uz
Feedback
ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

Kanalga Telegram’da o‘tish

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

Ko'proq ko'rsatish
3 534
Obunachilar
+24824 soatlar
+5847 kun
+97230 kun
Postlar arxiv
ይልማናደንንሳ

ምስራቅ ጎጃም፣ አዋባል፣ ፅድ ማርያም

#የድል_ዜና የጀግናው የሻለቃ መንበሩ ጌጋዬ (መምቤ) ደም በእጥፍ ተመልሷል። 201ኛ ኮር 54ኛ ክ/ጦር ድል ተቀዳጄ። <>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^ 54ኛ ክ/ጦር ተወርዋሪ ኃይሏንና ሻለቆችን በጋራ በሰራው የተጠና ኦፕሬሽን ሞጣ ሙገር ከተማ ላይ በጠላት ላይ ድልን ተቀዳጄ መጋ,24/7/2018ዓ/ም አነጋግ 11:45ሰዓት የተጀመረው ሞጣ ሙገር የነበረው የአብይ አህመድ ሰራዊትና ግብረአበሮቹ ወደ አመድነት ተቀይረዋል።  ምሽጉን በ3ደቂቃ ሰብሮ መግባት ጠላት ሙትና ቁስለኛ ሁኖ የተረፈው እግሬ አውጭኝ ብሎ ፈርጥጦ ወደ ከተማና ወደጫካ ፈርጥጧል። ከጫካ ለቀማ ላይ ነን በዛሬው አውደ ውጊያ 👁 1➔የተደመሰሰ መከላከያ➔ 42 2➔የተደመሰሰ ሚኒሻ  ➔ 29 3➔በእጅ የተያዘ 1ሻበል ባሻና 4መሰረታዊ ወታደር ይቀጥላል ከለቀማው (ጫቃ)😄 5➔ከ40በላይ የነፍስ ወከፍ መሳሪያ ገቢ ተደርጓል። ጭማሪ Loading --------------^^^^ አፋብን ቴወድሮስ ዕዝ 201ኮር 54ኛ ክፍለጦር ህዝብ ግንኙነት

ዛሬ መጋቢት 24 ቀን 2018 ዓ.ም "ሰላም ሳይኖር ምርጫ ሊኖር አይችልም: ገዳዮቻችንን በምርጫ ካርድ አናነግስም" በሚል መሪ ቃል በመላው አማራ ክልል ምርጫውን የሚቃወም የህዝብ ድምፅ እየተስተጋባ
+5
ዛሬ መጋቢት 24 ቀን 2018 ዓ.ም "ሰላም ሳይኖር ምርጫ ሊኖር አይችልም: ገዳዮቻችንን በምርጫ ካርድ አናነግስም" በሚል መሪ ቃል በመላው አማራ ክልል ምርጫውን የሚቃወም የህዝብ ድምፅ እየተስተጋባ ነው። በደብረማርቆስ ዙሪያ በደብረ ዘይት ቀበሌ እየተካሄደ ያለ ትዕይንተ ህዝብ ነው።

#ሸዋ_መዘዞ_ከተማ👏 ዛሬ መጋቢት 24 2018 ዓ. ም "ገዳዮቻችንን፣ በምርጫ ካርድ አናነግስም፣ በጨረቃ ምርጫ ዳግም ለባርነትና ለእልቂት ለብልፅግና ምቹ ሁኔታን አንፈጥርም በማለት መላው የአማራ ህዝብ ሰላማዊ ሰልፍ ወጣ

የህዝባችን የተቃውሞ ሰልፍ በአለም አቀፍ ጋዜጠኞች ተዘገበ👏👏👏👏
የህዝባችን የተቃውሞ ሰልፍ በአለም አቀፍ ጋዜጠኞች ተዘገበ👏👏👏👏

“ይህ ምርጫ ሳይሆን ድራማ ነው!” ሸዋ-ተሬ
+2
“ይህ ምርጫ ሳይሆን ድራማ ነው!” ሸዋ-ተሬ

"አበባው ለኔ... እሾሁ ለናንተ!" አብይ አህመድ በቤተ-መንግስት ኮሪደር ላይ ስለ ብልጽግና ተረክ እያላዘነና የውሸት አበባ እያሳየን ባለበት በዚህ ቅጽበት፣ የአሜሪካ ኤምባሲ ግን የኢትዮጵያን ካርታ
"አበባው ለኔ... እሾሁ ለናንተ!" አብይ አህመድ በቤተ-መንግስት ኮሪደር ላይ ስለ ብልጽግና ተረክ እያላዘነና የውሸት አበባ እያሳየን ባለበት በዚህ ቅጽበት፣ የአሜሪካ ኤምባሲ ግን የኢትዮጵያን ካርታ በደም ቀለም ነክሮ "ሞት ይሸታችኋልና ዞር በሉ" ብሎ ዓለምን አስጠንቅቋል። "እባብ ለጠላትህ፣ ርግብ ለወዳጅህ" እንደሚባለው ሳይሆን፣ የእርሱ አስተዳደር ለህዝቡ እባብ ሆኖ ለካሜራ ግን ርግብ ለመምሰል የሚሄድበት ርቀት መጨረሻም በነጩ ቤተመንግስት በአደባባይ ተጋልጧል። ከአማራ እስከ ኦሮሚያ፣ ከትግራይ እስከ አፋር ያለውን ምድር የመከራ አውድማ አድርጎት ሳለ፣ እርሱ ግን አሁንም በፓርኮች ግንባታ ስም የሰቆቃችንን አቧራ ሊያብስ ይሞክራል። "መሸጥ ካቃተው ነጋዴ በላይ ጩኸቱ አይሰማም" እንዲሉ፣ አብይና ግብረ-አበሮቹ "ሰላም ነው" ብለው ቢጮሁም የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ምስክርነት ግን የብልጽግናን ጭንብል አውልቆ ጥሎታል። ሀገሪቱን በፈንጂ፣ በእገታና በጦርነት አረንቋ ውስጥ ዘፍቆ ስለ ሽርሽር ማውራት በቁም መቃብር ላይ የመጨፈር ያህል እብደት ነው። ይህ የአሜሪካ ማስጠንቀቂያ ግልጽ መልዕክት አለው፤ የኢትዮጵያ ህዝብ ብቻ ሳይሆን ዓለምም የአብይን የቅዠት ጉዞ ሰልችቶታል። በመጨረሻም በቲቪ መስኮት የሚረጨው የብልጽግና ፕሮፖጋንዳ መሬት ላይ ባለው የአሜሪካ ኤምባሲ የጉዞ እገዳ ድባቅ ተመትቶ ፍርክስክሱ ወጥቷል።

ስማዳ ወረዳ የኳሳ ከተማ ገዳዮቻችንን በምርጫ አናነግስም‼️
ስማዳ ወረዳ የኳሳ ከተማ ገዳዮቻችንን በምርጫ አናነግስም‼️

አገዛዙ ለሚያደርገው የሐሰት ምርጫ በእነማይ ወረዳ ዲማ እና አካባቢው ከፍተኛ የሆነ ህዝባዊ ተቃውሞ ገጠመው!! በአብይ አህመድ አገዛዝ በአማራ ህዝብ ላይ እያካሄደ ያለውን ዘር ተኮር ጭፍጨፋን በመቃወም በሁሉም የአማራ ከተሞች እና የገጠር ቀበሌዎች ላይ መጋቢት 24/2018 ዓ.ም የተቃውሞ ሰልፎቾ እየተካሄዱ ይገኛሉ። የመኖር መብቱ የተነፈገው የአማራ ህዝብ በኮ/ል አብይ አህመድ አገዛ እየተካሄደበት ያለውን ዘር ተኮር ጭፍጨፋ እና የሐሰት ምርጫ በመቃወም በእነማይ ወረዳ ዲማ እና አካባቢው ማህበረሰብ ከፍተኛ ቁጣ ቀስቅሶል። በዲማ እና አካባቢው ማህበረሰብ የአገዛዙ ምርጫን በማስመልከት በህዝባዊ ተቃውሞዎች ከተነሱ መፈክሮች ውስጥ:- ✍️የአማራ ህዝብ ለምርጫ የሚሆን ግዜ የለንም!!! ✍️አምባ ገነኑ አብይ በቃን!!! ✍️ብልፅግና በቃን!!! ✍️ብልፅግና ገዳይ ነው!!! ✍️በድሮን እና በመድፍ ለሚጨፈጨፍ ህዝብ ምረጫ ቅንጦት ነው!!! ✍️ምርጫችን ፋኖነት ነው!! ✍️ በዚህ ምርጫ የሚሳተፍ የኢትዮጵያን ህዝብ መካድ ከእውነት ጋር መጋጨት ነው!!! የሚሉ መፈክሮች በማህበረሰቡ ላይ ከፍተኛ ቁጣን ያዘለ የተቃውሞ ሰልፎች ተካሂደዋል።       መጋቢት 24/2018 ዓ.ም የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክፍለ ጦር ሕዝብ ግንኙነት

⚫️#መጋቢት_24_የመርገምት_ቀን⚫️ የሀገሪቱ 'ምክትል' ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በ2011 ዓ/ም "በነገው ቀን የመጀመሪያውን ድፍድፍ ነዳጅ እናወጣለን፣በብዙ ሚሊዮን ቶን የሚቆጠር ድፍድፍ ነው የተገኘው፣እንኳን ደስ ያለን" በሚል ተናግረው ነበር።በወቅቱ አንድ ሊትር ነዳጅ  ከ18 ብር ያልበለጠ ነበር። ተገኘ የተባለው ነዳጅም የውሃ ሽታ ሆኖ ቀረ። ከሰባት ዓመታት በኋላ የአንድ ሊትር ነዳጅ ዋጋ 164 ብር ደርሶም እሱም ቢሆን ከነ አካቴው ጠፋና "ነዳጅ ቆጥቡ" አለ። ስምንት የቀላባይነትና የዋሾነት ዘመን! ስምንት የድንቁርናና የስግብግብነት ዘመን! ስምንት የጭፍጨፋና የእልቂት ዘመን! ስምንት ኢትዮጵያ እንደ ሀገር በሁሉም ዘርፍ የተዋረደችበትና የኮሰመነችበት ዘመን! ስምንት የጦርነትና የእልቂት፡ የመፈናቀልና የመሳደድ ዘመን! ስምንት የተላላኪነትና የአጎብዳጅነት ዘመን! ስምንት ሀገር በነቢንዛይድና በሌሎች ባዕዳን እጆች ቅኝ ግዛት የተገዛችበት ዘመን! ስምንት... ስምንት... ስምንት.... ጨምሩበት። በተለይ ደግሞ ለአማራ ሕዝብ እጅግ የከፋ፡ የመከራ መቀመቅ ውስጥ የገባበት ዘመን ነው። የጅምላ ሞት፣የጅምላ መፈናቀል፣የጅምላ እስር።በድሮንና በጀት፣በመድፍና በዙ23 እየተጨፈጨፈ ያለበት ዘመን። (ይህ ሲባል፦ ከስምንት ዓመት በፊት የነበሩት ዘመናት ለአማራ ሕዝብ ብሩህ ነበሩ ማለት አይደለም። ካለፉት በርካታ አሥርት ዓመታት ጀምሮ የአማራ ሕዝብ በከባድ ሕልውና አደጋ ላይ ወድቆ ለጆሮ የሚዘገንኑ፣ ለአይን የሚሰቀጥጡ አያሌ መከራዎችን ሲቀበል ነበር። ካለፉት ስምንት ዓመታት ወዲህ ደግሞ ፀረ አማራ ትርክቶች ስጋ ለብሰው በምኒልክ ቤተመንግስት ገብተው፡ ባንክና ታንኩን ተቆጣጥረው፡ ከዚህ ቀደም በአማራ ሕዝብ ላይ የሚዘንበውን የመከራ ዝናብን ላይ ዶፍ ጨመሩበት) 24/ዐ7/2018 ዓ.ም

የአማራ ክልል ም/ት ፕሬዚዳንት ፋኖ ምሬ ወዳጆን ለማነጋገር እንደሞከረ አነበብኩ። ሰውየው የምሬን ድምፅ ለመስማት ናፍቆ ይሁን ወይም “ምሬን እኮ አናገርኩት” በማለት እራሱን ከፍ ለማድረግ አስቦ ያደ
የአማራ ክልል ም/ት ፕሬዚዳንት ፋኖ ምሬ ወዳጆን ለማነጋገር እንደሞከረ አነበብኩ። ሰውየው የምሬን ድምፅ ለመስማት ናፍቆ ይሁን ወይም “ምሬን እኮ አናገርኩት” በማለት እራሱን ከፍ ለማድረግ አስቦ ያደረገው ይሁን አላውቅም። ምሬ ለአላማው መራራ እንደሆነ እስከዛሬ ሳይገባው ቀርቶ ግን አይመስለኝም። ምሬ መረር ያለ ንግግር ተናግሮት ሸኝቶቶታል። እነዚህ ብልፅግናዎች የፋኖን ትግል የጓደኛሞች ፀብ አድርገው ነው እንዴ የሚያዩት? እንዲህ አይነት የአላማ ትግል እኮ የሚቆመው በእውነተኛ ድርድር ወይም በማሸነፍና በመሸነፍ እንጅ፣ እግር ስር እየወደቁ በመለመን አይደለም። ብልፅግና በወታደር ሞከረ፣ አልሆነም። በቄሶችና በሸሆች ሞከረ አልሆነም። እንግዲህ አረጋን ወይም አብይን ድጋይ አሸክሞ መላክና የፋኖ መሪዎች ስር መደፋትና መለመን ነው የቀረው። ይህም እንኳን ቢሆን አይሳካም። ይህ ሁሉ ደም የፈሰሰው ወይም የአማራ ህዝብ ላለፉት 3 አመታት ዋጋ የከፈለው ጥቂት መሪዎችን ወደ አመራር ለማምጣት ወይም ግላዊ ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ እንዳልሆነ ሳትረዳ፣ ሺ ጊዜ ስልክ ብትደውል፣ ሺ ጊዜ አማላጅ ብትልክ፣ ሺ ጊዜ አባል ብታስኮበልል፣ ሺ ጊዜ ፕሮፓጋንዳ ብትነዘ የሚለወጥ ነገር አይኖርም።

መጋቢት 23 ቀን 2018 ዓ.ም የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ምኒልክ ዕዝ 101ኛ ኮር የህክምና ባለሞያዎችን አሰልጥኖ አስመርቋል። የምኒልክ ዕዝ ህክምና መምሪያን ጨምሮ በየ እዞቹ ባሉ ጤና መምሪያወች የህክምና አገልግሎት እየሰጡ ያሉ ታጋይ ሃኪሞችን ከትግሉ ጋር የሚያዋህዱ ሁለንተናዊ ስልጠናዎች ይሰጣሉ። እንዲሁም ከመጀመሪያ ህክምና እርዳታ እስከ ሌሎች ቀላልና መካከለኛ ቀዶ ጥገና ድረስ በሞያው ዘርፍ የካበተ ልምድ ባላቸው አሰልጣኞች የህክምና ሙያ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል:: በዚህም መሰረት የምኒልክ እዝ 101ኛ ኮር በቀድሞ ሰማዕቱ የ11ኛ ክፍለ ጦር 3ኛ ሻለቃ አርበኛ ሃኪም አድኖ ስጦታው በተሰየመ የስልጠና ፕሮግራም ታጋይ ሐኪሞችን አሰልጥኖ አስመርቋል።