uz
Feedback

Firibgarlarga uchmang! Telemetrio bunday kanallarni topadi va belgilaydi 👉 Belgini ko‘rmoqchi bo‘lsangiz, obuna bo‘ling

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

Kanalga Telegram’da o‘tish

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

Ko'proq ko'rsatish
4 443
Obunachilar
+824 soatlar
+657 kun
+91030 kun
Postlar arxiv
እናታለም ጎንደር ወደ ነበረባት የጀግንነት ክብሯ አየተመለሰች ነው የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ሲንተራል ኮማንዶ አባል የአፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ ሀብቴ ወልዴ እንወድሃለን አጋርነታችሁ አሳ
እናታለም ጎንደር ወደ ነበረባት የጀግንነት ክብሯ አየተመለሰች ነው የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ሲንተራል ኮማንዶ አባል የአፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ ሀብቴ ወልዴ እንወድሃለን አጋርነታችሁ አሳዩን አላችሁ የበላይ ልጆች።

የአደረጃጀት ዜና!      በመንግስትነት ስም ሃገረ መንግስቱን በመቆጣጠር ሃገር እናስተዳድራለን በማለት በትረ ስልጣኑን ተረክበው መንግስት ነን ብለው ሃገሪቷን የመሯት ሁሉም የሃገራችን መንግስታት ለአማራ ህዝብ የፈየዱለት አንዳችም ነገር የለም። ይልቁንም የህዝባችንን የፍትህና የህልውና ጥያቄዎችን በመደበቅ እልባት ከመስጠት ይልቅ የሚጠይቁ ባለ ምጡቅ አእምሮ አማራዊያንን ወደ ዘብጥያ ማውረድ ከፍ ሲልም ከነ አካቴው እስከ ወዲያኛው እንዲያሸልቡ ማድረግ ነበር። በዚህም የተነሳ የአማራ ህዝብ የህልውናና የፍትህ ጥያቄዎች ለብዙ ዓመታት ተምጠው የፋኖ ትግል ተወለደ። ይህ ትግልም ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ በወታደራዊ ፣ በፖለቲካዊ እንዲሁም በሌሎች አደረጃጀቶች እያደገ መምጣት ጀምሯል። በመሆኑም ትግላችን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለና በትግሉ ላይ በመሪነት ደረጃ የተቀመጡ አመራሮች ስለ አንድነት ያላቸውን ጽኑ ፍላጎትና ቁርጠኝነት ከፍ እያለ በተግባር በመምጣቱ ከአማራ ፋኖ ህዝባዊ ድርጅት /አፋህድ / ጎንደር ጠቅላይ ግዛት እዝ ጣይቱ ክ/ጦር ምክትል አዛዥ የነበረው አርበኛ ጌትነት አለባቸው  ሲመራው የነበረውን ሙሉ ሰራዊት ይዞ ከአፋህድ ቤት በመውጣት የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ እዝ  በይፋ መግለጫ በመስጠት መቀላቀሉን ካበሰርን ከሳምንት በላይ ሆኖናል። በመሆኑም 3 ብርጌዶችን በመያዝ ማለትም  ኮስትር ብርጌድ : ኮማንደር አረጋ አለባቸው ተወርዋሪ ብርጌድ እና ሜ/ጀኔራል ውባንተ አባተ ብርጌድን በመያዝ  አፄ እያሱ ክ/ጦር የሚል ስያሜ የተሰጠው ክ/ጦርን በማቋቋም በተቋማችን ሙሉ እውቅና አግኝቶ ተመስርቷል።   አፄ እያሱ ክ/ጦርም አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ እዝ ዳግማዊ ቴዎድሮስ 5ኛ ኮር 8ኛ ክ/ጦር ሆኖ በመካተት የሚቀጥል ይሆናል። ስለዚህ ይህን ክ/ጦር የኮሩ ም/ሰብሳቢ ፣ የኮሩ ም/ወታደራዊ ዘ /ኃላፊ ፣ የኮሩ ም/ ዘመቻ ዘ/ኃላፊ እንዲሁም የክ/ጦሩ አመራሮችና አባላት በተገኙበት የአመራር ድልድሉ / ሽግሽግ / እንደሚከተለው ተሰርቷል። 1)ሰብሳቢ .........  አርበኛጌትነት አለባቸው 2) ም/ሰብሳቢ ..... አርበኛጌታቸው መኩሪያው 3) ወ/አዛዠ ........... አርበኛግዛቸው መንጋው 4) ም/ወ/አዛዠ .......  አርበኛ ክንድዬ አሰፋ 5) ዘመቻ .............  አርበኛ ክንድዬ አረጋ 6) ም/ዘመቻ ......... አርበኛ ማርዬ አለባቸው 7) ህ/ግንኙነት ......... አርበኛ ፋሲል ውብሸት 8) ፖለቲካ መምሪያ ሀላፊ ...... አርበኛ አላዛር ዳ/ቴዎድሮስ 9) ህግና ስነ ምግባር .... አርበኛ ሰጤ ውበት 10) አደረጃጀት ዘርፍ .... አርበኛ ዜናው እሸቴ 11) ሎጀስቲክ .......... አርበኛ አታለል ተሰማ 12) ፋይናንስ ........... አርበኛ አለሙ ፍቅሬ 12.1. ኦዲተር .......... አርበኛ ገደፍ በላይነህ 12.2. ፅሀፊ .............አርበኛ ውበት ጥላሁን 12.3.) ግዠ ...........  አርበኛ አደባባይ ሙላት 14) ሰው ሀይል ........ አርበኛ ፀዳሉ ታድሎ 16)መረጃና ደህንነት**    በስተመጨረሻም በአመራርነት የተመረጡ የክ/አመራሮችን ቃለ መሃላ በማስፈፀምና የኮር አመራሮች ለሁሉም የክ/ጦር አመራሮችና አባላት መልእክት በማስተላለፍ የእለቱን ኘሮግራም ተጠናቋል። ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!! አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ እዝ ዳግ/ቴዎ/5ኛ ኮር ህ/ግን/ኃላፊ አብነት ሞላ                       መስከረም 22 / 2018 ዓ.ም ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን። ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️ https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk ‎

🔥በሚንስተር ደረጃ  በሚመራ የ facebook ሰራዊት ስነ-ልቦናው የሚጎዳ መሪም ወደ 4 የሚከፈል ትግልም የለንም‼️ ይህቺ ምድር ፦ ዓምላኳን እየሱስ ክርስቶስን የሠቀለች  ፣ ሶቅራጠስን መርዝ ግታ የገደለች  ፣ እነ ጆርዳኖ ብሩኖን በጧፍ ጠቅልላ አቃጥላ የገደለች ፣ እነ አርበኛ በላይ ዘለቀን በቀጭን ገመድ አንቃ የገደለች ምድር ናት ።  በመሆኗም ምክንያት ለሰው ልጆች የመከራ ምዕራፍ ሁሉ ሊታደጉት የመጡትን ደጎች አወክባ ፣ አቃጥላ፣ አሳዳ ያጠፋችበትን ታሪክ ደግመን ደጋግመን ብንገነዘብም  ይሔ የዚች ምድር መጥፎ ታሪካዊ ዳራዋ ነው ብለን በመሪያችን አርበኛ ዘመነ ካሴ  ላይ  ተንኳል እና ሴራ፤ ክፋት እና ምቀኝነት አየተመለከትነ በዝምታ ለማለፍ የሚያስችል የአዲሱ ትውልድ ድንቅ አስተሳሰብ አይፈቅድም ። አዲሱ ትውልድ የአጥናፉ አባተን እሳቤ ስለተማረበት  ጥዋት የመታው እንቅፋት ከሰዓት እንዲደግመው አይፈቅድም ። ምክንያቱ ደግሞ በእርሱ ላይ የሚደርሰው ሁሉ የአማራን ትግል ለማዳከም ወይም ለመጥለፍ ምንጩ ከዘዋሪ መሪ የዘለዓለም የአማራ ጠላቶች መሆኑን ቀድመን ስለምንረዳውም ጭምር ስለሆነ  ። በዚህ ምድር ላይ ታላቅ ዓላማ ፣ ፅናት እና ሞኞት ካለህ ፈተናዎችህ ብዙ ናቸው  ። ዓላማህ በገዘፈ ቁጥር እና ይሔን ዓላማሕን ለማስፈፀም በወሰንክ ቁጥር የገዘፈ ፈተና ይገጥምሐል ። ይሔ የምድር ባህሪ ነው ። ይሔን በውል መረዳት ትልቅ ጥንካሬ ይፈጥርልሐል ። ለሞት የደረሰ አደጋም ይሁን ቀላል የውጭ እና የውስጥ ሰውሰራሽ የሴራ  እንቅፋት  ሲገጥም ከፈተናነት ያለፈ ታሪክ እንዲሆን አድርገህ አልፈህው እና ጥለህው ትሔዳለህ ። "ሰው ከስሜት ክር የተሰፋ ሸማ " እንዲሉ አርበኛ ዘመነ ካሴ ቀስቅሶ ካነቃው እና መሣሪያ እንዲታጠቅ ካደረገበት ትልቅ የብሔርተኝነት ትግል  ይልቅ የተለያዩ ሰዎችን ባህሪይ የተረዳበት ፣ የተሸከመበት እና ችሎ ያለፈበት መንገድ በዚህ ትግል ውስጥ ትልቅ ትርጉም እንዳለው ነው የሚያስረዳው ። ለዚህም ነው አንዱ 'ሰባት' ቀንድ አንዱ ደግሞ 'ሰባ ሰባት' ቀንድ  ሌላኛው ደግሞ ' አንድ ሺ ሰባት'  ቀንድ ያለው ሐሳብ ተሸክሞ  ቢጠጋው ተረድቶ የሚያስተናግድበት መንገድ ሌላ ተጨማሪ መሰጠት እና ለመሪነት መፈጠርን የሚያሳየው ። ይሔ ደግሞ ያልተበረዘ የቤተሰቡ ጥሩ አስተዳደግ እና ጠለቅ ያለ በንባብ የዳበረ የአስኳላ እውቀቱ አጣምሮ ነገሮች የሚረዳበትን እና የሚያስረዳበትን አቅም ያሣያል ብየ አምናለሁ ። ጭዋታውም ፣ ቁጣውም ይሁን ቀልዱም ከዚህ ይቀዳሉ የሚቀዱም ናቸው  ። አርበኛ ዘመነ ካሴ አሁን ለደረሰበት ፖለቲካዊ አረዳድ ምንጩ 'እውነትን' እምቢ ብሎ የሙጥኝ መያዙ ነው ። ለዚህ ልክፍት በለጋ እድሜው የዳረገው ደግሞ እርሱም ሲናገር እንደሰማነው  የደራሲ 'አቤ ጉበኛ ' አጠቃላይ ድርሰቶች  ውስጡን አሸንፈው የአውነት እና የፍትህ ዘበኛ አድርገውት እንደቀሩ እርግጥ ነው ። አቤ ጉባኛነት ደግሞ ብዙ ማሸነፍ የማይችሉ ጠላት ይፈጠርበት ዘንድ የእውነት ተፈጥሮዋ ያስገድዳታል ። ለእኔ አርበኛ ዘመነ ካሴ የቬተናምን 'እውነት 'ለማግኘት የቬተናምን ተራሮች በእግሩ ለረጅም አመታት እንደዞረው የነፃነት ታጋይ 'ሁ ቺ ሚኒን ( Ho chi minh ) ይመሠልብኛል ። እርሱም ሀገራችን ውስጥ  የጠፋችዋን የአማራ 'እውነት 'ለማግኘት የኢትዮጵያን ተራሮችን በፍፁም ቅንነት እና በደስታ የድሮን፣ የጄት ፣የደፈጣ  ጥቃት እንዲሁም ሐሳዊያን የወንድ ወይዘሮዎችን የሐሰት ፕሮፖጋንዳ ሳይበግረው ወደ ዓላማው በፍጥነት እየተራመደ የሚሄድ ጀግና እና ተራማጅ አርበኛችን ነው ። አርበኛ ዘመነ ካሴ በዳግም የጣሊያን ወረራ ወቅት 'አማራ የሌለባት ኢትዮጵያ' አስረክባለሁ ብሎ በቴሌግራም መልዕክት ወደ ሮም  የላከውን ጣሊያናዊ  የማርሻል 'ባዶሊዪ' ን ሐሳብ በዚህ በኛ ዘመን ለማስፈፀም  በአብይ አህመድ ተላላኪነት እና  በምርኮኛው ብርሐኑ ጁላ አስፈፃሚነት  ወጥነው የጀመሩትን ጉዞ ያስቆመ ክስተት የሆነ መሪ ነው ። ለዚህም ነው ደላላ ሊኅቃኖች አማራ የሚባል ብሔር የለም በሚሉበት ወቅት ፥ የትግል ቀበኞች ፖርቲ በገንዘብ በሚሸጡበት ወቅት ፥ ድቡልቡል ማህይሞች አማራ መሆን መጥበብ ነው በሚሉበት ወቅት፦ እጅግ በጣም ደመቅ ብሎ የሚሰማ ድምፅ ከአርበኛ ዘመነ ካሴ አንደበት ወጦ ከአድማስ አድማስ እያስተጋባ ከዚህ ያደረሰን። የአንደበቱ መልዕክትም 'አማራ' ሲሏችሁ አትሸማቀቁ ይል ነበር ። ይህ ንግግር የዕይታ አድማሳችንን ያሰፋልን ፀረ -ግርዶሽ ነው ።   በልባችን ውስጥም የተቀመጠ ክቡር ቃል ሁኖ እያታገለን ይገኛል ። አርበኛ ዘመነ ካሴ በትግሉ ተፈትኖ ሳይናወጥ ፀንቶ ያለፈ መሪ ነው ። ትግሉን በስነ-ልቦና ወደ አሸናፊነት ፤ በሰው ሐይል ከምንም ወደ ሚሊዮኖች ፤ ከጣውላ መሣሪያ እስከ ሸተር  ያሣደገ ከፍ ሲልም ብዙ መሪዎችን የፈጠረ ድንቅ ወንድማዊ መሪያችን ነው ። በዓሁኑ ወቅት አብይ አህመድ ገና ሳያነጥስ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ይማርህ በሚልበት ጊዜ ፤ ተመስገን ጥሩነህ እኩል  ለማነጠስ በሚዘጋጅበት ጊዜ ፤ ታየ አፅቀ ስላሴ በሶፍት የአብይን ግንጭል ለመጥረግ እጁን በሚዘረጋበት ጊዜ እንዲሁም አረጋ ከበደ እና አገኘሁ ተሻገር ለታችኛው አመራር መሪያችን  ሊያነጥሱ ስለሚችሉ ለማነጠስ ተዘጋጁ ብለው ትዕዛዝ የሚያወርዱ ገረዶች በበቀሉበት ወቅት አርበኛ ዘመነ ካሴን የመሠለ ይሄን ሁሉ የባንዳ ሰንሰለት ሰብሮ የወጣ መሪ ማግኘት እና በእርሱ መመራትም እደለኝነትም ጭምር ነው ።      ########################### ምድር ላይ ያጣችሁት ድል በሚንስተር ደረጃ  በሚመራ የ facebook ሰራዊት ስነ ልቦናው የሚጎዳ መሪም ወደ 4 የሚከፈል ትግልም የለንም ። አርበኛ ዘመነ ካሴ ከአሸነፋችሁ ቆይቷል ።     ############################                       አንድ አማራ ! አዲስ ትውልድ ፣ አዲስ አስተሳሰብ ፣ አዲስ ተስፋ ! ©አርበኛ ግሩም ምሳሌ

የሚሊሻ ተቋሙ እየፈረሰ ነው በዛሬው እለት ሁለት የሚሊሻ አባላት ወደ ፋኖ ተቀላቅለዋል ። 1 ጌታቸው ይግዛው 2 ምኒችል ምንብየ ከወንድሞቻችን ጋር መዋጋት አንፈልግም በማለት በዛሬው እለት ሻለቃ አን
+1
የሚሊሻ ተቋሙ እየፈረሰ ነው በዛሬው እለት ሁለት የሚሊሻ አባላት ወደ ፋኖ ተቀላቅለዋል ። 1 ጌታቸው ይግዛው 2 ምኒችል ምንብየ ከወንድሞቻችን ጋር መዋጋት አንፈልግም በማለት በዛሬው እለት ሻለቃ አንሙት ያዛቸው ብርጌድን ተቀላቅለዋል።   ፋኖ ሐብታሙ የሱፍ የአፋብኃ ምዕራብም አማራ ቀጠና ቴድሮስ እዝ 1ኛ ክፍለ ጦር ህ/ግንኙነት መስከረም 22/2018 ዓ.ም

"እንኳን በአራት አቅጣጫ በአርባ አራት አቅጣጫ ይምጡ.... "መሪየ አርበኛ ዘመነ ካሴ አረመኒያዊ  የአረጋ ከበደ አገዛዝ የስነ ፍጥረቱ መነሻ የሆነውን የአማራ ጥላቻ አርበኛ ዘመነ ካሴን በመበቀል የሚወጣለት ይመስል ላለፉት 5 ዓመታት በልዩ ሁኔታ አካላዊና ስነ ልቦናዊ ስብራት ከማድረስ ባሻገር ሐይወቱን ያጠፋለኛል ያለውን ነገር ሁሉ ሲሰነዝር ቆይቷል። ከሮቦቱ አረጋ ከበደ እስከ አብይ እህመድ ድረስ፣ ከወታደራዊ እስከ ፖለቲካዊ አመራር፣ ከይፋዊ እስከ ዝግ ስብሰባ ፣ከመደበኛ እስከ ሻይቡና ፕሮግራም፣አጀንዳቸው ዘመነ ካሴን እንዴት እናጥፋ? ነው!!! ከሀገር ውስጥ ነባር ተቋማትን ሽጦ፣ከውጭ ዶላር ተበድሮ የሚገዛቸው ዘመናዊ የጦር እና የስለላ መሳሪያዎች መስፈርታቸው አርበኛ ዘመነ ካሴን የማጥፋት አቅም ነው። አሁንም ይሳካልኛል ያለውን ወታደራዊ እቅድ አቅዶ በሀገር ውስጥ ከሰለጠኑት "እግረኛ ሰራዊቱ "በተጨማሪ ውጭ ሀገር ድረስ ተልከው በጀት ፈጅተው የመጡ "የጦር መኮንኖችን"ዘመን ያፈራቸው የቅርብ የጦር መሳሪያ እስከ መድፍና ታንክ ድረስ፣የሀገሪቱን ምክትል ኢታማዡር ሹም በመሪ ደረጃ መድቦ የጀግኖቹ ቀየ መራዊ በ5 አቅጣጫ አሰልፎ ይገኛል። ታምር ይሰሩልኛል ብሎ መራዊ ከተማ ላይ ከደረደራቸው ሀይል፣ታንክና መድፍ ባሻገር አርበኛ ዘመነ ካሴ ከበባውን ሰብሮ ወጥቶ እንዳያዋርደኝ በማለት በቢኮሎና ገርጨጭ፤በቅንባባና ብራቃት፣በአፈሳና ፋግታ፣በብር አዳማና ሰከላ በኩል ሁለት ሳምንት ማሰልጠኛ አስገብቶ ያስወጣቸው የምስኪን ልጆችን እንቅልፍ ከልክሎ ደርድሯል።ከዚህም ጀርባ ፍኖተ ሰላምና ኮሶበር ላይ ከወለጋ አቅጣጫ እያመጣ ደጋፍ ሰጭ አራዊቱን እንደጉድ  እየከመረው ነው። እኛም ትላንት ገጥመን ካሸነፍንበት የስነ ልቦና ልዕልና ከፍ ብለን እየጠበቅናቸው ነው!!! በእርግጠኝነት  ለመላው ሕዝባችን የምንገባው ቃል ቢኖር ሰበር ዜና ለማንበብ መራዊ እስከ ተቀመጡት ጋዜጠኞቹ ድረስ አንጠልጥለን በጢምባራቸው እንደፋቸዋለን!!! አርበኛ እሸቱ ጌትነት አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠናቴወድሮስ ዕዝ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን። ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️ https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk ‎

"የኢንጅነር ክበር ተመስገን ብርጌድ በአንጀኔ ቀጠና ከአባት ፋኖ አባላት ጋር ውይይት አካሄደ !" መስከረም 22/2018 ዓ.ም "እንመክራለን፣ እንወያያለን፣ እንደራጃለን ጠላትን እንደመስሳለን!" የአ
+1
"የኢንጅነር ክበር ተመስገን ብርጌድ በአንጀኔ ቀጠና ከአባት ፋኖ አባላት ጋር ውይይት አካሄደ !" መስከረም 22/2018 ዓ.ም "እንመክራለን፣ እንወያያለን፣ እንደራጃለን ጠላትን እንደመስሳለን!" የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ የቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ፮ኛ ክ/ጦር የኢንጅነር ክበር ተመስገን ብርጌድ በአንጀኔ ቀጠና  ከሚገኙ አባት ፋኖ አባላት ጋር ውይይት አድርጓል። በውይይቱም የሕልውና ትግሉን የእድገት ደረጀ በተመለከተ የግንዛቤ ፈጠራ ስራ የተሰራ ሲሆን የአባላቱ የእርስ በእርስ ግንኙነታቸው ምን እንደሚመስልና በህዝብ አያያዝ ዙሪያ ተወያይተዋል። ድል ለአማራ ሕዝብ!! አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳስብ፣ አዲስ ተስፋ!!

የሸኔ ጥቃት በደቡብ ወሎ! አንድ የአካባቢው ነዋሪ << በደቡብ ወሎ ዞን ቃሉ ወረዳ 023/ ጀርጀሮ ቀበሌና አካባቢው የሸኔ ታጣቂ ቡድን ተደጋጋሚ ጥቃት እያደረሰብን ይገኛል። ከሳምንት በፊት ከኮቦምልቻ 'ኤላ' ወደምትባል ገበያ በመኪና በመጓዝ ላይ ከነበሩ ሰዎች መካከል በርካቶቹን አግተው ወስደዋል። ይህ ተደጋጋሚ ሁኔታ ማህበረሰቡን በማስቆጣቱ ፣ ከ2ቀን በፊት በቀበሌ በተደረገ ስብሰባ ላይ አመራሮቹ ህዝቡን ለማረጋጋት 'ታገቾቹን አስለቅቀናል' ቢሉም የተለቀቀ ታጋች አለመኖሩን አረጋግጠናል። >> << ይህ በእንዲህ እያለ በትናንትናው እለት ምሽት 3:00 አካባቢ የሸኔ ታጣቂዎች ወደዚሁ ቀበሌ ገብተው ጥቃት በመክፈት አንድ ሷሊህ የተባለ ወጣት ከቤቱ አግተው የወሰዱ ሲሆን በከፈቱት ተኩስ አንድ ሌላ የአካባቢው ነዋሪ አቁስለዋል። ማታ ማታ ከፍተኛ የህዝብ ስጋት ተፈጥሯል። ህዝቡ ራሱን ለመከላከል ቢፈልግም የወረዳና የዞን አመራሮች ፈቃደኝነት የላቸውም ፣ ይከለክሉናል። ። ይህን ቀበሌ ጨምሮ በባቲ ዙሪያ አካባቢዎች በስፋት ይንቀሳቀሳሉ። አመራሮቹን ሁሉ ቀያይረው ለእነሱ የሚመች አመራር ከመደቡ ሰነባብተዋል። በቅርቡ ከወለጋ ወደ300 የሚጠጉ የሸኔ ታጣቂዎች በዚህ አካባቢ መጥተው እንደተቀላቀሉ ይነገራል። ለማን አቤት እንደምንል ቸግሮናል። አንድ ቀን ሙሉ ቀበሌውን ጨፍጭፈውት ያድራሉ በሚል ስጋት እንቅልፍ አጥተናል። እባክህ መረጃውን አጋራልኝ! >> ብሎኛል! እኔም ለሚመለከታቸው አካላት ይደርስ ዘንድ መረጃህን ይሄው አድርሻለሁ! የቃሉ ወረዳ 023/ ጀርጀሮ ቀበሌ ማለት ከኮምቦልቻ ወደባቲ ስንጓዝ ደጋን ፣ ገርባ ፣ የሚባሉ ከተማዎችን እናገኛለን ። በገርባ ወደ ውስጥ ገባ ብሎ የሚገኝ ከተሁለደሬና ከወረባቦ የሚዋሰን ታቹን ለባቲ ዙሪያ ወረዳ ቅርብ የሆነ ቦቲ ነው። ©ዘር ይሁን ገሰሰ ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን። ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️ https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk ‎

ይህችም ትመዝገብልን ውድ አማራዊያን የአማራ ህዝብን የተደቀነበትን የህልውና አደጋ ለመቀልበስ እንዲሁም የአማራ ህዝብ በቁመቱና በወርዱ ልክ የተመጠነና ከመላው ኢትዮጵያን ጋር በሰላም ፣በፍትህና በእኩልነት የሚኖርበትን ስርዓት ለመገንባት የሞቀ ቤታችሁንና ቤተሰባችሁን ትታችሁ ከራስ በላይ ለወገን በማለት #ዱሩ_ቤቴ ያላችሁና በዱር በገደሉ ፣በቆላ በደጋ ዋጋ እየከፈላችሁ የምትገኙ ውድ የቁርጥ ቀን የአዲስ አበባ ብርሃኖች የኢትዮጵያ ተስፋ የአማራ ፍኖዎች። ነገሩ እንዲህ ነው ዘመን የወለደው ቀንደኛ ጠላት የሆነው የብልፅግና የሙት መንፈስ የተሸከመው ስራት አስጠባቂ ወላቃ መንግስት በአማራ ህዝብ ላይ ወረራና ዝርፊያ የእለት ተዕለት ስራ አድርጎ የተንቀሳቀሰው የኦሮሙማው ባንዳ አገር ሻጭ በውዷ ኢትዮጵያ ህዝብ ዘንድ እንድትመዘገብ ሁናለች። ሆኖም የአገዛዙ የብልፅግና ገረድ እንዲሁም በእሱ ተለጥፋችሁ የምትኖሩ በተለይ በአዲስ አበባ አንዳንድ ባለሃብቶች አልሚ ነኝ ባይ አብሯቹህ ከአብይ ወንበር አስጠባቂ ስልጣን ናፋቂዎች ከሆነው ከመንግስት ሠራተኛ በመሻረክ የሰው መሬትንና ንብርት በልማት መልኩ በህገ ወጥ ከገዥው ወራሪ ሀይል ጋር በመሆን በ7 አመት  ያላቻ ጋብቻ የተጋባችሁ ባለሃብቶች የዘረፋችሁትን የአዲስ አበባ አማርኛ ተናጋሪ ማህበርስ ያስለቀሳቹሁ ያፈናቀላቹ መሬቱን የነጠቃቹ ቆሻሻ ስራት ናፋቂዎች ስራቹሁን እያጣራን እንደምንፈርድባቹ አትጠራጠሩን። የትም አታመልጡንም። ብዙ በደል ያደረሱብንን ግፈኞች እየተዋጋችሁ ራሳችሁን የነፃነት መስዋዕት አድርጋችሁ ለእኛ ውድ ሕይወታችሁን የሰጣችሁን እናንተ ሰማዕታት የተሰዋችሁለትን እውነት ከጫፍ እናደርስ ዘንድ በጽኑ እንታገላለን ለዚህም ፍጹም ጽናታችሁ ከእኛ ጋር ይሁን እላለሁ። ዳዊት ከትግል ሚዳ ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን። ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️ https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk ‎

ይህችም ትመዝገብልን ውድ አማራዊያን የአማራ ህዝብን የተደቀነበትን የህልውና አደጋ ለመቀልበስ እንዲሁም የአማራ ህዝብ በቁመቱና በወርዱ ልክ የተመጠነና ከመላው ኢትዮጵያን ጋር በሰላም ፣በፍትህና በእኩልነት የሚኖርበትን ስርዓት ለመገንባት የሞቀ ቤታችሁንና ቤተሰባችሁን ትታችሁ ከራስ በላይ ለወገን በማለት #ዱሩ_ቤቴ ያላችሁና በዱር በገደሉ ፣በቆላ በደጋ ዋጋ እየከፈላችሁ የምትገኙ ውድ የቁርጥ ቀን የአዲስ አበባ ብርሃኖች የኢትዮጵያ ተስፋ የአማራ ፍኖዎች። ነገሩ እንዲህ ነው ዘመን የወለደው ቀንደኛ ጠላት የሆነው የብልፅግና የሙት መንፈስ የተሸከመው ስራት አስጠባቂ ወላቃ መንግስት በአማራ ህዝብ ላይ ወረራና ዝርፊያ የእለት ተዕለት ስራ አድርጎ የተንቀሳቀሰው የኦሮሙማው ባንዳ አገር ሻጭ በውዷ ኢትዮጵያ ህዝብ ዘንድ እንድትመዘገብ ሁናለች። ሆኖም የአገዛዙ የብልፅግና ገረድ እንዲሁም በእሱ ተለጥፋችሁ የምትኖሩ በተለይ በአዲስ አበባ አንዳንድ ባለሃብቶች አልሚ ነኝ ባይ አብሯቹህ ከአብይ ወንበር አስጠባቂ ስልጣን ናፋቂዎች ከሆነው ከመንግስት ሠራተኛ በመሻረክ የሰው መሬትንና ንብርት በልማት መልኩ በህገ ወጥ ከገዥው ወራሪ ሀይል ጋር በመሆን በ7 አመት  ያላቻ ጋብቻ የተጋባችሁ ባለሃብቶች የዘረፋችሁትን የአዲስ አበባ አማርኛ ተናጋሪ ማህበርስ ያስለቀሳቹሁ ያፈናቀላቹ መሬቱን የነጠቃቹ ቆሻሻ ስራት ናፋቂዎች ስራቹሁን እያጣራን እንደምንፈርድባቹ አትጠራጠሩን። የትም አታመልጡንም። ብዙ በደል ያደረሱብንን ግፈኞች እየተዋጋችሁ ራሳችሁን የነፃነት መስዋዕት አድርጋችሁ ለእኛ ውድ ሕይወታችሁን የሰጣችሁን እናንተ ሰማዕታት የተሰዋችሁለትን እውነት ከጫፍ እናደርስ ዘንድ በጽኑ እንታገላለን ለዚህም ፍጹም ጽናታችሁ ከእኛ ጋር ይሁን እላለሁ። ዳዊት ከትግል ሚዳ ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን። ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️ https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk ‎

ዘመቻ አርበኛ አደም አሊ (አባ ናደው) 9ኛ ቀን የአፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ንጉስ ሚካኤል አሊ ኮር እስከ መስከረም 30 ቀን 2018 ዓ.ም የሰጠውን የምህረት አዋጅ ተከትሎ በርካታ ኃይል ከጠላት ተነጥሎ ወደ ፋኖ እየገባ መሆኑ ተረጋገጠ:: ሰሞኑን በዘመቻ አርበኛ አደም አሊ (አባ ናደው) የአፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ንጉስ ሚካኤል አሊ ኮር በርካታ ቀጠናዎችን መቆጣጠሩ ይታወሳል:: በተንታ እና መቅደላ እንዲሁም በከላላ እና ጃማ ብሎም በመካነሰላም ግንባር የኮሩ ሰራዊት ቁልፍ አካባቢዎችን ከጠላት በመንጠቅ ሙሉ በሙሉ በመቆጣጠር የሲቪል አስተዳደር መዋቅር ከመዘርጋቱ ባሻገር የጠላት ኃይል ቀንደኛ አዋጊዎችን ስፍር ቁጥር ከሌለው ሰራዊት ጋር እስከወዲያኛው መሸኘት መቻሉን   የኮሩ ዋና አዛዥ አርበኛ አብነው ታደሰ በትናንትናው እለት መናገሩ ይታወሳል:: አርበኛው የፋሽስቱ ብልፅግና አገዛዝን ዙፋን እየጠበቁ በአማራ ህዝብ ላይ ዘር ማጥፋት እየፈፀሙ ላሉ የመከላከያ አድማ ብተና ሚሊሻና ፖሊስ አባላቶች  ትናንት መስከረም 21 ቀን ባስተላለፈው መልዕክት ከጠላት ተነጥለው ወደ ፋኖ እንድቀላቀሉ እስከ መስከረም 30 የምህረት አዋጅ ማወጁ ይታወሳል:: ይህን ተከትሎ በዛሬው እለት ብቻ አንድ ቲም የሚሆኑ ሚሊሻዎች በመካነሰላም ግንባር ከጠላት የከዱ ሲሆን ቁጥራቸው ያልተገለፀ የ23ተኛ ክፍለ ጦር አድማ ብተና አባላትም ከካምፕ መጥፋታቸው ታውቋል:: መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን! አፍብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ መስከረም 22/2018 ዓ.ም መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን! አፍብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ መስከረም 22/2018 ዓ.ም ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን። ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️ https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk ‎

#የተካደው_ሰራዊት‼️ #የምርኮኞች_ጥሪ‼️ መንግስት ክዶናል ፣ በማሰልጠኛና በዬ ግንባሩ ያለህ ሰራዊት ለከሀዲ መንግስት ራስህን አትገብር እኛ ተክህደናል....የምርኮኞች አሳዛኝ መልዕክትና ጥሪ ለመከላከያ ሰራዊትና ለኢትዮጵያ ህዝብ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://youtu.be/HP3yBUrO-GI?si=Mltr38tQ1DmAcV02

ሃሳብ ስጡበት እመለሳለሁ

ሰበር ዜና ‼️                                                                       👉የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ ጎጃም አገው ምድር 3ኛ ክፍለጦር ዘንገና እና ግዮን ብርጌድ ጠላት ላይ ጥቃት አደረሱ‼️ ጠላት በጣም በርካታ ሀይል ከአዲስ ቅዳም፣ከኮሶ በር፣ ከቲሊሊና ከተለያዬ ቦታ ያሰባሰበውን የአብይ አህመድ ወንበር አስጠባቂ ሀይል፤ ለጠላት ሀይል ቤርሙዳ ከሆነችው አሽፋ መገንጠያ እስከ አውካኒ ተራራ በወንድማማቾቹ ዘንገና ብርጌድና ግዮን ብርጌድ በተሰነዘረበት ጥቃት ጠላት ሙትና ቁስለኛ ሆኗል። ከአሁን በፊት ወንድማማቾቹ ብርጌዶች አሻፋ አውካኒ ላይ ከኮለኔል ያሬድ ኪሮስ እስከ ኮለኔል አባተ፣ ከክላሽ እስከ እስናይፐር ፣ከብሬል እስከ ዲሽቃ በመማረክ የጠላትን ሀይል ውጠው አስቀርተውታል። 👉የአናብስቶችን ምት መቋቋም ያቃተው ጠላት አባ አንዳርጌ የተባለ የ70 አመት ሽማግሌ አሽፋ ላይ ከቤት በማውጣት በአሰቃቂ ሁኔታ እረሽኖታል። ✍️አይበገሬዎቹ የጠላት የራስምታት የሆኑት ወንድማማቾቹ ዘንገና እና ግዮን ብርጌድ ጠላትን በሚገርም የጦርነት ጥበብ ካስተናገዱት በኋላ ወራሪውን ሀይል ወደ አጉት ስቦ በማስገባት በራቸውን ዘግተው እየጠበቁት ይገኛል። ዘሎ የገባው ጠላት መውጫ አጥቶ ላይና ታች እያለ ይገኛል። 👉በሌላ በኩል የግዮን ብርጌድ ተወርዋሪ ኮከቦች አባግስ ሻለቃና ግትም ሻለቃ ሰከላ የመሸገውን የጠላት ሀይል ከገባበት ጉድጓድ ድረስ በመግባት ጠላትን ሲያስጨንቁት ውለዋል። ይበልጣል የዉነቱ ጀግናዉ

ጥብቅ መረጃ! ፋሽስቱ የብልፅግና አገዛዝ ሰሞኑን በአፋብኃ ምኒልክ ዕዝ በዘመቻ አርበኛ አደም አሊ (አባ ናደው) የደረሰበትን ከባድ ሽንፈት ላለመቀበል ፋኖ የተዋጋኝ ብቻውን አይደለም ከትግራይና ከኤርትራ ሃይሎች ጋር ሆኖ ነው እና ሌሎችም ምክንያቶችን ሲደረድር ሰንብቷል:: ፋኖ ከፈጣሪው በታች ትጥቁም ስንቁም ሁሉ ነገሩ በውስጥም በውጭም ያለ የአማራ ህዝብ መሆኑ የአደባባይ ሐቅ ነው:: ፋኖ ከፈጣሪው በታች ራሱን ችሎ የቆመ ነው:: ተኩሱም አሸናፊነቱም ድል አድራጊነቱም የአባት የአያት የቅድመ አያቶቹ በአጠቃላይ ስሪቱ ነው:: ነገር ግን አብይ አህመድ ሽንፈቱን ላለመቀበል "ፋኖ ከትግራይና ከኤርትራ ሃይሎች ጋር ሆኖ ነው የወጋኝ" እያለ በሚዲያ ሚሊሻዎቹ በኩል ሲያለቅስ የሰነበተ መሆኑ ይታወቃል:: የማልቀስ መብቱም የተጠበቀ ነው:: ከዚህ ጋር ተያይዞም ፋኖ የወጋኝ ከትግራይና ከኤርትራ ሃይሎች ጋር ሆኖ ነው የሚለውን ለቅሶውንና ውንጀላውን በሃሰት ፕሮፓጋንዳ ለማጀብ ምንም ፋኖ ባልተማረከበት ሁኔታ ሐራ መሬት እየተባለ ከሚጣራው ቦታ የጌታቸው ረዳ ቡድን አባል የሆኑ የትግራይ ተወላጅ ታጣቂዎችን በማምጣት "ፋኖ ጋር ሆነን ስንዋጋ ወልድያ ዙሪያ በመከላከያ ተማረክን" እንዲሉ በማድረግ ዛሬ መስከረም 22/2018 ዓ.ም ደሴ ከተማ ፋና ቲቪ ቀረፃ እያካሄደ መሆኑን ለማረጋገጥ ችለናል:: ስለሆነም ፋኖ በብልፅግናው ቡድን በሃሰት ፕሮፓጋንዳና ውንጀላ እንዲሁም ሌሎች ምክንያቶች ቢደረደሩ የጀመረውን የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ለድል ከማብቃት የሚያደናቅፈውና የሚያግደው አንዳችም ሁኔታ እንደሌለ ሊታወቅ ይገባል። ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! መስከረም 22/2018 ዓ.ም አርበኛ Abebe Fentaw የአፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ሕ/ግ ኃላፊ

መረጃ❗ ብልፅግና ሐገሪቱ ላይ አለኝ የሚለውን መሳሪያ እና 11,000 ገደማ የኮማንዶ ሐይል ጎጃም መራዊ እና ዱርቤቴ ላይ አሰማርቷል(አርበኛው ይገኝባቸዋል  ብሎ በማሰብ)። ይህ ሓይል ዘመነካሴን ሳትገድ ል ወይም ደግሞ ከነነፍሱ ሳትይዝ ከመጣህ ወዮልህ ተብሎ ትዕዛዝ የተቀበለ የመጨረሻው የአገዛዙ ወታደራዊ ጫፍ ላይ ያለ ኢሊት ፎርስ ነው። በኛ በኩል ለወዳጆቻችን የምናሳውቀው ነገር ቢኖር በፍፁም በኛ ተማመኑ እንኳንስ የአብይ አህመድ ባሮ ሽንኩርት የዘመነን ጫፍ ሊነካ ቀርቶ የመጀመሪያ ደረጃ ጠባቂ ኦርዲናንሶችን ማለፍ ፈፅሞ አይችልምና ይህ አረመኔ ሐይል እንደለመደው ንፁሐንን ሊረ ሽን ይችላልና ህዝባችን ጥንቃቄ እያደረገ የተለመደውን መረጃ ለኛ የማቀበል ስራውን አጠናክሮ እንዲቀጥል እና እራሱን በበቂ ሁኔታ እንዲከላከል ጥሪ አስተላልፋለሁ። ንፁሐን ብቻ እራሳችሁን ጠብቁልን ሌላውን ለኛ ተውት ❗ ከግንባር ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን። ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️ https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk ‎