uz
Feedback

Firibgarlarga uchmang! Telemetrio bunday kanallarni topadi va belgilaydi 👉 Belgini ko‘rmoqchi bo‘lsangiz, obuna bo‘ling 👈

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

Kanalga Telegram’da o‘tish

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

Ko'proq ko'rsatish
4 133
Obunachilar
+224 soatlar
+4237 kun
+1 19130 kun
Postlar arxiv
#ትኩረት_የሚሻ_አሳዛኛ_መረጃ እንደሚታወቀው በትናንትናው እለት በማህበራዊ ሚዲያ ሰፊ ሽፋን ተሰጦት የነበረው የጣና ገዳማት ጉዳይ በጀግኖቹ ሻለቃ አቢ እና ሻለቃ ዳንኤል ሀብታሙ እየተመራ ሁለት የአገ
+2
#ትኩረት_የሚሻ_አሳዛኛ_መረጃ እንደሚታወቀው በትናንትናው እለት በማህበራዊ ሚዲያ ሰፊ ሽፋን ተሰጦት የነበረው የጣና ገዳማት ጉዳይ  በጀግኖቹ ሻለቃ አቢ እና ሻለቃ ዳንኤል ሀብታሙ እየተመራ ሁለት የአገዛዙን የባህር ኃይል ኮማዶ ተብየ የጫኑ ተዋጊ ጀልባዎች ማስመጥ የቻሉ ሲሆን ገዳማቱንና ማህበረሰቡን ለመታደግ ሲባል የወገን ኃይል ከቀጠናው መውጣቱን የገለጽን ቢሆንም በዛሬ እለት ደግሞ የወገን ኃይል በሌለበት ሁኔታ በጣና ገዳማት ላይ ኃይለኛ የሆነ የከባድ መሳሪያ ድብደባ ተፈጽሟል። ድብደባው የተፈጸመባቸው ገዳማት            1.ዳጋ እስጢፋኖስ            2.ወባ ኪዳነ-ምህረት            3.ደቅ አርሴማ            4.ኮታ ማርያም            5.ናርጋ ስላሴ በተጨማሪ የደቅ ማህበረሰብ  ጠላት "አንይህ" በማለት ወደ ተለያዩ አጎራባች ገዳማትና ቀበሌዎች በጀልባ የሸሸ ቢሆንም በእድሜ አጋፋ የሆኑና በአልጋ ቁራኛ በጽኑ በህመም ላይ የሚገኙትን እያሰቃየ ይገኛል። የተዘጉ ቤቶችን እያፈራረሰ ሙሉ የቤ እቃ ዱቄትና ሊጥ ሳይቀር ጀልባ አስጠግቶ እየጫነ ስለሆነ ድምፅ ትሆኑ ዘንድ አማራዊ መልዕክታችን ነው። የሰሜን ጎጃም ሀገረ ስብከትና የባህርዳር ሀገረ ስብከት በገዳማቱ ፣ በመነኮሳቱ ፣ በደቅ ደሴት ማህበረሰብ ላይ የሚፈጸመው ግፍ ባለማውገዛችሁ በአባትነታችሁ አፍረናል። ድል ለአማራ ፋኖ አዲስ ትውልድ ፣ አድስ አስተሳሰብ ፣ አዲስ ተስፋ ፋኖ ዳዊት ሽፈራው

ሰበር ዜና! ጎንደር ሪፈራር ሆስቲታል ህክምና ላይ የነበሩ 37 የአገዛዙ ስልጣን አስጠባቂ ሀይሎች መሞታቸው ተረጋገጠ ። የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል (አፋብኃ ) ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ ሰሞኑን በአጅሬ ጃኖራ ፣ በሚጦ ፣ ጦሃ ቀበሌ እና በሌሎች ቦታዎች በተደረጉ አውደ ውጊያዎች የአገዛዙ ብልፅግና ሆድ አደሮች በርካቶች በሞት ሲሸኙ የተቀሩት ደግሞ ከከባድ እስከ ቀላል ቁስለኛ ሁነው በቀጠናው ያሉ ሆስፒታሎችን እያጨናነቁ ይገኛል ።በቀጠናው ከሚገኙት ሆስፒታሎች መካከል አንዱ በሆነው ጎንደር ሪፈራል ሆስፒታል ለህክምና ከገቡት ቁስለኞች መካከል ዛሬ ጣት የሞቱትን ሶስት የሚኒሻ አባላትን ጨምሮ ከ37 በላይ የሚሆን የአገዛዙ ጡት ቆራጭ ሀይል አንድ ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ እስትንፋሳቸው መቋረጡ ተረጋግጧል። አንድ ስማቸው እንዳይገለፅ የጠየቁ የሆስፒታሉ ዶክተር ብዙ ጊዜ ለህክምና ከሚመጡት ቁስለኞች አብዛኛዎቹ ይሞታሉ ምክንያቱ ደግሞ ቁስለኞች ከአውደ ውጊያ ግንባሮች ሆስፒታል ሳይደርሱ ብዙ ደም ስለሚፈሳቸው እና በእነሱ የህክምና ሙያተኞች የሚሰጧቸው የመጀመሪያ ህክምና እርዳታ በቂ አለመሆኑ ተዳምሮ ለሞት ያበቃቸዋል ይላሉ ። አሁንም ጎንደር ሪፈራል ሆስቲታል በቁስለኞች በመሞላቱ ዛሬ ተህሳስ 26/2018 ዓ/ም 29 ቁስለኞ ወደ አይራ ሆስፒታል ተልከዋል ከ10 በላይ የሚሆኑት ቁስለኞች ደግሞ አሁንም ማንቂያ ክፍል እንደሚገኙ ጠቅሰው የሟቾች ቁጥር ከዚህ በላይ ሊያሻቅብ እንደሚችል ስጋታቸውን ጠቁመዋል ። ዶክተሩ የጎንደር ሪፈራል ሆስፒታል ሙያተኞች ቁስለኞቹ እንደሚመሞቱ እያወቁ በመከላከያ ሰራዊቱ ጫና የተነሳ በርካታ መዳህኒቶችን ለሟቾች እየባከኑ በመሆኑ ሌሎች በህይዎት የሚድኑ መደበኛ ታካሚዎችን በመዳህኒት እጥረት እና በስራ ጫና የተነሳ ማዳን አልቻልነም ይላሉ ። በመጨረሻም ዶክተሩ የአገዛዙ ሀይሎች የህክምና ጉዳይ በሆስፒታሉ አስተዳደሮች ውሳኔ ካልተሰጠበት በቅርቡ ሆስፒታሉ በመዳህኒት እጥረት ሙሉ በሙሉ መደበኛ ስራው ሊቋረጥ እንደሚችል ጠቁመው ይህ ድርጊት ጎንደር ዩኒቨርስቲ ከህብረተሰቡ ጋር ያለውን ጥሩ ግንኙነት ሊያሻክረው እንደሚችል ስጋታቸውን ጠቁመዋል። ጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር አለማቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች ለጤናው ዘርፍ የምትሰጡት እርዳታ እና ድጋፍ የት እየደረሰ ለምን አገልግሎት እየዋለ እንደሆነ በአግባቡ እንድትመረምሩ እና ለህብረተሰቡ ጤና እንድትጨነቁ ስንል ማሳሰብ እንወዳለን ። በተያያዘ ዜና ለስብሰባ የመጣው የአገዛዙ አመራር ስብሰባውን አቋርጦ ፈረጠጠ። የጎንደር ከተማ አንድ አካል በሆነችው ጠዳ ከተማ እግዚአራብ ቤተክርስቲያን ላይ የነበሩ ምዕመናንን ፋኖን ምረሽ እንድታስገቡ ብሎ ለማስፈራራት እና ለማሰር ዛሬ ተህሳስ 26/2018 ዓ/ም የመጣው የአገዛዙ ዘራፊ አመራር በጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር ቃኘው ብርጌድ አባላት በተከፈተበት ተኩስ ስብሰባውን አቋርጦ እስኪያልበው ድረስ ፈርጥጦ መገጭ ግድብ ገብቷል። የቃኘው ብርጌድ አባላት ለምዕመናን ጥበቃና እንክብካቤ በማድረግ በሰላም ወደ ቤታቸው እንዲመለሱ አድርገዋል። ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን !!!! አርበኛ  ታድሎ ደሴ (ካስትሮ ) የጎንደሬ በጋሻው ክ/ጦር ህ/ግን /ኃላፊ ታህሳስ 26/2018 ዓ/ም ከጎንደር ሰማይ ስር

አማራዎች ነን የዘሜ ልጆች!! እሳት በሚያዘንበው የጎጃም ምድር 25ኛ ክ/ጦር ሙሉ ለሙሉ ተደምስሳለች። 206ኛ ኮር ታህሳስ 26/2018 ዓ.ም =================================== የአረመኔው ሰራዊት በጠና መልኩ የ6ኛ ዕዝ 602ኛ ኮር 25ኛ/32ኛ/57ኛ ክፍለጦሮችን በማሰማራት ወደጮቄ ተራራ ለመውጣት ባደረገው እንቅስቃሴ 206ኛ ኮር 24ኛ ክ/ጦር ታህሳስ 24እና 25 ባደረገው ትንቅንቅ የአረመኔው ሰራዊት 25ኛ ክፍለ/ጦር ሙሉ ለሙሉ ተደምስሳለች። የመልሶ ማደራጀት ተግባሩን ለማደናቀፍ ከፍተኛ እንቅስቃሴ ሲያደርግ የነበረው ሜጀር ጀነራል ብርሀኑ ጥላሁን በመጨረሻም በእነ ሞት አይፈሬዎች ምድር ጎጃም ድባቅ ተመቷል። ለሶስት ቀናት በወሰደው ምርኮኛ እና ትጥቅ የመልቀም ሒደቱ ሙሉ ለሙሉ የተጠናቀቀ ሲሆን 206ኛ ኮር 3 ዲሽቃ 2 ሞርተር 8 ብሬን 5 ስናይፐር 230 ክላሽ 2 መቶ አለቃዎችን ጨምሮ 61የአረመኔው ሰራዊት ሲማረኩ ፣2 ሻለቃ አዛዦች ፣5(አምስት) መቶ አለቃዎች እና 420 የአረመኔው ሰራዊት ተደምስሰው ከ137 በላይ የጠላት ኃይል ቁስለኛ ሁነዋል። 32ኛ/57ኛ እና 25ኛ ክ/ጦርን አቀናጅቶ ማጥቃት ለማድረግ አቅዶ የነበረው የጀነራል ሶፊያ ማህመድ 602ኛ ኮር በቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ተደቅድቆ በየ ጫካው ሲለቀም ውሏል። የደረሰበትን ምት መቋቋም አቅቶት ብትንትኑ የወጣው የአረመኔው ሰራዊት 4ኛውን ዲሽቃ በ109ኛ ኮር የተማረከ ሲሆን ማህበረሰቡ ለሶስት ቀናት የጠላትን አስክሬን እየሰበሰበ እየቀበረ ይገኛል። አንድም አስክሬን ሳያነሳ ብትንትኑ ወጦ በየ ጫካው ወድቆ እየተገኘ የሚገኘው የመጄር ጀነራል ብርሀኑ ጥላሁን 25ኛ ክ/ጦር እስከ አሁን በአለው ተጨባጭ ሁኔታ 618 የሰው ኃይሉ ከጥቅም ውጭ ሁኗል። አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ ! አዲስ ተስፋ! የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት

አፋብኀ ምዕራብ አማራ ቀጠና፣ ቴዎድሮስ ዕዝ፤ 206ኛ ኮር፤ 24 ክ/ጦር፤ ታኀሳስ 24/2018 ዓ.ም በስናን ወረዳ የማረካቸው ምርኮኞች በተጨባጭ ማስረጃ...!

ከ60 በላይ ምርኮኞች.... #ሼር በማድረግ ለአገዛዙ አድርሱት! ጮቄ አፋፍ ላፋፉን፤ በአልቢን፣በምንሽር ስናን ቁልቁለቱን፤በዲሽቃ በብሬን ጠምዶ ነዳው አሉ የጦሩ ገበሬ 50 አለቃ ማክቤል፤የንብረት ቀኝ እጅ የአባጅሜው ደቦል!!! አፋብኀ ምዕራብ አማራ ቀጠና፣ ቴዎድሮስ ዕዝ፤ 206ኛ ኮር፤ 24 ክ/ጦር፤ ታኀሳስ 24/2018 ዓ.ም በስናን ወረዳ የማረካቸው ምርኮኞች በተጨባጭ ማስረጃ...! በወቅቱ በርካታ ቁጥር ያለው የአገዛዙ ቅጥረኛ ሰራዊት፣በፋኖ በደረሰበት ድምሰሳ እንደዎጣ ሳይመለስ ቀርቷል።ከ60 በላይ የሚሆኑት ደግሞ ህይወታቸውን ለማትረፍ እጃቸውን ሰጥተዋል። ይህ የአገዛዙ ቅጥረኛ ሰራዊት ሴቶቾን የሚደፍር፣ንፁሃንን የሚጨፈጭፍ፣የአማራን ንብረት የሚያዎድም፣ኢ ሰብአዊ ድርጊት የሚፈፅም፣የጦር ወንጀል፣ በአጠቃላይ በአማራ ህዝብ ላይ የዘር ማጥፋት (genocide) የሚፈፅም ወራሪ ኀይል መሆኑን እኛ ብቻ ሳንሆን በተከታታይ ባወጧቸው ሪፖርቶች ዓለም መስክሯል። ይሁን እንጂ እነዚህ ምርኮኞችን የዓለም አቀፉ ሕግ በሚፈቅደው ስርዓት በመያዝ የአካባቢው ማኀበረሰብና ፋኖ ምግብ በማብላት፣ውሃ በማጠጣት፣የሕክምና ድጋፍ በመስጠት ተገቢውን እንክብካቤ ሲያደርጉላቸው ተመልክተናል። አገዛዙ "ፋኖ ተበትኗል፣ተዳክሟል፣ፅንፈኛ ነው፣ዘራፊ ነው፣የተማረከ ሰራዊት የለኝም..." ወዘተ እያለ ቢያደናግርም፣እውነታው ግን ይህ ነው። "የፋኖ አንድነት" ማሸነፊያ መንገዳችን ነው!!

‎በአፍራሽ ተልዕኮው የሰከረውና በህዝብ ደም የጨቀየው የአረመኔው የአብይ አህመድ አገዛዝ የመቃብር አፋፍ ላይ ሆኖም በንፁሃን ህይወት ከመቀለድ አልተቆጠበም። ስርዓቱ በነበልባሎቹ የሕዝብ ልጆች እየተገረፈ እና ወታደራዊ አቅሙ ተዳክሞ የማሕበራዊ ሚድያ  ምላሱ እንደቀረ ይታወቃል። ‎ ‎ አሁን ላይ እሩጠው ያልጠገቡ   የ14 እና 16 ዓመት  ታዳጊዎችን ከትምህርት ገበታና ከእናታቸው ጉያ እየነጠቀ ለጦርነት መማገዱን ተያይዞታል። እነዚህ "ተምረው ለአገር ይበቁልናል" ብለው ወላጆቻቸው ተስፋ የተጣለባቸው እንቦቃቅላ ህፃናት ከትምህርት ቤት በር ላይ ታፍሰው ወደ ብርሸለቆ ማጎሪያ እያጋዘ ይገኛል። አረመኔያዊው የአብይ አገዛዝ  የጭካኔ ጥግ ምን ያህል እንደሆነ  የ7 ዓመት የእለት ከእለት ተግባሩ እንደሆነ ዓለም ያወቀው ጸሀይ የሞቀው ሃቅ ሆኑዋል። ‎ ‎ህፃናትን ለጦርነት መመልመል፣ማሰልጠንና ማሰማራት አለምአቀፋዊ የጦር ወንጀል (International War Crime) የሆነና በተለያዩ አለም አቀፍ ድንጋጌዎች የተከለከለ ተግባር ነው። ለጥቁሩ ሂትለር የአብይ አህመድ አገዛዝ ግን አለም አቀፍ ህግም ይሁን የሞራል ተጠየቅ ግድ የሚሰጡት አይደሉም። ለስልጣኑ መራዘም ይጠቅመኛል ብሎ ካሰበ የትኛውንም ህግ ይጥሳል፤ ኢ-ሞራላዊ የሆኑ ድርጊቶችንም ይፈጽማል። እነዚህ ህፃናት በአለም አቀፍ ድንጋጌዎች የተደነገገን የህግ ከለላ በመጣስ በአገዛዙ የት/ቤት ዩኒፎርም ለብሰው በመማሪያ እድሜያቸው ወታደራዊ ዩኒፎርም ለብሰው ወደ ወገናቸው በመተኮስ ለጋ ጉልበታቸውን ገብረውና ደማቸውን አፍሰው ስልጣኑን ይታደጉት ዘንድ ወደ ት/ቤት ከሚሄዱበት፣ ለመልእክት በሚንቀሳቀሱበት እና ከጓዳኞቻቸው ጋር ከሚዝናኑበት ቦታ አፍሶ ወደ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ተቋም አስገብተቿዋል። ከእነዚህ ህፃናት ውስጥ እድሚያቸው 14_16 የሚሆነኑ  ከ40 በላይ ምልምል ህፃናት በአካባቢው ባለ የፋኖ ድጋፍ በመታገዝ ከብርሸለቆ ማሰልጠኛ ተቋም በማስወጣት ለቴዎድሮስ ዕዝ፣ ለ09ኛ ኮር፣ ለ99ኛ ክፍለጦርን ተቀላቅለዋል። ‎ ‎አሰተያታቸውን ያጋሩ ከአገዛዙ ማሰልጠኛ አፈና ወጠው ከማህረሰቡ ጋር የተቀላቀሉ ምልምል ህፃናት የአገዛዙ አሰልጣኞች በስልጠና ካምፕ ውስጥ በሰልጣኞች አእምሮ ውስጥ የፍርሃት ቆፈን ለማስተጋባት እና አሁንም የተዛባ ትርክት በህጻናት አምሮ ለማስረጽ ሲሉ "በዙሪያችሁ ያለ ዘረኛው አማራ ነው፤ ከዚህ ከወጣችሁ ፋኖም ሆነ ህዝቡ አማራ ያልሆነን ይገድላል፤ ያግቷችሁና ቤተሰቦቻችሁን 200 ሺ እና ከዛ በላይ ይጠየቃል፤ ብሩ ቢሰጣቸው እራሱ ተቀብለው ይረሽኗችኋል" የሚል የተመረዘ ፕሮፓጋንዳ ሲያሰለጥኗቸው እንደቆዩ ይናገራሉ። ከዚህ ለመውጣት ብትጠረጠሩ የለጋ ልጆችን በፊታችን እንደ ሸንኮራ አገዳ እጅ እና እግር ሰብረው እንዲህ ነው ምናረጋችሁ እያሉ እንደሚያስፈራሯቸው የገለፁ  ሲሆን ነገር ግን ምንጊዜም ሞት ነው ብለን ደፍረን በመውጣታችን ያዬነው የህዝቡና የፋኖ እንክብካቤ ፍጹም የማይገናኝና ቱታ ለብሰን የወጣነውን የለበሰውን እያወለቀ የሚያለብስ ህዝበና ሰራዊት ነው ያገኘነው ሲሉ ምስክረነታቸውን ሰጥተዋል። ምልምል ህፃናቱ በአካባቢው ማህበረሰበቡና በክፍለጦሩ እንክብካቤ እየተደረገላቸው ይገኛል። ‎ ‎ሆኖም ፋኖ የህዝብ  ልጅ  ነውና   ተገቢውን  የተሀድሶ ስልጠና የሚሰጣቸው ሲሆን ቀይ-መስቀል እና አለም አቀፍ ተቋማት እንዲረከቧቸውና አገዛዙ እየፈጸመው ያለውን የጦር ወንጀል ከምልምሎች አንደበት እንዲሰማ እንጠይቃለን። ይህ የዛሬው ሁነት የሚያሳየን አንድ ሐቅ አለ፤ ይኸውም የአብይ አህመድ ስርዓት ቀፎው ባዶ እንደቀረና ማሕበራዊ ሚድያ ፕሮፓጋንዳ ብቻ  የቆመ የሰንበሌጥ ቤት መሆኑን ነው። አገዛዙ  በግዳጅ ያፈሳቸውን ህፃናት  ማቆየት የተሳነው፣ የሞራል ተጠየቅ የሌለውና ብስባሴውን ጨርሶ ፈርሶ በማለቅ ላይ እንደሆነ ማሳያ ነው። ‎ ‎በመሆኑም በጠላት ካምፕ ውስጥ ታፍሳችሁ የገባችሁና በውሸት ፕሮፓጋንዳ ተታልላችሁና ተገዳችሁ የተሰበሰባችሁ የአረመኔያዊው የሰራዊት አባላት፣ ሕዝባችሁን የምትክሱበት እና ሂወታችሁን የምታተርፉበት ጊዜው አሁን ነው እና ከእነዚህ ታዳጊዎች  ተማሩ። መሳሪያችሁን ወደ ኖጹሃን ከመተኮስ ታቀቡ። በመውደቅ ላይ ካለው አረመኔያዊ ሥርዓት ጋር ላለመውደቅ እና ምናልባት እድል ቀንቷችሁ በሂወት የመኖር እድል ብታገኙ እንኳን በታሪክ ፊት አንገታችሁን ከምትደፉበት የምትወጡበትን  የራሳችሁን ምርጫ ተከተሉ። ዛሬ በብርሸለቆ የታየውን የጀግንነት እና  የነፃነት  ፍለጋ ጉዞ፣በሁሉም ግንባሮች እንዲደገም ምርጫችሁን አስተካክሉ። አገዛዙ በቅርቡ በሕዝብ ልጆች ትግል ይንኮታኮታል። ‎ አርበኛ ስሜነህ ሙላቱ ‎ድል ለአማራ ህዝብ!! ‎አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ!!

የጀግና ትግል የህሊና ነው!!!! ህሊና በሰው የሚገኝ የፈጣሪ ምትክ ነው። እንደ ጀግና ኑር ከጀግናም ጋር ታገል እድል ብቅ ትል ይሆናል። ጨለማን ያላየ መብራት አያደንቅም መውደቅን ያላየ መነሳት አያ
የጀግና ትግል የህሊና ነው!!!! ህሊና በሰው የሚገኝ የፈጣሪ ምትክ ነው። እንደ ጀግና ኑር ከጀግናም ጋር ታገል እድል ብቅ ትል ይሆናል። ጨለማን ያላየ መብራት አያደንቅም መውደቅን ያላየ መነሳት አያውቅም።     ስለዚህ ትግላችን የአማራ  ህዝብ የህልውና ነው! !!!በሀሳት በብልፅግና ስራዓት  የተሺፈነውን እውነት በጋራ እውነትነትን እንመስክር ። ትግላችን ትናንት በተዘጋጀው ሀዲዳችን እየተጓዝን ነው። አርበኛ ስለሺ ከበደ

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም ፪ኛ ኮር ነበልባል ክፍለ ጦር በጠላት ላይ ከፍተኛ ድል ተቀናጀ !!         አፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም ፪ ኮር ነበልባል ክፍለ ጦር  ታህሳስ 26/2018 ዓ.ም ከለሊቱ አስራ አንድ ሰዓት አከባቢ የፋኖ አባላቶችን በለሊት ለመክበብ የተንቀሳቀሰው ጠላት ያላሰበውን ኪሳራና ውርደት ተከናንቦ ተመልሷል ።       በቀን ውጊያ አልሳካለት ያለውና ዘወትር የሰራዊቱን አባል በየተራራውና በየሸለቆው በፋኖዎች ጥይት እየረገፉበት የተማረረው የ5ኛ ሪፐፕሊካን ልዩ ኮማንዶ በማለት የሚጠራው፤ የአብይ አህመድ ወንበር አስጠባቂ ጉጅሌ ሰራዊቶች፤  ውጤት እናገኝበታለን ያሉትን የማታ ጉዞ ወደ ፋኖዎች ቢያደርግም በጀነራል ተፈራ ማሞ ብርጌድ  በሁለተኛ/፪ኛ ናደው ሻለቃ "ብሩድሬ" በተባለ አካባቢ 11:ዐዐ ሰዓት ላይ በተወሰደበት መብረቃዊ ጥቃት ከፍተኛ የሆነ የሰው ሀይሉን ሙትና ቁስለኛ ያደረጉት ሲሆን በተመሳሳይ ሰዓት "በር" በተባለ አካባቢ የተንቀሳቀሰውን ጠላት  በመቶ አለቃ አበባው ብርጌድ በሁለተኛ/፪ኛ መብረቁ ሻለቃ በተወሰደበት ጠንካራ ምት አብዛኛውን ከፊት የገባውን ቁጥሩ በውል የማይታወቅ ሀይሉን እስከወዲያኛው ተሽቶበታል ። ይህን ተከተሎ፤ ጠላት አንድ ሙሉ ኦራል ተሽከርካሪ ሙት እና ቁጥሩ በግምት የማይታወቅ ከፍተኛ ቁሰለኛውን በአምቡላንሥ እና በአይሱዙ መኪና ጭኖ በምንጃር ሸንኮራ አረርቲ ከተማ መግባቱን እማኞች ገልፀዋል ።   በዚህ ጥቃት ከፍተኛ የሰው ሀይሉ በመጠቃቱ ብስጭት ውስት የገባው አረመኔው አራዊት ሰራዊቱ ከየካንቡ ያለውን ሀይል ይዞ በመጣት ከጠዋቱ 2:25 ሰዓት ላይ "አሟልዩ" በተባለ አካባቢ ተቃት ለማድረስ ቢሞክርም  በነበልባሎቹ መብረቁ ሻለቃ በተወሰደበት ስቦ ማጥቃት  ተደናግጦ ሙትና ቁስለኛውን በአይሱዙና በአምቡላንስ ሰብስቦ ለመመለስ ተገዷል ። ይህ በእንዲህ እንዳለ፤ የግፈኛው አብይ አህመድ ሰራዊት የነበልባሎቹ ፋኖዎችን ክንድ መቋቋም ሲያቅተው ወደ መጣትበት ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ አረርቲ ከተማ ሲገባ "የቡድን መሳሪያ ማርኪያለሁ፣ የነፍስ ወከፍ መሳሪያዎችን ማርኪያለሁ እንዲሁም ብዙ የፋኖ ኃይሎችን ደምስሻለሁ..." በማለት ማህበረሰቡ ላይ የሀሰት ፕሮፖጋንዳ እየነዛ እንደሚገኝ ምንጮች ጠቁመዋል፤ ሲሉ የአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም ፪ ኮር  ሪፖርተር አርበኛ ጋዜጠኛ ይታገስ  ሰይፈ  መረጃውን አድርሰውናል ። -  " ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን" ‎አፋብኃ ደቡብ  አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የህዝብ ግንኙነት ዜና ክፍል።     ‎ታህሳስ 26/2018 ዓ.ም

ላስታ አሳምነዉ ኮር በአገዛዙ ሰራዊት ላይ የማያዳግም እርምጃ በመውሰድ በርካታ ድሎችን ተጎናፀፈ:: አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒልክ ዕዝ ግዙፉ ላስታ አሳምነዉ ኮር ክንፍ የሆኑት እሸት ክፍለ ጦር እና ነብሮ ተወርዋሪ ኮማንዶ ብርጌድ በጥምረት በመሆን ከላሊበላ ጋሻና-ከጋሸና ላሊበላ በሁለት አቅጣጫ እየተንቀሳቀሰ የነበረን የአገዛዙ ሰራዊት አይቀጡ ቅጣት ሲቀጡት ተፈራ ማሞ ክ/ጦር ደግሞ መነሻዉን አይና ከተማ አደርጎ ወደ ቅዱስ ሐርቤ እየተንቀሳቀሰ የነበረን ግትልትል ሰራዊት እንደ ቃሪያ ሲያራግፉት ዉለዋል። ምላሱ ብቻ የቀረዉ የብልፅግናዉ አገዛዝ በአፈ- ቀላጤዎቹ በኩል "ፋኖን ከምደረ ገፅ አጥፍቻለሁ" የሚል የዉሸት ፕሮፖጋንዳ ለገና በዓል ወደ ላሊበላ ከተማ ለሚመጡ እንግዶች ለማስረፅ የተለያዬ የክልል እና የዞን ሆድ አደር ካቢኒዎችን ይዞ በመምጣት ላይ እያለ በዛሬዉ ዕለት ማለትም በቀን 26/2018 ዓ.ም በእሸት ክፍለ ጦር እና በነብሮ ተወርዋሪ ኮማንዶ ብርጌድ ሲገርፍ ዉሎ ያሰበዉን ሳያሳካ ወደየመጣበት ተመልሷል። ወጊያዉም ከንጋቱ 11:00-6:00 የዋለ ሲሆን በዚህም ብዛት ያለዉ የነፍስ ወከፍ መሳርያዎች ሲማረኩ ከ30 በላይ የአገዛዙ ሰራዊት በእሸት ክ/ጦር እና በነብሮ ኮማንዶ ብርጌድ ሲደመሰሱ ከወደ ቅዱስ ሐርቤም በተፈራ ማሞ ክ/ጦር ሲገረፍ ዉሎ ሙትና ቁስለኛ ሁኖ ወደ አይና ከተማ ተመልሷል። ዉጊያን በበላይነት የአፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒልክ ዕዝ ም/ወታደራዊ አዛዥ እና የላስታ አሳመነዉ ኮር ሰብሳቢ አርበኛ ወንድሙ ማሩ የመራዉ ሲሆን አርበኛዉም "በደመቀ ሁኔታ ታህሳስ 29 የሚከበረዉ የገና በዓል አገዛዙ ከሚያስበዉ በላይ እኛ እንዲከበርልን እንፈልጋለን ነገር ግን በዚህ በዓል የብልፅግና አፈቀላጤ ሰለ አማራ ትግልም ሆነ ሰለ አማራ ፋኖ የዉሸት ፕሮፖጋንዳ እሚያሰራጩ ከሆነ እኛ በአቅራቢያዉ እስካለን ድረስ እርምጃ እንወስዳለን ብሏል"። መረጃውን ያደረሰን የአፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒልክ ዕዝ ሚዲያ እና ኮሚኒኬሽን መምሪያ ጋዜጠኛ ፋኖ ደረበ መኮንን ነው:: መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ታህሳስ 26/2018 ዓ.ም

ፋኖ ሰላዮችን ለምን ይገድላል? ድሮን ሲዘንብብን፣ በጅምላ ስንቀበር፣ እኅቶቻችንና እናቶቻችን ሲደፈሩና ጡታቸው ሲቆረጥ፣ ተቋማት ሲወድሙ አላዘኑልንም ድምፅም አልሆኑንም። ሙሉ የሀገሪቱ ጦር ሲዘምትብን ማንም ምን አላለም። ተፈጥሯዊ መብታችንን ተጠቅመን ራሳችንን ስንከላከል ግን እንደ ሀገር አፍራሽ እንደ እምቢተኛ እንቆጠራለን። የጠላት ተልእኮ ተሸካሚን ስንቀጣ፣ ጥቁር አማራውን ለሆዱ ብቻ የሚያስበውን አማራ ስንቀጣ የቅጣት ዓይነት ይመርጡልናል ይባሱንም በደላቸውን ንጽሑህን አድርገው ይዘግቡታል። ሕዝባችን ዓለም ላይ ያልተደረገ ግፍ ሲፈጸምበት እንዳላዩ አልፈው እኛ መቅጣት ስንጀምር ስለ ሰብአዊነት ይሰብኩናል ይከሱናል። ምርኮኛ አቀማጥሎ የሚይዝ ፋኖ ሰብአዊነትን ተግብሮ የሚኖር እንጅ ያለ አግባብ አይገድልም አይዘርፍም። እንደ ጦርነት ሕግ ይገጥማል ያሸንፋል ይማርካል ይደመስሳል። ሰላይን ይቀጣል። አንዳንንዶች የፋኖ ደጋፊ ነን የሚሉና የሦስተኛ ረድፍ የብልጽግና ደጋፊዎች ሳይቀር መሃል ሠፋሪነታቸውን መደበቅ ተስኗቸው በፋኖ የትግልና የሕዝብ አስተዳደር ብሎም የፍርድ አሰጣጥ ዙሪያ የእናውቅላችኋለን ጨኸት ያሰማሉ። እነዚህ ፋኖም ብልጽግናም ካሸነፉ በሰላም እንኖራለን የሚሉ ወላዋዮችና በሕዝብ ላይ ቁማር የሚይዙ ናቸው። ሰሞኑን ስለሚወራው ጉዳይም አርበኛ አስረስ፡ "ስለላ ላይ ተሰማርተዋል" በማለት የሚከስሷቸውን ሴቶች "እንደ ተዋጊ ኃይል" እንደሚቆጥሯቸው ተናግረዋል። "በሕገ ደንባችን መሠረት ለጠላት ስለላ ሥራ ሲሠራ የተገኘ ማንኛውም ሰው ላይ የሞት ቅጣት እርምጃ እንደምንወስድ፣ ሌላም አካባቢ ተመሳሳይ እርምጃዎችን እንደምንወስድ ይታወቃል" ብሏል። በቁጥጥር ስር ያሉ ሰዎች ላይ ግድያን መፈጸም እንደ የጦር ወንጀል ድርጊት ሊቆጠር የሚችል ስለመሆኑ ከቢቢሲ ጥያቄ ቀረበለት የፋኖ አመራሩ አስረስ "በምርኮ የተያዘ ሰው፤ በተኩስ ልውውጥ መሃል በፈቃደኝነት እጁን የሰጠ ሰው ሲሆን ነው። ይሄኛው ግን በልዩ ሁኔታ የስለላ ሥራ ሲሠሩ ስለሆነ በቁጥጥር ስር ዋሉት፤ በሕገ ደንባችን መሠረት እንደ ምርኮኛ የሚያዙ አይደሉም" የሚል ምላሽ ሰጥቷል። ©ብላክ ላዬን ሚዲያ

‎ወ/ሮ አየሁ አበባየሁን  እና  ወ/ሮ አታላይ አንቴን  #የገደ*ለው የወይዘሮ አየሁን ባለቤት በ23/04/2018 ዓ/ም #ያቆሰለው #አረ*መኔ ሰራዊት በቀን 24/04/2018 ዓ/ም  ሙሉ ለሙሉ #ተደም*ስሷል ። ‎ለምልክት  ቀረ ቢባል እንኳ #በምርኮ የተመዘገቡ ናቸው። ‎ ‎በርካታ ክላሽ ስናይፐር  ብሬን ዲሽቃ  ሞርተር እና የተለያዩ ተተኳሾች #ተማርከዋል። ‎የአረመኔው ስርዓት አዋጊዎች ተደም*ስሰዋል፤ ቀሪዎቹም ተጨብጠዋል። ‎ #በዘመቻው የአፋብኃ ምዕ/አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ  ዕዝ 206ኛ ኮር 24ኛ ክፍለጦር እና የ109ኛ ኮር 99ኛ ክፍለጦር የፋኖ ሰራዊቶች #ተሳትፈውበታል። ‎ ‎ቁጥራዊ ምርኮኞችን መሳሪያ ተተኳሽ እና የተማረኩ #የአረ*መኔው ስርዓት አገልጋዮችን ከቆጠራ በኃላ እምናሳውቅ ይሆናል። ‎ ‎አዲስ ትውልድ  አድስ አስተሳሰብ አዲስ ተስፋ፤ ‎ታህሳስ 26/2018 ዓ/ም Dejen M Endale ‎