ch
Feedback
ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

前往频道在 Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

显示更多
3 536
订阅者
+2524 小时
+3407 天
+72430 天
帖子存档
የህዝባችን የተቃውሞ ሰልፍ በአለም አቀፍ ጋዜጠኞች ተዘገበ👏👏👏👏
የህዝባችን የተቃውሞ ሰልፍ በአለም አቀፍ ጋዜጠኞች ተዘገበ👏👏👏👏

“ይህ ምርጫ ሳይሆን ድራማ ነው!” ሸዋ-ተሬ
+2
“ይህ ምርጫ ሳይሆን ድራማ ነው!” ሸዋ-ተሬ

"አበባው ለኔ... እሾሁ ለናንተ!" አብይ አህመድ በቤተ-መንግስት ኮሪደር ላይ ስለ ብልጽግና ተረክ እያላዘነና የውሸት አበባ እያሳየን ባለበት በዚህ ቅጽበት፣ የአሜሪካ ኤምባሲ ግን የኢትዮጵያን ካርታ
"አበባው ለኔ... እሾሁ ለናንተ!" አብይ አህመድ በቤተ-መንግስት ኮሪደር ላይ ስለ ብልጽግና ተረክ እያላዘነና የውሸት አበባ እያሳየን ባለበት በዚህ ቅጽበት፣ የአሜሪካ ኤምባሲ ግን የኢትዮጵያን ካርታ በደም ቀለም ነክሮ "ሞት ይሸታችኋልና ዞር በሉ" ብሎ ዓለምን አስጠንቅቋል። "እባብ ለጠላትህ፣ ርግብ ለወዳጅህ" እንደሚባለው ሳይሆን፣ የእርሱ አስተዳደር ለህዝቡ እባብ ሆኖ ለካሜራ ግን ርግብ ለመምሰል የሚሄድበት ርቀት መጨረሻም በነጩ ቤተመንግስት በአደባባይ ተጋልጧል። ከአማራ እስከ ኦሮሚያ፣ ከትግራይ እስከ አፋር ያለውን ምድር የመከራ አውድማ አድርጎት ሳለ፣ እርሱ ግን አሁንም በፓርኮች ግንባታ ስም የሰቆቃችንን አቧራ ሊያብስ ይሞክራል። "መሸጥ ካቃተው ነጋዴ በላይ ጩኸቱ አይሰማም" እንዲሉ፣ አብይና ግብረ-አበሮቹ "ሰላም ነው" ብለው ቢጮሁም የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ምስክርነት ግን የብልጽግናን ጭንብል አውልቆ ጥሎታል። ሀገሪቱን በፈንጂ፣ በእገታና በጦርነት አረንቋ ውስጥ ዘፍቆ ስለ ሽርሽር ማውራት በቁም መቃብር ላይ የመጨፈር ያህል እብደት ነው። ይህ የአሜሪካ ማስጠንቀቂያ ግልጽ መልዕክት አለው፤ የኢትዮጵያ ህዝብ ብቻ ሳይሆን ዓለምም የአብይን የቅዠት ጉዞ ሰልችቶታል። በመጨረሻም በቲቪ መስኮት የሚረጨው የብልጽግና ፕሮፖጋንዳ መሬት ላይ ባለው የአሜሪካ ኤምባሲ የጉዞ እገዳ ድባቅ ተመትቶ ፍርክስክሱ ወጥቷል።

ስማዳ ወረዳ የኳሳ ከተማ ገዳዮቻችንን በምርጫ አናነግስም‼️
ስማዳ ወረዳ የኳሳ ከተማ ገዳዮቻችንን በምርጫ አናነግስም‼️

አገዛዙ ለሚያደርገው የሐሰት ምርጫ በእነማይ ወረዳ ዲማ እና አካባቢው ከፍተኛ የሆነ ህዝባዊ ተቃውሞ ገጠመው!! በአብይ አህመድ አገዛዝ በአማራ ህዝብ ላይ እያካሄደ ያለውን ዘር ተኮር ጭፍጨፋን በመቃወም በሁሉም የአማራ ከተሞች እና የገጠር ቀበሌዎች ላይ መጋቢት 24/2018 ዓ.ም የተቃውሞ ሰልፎቾ እየተካሄዱ ይገኛሉ። የመኖር መብቱ የተነፈገው የአማራ ህዝብ በኮ/ል አብይ አህመድ አገዛ እየተካሄደበት ያለውን ዘር ተኮር ጭፍጨፋ እና የሐሰት ምርጫ በመቃወም በእነማይ ወረዳ ዲማ እና አካባቢው ማህበረሰብ ከፍተኛ ቁጣ ቀስቅሶል። በዲማ እና አካባቢው ማህበረሰብ የአገዛዙ ምርጫን በማስመልከት በህዝባዊ ተቃውሞዎች ከተነሱ መፈክሮች ውስጥ:- ✍️የአማራ ህዝብ ለምርጫ የሚሆን ግዜ የለንም!!! ✍️አምባ ገነኑ አብይ በቃን!!! ✍️ብልፅግና በቃን!!! ✍️ብልፅግና ገዳይ ነው!!! ✍️በድሮን እና በመድፍ ለሚጨፈጨፍ ህዝብ ምረጫ ቅንጦት ነው!!! ✍️ምርጫችን ፋኖነት ነው!! ✍️ በዚህ ምርጫ የሚሳተፍ የኢትዮጵያን ህዝብ መካድ ከእውነት ጋር መጋጨት ነው!!! የሚሉ መፈክሮች በማህበረሰቡ ላይ ከፍተኛ ቁጣን ያዘለ የተቃውሞ ሰልፎች ተካሂደዋል።       መጋቢት 24/2018 ዓ.ም የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክፍለ ጦር ሕዝብ ግንኙነት

⚫️#መጋቢት_24_የመርገምት_ቀን⚫️ የሀገሪቱ 'ምክትል' ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በ2011 ዓ/ም "በነገው ቀን የመጀመሪያውን ድፍድፍ ነዳጅ እናወጣለን፣በብዙ ሚሊዮን ቶን የሚቆጠር ድፍድፍ ነው የተገኘው፣እንኳን ደስ ያለን" በሚል ተናግረው ነበር።በወቅቱ አንድ ሊትር ነዳጅ  ከ18 ብር ያልበለጠ ነበር። ተገኘ የተባለው ነዳጅም የውሃ ሽታ ሆኖ ቀረ። ከሰባት ዓመታት በኋላ የአንድ ሊትር ነዳጅ ዋጋ 164 ብር ደርሶም እሱም ቢሆን ከነ አካቴው ጠፋና "ነዳጅ ቆጥቡ" አለ። ስምንት የቀላባይነትና የዋሾነት ዘመን! ስምንት የድንቁርናና የስግብግብነት ዘመን! ስምንት የጭፍጨፋና የእልቂት ዘመን! ስምንት ኢትዮጵያ እንደ ሀገር በሁሉም ዘርፍ የተዋረደችበትና የኮሰመነችበት ዘመን! ስምንት የጦርነትና የእልቂት፡ የመፈናቀልና የመሳደድ ዘመን! ስምንት የተላላኪነትና የአጎብዳጅነት ዘመን! ስምንት ሀገር በነቢንዛይድና በሌሎች ባዕዳን እጆች ቅኝ ግዛት የተገዛችበት ዘመን! ስምንት... ስምንት... ስምንት.... ጨምሩበት። በተለይ ደግሞ ለአማራ ሕዝብ እጅግ የከፋ፡ የመከራ መቀመቅ ውስጥ የገባበት ዘመን ነው። የጅምላ ሞት፣የጅምላ መፈናቀል፣የጅምላ እስር።በድሮንና በጀት፣በመድፍና በዙ23 እየተጨፈጨፈ ያለበት ዘመን። (ይህ ሲባል፦ ከስምንት ዓመት በፊት የነበሩት ዘመናት ለአማራ ሕዝብ ብሩህ ነበሩ ማለት አይደለም። ካለፉት በርካታ አሥርት ዓመታት ጀምሮ የአማራ ሕዝብ በከባድ ሕልውና አደጋ ላይ ወድቆ ለጆሮ የሚዘገንኑ፣ ለአይን የሚሰቀጥጡ አያሌ መከራዎችን ሲቀበል ነበር። ካለፉት ስምንት ዓመታት ወዲህ ደግሞ ፀረ አማራ ትርክቶች ስጋ ለብሰው በምኒልክ ቤተመንግስት ገብተው፡ ባንክና ታንኩን ተቆጣጥረው፡ ከዚህ ቀደም በአማራ ሕዝብ ላይ የሚዘንበውን የመከራ ዝናብን ላይ ዶፍ ጨመሩበት) 24/ዐ7/2018 ዓ.ም

የአማራ ክልል ም/ት ፕሬዚዳንት ፋኖ ምሬ ወዳጆን ለማነጋገር እንደሞከረ አነበብኩ። ሰውየው የምሬን ድምፅ ለመስማት ናፍቆ ይሁን ወይም “ምሬን እኮ አናገርኩት” በማለት እራሱን ከፍ ለማድረግ አስቦ ያደ
የአማራ ክልል ም/ት ፕሬዚዳንት ፋኖ ምሬ ወዳጆን ለማነጋገር እንደሞከረ አነበብኩ። ሰውየው የምሬን ድምፅ ለመስማት ናፍቆ ይሁን ወይም “ምሬን እኮ አናገርኩት” በማለት እራሱን ከፍ ለማድረግ አስቦ ያደረገው ይሁን አላውቅም። ምሬ ለአላማው መራራ እንደሆነ እስከዛሬ ሳይገባው ቀርቶ ግን አይመስለኝም። ምሬ መረር ያለ ንግግር ተናግሮት ሸኝቶቶታል። እነዚህ ብልፅግናዎች የፋኖን ትግል የጓደኛሞች ፀብ አድርገው ነው እንዴ የሚያዩት? እንዲህ አይነት የአላማ ትግል እኮ የሚቆመው በእውነተኛ ድርድር ወይም በማሸነፍና በመሸነፍ እንጅ፣ እግር ስር እየወደቁ በመለመን አይደለም። ብልፅግና በወታደር ሞከረ፣ አልሆነም። በቄሶችና በሸሆች ሞከረ አልሆነም። እንግዲህ አረጋን ወይም አብይን ድጋይ አሸክሞ መላክና የፋኖ መሪዎች ስር መደፋትና መለመን ነው የቀረው። ይህም እንኳን ቢሆን አይሳካም። ይህ ሁሉ ደም የፈሰሰው ወይም የአማራ ህዝብ ላለፉት 3 አመታት ዋጋ የከፈለው ጥቂት መሪዎችን ወደ አመራር ለማምጣት ወይም ግላዊ ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ እንዳልሆነ ሳትረዳ፣ ሺ ጊዜ ስልክ ብትደውል፣ ሺ ጊዜ አማላጅ ብትልክ፣ ሺ ጊዜ አባል ብታስኮበልል፣ ሺ ጊዜ ፕሮፓጋንዳ ብትነዘ የሚለወጥ ነገር አይኖርም።

መጋቢት 23 ቀን 2018 ዓ.ም የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ምኒልክ ዕዝ 101ኛ ኮር የህክምና ባለሞያዎችን አሰልጥኖ አስመርቋል። የምኒልክ ዕዝ ህክምና መምሪያን ጨምሮ በየ እዞቹ ባሉ ጤና መምሪያወች የህክምና አገልግሎት እየሰጡ ያሉ ታጋይ ሃኪሞችን ከትግሉ ጋር የሚያዋህዱ ሁለንተናዊ ስልጠናዎች ይሰጣሉ። እንዲሁም ከመጀመሪያ ህክምና እርዳታ እስከ ሌሎች ቀላልና መካከለኛ ቀዶ ጥገና ድረስ በሞያው ዘርፍ የካበተ ልምድ ባላቸው አሰልጣኞች የህክምና ሙያ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል:: በዚህም መሰረት የምኒልክ እዝ 101ኛ ኮር በቀድሞ ሰማዕቱ የ11ኛ ክፍለ ጦር 3ኛ ሻለቃ አርበኛ ሃኪም አድኖ ስጦታው በተሰየመ የስልጠና ፕሮግራም ታጋይ ሐኪሞችን አሰልጥኖ አስመርቋል።

ከነዓን የሚደርሱት የታመኑት ብቻ ናቸው። ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የሆነው የእስራኤል ሕዝብ (ሴቶችና ህጻናት ሳይቆጠሩ 600 ሺህ እስራኤላዊ) ከግብጽ ባርነት ወጥቶ ወደ ከነዓን ጉዞ የጀመረው፤ ከባርነት
ከነዓን የሚደርሱት የታመኑት ብቻ ናቸው። ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የሆነው የእስራኤል ሕዝብ (ሴቶችና ህጻናት ሳይቆጠሩ 600 ሺህ እስራኤላዊ) ከግብጽ ባርነት ወጥቶ ወደ ከነዓን ጉዞ የጀመረው፤ ከባርነት ወደ ነጻነት ለመሻገር ነበር። ነገር ግን ያ ሁሉ ሕዝብ፤ ቀይባህርንና ዮርዳኖስን ተሻገረ እንጂ የነጻነትን ጎዳና ከባርነት መንገድ ሊሻገረው አልቻለም ነበር። ከጉዞው አድካሚነትና የሚጓዝበትን ዓላማ ካለማወቅ የተነሳ፤ ከግብጽ የወጣው ሁሉም ህዝብ ሜዳ ላይ ሲቀር፤ እያሱና ካሌብ ብቻ ወጣቱን ትውልድ ይዘው ከነዓን ደረሱ። የአማራ ትግልም እንዲሁ ነው። አድካሚ ጉዞ፣ የውስጥ ሽኩቻ፣ የሠርጎ ገብና የጥቅመኞች ጫና እንደተጠበቀ ሆኖ፤ በተለያዩ ምክንያቶች የእናቴ ቀሚስ አደናቀፈኝ የሚለው ይበዛል። የሆነውም ይኸው ነው። ምንም እንኳን፤ "ትግሉ ሊጠራ ነው" በሚለው ከንቱ እሳቤ ባልስማማም፤ እጅ የሚሰጡት ሁሉ እጅ በመስጠታቸው የፋኖ ትግል የድል ጉዞ እንደማይደናቀፍ አምናለሁ። ምክንያቱም፤ ትግላችን የጸና ዓላማ ይዞ የተነሳ በመሆኑ። ማስታወሻ፦ የአማራ ፋኖ ውስጡን መፈተሽና ለእውነተኛው ዓላማ እንቅፋት የሆኑ፤ መሪዎችን፣ ግለሰቦችን፣ እሳቤዎችንና አካሄዶችን በጊዜ ሊከረክም ይገባዋል። ካልሆነ፤ እየፈጩ ጥሬ እንዳይሆን ያሰጋል። Dawit Amhara ከንጉሶች መንደር ከግንባር ሰላም እደሩልኝ ጓዶች እራሳችሁን ጠብቁልኝ ሰናይ ለሌት

ከምኒልክ ዕዝ እና ከጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ የተወጣጡ የፋኖ አሃዶች በጋራ በመሆን በመቄት ግንባር የጠላትን አከርካሪ ሰብረው ድል ተጎናፀፉ‼️ ብልፅግና ምርጫ በሚል ስም ሕጋዊነት አግኝቶ ተጨማሪ የአማራ ሕዝብን እንዲጨፈጭፍና በቋፍ የምትገኘው ሀገሪቱን ወደ ባሰ አዘቅት እንዲከታት፡ ምርጫ ለማካሄድ ሲንቀሳቀሱ በነበሩ ካድሬዎችና ወታደሮች ላይ ነው እርምጃው የተወሰደው። ከመጋቢት 22/2018 ዓ/ም ጀምሮ ለሁለተኛ ቀን እየተካሄደ በሚገኘው በዚህ ተጋድሎ በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ምኒልክ ዕዝ 106ኛ ኮር ስር ከምትገኘው ከ22ኛ ክ/ጦር እና በ303ኛ ኮር ስር ከ81ኛ ክ/ጦር፣ ከ16ኛ ክ/ጦር የተወጣጡ ኮማንዶዎች እንዲሁም በድርጅቱ ስር ጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ የራስ ጋይንት ተወርዋሪ ክፍለ ጦር አርበኞች ጋር በመቀናጀት በርካታ ጠላት ኃይልን በመደምሰስ ቀሪውን ማሽመድመድና ማፍረክረክ ተችሏል። ምርጫ በሚል ስም የብልፅግናን እድሜ ለማራዘምና ተጨማሪ የአማራ ሕዝብን ለማስጨፍጨፍ፡ የአገዛዙ ካድሬዎች ከፍተኛ ቁጥር ባለው ወታደር ታጅበው ምርጫ እናካሂዳለን በሚል እየተንቀሳቀሱ ባሉበት ነው ከመጋቢት 22/2018 ዓ/ም ጀምሮ እርምጃው እየተወሰደባቸው የሚገኘው። ከመቄት ጀምሮ አግሪትና ሲሲጊ ተብሎ እስከሚጠራው አከባቢ ድረስ በተጋድሎው የጠላት አከርካሪ የተሰበረባቸው አውደ ግንባሮች ናቸው። በዚህም የበታች ወታደራዊ አመራሮችና መስመራዊ አዋጊዎችን ጨምሮ በርካታ የአገዛዙ ወታደሮች ሙትና ቁስለኛ ሲደረጉ ከጦር መሣሪያዎች ጀምሮ ወታደራዊ ቁሳቁሶች እና ገዢ ይዞታዎች በፋኖ ቁጥጥር ስር ውለዋል። ከትናንት ምሽት ጀምሮ ዛሬ መጋቢት 23/2018 ዓ/ም ሙሉ ቀን በሦስት አምቡላንስና በሌሎች ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች ቁስለኛ ወታደሮች ለሕክምና ወደ መቄት ገረገራ ከተማ እየተጋዙ ይገኛሉ። በአሁን ሰአት ውጊያው ግለቱን ጠብቆ በፋኖ ጥምር ጦር የበላይነት እየተመራ በጠላት ላይ ብርቱ ማጥቃት እየተደረገ ይገኛል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ! 23/ዐ7/2018 ዓ.ም

📌አብይ አህመድ በግራኝ አህመድ መንገድ! ታሪክ ለሚማርበት መስታወት፣ ለማይማርበት ደግሞ ድጋሚ እጣ-ፈንታ ነው። ዛሬ በአማራው ህዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለው ሁለንተናዊ ጥቃት ድንገተኛ ክስተት ሳይሆን፣ ከአምስት መቶ ዓመታት በፊት በኢትዮጵያ ምድር ላይ ተከስቶ የነበረው የግራኝ አህመድ ወረራ መዋቅራዊ ቅጂ ነው። ነብዩ ጀነራል አሳምነው ጽጌም ከመሰዋዕቱ ትንሽ ቀደም ብሎ “ከአምስት መቶ አመት በፊት የገጠመን ፈተና አሁን ገጥሞናል” እንዳለው ከአምስት መቶ አመት በፊት የነበረውን ታሪክ ስንመረምር፣ በግራኝ አህመድ የጥፋት ዘመን እና ዛሬ አብይ አህመድ በሚከተለው የፖለቲካ ስልት መካከል ያለው ተመሳሳይነት የሚገረም ብቻ ሳይሆን እጅግ የሚያስደነግጥም ነው። ተክለ ጻድቅ መኩሪያ "የግራኝ አሕመድ ወረራ" በሚለው መጽሐፋቸው ላይ እንደከተቡት፣ ያ የወረራ ዘመን ወታደራዊ ድልን ብቻ ሳይሆን የማንነት መሠረቶችን የመናድ ዓላማ ነበረው። ዛሬም አብይ አህመድ “ብልጽግና” በሚል የዳቦ ስም እያከናወነ ያለው ተግባር፣ የአማራውን ህዝብ ከታሪክ ገጽ ለማጥፋትና መዋቅራዊ በደልን ለማንገስ የቀረጸው የዘመኑ ግራኝ መንገድ መሆኑን በግልጽ ያሳያል። የግራኝ አህመድ ወረራ ስኬታማ እንዲሆን ካደረጉት ዋና ዋና ስልቶች አንዱ “የተቃጠለ መሬት” (Scorched Earth) ፖሊሲ ነበር። ተክለ ጻድቅ መኩሪያ ይህንን በዝርዝር ሲገልጹት፣ ግራኝ ህዝቡን ለማንበርከክ የከተማውን ቅርስ ማውደም ብቻ ሳይሆን፣ ሰብሉ እንዲቃጠል፣ ከብቱ እንዲታረድና የውሃ ጉድጓዶች እንዲደፈኑ በማድረግ ህዝቡን ለረሃብና ለተስፋ መቁረጥ ዳርጎት እንደነበር ያስረዳሉ። ይህንን ምስል ዛሬ ላይ ወደ አማራው ስናመጣው የምናየው እውነታ አስደንጋጭ በሆነ መልኩ ተመሳሳይ ነው። በአብይ አህመድ ትዕዛዝ የሚንቀሳቀሰው ሰራዊት በድሮንና በከባድ መሳሪያ የታገዘ የገበሬ ማሳ ውድመት ሲፈጽም፣ የግብርና ግብዓቶችን—በተለይም ማዳበሪያን—ለህዝቡ በመከልከል በረሃብ እንዲቀጣ ሲያደርግ፣ የጥንቱን ወራሪ ስልት በዘመናዊ መልክ እያከናወነው መሆኑን እንረዳለን። አባ ባህርይ በድርሰቶቻቸው ውስጥ እንደገለጹት፣ ምድሪቱ በረሃብ አለንጋ ስትገረፍ፣ ህዝቡ መጠለያ አጥቶ በየዋሻውና በየጫካው ሲረግፍ፣ መከራው ከሰይፍ የከፋ ነበር። ዛሬም አማራው በገዛ መሬቱ ማምረት እንዳይችል፣ የኢኮኖሚ ምንጮቹ እንዲደርቁና የንግድ መስመሮች እንዲዘጉ መደረጉ፣ ህዝቡን ለረሃብ በመዳረግ የፖለቲካ የበላይነትን የመጫን የግራኝ አይነት ሴራ ሲሆን፣ ይህ ስልታዊ ረሃብ በአማራው የኢኮኖሚ አቅም ላይ ለዘመናት የማይጠገን ጉዳት ለማድረስ የታቀደ ነው። ከዚሁ ጋር ተያይዞ የሚነሳው ሌላው ጉዳይ ተቋማዊ ውድመትና የታሪክ አሻራን የማጥፋት ዘመቻ ነው። ግራኝ አህመድ የአማራውን የስልጣኔ ማዕከላት፣ ጥንታዊ የብራና መጽሐፍትና የስነ-ህንጻ ጥበቦችን በልዩ ትኩረት በማውደም የታሪክ መቆራረጥ ፈጥሮ ነበር። ተክለ ጻድቅ መኩሪያ በመጽሐፋቸው ላይ እንደጻፉት፣ እነዚያ የታሪክ መዛግብት መጥፋታቸው ህዝቡ ማንነቱንና ክብሩን የሚዘክርበትን መሠረት እንዲያጣ አድርጎታል። በአሁኑ ዘመንም አብይ አህመድ በታሪክ ላይ የከፈተው ዘመቻ ከዚያ የከፋ ነው። የአማራውን ታሪካዊ አሻራዎች የማሳነስ፣ ቅርሶችን የመመዝበር፣ የትምህርት ተቋማትንና ሌሎች ተቋማትን በማፈራረስ ህዝቡን ወደ ኋላ የመጎተት ስራው፣ ግራኝ የጀመረውን የማንነት ማጥፋት ስራ ዳር ለማድረስ የታለመ ስልታዊ ግብ ነው። የአማራ ተቋማዊ መሰረት ሲናጋ፣ ህዝቡ የመከላከል አቅሙ እንደሚደክም ጠላት በሚገባ ያውቃል። አባ ባህርይ እንዳሉት፣ መሰረቱ የተናጋ ህዝብ፣ ቤቱ ለጠላት ክፍት ይሆናል። ዛሬም እየተደረገ ያለው የአማራውን ተቋማዊና ስነ-ልቦናዊ መሰረት የመናድ ስራ፣ ህዝቡን ለዘላለማዊ ባርነት ለማዘጋጀት የሚደረግ ጥረት ነው። ወደ መዋቅራዊ መፈናቀልና የስነ-ህዝብ ስርጭትን የመለወጥ ሴራ ስንመጣ ደግሞ፣ አባ ባህርይ በድርሰቶቻቸው ውስጥ በወረራው ወቅት ህዝቡ መሬቱን ጥሎ እንዲሰደድና አዲስ ኃይሎች በቦታው እንዲተኩ የተደረገበትን መንገድ በዝርዝር አስፍረዋል። ይህ ስነ-ህዝባዊ ለውጥ የማንነት ጦርነት ዋነኛ መሳርያ ነው። ዛሬም አማራው ከአዲስ አበባ ዙሪያ፣ ከወለጋ፣ ከቤኒሻንጉልና ከሌሎች አካባቢዎች በጅምላ እንዲፈናቀል፣ ንብረቱ እንዲወረስና በማንነቱ ምክንያት እንዲሰደድ መደረጉ፣ ያንኑ የጥንት ወራሪ መንገድ የተከተለ ነው። ይህ አይነቱ ስር-ነቀል የህዝብ መፈናቀል ዓላማው አማራውን አናሳና በገዛ አገሩ ድምፅ አልባ ሆኖ እንዲኖር ማድረግ ነው። ህዝብን ከመሬቱ ማፈናቀልና በኢኮኖሚ ማዳከም፣ ለወራሪው ኃይል ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል። ግራኝ ሰራዊቱን ለማስፈርና አዳዲስ መዋቅሮችን ለመዘርጋት የተጠቀመበትን ስልት፣ ዛሬ አብይ አህመድ ብልጽግና በሚል የዳቦ ስም የአማራውን መሬት ለደጋፊዎቹ በማደልና ህዝቡን በማፈናቀል እየደገመው ይገኛል። የታሪክ ድርሳናት እንዳስተማሩን፣ የውስጥ ድክመትና የባንዳነት ሚና ለወራሪው ሁልጊዜም መንገድ ከፋች ነው። ተክለ ጻድቅ መኩሪያ በዝርዝር እንደሚያስረዱት፣ ግራኝ አህመድ በድል እንዲጓዝ ከረዱት ምክንያቶች አንዱ በወቅቱ የነበሩት የአማራ መኳንንት እርስ በርስ መጠላለፋቸውና ለወራሪው ኃይል መንገድ መክፈታቸው ነው። በታሪክ ድርሳኑ ውስጥ እንደምናነበው፣ የውስጥ ሽኩቻና የስልጣን ጥመኝነት ለጠላት ትልቁ መሳርያ ነበር። ዛሬም አብይ አህመድ በአማራው ውስጥ ባንዳዎችን በማብቀልና መሪዎችን በማጋጨት የግራኝን ስልት እየተጠቀመበት ነው። በአማራው ስም የሚነግዱ፣ የህዝባቸውን ስቃይ ለስልጣናቸው ማቆያነት የሚጠቀሙ ግለሰቦች የግራኝን መንገድ እንዲቀጥል እያገዙት ነው። አባ ባህርይ በአንድ ወቅት፣ “ውስጥ ሲላላ፣ ውጭ ይበረታል። አንድነቱ የጠፋ ህዝብ ለጠላት ሰይፍ ቅርብ ነው።” ብለው እንደመከሩት፣ ይህ እውነታ ዛሬም ለአማራው ህዝብ ትልቅ የህሊና ደወል ወይም ማስጠንቀቂያ ነው። መሪነት ዝና ሳይሆን መስዋዕትነት መሆኑን የዘነጉ መሪዎች፣ ህዝቡን ለዘመኑ ግራኝ አሳልፈው እየሰጡት ይገኛል። ማንኛውም ህዝባዊ ትግል ወደ ስኬት የሚሸጋገረው በቆራጥና በብልህ መሪዎች እጅ ሲወድቅ ነው። መሪነት ከፊት መቆም ብቻ ሳይሆን፣ የሚሊዮኖችን ተስፋ በትከሻ ላይ ተሸክሞ በማዕበል ውስጥ መጓዝ ነው። በተለይም በአሁኑ ወቅት የአማራ ህዝብ ለህልውናው በሚያደርገው ትግል ውስጥ፣ የመሪዎች ሚና ከምንጊዜውም በላይ ወሳኝ ሆኗል። ተክለ ጻድቅ መኩሪያ በአፄ ገላውዴዎስ ታሪክ ውስጥ እንዳሳዩን፣ የታሪክ ባለቤትነት የሚረጋገጠው በመከራ ቀን ጸንቶ በመቆም ነው። የግራኝ አህመድ ወረራ መጨረሻው የህዝቡ ተጋድሎና የአንድነት ጽናት እንደነበረው ሁሉ፣ የዛሬውም ጭቆና የሚያበቃው በመሪዎቻችን ብልሃትና በህዝባዊ አደራው ክብደት ላይ ነው። አብይ አህመድ የግራኝን የጥፋት መንገድ ቢመርጥም፣ የአማራው ህዝብ ግን በታሪኩ ውስጥ እንደታየው ከመከራ የመውጣትና ድል የመንሳት ተፈጥሯዊ ጥበብ አለው። አብይ አህመድ የግራኝን መንገድ ቢከተልም፣ አማራው ግን የነፃነቱን መንገድ ጠርጎ መውጣቱ አይቀሬ ነው። ጨለማው ተገፎ የነፃነት ጮራ ሲፈነጥቅ፣ ታሪክ ለእያንዳንዱ ተግባር የራሱን ፍርድ ይሰጣል። አደራውን የጠበቀ ህዝብ ሁልጊዜም ያሸንፋል! ©ethio 251

ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር ባደረገው መልሶ ማጥቃት በጠላት ላይ ሰባዊ እና ቁሳዊ ኪሳራ አደረሰ ። መጋቢት 23/2018ዓ.ም በትናንትናው እለት በቀን 22/07/2018ዓ.ም መነሻውን ከጭስ አባይና ባህርዳር በማድረግ በሁለት አቅጣጫ በሌሊት ተንቀሳቅሶ በ22ኛ ክፍለ ጦር ሻለቆች ካንፕ ልዩ ስሙ ወይራ እየተባለ በሚጠራው ቦታ ላይ ከበባ አድርጎ አነጋግ 11:00 ሰዓት ላይ ጥቃት ለመሰንዘር ሙከራ ቢያደርግም ክንደ ነበልባሎቹ የ22ኛ ክፍለጦር ሻለቆች መልሰው ባደረጉት የተቀናጀ ማጥቃት ሙሉ ቀን በተደሰገው እልህ አስጨራሽ ተጋድሎ ጠላትን አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት 1ኛ,ከ54 በላይ የአገዛዙ ሰራዊት ሲደመሰስ በርካቶችን ቁስለኛ ማድረግ ተችሏል። 2ኛ,05ጥቁር ክላሽና ከ500 በላይ የክላሽ ተተኳሽ ተማርኳል። ሽንፈቱን የተከናነበው የብልፅግና ግሪሳ ሀይል ተጨማሪ ሀይል ከባህርዳር በማስመጣት ቁስለኛና አስከሬኑን እያነሳ ይገኛል። 33ኛ ክፍለ ጦር በጎንጂ ቆለላ ወረዳ ለዝርፊያና ለውድመት በወጣው የብልጽግና አጥፊ ቡድን ላይ በወሰደው የተቀናጀ መብረቃዊ ጥቃት ከፍተኛ ኪሳራ አድርሷል። 📌 የአገዛዙ ሰራዊት ከደም ድንጋይ እስከ ሸበሌ ለውንብድና ተሰማርቶ ባለበት ወቅት የክፍለ ጦሩ አንደኛ እና አራተኛ ሻለቃዎች (ወለቄ እና ዜጋንሳ)፣ በአዲስ ዓለም ከተማ በፈጸሙት ጥቃት ወደ 10 የሚጠጉ የሥርዓቱ ጠባቂዎች ሙት እና ቁስለኛ ኾነዋል። የጠላት ኃይል በገጠር ቀበሌዎች በመሰማራት የአርሶ አደሩን ቤት፣ ምርትና ገለባ በማቃጠል ላይ እያለ፣ የ33ኛ ክፍለ ጦር ሻለቃዎች አዲስ ዓለም ከተማ ገብተው የዐቢይ ታማኝ ተላላኪዎችን እስከ ዋሸራ ሎጂ ድረስ በመከታተል የማያዳግም እርምጃ ወስደዋል። የዐቢይ መዝባሪ ቡድንም በአዲስ ዓለም ከተማ ያስቀመጣቸውን ጥቁር ዐማራዎች ለማትረፍ የዘረፈውንና "መሣሪያ አምጡ" በሚል ሰበብ ያገታቸውን ንፁሃን ይዞ ወደ ኋላ ለማፈግፈግ ተገዷል። "በጥቃቅን ትንኮሳ ተተኳሽ አስጨርሰን ምርጫውን በሰላም እናጠናቅቃለን" ያለው ብልጽግናም ቃዥቶ ቀርቷል። ክፋት ለማንም! በጎነት ለሁሉም! አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ ! ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት