uz
Feedback
ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

Kanalga Telegram’da o‘tish

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

Ko'proq ko'rsatish
2 956
Obunachilar
+424 soatlar
+147 kun
+38830 kun
Postlar arxiv
እየመጡ ነው እኛም እየቀበልናቸው ነው ግንቦት 01/10/2018 ዓ.ም አንድ የአገዛዙ ዙፋን ጠባቂ በመረሸን ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ፋኖን እየተቀላቀሉ። ደምበጫ ከተማ ካለው የአገዛዙ ካንፕ አባል የነበሩት
+1
እየመጡ ነው እኛም እየቀበልናቸው ነው ግንቦት 01/10/2018 ዓ.ም አንድ የአገዛዙ ዙፋን ጠባቂ በመረሸን ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ፋኖን እየተቀላቀሉ። ደምበጫ ከተማ ካለው የአገዛዙ ካንፕ አባል የነበሩት የ34ኛ ሻለቃ አባል የነበሩት ሁለት የአገዛዙ የአድማ ብተና አባላት ፋኖን ተቀላቀሉ። -አባው ጌትነት - በውቀት በላይ ብሬን ተኳሽ፣ የተባሉት የአድማ በትን አባላት አንድ የአገዛዙ ዙፋን ጠባቂ በመረሸን 99ኛ ክፍለ ጦርን ተቀላቅለዋል። አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ! ደምበጫ ወረዳ ጊዚያዊ መንግስት ሚዳያ ግንኙነት ክፍል

♦ ክብር #ለሠኔ 1/1997 ዓ.ም እና ለጥቅምት 22/1998 #የአዲስ_አበባ የነፃነት እና ዴሞክራሲ ሰማእታት 🙏 በአልሞ ተኳሾች የአዲስ አበባ ወጣት መሰዋዕትነት !! የአዲስ አበባ ጎዳናዎች የወጣቶች ደምና ሰቆቃ ፣ የእናቶችን ዋይታና ለቅሶ  ያስተናገዱበት መቼም የማይረሳ ጥቁር ቀን የዛሬ 21 ዓመት !         የምርጫ 1997 ውጤት መሰረቁን ተከትሎ፣ ሰኔ 1/1997 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከፍተኛ የሆነ ህዛባዊ እንቅስቃሴ እና ተቃውሞ ተካሂዶአል፡፡የምርጫው መሰረቅ ለመቃወም አደባባይ የወጡት ዜጎቻችን ላይ ፋሽስታዊ እርምጃ በአገዛዙ ስርዓት ጠባቂዎች አማካኝነት ተወስዶባቸዋል፡፡ ነገሩን ይበልጥ አሳዛኝ የሚያደርገው ሙሉ በሙሉ ወታደራዊ ትጥቅ የታጠቁ ወታደሮች ፣አደባባይ ባዶ እጃቸውን በወጡ የአዲስ አበባ ወጣቶች ላይ በአልሞ ተኳሾች የተወሰደው እርምጃ የስርዓቱ ልኬለሽ አምባገነን ባህሪ ፍንትዉ አድርጎ የሚያሳይ ነው፡፡        በወቅቱ የነበረው አስከፊ ጭፍጨፋ የአገዛዙ ስርዓት ዋና መሪ የሆኑት አቶ መለስ ዜናዊ፣ የአገሪቱ የጸጥታ ሃይሎች በሙሉ በአንድ ዕዝ ሰንሰለት ሥር ገብቶ ተጠሪነቱ በቀጥታ ለእሳቸው እንደሆነ፣ በሬዲዮና በቴሌቭዥን መመሪያና አዋጅ ማስነገራቸው የሚታወስ ነው፡፡ የእሳቸው እና የመንግስታቸውን ጥሪ የተቀበለው በልዩ ስሙ የአጋአዚ ጦር የሚባለው፣ በአዲስ አበባ ቁጥሩ ቀላል የማይባል የሰው ሕይወት ቀጠፈ። በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ነፃነት ጠያቂዎች በአገዛዙ ሥርዓት አገልጋዮች አማካኝነት ወደተለያየ የማጎሪያ ስፍራ በመውሰድ  በዜጎቻችን ላይ ከፍተኛ ስቃይ እና እንግልት እንዲደርስባቸው አደረጉ ።        ሰኔ 1 ቀን 1997 ወገኖቻችን ላይ የተፈጸመው አሰቃቂ ጭፍጨፋ፤ ሁሌም የማንረሰው ዛሬም ድርስ በሁላችን ህሊና የሚታወሰው ነው፡፡ በተለይ ኮተቤ መምህራን ኮሌጅ ፊት ለፊት ግንባሯን በጥይት ተመታ የተገደለችው  የ18 አመቷ ወጣት ሽብሬ ደሳለኝ፤ቀድሞ በተተኮሰ ጥይት የወደቀውን ወንድሙን አብረሃም ይልማ አስከሬን ታቅፎ ያለቅስ የነበረው በጥይት ተበሳስቶ የተገደለው የፈቃዱ ይልማ አሟሟት እንዴት ይረሳል ? የ14 አመቱ ነብዩ አለማየሁ ደብተሩን ይዞ ከትምህረት ቤት ሲመለስ አልሞ ተኳሽ በሆኑ ወታደሮች መገደሉ እና የወላጅ እናቱ የይድረሱልኝ እሮሮና ለቅሶ ዛሬም ድረስ በአገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ልብ ውስጥ የተቀመጠ ሐዘን ነው፡፡ ውድ ህይወታቸውን መሰዋዕትነት የከፈሉ ወገኖቻችንን መቼም አንረሳቸሁም !     ክብር ለሠኔ 1/1997 ዓ.ም.እና ለጥቅምት 22/1998 የአዲስ አበባ የነፃነት እና ዴሞክራሲ ሰማእታት 🙏 ይድነቃቸው ከበደ

ፋሽስቱ የኦሮሙማ አገዛዝ "አለኝ" የሚለውን ኤሊት ፎርስ ሸዋ ላይ አጥር ለመስራት ቢሞክርም፣ ነበልባሉ ፋኖ ግን በዛሬው እለትና ባለፉት ቀናት ምሽጉን ሰብሮ በመግባት የሚሰራውን ስራ ከመስራት እሚያስቆመው እንዳልሆነ ሰሞነኛ ሸዋ ላይ የፋኖ ገደሎች ትልቅ ማሳያ ናቸው። ​ባለፉት ቀናት አገዛዙ "የኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ" ብሎ በሚጠራው አካባቢ፣ ከናዝሬት ከተማ በግምት 20 ኪሎ ሜትር ገደማ ርቃ በምትገኘው መኩዬ (መኩቤ) ላይ ነበልባሎቹ ፋኖዎች ምሽግ ሰብረው በመግባት እርምጃ ወስደውባቸዋል። ከፋኖ ጥይት የተረፉትን የፋሽስቱ አብይ አህመድ የጦር መኮንኖች፣ "ለምን ሸሻችሁ? ምሽጋችሁ ተሰብሮ ካምፓችሁ እንዴት ተደፈረ?" በሚል ወደ 15 የሚሆኑ የሰራዊቱን አባላት ረሽነዋቸዋል። ​በተጨማሪም ዛሬ አገዛዙ "የኦሮሚያ ሰሜን ሸዋ" ብሎ በሚጠራው ቀጠና ፋኖ በሰራው ልዩ ኦፕሬሽን፣ በግራርያ (ፍቼ ሰላሌ) አውራጃ የደብረ ሊባኖስ ወረዳ ዋና ከተማን ጨምሮ ከፍቼ ከተማ በግምት ከ5 እስከ 15 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኙት የደብረ ሊባኖስ ወረዳ ዋና ከተማ እና ሴት ደብር ከተሞች ላይ ነበልባሉ ፋኖ ረፋዱ ላይ ቁጥጥር አድርጓል። በእነዚህ አካባቢዎች የደብረ ሊባኖስ ወረዳ ነዋሪዎችን "የፋኖ ደጋፊ ናችሁ" በሚል ለሞት፣ ለስደት፣ ለከፍተኛ እስርና ለእንግልት የዳረጉ የወረዳው የብልጽግና አመራሮች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ተፈጽሟል። በዚህም የፀጥታ ዘርፍ ኃላፊውና ሌሎች ቆስለው ወደ ፍቼ ከተማ ሆስፒታል የተወሰዱ ሲሆን፣ ለአገዛዙ ቅጥረኛ በመሆን በመረጃ ስራ ላይ ሲያገለግሉ በተገኙ ባንዳዎች ላይ ነበልባሉ ፋኖ የማያዳግም እርምጃ በመውሰድ ቦታዎቹን ተቆጣጥሯል። ወደተሟል የአማራ የነጻነት ድል ስንቃረብ የመጫወቻ ሜዳው መቀየሩ አይቀሬ ነው!

204ኛ አስቻለው ደሴ ኮር ለወራት ያሰለጠናቸውን የፋኖ ኮማንዶ ሠራዊት አባላትን አስመረቀ። ግንቦት 30/2018 ዓ.ም አፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዕዝ 204ኛ አስቻለው ደሴ ኮር ግዙፉ እቴጌ
204ኛ አስቻለው ደሴ ኮር ለወራት ያሰለጠናቸውን የፋኖ ኮማንዶ ሠራዊት አባላትን አስመረቀ። ግንቦት 30/2018 ዓ.ም አፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዕዝ 204ኛ አስቻለው ደሴ ኮር ግዙፉ እቴጌ ጣይቱ ክፍለ ጦር ለወራት ያሰለጠናቸውን የፋኖ ሰራዊት አባላት በዛሬው ዕለት በደማቅ ሥነ-ሥርዓት አስመርቋል። በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የዕዝ፣ የኮር እና የክፍለ ጦር ከፍተኛ አመራሮች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ የሀይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ወጣቶች እና የአካባቢው ማኅበረሰብ አባላት ተገኝተዋል። የኮሩ ዋና አዛዥ ሜጀር ጀኔራል ተሾመ አበባውን ጨምሮ ከፍተኛ አመራሮች በመርሃ ግብሩ ላይ ተሳትፈዋል። በዕለቱ የተገኙት ክቡር እንግዳ ባስተላለፉት መልዕክት፣ “ይህ የኮማንዶ ኃይል የአማራን ህልውና ከማስከበር ባለፈ ለሕዝቡ መከታና ጋሻ በመሆን ትልቅ አቅም የሚፈጥር እና ጠንካራ አሸናፊ ኃይል ነው” ብለዋል። ተመራቂዎቹ በቆይታቸው ወቅት የወታደራዊ ስልጠና ንድፈ ሐሳብን ከተግባራዊ ልምምድ ጋር በማጣመር በቂ ዝግጅት ማድረጋቸው ተገልጿል። በምረቃው ሥነ-ሥርዓቱም የሰለጠኑበትን ጥበብና ወታደራዊ ዝግጁነታቸውን የሚያሳዩ የማርሽ ትርኢቶችና ሌሎች ልዩ ልዩ ትዕይንቶች ቀርበዋል። በተጨማሪም በስልጠናቸው ከፍተኛ ውጤትና ዓርአያነት ላሳዩ የኮማንዶ አባላት የዕውቅናና የሽልማት አሰጣጥ ተከናውኗል። 204ኛ አስቻለው ደሴ ኮር የተጣለበትን ታሪካዊ ኃላፊነት ለመወጣትና የሕዝቡን ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ መሰል የሰው ኃይል ግንባታዎችን አጠናክሮ እንደሚቀጥል በዕለቱ ተገልጿል። መረጃውን ያደረሰን የአፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዕዝ 204ኛ አስቻለው ደሴ ኮር ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ነው።

አፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ መሐመድ ቢሆነኝ ኮር አስቴ ጎማ ተራራ ክፍለ ጦርና አፄ ዘረአ ያእቆብ ኮር አፄ ይኩኖ አምላክ ክፍለ ጦር በጋራ ታላቅ የህዝብ ወይይት መድረክ አካሂደዋል። አፋ
+2
አፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ መሐመድ ቢሆነኝ ኮር አስቴ ጎማ ተራራ ክፍለ ጦርና አፄ ዘረአ ያእቆብ ኮር አፄ ይኩኖ አምላክ ክፍለ ጦር በጋራ ታላቅ የህዝብ ወይይት መድረክ አካሂደዋል። አፋብን ሸ/ጠ/ግ/አ/ዕ አፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ መሐመድ ቢሆነኝ ኮር በአስቴ ጎማ ተራራ ክፍለ ጦርና አፄ ዘረዓያዕቆብ ፩ኛ ኮር አፄ ይኩኖ አምላክ ክፍለ ጦር በሚያስተዳድሩት ሽዋ ጠቅላይ ግዛት ይፋት አውራጃ አንፆኪያ ገምዛ ወረዳ ሃገረማርያም ሟጨራ ቀበሌ በመስኖ ከተማ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ታላቅ የህዝብ ወይይትና የአንድነት ፕሮግራም የተደረገ ሲሆን የአፋብን ወታደራዊ ቃል አቀባይ አበርኛ አበበ ሙላቱ፥ የዕዝ ከፍተኛ አመራሮች፥የኮርና ክ/ጦር አመራሮች በተገኙበት ከህዝባችን ጋር ፊት ለፊት በመወያየት ለተፈጠሩ የህዝብ ቅሬታና ችግሮች ተገቢና ፍትሃዊ መልስ በመስጠቱ ህዝባችን ደስታውን ገልጿል። የህዝብ መድረኩ የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች የተሳተፉ ሲሆን አማራ ያለ ፋኖ መኖር አይችልም ታግላችሁ ስላኖራችሁን እናመሰግናለን አብረናችሁ በመታገል ታሪክ እንሰራለን አንድነታችንን በማፅናት ዳግም ቃላችንን በማደስ በድል ተጠናቋል። ክብር ለትግሉ ሰምአታት ድል ለአፋብን አፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ግንቦት 30/09/2018ዓ/ም

Baye Desta Per ዋለ አባተን ጨምሮ የምስራቅ ጎጃም ካድሪን በእንባ ያራጨው የሻለቃ በርይሁን ውዱ ድምሰሳ በተጨማሪ ደግሞ 6 አድማ ብተናዎችን ወደ ጥቁር አንበሳ ተልከዋል። 201ኛ ኮር ግንቦት30/2018 ዓ.ም ~~~~~~~ ከታች በምስሉ ላይ የሚታየው የ36ኛ ሻለቃ የአድማ ብተና አዛዥ ሻለቃ በርይሁን ውዱ በጀብደኛው 206ኛ ኮር 14ኛ ክ/ጦር በጅበላ ሙተራ ሻለቃ የተደመሰሰ ነው። ጠንካራ የሚባሉ አራት አጃቢዎቹን አስከትሎ ከ23 የሰራዊት አባላት ጋር ከደብረ ማርቆስ ወደ ሊባኖስ እየሔደ ባለበት የቦ ማርያም አካባቢ በተደረገበት የደፈጣ ጥቃት ድባቅ ተመቷል። ዋለ አባተ የምስራቅ ጎጃም አስተዳደሪ ስቅስቅ ብሎ ያለቀሰበት ትልቅ ድል ተቀናጅተናል። የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ፣ የብልፅግና ሹማምንትና አዛውንት ደረት እየደቁ በሚገኙበት በዚህ ስዓት በደብረ ማርቆስ ሆስፒታል በነፍስ ውጭ ነፍስ ግቢ ማጣጣር ላይ የነበሩት ፦ 1. ግዛት ወርቁ 2. ሰጠኝ አላምነህ 3.ጌታሰው ታደሰ 4. ማሙሸ አዳነ 5. ፈለቀ ጌታቼው 6. መሀመድ አህመድ ህይወታቸውን በደብረ ማርቆስ ሆስፒታል መታደግ ባለመቻሉ ወደ ጥቁር አንበሳ ተልከዋል። 1. ሁሴን ያሲን- ደብረ ማርቆስ ሆስፒታል የሚገኝ ከባድ ቁስለኛ 2.ፋሲል ሲሳይ- ቀላል ቁስለኛ። በዚህ ስዓት የደብረ ማርቆስ ከተማ ነዋሪዎች በጀግኖች ልጆቻቸው ጀብድ በሃሴት እየቦረቁ መሆናቸውን ታውቋል። አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳብ! አዲስ ተስፋ!! ግንቦት 30/2018 ዓ.ም Baye Desta Per የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ

የቡልጋ ክ/ጦር የፋኖ ሰራዊት የምርጫ ኮሮጆ ለመዉሰድ በመጣ የአገዛዙ የጠላት ሀይል ላይ ድል ተቀዳጀ። *            ቀን/30/9/2018ዓ.ም አፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነዉ ዕዝ ከሰም ፪ኛ ኮር አይበገሬው የቡልጋ ክ/ጦር የፋኖ አባላት የአብይ አህመድን የድራማ ምርጫ ኮሮጆ ከመተህብላ ከተማ ወደ አ.አ በምንጃር ለመዉሰድ በመጣ ሀይል ላይ ከፍተኛ ኪሳራ አደረሰ። ጠላት መነሻዉን ከምንጃር አረርቲ ከተማ አድርጎ ወደ መተህብላ ከተማ ለመግባትና የምርጫ ኮሮጆዉን ይዞ ለመዉጣት ያደረገዉ ሙከራ በቡልጋ ክፍለጦር አናብስቶች ተገርፎ እንዳሰበዉ ሳይሳካለት ቀርቷል ። ዉጊያ ከጠዋቱ 2:00 ሰአት የተጀመረ ሲሆን የወገን ሀይል ከፍተኛ ተጋድሎ አድርጎ ስለነበር እስከ 10:00 ሰአት ድረስ ከፍተኛ የሆነ ትንቅንቅ የተደረገበት ሲሆን ልዩ ቦታዉ ከአክርሚት እሰከ ተሬ በሚባል አካባቢ ዉጊያዎች ተካሂዷል።በዚህም አዉደ ዉጊያ የጠላት ሀይል ላይ  ከፍተኛ የሆነ ሰብአዊእና ቁሳዊ ኪሳራ ማድረስ ተችሏል። በዚህም ጠላት በደረሰበት መብረቃዊ ምት መደናገጥ ዉስጥ የገባ ሲሆን የምርጫ ኮሮጆዉን ወደ ምንጃር ይዞ መዉጣት እንደማይችል  በፋኖ ብርቱ ክንድ ቦታው በደፈጣና በምሽግ መያዙን የተረዳው ጠላት መንገድ በመቀየር በመተሀራ በኩል በሚያስወጣዉ መንገድ ይዞ ለመዉጣት ተገዷል።በዚህም ግንባር ከአባት አርበኞች  ጥምር ጦር ጋር  ቀላል የማይባል ዱላ ያረፈበትና የአገዛዙ ሰራዊት ተሽመድምዶ ሽንፈቱን አምኖ በመቀበል አቅጣጫ ቀይሮ ተንቀሳቅሷል። "ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!" "ክብር ለትግሉ ሰማዕታት!"    የመረጃ ምንጭ -የከሰም ኮር ህ/ግንኙነት ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ!!

ከአፋብን ምኒልክ ዕዝ የተሰጠ ጥብቅ ማስጠንቀቂያ! በአማራ ህዝብ ላይ ዘር ማጥፋት እየፈፀመ ያለው የብልፅግና አገዛዝ ነውሩን ለመሸፈንና በዋናነት የአዲስ አበባን ዲሞግራፊ ለመቀየር እየተጠቀመበት ያለውን የኮሪደር ልማት ሌሎች አካባቢዎችም ላይ ለማስመሰል እየሰራ ያለ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን በዚህም ኮሪደር ልማት ለመመረቅ በሚል አብይ አህመድ ወይም ምክትሉ ተመስገን ጥሩነህ ሰኔ 02/2018 ዓ.ም ወልድያ ከተማ እንደሚመጡ ለማረጋገጥ ችለናል! በዚሁ በዕለተ ማክሰኞ ሰኔ 02/2018 ዓ.ም ወልድያ ከተማ ሊካሄድ ለታሰበው አማራ ላይ እየተፈፀመ ያለውን "ዘር ማጥፋት" ትኩረት መንፈጊያ የብልፅግና ዝግጅት ላይ የሃይማኖት አባቶች፣ የሃገር ሽማግሌዎች፣ ታዋቂ ግለሰቦችና እንዲሁም አንዳንድ ቲክታከሮች ልትገኙ ጥሪ እንደተደረገላችሁ መርሃ ግብሩን የሰሜን ወሎ ዞን እና የወልድያ ከተማ አስተዳደር የውስጥ አርበኞች አድርሰውን ለማወቅ ችለናል! በመሆኑም የአማራ ህዝብ ላይ ዘር ማጥፋት እየተፈፀመ ባለበት በዚህ ጊዜ እንዲሁም ሰሞኑን ኦሮሚያ የአርሲ ኦርቶዶክሳዊያን በግፍ በታረዱበትና በተጨፈጨፉበት አሁንም ታቦት ተሸክመው ስደት ላይ ባሉበት ነባራዊ ሁኔታ የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት እና የወልድያ ከተማ አስተዳደር ቤተ-ክህነት የኃይማኖት አባቶች ምዕመናንን ገዳይ አሰማርቶ እያስጨፈጨፈ እና እየጨፈጨፈ ያለዉ የአገዛዙ ድግስ ላይ ባለመገኘት አባታዊ ግዴታችሁን  እንድትወጡ ስንል ጥብቅ መልዕክት እናስተላልፋለን። ከዚህ ውጭ ግን አለማዊ ህይወት ላይ ያሉ አርቲስቶች ሳይቀሩ አርሲ ላይ በግፍ ለታረዱና ለተጨፈጨፉ ወገኖቻቸው ቅድሚያ በመስጠት የአዲስ አበባው የብልፅግና የሙዚቃ ድግስ ላይ ባልተገኙበት ሁኔታ መሃል ወልድያ ከተማ በህዝባችሁ መካከል ሆናችሁ ይህንን የማታደርጉና ቀላል የሚባለውን መስዋዕትነት የማትከፍሉ ከሆነ የኃይማኖት ልጆቻችሁን በግፍ እያረዱና እየጨፈጨፉ ካሉት የብልፅግና ሹማምንቶች ለይተን እንደማናያችሁ ልናሳውቃችሁ እንወዳለን። በመጨረሻም ከላይ በዝርዝር ለተገለፃችሁ አካላቶች እንዲሁም ለወልድያ ከተማ እና አካባቢው ማህበረሰባችን በዕለተ ማክሰኞ በገበያ ቀናችሁ የሚወጣውንም ህዝብ ለድግሳቸው ለመጠቀም ሲባል ገዳያችን ብልፅግና ባዘጋጀው "የሃገሩ ሰላም ነው እና ልማት ነው!" የሚል ህዝብ ማታለያና ማጭበርበሪያ ዝግጅት ላይ እንዳትገኙ ስንል መልክታችንን እያስተላለፍን ይህንን ተላልፎ በተገኘ ማንኛውም አካል ላይ ግን  ገዳይ እና አስገዳይ ከሆነው አገዛዝ ለይተን እንደማናየዉ እና በተናጠልም ይሁን በቡድን ለምንወስደው እርምጃ ሃላፊነት የማንወስድ መሆኑን ከወዲሁ ጥብቅ መልክታችንን እናስተላልፋለን! ህልውንችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብን ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ ግንቦት 30/2018ዓ.ም

​104ኛ ኮርን ለመክበብ የሞከረዉ የአገዛዙ ሰራዊት ራሱ ተከቦ ሲቀጠቀጥ ዉሏል!! ​አፋብን ወሎ ቤተ አማራ ምኒልክ ዕዝ ስር የሚገኘውን 104ኛ ኮርን "አፍናለሁ" በሚል ትዕቢትና ቅዠት ተሞልቶ ወደ ግንባር ያመራው የአገዛዙ ሠራዊት በጀግኖች ክንድ ራሱ ታፍኖ  ሲቀጠቀጥ አርፍዷል። ​ ግንቦት 30 ቀን 2018 ዓ.ም የአገዛዙ ጦር በ104ኛ ኮር፣ 23ኛ ክፍለጦር ስር የሚገኘውን 1ኛ ሻለቃን በብዛትና በኃይል ለመክበብ አስቦ ሰፊ እንቅስቃሴ ያደረገ ቢሆንም  በጀግኖቹ  ስልታዊ ዝግጅትና የንቃት ደረጃ የጠላትን ዕቅድ አስቀድመዉ አክሽፈዉታል። ​የአገዛዙ ሠራዊትም  በተንታ ወረዳ ልዩ ስሙ "ኮረት" በተባለ ስፍራ ላይ ሲደርስ፣ ገና ከጅምሩ ባልጠበቀው አስደንጋጭ ጥቃት  የተሰነዘረበት ሲሆን የ1ኛ ሬጅመንት ተናዳፊዎቹ የጠላትን  ከበባ በመስበር ፈጣንና ኃይለኛ የፊት ለፊት ዉጊያ በማድረግ በጠላት ላይ ድልን ተጎናጽፈዋል። ​በዚህ እልህ አስጨራሽ ዉጊያም  አጥቂ የነበረው የአገዛዙ ሰራዊት ተጠቂ በመሆን ራሱን መከላከል አቅቶት ታፍኖ ሲቀጠቀጥ  ዉሏል። በዚህም ዉጊያ በርካታ የአገዛዙ ሠራዊት አባላት ሙትና ቁስለኛ  ሲሆኑ  በርካታ የጦር መሳሪያዎችና ትጥቆች ሲገኙ የጠላት ስልታዊና ወታደራዊ ዕቅድ ሙሉ በሙሉ እንዲከሽፍ አድርገዉታል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብን ወሎ ቤተ አማራ ምኒልክ ዕዝ ሚዲያ እና ኮሚዩኒኬሽን  መምሪያ!! ግንቦት 30/2018ዓ.ም

የእነ አረጋ ከበደ ሙሴዎች መሪ መገደሉ ተሰማ። በጠላት የ36ኛ ሻለቃ የድማ ብተና አዛዥ ሻለቃ በርይሁን ጨምሮ 16 አድማ ብተና አባላት ተደመሰሱ። 23 የአድማ ብተና አባላትን በመያዝ ከደብረ ማርቆስ
የእነ አረጋ ከበደ ሙሴዎች መሪ መገደሉ ተሰማ። በጠላት የ36ኛ ሻለቃ የድማ ብተና አዛዥ ሻለቃ በርይሁን ጨምሮ 16 አድማ ብተና አባላት ተደመሰሱ። 23 የአድማ ብተና አባላትን በመያዝ ከደብረ ማርቆስ ከተማ ተነስቶ ወደ ሊባኖስ ሲንቀሳቀስ በነበረው ሻለቃ በርይሁን ላይ የቦ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ ላይ መብረቃዊ ጥቃት የፈፀሙት በአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር 14ኛ ክ/ጦር የጅበላ ሙተራ ሬጅመንት አርበኞች አንፀባራቂ ድል ተቀዳጅተዋል። በዚህ የቆረጣ ማጥቃት፡ የደብረ ማርቆስ ከተማ ነዋሪዎችን በጅምላ በማሰር በመደብደብ፣ በመረሸንና ዘረፋ በመፈፀም አሰቃቂ ድርጊት ይፈፅም የነበረው ሻለቃ በርይሁን ጨምሮ 16 የአድማ ብተና አባላት ሲደመሰሱ። ሰባት የሚሆኑት በፅኑ ቆስለው ለሕክምና ወደ ደብረ ማርቆስ ሆስፒታል መግባታቸው ተረጋግጧል ሲል የ206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት ክፍል ገልጿል።

ሰበር ዜና! ሰራዊታችን ለተከታታይ ሁለት ቀናት ባደረገው ልዩ የተቀናጀ ኦፕሬሽን ጀግናው የራስ አበበ አረጋይ ክፍለጦር የደብረ ሊባኖስ ወረዳ ሁለት ከተሞችን ተቆጣጠረ።     አፋብን ሸ/ጠ/ግ/አ/ዕዝ የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ አፄ አምደ ፅዮን ኮር አካል የሆነውየራስ አበበ አረጋይ ክፍለጦር ከአርበኞች ጦር ሰራዊት ጋር በቅንጅት በተሰራ ልዩ ኦፕሬሽን በግራርያ (ፍቼ ሰላሌ) አውራጃ የደብረ ሊባኖስ ወረዳ ዋና ከተማን ጨምሮ ሴት ደብር እና ውሻ ገደል የሚባሉ ሁለት የወረዳ ከተሞችን ዛሬ ረፋዱ ላይ በቁጥጥር ስር ማድረጉን ኮሩ በላከው የግንባር መረጃ አስታውቋል። የደብረ ሊባኖስ ወረዳ የሆኑ በርካታ ነዋሪዎችን "የፋኖ ደጋፊ ናችሁ" በሚል ብዙዎችን ለሞትና ለስደት እንዲሁም ለከፍተኛ እስርና እንግልት የዳረጉ የወረዳው የብልፀሰግና አመራሮች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ሲፈፀም የፀጥታ ዘርፍ ኃላፊውና ሌሎች ቁስለኛ ሆነው ወደ ፍቼ ከተማ ሆስፒታል የተወሰዱ ሲሆን፣ ለአገዛዙ ቅጥረኛ በመሆን የመረጃ ስራ ላይ ሆነው ሲያገለግሉ በተገኙ ባንዳዎች ላይ ክፍለጦሩ የማያዳጋም ርምጃ በመውሰድ ከተማውን ተቆጣጥሯል። የህዝብ ልጅ የሆነው ጀግናው ሰራዊታችን ትላንት ግንቦት 29 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ዛሬ ግንቦት 30 ቀን 2018ዓ.ም ዕኩለ ቀን ድረስ በሞርተርና ዙ-23 ታጅቦ ከገጠመው አገዛዝ ጋር ባደረገው ልዩ ተጋድሎ ከተሞቹን ሲቆጣጠር እስከ ጫጋል ከተማ ድረስ አድማሱን ባሰፋው ውጊያ ሽንፈቱን የተከናነበው የብልፅግናው  የግለሰቦች ታዛዢ ዘራፊ ሰራዊትና ጥምር ጦር ወደ ፍቼ ከተማ መፈርጠጡን ዕዙ በመረጃው አረጋግጧል።      ''ክብር ለትግሉ ሰማዕታት''    ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ       ግንቦት 30/2018ዓ.ም

የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በአርሲ ምድር በተፈጸመው ጥቃት ላይ ፍትህ ጠይቀዋል። በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ አርሲ ዞን አህጉረ ስብከት ስር በሚገኙት የአሰኮ፣ ሽርካ፣ ሆንቆሎ ዋቤ እና ሙኔሳ ወረዳዎ
የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በአርሲ ምድር በተፈጸመው ጥቃት ላይ ፍትህ ጠይቀዋል። በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ አርሲ ዞን አህጉረ ስብከት ስር በሚገኙት የአሰኮ፣ ሽርካ፣ ሆንቆሎ ዋቤ እና ሙኔሳ ወረዳዎች በንጹሐን ምዕመናንና በቤተ ክርስቲያናት ላይ ተፈጽሟል የተባለውን ጥቃት በመቃወም ምዕመናን፣ ወጣቶች እና የማኅበረሰብ ክፍሎች ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ፍትህ እየጠየቁ መሆኑ ተገልጿል። በተመሳሳይ ምዕመናንና ወጣቶች “እኛ የአቡነ ጴጥሮስ ልጆች ነን፤ የአባቶቻችንን ሃይማኖት በጽናት እንጠብቃለን” በማለት ለተጎዱ ወገኖች ፍትህ እንዲሰጥ ጥያቄያቸውን አቅርበዋል። #ፍትህ_ለአርሲ_ኦርቶዶክሳውያን #አርሲ  #ኢትዮጵያ