ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)
Kanalga Telegram’da o‘tish
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
Ko'proq ko'rsatish4 383
Obunachilar
+724 soatlar
+2667 kun
+1 44330 kun
Postlar arxiv
Tesfaye Woldesilassie:
በምሥራቅ አርሲ እንቆሎ ዋቤ ወረዳ በመጭቱ በቀቅሳ ቀበሌ ነዋሪዎች የነበሩና ኅዳር 17 ቀን 2018 ዐ ም ታግተው ከተወሰዱት 19 ኦርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖች ውሰጥ ኅዳር 18 ቀን 11 መገደላቸውን አሥራ አንድ ኦርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖች መገደላቸውን ዐደባባይ ሚዲያ ዘግባለች፡፡
ይኸ ማለት ከጥቅምት አጋማሽ ጀምሮ በምስራቅ አርሲ የተገደሉ ክርስቲያኖችን ቁጥር 69 ደርሷል፡፡ በመቶዎች አህኑም በእገታ ላይ ሲሆኑ፣ በሺህዎች ተፈናቅለዋል፣ በርካቶች በህት ንብረታቸው ተዘርፏል ወድሟል፡፡
መንግሥትም ቤተ ክህነትም ቅንጣት ታክል ሳይተነፍሱ የኦርቶዶክሳውያንን ጭፍጨፋ በማስቻል ላይ ናቸው፡፡ ሁለቱም አካላት ለፍርድ የሚቀርቡበት ቀን ሩቅ አይደለም፡፡
የአርሲ ኦርቶዶክሳውያን ደም በምድር ሰሚ ባያገኝም ወደ ሰማይ ይጣራል፡፡
#በምዕራብ_ሐረርጌ_የታፈነው_ጩኸት_እና_በአርሲ_የቀጠለው_ዘር_ፍጅት!በምዕራብ ሐረርጌ ዞን፣ ጭሮ ወረዳ፣ ላሎ ጉዶ ቀበሌ፣ ኢፈ ባስ(ifabaas) በምትባል የገጠር መንደር ውስጥ በኅዳር 15 ቀን 2018 ዓ.ም ከምሽቱ 3:00 እልፌ ተስፋ ወሌ የሚባሉ እናት በጥይት ተደብድበው ተገድለዋል። በዚኹ ቀበሌና በአጎራባች ቀበሌዎች ያብዶ ሸንበቆ፣ ረብሱ፣ ሼክ አደም፣ ሉጎ በርካታ ሃይማኖትና ማንነትን ማዕከል ያደረጉ ጭፍጨፋዎች የሚካሄዱባቸው ናቸው። ብንናገርም ሰሚ የለም። ሕዝቡና ሚዲያውም እኛን ረስቶናል ይላሉ የአካባቢው ነዋሪዎች በምሬትና በፍርኃት ተውጠው። በወረዳው በቅርቡ የአንድ ቤተሰብ አባላት የኾኑ ተፈሪ መንገሻ ከነ ባለቤቱ ቀለሟ በለጠ ጋር፣ ባለው መንገሻ፣ አሳምነው አባይነህ የተባሉ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች በአሰቃቂ ኹኔታ በስለትና በጥይት ተደብድበው ተገድለዋል፤ በርካቶችም ቆስለዋል። ግድያውን የሚፈጽመው በአካባቢው ሰዎች አጠራር ኦነግ ሸኔ(ራሱን ኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ብሎ የሚጠራው ኃይል) ነው። ይኽን መረጃ እያጣራን ባለንበት አፍታ በአርሲ ዞን በሆንቆሎ ዋቤ ወረዳ፣ በቀቅሳ ቀበሌ በአጨዳ ላይ የነበሩ ከ19 በላይ ገበሬዎች ኅዳር 18 ቀን 2018 ዓ.ም ታፍነው መወሰዳቸውን ከቦታው ለማረጋገጥ ችለናል። በዚኹ አካባቢ በቅርቡ ወንድማማቾችን ጨምሮ ሦስት ንጹሓን እንደተገደሉ ይታወሳል። እናት ፓርቲ በምዕራብ ሐረርጌ ባሉ በርካታ ቀብሌዎች በጥንቃቄ ተደብቆ የሚካሄድውን ጭፍጨፋና እገታ፤ እንዲኹም በአርሲ እየተካሄደ ያለውን ዘር ፍጅት በጽኑ እናወግዛለን፤ የታገቱትም ያለምንም ቅድመ ኹኔታ እንዲፈቱ እንጠይቃለን። ፈጣሪ አገራችን ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ! እናት ፓርቲ ኅዳር ፲፱ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
እንደሻው አያል ይባላል ምስራቅ ወለጋ ዞን ጊዳ አያና ወረዳ አንገር ጉትን ከተማና አካባቢዋ ላይ አሉ ከሚባሉ የአማራ ነጋዴ ባለ ሀብቶች ግንባር ቀንደም ነበር ከስራ በስተቀር ፖለቲካ በሚወራበት አካባቢ አይደርስም ቡና ቤት ተቀምጥ እንኳን ፖለቲካ ወሬ ከተጀመረ ተነስቶ ይሄዳል ከስራው በስተቀር ምንም አይነት ወሬ የማያውቀው ይህ አመለ ሸጋ ባለሀብት በፋኖ አሳባው ከወር በፊት አንገር ጉትን ከተማ ላይ ለጥያቄ ትፈለጋለህ ተብሎ የተያዘ ሲሆን ከተያዘ ጀምሮ አድራሻው መጥፋቱንና ቤተሰቦቹ ተደጋጋሚ ለመጠዬቅ ወደ ከተማ አስተዳዱሩ ፖሊስ ጣቢያ ቢሄዱም ጥፉ የት እንዳለ አናውቅም ተብለው መባረራቸውን ቤተሰቦቹ ገልጸውልናል።ምንም ሁን ምን አማራ ከሆንክ አይምሩህም።
#መርጦ አልቃሽና አዛኝ መሳይ መንጋ!
#ማንም ይቁረጠው ማን እጅ ሲቆ''ረጥ ስታይ አሳዝኖሀል አይደል? አጀንዳ አድርገኸዋልም አይደል? መፈጠርህን ሁሉ አስጠልቶሀል አይደል ?
እውነት ነው! ያሳዝናልኮ!😥
ታዲያ ግን ፦
#ጡት በሳ'ንጃ ሲዘ'ለዘል ስለምን እንዲህ አላብከነከነህም?
#እናት ልጇን እንደታቀፈች በድሮን ጥቃት ወደከሰልነት ስትቀየር ስለምን ስቅስቅ ብለህ አላለቀስክም ?
#አርሷደር ሞፈር እንደጨበጠ እርሻው ላይ ሲረ'ሸን ስለምን አንጀትህ አልተንሰፈሰፈም ?
#የቆሎ ተማሪ እየተሰበሰበ ጥይት እንደቆሎ ሲዘንብበት '' ምነው ፈጣሪ ሆይ! ኢትዮጵያን የግፍ ምድር አደረካት?'' ስትል አንጋጠህ እንኳ አላነባህም?
#ህፃናት በቡድን ተደፍረው በአሰቃቂ ሁኔታ ሲገደሉ እንዴት ''እግዜዮ አምላኬ ፣ ያ አላህ ..!'' ብለህ አላለቀስክም ?
#ወጣቶች እየተለቀሙ ''faኖ ናችሁ'' ተብለው በሰልፍ ሲረሸኑ እንዴት ''በቃ!'' ብለህ ማንባት አልቻልክም?
#ዜጎች አማራ በመሆናቸው ብቻ በቤት ውስጥ ተሰብስበው በጅምላ እሳት ሲለቀ''ቅባቸው ፣ በቢላ ሲታ''ረዱ ፣ ተሰብስበው ሲረ''ሸኑ ፣ ስለምን ሰዋዊ ህሊናህ ሞግቶህ ወደህግም ወደፈጣሪም መጮህ አቃተህ ?
#መተከል ላይ የሰው ልጅ በማንነቱ ታር''ዶ ኩላ''ሊቱ ሲበላስ አልሰማህም ይሆን ?
''ሬሳ ክቡር ነው'' በሚል ማህበረሰብ ውስጥ ገድለው አስከ'ሬንን መጫወቻ ሲያደርጉትስ ጥቂት እንኳ ሀዘን አድሮብህ ይሆን ?
#በምድር ላይ ተፈፅሞ በአማራ ህዝብ ላይ ያልተፈፀመ ሰቆቃ አለመኖሩን አስታውሰህ ቁጣህ ገንፍሎ ፣ እንባህ እንደጅረት ወርዶ ፣ ጣቶችህ የሀዘን ቃላትን ከትበውስ ያውቁ ይሆን ?
#እንደዚያ ከሆነ እመነኝ! ዛሬ እጅ ሲቆ''ረጥ ያዘንከው ሀዘን እርግጥም ከሰብአዊ ስሜት የመነጨ መሆኑን ቅንጣት አልጠራጠርህም!
@save amhara fano
አባ ዮሴፍ የብልጽግናን አንብሮተ እድ ከሚጠባበቁ ከጵጵስና ሰልፈኞቹ አንዱ ናቸው።
አባ ዮሴፍ የሰላም ካውንስል ሰብሳቢ የሆኑትም ለዚሁ ፐርበዝ ነበረ።
በእርግጥ አባ ዮሴፍ በጣም ሰፈርተኛ ከፋፋይ መንደርተኛም ናቸው።
የጎንደርን ሊቃውንት በመጀመሪያ በሰፈር ከፋፈሉት ቀጥሎ ሃይማኖት፣አቋም፣ አቅምም ያላቸውን አባቶች የማሳደድ ስራቸውን ጀመሩ።
አባ ዮሴፍ ብልጽግና ያላዘዛቸውን አንዳችም አይሰሩም አባሩ ያላቸውን ያባርራሉ አሳስሩ ያላቸውን ያሳስራሉ።
አባ ዮሴፍ አማን የሚባል ወንድም ነበራቸው በፊት ከጎጃሞች ጋራ ነበረ በሗላ ወደ ደቡብ ጎንደር መጣ ቀጥሎ እጅ ሰጠ አሁን ደሞ ድራማውን ጨርሶ ወደ ፋኖ ገብቷል።
አባ ዮሴፍ ፓጋን ጋንግስተር ሰው ነው እንጂ ሃይማኖት የለውም።
አባ ዮሴፍ ቅማንትና አማራ የሚለውን ፖለቲካም ከሚዘውሩት አንዱ ነው
ጆሲ በጽድቁ አይገኙም እንጂ እሳቸው የሌለበት የሴራ ሰፈር አይገኝም
አሁን ቤተ ክርስቲያን ላይ በማደረገው የጎንደርን ወጣት ፈርቻለሁ ጠባቂ መድቡልኝ ብለዉ ሁለት አጃቢ ተመድቦላቸው እስከ መቅደስ ድረስ እየሄዱ ነዉ
ሰበር ዜና
የሸኔው አውራ ክፉኛ ቆስሏል
ሰኚ የተባለው አመራር ተሰናብቷል
ሀገር ማተራመስና ንጹሐንን መግደል የትግል ስልት በማድረግ የሚታወቀው የሸኔ አሸባሪ ቡድን አውራ ለጥቂት ከሞት እንዳመለጠ ታማኝ የመረጃ ምንጮች አስታወቁ፡፡
በቄለም ወለጋ ዞን ቄለም አካባቢ አሽንፋ የተባለ ቦታ ሲንቀሳቀሱ በነበሩ የቡድኑ ከፍተኛ አመራሮች ላይ ኅዳር 10 ቀን 2015 ዓ.ም በተወሰደው እርምጃ የሸኔ መሪ ነኝ የሚለው መሮ (ኩምሳ ድርባ) ከፍተኛ የመቁሰል አደጋ ደርሶበት በሞትና ሕይወት መካከል የሚገኝ ሲሆን፤ ሰኚ የተባለው የቡድኑ ቁልፍ አመራር ደግሞ መሞቱ ታውቋል።
በቡድኑ አመራሮች ላይ የተወሰደው ድንገተኛ ጥቃት በታጣቂው ዘንድ ከፍተኛ መደናገጥ መፍጠሩንና የስነ ልቦና ጫና ውስጥ እንደከተታቸው የሚገልጹት በስፍራው የሚገኙ ታማኝ የመረጃ ምንጮች፤ ክስተቱ በቡድኑ አመራሮች መካከል መጠራጠር እንዲፈጠር ማድረጉን ያመለክታሉ፡፡ በተለይ በመሮ ዙሪያ ከሚገኙ አመራሮች እና ጠባቂዎች መካከል ለመንግሥት አካላት መረጃ የሚሰጡ ይኖራሉ የሚለው መላምት አንዱ ሌላውን እንዳያምን እርስ በእርሳቸውም እንዲወነጃጀሉም እያደረገ መሆኑን ይጠቁማሉ።
መሮ ሕክምና የማያገኝ ከሆነ በደረሰበት ከፍተኛ ጉዳት ምክንያት ሕይወቱ ሊያልፍ እንደሚችል በቅርቡ ያሉ ሰዎች እየገለጹ መሆኑን ከታማኝ ምንጮች የተገኙ መረጃዎች ያመለክታሉ።
@Fanomediaa
ጎዣም ‼️ ጠላት በሌሊት እንቅስቃሴ ሊያደርግ ጓዙን ሸክፏል።
መላው የወገን 77ኛ & 88 ኛ ክ/ጦር ጥንቃቄ አይለይህ !!!
ወንበርማ፣እሁዲት፣ጓጉሳ፣አችጊ፣ቡሬ ዙሪያ አጠቃላይ የገጠር ቀበሌዎች።
🔥#በሶስት_ግንባር_በተካሄደው #አውደ_ዉጊያ_ጨፍጫፊው_ተጨፍጭፏል‼
በአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 105ኛ ኮር በ44ኛ ክፍለ ጦር በወሰእርምጃ አረመኔ ቡድን በባንጃ ወረዳ ሱርታ፣ ምርክታና ዣንኩታ ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ተጨፈጨፈ።
#ጡት #ምላስና #ብልት ቆራጩ አረመኔው ሀይል በጠዋቱ ከሰከላ በመነሳት ወደ እንጅባራ ዙ23፣ ሞርታርና ድሽቃወችን ጨምሮ ብዛት ያለዉን ጥምር ሀይል በመያዝ ሬሽን ለመቀባበል በሚል እየተንቀሳቀሰ በነበረበት ሰሃት ሱርታ ሚካኤል ላይ በ44ኛ ክፍለ ጦር በደፈጣ የተጀመረዉ ጥቃት ወደ መደበኛ አውደ ዉጊያ ተሻግሮ ከጥዋት 4:00 እስከ ምሽት 11:00 ዘልቆ የጠላት ሀይል በቦምብ ጭምር ተጨፍጭፏል።
በተመሳሳይ ሁኔታ ከእንጅባራ በሁለት አቅጣጫ የወጣዉን የመከላከያ ዘራፊ ቡድን እንጅባራ ከተማ ስር #ምርክታና #ዣንኩታ ላይ በተፈፀመ የደፈጠ ጥቃት ከ10 በላይ ዙፋን ጠባቂ ተወግዷል።
ከሰሞኑ ሰከላ ወረዳ #አጉት ቀበሌ በዚህ ከሰከላ በተነሳው አረመኔ ሀይል ብዛት ያላቸዉ ንፁሃን ገበሬዎችና ወጣቶች ታፍነዉ ሲወሰዱ ከታፈኑት ውስጥም ስድስቶቹ ምላሳቸዉን እና ብልታቸዉን እንዲሁም የተለያየ የአካል ክፍላቸዉን በመቆራረጥ አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ እንደ ተፈፅመባቸዋው አይዘነጋም።
በተደጋጋሚ በሄደበት አካባቢ ሁሉ እንደ ተለከፈ ውሻ ያገኘውን የአማራን ህዝብ እያረደ ሲበላ፣ ሲጨፈጭ የቀጠለዉን ወንበዴ ቡድን በ44ኛ ክፍለ ጦር ከሁለት ቀን በፊት በደርዘን ተማርኮ፣ ብዙ ሬሳ ጥሎ፣ ቁስለኛ አንጠልጥሎ እንዲሄድ የተደረገ ቢሆንም ዛሬም እንደ ልማዱ ህዳር 18/2018 ዓ.ም ከሰከላ እንጅባራ እየተንቀጠቀጠ ለማለፍ ሲሞክር በጀግኖቹ 105ኛ ኮር 44ኛ ክፍለ ጦር ነበልባሎች ተለብልቦ ከ20 በላይ ሬሳ ጥሎ ብዛት ያለዉን ቁስለኛ ተሸክሞ ወደ መጣበት ሰከላ ከተማ ተጨፍጭፎ እንዲፈረጥጥ ተደርጓል።
ያለምንም ጉዳት በተካሄደዉ አውደ ዉጊያ ጠላት ከባድ መሳሪያዎችን ቢጠቀቀምም እንኳ ከሞትና ከመፈርጠጥ አልዳነውምም።
ስለሆነም የተጀመረዉን ተናበባዊ ጥቃት በማጠናቀር በቅርቡ የጠላትን አከርካሪ ሰብረን አስደማሚ የሆነ ድል የምናበስር ይሆናል።
የወንድሞቻችንና የእቶቻችን ደም ምለሳም ተጠናክሮ ይቀጥላል።
©የ44ኛ ክፍለ ጦር ህዝብ ግንኘነት ፋኖ አለበል አወቀ
18/ዐ3/2018 ዓ.ም
የአማራ ፋኖ ጉዳይ መረጃ ከፈለጉ ከታች ካሉት የቴሌግራም ቻናል join ያድርጉ👇👇👇👇
Ab 1
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
Ab 2 https://t.me/abcdefghijklmnopqrstuvwxyz071167
Ab 3
https://t.me/minilik28
24/7 መረጃ ለማድረስ ዝግጁ ነው ለሌሎችም share በማድረግ የገባነው ትግል ዳር እናድርስ💪🔥
+3
ከግሸን እስከ ጅብጎዶ ቀበሌ ድረስ በተደረገ ተጋድሎ የጠላት ኃይል ከባድ የሆነ የሰብአዊና ቁሳዊ ኪሳራ መከናነቡ ታውቋል‼️
በውጊያው ከተገደሉ የአገዛዙ ወታደሮች መካከል የጥቂቶቹን አስከሬን ተመልከቱ።
ብልፅግና የድሀን ልጅ በግዴታ እያመጣ በየሜዳው የአሞራና የአውሬ ቀለብ እያደረጋቸው ቀጥሏል ፣ የኢትዮጵያ ህዝብ ልጆቹን ለአገዛዙ ስልጣን እየገበሩ ቀጥለዋል‼️
18/ዐ3/2018 ዓ.ም
ሰበር የድል ዜና!
ምኒልክ ዕዝ ልጅ ዕያሱ ኮር 23ኛ ክ/ጦር በቀን 17/03/2018 ዓ/ም ጀምሮ በተጀመረውና ተጠናክሮ በቀጠለው ተጋድሎ በጊሸን እና አባላ ሰፍሮ የነበረዉ ሰሜን ምስራቅ ዕዝ 801ኛ ኮር 45ኛ ክ/ጦር የብልፅግናዉ አራጂ ቆራጭ ሰራዊት አዳሩን 23ኛ ክ/ጦር ወደ ምትንቀሳቀስበት ቀጠና ተጉዞ ወደ ደልባ ለመግባት ቢሞክርም ቀድመዉ በአናብስቶቹ እና በአይበገሬዎቹ በ23ኛ ክ/ጦር በወገን ኃይል ተብትቦ የተያዘ እና ስቦ በመስገባት ታክቲክ አይበገሬዎቹ የአሳምነዉ ግልገል የብልፅግናዉ ሠራዊት የአሞራ ሲሳይ ሁኖ አንዲቀር አድርጎታል።
ዉጊያዉ ከቀኑ 5:30ስዓት እስከ ምሽት 5:10 ስዓት የተካሄደ ሲሆን የመጣዉ የአብይ ሰራዊት ዘለህ ግባ በሚባል ሁኔታ ተስቦ እንድገባ ከተደረገ ቡኃላ መመለስ እንዳይችል አድርገዉ ከቀኝም ከግራም በአናብስቶቹ አይቀጡ ቅጣት ሲቀጣ ዉሎል።
ነገር ግን በአለም የቱሪስት መስህብ ዉስጥ የምትታወቀው ጊሸን ደብረ ከርቤ ገዳም ዉስጥ ከትሞ የሚኖር አስነዋሪዉ የብልፅግና ሰራዊት ከገዳሙ ዉስጥ ሁኖ ሞርተር እያሰወነጨፈ ወደ ኋላ ለማዉጣት ቢሞክርም መዉጣት እንደመግባት ቀላል አይደለም እና የአብይ ሎሌዎች ብዙ የድሀ ልጆች ድንጋይ ተንተርሰዉ እስከ ወዳኛዉ እንደሸኙ አድርጓቸዋል።
በአዉደ ዉጊዉ የተገኙ ድሎች
1. ከ50 በላይ የተደመሰሰ እና ቁጥሩ በውል ያልታወቀ ቁስለኛ
2. 650 የክላሽ ተተኳሽ
3. 450 የብሬን ተተኳሽ
4. 295 የድሽቃ ተተኳሾች ገቢ ሁኗል:: እንደሁም አንድ የጥላት ሀይል በአመራር ደረጃ አብሮ ተሰዉቶል።
ከ 4 መኪና በላይ ቁስለኛ ይዞ ወደ ደሴ ለመግባት ቢሞክርም በቀን 18/03/2018 የ 23ኛ ክ/ጦር ቃንኝ ቁስለኛ ይዞ እንዳይወጣ በድጋሚ ዚሃ ላይ ጥቁር አሰፍልቱን ዘግተዉ አነብስቶቹ እየገረፉት ነዉ።
እሬሳ እንኳን ማንሳት በማይችልበት ሁኔታ እግሬ አዉጭኝ ብሎ ኮብልሎል።
የአለም የጦር ህግ በአስቀመጠዉ የሁለት ተፋላሚ ሀይሎች የማርኩትን የጥላት ሀይል በህግ አግባብ መያዝ የግድ ይላል እና እኛም የቆሰሉ የተሰዉ የተማረኩ የጥላት ሃይል የተሰዋዉን ማስቀበር የቆሰለዉ ህክምና እንዳገኝ የማድርግ ስራ እየሰራን እንገኘለን።
መዳረሻዉ ድል እና ነፃነት የሆነዉ የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልዉናችን በተባበር ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒሊክ ዕዝ ልጅ እያሱ ኮር ህዝብ ግንኙነት
ህዳር 18/2018 ዓ.ም
ከወልድያ ከተማ በቅርብ ርቀት ምንም አይነት የጥይት ድምፅ ያልተሰማበት ውጊያ ተካሄደ!
ከወልድያ ከተማ በቅርብ ርቀት በታሪካዊቷ መርጦ እየሱስ ከተማ አጥቢያ ለሊቱን ያለ ምንም የጥይት ተኩስ በሳንጃ ጩቤ ብቻ ለአጭር ሰዓታት ከባድ ተጋድሎ መደረጉ ታውቋል።
ምኒልክ ዕዝ፡ የራስ ወሌ ብጡል መናገሻ በነበረችው በታሪካዊቷ መርጦ እየሱስ ከተማ ውስጥ መሽገው በነበሩ የአገዛዙ ወታደሮች ላይ ዛሬ ህዳር 18/2018 ዓ/ም አጥቢያ ለሊቱን ባካሄደው በሳንጃ ጩቤ በታገዘ ለአጭር ሰዓታት በቆየ ከባድ የጨበጣ ውጊያ ታላቅ ድል መቀዳጀቱን ዕዙ በሕዝብ ግንኙነት መምሪያው በኩል ለመረብ ሚዲያ በላከው መረጃ አስታውቋል።
በአፋብኃ ምኒልክ ዕዝ ዞብል አምባ ክ/ጦር ስር የሚገኙት "ተወርዋሪ አናብስት" በሚል ቅፅል ስም የሚጠሩት የ6ኛ ሻለቃ አባላት፡ የራስ ወሌ ብጡል መናገሻ በነበረችው በታሪካዊቷ መርጦ እየሱስ ከተማ ዛሬ አጥቢያ ለሊቱን ሰርገው በመግባት በከተማዋ የነበሩ የጠላት ብልፅግና ቡድን ተላላኪ ወታደሮች ላይ የሳንጃ ጩቤ ጥቃት በመክፈት በርካታ ወታደሮችን ሲገድሉ አንድ የሻምበል መሪንና ሌሎች የክፍለጦር አመራሮችን አንገታቸውን አንቀው ይዘዋቸው ወጥተዋል።
ምንም አይነት የጥይት ድምፅ ባልተሰማበት በዚህ የአጭር ሰዓት የሰርጂካል ኦፕሬሽን፡ የፋኖ አባላቱ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮችን እስከ አጃቢዎቻቸው በመግደል እንዲሁም የሻምበል አዛዡንና ሌሎች የጠላት አመራሮችን ከሶስት ጥቁር ክላሽ ጋር ማርከው ይዘዋቸው ወደ ቀጠናቸው መሄዳቸውን ነው ምኒልክ ዕዝ ለመረብ ሚዲያ በላከው መረጃ ያስታወቀ።
ውጊያው ያለምንም የጥይት ኮሽታ የተካሄደ ነው የተባለ ሲሆን፡ የፋኖ ኃይል ወደ ጠላት ካምፕ ዘልቆ መግባቱ የታወቀው ደረታቸው ላይ የፋኖ ሳንጃ የተሰካባቸው ወታደራዊ አመራሮችና አጃቢዎቻቸው የሲቃ ድምፅ ሲያወጡ ብቻ ነው ተብሏል።
የፋኖ አባላቱ የገደሉትን ገድለው የማረኩትን ማርከው ተልዕኳቸውን አጠናቀው ከወጡ በኋላ: "ጅብ ከሄደ ውሻ ጮኸ" እንዲሉ አበው፡ ሙትና ቁስለኛ ከመሆን የተረፈው የአገዛዙ ኃይል በከተማዋ ዙሪያ የሚገኙ ተራሮችን በድሽቃና በሞርተር ሲደበድብ እንደነበርም መረብ ሚዲያ ለማረጋገጥ ችሏል።
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ ፩ ኮር በፍቃዱ በላይ ክፍለ ጦር አሳምነው ፅጌ ብርጌድ አናብስቶችን ለማፈን ጥርት ለማድረግ አልሳካለት ያለ የአብይ አህመድ ወንበር አስጠባቂ ኃይል በደራ አውራጃ በሜካናይዝድ በታገዘ ንፁሃንንና ከአስራ አምስት በላይ ከብቶችን ጨፈጨፈ።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በቀን 15/03/2018 ዓ.ም እድሜያቸው የ13ና የ14 አመት ልጅች አፍኖ እርጅም መንገድ በእግራቸው ይዞ ከሔደ ቀኃላ በአሰቃቂ ሁኔታ የአብይ አህመድ እና የብአዴን ተላላኪ ኃይል አሁንም እንደትናንቱ ለአማራ ህዝብ አረመኔያዊ ተግባሩን አሳይቷል።
እንዲሁም በአለም አቀፉ ህግ አንድ ሰራዊት ሲማረክ በወታደራዊ ጥበብ መያዝ ሲችል ከዓፄ ዘርዓ ያዕቅብ ፩ ኮር በፍቃዱ በላይ ክፍለ ጦር አሳምነው ፅጌ ዕዝ በአብይ አህመድ እጅ የወደቁ ሁለት ፍኖዎችን ከአንገታቸው በላ ያለው የሰውነት ክፍላቸውን ከሁለት ሰንጥቆ አረመኔያዊ ተግባሩን እየሰራ ከመሆኑም በላይ አሁንም በደራ አውራጃ የማህበረሰቡ የሰብል መሰብቢያ ወቅት በመሆኑም የአሳምነው አናብስቶች በትር መቋቋም ሲያቅተው በሞርተር የተሰበሰበውን ከሰባት በላይ የጤፍ ክምሮችንና አራት የህብረተሰብ ቤቶችን አቃጥሏል።
ሁኖም ደራ ከኦሮሚያ አዋሳኝ ቦታ እንደመገኘቷ አብይ አህመድና ሽመልስ አብዲሳ በአዋቀሩት የዳቦ ስም የሚሰጡት ኦነግ ሸኔ በሆነው ሰው በላ ኃይል የአማራን ህዝብ ልክ እንደ ሌሎች እንደ አርሲ፤መተከል፤ወለጋ ለማጥፋት እየሞከረ ይገኛል።
በመጨረሻም የዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ ኮር በፍቃዱ በላይ ክፍለ ጦር አሳምነው ፅጌ ክፍለ ጦር አናብስቶች በደራ አውረጃ እየከፈሉት ያለ ይብል የሚባል ሲሆን ይህን አረመኔያዊ አገዛዙ በአማራ ህዝብ ላይ የሚያደርሰውን ስቃይን እንግልት ከላያችን ላይ አውርደን የምንጥልበት ቀን ቅርብ ይሆናል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን
መረጃው የአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጣና አሳምነው ዕዝ አፄ ዘርያዕቆብ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ነው
ህዳር 18/03/2018 ዓ.ም
አብይ ጋር የሚታዩት የጊኒ ቢሳዋ ፕሬዚዳንት ኡማሮ ሲሶኮ በትናንትናው ዕለት በሪፐብሊካን ጋርዶቻቸው መፈንቅለ መንግስት ተደርጎባቸው ወደ ወህኒ ተወርውረዋል።
ፕሬዚዳንት ሲሶኮ ወደ አዲስ አበባ የመጡት በቅርቡ ነበር።
አንድ መሪ ወደ ውጭ ሀገራት ለጉብኝት መሄዱ ወይም ከሌሎች ታላላቅ መሪዎች ጋር መገናኘቱ ለሥልጣኑ ጥንካሬ ምልክት ወይም አስተማማኝ ምሳሌ አይደለም።
ጋዳፊ ላይ ምዕራባውያኑ " መርሲነሪ'ዎችን ጭምር በማሰለፍ ከሥልጣን እንዲወገዱ ያደረጓቸው የወቅቱ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ጋር ተገናኝተው በሰፊው መጨዋወታቸው የዓለም ዜና ከሆነ ከወራት በኋላ ነው።
ከራስህ ሕዝብ ጋር ዐይን እና ናጫ ሆነህ ከሌሎች ሀገራት መሪዎች ጋር ፎቶ በመነሳት ፕሮፓጋንዳ ለመሥራት መሞከር፤ ከመጣው አደጋ አያተርፍም።
