uz
Feedback
قناة للْمࢪأة السلفية 𐙚

قناة للْمࢪأة السلفية 𐙚

Kanalga Telegram’da o‘tish

https://t.me/https_Aselefya وَمَن جَاهَدَ فَإِنَّمَا يُجَاهِدُ لِنَفْسِهِ ۚ إِنَّ اللَّهَ لَغَنِيٌّ عَنِ الْعَالَمِينَ

Ko'proq ko'rsatish
1 558
Obunachilar
+124 soatlar
+27 kun
+330 kun
Postlar arxiv
~ ምቀኛ ሰው ቁጭቱ ረጅም እድገቱ ምንም ነው። ኢማም አሽሻፊዒይ (ረሒመሁላህ) 🍁
~ ምቀኛ ሰው ቁጭቱ ረጅም እድገቱ ምንም ነው። ኢማም አሽሻፊዒይ (ረሒመሁላህ) 🍁

🧷ችግር እንደ ማዕበል ነው ፤ ታግሰው ከጠበቁት ያልፋል ፈተና እንደ ዱላ ነው፣ ጨክነው ከቻሉት ይሰበራል መከራ እንደ ፍጡር ሁሉ ነው፣ አጀልና የጊዜ ገደብ አለው ያበቃል፡ የጠበበ ነገር መስፋቱ አይ
🧷ችግር እንደ ማዕበል ነው ፤ ታግሰው ከጠበቁት ያልፋል ፈተና እንደ ዱላ ነው፣ ጨክነው ከቻሉት ይሰበራል መከራ እንደ ፍጡር ሁሉ ነው፣ አጀልና የጊዜ ገደብ አለው ያበቃል፡ የጠበበ ነገር መስፋቱ አይቀርም አንቆ የያዘህ ነገር ይረግባል ያሳሰበህ እንደ ጉም ይተናል ያስጨነቀህ ጉዳይ እፎይታ ይኖረዋል አንዳንድ ጊዜ ተስፋ"አንዳንዴ ደግሞ ባዶነት አንዳንዴ ጨለማ" አንዳንዴ ደግሞ ብርሃን እየታየን ዕድሜያችንን በዚሁ መሃል እንጨርሳለን" ህይወት በእየፍርጇ ለየቅል ናት" አንዳዱ የሚታከምበት ገንዘብ ሀብት ኑሮት ከማይድን በሽታ ጋር ይሰቃያል" አንዳንዱ ደግሞ በገንዘብ እጥረት ምክኒያት ታክሞ መዳን የሚችለውን በሽታውን  ተው ማረኝ እያለ  አብሮት ይኖራል። ~

🧷ችግር እንደ ማዕበል ነው ፤ ታግሰው ከጠበቁት ያልፋል ፈተና እንደ ዱላ ነው፣ ጨክነው ከቻሉት ይሰበራል መከራ እንደ ፍጡር ሁሉ ነው፣ አጀልና የጊዜ ገደብ አለው ያበቃል፡ የጠበበ ነገር መስፋቱ አይ
🧷ችግር እንደ ማዕበል ነው ፤ ታግሰው ከጠበቁት ያልፋል ፈተና እንደ ዱላ ነው፣ ጨክነው ከቻሉት ይሰበራል መከራ እንደ ፍጡር ሁሉ ነው፣ አጀልና የጊዜ ገደብ አለው ያበቃል፡ የጠበበ ነገር መስፋቱ አይቀርም አንቆ የያዘህ ነገር ይረግባል ያሳሰበህ እንደ ጉም ይተናል ያስጨነቀህ ጉዳይ እፎይታ ይኖረዋል አንዳንድ ጊዜ ተስፋ"አንዳንዴ ደግሞ ባዶነት አንዳንዴ ጨለማ" አንዳንዴ ደግሞ ብርሃን እየታየን ዕድሜያችንን በዚሁ መሃል እንጨርሳለን" ህይወት በእየፍርጇ ለየቅል ናት" አንዳዱ የሚታከምበት ገንዘብ ሀብት ኑሮት ከማይድን በሽታ ጋር ይሰቃያል" አንዳንዱ ደግሞ በገንዘብ እጥረት ምክኒያት ታክሞ መዳን የሚችለውን በሽታውን ተው ማረኝ እያለ አብሮት ይኖራል። ~

🧷መልካም ትዕግስት ብሎ ማለት በችግር መሀል ሁነሽ እየተፈተንሽ" ልብሽ ግን አልሀምዱ ሊላህ ሲል ነዉ። https://t.me/https_Aselefya
🧷መልካም ትዕግስት ብሎ ማለት  በችግር መሀል ሁነሽ እየተፈተንሽ" ልብሽ ግን አልሀምዱ ሊላህ ሲል ነዉ። https://t.me/https_Aselefya

ራስን በራስ ማርካት!–ክፍል 1― ~ በርግጥም የምንኖርበት ዘመን ከባድ ነው። ቴክኖሎጂው የመጣው ህይወትን ሊያቀል ነበር፤ ነገር ግን ሰይጣን ለክፉ ተጠቅሞበት በጣትህ ጫፍ በሚነካ ስክሪን አማካኝነት ወደ መኝታህ ገብቷል። ዛሬ ላይ ብዙ ወጣቶች በድብቅ የሚያለቅሱበት፣ ከሰው ተደብቀው አንገት የሚደፉበት፣ የህሊና እረፍት ያጡበት ትልቁ በሽታ «ኢስቲምናእ» (ራስን በራስ ማርካት) አንዱና ትልቁ የወጣቱ ችግር ነው። ይህ ተግባር ዝም ብሎ መጥፎ ልማድ ብቻ አይደለም፤ የወጣትነትን ወዝ የሚጠጣ፣ ከአላህ የሚያጣላ፣ የነገን ተስፋ የሚያጨልም «የድብቅ ካንሰር» ነው። እስቲ ቆም ብለህ ተመልከት! ጌታችን አላህ የሰው ልጅን ሲፈጥር ክብር ሰጥቶታል። ስሜትንም የሰጠህ ለተፈቀደ ትዳርና ለዘር መተካት እንጂ በእጅህ ልትጫወትበት አይደለም። በቁርኣን ውስጥ አማኞችን ሲገልፅ እንዲህ ይላል፡- «እነዚያም እነሱ ብልቶቻቸውን ጠባቂዎች ናቸው፡፡ በሚስቶቻቸው ወይም እጆቻቸው በያዙት (ባሮች) ላይ ሲቀር፡፡ እነርሱ (በነዚህ) የማይወቀሱ ናቸውና፡፡ ከዚያም ወዲያ (ሌላን) የፈለጉ ሰዎች እነዚያ እነሱ ወሰን አላፊዎቹ ናቸው፡፡» (ሱረቱ አል-ሙእሚኑን 5-7) ከዚህ አያ መረዳት እንደምንችለው ከትዳር ውጪ ስሜትን ማውጣት «ወሰን አላፊነት» ነው። ነብያችን(ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) ወጣቶችን አግብተው ራሳቸውን እንዲጠብቁ፣ ካልቻሉ ደግሞ እንዲጾሙ አዘዋል እንጂ ራስን በራስ ማርካትን አልፈቀዱም። ውድ ወንድሜ! ስሜትህን በተከለከለ መንገድ ባወጣህ ቁጥር፣ ከአላህ እዝነት ትርቃለህ። ዱዓህ እንዳይሰምር፣ ዒባዳህ እንዳይጣፍጥህ የሚያደርገው ይሄው የረከሰ ተግባር ነው።አላህ የሰጠህን የተከበረ አካል ማርከስ በእስልምና የተጠላ ተግባር ነው። ከ አላህ ጋር ከማጣላቱ ባሻገር ይህ ሱስ ከአደንዛዥ ዕፅ ባልተናነሰ በአእምሮ ላይ ከባድ ተጽእኖ አለው። ዶክተሮች ይህን ተግባር በሚፈፅሙ ሰዎች ላይ የሚከተሉትን አደጋዎች ያስቀምጣሉ፡- 📎1ኛ―የአእምሮ ባርነት (Addiction): ልክ እንደ ኮኬይን አእምሮህ ላይ የደስታ ሆርሞን (Dopamine) በውሸት እንዲረጭ ስለሚያደርግ፣ አእምሮህ ይደነዝዛል። ነገ ከትዳር አጋርህ ጋር የምታገኘው ተፈጥሯዊ ደስታ አይጣፍጥህም። 🕹2ኛ―የማስታወስ ችሎታ መቀነስ እና የመርሳት ችግር፡ አእምሮ ሁሌም በወሲባዊ ቅዠት ስለሚጠመድ፣ ለትምህርትና ለቂርኣት እንድሁም ለቁምነገር የሚሆን ቦታ ያጣል። ብዙ ተማሪዎችም ሆኑ ብዙ ዒልም ፈላጊዎች ትምህርታቸውን እና ዒልም መማራቸውን የጠሉት በዚህ ምክንያት ነው። 😞3ኛ―የጭንቀት እና የደብርት በሽታ (Depression): ድርጊቱን ከፈጸምክ በኋላ የሚሰማህ የጥፋተኝነት ስሜት ራስን መጥላትና ባዶነት ወደ ድብርት ይወስዳል። "እኔ ርካሽ ነኝ" ብለህ እንድታስብ ያደርግሃል። 👨‍👦4ኛ―የትዳር ህይወትን ማበላሸት፡ ራስን በራስ በማርካት የለመደ ሰው፣ በትዳር ውስጥ ያለውን ትክክለኛ ግንኙነት መፈጸም ይከብደዋል (Sexual Dysfunction)። ለወንዶች የቶሎ መጨረስ ችግር (Premature Ejaculation) ዋነኛ መንስኤው ይህ መጥፎ ልማድ ነው። 🎯5ኛ―የሰውነት መዛል እና የጀርባ ህመም፡ የወጣትነት ጉልበትህን በከንቱ እያፈሰስክ ስለሆነ፣ ለእድገት የሚሆን ጉልበት ታጣለህ። አይንህ ይቦዝዛል፣ ጉልበትህ ይንቀጠቀጣል፣ኑርህም ይጠፋል…ከሁሉም በላይ የሚያስፈራው ግን የአኼራ ጉዳይ ነው። ውድ ወንድሜ! እስኪ ለአፍታ ቆም ብለህ አስብ!ያ በጨለማ የቆለፍከው በር ሰዎች እንዳያዩህ ነው አይደል? ግን የዓለማቱ ጌታ አላህ እየተመለከተህ እንደሆነስ ዘነጋህን? እጅህ፣ እግርህና ብልትህ ነገ በአላህ ፊት «እንዲህ አደረገብን»ብለው ሲመሰክሩብህ ምን ልትመልስ ነው? ያንተ እኩዮች ቁርኣን ሲያነቡ፣ ኢልም ሲቀስሙ፣ በትዳር ሲረጋጉ፤ አንተ ግን መጸዳጃ ቤት ውስጥ ወይም አልጋህ ላይ ከራስህ ጋር ትታገላለህ። ይህ ላንተ ክብር አይመጥንም! የወደፊት ሚስትህ ንጹህ ሆና እየጠበቀችህ፣ አንተ ግን አላህ በሐላል ላይ እንድታውለው የሰጠህን ውድ ስጦታ በቆሻሻ ቦታ እያፈሰስከው ነው። ነገ ትዳር ስትይዝ የምትሰጠው ፍቅር፣ የምትሰጠው ጉልበት ከየት ይመጣል? ጨርሰህው እኮ ነው! ሞት በዚያ ሁኔታ ውስጥ ቢመጣስ? አላህ ይጠብቀንና፣ ያንን ቆሻሻ ቪዲዮ እያየህ ወይም ያንን ሐራም እየፈጸምክ ነፍስህ ብትወጣ፣ ከአላህ ጋር እንዴት ትገናኛለህ? ወንድሜ... እህቴ... ይሄ ጉዳይ ቀልድ አይደለም። የእሳትና የጀነት ጉዳይ ነው። 🔍መፍትሄው ምንድን ነው? ☑ተስፋ አትቁረጥ! አላህ መሐሪ ነው። ዛሬውኑ ቆርጠህ ከተነሳህ መመለስ ትችላለህ።ወሏሂ ከዚህ ሱስ መውጣት ከባድ እንደሆኑ ብታስቡም በ አላህ ከታገዛችሁና ከወሰናችሁ እጁግ በጣም ቀላል ነው። ☑በንፁህ ልብ አልቅሰህ አላህን ምህረት ጠይቅ። «ጌታዬ ሆይ! ተሸነፍኩ፣ አቅም አነሰኝና እርዳኝ» በለው። ☑ብቸኝነትን አጥፋ። ይህ ሱስ የሚመጣው ለብቻ ስትሆን ነው። ከሰዎች ጋር ተቀላቀል። ስልክህን መኝታ ቤት አታስገባ። ☑የአይን ዚናን ተጠንቀቅ።እይታህን ስበር። በቲክቶክና በፌስቡክ የሚመጡ ስሜት ቀስቃሽ ምስሎችን አግድ (Block)። አይን የልብ መስኮት ናት። ☑ጾም እና ስፖርት ስራ። ነብያችን እንዳሉት ጾም ጋሻ ነው። ስፖርት ደግሞ ትርፍ ጉልበትህን በጥሩ ነገር እንድታወጣው ይረዳሃል። ☑ትዳርን አስብ። አቅሙ ካለህ አግብ። ካልቻልክ እራስህን ለትዳር አዘጋጅ እንጂ በሐራም አትጨርስ። 🫀ያ አላህ! በዚህ የሱስ ሰንሰለት ተጠፍረው የሚሰቃዩ ወንድም እህቶቼን አንተ ድረሰላቸው። በወንጀል የጠቆረውን ልባቸውን በምህረትህ ብርሃን አፅዳው። የዚህን ሱስ አስከፊነትና አስጠያፊነት አሳይተህ፤ ከልባቸው ጠልተው እንዲርቁትና በምትኩ የአንተን ፍቅርና የኢማንን ጣፋጭነት አላህ ይለግሳቸው። አላህ ሆይ! ወዳንተ መመለስን ለከበዳቸው ሁሉ እጃቸውን ይዘህ ወደ ብርሃን ማውጫው መንገድ ምራቸው። t.me/Sle_qelbachn1 t.me/Sle_qelbachn1

هذه الحياة الدنيا تبدأ ببكائك وتنتهي بالبكاء عليك" የዱኒያ ህይወት ባንተ ለቅሶ ትጀምርና ባንተ ላይ በማልቀስ ታልቃለች ። ~
هذه الحياة الدنيا تبدأ ببكائك وتنتهي بالبكاء عليك" የዱኒያ ህይወት ባንተ ለቅሶ ትጀምርና ባንተ ላይ በማልቀስ ታልቃለች ።   ~         

أشغلي نفسكِ بما ينفعكِ في الدارين، تزودي بالعلم النافع والعمل الصالح ولا تكوني من الغافلين في ثوب العابدين. https://t.me/http
أشغلي نفسكِ بما ينفعكِ في الدارين، تزودي بالعلم النافع والعمل الصالح ولا تكوني من الغافلين في ثوب العابدين. https://t.me/https_Aselefya

ተግባር ያበላሸውን ንግግር አያሥተካክለውም። ~
ተግባር ያበላሸውን ንግግር አያሥተካክለውም። ~

إستَمِع!

📚 አድ-ዳእ ወድ-ደዋእ(ሙኽተሶር) مختصر الداء والدواء -ክፍል 12- 🎙በ ወንድም አቡ ሱፍያን t.me/Sle_qelbachn1

መልካምነት! መልካምነት ሰው ለራሱ የሚያስፈልገውን መልካም ነገር ለሌላው እንድሆንለት መፈለግ ለእርሱ ያለውን ማካፈል:- ኢስላም ባዘዘው መሠረት ለማንኛውም አካል ዘር :ቀለም:ፆታ:ማንነት........
+1
መልካምነት!
መልካምነት ሰው ለራሱ የሚያስፈልገውን መልካም ነገር ለሌላው እንድሆንለት መፈለግ ለእርሱ ያለውን ማካፈል:- ኢስላም ባዘዘው መሠረት ለማንኛውም አካል ዘር :ቀለም:ፆታ:ማንነት........ሳይለይ በጎ መዋልን ይጠቀልላል" መልካምነት ከሰው ልጆች አልፎ ለእርድ በቀረበች እንስሳ ላይ መልካም መፈፀም እንዳለብን ኢስላም ይጠቁማል: መልካምነት የውለታ መመለስን ቀመር አይተካም: መልካም ስትሆን ፊትህ በፈገግታ ይሞላል: መልካም ስትሆን ልቦነህ በደስታ ይሞላል: መልካም ስትሆን በተግባርህ ላይ ነሻጧ ይኖርሀል። https://t.me/UstazKedirAhmed https://t.me/UstazKedirAhmed

🧷كان مالك بن دينار رحمه الله يقول ኢማም ማሊክ ቢን ዲናር እንድህ የል,ነበር « إِنَّمَا الْخَيْرُ فِي الشَّبَابِ » ጡሩ ነገር ያለው በወጣትነት ውስጥ ነው"
🧷كان مالك بن دينار  رحمه الله يقول ኢማም ማሊክ ቢን ዲናር እንድህ የል,ነበር « إِنَّمَا الْخَيْرُ فِي الشَّبَابِ » ጡሩ ነገር ያለው በወጣትነት ውስጥ ነው" ወንድም እህቶቸ,,ኸይር ለመሥራት በላጩና የሚያምረው በወጣትነታችን ነውና" በወጣትነታችን መልካም ስራወችን አብዝተን እንስራ። https://t.me/https_Aselefya

🧷كان مالك بن دينار رحمه الله يقول ኢማም ማሊክ ቢን ዲናር እንድህ የል,ነበር « إِنَّمَا الْخَيْرُ فِي الشَّبَابِ » ጡሩ ነገር ያለው በወጣትነት ውስጥ ነው"
🧷كان مالك بن دينار  رحمه الله يقول ኢማም ማሊክ ቢን ዲናር እንድህ የል,ነበር « إِنَّمَا الْخَيْرُ فِي الشَّبَابِ » ጡሩ ነገር ያለው በወጣትነት ውስጥ ነው" ወንድም እህቶቸ,,ኸይር ለመሥራት በላጩና የሚያምረው በወጣትነታችን ነውና" በወጣትነታችን መልካም ስራወችን አብዝተን እንስራ። ~

የዱንያ እና የአኺራ እሳት https://t.me/msirage4

⏰ለማስታዎስ! ~ ዛሬ ማታ አድ-ዳእ ወድ-ደዋእ(ሙኽተሶር) مختصر الداء والدواء ደርስ ይኖረናል! (ኢንሻ አላህ)– ⚠️ሸይኹ ወንጀሎች በሕይዎታችን ላይ የሚያመጡትን አደጋ መዘርዘር ቀጥለዋል! t.me/Sle_qelbachn1

ውድ እህቴ ሆይ! በመጀመሪያ፣ ይህንን ነገር በግልፅ ስትናገሪ "አደብ ማጣት" ሳይሆን፣ ነፍስሽን ለማዳንና ወደ አላህ ለመመለስ የምታደርጊው ሙጃሀዳ መሆኑን እወቂ። በልብሽ ውስጥ ያለው ፀፀት አላህ እ
ውድ እህቴ ሆይ! በመጀመሪያ፣ ይህንን ነገር በግልፅ ስትናገሪ "አደብ ማጣት" ሳይሆን፣ ነፍስሽን ለማዳንና ወደ አላህ ለመመለስ የምታደርጊው ሙጃሀዳ መሆኑን እወቂ። በልብሽ ውስጥ ያለው ፀፀት አላህ እንደወደደሽና እንደመረጠሽ ምልክት ነው። ልብሽ ቢሞት ኖሮ፣ ወንጀሉን እየሰራሽ ሰላም ይሰማሽ ነበር። ነገር ግን አላህ ከዚህ አዘቅት እንድትወጪ ፈልጎ ነው ይህንን የጸጸት እሳት በውስጥሽ የለኮሰው። የኔ ምክሬ፦ 1ኛ―"ላለመገናኘት መወሰን" ብቻ በቂ አይደለም፤ መንገዱን መዝጋት እንጂ! "እንፀፀታለን፣ ላለመገናኘት እንወስናለን፣ ግን ተመልሰን እንገናኛለን" ያልሽው ነገር በጣም የተለመደ የሸይጣን ወጥመድ ነው። ችግሩ ያለው ውሳኔው ላይ ሳይሆን አፈፃፀሙ ላይ ነው።አንቺና እሱ ብቻችሁን በሆናችሁ ቁጥር እናንተ እሳትና ቤንዚን ናችሁ። "አንነካካም" ብሎ መገናኘት፣ እሳት እያቀጣጠሉ "አትቃጠል" እንደማለት ነው። ስለዚህ የመጀመሪያው መፍትሄ፤ ግንኙነቱን ሙሉ ለሙሉ ማቋረጥ ነው። ሃላል እስክትሆኑ ድረስ ስልክ መደዋወል፣ ቻት ማድረግ፣ እና በአካል መገናኘት መቆም አለበት። "በቀስ በቀስ እተዋለሁ" የሚባል ነገር በዝሙት መንገድ ላይ አይሰራም። ቆራጥ ሁኚ! ቁጥሩን ብሎክ አድርጊ፣ ይህ የሚከብድሽ አሁን ብቻ ነው፤ በኋላ ግን ነፃነት ይሰማሻል። 2ኛ― "ተማሪዎች ስለሆንን አንጋባም" የሚለው አስተሳሰብ በብዙ ወጣቶች ላይ ያለ የተሳሳተ ግንዛቤ ነው።ቤተሰብን በማማከር፣ ወጪን ሳታበዙ፣ ተማሪዎችም ሆናችሁ ኒካህ ማሰር ትችላላችሁ። የግድ አብሮ መኖር፣ ትልቅ ቤትና ሰርግ አያስፈልግም። ኒካህ ካሰራችሁ በኋላ እራሳችሁን ችላችሁ እስክትኖሩ ድረስ በቤተሰብ ቤት እየኖራችሁ እንደ ባልና ሚስት መገናኘት ትችላላችሁ። ይህም ግንኙነታችሁን "ሃላል" ያደርገዋል፤ ከአላህም ቁጣ ያድናችኋል።ነገር ግን ይህንን አማራጭ አቅርበሽለት "አይ አሁን ላይ ለ ትዳር ዝግጁ አይደለሁም" ካለ፣ እመኚኝ ይህ ወንድ ለጊዜያዊ ስሜቱ እንጂ ለአንቺ ክብርና ለዲንሽ አይጨነቅም። በዚህ ጊዜ እሱን ማጣት ለህይወትሽ ትርፍ ነው። ቁርኣን ላይ አላህ "ዝሙትን አትስሩ" ሳይሆን ያለው "ወደ ዝሙት አትቅረቡ" ነው። ምክኒያቱም አንዴ ከተጠጋሽ በኋላ መመለሱ እጅግ ከባድ ስለሆነ ነው። አሁን የምትሰሩት ነገር "ለዝሙት የቀረበ" እንጂ ዋናው አይደለም ብለሽ እንዳትጽናኚ። ነገሩ እንደ ቁልቁለቱ መንገድ ነው፤ ፍሬን የለውም። ዛሬ የጀመራችሁት ንክኪ፣ ነገ ወደማይመለስ የከፋ ወንጀል እና እርግዝና ወይም በሽታ ሊመራ ይችላል። ያኔ ፀፀቱ የከፋ ይሆናል። ውድ እህቴ፣ አንቺ የአላህ ውድ ባሪያ ነሽ። አካልሽ የተከበረ ነው። ለጊዜያዊ ስሜት ተብሎ በየሳምንቱ የሚደረግ ንክኪ ክብርሽን ይነካል። "በሃላል እስክንገናኝ ድረስ እኔን ማግኘት አትችልም" በይው። ይሄ ወንድ እውነት የሚያከብርሽ ከሆነ ውሳኔሽን ያከብራል፤ ካልሆነ ግን መንገዱን ጨርቅ ያድርግለት። ስለዚህ ከዚህ ሰዓት ጀምሮ «አላህ ሆይ! ለአንተ ብዬ ይህንን ነገር ተውኩት፣ አንተ የተሻለውን ስጠኝ!» ብለሽ ቃል ግቢ። አሁንኑ ተውበት አድርገሽ በኢስቲግፋር እና በዱዓ ተመለሺ። ለአላህ ስትይ ስሜትሽን መተውሽ በራሱ ትልቅ ኢባዳ ነው። የመጨረሻ መልዕክቴ! ይህ ግንኙነት ወይ ወደ "ሃላል ጋብቻ" መቀየር አለበት፣ ወይም ሙሉ ለሙሉ መቆም አለበት። መሃል ላይ የሚባል ነገር የለም። መሃል ላይ መሆን ነፍስያሽን እያደማሽ እንድትኖሪ ያደርግሻል። ለአላህ ብለሽ የምትተይው ነገር ሁሉ፣ አላህ በሌላ በተሻለ ነገር እንደሚተካልሽ አስቢ። አላህ ልብሽን ያጽናልሽ፣ ከዚህ ፈተና በሰላም ያውጣሽ! ጠንካራ ሁኚ! ✍ደካማው ወንድምሽ አቡ ሱፍያን― t.me/Sle_qelbachn1 t.me/Sle_qelbachn1

ሰዎች በስራ ከተሽቀዳደሙህ በኒያ ተሽቀዳደማቸው። #ማስታወሻ

~ ተክፊሪይ & ለተሚይ ዛሬ ለተሚዮች ያመጡት የ(ኢልዛም) ቢድዓ ትላንት ሐጁሪዮች ያመጡትን ራሱኑ ነው። የዛሬ ተክፊዮች የትላንት ሓጁሪዮች አባታችን የሕያ አልሓጁሪይ ሙብተዲዕ ያለውን ካላልክ ብለው ሀገር ሲበጥብጡ ነበር። የለተሞው መንጋ ደግሞ አባታችን ዓብዱልሐሚድ የለከፈውን ካለከፍክ ሱኒይ አይደለህም ይልሃል። ወደድክም ጠላህም የሕያ እና ዓብዱ በስም እንጅ በጥፋት አይራራቁም። ተከታዮችም ስማቸው እንጅ የተለያየው ተግባራቸው ኮፒ ነው። ለማንኛውም የመንሃጅ ቂብላ የጠፋበት የተክፊሩ ጎርፍ እና የለተሞው መንጋ ሁኔታ ባጭሩ ሲገለፅ እንዲህ ነው። ከሱፊያ ወይም ከኢኽዋን ወጣሁ ይልና አንድ ሁለት ወር ይቀራል። ከዚያ "አሊፍ" እና "ባ"ን የለየ ሲመስለው ተክፊሪዩ "ጀምዒዮዮዮች፣ ሙርጅኣዎች..." እያለ መጮህ ይጀምራል። ለተሚዩ ደግሞ "እነፉላን አዲሶቹ ሙመይዖች፣ ኢኽዋን ሁነዋል...ያዙን ልቀቁኝ" እያለ ይቀደዳል። ኢኽዋን ዳቦ ይሁን ቂጣኮ አያቀውም። እስኪ መጀመሪያ ቁርአን በትክክል ቅራ። ከዚያም አደብ ይዘህ ኪታብ ተማር አንብብ አጥና። ዝም ብለህ "ሲሉ ሰማሁ ብየ እላለሁ ነቢየ" ነገር አትሁን። በጎተቱህ አትጎተት ሰው ነህ በግ አይደለህም። ያለ ዕውቀት አስሩን እየጨረገድክ ነገ አላህ ፊት ማንም አብሮህ አይቆምም ለነፍስህ ስትል አላህን ፍራ። ▫️ ታላቁ ዓሊም ሙሐመድ አማን አልጃሚይ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፦ "ኡሱሉ ሰላሳን ብቻ ትማርና ክፍልህን ዘግተህ በሰዎች ላይ ብይን ትሰጣለህ። እገሌ ጣኦት፤ እገሌ ጃሂል፤ እገሌ ሙብተዲዕ፣ ሙብተዲዕን ሙብተዲዕ ያላለ እራሱ ሙብተዲዕ ነው። ከነዚህ ምንም ካልተማሩ መሃይሞች በየመስጂዶችና ቤቶች በየአቅጣጫው ፈትዋዎች ይፈበረካሉ። እባካቹህ ለሰዎች እዘኑ። አረ ለነፍሳቹህ እዘኑ።" t.me/Abu_lmran_Alaseriy t.me/Abu_lmran_Alaseriy