ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea
Ir al canal en Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
Mostrar más2 944
Suscriptores
-1024 horas
+77 días
+37930 días
Archivo de publicaciones
ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ የተሰጠ ጥብቅ መመሪያ
በአስገዳጅነት ለምርጫ ለተመዘገባችሁ አማራውያን ወገኖቻችን፤
አምባገንኑ የብልፅግና አገዛዝ ሕዝባዊ እምቢተኝነቱን በመፍራት፣ በየቀበሌውና በየመንደሩ ካድሬዎቹንና ታጣቂዎቹን በማሰማራት የ"ምርጫ ምዝገባ" በግድ እና በማስፈራራት መፈፀሙን እንረዳለን።
ነገር ግን እውነታው፤ ምርጫው ተካሄደ አልተካሄደ ብልፅግና ራሱን መርጦ የጨረሰ መሆኑ ነው! ግንቦት 24 ቀንን የፈለገው ለዓለም ሕዝብ የውሸት ሕጋዊነትና መስፈርት ያሟላ መስሎ ለመታየት ብቻ ነው።
ስለሆነም፣ የምርጫ ካርድ የያዛችሁ ወገኖቻችን የገዥው አካል የድራማ መሣሪያ እንዳትሆኑና ወደተዘጋጁት የምርጫ ጣቢያዎች እንዳትሄዱ እያሳሰብን፣ የሚከተሉትን መመሪያዎች በአስቸኳይ ተግባራዊ እንድታደርጉ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፦
1. ለጠቅላላው ሕዝባችን፦
በዕለቱ (ግንቦት 24) ማንኛውም ዜጋ ለድራማ ወደተዘጋጁት የምርጫ ጣቢያዎች ባለመሄድ፣ ለህልውናው መከበር ያለውን ፅኑ አቋም በተግባር እንዲያረጋግጥ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
2. ለሕዝብ አገልግሎት ተቋማት ሠራተኞች፦
ሥርዓቱ በአስገዳጅነትና በጥቅማጥቅም የራሱ መጠቀሚያ ሊያደርጋችሁ እንደሚፈልግ እናውቃለን። በመሆኑም ከመደበኛ የሥራ ጫናና ከሥርዓቱ ፖለቲካዊ ተፅዕኖ ራሳችሁን እንድታቅቡ፣ መላው የመንግሥት ሠራተኛ ከእሁድ ጀምሮ በቤቱ ቁጭ በማለትና ለጥሪዎች ምላሽ ባለመስጠት የሕዝብ ወገንተኝነቱን በተግባር እንዲያሳይ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
1. ለአስገዳጅ ካድሬዎችና አጎብዳጅ ታጣቂዎች የተሰጠ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ፦
ሕዝባችንን እያስፈራራችሁ የጥፋት የምርጫ ምዝገባ የምታድሉና በዕለቱ አስገድዳችሁ ለማስመረጥ ያቀዳችሁ የአገር ውስጥ ባንዳዎች ድርጊታችሁን በአስቸኳይ አቁሙ! የእያንዳንዱ አስገዳጅ ስም ዝርዝር እየተመዘገበና እየተጠናቀቀ መሆኑን በውል እወቁት!
ክብር ለትግሉ ሰማዕታት!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
+2
የስቦ ማስከዳት ስራው ተጠናክሮ ቀጥሏል የጠላት ከምፕ እየፈራረሰ ነው
==========================
ግንቦት 23/2018 ዓ.ም
ህፃናትን በግዳጅ እያፈሰ ለውትድረና እየማገደ ያለው የአብይ ስርአትን በመተው ሰራዊቱ ከመርጦ ለማርያም እና ከድጎ ፅዮን በመውጣት ወደ 201ኛ ኮር 74ኛ እና 54ኛ ክፍለ ጦርን ተቀላቅለዋል።
1.ተፈራ አድማስ .........አድማ በትን
2.አለቃ ተሜ ............አድማ በትን
3.አንማው ሀብቴ...........ሚሊሻ
4.ደረጃው ገደፋው....... .ፓራኮማንዶ
5.እውነቴ በቃሉ..........ፓራኮማንዶ
6.ስማቸው የኔአለም.........ፓራኮማንዶ ከዚህ በሗላ ምንም አይነት ሰራዊት የመታገል ፍላጎት የለውም እኛም የገባነው የትጥቅ ችግር ስላለብን ነው በማለት ሀሳባቸውን የገለፁ ሲሆን በክፍለጦር አመራሮች አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
አፋብን ቴወድሮስ ዕዝ 2ዐ1ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
+3
በአማራ ክልል የከተሞች ውጥረት እና የደህንነት ስጋት አሳሳቢ ሆኗል
ወልዲያ እና ጎንደር —
በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች እየተባባሰ በመጣው ግጭት እና ውጥረት ሳቢያ የሲቪል ነዋሪዎች እና የንብረት ደህንነት ላይ ስጋት መደቀኑ ተሰማ።
በወልዲያ ከተማ ጎንደር በር ተብሎ በሚታወቀው አካባቢ፣ የብልጽግና ፓርቲ (ብአዴን) የጸጥታ ኃይሎች በባጃጅ ተሽከርካሪዎች ላይ የቦምብ ጥቃት መፈጸማቸው ተዘግቧል። ጥቃቱ የባጃጅ ተሽከርካሪዎችን ሙሉ በሙሉ ማውደሙን የአካባቢው ምንጮች ገልጸዋል።
በተያያዘም፣ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በትላንትናው ዕለት ምሽት በጋራ ሆነው የእግር ኳስ ጨዋታ በመመልከት ላይ እያሉ በደረሰ የቦምብ ጥቃት፣ በበርካታ ተማሪዎች ላይ ጉዳት መድረሱ ታውቋል።
የአካባቢው ነዋሪዎች እና የህዝብ ተወካዮች እንደሚሉት፣ ገዢው ፓርቲ በተለይም ፋኖ በምርጫ ሂደት ላይ ያወጣውን መመሪያ ህዝቡ በስፋት እየተገበረ መሆኑን ተከትሎ፣ ስርዓቱ በየከተማው እየወሰደ ያለው እርምጃ የበቀል እና የሽብር መገለጫ ነው ሲሉ ይከሳሉ።
በአሁኑ ወቅት በተለያዩ ከተሞች በጸጥታ ኃይሎች እየተወሰዱ ያሉ እርምጃዎች መላውን ህዝብ ለከፍተኛ ስጋት እየዳረጉ ይገኛሉ።
በመሆኑም፣ በየአካባቢው ሊከሰቱ የሚችሉ ተመሳሳይ የሽብር ተግባራትን ከግምት በማስገባት፣ ህዝቡ በንቃት እንዲጠነቀቅ እና አስፈላጊውን የደህንነት ጥንቃቄ እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቧል።
አስቸኳይ
ከአማራ ሕዝባዊ ማሕበራት ፎረም የተሠጠ መግለጫ
ብርሃን ከጨለማ ጋር ምን ኅብረት አለው?
በትብብር ስም የተሰባሰበ ባንዳ በምርጫ ታዛቢነት ሽፋን በሚሰራ ሸፍጥ የሚቆም ትግል ዛሬም የለም ነገም አይኖርም!
አማራ ብልሃትንና አርቆ አሳቢነትን እንደ ምኒልክ የወረሰ፣ ደግነትን እንዲሁም ሀገር ወዳድነትን ደግሞ እንደ ደጃዝማች በላይ ዘለቀ የተላበሰ፣ እንደ ዐፄ ቴዎድሮስ የተንቀለቀለ የአንድነት ስሜት ያለው፣ እንደ ገብርዬ ታማኝ፣ ኩሩ ጨዋ ሰውና ሀገር ወዳድ ሕዝብ ነው። ይኸን ታላቅ ሕዝብ ያለበትን ዘርፈ ብዙ ችግር ለመቅረፍ የተቋቋመው የአማራ ሕዝባዊ ማሕበራት ፎረም መነሻችን የአማራ ሕዝብ ችግር መዳረሻችን የአማራ ሕዝብ ታላቅነት ራዕይና ተልዕኮ አድርጓ ፈተናን እየፈተነ በእሳትና በሞት ጥላ ስር ሆኖ ሁለተናዊ ትግል እያደረገ ይገኛል።
ይሁን እንጅ ለአማራ ጥፋት የተመሰረተው የጨርቦሌ ፖለቲካ ! አማራ "ታላቅ ነበርን ታላቅም እንሆናለን" ህልም ለማጨገፍ በትብብር ስር የተሰባሰቡ የፓለቲካ ቁማርተኞች በባህርዳር : አዲስ አበባ:ቻግኒ:እጅባራና ሌሎች ከተሞች በሲቪክ ማሕበራችን ስም ልቅምቃሚ ገንዘብ ለማግበስበስ የትብብሩ ታዛቢ እየመረጡ እንደሚገኙ በማስረጃ ደርሰንበታል። ይህ ባንድነት እንዲቆም ጥረት ብናደርግም ከዚህ እኩይ ተግባር አልተቆጠቡም ።
ባንዳ ማለት «ከሃዲ»፣ «አገር ሸክም» ወይም ለገዛ አገሩና ወገኑ ሳይሆን ለጠላት የሚያግዝ እና የሚሰልል ሰው ማለት ነው ይህ ቃል በዋነኝነት ጥቅም ላይ የዋለው በኢትዮጵያ የጣሊያን ወረራ ዘመን (1928-1934) ሲሆን፤ በወቅቱ ለወራሪው ኃይል አድረው አገራቸውን የሸጡና ወገናቸውን ያስጨፈጨፉ ግለሰቦችን ለመግለጽ ይጠቅም ነበር ዛሬም በፓርቲ ስም በባንድነት ተግባር የተሰማሩ ሆድ አደሮች የሕዝባችን የጀርባ ቁስል ሁነዋል።
የባንዳ መገለጫዎች
በአማርኛ ቋንቋ የባንዳነት ባህሪ ተብለው የሚታወቁት፡
ክህደት፡ ለጥቅም ወይም ለግል ፍላጎት ሲባል አገርን ለጠላት አሳልፎ መስጠት
ቅጥረኛነት፡ የውጭ ኃይሎች ወይም የጠላት አላማ አስፈጻሚ መሆን
የውስጥ ሰላይነት፡ የጠላት መንገድ መሪና የስንቅ አቅራቢ መሆን
ከላይ የተጠቀሱ መገለጫን ስምና ልብስ ያደረጉ ፍርፋሪ ለቃሚዎች
በምርጫ ስም የግል ኪሳቸውን ለማድለብ የሚፈፅሙት ተግባር መላው ሕዝቡ እንዲውቀው ታላቅ ትግል የምናደርግ መሆኑን ከወዲሁ በማሳወቅ የአማራ ሕዝባዊ ማሕበራት ፎረም በፖለቲካ ፓርቲም ሆነ በሲቢክ ማሕበር ስም በምርጫ ታዛቢነትም ሆነ ምርጫ ነክ ጉዳዮች ላይ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ተሳትፎ የሌለው መሆኑን በማሳወቅ ከሁሉም ማስተዋል ይቅደም እያልን በ1960ዎቹ የስልጣን ጥመኝነት ጥላቻ የቅኝ ገዥ ፍላጎት አስፈፃሚ የኢትዮጵያን የወቅቱን የፖለቲካ አሰላለፍ ያልተረዱ የተዘበራረቀ የፖለቲካ አላማ ያላቸው እና በስሜት ያበዱ የጨርቦሌ ፖለቲካ የልጥ ፓርቲ ቅዥት ዛሬ ነገም የሚቆም የአማራ ሕዝብ ትግል እንደሌለ በማሳወቅ ጭምር ነው።
ታላቅ እንደነበርን ታላቅ እንሆናለን
ግንቦት 23 /2018 ዓ.ም
አማራ - ባህርዳር
#ሰበር_የድል_ዜና
በሸዋ ከሁከቱ ኮሮች የተውጣጡ ጥቂት ሻለቆች እጅን በአፍ የሚያጭን ጀብድ ፈፀሙ:: ራሱን ጥምር ጦር ነኝ ብሎ የሚጠራው ቀይ ቦኔት ለባሹ የሀገር የመከላከያ ኮማንዶ, የአማራ አድማ ብተና እና የአማራ ሚሊሻ እንደ ቅጠል እየረገፈ ይገኛል::
አፋብን ሸ/ጠ/ግ/አ/ዕዝ
የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ዛሬ እሁድ ከማለዳ 11:00 ጀምሮ ከሁለቱ ኮሮች በተውጣጡ ጥቂት ሻለቃዎች በደብረብረሃን ከተማ ዙሪያ እያካሔደ ባለው ጠንካራ የቅንጅት ኦፕሬሽኝ የአገዛዙ ሪፓብሊካን ጋርዶችን ጨምሮ በርካታ አየር ወለድ ኮማንዶ አባላት፣ የማራ አድማ ብተና እና የአማራ ሚሊሻ አባላት ተደምስሷል።
የሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ከአፄ አምደ ፅዮን ኮር እና ከአፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ኛ ኮር የተወጣጡ የክፍለጦር ውስን ሻለቆች የአንበሳውን ድርሻ በወሰዱበት አስደማሚ ልዩ መብረቃዊ ኦፕሬሽን ዘመናዊ ሹተርን (Shutter) ጨምሮ በርካታ ዘመናዊ ጥርጥር ክላሽን ኮቭ እና በርካታ ተተኳሽ እንዲሁም የአገዛዙ ሰራዊት በምርኮ ሲያዙ፣ በርካቶች ተደምስሰዋል።
ጀግናው የፋኖ ሰራዊታችን የአውደ ውጊያ አድማሱን አስፍቶ በደብረብርሀን ዙሪያ እያካሔደ ባለው የተቀናጀ ውጊያ በአይነቱ ለየት ያለ ድል እየተጎናፀፈ ሲሆን ፣ በርካታ የአየር ወለድ አባላቱ ቁስለኛና አስክሬን በ 4 አንቡላንሶች ወደ ደብረብርሃንና አዲስ አበባ እያመላለሰ ይገኛል።
በሌላ የደፈጣ አውደ ውጊያ የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ አጼ ዘር ዓያዕቆብ አንደኛ ኮር ሰባት ለሰባ ክፍለጦር ትላንት ማታ ማለትም በቀን 23/08/208 ዓ.ም ከምሽቱ 12:00 ሰዓት ከአጣዬ ከተማ ተነስቶ ወደ ጨፋ ሲጓዝ የነበረ ሚሊሻ በጫነ ተሽከረካሪ ላይ ጥቃት በመሰንዘር ዋናው አስፋልት ልዩ ቦታው እንቶሌ በሚባል አካባቢ ደፈጣ በመጣል ፋኖዎቹ ታሪክ ሰርተዋል። በዚህም በመኪናው ላይ ተጭነው የነበሩት ሚሊሻዎች በርካቶቹን መደምሰስ ተችሏል።
ዕዙ እየተካሄደ ያለውን የአውደ ውጊያ መረጃዎችን አሰባስቦ በዝርዝር የሚመለስ መሆኑን እየጠቆምን ውጊያው ተጠናክሮ መቀጠሉን በመግለፅ በድጋሚ ድል ለጀግናው የፋኖ ሰራዊታችን እንመኛለን።
''ክብር ለትግሉ ሰማዕታት''
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን
የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ
ግንቦት 23/2018ዓ.ም
+9
➤ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ አፄ አምደ ጽዮን ኮር በደብረ ብርሃን ዙሪያ ደማቅ አኩሪ ድል ተቀዳጅቷል !!! 💪🔥
ግንቦት 23/2018 ዓ.ም
ድል ለአማራ‼️
በአፋብን ቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክፍለ ጦር ጊ/መንግስት አስተዳደር የተላለፈ ጥብቅ መልዕክት:
64ኛ ክ/ጦር ግንቦት 23/2018 ዓ.ም
~~~
ኩሩው አማራ በመሠረታት እና በኖረባት ሀገሩ ዘሩ እንዳይቀጥል ለበርካታ ዘመናት ሙህራኑን እና የነቃ ዜጋውን ሁሉ ሲገብር ቆይቷል። ታሪካዊ ጠላት ነን ባዮች የሐሰት ትርክትን እየፃፋ ለብሄር ጥላቻም ዳርገውት ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ተንቀሳቅሶ ሰርቶ ለመኖር አቅቶት ይባስ ብሎም በእድሜው ያፈራውን ቤት እና ሀብት ንብረት እየተወረሰ ጠላቶቹ ወደሠሩለት የብሔር አጥር ብቻ እንዲኖር ተፈርዶበታል።
ሆደ ሰፊነቱ ከልክ ሲያልፍ በሰላማዊ ሠልፉ አትግደሉኝ ቢልም እንደ ልማደኛ ሲቆጥሩት ይህን የጭቆና ቀንበር አሽቀንጥሮ ለመጣል ነፍጥ ካነሳ እነሆ 3 ዓመት ሞላው። በእነዚህ የትግል ዓመታት በዓለም ተፈፅሞ የማያውቅ የጦር ወንጀሎች ተፈፅመውበታል።
✍️ ንፁሀን በድሮን እና በከባድ መሳሪያ በጅምላ ተጨፍጭፈዋል፣
✍️ የሀይማኖት እና የህዝብ ተቋማቱ በሙሉ ወድመዋል፣
✍️ በሺዎች የሚቆጠሩ የነቁ ሙህራን አድራሻቸው ጠፍተው እስር ቤት ወርደዋል፣
✍️ብዙ ሺዎች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው በድንኳን እንዲኖሩ ተደርጓል፣
✍️የኢኮኖሚ ፖለቲካዊ አሻጥር ተሠርቶበታል። ሞኝ መሳይ ገዥዎቹ ይህን ሁሉ ደባ እየፈፀሙበት ለሚቀጥሉት አምስት አመታት ዘሩን ፈፅሞ ያጠፉ ዘንድ ሠላማዊ ምርጫ እያሉ ይላላጣሉ። ለዚሁም አንድም እውነተኛ ተፎካካሪ ፓርቲ በሌለበት ብል*ግና ግንቦት 24/2018 ዓ.ም የምርጫ ቀን ብለው ቢወስኑለትም በተቆጣጠሯቸው ጥቂት የወረዳ ከተሞች የምርጫ ኮረጆዎች አስቀድመው ተሞልተው ተቀምጠዋል። ምክንያት የምርጫ ታዛቢም ሆነ የሚሞግት ተፍካካሪ ባለመኖሩ ነው።
በዚህም መሠረት የማይታጠፍ የትጥቅ ትግል የጀመረው ድርጅታችን አፋብን በተቆጣጠረው 80% ነፃ ግዛቱም ሆነ፣ ጠላት በተቀመጠበት ከተማ ምንም አይነት የማደናገሪያ ምርጫ መካሄድ ስለሌለበት፦
1ኛ.በከተሞች ያለ ማህበረሰብ የራሱን ጥንቃቄ እንዲያደርግ፣
2ኛ.በጊ/መንግስት አደረጃጅት ስር ያለው የጎበዝ አለቃ ጦር ለግንቦት 24/2018 ዓ.ም ለትዕዛዝ ዝግጁ ሆኖ እንዲጠባበቅ በጥብቅ እናሳውቃለን።
ላናሸንፍ የጀመርነው ትግል የለም!! አማራነት ወይም ሞት ድል ለአማራ ፋኖ !! ድል ለአማራ ህዝብ!!
አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ !!
ግንቦት 23/2018 ዓ.ም
ፋኖ ሞገስ ውዱ
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክ/ጦር ጊ/መንግስት ኃላፊ
ሰበር ዜና!
አፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዘለቀ ዕዝ 208ኛ ኮር ደባርቅ ከተማ በልዩ ኦፕሬሽን የአገዛዙን 53ኛ ክፍለጦር አመራር ከነ ሶስት አጃቢዎቻቸው ወደ ላይ ሽኝት አድርገውለታል።
በምስራቅ ጎጃም ደባይ ጠላት ግን ወረዳ በዛሬው ዕለት በዝግ አዳራሽ ምርጫ መደረጉ ተረጋግጧል።
ግንቦት 22/2018 ዓ.ም
~~
በምስራቅ ጎጃም ደባይ ጥላት ግን ወረዳ በቁይ ከተማ ባሉ ሁለት ቀበሌዎች ብቻ ብልፅግና ምርጫ ለማስፈፀም ወስኖ የተንቀሳቀሰ ቢሆንም ግንቦት 24 በቁይ ከተማ ውጊያ ይከፈትብኛል ብሎ በመስጋት የሁለቱን ቀበሌ ምርጫ አስፈፃሚዎችን በመጠቀም በዝግ አዳራሽ የምርጫ ወረቀት በኮሮጆ ሲያስገቡ ውለዋል።
በወረዳው ካሉ 25 ቀበሌዎች 22ቱ በፋኖ ቁጥጥር ስር በማዋላቸው ከቁይ ከተማ ውጭ መንቀሳቀስ የማይችለው የብልፅግና ስርዓት፦
- አርሶአደሮችን ( የመሬት ማረጋገጫ ደብተር መዝገብ ከመሬት አስተዳደር ቢሮ በመውሰድ)፤
- ነጋዴዎችን( ከንግድ ፍቃድ ማረጋገጫ - ከንግድ ፅ/ቤት ሰነድ በመውሰድ)
- የሐይማኖት አባቶችን (ከወረዳው ቤተ ክህነት መዝገብ በመውሰድ)
-ተማሪዎችን ( ከሁለተኛ እና አንደኛ ት/ቤት በተጨማሪም ከትምህርት ጽ/ቤት መዝገብ በመገልበጥ) ምዝገባና ድምፅ በኮሮጆ የማስገባት ሒደቱን መፈፀሙን አረጋግጠናል።
ይሁን እንጂ እስከ አሁን
ከቁይ- ደብረ ማርቆስ
ከቁይ- ቢቸና
ከቁይ- ናብራ ፣ ደብረ እየሱስ፣ የዳማ የሚወስዱ የትራንስፖርት መስጫ መንገዶች እንደተዘጉ ሲሆን በደባይ ጠላት ግን ወረዳ ቁይ ከተማን ጨምሮ ካሉ 25 ቀበሌዎች ውስጥ ደባይ ጥላት ግን ወረዳ ካሉ 25 ቀበሌዎች መካከል ፦
1.ደቤት
2.ገሜ.
3.አንገች
4.አጋምና
5.ወደብ ኢየሱስ
6.ይጥባቆ
7.ደብር ከተማ
8.ደብር ዙሪያ ቀቀሌ
9.ሽሜ
10.እነቆይ ቀበሌ
11.ናዝሬት መድሐኒአለም
12.ናብራ ሚካኤል
13.ናብራ የባላት
14.ናብራ ጎቻ
15.ቅድስቴ
16.የባባት
17.የዳማ
18.አፈራሜ
19.ጀረምስ
20.አራጆ
21.እመውላድ
22.ቁይ ዙሪያ ቀበሌዎች በ206ኛ ኮር 24/ኛ ክ/ጦር ደባይ ጮቄ ሻለቃ ቁጥጥርስ ሲሆን የደባይ ጠላት ወረዳ ጊዚያዊ መንግስት በሁሉም ቀበሌዎች መንግስታዊ መዋቅር በመዘርጋት እያስተዳደራቸው ይገኛል።
አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ!
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
+1
ጎጃሜ ቡዳ ነው አወ ቡዳ ነው፤
ቢበላ አይደለም ወይ ነጭ ያነካው፤
ቢበላ አይደለም ወይ ውጦ ያስቀረው።
ዛሬ በጠዋቱ የደጃዝማች በላይ ዘለቀ ልጆች በእነማይ ወረዳ ሁለት አምባ ዲቢሳ በኦባማ መኪና ሲንቀሳቀስ የነበረውን ጠላት ከነተሽከርካሪው ከጥቅም ውጭ አድርገውታል።
ይህን ዘመናዊ ሹተር መሳሪያ የታጠቀው 64ኛ ክ/ጦር በፈፀመው ጥቃት በርካታ የጠላት ኃይል ደምስሷል። በቢቸና ከተማም ምርጫ አስፈፃሚዎች ቀብር አስፈፃሚዎች ሁነዋል። በከተማዋ የባንዳ ልቅሶና እሪታ እየቀለጠ ነው።
እናማ አው "ቡዳ" ነን !! በላይ እየመጡ በታች ሲጠበቁ ማለት አሁን ነው።
+9
"ምርጫ ብሎ ነገር የለም " ያለው የባሶሊበን ወረዳ ህዝብ ከ206ኛ ኮር 34ኛ ክ/ጦር ጋር ውይይት አድርጓል።
ግንቦት 22/2018 ዓ.ም
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
በአማራን ህዝብ ላይ ግልፅ የዘር ማጥፋት ጦርነት የከፈተው የብልፅግና ስርዓት ያዘጋጀውን ምርጫ መንግስታዊ ውንብድና ነው ያለው የባሶሊበን ህዝብ ከ206ኛ ኮር 34ኛ ክ/ጦር ጋር እየመከረ ይገኛል።
በባሶሊበን ወረዳ የአገዛዙ ሰራዊት ሴቶችን እየደፈረ ንፁሐንን እየረሸነ ፣ በድሮን፣ በመድፍ እና በታንክ የታገዘ ጦርነት እንደቀጠለ ባለበት ነባራዊ ሁኔታ ይደረጋል የተባለው ምርጫ በዲሽቃ፣ በሞርተር እና በአረመኔው ሰራዊት ታጅቦ በሁለት ቀበሌዎች ብቻ ለማከናወን መወሰኑ የብልፅግናን ወንበዴነት የሚያረጋግጥ መሆኑን አንስተዋል።
አፋብን የጣለው የተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ገደብ ሙሉ ለሙሉ የተተገበረ ሲሆን ህዝቡ ከትግሉ ጎን መቆሙን ያረጋገጠበት እንደሆነም ተገልጿል።
አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ ! አዲስ ተስፋ!
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
አይበገሬው 64ኛ ክ/ጦር የሻላቃ መሪውን፣ ብሬን ተኳሽ ጨምሮ 10 የአድማ_ብተና፣ ፖሊስ እና የሚሊሻ አባላት በደፈጣ ኦፕሬሽን እስከወዳኛው ሲያስወግድ 7ቱ ቀላል እና ከባድ ቁስለኛ ሆነዋል!!
64ኛ ክ/ጦር ግንቦት 22/2018 ዓ.ም
~~~~~~~
ግንቦት 22/2018 ዓ.ም አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር አይበገሬው 64ኛ ክ/ጦር ቃኝና መሃንዲስ በእነማይ ወረዳ ሁለት አምባ ዲቢሳ ቀበሌ የአገዛዙን የሐሰት ምርጫ እና አፋብን ያወጣውን የመንገድ ክልከላ በጣሰ ባጃጅ ላይ እርምጃ ሲወሰድ የአገዛዙ የሐሰት ምርጫ ለማስፈፀም ከየትመን ከተማ ወደ ቢቸና ከተማ በአንድ ኦባማ በጉዞ ላይ የነበሩ አድማ_ብተና፣ፖሊስ እና ሚሊሻ የጫነ ተሽከርካሪ በወሰደው ልዩ የደፈጣ ኦፕሬሽን ድል ተቀዳጅቷል።
በክ/ጦሩ ቃኝ እና መሃንዲስ አባላት ቁጥጥር ስር የዋለው ባጃጅ ለማስለቀቅ ከየትመን ከተማ በአንድ ኦባማ በጉዞ ላይ የነበሩ አድማ_ብተና፣ፖሊስ እና ሚሊሻ አባላትን በመያዝ ወደ ሁለት አንባ ዲቢሳ ቀበሌ ያቀና ቢሆንም በጀግኖቹ የደጅ አዝማች በላይ ዘለቀ ልጅች በፊደራል መንገድ ጥቁር አስፖልት ሁለት አምባ ዲቢሳ ልወያ ጎጥ ላይ በወሰዱት የደፈጣ ጥቃት የአገዛዙ ቅጥረኛ #ሚሊሻ አባላት ወደ አፈርነት ተቀይረዋል።
የ64ኛ ክ/ጦሩ ቀኝ እና መሃንዲስ በሰራው ልዩ የደፈጣ ኦፕሬሽን 10 የሞተ ሲሆን 7 ቀላል እና ከባድ ቁስለኛ ሆነዋል ከእነዚህም ውስጥ:-
1ኛ. ላለም ጌታነህ አድማ_ብተና ሻለቃ መሪ የሞተ
2ኛ. ፖሊስ ይታያል ሙሉቀን ብሬን ተኳሽ የሞተ
3ኛ. ቢያድግ አይችሉም የማህበራት ፅ/ቤት ኃላፊ ቀላል ቁስለኛ
4ኛ. ሚሊሻ ሰይድ ዳውድ ቀላል ቁስለኛ እና
5ኛ. ሚሊሻ ጌትነት ውበት
6ኛ. ሚሊሻ ስማቸው ይሆንስ
7ኛ. ሚሊሻ ይበልጣል ሽፈራው ከባድ ቁስለኛ በመሆን ደ/ማርቆስ ሆሲፓታል የገቡ ሲሆን ስማቸውን ለግዜው ማግኘት ያልቻልናቸው የአገዛዙ ቅጥረኛ ሚሊሻ እና አድማ ብተና አባላት በአንድ ፖትሮል እና አንድ አንቡላስ ሙት እና ቁስለኛ ሆነው ቢቸና ከተማ መግባታቸው ተረጋግጦል። በዚህ የደፈጣ ጥቃት ሚሊሻዎችን የጫነ አንድ ኦባማ ተሽከርካሪ ከጥቅም ውጭ ሆኗል።
በፋኖ ሀይሎች ከፍተኛ ጉዳት ያስተናገደው የአገዛዙ ቅጥረኛ ሚሊሻ #ሹፊር አየለ ግሩም የተባለ የቢቸና ተወላጅ አስገድደው እንዲጭናቸው ከአደረጉ በሆላ ለፋኖ ቀድመህ መረጃ በመስጠት ነው በማለት በአሰቃቂ ሁኔታ ገለውታል። በየትመን ከተማ አቶ በላይነህ አድማስ የተባለ ንፁሀን በአራት ጥይት ተመቶ ከባድ ቁስለኛ የሆነ ሲሆን በደጀን የመጀመርያ ደረጃ ሆሲፒታል በመግባት ህክምና እያገኘ ይገኛል።
የደጅ አዝማች በላይ ዘለቀ ልጆች የ64ኛ ክ/ጦር ቀኝ እና መሃንዲስ በሰሩት ከባድ የደፈጣ ጥቃጥ አገዛዙ በድንጋጤ ውስጥ መግባቱ የተነሳ ከደ/ማርቆስ፣ ደጀን፣ የትኖራ፣ ጢቅ የሚገኝውን የሰው ሀይሉን ከከባድ መሳሪያዎች መድፍ፣ ዙ23፣ አራት ድሽቃ የመሳሰሉት በመያዞ በሸበል በረንታ መረገጭ ንዑስ ከተማ በመግባት ወደ አራጢ ከተማ ከባድ መሳሪያ ሲተኩስ ውሏል።
በዚህ የደፈጣ ጥቃት ዘግይተው የሚደርሱን ትክክለኛ መረጃዎችን ለህዝባችን፣ ለትግሉ ደጋፊ እና ለሰራዊታችን መረጃው እንደደረሰን በክ/ጦሩ ድር ገፅ የምንገልፅ መሆኑን እናሳውቃለን።
ላናሸንፍ የጀመርነው ትግል የለም!! ወጥር አማራ🔥
አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ!!
ግንቦት22/2018 ዓ.ም
Yibeltal Getie Mitiku
አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክ/ጦር ሕዝብ ግንኙነት
የአገዛዙ 103ኛ ኮማንዶ ክፍለጦር አባላት መክዳትን ተከትሎ የፋኖ አመራሩ ወላጅ እናት በብልፅግናው አመራሮች መታሰራቸውን ኮሩ አስታወቀ።
አፋብን ሸ/ጠ/ግ/አ/ዕዝ
ያለማቋረጥ በርካታ የ103ኛ ኮማንዶ ክፍለጦር አባላት በየቀኑ ፋኖን እየተቀላቀሉ ሲሆን፣ በዛሬው ዕለትም ግንቦት 22 ቀን 2018ዓ.ም የክፍለጦሩ ጋንታ መሪ የኦሮሞ ብሔር ተወላጁ ፶ አለቃ ፈይሳ ገመቹ የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ አፄ አምደ ፅዮን ኮር የ7ለ70 ክፍለጦርን መቀላቀሉን ኮሩ በላከው የግንባር መረጃ አስታውቋል።
የመከላከያውን ፍለሰት ተከትሎ "ልጅሽ ሰራዊታችንን እያስኮበለለብን ነው" በሚል የፈጠራ ወሬ ከቀጠናው ውጭ የሚገኘውን የአፄ አምደ ፅዮን ኮር ምክትል ዘመቻ ኃላፊ የፋኖ መመኪያ መሸሻ ወላጅ እናት የሆኑትን ወ/ሮ አሳበች መንገሻ በአገዛዙ ኃይሎችና በመከላከያ አመራሩ ትዕዛዝ ሰጭነት ከግንቦት 18/2018ዓ.ም ጀምሮ በአጣዬ ከተማ ዝግባ ሰፈር የመከላከያ ካምፕ ውስጥ በግፍ ታስረው እየተሰቃዩ መሆናቸውን ቤተሰቦቻቸው ገልፀዋል።
በዚሕ አረመኔ ድርጊቱ ያላቆመው የአገዛዙ ዘራፊ ሀይል የኤፍራታና ግድም ወረዳ የመተኬ ሸረፋ ነዋሪ የሆኑትን የሁለት አባት አርበኞችን የአቶ አውራሪስ ማሞን ሁለት በሬዎች እና የሴት ልጁን ሳምሰንግ ዘመናዊ ስልክ እንዲሁም የአቶ ካሳዬ ክብረትን አንድ በሬ በመዝረፍ የሀይማኖት ግጭት ለማስነሳት በማሰብ ለኢድ ዓል-አድሃ (አረፋ) በዓል ለመከላከያ ሰራዊቱ የተዘረፉትን 3 በሬዎች መታረዳቸውን ኮሩ አረጋግጧል።
አገዛዙ እንደ ህዝብ የአማራን ህዝብ እየገደለና ለከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ውድቀት እየዳረገው መሆኑን መላው ህዝባችን ጠንቅቆ በማወቅ በውድቀቱ ዋዜማ ላይ የሚገኘውን አሸባሪ ስርዓት ለመጣል በሀሰተኛ የምርጫ ድራማ ላይ ባለመሳተፍ ከፋኖ ጎን ተሰልፎ ነፃነቱን እንዲያውጅ ሲል ኮሩ መልዕክቱን አስተላልፏል።
''ክብር ለትግሉ ሰማዕታት''
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን
የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ
ግንቦት 22/2018ዓ.ም
