ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea
Kanalga Telegram’da o‘tish
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
Ko'proq ko'rsatish2 952
Obunachilar
+424 soatlar
+147 kun
+38830 kun
Postlar arxiv
አይበገሬው 64ኛ ክ/ጦር የሻላቃ መሪውን፣ ብሬን ተኳሽ ጨምሮ 10 የአድማ_ብተና፣ ፖሊስ እና የሚሊሻ አባላት በደፈጣ ኦፕሬሽን እስከወዳኛው ሲያስወግድ 7ቱ ቀላል እና ከባድ ቁስለኛ ሆነዋል!!
64ኛ ክ/ጦር ግንቦት 22/2018 ዓ.ም
~~~~~~~
ግንቦት 22/2018 ዓ.ም አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር አይበገሬው 64ኛ ክ/ጦር ቃኝና መሃንዲስ በእነማይ ወረዳ ሁለት አምባ ዲቢሳ ቀበሌ የአገዛዙን የሐሰት ምርጫ እና አፋብን ያወጣውን የመንገድ ክልከላ በጣሰ ባጃጅ ላይ እርምጃ ሲወሰድ የአገዛዙ የሐሰት ምርጫ ለማስፈፀም ከየትመን ከተማ ወደ ቢቸና ከተማ በአንድ ኦባማ በጉዞ ላይ የነበሩ አድማ_ብተና፣ፖሊስ እና ሚሊሻ የጫነ ተሽከርካሪ በወሰደው ልዩ የደፈጣ ኦፕሬሽን ድል ተቀዳጅቷል።
በክ/ጦሩ ቃኝ እና መሃንዲስ አባላት ቁጥጥር ስር የዋለው ባጃጅ ለማስለቀቅ ከየትመን ከተማ በአንድ ኦባማ በጉዞ ላይ የነበሩ አድማ_ብተና፣ፖሊስ እና ሚሊሻ አባላትን በመያዝ ወደ ሁለት አንባ ዲቢሳ ቀበሌ ያቀና ቢሆንም በጀግኖቹ የደጅ አዝማች በላይ ዘለቀ ልጅች በፊደራል መንገድ ጥቁር አስፖልት ሁለት አምባ ዲቢሳ ልወያ ጎጥ ላይ በወሰዱት የደፈጣ ጥቃት የአገዛዙ ቅጥረኛ #ሚሊሻ አባላት ወደ አፈርነት ተቀይረዋል።
የ64ኛ ክ/ጦሩ ቀኝ እና መሃንዲስ በሰራው ልዩ የደፈጣ ኦፕሬሽን 10 የሞተ ሲሆን 7 ቀላል እና ከባድ ቁስለኛ ሆነዋል ከእነዚህም ውስጥ:-
1ኛ. ላለም ጌታነህ አድማ_ብተና ሻለቃ መሪ የሞተ
2ኛ. ፖሊስ ይታያል ሙሉቀን ብሬን ተኳሽ የሞተ
3ኛ. ቢያድግ አይችሉም የማህበራት ፅ/ቤት ኃላፊ ቀላል ቁስለኛ
4ኛ. ሚሊሻ ሰይድ ዳውድ ቀላል ቁስለኛ እና
5ኛ. ሚሊሻ ጌትነት ውበት
6ኛ. ሚሊሻ ስማቸው ይሆንስ
7ኛ. ሚሊሻ ይበልጣል ሽፈራው ከባድ ቁስለኛ በመሆን ደ/ማርቆስ ሆሲፓታል የገቡ ሲሆን ስማቸውን ለግዜው ማግኘት ያልቻልናቸው የአገዛዙ ቅጥረኛ ሚሊሻ እና አድማ ብተና አባላት በአንድ ፖትሮል እና አንድ አንቡላስ ሙት እና ቁስለኛ ሆነው ቢቸና ከተማ መግባታቸው ተረጋግጦል። በዚህ የደፈጣ ጥቃት ሚሊሻዎችን የጫነ አንድ ኦባማ ተሽከርካሪ ከጥቅም ውጭ ሆኗል።
በፋኖ ሀይሎች ከፍተኛ ጉዳት ያስተናገደው የአገዛዙ ቅጥረኛ ሚሊሻ #ሹፊር አየለ ግሩም የተባለ የቢቸና ተወላጅ አስገድደው እንዲጭናቸው ከአደረጉ በሆላ ለፋኖ ቀድመህ መረጃ በመስጠት ነው በማለት በአሰቃቂ ሁኔታ ገለውታል። በየትመን ከተማ አቶ በላይነህ አድማስ የተባለ ንፁሀን በአራት ጥይት ተመቶ ከባድ ቁስለኛ የሆነ ሲሆን በደጀን የመጀመርያ ደረጃ ሆሲፒታል በመግባት ህክምና እያገኘ ይገኛል።
የደጅ አዝማች በላይ ዘለቀ ልጆች የ64ኛ ክ/ጦር ቀኝ እና መሃንዲስ በሰሩት ከባድ የደፈጣ ጥቃጥ አገዛዙ በድንጋጤ ውስጥ መግባቱ የተነሳ ከደ/ማርቆስ፣ ደጀን፣ የትኖራ፣ ጢቅ የሚገኝውን የሰው ሀይሉን ከከባድ መሳሪያዎች መድፍ፣ ዙ23፣ አራት ድሽቃ የመሳሰሉት በመያዞ በሸበል በረንታ መረገጭ ንዑስ ከተማ በመግባት ወደ አራጢ ከተማ ከባድ መሳሪያ ሲተኩስ ውሏል።
በዚህ የደፈጣ ጥቃት ዘግይተው የሚደርሱን ትክክለኛ መረጃዎችን ለህዝባችን፣ ለትግሉ ደጋፊ እና ለሰራዊታችን መረጃው እንደደረሰን በክ/ጦሩ ድር ገፅ የምንገልፅ መሆኑን እናሳውቃለን።
ላናሸንፍ የጀመርነው ትግል የለም!! ወጥር አማራ🔥
አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ!!
ግንቦት22/2018 ዓ.ም
Yibeltal Getie Mitiku
አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክ/ጦር ሕዝብ ግንኙነት
የአገዛዙ 103ኛ ኮማንዶ ክፍለጦር አባላት መክዳትን ተከትሎ የፋኖ አመራሩ ወላጅ እናት በብልፅግናው አመራሮች መታሰራቸውን ኮሩ አስታወቀ።
አፋብን ሸ/ጠ/ግ/አ/ዕዝ
ያለማቋረጥ በርካታ የ103ኛ ኮማንዶ ክፍለጦር አባላት በየቀኑ ፋኖን እየተቀላቀሉ ሲሆን፣ በዛሬው ዕለትም ግንቦት 22 ቀን 2018ዓ.ም የክፍለጦሩ ጋንታ መሪ የኦሮሞ ብሔር ተወላጁ ፶ አለቃ ፈይሳ ገመቹ የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ አፄ አምደ ፅዮን ኮር የ7ለ70 ክፍለጦርን መቀላቀሉን ኮሩ በላከው የግንባር መረጃ አስታውቋል።
የመከላከያውን ፍለሰት ተከትሎ "ልጅሽ ሰራዊታችንን እያስኮበለለብን ነው" በሚል የፈጠራ ወሬ ከቀጠናው ውጭ የሚገኘውን የአፄ አምደ ፅዮን ኮር ምክትል ዘመቻ ኃላፊ የፋኖ መመኪያ መሸሻ ወላጅ እናት የሆኑትን ወ/ሮ አሳበች መንገሻ በአገዛዙ ኃይሎችና በመከላከያ አመራሩ ትዕዛዝ ሰጭነት ከግንቦት 18/2018ዓ.ም ጀምሮ በአጣዬ ከተማ ዝግባ ሰፈር የመከላከያ ካምፕ ውስጥ በግፍ ታስረው እየተሰቃዩ መሆናቸውን ቤተሰቦቻቸው ገልፀዋል።
በዚሕ አረመኔ ድርጊቱ ያላቆመው የአገዛዙ ዘራፊ ሀይል የኤፍራታና ግድም ወረዳ የመተኬ ሸረፋ ነዋሪ የሆኑትን የሁለት አባት አርበኞችን የአቶ አውራሪስ ማሞን ሁለት በሬዎች እና የሴት ልጁን ሳምሰንግ ዘመናዊ ስልክ እንዲሁም የአቶ ካሳዬ ክብረትን አንድ በሬ በመዝረፍ የሀይማኖት ግጭት ለማስነሳት በማሰብ ለኢድ ዓል-አድሃ (አረፋ) በዓል ለመከላከያ ሰራዊቱ የተዘረፉትን 3 በሬዎች መታረዳቸውን ኮሩ አረጋግጧል።
አገዛዙ እንደ ህዝብ የአማራን ህዝብ እየገደለና ለከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ውድቀት እየዳረገው መሆኑን መላው ህዝባችን ጠንቅቆ በማወቅ በውድቀቱ ዋዜማ ላይ የሚገኘውን አሸባሪ ስርዓት ለመጣል በሀሰተኛ የምርጫ ድራማ ላይ ባለመሳተፍ ከፋኖ ጎን ተሰልፎ ነፃነቱን እንዲያውጅ ሲል ኮሩ መልዕክቱን አስተላልፏል።
''ክብር ለትግሉ ሰማዕታት''
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን
የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ
ግንቦት 22/2018ዓ.ም
+3
ሰበር ዜና!!!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ወሎ ቤተ አማራ ጀብደኛው ምኒልክ ዕዝ የ102ኛ ኮር በዘመቻ አንሻ ሰይድ ከወንድም 101ኛ ኮርና ልዩ ዘመቻ በጋራ ግንቦት 20/2018ዓ/ም በብልፅግና ወንበር አስጠባቂ ሰራዊት ላይ በተኩለሽ ከተማ ዙሪያ እርምጃ መውሰዳቸው ይታወቃል።
በመሆኑም አሁን በደረሰን መረጃ የ102ኛ ኮር የ65ኛ ከፍለጦር በወሰደችው የሞርተር 82 ኢላማውን የጠበቀ ድብደባ በማድረግ የአገዛዙን የ45ኛ ክፍለጦር አዛዥ ኮሌኔል ተርፋታን ጨምሮ ድሽቃ ምደብተኞቾን ልዩ ቦታው አምዳምባ አቦ 026 ቀበሌ ላይ ሙሉ በሙሉ ተደምስሰዋል።
በተጨማሪም የጠላት 45ኛ ክፍለጦር ድሽቃ ሙሉ በሙሉ ከጥቅም ወጭ መሆኑን የውስጥ መረጃችን አድርሶናል።
ሌላው የብልፅግና ወንበር ጠባቂው የ45ኛ ክፍለጦር አዛዥ ኮሌኔል ተርፋታ ዛሬ ግንቦት 22/2018ዓ/ም በሐራ ከተማ ከሌሎች የሬጅመንት አመራሮች ጋር የቀብር ስነ-ስርዓታቸው መከናወኑን የውስጥ መረጃዎቻችን ገልፀውልናል።
በመጨረሻም የጠላት 45ኛ ክፍለጦር ዙ-23 በቀድሞው ዞብል አምባ ክፍለጦር የአሁኑ 12ኛ ክፍለጦር ሜካናይዝ አልሞ ተኳሾች በወሰዱት ስብጥር የሞርተርና የድሽቃ ተኩስ ሙሉ በሙሉ እርምጃ ተወስዶበታል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የአፋብን ወሎ(ቤተ-አማራ) ምኒልክ ዕዝ የ102ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት መምሪያ መረጃዉን አድርሷል።
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ወሎ ቤተ- አማራ ምኒልክ ዕዝ ሚዲያ እና ኮምኒኬሽን መምሪያ!!
ግንቦት 22/2018 ዓ.ም
የትውልዱ መሪ የአማራ ፋኖ ልዩ ምልክት አቢዮተኛው የአፋብን ሊቀመንበር አርበኛ ዘመነ ካሴ በስራ ላይ
እስኪ ለአንድ አፍታ ቆም በሉና የነጻነትን ዋጋ እናስተውል…
ዛሬ በአራቱም የአማራ ግዛቶች እየተከፈለ ያለው መስዋዕትነት በቃላት የሚገለጽ አይደለም። በምቾት ዓለም ውስጥ ሆነን ስልካችንን ስናነሳ፣ እዚያ ማዶ ግን ስንቱ የሚወደውን ሞቅ ያለ ቤቱን፣ ስንቱ ናፋቂ ልጆቹንና ውድ ቤተሰቡን በትኖ በዱር በገደሉ እየተዋደቀ ይገኛል።
የአማራ ልጅ ፋኖ እንደ ማንኛውም ሰው “በርገር ልብላ፣ የደላኝ ሕይወት ልኑር” አላለም። የሚወዳትን አንዲት ነፍሱን ሳይሳሳ ለአማራ ሕዝብ ሕልውና አሳልፎ የሰጠው፣ የአረመኔው ሥርዓት ወገኑን ለማጥፋት ሌት ከቀን እየሠራ መሆኑን ስላወቀ ነው—ይህ ደግሞ ጥቁርም ነጩም የሚያውቀው የትውልድ ሐቅ ነው!
ነገር ግን... ልብን በሀዘን የሚሰብረው ትልቁ ሕመም ምን እንደሆነ ታውቃላችሁ? እነሱ በረሃብና በጥም እየተቃጠሉ፣ የጥይት ናዳ እየተጋፈጡ ደማቸውን ሲያፈሱ፤ እዚህ ማዶ ግን አንዳንድ ወገኖች ለሚዲያ ፍጆታና ለጊዜያዊ ጥቅማ ጥቅም ሲሉ የፋኖን ስም እየለዩ ይሰድባሉ። ይህ እጅጉን ልብ የሚሰብር አማራዊ ክህደት ነው!
📌 ቆም ብለን የምናስበው እውነት፡ አማራን ማዳን የምንችለው ጀግኖችን በመሳደብና ስም በመስጠት አይደለም፤ ጀግኖችን በዕውቀት፣ በሃሳብና በጉልበት በመርዳት እንጅ! ከታች ካለው ተዋጊ ጀሌ ጀምሮ እስከ ንጉሱ ዘሜ (ዘመነ ካሴ) ድረስ እያንዳንዱ የአማራ ልጅ የሚከፍለው መስዋዕትነት ለአንድ ዓላማ ብቻ ነው ለአማራ የመኖር ነፃነት!
እንደ ኢትዮጵያ ተወልደን፣ እንደ አማራ የምንታረድባትና የምንሞትባት ሀገር እንድትኖር የአማራዊ ተፈጥሯችንና የማንነት ክብራችን በፍጹም አይፈቅድልንም! ውድ በውስጥም በውጭም የምትኖሩ አማራውያን… ታሪክ ጥሪውን እያቀረበ ነው። ከቻላችሁ ኑ፣ ክንዳችንን አስተባብረን አብረን እንስራ። ካልሆነ ግን የጀግኖችን ሞራል አንስበር።
ይህ መልዕክት የሁላችንም የቤት ሥራ ነው። ትግሉ የጋራችን እንደመሆኑ መጠን፣ ከተመቻችሁ ለመላው የአማራ ፋኖ ትግል ደጋፊዎቻችን በሙሉ ሼር በማድረግ አድርሱልን! ✊❤️
#Dawit #Amhara ቀጥታ ከግንባር 👑 ከንጉሶች መንደር
Repost from ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea
የጀግንነት ማህደር የዋልታ እና የማገሩ ስልጣኔ አርበኛ መከታው ማሞ፤
አማራ ማለት ለዚህች ውድ አገር ለኢትዮጵያ ዋልታና ማገር ነው! ታሪክ የገመደው፣ ጀግንነት የወለደው ይህ ታላቅ ህዝብ፣ ለሀገረ መንግስቱ መመስረትና መጽናት የማይናወጥ አለት ሆኖ ዘመናትን ተሻግሯል።
ከዳግማዊ አፄ ሚኒልክ መንገሻ፣ ከታላቋ የሸዋ ጠቅላይ ግዛት... ታሪክ ደጋግሞ ከሚያነሳቸው የጀግኖች አውድማዎች መካከል የሸዋ መሬት ቀዳሚዋና ዋናዋ ነች። ይህች መሬት በአቀማመጧ አስደናሚ ናት ደመናን የሚቧጥጡ ተራራዎቿ፣ ቅዝቃዜያቸው አጥንት የሚሰረስር ብርዳማ ስፍራዎቿ፣ እና ታሪካዊ ሚስጥርን ያቀፉት ቆላማ ግዛቶቿ የጀግኖች መፈልፈያ እቶን ሆነው አገልግለዋል።
በዚሁ አስገራሚ መልክዓ ምድር በታላቁ ስምጥ ሸለቆ፣ በሸዋረቤት ዙሪያ ተፈጥሮ ካበቀለቻቸው እምቡጥ ጀግኖች መካከል ዛሬ የአንዱን ስም በወርቅ ቀለም እንድፅፍ አማራዊ ግዲታዬ ያስገድደኛል። እርሱ.የታላቁ የአማራ ህዝብ የመኖር ነፃነት የሆነው የድርጅታችን (የአፋብን) ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር አርበኛ መከታው ማሞ ነው!
እርበኛ መከታው ማሙ በንግግሩ መልካም፣ በአስተሳሰቡ እጅጉን ጥበበኛና አስተዋይ ሰው! ከመሆኑም በላይ የአርበኛው መከታው ማሙ ማንነት የሚገለጠው በቃላት ድርደር ብቻ አይደለም። የእርሱ መልካም ባህሪ፣ ለህዝቡ ያለው ተቆርቋሪነት፣ እና በጦር ሜዳ ላይ የሚያሳየው ስልታዊና አስደማሚ የሰራዊት እንቅስቃሴ እርሱ እውነተኛ፣ ባለማዕተብና ታማኝ የአማራ ልጅ መሆኑን በግልጽ ያሳብቃሉ።
እርሱ ለወገኑ ጋሻ፣ ለጠላት ደግሞ የማይሻገር የቁም ቅዠት ነው! በሸዋ ምድር የበቀለው ይሄ ጀግና፣ የአባቶቹን አደራ ተሸክሞ፣ የማንነትንና የነጻነትን ሰንደቅ አንግቦ በቁርጠኝነት እየተጓዘ ይገኛል።
ታሪክ ሁሌም ጀግኖቹን ያስታውሳል። የሸዋ መሬት ዛሬም እንደትላንቱ መከታዎችን ማፍራቷን ቀጥላለች! የአርበኛ መከታው ማሙ የጀግንነት ጉዞ ይቀጥላል! #Dawit #Amhara ከንጉሶች መንደር!!
የአማራ ፋኖ የግንባር ወቅታዊ ፈጣንና ትኩስ መረጃዎችን ለማግኘት #የቴሌግራም ገፃችን ይወዳጁ!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
ሰበር ዜና!
የብልፅግና አመራሩ በጀብደኛዉ ምኒልክ ዕዝ ፋኖወች አስከወዲያኛዉ ተሸኘ!!
የምኒልክ ዕዝ የከተማ ሰርጂካል ኦፕሬሽን ቲም የአንጎት ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ኃላፊ በሆነው በአቶ ተመስገን ያረጋል ላይ የማያዳግም እርምጃ መውሰዱን ገለጸ።
በአመራሩ ላይ እርምጃውን የወሰዱት የምኒልክ ዕዝ ሰርጂካሎች አማካኝነት ነዉ።፣ ስለ ኦፕሬሽኑ ዝርዝር መረጃ በሰፊዉ ነገ እምናደርስ ይሆናል።
መዳረሻውን ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ሕዝብ የሕልውና ተጋድሎ ይቀጥላል ሲል የ106ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት መምሪያ መረጃዉን አድርሷል።
ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ወሎ ቤተ- አማራ ምኒልክ ዕዝ ሚዲያ እና ኮምኒኬሽን መምሪያ
ግንቦት 21/2018 ዓ.ም
አማራነት ውድ ዋጋ እንዳለው ጠንቅቀን እናውቃለን!
የአማራ ሕዝብ ከሰማይ በታች ያላየው እና ያልቀመሰው የበደል አይነት የለም። ይህንን በደል የምንገረስሰው ደግሞ በኛ በልጆቹ የተባበረ ክንድ ነው። የአማራን ሕዝብ የሕልውና አደጋ በመቀልበስ፤ በኢትዮጵያ ምድር ለአማራ ሕዝብ ሕልውና ዳግም ስጋት የማይሆንበትን ስርዓት እንተክላለን።
ለዚህ ብቸኛው መዳኛችን አማራነት ነው የጠየቀውን ሁሉ ከፍለን አማራን ወደ ነበረበት የክብር ማማ እንመልሰዋለን።
©Birhanu Chalie Demelash
የአማራ ልጅ ፋኖ የብዙዎቹ የጀግኖች ባለቤት ነው ይህችን ደስ የምትል የአማራ ልጅ የትግል እንቅስቃሴ ስንጋብዛችሁ ከታላቅ ክብር ጋር ነው።
የአማራ ፋኖ ወሎ (ቤተ-አማራ ) ምኒልክ ዕዝ ጀብደኛው የ102ኛ ኮር በብልፅግና አገዛዝ የጥምር ጦር የሰራዊት አባላት ላይ በዘመቻ አይሻ ሰይድ በተኩለሽ ከተማና ዙሪያ መብረቃዊ ጥቃት በመፈፀም ሁለት የጠላት ምሽጎችን አስለቀቀ ።
በሰሜን ወሎ ዞን በራያ ቆቦ ወረዳ በተኩለሽ ከተማ ግንቦት 20/2018ዓ/ም ከቀኑ10 ሰዓት የ102ኛኮርና የ1ዐ1ኛ ኮር እንድሁም ነበልባሏ ልዩ ዘመቻ በጋራ ማጥቃት በማይታሰብ ሁኔታ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የጨፍጫፊውና የአምባገነኑን የሰራዊት አባላት ተደመሰሰ።
የ102ኛ ኮር የጥንካሬ ምልክት የሆነችው 12ኛ ክፍለጦር ከተኩለሽ ከተማ በሰሜን ምስራቅ ማለትም በሽዎች ማሪያም እስከ ምሽቱ 4 ሰዓት ድረስ ነበልባሏ 2ኛ ሻለቃ ፣የ3ኛ ሻለቃና የ6ኛ ሻለቃን ሙሉ ሀይል በማስጠጋት በሞርተርና በድሽቃ በአስገራሚ ሁኔታ ሽፋን በመስጠት የጨበጣ ተኩስ በመክፈት ሙሉ በሙሉ በማጥቃት ከፍተኛ ኪሳራ አደረሱበት።
ጠላት ወደ ጀመዶና በረሀ ማሪያም እንድሁም ራያ ቆቦ ወረዳ ያሉ የገጠር ቀበሌዎችን ለመያዝ እንቅስቃሴ ለማድረግ ቢሞክርም የሀይል የበላይነት ተወሰዶበታል።
በተጨማሪም የ12ኛ ክፍለጦር 1ኛ ሻለቃ፣ 4ኛ ሻለቃና 5ኛ ሻለቃ በመካናይዝ የታገዘ አውደ ውጊያ ከተኩለሽ ከተማ በሰሜን ምዕራብ በኩል በሞርተር 82 ኢላማውን የጠበቀ ድብደባ በማድረግ ሁለት የጠላት ምሽግ በማስለቀቅ ወሳኝ የሆነውን ገዥ ቦታ ተቆጣጥረዋል።
ሌላው ጠላት ግንቦት 20/2018ዓ/ም ከቀኑ 11ሰዓት ከጮቢ በር ወደ አማያ፣ ባይባዋና ሽዎች ማሪያም ለመውጣት የሞከረ ቢሆንም የ12ኛ ክፍለጦር 120 ሜካናይዝ በመጠቀም ጉዳት በማድረሷ እንቅስቃሴውን ሙሉ በሙሉ መግታት ተችሏል።
እንድሁም የ101ኛ ኮር የ11ኛ ክፍለጦር ጀግኖች ከተኩለሽ ከተማ በደቡብና በደቡብ ምዕራብ በኩል በተለምዶው ስንቄ አምባ በተባለ አካባቢ በመግባት ሁለት የጠላት ስትራቴጅክ ቦታዎችን በከፍተኛ ውጊያ በመደምሰስ ተቆጣጥረዋል።
የቀድሞው ካላኮርማ ክፍለጦር የአሁኑ 49ኛ ከፍለጦርና የ65ኛክፍለጦር በጋራ በመሆን የጥላትን የሀይል ሚዛን ለማዛባት ከተኩለሽ ከተማ በምስራቅና በደቡብ ምስራቅ ያሉ ቀጠናዎችን በመቆጣጠር የጥላት ሀይል እንዳይንቀሳቀስ ማድረግ ችለዋል።
ጠላት ከላይ በተጠቀሱት አካባቢዎች ሆርማትና ቆቦ ከተማ ከባድ መሳሪያ በማስወንጨፍ ሙሉ አቅሙን የተጠቀመ ቢሆንም የ49ኛና የ65ኛ ክፍለጦርን ክንደ ብርቱዎቹን መቋቋም ባለመቻሉ ወደ ሌላ ቦታ ሀይል እንዳይንቀሳቀስ አድርገውታል።
በመጨረሻ የድርጅታችን መኩሪያ የሆነችው ልዩ ዘመቻና የቀደሞው ሀውጃኖ ክፍለጦር የአሁኑ የ15ኛ ክፍለጦር በአባሆይ ጋሪያ በወንዳችና በሙጃ በኩል መንገድ በመዝጋት የጠላት ሀይል ወደ ምስራቅ በኩል እንዳይንቀሳቀስ የአንበሳውን ድርሻ ወስደዋል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
"ክብር ለትግሉ ሰማዕታት"
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአፋብን ወሎ(ቤተ-አማራ) ምኒልክ ዕዝ የ102ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት መምሪያ
ግንቦት 21/2018 ዓ.ም
ዉድ ቤተሰቦቻችን ሙሉ ትረካዉን በመስማት ሀሳብ አስተያየትዎን comment ላይ በማስቀመጥ አጋርነታቹህን እንድታሳዩን በአክብሮት እንጠይቃለን! https://youtu.be/wbVMGHCXgPg?si=RDSdKk-a-kwAbQyD
Repost from ተራራው ሚዲያ (Teraraw Media )
ዉድ ቤተሰቦቻችን ሙሉ ትረካዉን በመስማት ሀሳብ አስተያየትዎን comment ላይ በማስቀመጥ አጋርነታቹህን እንድታሳዩን በአክብሮት እንጠይቃለን! https://youtu.be/wbVMGHCXgPg?si=RDSdKk-a-kwAbQyD
የአብይ አህመድ አገዛዝ ራእይ ለራሱ ትንሽ የስልጣን ዘመኑን የሚያራዝምለት ቢመስለዉም በአፍሪካ ቀንድ ላይ ሰፊ የባሩድ ክምር የመለኮስ አደጋ አለዉ!!
ዘ ኢኮኖሚስት (The Economist) ያቀረበውና "የኢትዮጵያው አብይ አህመድ ኢምፔሪያላዊ ራዕይ" በሚል ርዕስ የተሰናዳው ትንታኔ፤ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር እየተከተሉት ያለውንና ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጎላ የመጣውን ደፋር ቀጣናዊና ሀገራዊ ስትራቴጂ ያብራራል።
አብይ አህመድ የኖቤል የሰላም ሽልማት ካሸነፈ የሊበራል ለውጥ አራማጅነት ተነስቶ፣ እንዴት የቀድሞ የኢትዮጵያ ነገስታትን ታላቅና ማዕከላዊ ምኞት ወደሚያንፀባርቅ መሪነት እንደተቀየረ ያሳያል። ይህ አካሄድ ለኢትዮጵያ መረጋጋትም ሆነ ለአጠቃላይ የአፍሪካ ቀንድ ከፍተኛ አደጋዎችን ያዘለ መሆኑን ይተነትናል።
ለዚህ "ኢምፔሪያላዊ ራዕይ" መነሻ የሆኑት ዋና ዋና አውዶችና ጭብጦች የሚከተሉት ናቸው፦
1. የቀይ ባህር አባዜ እና የቀጣናው ውጥረት
የአብይ ራዕይ በጣም ተለዋዋጭና አደገኛ የሆነው አካል ለቀይ ባህር ያለው ቁርጠኛ አቋም ነው። ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ. በ1993 ኤርትራ ነጻነቷን ስታገኝ የባህር በር አልባ ሆናለች። አብይ የባህር በር ማግኘት ለኢትዮጵያ "የህልውና ጉዳይ" መሆኑን በይፋ የገለጹ ሲሆን፣ ወደ 150 ሚሊዮን እየተጠጋ ያለ ህዝብ በ"ጂኦግራፊያዊ ወህኒ ቤት" ውስጥ ሊኖር አይችልም ማለታቸው ይታወሳል።
የሶማሊላንድ ስምምነት፦ ይህንን ራዕይ እውን ለማድረግ መንግስታቸው የባህር ኃይል ጦር ሰፈር ለመከራየት ራስ ገዟ ከሆነችው ሶማሊላንድ ጋር አወዛጋቢ የመግባቢያ ሰነድ (MoU) ተፈራርሟል።
የቀጣናው መዘዝ፦ ይህ እርምጃ ሶማሊላንድን እንደ ራሷ ሉዓላዊ ግዛት የምታየውን ሶማሊያን በእጅጉ አስቆጥቷል። ወታደራዊ ፍጥጫዎችን የቀሰቀሰ ሲሆን፣ እንደ ግብፅ ያሉ የቀጣናው ተቀናቃኞች ከሶማሊያ ጋር የጥበቃ ስምምነት እንዲያደርጉ በማስገደድ በሰፊው የአፍሪካ ቀንድ ቀጠናዊ ጦርነት የመነሳት አደጋን ከፍ አድርጎታል።
2. ሀገሪቱን በራሱ ምስል መቅረጽ (የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት)
በሀገር ውስጥ፣ አብይ የቀድሞውን የብሔር-ፌደራሊዝም ጥምረት (ኢህአዴግን) በመበተን በምትኩ ከፍተኛ ማዕከላዊነት ያለውን ብልጽግና ፓርቲን መስርተዋል።
የአዲስ አበባ ገጽታ ለውጥ፦ የዚህ ራዕይ ዋነኛ አካላዊ መገለጫ በዋና ከተማዋ አዲስ አበባ እየተካሄደ ያለው ሰፊው የ"ኮሪደር ልማት ፕሮጀክት" ነው። ይህ ግዙፍ የከተማ ማደስ ዘመቻ አረንጓዴ ቦታዎችን፣ ሰፊ መንገዶችን እና ዘመናዊ መሠረተ ልማቶችን የሚገነባ ሲሆን፤ ዓላማውም ከብሔራዊ ምርጫ በፊት የኢትዮጵያን ኃያልና የወደፊት ገጽታ ለማሳየት ነው።
የታሪክ ንጽጽር፦ ተቺዎች እንደሚሉት ይህ ከላይ ወደ ታች የሚወርድ የዘመናዊነት ዘመቻ የቀድሞ የኢትዮጵያ ነገስታት ፍፁም የመንግስት ስልጣንን ለማሳየት ያደረጓቸውን ግዙፍ የስነ-ህንጻ ለውጦች ይመስላል። ይህም ብዙ ጊዜ ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር በቂ ምክክር ሳይደረግ እና የተፈናቀሉ ዜጎችን ግምት ውስጥ ሳያስገባ የሚተገበር ነው።
3. የሀገር ውስጥ ግጭት እና ማዕከላዊነት
አብይ የኢትዮጵያውያንን አንድነት (መደመር) ቢሰብኩም፣ ማዕከላዊ ስልጣንን ለማስከበር ያደረጉት ጥረት በሀገር ውስጥ ከባድ ተቃውሞዎችን አስከትሏል።
ከህወሃት (TPLF) ጋር አስከፊ የእርስ በእርስ ጦርነት ካደረጉ በኋላ፣ የፌደራል መንግስቱ አሁንም በሌሎች ክልሎች በተለይም ከአማራ ፋኖ ሚሊሻዎች እና ከኦሮሞ አማፂያን (ኦነግ ሸኔ) የነፈሰባትን ጠንካራ ወታደራዊ ተቃውሞ እየገጠመው ይገኛል።
ትንታኔው አንድ ትልቅ ተቃርኖን ያሳያል፦ አብይ
• ታላላቅ መዋቅራዊ ለውጦችን እያደረገ ሰፊ የግል ስልጣን በዙሪያው እያከማቸ ባለበት በአሁኑ ወቅት፣ የሀገሪቱ ዳርቻዎች ግን በአካባቢያዊ የእርስ በእርስ ግጭቶች ምክንያት እየተዳከሙ ነው።
4. የአስተሳሰብ ውህደት፦ ጴንጤቆስጣሊዝም እና ብልጽግና
የአብይ ኢምፔሪያላዊ ዘይቤ በጴንጤቆስጣሊዝም እና በ"ብልጽግና ወንጌል" አስተሳሰቦች ከተቀረጸ የዓለም እይታ ጋር የተቆራኘ ነው። ሃይማኖትን ከመንግስት አስተዳደር በጥብቅ ከሚለዩት ማርክሲስታዊ አስተሳሰብ ከነበራቸው የቀድሞ መሪዎች በተለየ፣ አብይ ሃይማኖታዊ ንግግሮችን አዘውትረው ይጠቀማሉ። ኢትዮጵያን በእግዚአብሔር የተመረጠች ሀገር አድርገው የሚስሉ ሲሆን፣ ሀገሪቱን ወደ ላቀ ዓለም አቀፋዊ ደረጃ ለማድረስ የተመረጡ መሪ መሆናቸውን በጽኑ ያምናሉ።
የኢኮኖሚስት መደምደሚያ፦ አብይ አህመድ እ.ኤ.አ. በ2019 ምዕራባውያን አክብረውት እንደነበረው ዓይነት የዲሞክራሲያዊ መግባባት ፈጣሪ መሪ መሆናቸው አብቅቷል። ይልቁንም በአሁኑ ጊዜ የሚንቀሳቀሱት እንደ ዘመናዊ ንጉሠ ነገሥት በአንድ ወገን ውሳኔ የመስጠት አስተሳሰብ ነው—ይህ ቁማር ምናልባት በሀገር ውስጥ ስልጣናቸውን ለአጭር ጊዜ ሊያጠናክርላቸው ቢችልም፣ በአፍሪካ ቀንድ ላይ ግን ሰፊ የባሩድ ክምር የመለኮስ አደጋ አለው።
በዘመቻ አንሻ ሰይድ እንዲሁም በቀኝአዝማች ጨለፍ ተስፋው አርባ ቀን መታሰቢያ በመቄት ወረዳ ታሪክ ተሰራ!
ግንቦት 21/2018 ዓ/ም አፋብን ወሎ ቤተ አማራ ምኒልክ ዕዝ የ106ኛ ኮር እና የ303ኛ ኮር አሃዶች በመቄት ታላቅ ጀብድ ፈፅመዋል። የ106ኛ ኮር አካል የሆነችው አናብስቷ 22ኛ ክፍለጦር፣ ከ303ኛ ኮር 81ኛ ክፍለጦር አንድ ሻለቃ ጋር በመጣመር ቀን ሙሉ በወሰደ ተጋድሎ በብልፅግናው አገዛዝ ላይ መብረቃዊ ጥቃት ፈፅመዋል።
የአገዛዙ ሰራዊት ከጋሸና፣ከኮን እና ከመቄት የተውጣጣ ከአንድ ክፍለጦር በላይ ዙ-23፣ ሁለት (2) ሞርተር 82 በማሰለፍ የእልቂት አዋጁን በአማራው ላይ ለመፈፀም ቢሞክርም የቀኝአዝማች ጨለፍ ተስፋው ልጆች ብርቱ ክንዳቸውን ሲያሳርፉበት ውለዋል። በማለዳው የተጀመረው አውደ ውጊያ ከጋሸና ጫፍ እስከ መቄት ጫፍ የሸፈነ ነበር።
በዚህ ታሪካዊ ትንቅንቅ የጠላት ሀይል ባልጠበቀው መንገድ የመቄት ሜዳዎች አረንቋ ሁነውበት ውለዋል። የአገዛዙ ዘረ ፈጅ ሰራዊት በደረሰበት ከባድ ማጥቃት ብትንትን የወጣ ሲሆን በርካቶችን ሙት እና ቁስለኛ ማድረግ ተችሏል።
በአውደ ውጊያው በጠላት ላይ የደረሰ ሰብዓዊ ጉዳት፦
✅ የተደመሰሰ 37
✅ የቆሰለ 28
✅ የተደመሰሰ አመራር 2
በጠላት ላይ የደረሰ ቁሳዊ ኪሳራ፦
✅ የተማረከ ክላሽንኮቭ 23
✅ የብሬን ተተኳሽ 1075
✅ የክላሽ ተተኳሽ 2150
✅ የዲሽቃ ተተኳሽ 570
✅ የእጅ ቦምብ 13
በመጨረሻም ጠላት በዘፈቀደ በሚተኩሰው ከባድ መሳሪያ የግለሱብ ቤት እንዲሁም የእርሻ አትክልት አውድሟል።
መዳረሻውን ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ሕዝብ የሕልውና ተጋድሎ ይቀጥላል!
የ106ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት መምሪያ!
ግንቦት 21/2016 ዓ/ም
