ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)
Kanalga Telegram’da o‘tish
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
Ko'proq ko'rsatish4 418
Obunachilar
+1224 soatlar
+287 kun
+1 15930 kun
Postlar arxiv
+3
ሁሌም ከስራ የማይለየው ብርጌድ አንዴ በውጊያው፣ አንዴ ማህበረሰቡን በማወያየት ፣ አንዴ ጦርን በማወያየት አለፎም ለህዝባችን ፍትህ በመስጠት የሚታወቀው አፋብኀ ምዕራብ አማራ ቀጠና ተረወድሮስ ዕዝ የቀኝ ጌታ ዮፍታሄ ንጉሴ 6ተኛ ክፍለጦር ደምበጫ ኢንጅነር ክበር ተመስጌን ብርጌድ ዛሬም እንደ ትናንቱ የዘለቃ እነወንድ ቀጠና የሚገኘውን የአራሽ ፋኖዎችን ሲያወያይ ውሏል።
ስንወያይ ስንነጋገር ስንሰባሰብ ችግሮቻችንን እንፈታለን የጠላትን ቅስም እንሰብራለን ገና በወሬ ስርዓቱን እናሽመደምደዋለን።
ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን።
ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን እና ፊስቡክ ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
https://www.facebook.com/share/p/17FBBgD9xG/
የአገዛዙ ካንፕ በብርሃን ፍጥነት እየተናደ ነዉ ‼️
እንኳን ደህና መጣችሁ‼️
የመሪያችን አርበኛ ዘመነ ካሴን ጥሪ የተቀበሉ 11 ወንድሞቻችን ብርጌዳችንን ተቀላቅለዋል‼️
ከዚህ ቀደም በድርጅታችን መሪ አርበኛ ዘመነ ካሴ የተላለፈዉን የምህረት ጥሪ በመቀበል እና ብርጌዳችን የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴወድሮስ እዝ ፫ኛ ጎጃም አገዉ ምድር የ፲/አ ኤፍሬም አጥናፉ ብርጌድ መስከረም 23/2018 ዓ/ም አዲስ ቅዳም ከተማ ከተደረገዉ <ዘመቻ ሀምሳ አለቃ አይሸሽም ተክሌ ኦፕሬሽን> በኋላ ያስተላለፈዉን
"ፋኖን ተቀላቅላችሁ ህይወታችሁን ትረፉ!" አዋጅ በማክበር ስማቸዉ ለጊዜዉ እንዲጠቀስ ያልፈለጉ 3 የወጡ ወንድሞቻችንን ጨምሮ
1ኛ ሀምሳ አለቃ ምህረት አደራ ከአድማ ብተና
2ኛ ሀብታሙ ተገኘ ከሰላም አስከባሪ
3ኛ ያዛቸዉ ካሳሁን ከሰላም አስከባሪ
4ኛ ፈጠነ አስማረ ከሰላም አስከባሪ
5ኛ በላይነህ ገረም ከሰላም አስከባሪ
6ኛ ፍቅረ ማሪያም ምትኩ ከሰላም አስከባሪ
7ኛ ስዩም አበጋዝ መከላከያ
8ኛ ተስፋየ ተክሌ መከላከያ
በድምሩ 11 ወንድሞቻችን መስከረም 26/27//2018 ዓ/ም እና ጥቅምት 1/2018 ዓ/ም አዲስ ቅዳም ከተማ ከተከማቸዉ የጠላት ካምፕ በማምለጥ
የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ እዝ ፫ኛ ጎጃም አገው ምድር ክ/ጦር ፲/አ ኤፍሬም አጥናፉ ብርጌድን በሰላም ተቀላቅለዋል።
➾ከሰሞኑ እጅግ በጣም ብዙ የፋሽስቱ ጦር ከኦሮምያ ወደ አማራ ክልል ገብቷል።
የኦሮምያ ልዩ ኀይሎችም በብዛት ገብተዋል። ነገር ግን ከፖለቲካ ካድሬዎች በስተቀር ብዙዎቹ ጦርነቱን አይደግፉትም።
የመከላከያ አዛዦች ፋኖ ወደ መደበኛ ውጊያ ( conventional warfare ) እየገባ ስለሆነ፣ በአለን የሰው ኀይል ብዛትና በጦር መሳሪያ ብልጫ ታግዘን፣ ፊት ለፊት ገጥመን እናሸንፈዋለን ብለው ያምናሉ። ደቡብና ኦሮምያን ለሸኔ ( OLA) ትተው ሠራዊቱን አማራ ላይ ያሰፈሩትም ለዚህ ነው።
በእርግጥ መከላከያ የሰው ቁጥርና የመሳሪያ ብልጫ ቢኖረውም፣ ፋኖ ደግሞ የውጊያ ቆራጥነት እና የውጊያ መሬት ብልጫ አለው። ፋኖ የሚዋጋው በራሱ ህዝብ መሃልና በሚያውቀው ዱርና ገደል ነው። የአማራ ክልልን የመሬት አቀማመጥ ሲያይ የኦሮምያ ልዩ ሀይል ሲኦል የገባ ሊመስለው ይችላል፥ ምነው ባልተፈጠርኩ እያለ ቢያለቅስም አንፈርድበትም።
በ5 ዓመቱ የጣሊያን ወረራ ወቅት አባቶቻችን የጣሊያን ጦር በብዛት በመሳሪያ ታጅቦ ሲመጣባቸው ፊት ለፊት እንዲገጥም እድል አይሰጡትም። ወደሚያውቁት መሬት ይስቡና አስገብተው ልኩን ያሳዩታል። ፋኖ ዘመነ ስቦ መምታት የሚለው ይህን ስልት መሰለኝ።
ታላቁ የሮማ ጦር ጀርመንን መወቆጣጠር ሳይችል የቀረው በዚህ ምክንያት ነው። የዛሬ 2ሺ ዓመት የአውግስጦስ ቄሳር ጦር በጄኔራል ቫረስ እየተመራ ጀርመንን ለመውረር ተነሳ። አርሚኒየስ የተባለው ሮማውያን ያሳደጉት ጀርመናዊ የጦር መሪ የሮምን ጦር አታሎ ቲዩቶን ቡርግ ወደ ተባለ ጫካ ና ረግረጋማ ቦታ አስገባቸው። ከዚያ በሁዋላ የጀርመን ነገዶች እንደ ግሪሳ ወፍ የተበተነውን የሮም ጦር እንዳለ ፈጁት። ጄኔራል ቫረስ ራሱን አጠፋ። አውግስቶስ ውርድት ተከናነበ።
የናፖሊዮንና የሒትለር ወታደሮች ሩሲያ ውስጥ ተመሳሳይ መከራ ደርሶባቸዋል።
የውጊያ ቦታንና ጊዜን ማወቅ እጅግ ወሳኝ ነው። በእርግጥ የሳተላይት እና የድሮን ቴክኖሎጂ ብዙ ነገሮችን ቀይሯል። ቢሆንም ይህን ወደ አማራ ክልል እንደ ግሪሳ የገባውን ጦር እየሳቡና እየቆራረጡ እንዳይወጣ ማድረግ የፋኖ ስራቴጂስቶች ትልቁ የቤት ሰራ ነው። አብይ አህመድ ይህ ጦር ከተሸነፈበት ከዚያ በኋላ የሚያዋጋው እንደ ሙሽራ በእንክብካቤ የተያዘውን ሪፐብሊካን ዘበኛ ነው። የዚህ ኀይል አቅም ከፌደራል ፖሊስ አቅም ትንሽ ከፍ ቢል ነው። የቅቤ ገንፎ እየበላ የፋፋ ወታደር፣ በረሀ ወርዶ ቆሎ እየቆረጠመ ይዋጋል ብለህ አትጠብቅ።
ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን።
ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን እና ፊስቡክ ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
https://www.facebook.com/share/p/17FBBgD9xG/
ተመልከቱ የብልጽግና ባሪያ በአማራ ክልል የተሰማራዉ አራዊት ወንድሞቻችንን ህዝብ በተሰበሰበበት ባደባባይ ሲረሽናቼዉ ትመር እንደሁ ምረር ታገል ለነጻነት
ሰበር ዜና‼️
የአማራ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የኃለማርያም ማሞ ክ/ጦር በ ባደረገው ሶስት የጦርነት ግምባሮች ድልን ተቀዳጀ !
በቀን 02/02/2018 ዓ.ም የአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የኃለማርያም ማሞ ክ/ጦር፡ በአገዛዙ ሰራዊት ላይ ከፍተኛ የሆነ ጥቃት ማድረሱን የከሰም ሚዲያ ምንጮች ገልፀዋል ። የአፋብኃ ኃለማርያም ማሞ ክ/ጦር፤ የክፍለጦሩ ቃኝና መሃንዲስ እና ሺህ አለቃ 4 በጋራ በመሆን በሀገረማርያም ከሰም ወረዳ፡ ዛላ ዘንባባ ቀበሌ እና የኔቾ ቀበሌ የፋኖ ሀይሎች ማህበረሰቡን ለማወያየት በሚንቀሳቀሱበት ወቅት የጠላት ሀይል ስብሰባውን ለማደናቀፍ፤ ከሰፈረበት ኮምፕ እንቅስቃሴ ቢያደርግም በኃለማርያም ማሞ ልጆች በክ/ጦሩ ቃኝና መሃንዲስ እና ሺህ አለቃ 4 በቅንጅት በመሆን በቆረጣ በመግባት ክፉኛ መመታቱ ነው የተሰማው ።
የአቢይ አህመድ ቅጥረኛ የኮማንዶ ሰራዊት ሀይል፤ የፋኖን ክንደ-ብርቱነትን መቋቋም ሲያቅተው ከባባድ መሣሪያዎችን አቅጣጫው ወደ ማይታወቅ ስፍራ ሲጥል ውሏል ። በዚህም የአርሶ-አደሩን የቤት እንሰሳና ንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱን የአፋብኃ የኃ/ማሞ ክ/ጦር፡ ዘመቻ መምሪያ ሀላፊ ፋኖ ደፋሩ ተ/ሚካኤል ከስፍራው መረጃውን አድርሰውናል ።
በሌላ በኩል፤ የኃለማርያም ማሞ ክ/ጦር፡ ሺህ አለቃ 1 በቁምድንጋይ ቀበሌ እና ሺህ አለቃ 2 ዛላዘንባባ ቀበሌ እንዲሁም የኔቾ ቀበሌ ከጠዋቱ 2:00 አንስቶ እስከ ምሽት 1:00 ሰዓት ድረስ በቅንጅት በተደረገው የአውደ-ውጊያ ግምባሮች የአገዛዙ ሰራዊት በከፍተኛ የሆነ ሙትና ቁስለኛ አስተናግዷል ። ጠላት በፋኖ ሀይሎች ምት ቀላል እና ከባድ ጉዳት የደረሰባቸውን የአገዛዙን ሰራዊት በአምፑላንስ መኪና ወደ ሆስፒታል ሲያመላልስ ውሏል ። በዚህም 4 ሙት ፥ 2 ከባባድ ቁስለኛ ፥ 6 ቀላል ጉዳት ማስተናገዱ ነው ውስጥ አዋቂዎች መረጃውን ያደረሱን ። በመጨረሻም፤ ጠላት ወደ መጣበት 'እግሬ አውጪኝ' ፈርጥጦ መመለሱ ነው የታወቀው ።
የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ሀይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰሞኑ ነፃ በወጣችው ግሸ ራቤል ወረዳ ከሚኖሩ የመንግስት ሰራተኞች ጋር በታሪካዊቷ "ራቤል" ከተማ ውይይት አካሄደ።
===============
የአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ በታሪካዊቷ "ራቤል" ከተማ ያሉ የአገልግሎት ሰጭ ተቋማት መደበኛ ስራቸውን እንዲቀጥሉ የሚያስችል ውይይት ከመንግስት ሰራተኞች ጋር አካሄዷል::
የመወያያ የመነሻ ሐሳብ ያቀረቡት የአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ አርበኛ አሸናፊ ምንዳ አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ክፍት ሆነው ለህዝባቸው አገልግሎት እንዲሰጡ የተሰደዱ የብልጽግና የፖሊስና የሚኒሻ አባላት ከነቤተሰቦቻቸው ተመልሰው የበደሉትን ህዝብ ይቅርታ ጠይቀው ህይወታቸውን እንዲመሩ እና የህዝብ ተቋማት ንብረቶች ለግለሰቦች ጥቅም ሳይውሉ በስርዓት ተቆጥረው ለህዝብ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማስቻል ነው መድረኩ የተዘጋጀው ብለዋል::
በተጨማሪም የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ አርበኛ አሸናፊ ምንዳ አውቀውም ሆነ ሳያውቁ ከአማራ ህዝብ ጭርፍጫፊ የብልጽግና ስርዓት ጎን ተሰልፈው የነበሩ የብልጽግና አመራሮች ፖሊስና የሚኒሻ አባላት በቀጥታ ከፋኖ አመራሮች ጋር ተነጋግረው ወይም በሀይማኖት አባቶች እና በሀገር ሽማግሌዎች በኩል በቀጣይ ከእንደዚህ አይነቱ የጥፋት ቡድን ጋር ደግመው ላይሰሩ ቃል ገብተው ከመጡ ፋኖ በባለፉት ተግባራቸው እንደማይጠይቃቸው በአቋም እንደተያዘ ማረጋገጫ ሰጥቷል::
በውይይቱ የተሳተፉት የመንግስት ሰራተኞች የፋኖን ተቋማዊ ለውጥ እንደ ተዓምር በመግለጽ አማራን አማራ ላለማፈናቀል የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ሀይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የወሰደው የበሰለ አካሄድ የአማራን አንድነት የሚያመጣ ተግባር ነው ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል::
ፋኖ ወደ ታሪካዊቷ "ራቤል" ከተማ የገባበት አግባብ ብስለት በተሞላ መልኩ የተጠና በመሆኑ አገልግሎት ሰጭ ተቋማትን ከስግብግብ ዘራፊዎች የታደገ ነው ሲሉም አስተያየታቸውን ጨምረዋል::
በተጨማሪም እነዚህ የመንግስት ሰራተኞች በቀጣይ ቢስተካከሉ እና በአንክሮ ቢታዩ ያሏቸውን ጥያቄዎችና አስተያየቶች አቅርበዋል::
ከመንግስት ሰራተኞች የተሰጡ አስተያየቶችን በቀጥታ ተቀብለን እናስተካክላለን ያሉት የአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ህግ አገልግሎት መምሪያ ሀላፊ አርበኛ ተስፋየ ገስጥ የፋኖ አባሎቻችን ዕዙ የሚያስተላልፈውን ትዕዛዝ ከመፈጸም ውጭ በድርጅታዊ እና አስተዳደራዊ ጉዳዮች የማይገቡ መሆኑን አውቃችሁ በቀጣይ በሚዘረጋው መዋቅር የራሳችሁን አስተዋጽኦ ልታደርጉ ይገባል ሲሉ ማደማደሚያ ሰጥተዋል::
መረጃዎን ያደረሰን የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አማረ ታዘዘ
" ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን"
አፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ህዝብ ግኑኝነት ዜና ክፍል
ጥቅምት 09/02/2018 ዓ.ም
ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን።
ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን እና ፊስቡክ ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
https://www.facebook.com/share/p/17FBBgD9xG/
+2
ምሽግ አሰባበር እንዴትና ምን እንደሆነ ለማያውቁት "በመከላከያ ስም" ለሚንቀሳቀሱት ለብልፅግና የመንደር ዱርየዎች አሳዩዋቸው።
ሰሞኑን ፋኖ በሰበራቸው ወሳኝ ምሽጎች ውስጥ በርካታ የጠላት ብልፅግና ቡድን ወታደር አስከሬን የአሞራ ቀለብ ሆኖ ቀርቷል።
ሕዝባዊ የምክክር መድረክ በኤፍራታ እናግድም ወረዳ ካብሳራምባ ደጉቼ ቀበሌ የተደረገ ውይይት!!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ አንደኛ ኮር ትግሉ ከጀመረ ጀምሮ ብዙህ ቀበሌዎችን በስሩ እያስተዳደረ ይገኛል።
የአሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ አንደኛ ኮር ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አርበኛ ፋኖ ያሬድና የኮሩ አመራሮች በተገኘበት ሰፊና ጠለቅ ያለ እርጅም ሰዓት የወሰደ በዚሁ በኤፍራታ እናግድም ወረዳ ካብሳራምባ ደጉቼ ቀበሌ የፖለቲካ ትምህርት እና የህዝብ አደረጃጀት ዙሪያ ከፋኖ አመራሮች በሚያምርና በሚያስደምም መልኩ ለህዝቡ ግንዛቤ የኮሩ ከፍተኛ አመራሮች እና ማህበርሰቡ ውይይት ተካሂዷል። በውይይቱም ከላይ እንደጠቀስነው አብይ አህመድ በኤፍራታና ግድም ወረዳዎች ላይ በፖለቲካና ትምህርት ጉዳዩ ያለ የሌለውን በትር ከተጠቀመባቸው የአማራ ወረዳዎች አንዱ ነው ።
ሆኖም ብአዴን የአብይ እኩይ ሲራ ተቀብለው በአማራ ህዝብ ላይ ፖሊቲካም ይሁን ትምህረትና የህዝብ አደረጃጃት እንዳይሰራ ሲያደርግ የቆየ ሲሆን ፋኖዎች በሚያስተዳድራቸው ወረዳና ቀበሌ አሁን ባለው የፖለቲካ ትምህርት እና የህዝብ አደረጃጅት ጉዳይ ለህብረተሰቡ ሰፊ ሚና የተጫወተበትና ፋኖች ይህን አረመኔያዊ ስራት ለመጣል ከወጡ ጀምሮ በሰላም መውጣትና መግባት እንደቻሉ አልፎም ተርፎም ተማሪ ልጆቻቸው በሰላም ወደ ትምህርት ቤት ገብተው ተምርው እንዲመለሱ የተደረገበት የህዝብ አደረጃጅትም ሰላማቸውን ያስገኘ ለኮሩ አመራሮች ሰፋ ያለ ገንቤና ሃሳብ ከማህበረሰቡ ያሳዩበት መድረክም ነበር።
በመጨረሻም የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዐፄ ዘርዓ ያዕቆብ አንደኛ ኮር አመራሮች እና የዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ አንደኛ ኮር ፖለቲካ ዘርፍ አርበኛ ያሬድ በኤፍራታና ግድም ወረዳ ካብሳራምባ ደጉቼ ሸበሌ ከሚኖሩት ማህበረሰብ ጋር በነበራቸው ወይይት እጅጉ ተደስተው ማህበረሰቡም ለፋኖ አመራሮች እናንተ ማለት እኛ ነን እናንተ ስትኖሩ እኛ መኖር እንችላለን ከዚህ በፊት ለፋኖ ድጋፍ ስናደርግ የቆየን ሲሆን ከዚህ በላይ ድጋፋችን እናደርጋለን በማለት ህዝባዊ መድረኩ ተጠናቋል!!
መረጃዎን ያደረሰን የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አማረ ታዘዘ
ጥቅምት 03/02/2018 ዓ.ም
""""""ዘራፊወች ላይ እርምጃ ተወሰደ 👇👇
ጥቅምት 02/2018 ዓ.ም ከምሽቱ 2:00 ሰአት ላይ በመሸንቲ መስመር ልዩ ቦታው መቶ ካብ ተብሎ የሚጠራው ቦታ በፋኖ ስም የተለያዩ ዝርፊያወችን ሲፈፅሙ የነበሩ የአረመኔው ስርዓትና አሽከር ተባባሪ የሆኑ አካላት ላይ የጣናዉ መብረቅ ብርጊድ ቃኝና መሃድስ ባደረጉት የተጠና ልዩ ኦፕሬሽን ደረጀ ሞላ የተባለ ሚሊሻ እስከወዳኛዉ የተሸኘ ሲሆን በዚህ ቀጠና ላይ ያለውን የሚፈፀሙትን ወንጀሎች በመከታተል ቀጣይነት ያለው እርምጃ ለመውሰድ ብርጌድ በትኩረት እየሰራ ሲሆን ህዝቡ ማንኛውን ጥቆማ በመስጠት እንድትተባበሩን በማለት ጥሪ አስተላልፈዋል።
ፋኖ ሐብታሙ የሱፍ የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴድሮስ ዕዝ 1ኛክ/ጦር ህዝብ ግንኙነት
ጥቅምት 03/2018 ዓ.ም
➾በንፁሐን ላይ የድሮን ጥቃት ደረሰ‼
ፋይሽቱ ኃይል አዴት አቅራቢያ በምትገኘው ሮብገበያ ተብላ በምትጠራ ቦታ ድሮን የጣለ ሲሆን አምስት ንፁሐንን አርሶአደሮች መገደላቸው ታውቋል።
የአሻራ ምንጮች ከቦታው እንዳረጋገጡት ከሆነ ከቀኑ 6:00 ሰዓት አካባቢ ዛሬ ጥቅምት 03/2018 ዓ.ም በይልማና ዴንሳ ወረዳ አዴት አቅራቢያ ልዩ ስሟ ሮብገበያ በተባለች ቦታ ድሮን የጣለ ሲሆን አምስት አርሶ አደሮች በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደሉ ሲሆን ሴቶችና ህፃናት እንዲሁም የቀንድ ከብቶችም የጥቃቱ ሰለባ መሆናቸውን የአይን እማኞች ለአሻራ ገልጸዋል።
ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን።
ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ ቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ፮ኛ ክፍለጦር ንጉስ ተክለሃይማኖት ብርጌድ የተለመደ ተግባሩን አሁንም አጠናክሮ ቀጥሏል።
በቀን 02/02/2018 ዓ.ም በደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር አብማ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 08 ውሀ ጋን ተብሎ በሚጠረው አጥቦ አይለብሴ የሚኒሻ ካንፕ ላይ የንጉሱ ተርቦች ከቀኑ 11:00 ስዓት ባደረጉት ድንገተኛ ኦፕሬሽን የብአዴንን አገልጋዮች ሙት እና ቁስለኛ አድርገውታል። በተመሳሳይ ሌሊት 10:00 በዚሁ ቦታ ላይ በንጉሱ ልጆች በተፈፀመ የቦንብ ጥቃት ዋርድያዉ እስከ ወዲያኛው ላይመለስ ተሽኝቷል።
ይህንን ጀብድ የተመለከቱት ሲርበን አጉራሽ ሲበርደን አልባሽ የሆነው የደብረ ማርቆስ ከተማ እና አካባቢው ማህበረሰብ የንጉሱ ጀግኖች ደማችንን እየመለሳችሁት ነው በርቱልን ሲሉ አድናቆታቸውን እና መልዕክታቸውን እየለገሱን ይገኛሉ።
ድላችን በተባበረ ክንዳችን‼️
አዲስ ትውልድ‼️አዲስ አስተሳሰብ‼️አዲስ ተስፋ‼️
የንጉስ ተክለሃይማኖት ብርጌድ ህዝብ ግንኙነት
#ፋኖ_ባዬ_ሽፈራው (ቀኜ)
ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን።
ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ የሰባት ለሰባ ደመላሽ ሻለቃ ተወርዋሪዋ የአሳምነው አናብስቶች
ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን።
ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
አፋብኃ ወለጋ ክ/ሀገር ቢዛሞ ዕዝ✊🏽💪🏽
ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን።
ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
