uz
Feedback

Firibgarlarga uchmang! Telemetrio bunday kanallarni topadi va belgilaydi 👉 Belgini ko‘rmoqchi bo‘lsangiz, obuna bo‘ling 👈

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

Kanalga Telegram’da o‘tish

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

Ko'proq ko'rsatish
4 129
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
+4197 kun
+1 13230 kun
Postlar arxiv
‹‹የአማራ ብሔርተኝነት ዝግመተ-ለውጥ እና የሦስቱ ትውልድ ቅብብሎሽ›› የአማራ ብሔርተኝነት ዝግመተ-ለውጥ በታሪክ ሂደቱ ውስጥ በግልፅ እንደሚያሳየው ከመከላከል (Defensive) ወደ መጠየቅ (Assertive) አሁን ደግሞ ወደ ሕልውና ትግል (Existential struggle) የተሸጋገረ ስልታዊ የፖለቲካ ጥያቄዎችን አንግቦ በመያዝ ያደገ ትግል እንጂ በበልግ ዝናብ የበቀለ ቡቃያ አይደለም። የአማራን የብሄርተኝነት አሻራ የመዐሕድ ትውልድ በአማራ ብሔርተኝነት ታሪክ ውስጥ "የመጀመሪያው ትውልድ" ወይም የንቃተ-ህሊና መክፈቻ ደውል የደወለ ትውልድ እንደመሆኑ እየተቃጣበት ካለው ማንነት ተኮር አደጋ ራሱን እንዲከላከል በማድረግ ፈር ቀዳጅ ሚናውን እንደተወጣ ከታሪክ መረዳት እንችላለን፡፡ በወቅቱ መዐሕድ ሲመሰረት ዓላማው አማራን ተደቅኖበት ከነበረው ስልታዊ ጥቃት "ለመከላከል" በማሰብ እንደነበር ይታወቃል ፤ ይሰነዘሩ የጥቃቶችን ለመከላከል የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ በጊዜው የትግል አማራጭ ተደርጎ በተወሰደው የትግል ምርጫ መሰረት በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በተለይ በበደኖ እና በአርባጉጉ በአማራው ላይ የሚፈጸመውን ማንነት ተኮር ግድያዎችን ለዓለም በማሳወቅ የመከላከል ድምፅ ለመሆን ከመብቃቱም በላይ ከዚህም ጎን ለጎን በወቅቱ አማራው "ጨቋኝ ነው" ተብሎ እየተዘራ የነበረውን ፖለቲካዊ ትርክት ተወቃሽነት በወቅቱ ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ ይህንን የተሳሳተ የታሪክ ስም የማጥፋት ዘመቻ በመከላከል የሕዝቡን የሞራል ልዕልና ለመጠበቅ የሄዱበት ርቀት እንደነበርም ከታሪካቸው መረዳት እንችላለን። ምንም እንኳን ፕሮፌሰሩ የመሩት ያ ትውልድ በአመራ ብሔርተኝነት ምዕራፍ ውስጥ የብሄርተኝነቱን ችቦ በመለኮስ የመጀመሪያው ትውልድ ቢሆንም ብሔርተኝነቱ ግን ግልፅ መስመር ያለነበረው በመሆኑ መዐሕድ "የመላው አማራ" የሚልውን ስም ቢይዝም በውስጡ በነበሩ ጠንካራ ኢትዮጵያኒስት ስሜት ጋር ተጋምዶ በሁለት ማነቆ የተጠረነፈ ስብስብ ነበር። ምን አልባትም ይህ የሆነው አማራው ራሱን ችሎ በብሔር የሚያደራጅ ከሆነ "ኢትዮጵያን ትፈርሳለች" በሚል የወቅቱ ሊህቃን የተሳሳተ እሳቤ ፣ ስጋት ወይም ጥርጣሬ ይመስላል ያ ትውልዱ ራሱን ለመከላከል ሲል ብቻ እንዲደራጅ እና እየተቃጣበት ያለውን ማንነት ተኮር ጥቃት እንዲመክት ሲያስተምሩ ሲያነቁ የነበረው። የሆነው ሆኖ ያንጊዜ የታለመው የመዐሕድ ‹‹የመከላከል መንፈስ›› ነው አሁን ባለው የአማራ ፋኖ ንቅናቄ ውስጥ ሞራላዊ መሠረት በመጣል ለህልውናው ትግል እንደ መነሻ ምክንያት በመሆን እያገለገለ የሚገኘው፡፡ ከመዐሕድ ታሪክ ውስጥ የምንማረው ትልቁ ቁምነገር ቢኖር የፖለቲካ ንቃት ያለ ኃይል ዋስትና ሊኖረው እንደማይችል እና እነዚህ ሁለት የብሄርተኝነት መስራች ስሮች (The Founding Roots of Nationalism) ብሄርተኝነት እስክሰርፅ ድረስ የማይነጣጠሉ ይልቁንም ተመጋጋቢ እንደሆኑ ነው። መዐሕድ በወቅቱ የነበረውን አደጋ ቀድሞ ከመረዳትም በላይ ፖለቲካዊ ሂደቱን እና ትኩሳቱን ጠንቅቆ በመገንዘቡ ነበር ወቅቱን የዋጀ ጭንቅላት ሊኖረው የቻለው ነገር ግን ለጭንቅላቱ የሚሰነዘረውን ወይም የሚቃጣውን ዱላ ሁሉ ሊመክትበት የሚችል ክንድ ወይም ኃይል አልነበረውም ፤ ነበረው ቢባል እንኳን በቂ ኃይል አልነበረም፡፡ አርበኛ ደራሲ እና ጋዜጠኛ አሰግድ መኮንን አዳኝ እና ገዳይ በሚለው መፅሐፉ በሸዋ ቀጠና ይንቀሳቀስ እና በአስማረ ዳኜ ይመራ የነበረው ኃይል የመዐሕድን ተልዕኮ ለማስፈፀም በሸዋ ይንቀሳቀስ እንደነበረ በግልፅ ያስቀመጠ ቢሆንም በወቅቱ ከነበረው አጠቃላይ የኃይል አሰላለፍ አንፃር ግን እዚህ ግባ የሚባል ኃይል እንዳልነበረ የሚታወቅ ነበር፡፡ በጥቅሉ የመዐሕድ መንፈስ አሁን ካለው የአማራ ፋኖ ንቅናቄ አንፃር ካየነው ከሦስት ዋና ዋና አንግሎች አንጻር ማየት እንችላለን፡- ሀ. የመጨረሻ የአማራጭ ስነ-ልቦና መዐሕድ በወቅቱ አማራ በማንነቱ ብቻ ተመርጦ እየተገደልን ነው ፤ ማንነትን መሰረት ያደረገ መገደል እና መፈናቀል ይቁም በሚል ነበር የትግል ጥያቄውን ሲያነሳ የነበረው አሁን ላይ ያለውም የአማራ ፋኖ ንቅናቄ ወደ ትጥቅ ትግል ከመግባቱ በፊት የነበረው መንፈስም የአማራ ህዝብ ህልውና አደጋ ተጋርጦበታል በሚል ተጨባጭ እና ተመሳሳይ ይዘት ያለው ሃሳብ በማንገብ ነበር ትግሉን የጀመረው። አሁንም ግልፅ እና ተጨባጭነት ባለው መልኩ በመዋቅር ደረጃ እየተደገፈ እና እየተፈፀመ ያለው አማራን በማንነቱ ብቻ የማጥፋት ሁሉን አቀፍ ጥቃት መከላከል ተፈጥሯዊ መብት በመሆኑ የተቃጣበትን ማንነት ተኮር ጥቃት ለመከላከል ተገደን የገባንበት ትግል በመሆኑ የመዐሕድ መከላከል መንፈስ ቀጥታ የታሪክ ተዛምዶ ውጤቱ የመኖር ወይም ያለመኖር ውርሱ ከመዐሕድ የተወረሰ የመንፈስ ልጁ ሆኖ እናገኘዋለን። ሁ. የታሪክ ሰነዶች እንደ ትግል መነሻ መዐሕድ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ ህልውናውን እስኪነጠቅ ድረስ የመዘገባቸው ማንነት ተኮር ግድያዎች፣ መፈናቀሎች እና የወሰን እና የማንነት ጥያቄዎች አሁን ላለው የአማራ ፋኖ ንቅናቄ የፍትሐዊነት ጥያቄ መነሻ ነጥቦች ሆነው እያገለገሉ እንደሆነ የሚታወቅ ሲሆን ይህ ማንነት ተኮር ጥቃት ታሪካዊ በደል ላይ የቆመ በመሆኑ ፍትሐዊ መሰረት አለው ብሎ ሲል ዝም በሎ ከመሬት በመነሳት ሳይሆን መረጃዎችን እና ማሳያዎችን ከመዐሕድ የትግል ሰነዶች በመውሰድ ማረጋገጫ ስላለው ነው። ለዚህ ጥሩ ማሳያ የሚሆነው "ፕሮፌሰር አስራት የአማራ ጥላቱ ሆዳሙ አማራ ነው በለው ያሉት ቃል" በፋኖ ንቅናቄ ውስጥ እንደ ትልቅ የሞራል ጉልበት የሚወሰድ ታሪካዊ ንግግር ነው። ሂ. ከከተማ ወደ ገጠር የዞረ የትግል ስልት መዐሕድ ጥቃትን ለመከላከል የሞከረው በከተማ ሰላማዊ ሰልፍ እና በጋዜጣ እንደነበር የሚታወቅ ሲሆን አሁን ላይ ያለው የአማራ ፋኖ ንቅናቄ ግን ያንኑ የመከላከል መንፈስ ወደ ገጠር እና ወደ ትጥቅ በመውሰድ ትግሉን ከፍ ወዳለ ደረጀ መቀየር እና ማሳደግ የቻለበት ሁኔታ ነው ያለው። ከዚህ ላይ ልብ ልንለው የሚገባ ጉዳይ ቢኖር የመዐሕድ ራስን የመከላከል መንፈስ በፖለቲካዊ ንግግር ብቻ ውጤት ስላላመጣ ፤ አሁን ያለው ትውልድ ያንኑ ራስን የመከላከል መንፈስ በክንዱ ወይም በኃይል አማራጭ ለማስቀጠል ቁርጠኝነቱን አሳይቷል፡፡ ለዚህም ነው ፕሮፌሰር አስራት የጀመሩትን ውጥን ሃሳብ የአማራ ፋኖ ይጨርሰዋል" ተብሎ በተደጋጋሚ ሲነገር የሚሰማው። ከላይ ለማሳየት እንደሞከርኩት በፕሮፌሰሩ ይመራ የነበረው የመዐሕድ ትውልድ በፖለቲካው ሜዳ ዓለምን ለማሳመን ሞክሮ በኃይል እንዴት ሊሸነፍ ቻለ የሚለውን ሲሆን በዚህ ጉዳይ ላይ የፋኖ ኃይል ለራሱ የመዐሕድን ጉድለት እና ጥንካሬ ለራሱ በመጠየቅ ራሱን ሊፈትሽበት እንደሚገባ ነው ፤ አሁን ላይ ያለው የአማራ ፋኖ ከመዐሕድ የተሻለ ክንድ ወይም የኃይል አማራጭ እንዳለው የሚታይ ሀቅ ቢሆንም ከመዐሕድ ሊወስደው የሚገባው ትልቁ ቁምነገር የሚዲያ ተፅዕኖ ፣ የዲፕሎማሲ ሚና ወይም በአጭሩ አገላለጥ ብስለት የተሞላበት የፖለቲካ አካሄድን የኃይል ሚዛን እየጠበቀበት ካለው ኃይል እንዴት ላጣጥመው የሚለውን ጥያቄ መሆን አለበት ። በአጭር አማሪኛ መዐሕድ በፖለቲካ ዓለምን ለማሳመን ሞክሮ በኃይል ተሸነፏል ፤ ፋኖ ክንዱ በሰነዘረው ብትር ጥላትን በማሸነፍ ዓለምን ለማሳመን እየታገለ ያለ ትኩስ ኃይል በመሆኑ ሁለቱ ሲደመሩ (ኃይል + ስልታዊ ፖለቲካ) አማራው የሚፈልገውን የህልውና ዋስትና በማረጋገጥ ትግሉን በአጭር ጊዜ እንዲያጠናቅቅ የሚያስችለው ይሆናል።

በእስር ላይ የሚገኙት መምህርት መስከረም አበራ ዓይናቸው በጽኑ መታመሙን ጠበቃቸው ገለጹ ከሁለት ዓመት በላይ በእስር ላይ የሚገኙት መምህርት መስከረም አበራ “ ዓይናቸው በጽኑ መታመሙን ” ጠበቃቸው ሰለሞን ገዛኸኝ ተናግሯል። በእነ ዶክተር ወንደሰን አሰፋ መዝገብ ተከሳሾች መካከል አንደኛዋ የሆኑት መስከረም ከዚህ ቀደም ምንም ዓይነት ህመም ገጥሟቸው የማያውቅ መሆኑን ጠበቃቸው ያስታውሳሉ። ነገር ግን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ዓይናቸው እጅጉን መታመሙን ጠቅሰዋል። ይሁንና “ ካለፈው አንድ ወር ጀምሮ ዓይኗ ይቀላል፤ በጣም ስጋው ይታያል፤ ያማት ነበር፤ እንድትታከም ፍርድ ቤቱን ጠይቄ፣ ሄዳ ተመርምራ ነበር ” በማለት የጤና ክትትሉን አስታውሰዋል። በኋላም ሁለተኛ ምርመራ ማድረጋቸውን ያወሳሉ። ጠበቃ ሰለሞን ከትናንት በስቲያ ሐሙስ ‛ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ’ በመሄድ መምህርቷን በአካል ያገኟቸዋል። ከዚህ ቀደም አንድ ዓይናቸውን ብቻ ቢሆንም ሲያገኟት ግን ሁለቱም መታመማቸውን ይመለከታሉ። “ሁለቱም ዓይኖቿ ታምመዋል፤ ከፍተኛ ስቃይ ውስጥ ነው ያለችው ” ያሉት ሰለሞን ከዚያም ትናንት ዓርብ በአስቸኳይ ፍርድ ቤት ይሄዳሉ። “ የፍርድ ቤቱ የመሃል ዳኛም ያለምንም ማወላወል፣ በፍጥነት ትታከም የሚል ትዕዛዝ ሰጥተው ነበር፤ ነገር ግን የትዕዛዙ ወረቀት ሳይወጣ ቀርቷል ” ብለዋል። እናም ዛሬ ቅዳሜ፣ ነገም እሁድ፣ ሰኞም በዓል በመሆኑ መምህርት መስከረም አስቸኳይ ህክምና የማግኘታቸው ነገር አጣብቂኝ ውስጥ መግባቱን አመልክተዋል። መምህርቷ ግን በጽኑ መታመማቸውን አጽዕኖት ሰጥተዋል። ©አዲስ ማለዳ

''ጠዋት ታይተው ማታ የጠፉ ህልፈታቸው ተመሳሳይ የሆነ ተወዳጅ አርቲስቶች ..............'' ጠዋት ለስራ ወተው ታመሙ ሆስፒታል ሲደርሱ አረፉ ከሚል ዜና ውጭ የሞታቸው ምክንያት በዝርዝር ያል
''ጠዋት ታይተው ማታ የጠፉ ህልፈታቸው ተመሳሳይ የሆነ ተወዳጅ አርቲስቶች ..............'' ጠዋት ለስራ ወተው ታመሙ ሆስፒታል ሲደርሱ አረፉ ከሚል ዜና ውጭ የሞታቸው ምክንያት በዝርዝር ያልታወቀ እና ለህዝብ ይፋ ያልተደረገው ምርጥ ኢትዮጵያዊ አርቲስቶች ከብዙዎቹ በጥቂቱ......... ይህ ተመሳሳይ የአርቲስቶቹ ህልፈት እንደት ያዩታል በቅንነት ሀሳብዎን ያካፍሉን?

🔥የአማራ ተወላጅ የሆኑ 17 የደምቢዶሎ ዩኒቪርስቲ ተማሪዎችን የበላው ጅብ መጮህ የጀመረ ይመስላል‼️ ታግተው ደብዛቸው ጠፍቶ በቀረው 17 የአማራ ተወላጅ የደምቢዶሎ ዩኒቪርስቲ ተማሪዎች እገታ ዙሪያ መረጃ እንዳለውና በተማሪዎቹ ጠፍቶ መቅረትም ሲሳለቅና ሲዘባበት የነበረው የቀድሞው የደምቢዶሎ ዩኒቪርስቲ ፕረዝዳንት፡ የአሁኑ የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ ዶ/ር ለታ ተስፋዬ ጁሌ ባረፈበት ሆቴል ሕይወቱ አልፎ መገኘቱን ጣቢያችን ለማረጋገጥ ችሏል። በማንነታቸው ምክኒያ ከሚማሩበት ደምቢዶሎ ዩኒቨርስቲ ህዳር 25/2012 ዓ/ም የታገቱት 17 ተማሪዎች ደብዛቸው ጠፍቶ ከቀረ ስድስት ዓመታትን አስቆጥረዋል። ከቤተሰብና ከዘመድ አዝማድ፡ ከወገን ጋር ተላቅሶ መቅበር <ዳስ ጥሎ ኩሎ የመዳር> ያህል የሚቆጥሩት የታጋች ቤተሰቦች እርማቸውን ማውጣት ከብዷቸው ዛሬም በሀዘን ተውጠው ተቀምጠዋል። በወቅቱ የወጡ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት፡ ታግተው ደብዛቸው ስለጠፋው ተማሪዎች ለሚዲያ መረጃ ሰተዋል ተብለው የተጠረጠሩ በዛው በዩኒቨርስቲው ውስጥ ይማሩ የነበሩ ሌሎች የአማራ ተወላጅ ተማሪዎች በዩኒቨርቲው ፀጥታ አካላት ተይዘው ከባድ ድብደባ ከተፈፀመባቸው በኋላ ህይወታቸው አልፏል።አንዳንዶቹም በዩኒቨርቲው ፀጥታ አካላት ታፍነው ተወስደው ደብዛቸው ጠፍቶ ቀርቷል። ገሚሶቹ የአማራ ተወላጅ ተማሪዎችም፡ ያለማንም ከልካይ በዩኒቨርስቲው ውስጥ በሚንቀሳቀሱ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ተገድለዋል።አንዳንዶቹም  በተዓምር ሕይወታቸው ተርፎ ትምህርታቸውን አቋርጠው ተመልሰዋል። የአማራ ተወላጅ ተማሪዎቹ በማንነታቸው ምክኒያት ይህ ሁሉ የመከራ መዓት ሲወርድባቸው በወቅቱ የዩኒቨርስቲው ፕረዝዳንት የነበረው ዶ/ር ለታ ተስፋዩ፡ ከኦነግ ኃይሎች ጋር ተባብሮ የድርጊቱ ዋና አቀናባሪና አስፈፃሚ እንደነበረ ሲነገርበት የቆየ ሲሆን፡ ከተማሪዎቹ እገታ በኋላ መረጃ የማጥፋትና የመደበቅ ስራ ላይ ተጠምዶ እንደነበር ጣቢያችን ባደረገው ማጣራት ለማረጋገጥ ችሏል። ሌላው ቢቀር የልጆቻቸውን አስከሬን ከዘመድ አዝማድ ጋር ተላቅሶ ቀብሮ እርም ማውጣት ያልቻሉት የታጋች ተማሪ ቤተሰቦች እንባ ከፈጣሪ ዘንድ ደርሶ ጎርፍ ሆኖ የተመለሰ ይመስላል።  እነዛን ለጋ የቤተሰብና የሀገር ተስፋዎችን ቅርጥፍ አድርጎ የበላውም ጅብ መጮህ ጀምሯል። ታግተው ደብዛቸው የጠፋው የ17 ተማሪዎችን ጨምሮ ስለታገቱት ተማሪዎች መረጃ አውጥታችኋል በሚል በዩኒቨርስቲው ውስጥ በአሰቃቂ ሁኔታ በተገደሉ ተማሪዎች ደም እጁ የጨቀየው ዶ/ር ለታ ተስፋዩ በድንገት ሕይወቱ አልፎ ተገኝቷል። የቀድሞው የደምቢዶሎ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት፡ የአሁኑ የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ እንዲሁም የፓርላማ አባሉ ዶ/ር ለታ ተስፋዬ ጁሌ፡ ከቀናት በፊት ለስራ ጉዳይ ከሌሎች የልኡካን ቡድኑ አባላት ጋር ሆኖ ወደ አሜሪካ ዋሺንግተን ዲሲ አቅንቶ ነበር። ለታ ተስፋየ ባረፈበት በቨርጂኒያ ልዩ ቦታው ሂልተን ሆቴል ሕይወቱ አልፎ መገኘቱን መረብ ሚዲያ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና ሌሎች የሀገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት ካወጧቸው የሀዘን መግለጫዎች ተመልክቷል። የዐብይ አህመድ የሴራ ገመድ ፈታይ ከሆኑ አመራሮች መካከል አንዱና ዋናው ለታ ተስፋዬ ጁሌ፡ ከኦነግ ኃይሎች ጋር ተባብሮ ቅርጥፍ አድርጎ የዋጣቸውን የአማራ ተወላጅ ተማሪዎችን ሳይተፋ ድፍት ብሏል። የአማራ ተወላጆችን በጅምላ በመጨፍጨፍ፣ ሐገሪቱ እንድትፈርስ ከታሪካዊ ጠላቶች ጋር በማበር ሴራ ከመጎንጎን ውጭ ከማያውቀውና  የትውልድ አምካኝ ጭራቅ ከሆነው ከብልፅግና ቡድን ወገን የሆኑ ባለስልጣናት፡ እየተምዘገዘገ እየመጣባቸው ከሚገኘው ከፋኖ ፍርድ ቀን ከመድረሳቸው በፊት፡ ፅዋው ካፍ እስከ ገደፉ ሞልቶ እስኪፈስ የበደሉት ሕዝብ እምባ ጎርፍ ሆኖ ጠራርጎ እያጠፋቸው ነው።

ፋኖ ነኝ  ሞትን ሞቸ አልጠብቀውም! ......................................................... አንድ ወታደር መራብን መታረዝን መገፋትን ይችላል! እልፍ መከራንና ችግርን በፅናት ያልፋል! እያንዳንዱ መሬት ላይ ያለው ታጋይ ፋኖ የትግል መርሁ አንድና አንድ ነው:: እሱም የአማራን ህዝብ ህልውና ማረጋገጥ እያንዳንዱ ፋኖ የማይችለው የአማራ ህዝብ አንገት ደፍቶ ማዬት ብቻ ነው የማይችለው የአማራ ህዝብ የመኖርና ያአለመኖር የህልውና አደጋ ውስጥ ገብቶ ማዬትን ነው። አንደበት ቢኖራቸው መናገር ቢችሉ የአማራ ግዙፍ  ተራሮች በውስጣቸው እያመረቀዙ ያኖሩት የእናት ጡት ነካሺ በሆኑት ባንዳወች የተፃፈን ጥቁር ታሪክ ፀሀይ እና ጨረቃ ሰማይ እና ምድሩ ገፉን አፍ አውጥተው እንደ ሰውኛ አምጥተው በገለፁት ነበር። አንደበት ኑሮዋቸው መመስከር ቢችሉ በወልቃይት ጠገደ ሰቲት ሁመራ ወለጋ በደኖ ጉራ ፈርዳ ከሚሴ አጣዬ ቅራቅር  ወዘተ ---በአማራ ህዝብ ላይ የደረሰውን አንረሳም። እነዚህ ለሀገር ክብር የቆሙ ልጆቻቸውን በጉያቸው ሸሽገው ያቆዮ ተራሮች ይናገሩ ነበር።ፋኖ እንደፍም በሚንተገተግ የአማራነት ወኔ በፅናት የአልሸነፍ ባይነት የቆመ ነፍጡን በእጁ ወኔውን በልቡ የያዘ ብቻውን የሚዋጋ መሆኑን የሚዘከርባቸው የአማራ ተራሮች ምስክር ናቸው ። ፋኖ አሁን ላይ ከአደረጃጀትነት አልፎ ወደ አይድወሎጅነት ወደሰወች እሳቤነት መቀየሩን ወስን አመራሮች ባለማወቃቸው በሚድያ መብለጭለጭ ውስጥ ተሸውደው ትግሉ ግለሰቦች የሚወስኑት መስሏቸው ሲሳቱ ይስተዋላል። ፋኖ የጀመረው የትግል መስመር የመርህ የአላማ ልዩነት የሌለው መሆን ለማስተዋል የጠቢብ ዐይንን የሚፈልግ አይደለም። አማራነት አሸንፎ በጎጥ ባለመደራጀት  ጎጠኝነት ነግሶ አማራነት ዕረክሶ ወይም አማራነት ምላሳቸው ላይ እንጅ ልባቸው ውስጥ በሌለው በደም ነጋደ ሌባዎች አናሳ ግለሰቦች ሴራ እነሱ አማራ እውነተኞች ታጋዮች አማራ መሳይ ተብለው ብዙ መስራት ሲቻል በርካታ የእውነት ታጋዮች ስራ ፈት ሁነው እንድቀመጡ ሆነዋል። በጎጠኞች የፖለቲካ ምህዳር ውስጥ ግን የጎጤ ጂብ አንበሳ ነው በሚል አስተሳሰብ አማራነትን መዘኑት። ብቻ በየተራራ ሸንተረሩ በዱር በገደሉ እየቀበርናቸው እዚህ ያደረሱን የንፁህ ታጋይ ጓዶች ደም  ይፈርዳል። ስለ ህዝብ ለክብር ለመሰዋት በቆረጡ የአማራ ህዝብ የቁርጥ ቀን ልጆች ህልውናው የተረጋገጠ አማራነት ይመጣል። ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አማራነት እስከ ምፅአት ሞት! ወይ ፋኖ ሆኖ መኖር ወይ በፅናት መሰዋት። የጊዜ ጉዳይ ነውጂ በማንም የደሀ ልጂ ደም ማንም ስም ሊገዛ አይችልም   አ ። ራ ። ት። ነጥብ። እንደ እርግብ ቀርባችሁ እንደ እባብ ነድፋችሁናል። አስተምራችሁናል ስለ ሁሉም ነገር እናመሰግናለን። አርበኛ ኮማንዶ አሌክስ ገርባው  ከአፋብኃ ሚኒልክ ዕዝ ጥር 8/2018 ዓ.ም

የሞተን ቀስቃሽ ግፍ ተፈፀመብን‼️ ጋሎች: ባንደበት ካሉት የከፋና ዘግናኝ ወንጀል ፈጽመዋል:: ዛሬ በቁሙ ቤቱን ሲያፈርሱ : በቦንብ ፣ በድሮን ሲጨፈጭፉት ከፍተኛ ወንጀሎች: የዘር ፍጅት እና አገር ክደትን ሳያሰልሱ: ባዋጅ እየፈጸሙ ነው:: ጋላ ኢትዮጵያን የወረረ: ከአራዊት የባሰ ፍጡር መሆኑን: መገንዘብ:: የዛሬ 50 አመት የጀመረ የጋላን ጠላትነት: አማራ ለመረዳት የበቃው ገና አሁን ነው:: በምንም አይነት ይህንን ሁሉ ግፍ የፈጸመ ጋላ: ሳይቀጣ አብረን መኖር የማንችል መሆኑን አማራ ሁሉ ሊታጠቀው የሚገባ ሃቅ ነው:: አሁን ምርጫው የእኛ የአማሮች ነው ቤተሰብ ዲቭ ነኝ ከግንባር

በኦህዴድ ብልጽግና አገዛዝ በእስር ላይ የሚገኙ የፖለቲካ እና የሕሊና እስረኞች የጥር 6/2018 የችሎት ውሎ መረጃ በተለያዩ መዝገቦች በሽብር ወንጀል የተከሰሱ የፖለቲካ እና የሕሊና እስረኞች ጥር 6/2018 በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ቀርበው ነበር። (1)~ በእነ ዶ/ር ወንድ ወሰን አሰፋ መዝገብ ፦ እነ ዶ/ር ወንድ ወሰን አሰፋ (23) የፖለቲካ እና የሕሊና እስረኞች በአባሳሙኤል ገላን ከፍተኛ ጥበቃ ማ/ቤት በፕላዝማ ቀርበው ችሎቱን ተከታትለው። ተከሳሾቹ በችሎት ፊት ሲቀርቡ በኦህዴድ ብልጽግና አገዛዝ እና የፍትህ ሂደቱ ላይ የሚሰጡት አስተያየት ቅር ያሰኘው ፍ/ቤቱ ጉዳያቸውን በፕላዝማ በኩል እንዲከታተሉ ማድረጉ ይታወቃል። ፍ/ቤቱ ጥር 6/2018 በነበረው ችሎት የዐቃቤ ሕግ ምስክሮችን ቃል እና የሰነድ ማስረጃ አስተያየት ክርክርን መርምሮ ብይን እንደሚሰጥ የገለፀ ቢሆንም አልደረሰልኝም በማለት ለጥር 27/2018 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። (2)~ በእነ ሰለሞን ፍቃዱ ጣሴ መዝገብ ፦ ተከሳሾች ከቂሊንጦ ማ/ቤት በችሎት የተገኙት   ዐቃቤ ሕግ የተከሳሾች ጠበቆች በሰጡት የሰነድ ማስረጃ አስተያየት ላይ ምላሹን ይዞ እንዲቀርብ ሲል ፍ/ቤቱ በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት ነው። በእለቱ ዐቃቤ ሕግ የሰነድ ማስረጃ አስተያየቱን ከመስጠቱ በፊት ተከሳሾች በኢሰመኮ ሪፖርት የተረጋገጠ ሲሉ ያቀረቡት ከፍተኛ የሆነው የሰብአዊ መብት ጥሰት ስላልደረሰኝ ምላሹን ለማዘጋጀት በቅድሚያ ሰነዱ ሊደርሰኝ ይገባል ሲል ተከራክሯል። በጠበቆች በኩልም በደንበኞቻቸው ላይ የተፈፀመው የሰብአዊ መብት ጥሰትን ያካተተው የኢሰመኮ ሪፖርት በችሎቱ በኩል እንደደረሳቸው አስተውሰዋል። ፍ/ቤቱም ዐቃቤ ሕግ የኢሰመኮ ሪፖርትን ተመልክቶ የሰነድ ማስረጃ አስተያየት ምላሹን ይዞ እንዲቀርብ በማዘዝ ጥር 15/2018 ለብይን ቀጠሮ ይዟል። (3)~ እሱባለው ፦ ተከሳሹ ከማ/ቤት በችሎት የተገኘ ሲሆን ዐቃቤ ሕግም አሉኝ ያላቸውን ምስክሮች አቅርቦ አስመስክሯል። ከሳሽ ዐቃቤ ሕግ ፦ (1)~  ተስፋዬ ጫላ ወርቁ እና (2)~ አበበ ደሴ የተባሉ ምስክሮችን አቅርቦ እንዲመሰክሩ አድርጓል። ተስፋዬ የተባለው ምስክር የሚመሰክረውን በጁ መዳፍ ላይ በመጻፍ እያነበበ መመስከሩ ቢረጋገጥም ዳኞች በማስጠንቀቂያ አልፈውታል። (4)~ ሰይድ ጌታቸው በላይ ፦ ተከሳሽ ሰይድ ጌታቸው በላይ በእለቱ በችሎት የተገኘ ሲሆን ዐቃቤ ሕግም አሉኝ ያላቸውን ሁለት ምስክሮች እንዲሰሙ አድርጓል። ምስክሮችም የደረጃ ምስክሮች ሲሆኑ የ27 (2) ቃሉን ሲሰጥ አብረው እንደነበሩ መስክረዋል። ሰይድ በበኩሉ ፌደራል ፖሊስ በምርመራ ወቅት ከፍተኛ ድብደባ በመፈፀም እያሰቃዩ የሚፈልጉትን አስገድደው እንዲፈርም ስለማድረጋቸው የዐይን እማኞች ስለመኖራቸው አስረድቷል። ዐቃቤ ሕግ ሁለት ምስክሮችን ካሰማ በኋላ የምስክር ሂደቱን እንዳጠነቀቀ መግለፁን ተከትሎ ፍ/ቤቱ ለብይን በማለት ለየካቲት 3/2018 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። (5)~ እንየው ደምስ ፦ በሽብር ወንጀል ክስ የተመሰረተበት እንየው ደምስ ጥር 6/2018 በችሎት የተገኘ ሲሆን በእለቱም ከፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ ሜክሲኮ ወደ ቂሊንጦ ማ/ቤት በመውረድ ጉዳዩን በማ/ቤት ሆኖ እንዲከታተል ሲል ፍ/ቤቱ መወሰኑ ታውቋል። (አውሎግሶን አንድነት ፣ ጥር 7/2018)

የፋኖ ወታደራዊ አባል የሆነው ወጣት ሞላልኝ አብዩ በተቋሙ ወታደራዊ አገልግሎት እና በትግል ልምድ በአካባቢው የታወቀ ጀብደኛ ነው። ይህ ወጣት ከዚህ በፊት በቴዎድሮስ ዕዝ የ105ኛ ኮር 44ኛ ክፍለጦ
+1
የፋኖ ወታደራዊ አባል የሆነው ወጣት ሞላልኝ አብዩ በተቋሙ ወታደራዊ አገልግሎት እና በትግል ልምድ በአካባቢው የታወቀ ጀብደኛ ነው። ይህ ወጣት ከዚህ በፊት በቴዎድሮስ ዕዝ የ105ኛ ኮር 44ኛ ክፍለጦር ውስጥ ለሶስት አመታት ገደማ አገልግሏል። በአገልግሎት ዘመኑ በብሬን እና በስናይፐር ተኳሽነት፣ እንዲሁም በክላሽንኮፍ መሳሪያዎች አማካይነት ብዙ ተግባራዊ ውጤቶችን አስመዝግቧል። በርካታ ቁጥር ያላቸው ራሳቸውን የመከላከያና የአድማብተና መኮንን እያሉ የሚጠሩ አመራሮችን ጨምሮ የጠላት የሠራዊት አባላትን መግደል ችሏል። በተጨማሪም በወቅቱ የጠላት ወረዳ በነበረችው በሰከላ ወረዳ በተደጋጋሚ ጊዜ ሠርጎ በመግባት መረጃ በማሠባሰብና የጠላት ኃይሎችን በማስወገድ ይታወቃል። በወታደራዊ አገልግሎቱ ወቅት በሠርጎ ገብ ጥቃት፣ በእጅ በእጅ ውጊያ እና በስቦ ማስከዳት ወታደራዊ ስልት በአጠቃላይ 19 የነፍስ ወከፍ መሳሪያዎችን መረከቡ ተመዝግቧል። ይህም ወጣቱ በወታደራዊ ልምድ እና በእቅድ ቀማሪነት ዙሪያ ያለውን ክህሎት ያሳያል። በዚህም ስራው የአፋብኃ ወታደራዊ ክንፉና 105ኛ ኮር ለረጅም ጊዜ ስራውን ሲከታተል ቆይቶ ጀብዱውን የሚመሠክር የእውቅና ወረቀት አበርክቶለታል።

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኅይል (አፋብኅ) በየጊዜው እያሳዬ ያለው የፖለቲካና የስነልቦናዊ ግንዛቤ ሥልጠናዎች እንዲሁም የመዋቅርና የአስተዳደር አደረጃጀቶችን የማጠናቀር ሂደት ይበልና ተጠናክሮ ይቀጥል የሚያሰኝ ነው የአፋብኅ አመራሮች በየወቅቱ እያደረጉት  ያለው በሳል አመራር የአማራንና የፋኖን ትግል የሚደግፉ ወገኖችን እያኮራ ሲሆን በጠላት ሰፈር ደግሞ ድንጋጤንና ሽብርን ፈጥሯል መንግሥት ተብየው ብልፅግና በመቶ ሚሊዮን ብር የሚገመት ወጪ እየከፈለ በሶሺያል ሚዲያና በመንግሥት የመገናኛ አውታሮች ፕሮፓጋንዳውን ቢቀጥልም በመሬትና በውጊያው ቦታ ያለው እውነታ ግን ብልፅግናን እንቅልፍ እየነሳው ይገኛል በየቀኑ በመቶዎች የሚቆጠሩ የብልፅግና ወታደሮችና ሚሊሻዎች ለአፋብኅ እጅ እየሰጡ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ በሺዎች የሚቆጠሩ ምርኮኞችና ህይወታቸውን እያጡ ይገኛሉ በተጨማሪ ከአገዛዙ ጋር ሆነው በባንዳነት ብልፅግናን የሚያገለግሉ ባንዳዎችና ሆዳሞች ለምሳሌ የደብረሲናው ከንቲባ አይነት አድርባዮች የማይቀረውን የአማራን ሕዝብ ቅጣት እየተቀበሉ ይገኛሉ ትግሉ ወደመጨረሻው የድል ጉዞ እየሄደ ለመሆኑ ዋና ማመላከቻ ደግሞ በማስመሰል ከአማራ ሕዝብ ጋር እንታገላለን እያሉ የብልፅግናን አላማ በተዘዋዋሪ ለማሳካት በፋኖ መሀል ተሰግስገው የነበሩ ባንዳዎች ተልእኮአቸው አልሳካ ሲል አንድ በአንድ በየቀኑ የአማራን ትግል እንዲያፈርሱ ከላካቸው አባት ፖርቲያቸው ብልፅግና ጉያ ተመልሰው እየገቡ ይታያሉ እነኝህ ግለሰቦች በፋኖ ውስጥ በነበሩበት ወቅት ምንም ተከታይ እንደሌላቸው የሚያሳየው ማስረሻ ሰጤ ብልፅግና ጋ ተመልሶ ሲገባ የተከተለው አብረው የነበሩት የፋኖ ተዋጊዎች ሳይሆኑ ጌታዋን ተከትላ የምታድረው አንዲት ውሻው ብቻ ናት መቅለልና መዋረድ ማለት ይኸ ነው የአፋብኅ አመራሮች በአሁኑ ወቅት ሌት ተቀን በትእግስትና በሰከነ መንገድ አንድ ወጥ ፓለቲካዊ አስተዳደራዊና ወታደራዊ መዋቅር ለመመስረት እያደረጉ ያሉበት ሂደት ደግሞ ለብልፅግናና ተከታዮቹ ድንጋጤን የአማራንና የፋኖን ትግል ለሚደግፉት መላ ኢትዮጵያውያን ደግሞ ደስታን እየፈጠረ ይገኛል ያለ ጥርጥር የአፋብኅና የአማራ ትግል ያቸንፋል

206ኛ ኮር ትምህርትን ለማስጀመር ከመምህራንና ከርዕሰ መምህራን ጋር እያደረገ ያለው ውይይት የአረመኔው ሰራዊት በመምህራን ላይ በሚያደርገው አፈናና እስር ምክንያት ተደናቅፏል። ጥር 8/ 2018 ዓ.ም =================================== የ206ኛ ኮር በድርጅቱ በአፋብኃ መመሪያና ደንብ መሰረት ትምህርትን በተመለከተ ባቀረበው ጥናታዊ ሰነድ ተንተርሶ 206ኛ ኮር የመማር ማስተማሩን ሒደት ለማጀመር ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ውይይት እያደረገ ሰንብቷል። ከሩ በሚንቀሳቀስባቸው ባሉ ሁሉም ወረዳዎች መምህራንን በማወያየትና ሰነዱን ለታሳታፊዎች በማቅረብ ትምህርትን ለማስጀመር የጋራ ኮሚቴ አቋቁሙ ወደ ስራ በሚገባበት ወቅት የአረመኔው ስርዓት መምህራንን በማፈን ደሞዛቸውን በመንጠቅ ከፍተኛ በደል እየፈፀመባቸው ይገኛል። ኮሩ በተቆጣጠረባቸው ቀጠናዎች በአረመኔው ሰራዊት የፈራረሱ ትምህርት ቤቶችን ጨምሮ አገልግሎት የሚሰጡ የጤና ተቋማትን ክፍት በማድረግ መምህራን እንዲጎበኙ ሲሆን የህዝብ አገልግሎት ሰጭ ተቋማትን በልዩ ሁኔታ ጥበቃ በሚያደርገው 206ኛ ኮር ቀጠና ባንኮች፣ ጤና ጣቢያዎችና የንግድ ተቋማት ለህዝብ ክፍት ሁነው አገልግሎት ሲሰጡ መምህራን ተዘዋውረው ተመልክተዋል። የትግላችንን አላማ በማጠልሸት የተጠመደው የብልፅግና ተራ ፕሮፓጋንዳ በገሀድ መጋለጥ ሲጀምር መምህራንን በማሰርና በማሰቃየት ተጀምረው የነበሩ እንቅስቃሴዎችን አደናቅፏል ። ኮሩ ከሚመለከተው አካል ጋር በመወያየት ዘላቂ መፍትሔ ለማምጣት የሚያደርገውን ሙከራ አጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን ተከታታይ የውይይት መድረኮችን በማዘጋጀት ለተለያዩ ባለ ድርሻ አካላት ጥሪ ያደርጋል። አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት

አጋልጥ! የብርጌድ አደረጃጀት የተቀየረው ሰኔ 2017 ዓ.ም ነው። ከሰሞኑ በደብረብርሃን ዙሪያ ከፍተኛ ጡጫ ያስተናገደው አገዛዙ በዲጅታል ሚድያዎቹ አማካኝነት የሀሰት ፕሮፖጋንዳ እየነዛ ይገኛል። በአ
አጋልጥ! የብርጌድ አደረጃጀት የተቀየረው ሰኔ 2017 ዓ.ም ነው። ከሰሞኑ በደብረብርሃን ዙሪያ ከፍተኛ ጡጫ ያስተናገደው አገዛዙ በዲጅታል ሚድያዎቹ አማካኝነት የሀሰት ፕሮፖጋንዳ እየነዛ ይገኛል። በአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ስር የሚገኙ ክ/ጦሮች ሰኔ 2017 ዓ.ም ከአፋብኃ በወረደ የአደረጃጀት መመሪያ መሰረት የብርጌድ አደረጃጀት ቀርቶ ሻለቃ ከዛም ክ/ጦር እንደሆን ተደርጓል። ስለሆነም አንበሳው ብርጌድ የሚባል አደረጃጀት በአሳምነው ዕዝ ስር የለም። ውሸትም ልክ አለው!

ትግሉ ሲጀመር ሠራዊት ገንብቶ የፀና ሃሳብ ይዞ የገባው የመጨረሻውን የድል ዋንጫ ያነሳል። የfacebook አካውንት እና ወ.ዘ.ተ...አጀንዳዎች ይዞ የገባው አይፀናም።   ገና ዙሩ እየከረረ ጨዋታው አማራዊ የጀግንነት  ስነልቦናን፣ መልካም ስብዕናን፣ አዕምሮን ፣ አቅምን እና ተዓማኒነትን የሚጠይቅበት ውስብስብ ደረጃ ላይ  እየደረሰ እየመጣ ስለሆነ  ..... የሚጠበቅ ነው። ...ማንም ይሁን ማን (ነጋዴ ይሁን ደላላ) የአጭበርባሪነት ባህሪ ያለው ግለሰብ ሆነ ቡድን በትግሉ ውስጣዊ ጉዳይ በመግባት ትግሉን በመጥለፍ  የሚፈልጉትን ግላዊ አጀንዳ በማስፈፀም ትግሉን እና መሪዎችን compromise በማድረግ በታትኖ በችርቻሮ  ለጠላት አሳልፎ ለመሸጥ  የተለመደ የሽቀጣ ፍላጎት ያለውም የትም አይደርስም።  የደንባራ እና ፋራ  ብዓዴን አመራሮች ላይ የተለመደች "ሿሿ"  በዚህ ትውልድ ትግል ላይ ቦታ የላትም። የእያንዳንዱን ፍላጎት  በፈርጅ በፈርጁ map ማድረግ ላይ ሰነፍ እንዳልሆንንም መታወቅ አለበት። ©በዛብህ

ሁለት ቃኝ እና መሀንዲስ የአገዛዙ ሰራዊት ፋኖን ተቀላቀሉ። ጥር 08/2018 ዓ.ም 1ኛ.ኤሊያስ ጫሌ.... አዳነ ከ6ኛ ዕዝ 602 ኮር 75ኛ ክፍለ ጦር 5ኛ ሬጅመንት 64ኛ ክ/ጦር ከእነማይ ወረዳ
+3
ሁለት ቃኝ እና መሀንዲስ የአገዛዙ ሰራዊት ፋኖን ተቀላቀሉ።        ጥር 08/2018 ዓ.ም 1ኛ.ኤሊያስ ጫሌ.... አዳነ ከ6ኛ ዕዝ 602 ኮር 75ኛ ክፍለ ጦር 5ኛ ሬጅመንት  64ኛ ክ/ጦር ከእነማይ ወረዳ 2ኛ. መኳንት መላኩ....25ኛ ክ/ጦር 3ኛ ሬጅመንት ከሰዴ ወረዳ 54ኛ ክ/ጦርን  የተቀላቀሉ ሲሆን አገዛዙ በአማራ ላይ እያካሄደ ያለውን አስነዋሪ ተግባር እና ስራ በማስጠላቱ ጥር 08/2018 ዓ.ም  የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ እና 54 ክፍለ ጦርን ተቀላቅሏል። አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሱብ፣ አዲስ ተስፋ!! የቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት

ከድርጅታዊ እርምጃ ያመለጡ ሌቦች እንጅ ፋኖዎቻችን አልጠፉንም!! ዛሬ በጠዋቱ የብልፅግና ሳይበር ሚሊሾች ከወደ ሸበል በረንታ ፋኖ እጅ ሰጠ የሚል ዜና ይዞ ብቅ ብሏል። ዜናው ለብልፅግና ሰይበር ሚሊሾች በደስታ ያስፈነጠዘ እንደሆነ ያስታውቃል። ምክንያቱም በአባኮስትር መንደር ክላሽ አንከርፍፎ እጅ የሚሰጥ ፋኖ ፍለጋ ቢኳትኑም ሳይሳካላቸው ቀርቷል። ለማለዳው የብልፅግና ድራማ ተዋናይ ፎቷቸው የተለጠፉ አራቱ ሰዎች በህግ ማስከበር እርምጃ ከተወሰደባቸው ያለው ብዙነህ እና ጎዶቹ ጋር በመሆን በፋኖ ላይ ጥቃት በመፈፀም እና ለጠላት መረጃ ሆነው በደራና ወሎ በረሃማ ቦታዎች እየተንቀሳቀሱ ህዝብን ሲያሰቃዩ ከነበሩት ሽፍቶች መካከል ናቸው።ወደጠላት ሲሄዱ በኋላ ደጀናችን በተደረገባቸው የተኩስ ልውውጥ ከሞቱት በተጨማሪ ፎቶው ላይ ከሚታዩት አንደኛው ቁስለኛ ነው።ከነዚሁ ሌቦች ጋር ግንኙነት በመፍጠር ሰው በማገት፣ እና ዘረፋ ላይ የነበሩትንም 64ኛ ክ/ጦር በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያደረገ ይገኛል። ይህን እውነት ሙሉ የሸበል በረንታ ህዝብ የሚያውቀው ሃቅ ቢሆንም አይናችሁን ጨፍኑና ላሞኛችሁ የሚለን የሸበል በረንታው ብልፅግና ፋኖ እጅ ሰጠኝ ለማለት የፋኖ ዩኒፎርም አልብሶ ፎቶ ሲያዘዋውር አርፍዷል። እውነታውን ለሸበል በረንታ ህዝብና ለ64 ክ/ጦር ሰራዊት እንተወውና በብልፅግና ዘገባ የተወዛገባችሁ በአባኮስትር ቀየ ለጠላት ክላሽ አንከርፍፎ በሰልፍ እጅ የሚሰጥ ፋኖ እንደሌለ እና እንደማይኖርም ማሳወቅ እንወዳለን። መረጃው የ64ኛ ክ/ጦር ሕዝብ ግንኙነት ነው።