት በሌለበት የተደረገ በመሆኑ ነው!'' ✅'' ያው በፈሳ*ችሁም እንደማትዋጉ ስለማውቅ ፥ ከባለፈው ስምምነት ላይ ' ከክልሉ መንግስት ጋር ሁነን እንዋጋለን' የሚለውን አንቀፅ ያወጣሁት እኔ ነኝኮ!'' ✅'' ቁርስ ፣ ምሳ ፣ ራት ከሚለው ፖኬጅ ውጪ መክሰስ ለማስጨመር አዲስ ስምምነት መፈራረም ግን ፌር አይደለም!'' ✅'' ከየመንገዱ የለቃቀሟቸውን ወጣቶች በእናንተ ስም እየነዳችሁ ወደእሳት ለመማገድ ተስማምታችሁ የተፈራረማችሁት የስምምነት አንቀፅ ግን ፍፁም አረመኔነት ነው!'' ✅'' በመላው ኢትዮጵያ ተዘዋውረው የኮሪደር ልማቱን ቢያንስ 1000 ጊዜ ይጎበኛሉ የሚለው አንቀፅ የተካተተው ፣ በፈረስና በበቅሎ ስናጓጉዘው የነበረውን ኮሎኔል ፈንታው በመንገድ ወዝውዞ ድፍት ለማድረግ የታቀደ ነው!'' ✅'' ከሁሉ ከሁሉ የቆጨኝ ኮሎኔል ፈንታው በቁሙ መሞቱ ካልቀረ የጃል ሰኚን ያህል እንኳ ሰራዊት ሳይዝ ከአራት ወታደሮች ጋር እግሬ አውጪኝ ማለቱ ነው!'' ✅'' በስምምነቱ ላይ የጠጅም ሆነ የውስኪ ስም አለመጠቀሱ ለማስረሻ ሰጤ የተደገሰለትን ክፉ ድግስ አመላካች ነው!'' ✅'' እኛ የድራማ ተመልካቾቻችሁን እንዳታሰለቹን በየሚዲያው faኖን ለመፈረጅ ህወሓትና ሻዕቢያን ብቻ አትጠቀሙ። ቦኮሀራም ፣ አልሸባብ ፥ አይኤስ ፣ ታሊባን ፥ ...ወዘተን እያቀላቀላችሁ ተጠቀሙ!'' ✅'' ማስረሻ በስምምነቱ ሰሞኑን መከላከያ የገደ*ለው ወንድሙን የደም ካሳ እንዲከፈለው ጠይቋል የሚባለው እውነት ከሆነ 8ተኛው ሺ ከነገ ወዲያ ነው ማለት ነው!'' የቱ ኮማች ተመቻችሁ? የእናንተንም አስቂኝና ዘና የሚያደርጉ አስተያየቶች እስኪ አጋሩኝ!

የማታውቋቸው ካላችሁ ተዋወቋቸው "የአሳምነው ፅጌ አደራ አስቀጣዮች ናቸው"ከምሽግ ምሽግ እንደ አቦሸማኔ እየተወረወሩ ጠላትን አፈርከድሜ ያስበሉታል! እነሱ የተዋጣላቸው አለም የመሰከረላቸው ጦረኞች ናቸ
+3
የማታውቋቸው ካላችሁ ተዋወቋቸው "የአሳምነው ፅጌ አደራ አስቀጣዮች ናቸው"ከምሽግ ምሽግ እንደ አቦሸማኔ እየተወረወሩ ጠላትን አፈርከድሜ ያስበሉታል! እነሱ የተዋጣላቸው አለም የመሰከረላቸው ጦረኞች ናቸው ።ለወዳጆቻቸው ወዳጅ ናቸው! ለጠላታቸው ደግሞ እንደ አራስ ነብር ይሶረፋሉ እነሱ ሲስቁ እንጅ ሲቆጡ ቀና ብሎ ለማየት ያስፈራሉ ። ጅንን ቅብርር ያሉ የአማራ የቁርጥ ቀን ልጆች ናቸው። ከቤተ አምሐራ ሰማይ ስር !

ስደተኛ የነበረውን የአማራ ትግል ጥርት ባለ የአማራ ብሔርተኝነት ፣ በራሳችን የትግል መልከኣምድር ፣ በራሳችን የተፈጥሮ ሐብት ፣ በራሳችን ህዝብ መትከል ስንጀምር መነቀል አለበት በማለት ባለፉት በር
+1
ስደተኛ የነበረውን የአማራ ትግል ጥርት ባለ የአማራ ብሔርተኝነት ፣ በራሳችን የትግል መልከኣምድር ፣ በራሳችን የተፈጥሮ ሐብት ፣ በራሳችን ህዝብ መትከል ስንጀምር መነቀል አለበት በማለት ባለፉት በርካታ ወራት እንደነዚህ ሰዎች የተፈታተነን አልነበረም ። ትውልዱ የጠንካራ አስተውሎት እና የውሳኔ ባለቤት በመሆኑ ከትግሉ ሜዳ ሲያባርራቸው የአብይ አህመድ የበየ አይነት ካምፕ ውስጥ ገብተው ግዙፉን የአማራ አብዮት ለማጥላላት ሲጋጋጡ እያየናቸው ነው ። ትግላችን ራስ በቅ ነው ! ትግላችን አብይን ከመጣል ባሻገር ነው ! ትግላችን የአማራን ህዝብ የልዕልና ከፍታ የተሸከመ ነው !

የብልፅግና አማራ ጠሉ አረመኔያዊ ስርዓት የፊስቡክ አካውንት ስለተዘጋ 2k እናስገባው ቻሌንጁን ተቀላቀሉ https://www.facebook.com/share/p/1BxouFFSAm/

የሀይማኖት ክሀድያን ሀይማኖቱ እንዳይቀጥል አያደርጉትም‼️ የሀይማኖት ክሀድያን የነበሩበትን የሀይማኖት ተቋም ከህደው በመውጣት የወጡበትን ሀይማኖት ተቋም ስም በመጥራት ፣የተቀደሠውን ቃልና ቦታ ማንቆሸሽና ማራከስ እንደክብርና እንደጽድቅ ይቆጡሩታል። ክሀድያኑ የወጡበትን ሀይማኖት እንዳይመለክ፣እንዲጠፋ አላደረጉትም፣ ሁሉም የሀይማኖቱ ተከታዮች ተሠልፈው እነሡ ወደገቡበት ሀይማኖት እንዲገቡም አላደረጉትም፣ይልቁንም የሀይማኖት ተከታዮች እንዲበረቱና ሀይማኖታቸውም ደግሞ የበለጠ እንዲጠነክር ያደርጉታል። የፋኖን ተቋም ክደው የሚወጡ ክሀዲ ባንዳዎችም ፣ቁልጭ ያለ መነሻና መዳረሻ ያለውን የአማራን የህልውና ትግል ክደው በመውጣት፣ውድ የአማራ ልጆች የረገፉበትን የህልውና ተጋድሎ ቆሻሻ ስም በመቀባትና በማራከስ አንድ ጋት ወደኋላ አይመልሱትም። ይልቁንም የበለጠ እንዲጠነክርና እንዲበረታ ያደርጉታል እንጂ። ፋኖነት አሸናፊነት ነው።ፋኖነት የተበርካኪነትና እጂን ዘርግቶ መሳሪያ ለጠላቶቹ የሚሠጥ ሳይሆን የመጨረሻዋን አንድ ጥይት ወደራሱ የሚተኩስ የጀግንነትና የአርበኝነት ጥግ ነው። ክብር ለአማራነታቸው ሲሉ ስቀው ለተሠው ሰማዕታት‼️

ባለ ሽርጡ ክፍለ ጦር መርሳ ከተማ አቅራቢያ የአገዛዙ ሰራዊት ላይ የአር ፒ ጂ ጥቃት በመፈፀም ታላቅ ድል ተጎናፀፉ:: የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚሊኒክ ዕዝ ምስራቅ አማራ ኮር 1 የባለ ሽርጡ ክፍለ ጦር በጠላት ላይ መብረቃዊ ጥቃት አደረሰ። ዛሬ ጥር 14/2018 ዓ.ም ከጧቱ 12:00 ላይ በሰሜን ወሎ ዞን ሀብሩ ወረዳ መርሳ ከተማ አቅራቢያ ሊብሶ ኤላ እየተባለ በሚጠራ ቦታ ላይ የስርዓቱን ወንበር ጠባቂ ሰራዊት በአንድ ተሳቢ፣አንድ ሲኖትራክ እና አንድ ፖትሮ ከመርሳ ወደ ደሴ ሲጓጓዝ በባለሽርጡ ክፍለጦር ቃኝ በተያዘ ደፈጣ ሙሉ ለሙሉ በመደምሰስና በማውደም ታላቅ ድል ተጎናፀፈዋል። በዚህ 100% ኢላማውን በጠበቀ የአርፒጅ /RPG/ ጥቃት ከመርሳ ወደ ደሴ በአንድ ተሳቢ ፣በሲኖ ትራክ እና በአንድ ፖትሮል ተጭኖ ሲንቀሳቀስ የነበረውን ጨፍጫፊ ሰራዊት ሙሉ በሙሉ ከነ ተሽከርካሪው ማውደምና መደምሰስ ሲቻል፣ ስርዐቱ ሙትና ቁስለኛውን በአስር አንቡላንስ ወደ መርሳ ሆስፒታል ሲያመላልስ አርፍዷል። በዚህ አውደ ውጊያ ከተደመሰሱት የስርዓቱ ሀይሎች መካከል ለጊዜዉ ስማቸዉ ያልታወቀ ከፍተኛ አመራሮችም ይገኙበታል። በፋኖ ምት የተበሳጨዉ የጠላት ብልፅግና ሰራዊት ንፁሃን ወገኖቻችን ኢላማ በማድረግ የአርሶ አደሮችን ህይወት ሲቀጥፍና በመንገድ እያስቆመ በመደብደብና ንብረትም ሲያወድም ውሏል። የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምስራቅ  አማራ ቀጠና ሚሊኒክ  ዕዝ ጥር 14/2018 ዓ.ም

#የጠላት_እንቅስቃሴ‼️   ብዛት ያለው የአድማ ብተና እና መከላከያ ጥምር ኃይል ከቀኑ 7:00 አካባቢ ከባህርዳር ከተማ ወደ ጎንደር መውጫ በር እየተጓዘ ነው መረጃው ለወገን ሀይል ይድረስ‼️ 14/ዐ5/2018 ዓ.ም

የወለጋ ክፍለ ሀገር ፋኖ እዝ (ቢዛሞ) የድርጅቱ መዋቅር አካል የሚሆኑበትን ሁኔታ ላይ ውሳኔ ተላልፏል። እዙ በድርጅቱ ውስጥ የጠቅላላ ጉባኤ፣ ማዕከላዊ ኮሚቴ እና የስራ አስፈፃሚ እንዲሁም ሌሎች መዋ
+3
የወለጋ ክፍለ ሀገር ፋኖ እዝ (ቢዛሞ) የድርጅቱ መዋቅር አካል የሚሆኑበትን ሁኔታ ላይ ውሳኔ ተላልፏል። እዙ በድርጅቱ ውስጥ የጠቅላላ ጉባኤ፣ ማዕከላዊ ኮሚቴ እና የስራ አስፈፃሚ እንዲሁም ሌሎች መዋቅሮች ውስጥ ተመጣጣኝ እና አስፈላጊ ውክልና እንዲኖረው ወስኗል።

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ በቤንች ሸኮ ዞን የምንገኝ የአማራ ብሔር ተወላጆች፣ብሔርን መሰረት ያደረገ ግፍ እና በደል እየደረሰብን እና እየተፈፀብን እንገኛለን።አማራ ብሔር በመሆናችን ብቻ ፍትህ የማገኘ
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ በቤንች ሸኮ ዞን የምንገኝ የአማራ ብሔር ተወላጆች፣ብሔርን መሰረት ያደረገ ግፍ እና በደል እየደረሰብን እና እየተፈፀብን እንገኛለን።አማራ ብሔር በመሆናችን ብቻ ፍትህ የማገኘት መብታችን እንደተጠማን ቆየን።የአማራ ብሄር በመሆናችን ብቻ ከመንግስት መስራያ ቤቶች የማፈናቀል ስራ ተሰርቶብናል።የአካባቢ ብሄር ተወላጅ ሹማምንቶች የአማር ብሄር ቢሮ እንዳይሰራ በማስወጉድ የተማረውን አማራ በአደባባይ እያባረሩት ይገኛሉ።እነዚህ የአካባቢ ተሻሚዎች አላማቸው የተማረውን የአማራ ብሔር በውስጥ የማጥፋት ዘመቻ ይዘው እየሰሩት ይገኛል ፣የሶሻል ሚዲያ ሽፋን እንድትሰጥልን እንጠይቃለን ፣

#የጥንቃቄ_መልዕክት‼️ አሁን ከጥዋቱ ጀምሮ በመላው ሽዋ ደብር በርሃን ዙራያ በቀጠናና አካባቢው በስፋት የድሮን ቅኝት እየተደረገ ስለሆነ ጥንቃቄ አይለየን‼️ ጥር 14/ዐ5/2018 ዓ.ም በአምስቱም
#የጥንቃቄ_መልዕክት‼️ አሁን ከጥዋቱ ጀምሮ በመላው ሽዋ ደብር በርሃን ዙራያ በቀጠናና አካባቢው በስፋት የድሮን ቅኝት እየተደረገ ስለሆነ ጥንቃቄ አይለየን‼️ ጥር 14/ዐ5/2018 ዓ.ም በአምስቱም ማዕዘን የፋኖን አውደ ውጊያዎች ከግንባር  ሁነን እየሰራን 24 ስዓት እንገኛለን ከታች ባለው ቴሌግራም ሊንክ ጆይን በማድርግ ይወዳጁን። https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

''በአማራ ክልል በተፈጸሙ ከ70 በላይ የድሮን ጥቃቶች ቢያንስ 669 ሰዎች መገደላቸውተሰማ!'' የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት የኢትዮጵያ መንግሥት ኃይሎች በአማራ ክልል ቁጥራቸው 40 የሚደርስ የራሳቸው ወገን የሆኑ ሚሊሽያዎችን በድሮን ጥቃት መግደላቸውን አንድ ነርስ እና አንድ የአካባቢውን ባለሥልጣን ጠቅሶ የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘገበ። በየጊዜው በክልሉ በሰው አልባ አውሮፕላኖች ጥቃት እንደሚፈጽም የሚነገርለት ጦሩ፣ ባለፈው ጥር 15 ቀን 2018 ዓም በዋግህምራ አካባቢ በተፈፀመው ጥቃት የመንግስት ደጋፊዎች የሚገኙበትን ካምፕ መትቷል ሲሉ ማንነታቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ የአካባቢው ባለስልጣን ለፈረንሳይ ዜና አገልግሎት በስልክ ተናግረዋል። ጥቃቱ ከመፈጸሙ በፊት ምንም እንኳን ድሮኑ በካምፑ ላይ ቢያንዣብብም ጦሩ በማግስቱ የተፈጸመው ጥቃት "ስህተት" መሆኑን ለአካባቢው ባለሥልጣናት እንደገለጸ ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁት ኃላፊ ጨምረው ገልጸዋል። "ወዲያውኑ ጭስ እና እሳት አየሁ ፤ ወደ ስፍራውም ሮጬ ሄድኩ፤ የሞቱ ሰዎች አካላት እንዲሁም የቆሰሉ ሰዎች በህምመ ሲሰቃዩ ተመለከትኩ" በማለት ባለሥልጣኑ አስረድተዋል። ባለሥልጣኑ 36 ሰዎች ወዲያውኑ መገደላቸውን እንዲሁም ሁለት ተጨማሪ ሰዎችም ሆስፒታል ውስጥ መሞታቸውንም ተናግረዋል። አበባው ዝናቡ የተባሉ የሕክምና ባለሞያ የተገደሉት ሰዎች ቁጥር "ከ40 በላይ" እንደሆነ መናገራቸውን የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘግቧል። ባለሥልጣኑ"ላለፉት ስድስት ዓመታት መንግስትን ከጥቃት ለመከላከል ከቤተሰቦቻቸው እና ከሚወዷቸው ርቀው በበረሃና በዱር ሸንተረሩ ሲዋጉ የቆዩ የሚሊሽያ አባላት መኖሪያ መሆኑ የሚታወቅ ካምፕ በኛ ኃይሎች እንዴት ጥቃት ደርስበት?" ሲሉ ይጠይቃሉ። አንድ የጦሩ ቃል አቀባይ ስለደረሰው ጥቃት ምንም መረጃ እንዳልደረሳቸው ለፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ተናግረዋል። በአማራ ክልል የመንግሥት የፀጥታ አስከባሪዎች እና የፋኖ ታጣቂዎች ከሚያዚያ 2015 ዓ.ም. አንስቶ ውጊያ ውስጥ ቆይተዋል። በዓለም ዙሪያ የሚካሔዱ ግጭቶችን የሚመዘግበው አክሌድ (ACLED) የተሰኘ ገለልተኛ ተቋም ከጎርጎሮሳዊው 2023 ዓ.ም አንስቶ በአማራ ክልል በተፈጸሙ ከ70 በላይ የድሮን ጥቃቶች ቢያንስ 669 ሰዎች መገደላቸውን አስታውቋል።

የፋኖን አንድነት በጉጉት ሲጠብቁ የነበሩት የአገዛዙ ወታደሮችም ጭምር ናቸው። ፋኖ አንድ ወጥ ድርጅት መስርቶ አንድነቱን ባወጀ ማግስት የአገዛዙ ጦር በገፍ እየተናደ ፋኖን እየተቀላቀለ መሆኑ ታውቋል።
የፋኖን አንድነት በጉጉት ሲጠብቁ የነበሩት የአገዛዙ ወታደሮችም ጭምር ናቸው። ፋኖ አንድ ወጥ ድርጅት መስርቶ አንድነቱን ባወጀ ማግስት የአገዛዙ ጦር በገፍ እየተናደ ፋኖን እየተቀላቀለ መሆኑ ታውቋል። የፋኖን አንድ መሆን በጉጉት ሲጠብቅ የነበረው በመከራ ውስጥ የሚገኘው የአማራ ሕዝብና ሌሎች የዚህ ፀረ ሕዝብ ኦህዴድ መር ብልፅግና አገዛዝ ተጠቂ የሆኑ ብሔር ብሔረሰቦች ብቻ ሳይሆኑ አገዛዙን እያገለገሉ የሚገኙ ወታደሮችና ወታደራዊ አዛዦችም ጭምር ናቸው። የአገዛዙ ወታደሮች በጉጉትና በተስፋ ሲጠብቁት የነበረው የፋኖ አንድነት የብስራት ዜና መሰማቱን ተከትሎ፡ ጨርቄን ማቄን ሳይሉ ከስምሪት ቀጠናቸው በመጥፋት በገፍ ፋኖን እየተቀላቀሉ መሆኑን ፍኖተ አማራ ሚዲያ ለማረጋገጥ ችሏል። ሙሉ ዘገባውን አድምጡት👉h

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ የፖሊት ቢሮ ጥር 13 ቀን 2018 ዓ.ም ባካሄደው 2ኛው ድርጅታዊ ስብሰባው በተለያዩ አጀንዳወች ላይ ውይይት አድርጎ ውሳኔወችን አሳልፏል። በዚህም መሠረት:- ፩) የድርጅቱ ስራ አመራር አባላት በተገኙበት በዚህ የውይይት መድረክ ላይ ፖሊት ቢሮው አርበኛ እስክንድር ነጋ ያቀረበውን ማመልከቻ መርምሯል። በዚህም አርበኛ እስክንድር በግለሰባዊ ችግር ምክንያት ድርጅቱ በመደበበት የኃላፊነት ቦታ ላይ መቀጠል እንደማይችል ይልቁንም በድርጅት አባልነት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ለመቀጠል ዝግጁ መሆኑን እና የሚጠበቅበትን ሀላፊነቶችና ግዴታዎች በሙሉ እንደሚፈፅም ጠቅሶ ያቀረበው ጥያቄ በነፃ ፈቃዱ እና ፍላጎቱ የቀረበ መሆኑን ፖሊት ቢሮው አረጋግጧል። ሆኖም ግን ማመልከቻው ለፖሊት ቢሮው በደረሰበት ቅፅበት ለሚዲያ የወጣበት መንገድ የድርጅቱን አሰራር የሚጥስ እና ያልተገባ ትኩረት ለማግኘት የተደረገ መሆኑን ፖሊት ቢሮው ገምግሟል። ግለሰቡም ማመልከቻው ከአሰራር ውጭ በሚዲያ በኩል ይፋ መደረጉ ስህተት መሆኑን ላነጋገሩት የፖሊት ቢሮ አባላት አሳውቋል። እንዲሁም የድርጅታችን ምስረታ ይፋ በሆነ ማግስት እጅግ አንገብጋቢ ጉዳዮች እያሉ ይህ ጥያቄ መቅረቡ ግዜውን የጠበቀ አለመሆኑን አምኖበት በቃል ይቅርታ ጠይቋል። በመሆኑም አሳማኝ ምክንያቶች ካሉም እንኳን ትክክለኛውን ጊዜ መጠበቅ ሲገባው ከሌሎች አስቸኳይ የህልውና አጀንዳ በላይ ይህ ጉዳይ የድርጅቱ የመጀመሪያ አጀንዳ ሆኖ መቅረቡ ፖሊት ቢሮውን ያሳዘነው ቢሆንም ግለሰቡ በአባልነት ብቻ ለመቀጠል ያቀረበውን ማመልከቻ ፖሊት ቢሮው ተቀብሎታል። ፖሊት ቢሮዉ ለአርበኛ እስክንድር ተሰጥቶ በነበረው የኃላፊነት ቦታ ላይ ሌላ ሰው የሚተካ ይሆናል። ፪) የወለጋ ክፍለ ሀገር ፋኖ እዝ (ቢዛሞ) የድርጅቱ መዋቅር አካል የሚሆኑበትን ሁኔታ ላይ ውሳኔ ተላልፏል። እዙ በድርጅቱ ውስጥ የጠቅላላ ጉባኤ፣ ማዕከላዊ ኮሚቴ እና የስራ አስፈፃሚ እንዲሁም ሌሎች መዋቅሮች ውስጥ ተመጣጣኝ እና አስፈላጊ ውክልና እንዲኖረው ወስኗል። ፫) በድርጅቱ መተዳደሪያ ደንብ በተጠቀሰው መሠረት የአባት አርበኞች ምክር ቤት መዋቅር እንዲቋቋም ውሳኔ ተላልፏል። ዝርዝር ጉዳዩን በቀጣይ የምናሳውቅ ይሆናል። የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ

ለአንድ ግለሰብ ስልጣን ሲል ታዳጊው ህይወቱን ገበረ ይህ የምትመለከቱት ሩጦ ያልጠገበ ታዳጊ ልጅ ለአብይ አህመድ ስልጣን ሲል ህይወቱን ገብሯል። ለወደፊቱ በተለይ ደቡብ ወንድ ልጅ ብርቅ የሚሆንበት ጊ
+2
ለአንድ ግለሰብ ስልጣን ሲል ታዳጊው ህይወቱን ገበረ ይህ የምትመለከቱት ሩጦ ያልጠገበ ታዳጊ ልጅ ለአብይ አህመድ ስልጣን ሲል ህይወቱን ገብሯል። ለወደፊቱ በተለይ ደቡብ ወንድ ልጅ ብርቅ የሚሆንበት ጊዜ ሊመጣ ይችላል። በውድም በግድም እየታፈሱ ታዲጊዎች ወደ ወታደራዊ ማሰልጠኛዎች ይጋዛሉ። ለብለብ ስልጠና ይሰጣቸውና ወደ ጦር ሜዳ ይላካሉ። ታዳጊዎች ናቸው እና ጦርነት ሲጀመር ይደናበራሉ። ከዚያ ይገደላሉ።

አሁን አንድነት ተመሰርቷል የቀደሞው አጋዚዎች ብኋላም የአማራ ልዩ ሃይል ኮማንዶ ዩኒቶች አሁን ለመቀላቀል ምክንያት አያስፈገውም ኑ ተቀላቀሉ።
አሁን አንድነት ተመሰርቷል የቀደሞው አጋዚዎች ብኋላም የአማራ ልዩ ሃይል ኮማንዶ ዩኒቶች አሁን ለመቀላቀል ምክንያት አያስፈገውም ኑ ተቀላቀሉ።

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን ) ለሃገራዊ ፀረ ብልፅግና ኃይሎች ላቀረበው ጥሪ የጋምቤላ ታጣቂ ኃይሎች ጥምረት ጥያቄውን ተቀብሎ አብሮ እንደሚሠራ አሳውቋል። ይሄ ታጣቂ ኃይል ጋምቤላ ክልል ከማጃንግ እና ጋምቤላ ከተማ ውጭ ያሉ 3 ዞኖችን ተቆጣጥሮ የሚገኝ ኃይል ነው። በመላው ሐገሪቱ የሚገኙ አካባቢዎች እና ህዝቦች ፀረ ብልፅግና ትግል ለማድረግ ለጀግናው የአማራ ፋኖ ጥያቄ እያቀረቡ ሲሆን የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን ) ጥያቄያቸውን ተቀብሎ አብሮ ለመስራት ተዘጋጅቷል ። አዲሱ ትውልድ በኢትዮጵያ ሰማይ ስር ፀረ አማራ የሆኑ የትርክት ፣ የሐይል ፣ የፖለቲካ አቋሞችን በመቀየር ሁሉም ሐይሎች ፣ ሁሉም የፖለቲካ ትግሎች ፣ ሁሉም ትርክቶች ፀረ ብልፅግና እንዲሆኑ አድርጓል ። ገና የደረሰብንን ውድመት በበቂ ሳናስረዳ ፣ ገና ያለንን ሰፊ መልካአምድር ሳንጠቀም ፣ ገና ያለንን የተፈጥሮ ሐብት ለትግሉ ማዋል ሳንጀምር ፣ ገና ሚሊዮን ወጣቶችን ዘመናዊ የጦር መሳሪያ ሳናስታጥቃቸው ፣ ገና ዕውቀታችንን እና ጥበባችንን ፍልስፍናችንን ከተፈጥሯዊ ጀግንነታችን ጋር ሳናጣምራቸው ጠላቶቻችን የቆሙባቸውን የህልውና ምሰሶዎች አፍርሰን ፣ የገነቡትን ሁለንተናዊ ፀረ - አማራነት ደርምሰን ለድል እየበቃን ነው ። ማሳሰቢያ :- ትግሉ አብይን ከመጣል ባሻገር ረጅም የትውልድ ቅብብሎሽ በአዳዲስ ተለዋጭ ስልቶች እየተመራ እስከ ዓለም ፍፃሜ ይቀጥላል ።