Secrets of Truth - 𝘽𝙮 𝙍𝙚𝙨𝙝𝙖𝙙
Kanalga Telegram’da o‘tish
● ዲናችንና በሚመለከት ወቅታዊ መረጃዎችን ➶ Current information about Muslims and Islam 🔗 ሌሎችንም አንገብጋቢ ጉዳዮችን የምንተዋወስበት Channel ነው‼️ ➞ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ አጠር ያሉ ስንኞች (በተለይም ስለ ፈለስጢን 🇵🇸) 🎯 አላማዬ:- የእውነትን ሚስጥሮች ማጋለጥ ነው‼️ #Free_Palestine 🇵🇸
Ko'proq ko'rsatish213
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
-17 kun
-430 kun
Postlar arxiv
عن النعمان بن بشير، رضي الله عنه ، أن رسول الله صلى الله عليه وسلم، قال: إن الدعاء هو العبادة ، ثم قرأ: " ادعوني أستجب لكم، إن الذين يستكبرون عن عبادتي [غافر: 60] " ، رواه "أحمد" في "المسند" (18352)، و"البخاري" في "الأدب المفرد" (714).
ይ🀄ላ🀄ሉን👇👇 share👇
tiktok.com/@secretsof_truth
Instagram.com/secretsof_truth
t.me/Secretsof_Truth
Fb.com/SecretsofTruth1
ummalife.com/ReshadMuzemil
► ለሀሳብ፣ አስታየት ወይም ጥቆማ 👇👇
t.me/ReshadMuzemil
#ከወሳኝ ነቢያዊ ዱዓዎች ውስጥ!
ከዘይድ ቢን አርቀም (رضيﷲ عنه)ተይዞ ረሱል (ﷺ) ይህን ዱዓ ያደርጉ ነበር፡‐
”اللَّهمَّ آتِ نفسي تقواها وزكِّها أنت خيرُ من زكّاها أنت
وليُّها ومولاها“
“አላህ ሆይ! ለነፍሴ ተቅዋን ለግሳት:: አጽዳትም። ከአንተ የትሻለ የሚያፀዳት የለምና፡፡ አንተ አስዋቢዋም
አምላኳም ነህ።”
📚 ሙስሊም ዘግበውታል: 2722
ይ🀄ላ🀄ሉን👇👇 share👇
tiktok.com/@secretsof_truth
Instagram.com/secretsof_truth
t.me/Secretsof_Truth
Fb.com/SecretsofTruth1
ummalife.com/ReshadMuzemil
► ለሀሳብ፣ አስታየት ወይም ጥቆማ 👇👇
t.me/ReshadMuzemil
ኢብኑ አልቀዪም፦(ረሂመሁላህ) እንዲህ ብለዋል፦
"የጁምዐ ዕለት የዒባዳ ዕለት ነው፣
👉 ከቀናት አንፃር እንደ ወርሃ ረመዳን ዒባዳ የሚወደድበት ዕለት ሲሆን
👉 በዕለቱ ልክ እንደ "ለይለቱ አልቀድር"
ዱዓ ተቀባይነት የሚያሆንበት ሰዓት አለ።"
【ዛዱል ሚዓድ 1/198】
አላህ ይወፍቀን
©️ Toleha Ahmed
ይ🀄ላ🀄ሉን👇👇 share👇
tiktok.com/@secretsof_truth
Instagram.com/secretsof_truth
t.me/Secretsof_Truth
Fb.com/SecretsofTruth1
ummalife.com/ReshadMuzemil
► ለሀሳብ፣ አስታየት ወይም ጥቆማ 👇👇
t.me/ReshadMuzemil
አላህ ከወሰነብን ውጪ ምንም የሚነካን ነገር አይኖርም:: ምንም አይነት ፈታኝ እና አስደንጋጭ ነገር በህይወታችን ቢገጥመን የአላህ ውሳኔ ካልሆነ በስተቀር ምንም አይነት ጉዳት እኛ ላይ አይደርስብንም:: አላህ ከእኛ ጋር ከሆነ የፍጡራን ተንኮል እና ጥቃት በዚህ ምድር ላይ ፈፅሞ ሊነካን አይቻለውም::
አንድ አሕ - ባሽ ራሳቸው በፈጠሩት የትላንቱ ረብሻ (የወሃብቶች እውነተኛ ማንነት ሲጋለጥ) እያለ ፅፏል። "የአባዬን ወደ እማዬ" አሉ። ይልቅ ይሄውና እውነተኛ ማንነታችሁ! "እርምጃ እንወስዳለን ሴቱም ወንዱም ተነስ!"
በዚህ እድሜ ለነውጥና ሁከት የሚቀሰቅስ ካለ ወጣቱ ምንም ቢያደርግ አይደንቅም።
=
የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor
ጉዳዩ ከዓሊይ መስጂድ በላይ ነው‼
=========================
✍ አሁን በዓለይ መስጂድ የሆነው ጉዳዩ ከበስተጀር በቅንጅበየተሰራ ነው። ቅንጅቱም የመጅሊሱን አንድነት በማይፈልጉ አካላት የተቀነባበረ ነው። ይህን ለማሳካት ኢ መደበኛ በሆነ መልኩ ከከተማ የሰላምና ፀጥታ አንዳንድ አካላት፣ ከፖሊስ አንዳንድድ አካላት በተለይ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚስነር አቶ ጌቱ እና አንዳንድ ዳኞችን ጭምር በገንዘብ በመያዝ እየተሰራ ያለ ስራ ነው። ማሳያዎቹ የመጅሊሱ አዲስ መዋቅር ከ300 በላይ መስጂዶችን ያዋቀረ ሆኖ ሳለ ከ5 በማይበልጡ መስጂዶች ላይ ያነጣጠረ ብጥብጥ እንዲነሳ ሆን ተብሎ እየተሰራ መሆኑ ነው።
በዚህ ቅንጅት የሚሰራ ለመሆኑ ማሳያው:-
1) ብጥብጡን የሚያስነሱት አካላት የፀጥታ ሰዎች እያወቋቸውና ጩበፀ ይዘው እንደነበር እየጠቀሱ በቁጥጥር ስር የማያውሏቸው መሆኑ።
2) ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ላይ በሚገኝ አንድ መስጂድ ውስጥ ብጥብጥ አስነስተው የወምጀል ድርጊት ከተፈፀመ በኃላ የክፍለ ከተማው መጅሊስ ቅሬታና ቃል አልቀበልም በማለት በተቃራኒው በጥቅም ከተሳሰሩት አካል ገንዘብ በመቀበል በወረዳ እስልምና ጉዳይ ም/ቤት አባል በሆነው አቶ ሙባረክ ላይ ክስ እንዲመሰረት እና በሐሰት እንዲመሰከርበት በማድረግ 10 አመት እንዲፈረድበት አድርገዋል።
3) ጠሮ መስጂድ ላይ በከተማ ደረጃ ያለው የመንግስተ የፀጥታ አካላት በተለይ የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ሰላምና ፀጥታ ጉዳዩን በዝርዝር እያወቀ እና ከ10 አመት በላይ ያሰገደ በሙፍቲ ጊዜ ጭምር ኢማም የነበረን ሸይኽ አባረው ብጥብጥና ረብሻ አስነስተው ሲያበቁ ችግር ፈጣሪዎችን ትተው ሰላማዊያን አስረው ከዳኞች ጋር በመመሳጠር ገንዘብ በኘስጠት አላግባብ እምዲፈረድባቸው አድርገዋል።
ከዚህም ባሻገር ስራው በተና መልኩ በተለይ ከኮሚሽነር ጌቱና ከአንዳንድ ዳኞች ጋር እየተሰራ መሆኑን የሚያሳየው:-
4) የዓልይ መስጂድን በሐይል ተቆጣጥረው ውስጥ ባልተለመደ መልኩ ያደሩ ሰዎች ማንንት እንዲጣራ በክፍለከተማ እስልምና ጉዳዮች በወረዳው እስልምና ጉዳዮች ተጠይቆ የፓሊስ መስጂድ መግባት አልችልም የሚል መልስ የሰጠ ቢሆንም በኃላ ላይ እራሱ ወደ መስጂዱ ቅጥር ጊቢ በመግባት በመስጂድ ውስስጥ ባልተለመደ መልኩ በብዛት ያደረቱን በጓሮ በር እንዲወጡ አድርጓል።
5) እነዚህ መዋቅሮች ከሙስሊሙ ተቋም ጋር ሳይሆን ከበጥባጭ ግለሰቦች ጋር የበለጠ በቅርበት የሚሰሩ መሆኑ።
6) በአዲስ አበባም ሆነ በአዲስ ከተማክፍለ ከተማና በወረዳ 12 እስልምና ጉዳዮች ለሚፃፍላቸው ደብዳቤዎች ምላሽ የማይሰጡ መሆኑ።
7) አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 እና ወረዳ 12 እና 13 ብጥብጥበተነስቶ ወይም ደግሞ የመስጂድ እቃዎችን ሲያሸሹ የክፍለ ከተማው እስልምና ጉዳይ እና የየወረዳዎቹ እስልምና ጉዳዮች አቤቱታ ለማቅረብ ወይ ህግ እንዲከበር ወደ መንግስት አካላት ሲሄዱ ከበላይ ታዘናል ክስ ለመመስረት አንችልም ብለው በተደጋጋሚ ይመልሳሉ። በሌሌላ በኩል መወቅሩ ላይ ባሉ ልጆች ላይ ከኢመደበኛ ቡድን የሚቀርበውን የሐሰት ክስ ግን ተቀብለው ያስናግዳሉ።
በቀጥታ የመጅሊሱን የበላይ አመራሮች የማጥቃትና የማሸማቀቅ ስራ በተጠና መልኩ ከበስተጀርባ ሁከት ከሚደግስ አካል ተልእኮ ይዘው እየሰሩ መሆኑን ለማሳየት:-
8) በአንድ ከስራ በተሰናበተ የጥበቃ ሰራተኛ ጉዳይ ሸይኽ ሱልጣን አማን ኤባ ታስረው ይቅረቡ፣ሸይኽ ሐሚድ ሙሳ ታስረው በይቅረቡ ኡስታዝ መሐመድ አባተ ታስረው ይቅረቡ የሚል የፍርድ ቤት ትእዛዝ የሚፅፋ መሆኑ።
9)በተመሳሳይ ጉዳይ የአዲስ አበባ መጅሊስ ስራ አስኪያጅ አቶ ሪያድ ጀማል ታስሮ ይቅረብ የሚል ደብዳቤ ከፍርድ ቤት ማፃፍ።
10)የዲስ አበባ የአስተዳደርና ፋይናንስ አስተዳደርነአቶ ገዛሊ አባፊራ ታስሮ ይቅረብ የሚል ደብዳቤ ከፍርድ ቤት ማፃፍ
ከዚህም በላይ ሴራቸው ቀላል እንዳልሆነ በመንግስት ውስጥ ከተሰገሰጉ በመንግስት ላይ የሚሰሩና የግል የገንዘብ ጥቅም ያራለላቸው አካላት ድጋፍ እያገኙ የሚሰራ ከባድ ሴራ መሆኑን የሚያሳየው:-
11) የጠቅላይ ም/ቤቱ ፕሬዝዳንት ሸይኽ ሐጂበኢብራሒም ታስረው ይቅረቡ የሚል የፍርድ ቤት ደብዳቤ ማፃፍ መቻላቸው ነው።
Via: Inbox
ቪድዮውን ተመለከትኩት‼
==================
(ሳናስመስል ስለ እውነት እናውራ!)
||
✍ እስልምና ፍትሐዊ እምነት ነው። በቅርብ ቤተሰባችንም ላይ ሆነ በነፍሳችን ላይ እውነትን እንድንመሰክር አዞናል። በዳይ የኛ ሰው ቢሆንና ተበዳይ ጠላታችንም ቢሆን ከተበዳይ ጎን እንድንቆም አዞናል። ይህን ካደረግን ከማንም በላይ ያገዝነው ተበዳዩን ጠላታችንን ሳይሆን በዳዩን ወዳጃችንን ነው። ምክንያቱም አርዓያችን ውዱ ነቢይ ﷺ «ወንድምህን በዳይም ሆኖ ተበዳህ እርዳው!» ብለዋል። «ተበዳይ ከሆነ እሺ፤ በዳይ ከሆነ ግን እንደት ልንረዳው እንችላለን?» ብለው ሶሐቦች ሲጠይቋቸው፤ «ከበደል እጁን መከልከላችሁ ከእርዳታ ነው!» ብለዋል።
ስለሆነም ዛሬ ሎሚ ሜዳ በሚገኘው በዓሊ መስጅድ በተፈጠረው አሳዛኝ ክስተት አፍረናል። እንደ ሙስሊም በዚህ ደረጃ በጥላቻ መተያየታችን ያስተዛዝበናል። ከባለፉ መሰል ታሪኮች ጠባሳ መማር አለመቻላችን ያሳዝናል።
እዚሁ ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የተጎዳውን ፎቶውን ሲዘዋወር ያየሁት አንድ ወንድም ጉዳይ ለማጣራት ሞክሬ ነበር። በመጨረሻም ሁኔታየውን ሳይቆራረጥ የሚያሳይ ቪድዮ ተመልክቻለሁ።
ነገሩ እንዲህ ነው። ሰሞኑን እዚሁ መስጅድ ላይ የኮሚቴ ለውጥ ተካሂዶ ነበር። ላለፉት አመታት መስጂዱ የሚጠበቅበትን የተሟላ አገልግሎት ሳይሰጥ አሳልፏል። የተሻለ ዲናዊ እንቅስቃሴ እንዲኖርና የአካባቢው ተወላጅ ህፃናትም ቁርኣንን በነፃነት እንዲቀሩና ማኅበረሰቡም ዲኑን እንዲማር ጠንካራ ኮሚቴ ማቋቋም አስፈላጊ ሆኖ ስለተገኘ ለውጥ ተደርጓል።
የተደረገው ለውጥ ነውጥ የሆነባቸውና ጥቅማቸውን የነካባቸው አንዳንድ የበፊት ኮሚቴ አባላት ከተላላኪዎቻቸው ጋር በመሆን አዲስ የተመረጡትን ኮሚቴዎች ጨለማን ተገን አድርገው ከመስጅድ ሲመለሱ መንገድ ላይ ጠብቀው ደበ'ደቧቸው፤ የግድ'ያ ሙከራ ፈፀሙባቸው። መኖሪያ ቤታቸው ድረስ በመሄድ ኒቃብ የለበሰች ወላጅ እናት ሳትቀር በጨካኞቹ ተደበ'ደበች።
ነገሩ ለወዲያው የተወሰነ ተረጋጋ፤ ሆኖም ግን ከዚያ ቀን ጀምሮ ውጥረቶች በየቀኑ ይታዩ ነበር።
የተወሰነ ረገበ ስንል ዛሬ አገረሸበት። ዛሬ ከፈጅር በኋላ ረመዿንም እየመጣ ስለሆነ የአካባቢው ወጣቶች የመስጂዱን ምንጣፍ ለመቀየር ሥራ ጀመሩ።
ነገር ግን ቀድሞም ውጥረት ስለነበር መስጂዱ አካባቢ ነገር ለማቀበል የተመደበች ሴት «ውሃ'ብያ» የሚሏቸው ሰዎች የመስጅዱን ምንጣፍ እየቀሩ ነው ብላ ለጸብ ወዳዶቹ ሁሉ አሰራጨች። እነርሱም በተጠንቀቅ ስለነበሩ መጀመሪያ ከዚያው አካባቢ ተሰባሰቡ። ቀጠሉና በጠሮ፣ በአንዋርና በበኒ ላለው ክንፋቸው ተደዋውለው ተሰባሰቡና መስጂዱን ከበቡት።
በዚህ ወቅት መስጂዱ ውስጥ ምንጣፍ ለመቀየር እየተሰናዱ የነበሩትና ሲያጸዱ የነበሩ ወንድሞች ስጋት ስለገባቸው የመስጂዱን ቅጥር ግቢ በር ዘጉት። ከውጭ የተሰባሰቡት ቡድኖች የመስጀዱ በር ቢዘጋባቸውም በመስጂዱ አጥር ላይ ተንጠልጥለው በመግባት መስጅዱ ውስጥ ያሉትን ለመጨ'ፍጨፍ ቋመጡ። አንዱ ከአንዋር መስጅድ የደረሰው ቡድን መሪ በመስጂዱ በር ላይ ተንጠላጥሎ በመግባት በሩን ሲከፍትላቸውና ሲገቡ ይታያል። ይህ ቪድዮ ሁኔታውን በግልፅ ያሳያል።
(ቪድዮው በዚህ ሊንክ ይገኛል። https://t.me/MuradTadesse/33975)
ውስጥ ከገቡ በኋላ የመስጂዱ የታችኛው ክፍል ላይ ነበሩ። እነዛኞቹ ፎቅ ላይ ናቸው። ከውጭ የገባው ቡድን የመስጅዱን የቁርኣን ማስቀመጫ እያነሳ ፎቅ ላይ ወዳሉት ልጆች በመወርወር ጭንቅላታቸውን ሲፈነክቷቸው በቪድዮው ላይ ይታያል።
ይህም አልበቃቸው ብሎ አንዱ ተንጠላጥሎ ወደ ፎቅ በመውጣት ጥቃት ለመፈጸም ሲሞክርና ሌሎች ሲከለክሉት ይታያል። ወደ ፎቅ ወጥቶ ለመደብ'ደብ የሚጥረውን ልጅ የሚከለክለው ልጅ ሁለት ጊዜ ጭንቅላቱ ላይ በቁርኣን ማስቀመጫው ሲፈነከት ይታያል። የዚህን ጊዜ ተበሳጭቶም ይመስላል ወደ ፎቅ ለመውጣት የሚጥረውን ልጅ የጨመደደውን ብረት ከእጁ አስለቅቆ ወደ ታች ሲጥለው ይታያል።
እዚህ ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የተጎዳ ሆኖ ፎቶው ሲሰራጭ የምናየው ወንድም በዚህ መልኩ የተጎዳ ነው። ወደ ፎቅ ወጥቶ ጥቃት ለመፈፀም ሲሞክር ወደ መሬት የተወረወረ። በርግጥ ጉዳት ደርሶበታል።
ግን እኔ ለህሊናችን ስንል አላህን ፈርተን ሐቁን እንፍረድ ያልኩት፤ ይህ ወንድም ለዚህ ለግጭት ብሎ ተሳስቶም ይሁን ሆነ ብሎ ወደ መስጂዱ ባይመጣ ኖሮ፤ ወደ መስጂዱ ከመጣ በኋላም ጥቃት ለመፈፀም በዚያ መልኩ ወደ ላይ ፎቅ ለመውጣት ባይሞክር ኖሮ፤ ለዚህ ይዳረግ ነበር ወይ?
ሁላችንም በነዚህ ልጆች ቦታ ራሳችንን አድርገን እንፍረድ። ልጁ ወደ ፎቅ እየወጣ ያለው ሊስማቸው ወይም ሰላምታ ሊለዋወጡ አይደለም። ሊደበድባቸው ሲመጣ እጁን ወደ ላይ ስበው ሊያግዙት ነው ወይንስ ከራሳቸው ለመከላከል ወደመጣበት መመለስ ነው ያለባቸው? ከኋላ ያስከተለው መንጋ የቁርኣን ማስቀመጫ ሳይቀር እየወረወረ እየፈነከታቸው ነው። በዚህ ስሜት ውስጥ ሆነው እንደት ይህንን ልጅ ሊታገሱት ይችላሉ?
ወደነርሱ ሲወጣ የሟጨጨውን እጅ ማስለቀቅ ነው ያለባቸው ወይንስ እንዲወጣ እጁን መሳብ?
ይሄ ልጅ ተሳክቶለት ፎቅ ላይ ቢወጣ እርሱ ላይ ከደረሰው ጉዳት በባሰ መልኩ ፎቅ ላይ ባሉት ልጆች ላይ ጉዳት አለማድረሱን ነው እንደ የምትመለከቱት?
ሁሉም መንስዔውን ሳያጣራ ውጤቱን አይቶ ይፈርዳል። መነሻውና ሰበቡ ምንድን ነው ብለን እንጠይቅ። ከመሃል እየተነሳን አናውራ። አጉል ፍትሐዊ፣ መካከለኛና ሚዛናዊ ለመባል አንጋጋጥ። እምነታችንንና መንሃጃችንን ካልኖርነው ስም ብቻ ነው የምንሆነው።
ይህን ወንድም ጨምሮ የተፈነከቱና የተጎዱ ወንድሞችን አላህ ዓፊያቸውን በቶሎ ይመልስላቸው። ይህኔ ከጀርባቸው ሚስኪን እናትና አባት ይኖራሉ። አላህ ከጥፋት ቀልባቸውን ይመልሰው። ማስተዋልን ያድላቸው። ማንም ፎቶ ስላየ ብቻ ምክንያቱን ሳያጣራ ፍትሕ እንዳያዛባና የአላህን ባሮች እንዳበድል ለነፍሱ ይፍራ።
መስጂዶች ዒባዳህ ማድረጊያዎች እንጂ ቡድን እየፈጠሩ ደም መፋሰሻዎች አይደሉም። በተለይም ጠሮ፣ አንዋር፣ በኒና ዓሊ መስጂዶችን የያዘውና በተደጋጋሚ ሁከት እያስተናገደ ያለው የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደርና የጸጥታ አካል ራሱን ሊፈትሽ ይገባል።
ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እልባት ሊበጅ ይገባል። በነገ በጠባ ጭቅጭቅ ሰለቸን። ለፍቅር ያለን ጊዜን ሳይበቃን ለጸብ አይትረፈን። እናስተውል። አላህን እንፍራ!
||
ወንድማችሁ፦ ሙራድ ታደሰ
=========
አትሸወድ! በፍትህ ሽፋን አጉል ለአሕ - ባሽ ውግንና አታሳይ። ብልሹ ዐቂዳቸውን እስካልተቀበልክ ድረስ እነሱ ዘንድ አንተም ሙስሊም አይደለህ። መስጂዶችህም መስጂዶች አይደሉም። ኢማሞች ሳይቀሩ የሚገ 'ደሉት፣ መስጂዶች በእሳት የሚጋዩትና የጦር አውድማ የሚሆኑት ያለ ምክንያት አይደለም። ቢችሉ ከጠላት ጋር ተሰልፈው ቢያጠፉህ ደስታቸውን አይችሉትም። ስለዚህ ባላሰብነው አቅጣጫ ለነዚህ ፀረ ኢስላም አካላት ድጋፍ እንዳንሰጥ መጠንቀቅ ያስፈልጋል።
= Ibnu Munewor
ህይወት ከቁርአን ጋር ሌላ አድስ ህይወት ነው! °`
የቁርኣን ሰዎች ማን ናቸው?
➧ኢብኑል ቀዪም እንዲህ አሉ:-
የቁርኣን ባልተቤቶች ማለት:- ቁርኣንን በልባቸው ሸምድደው ባይዙም እንኳን የቁርኣንን መልእክት የተረዱና በቁርኣን ውስጥ በተጠቀሱ ብይኖች የሚሰሩ ናቸው።
ቁርኣንን ሓፍዞ (ሸምድዶ) መልእክቱን ያልተረዳና በቁርኣን ውስጥ በተጠቀሱ ድንጋጌዎች የማይሰራ የቃላት አሰካኩን አሳምሮና ቀጥ አድርጎ ቢያነበንበውም በፍፁም የቁርኣን ሰው አይባልም።"
📚ዛዱ'ል መዓድ
ﺯﺍﺩ ﺍﻟﻤﻌﺎﺩ [٣٢٧/١]
ይህ የ ተከበረውን የ አላህ ቤት ዘሎ የገባው መሀመድ ( ጋሚኒ ) ይባላል በ ቀድሞ የ መጅሊስ አመራር ላይ የወጣቶች አደራጅ ነበር አሁን ላይ ከ አንዋር እና በኒ ልጆች ጋ በማበር ሰፈራችንና መስጂዳችን የሁከት ቀጠና እያደረገ ያለ ግለሰብ ነው
የ ህግ አካላት ባለፈውም ብጥብጥ ላይ ጥቆማ ተሰጥታቸው የነበረ ቢሆንም ተገቢውን እርምጃ ባለመውሰዳቸው ዛሬ ይህንን ዘግናኝ ጭፍጨፋ ሊመራ ችሏል !!!
የዐሊ መስጂድ ጉዳይ
~
አንድ ቪዲዮ እየተዘዋወረ ነው። ከላይ ምንጣፍ የሚያነጥፉ ልጆች አሉ። ከታች እነሱን የሚቃወሙ አሕ'ባሾች አሉ። (አሕ'ባሽ ስላልኩ የሚደብራችሁ ትኖራላችሁ አውቃለሁ። እነሱ ወሃB ብለው አክፍ 'ረው ደም እያፈሰሱ አጉል የሆነ ጥንቃቄ ማሳየት አልሻም።)
ከታች ያሉት አሕ'ባሾቹ ፎቅ ላይ ያሉትን ከስር ሆነው የቁርኣን ማስቀመጫ እየወረወሩ ይመታሉ። ሌሎቹ ደግሞ ላይ ያሉትን ለመደባደብ ከስር ሲንጠላጠሉ ይታያሉ። ከተንጠላጠሉት ውስጥ አንዱን ከላይ መትተው ሲጥሉት ይታያል። በዚህ ቪዲዮ መሰረት ማነው ጥፋተኛው? ማነውስ ጠብ ጫሪው? ለምን የምትፈልጉትን ብቻ ለይታችሁ ማጉላት ላይ አነጣጠራችሁ? ከላይ ያሉት የሚደበደቡት ልጆች ቦታ ላይ ብትሆኑ ምንድነው የምታደርጉት? ዝም ብለው ይሙቱ? ደግሞም በአሕ'ባሽ ተደብድቦ እዚያው በደም የተነከረ ልጅ አለ። እሱን ግን ባላየ ነው የሚያልፉት። ግጭቶችን መቆጣጠር ያስፈልጋል፣ አዎ። ደም መፍሰስ የለበትም፣ አዎ። ወሃB ወሃB እያሉ ቡድናዊ ነጥብ ለማስቆጠር ሲጠቀሙት ግን ጥግ ይዘን ልንመለከት አይገባም። ይሄ በወንበር ያኮረፉ አሕ - ባሾች የሚያቀናብሩት ሴራ ነው።
= Ibnu Munewor
የእውነት ለዲን ከሆነ የምንሠራው፣ የእውነት የአላህን ፊት ፈልገን ከሆነ የምንሠራው፤ «ላ ኢላሃ ኢለ-ል'ሏህ» የሚል ወንድምህን የአላህን ቤት ላሳምር ባለ ባላንጣ ይመስል ደሙን አታፈስም።
የነዚህ ቡድኖች ላኪያቸው ማን እንደሆነ ይታወቃል። ከታች ያለው ፎቶም መስካሪ ነው።
ላኪያቸው ደግሞ ከነማን ጋር ግንኙነት እንዳለው ግልፅ ነው።
አሁንም በየሰፈሩ ያገኛችሁትን «ውሃብያ» ሁሉ ግደሉ የሚል መልዕክት እየተሰራጨ ነውና ሁሉም ሰፈሩንና መስጂዶቹን ከዚህ ተስፋ ከቆረጠ ቡድን ይጠብቅ።
የሚመለከተው አካልም ከዚህ የከፋ ነገር ሳይከሰትና ባለው የሃገራችን ተጨባጭ ላይ ሌላ የግጭት ግንባር እንዳይከፍቱ ከወዲሁ ሊታሰብበት ይገባል።
አላህ ቀልብ ይስጣቸው።
|| Murad Tadesse
ፍትሃዊው ጌታ!
ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
﴿اللَّهَ لَا يَظْلِمُ مُؤْمِنًا حَسَنَةً، يُعْطَى بِهَا فِي الدُّنْيَا، وَيُجْزَى بِهَا فِي الْآخِرَةِ، وَأَمَّا الْكَافِرُ فَيُطْعَمُ بِحَسَنَاتِ مَا عَمِلَ بِهَا لِلَّهِ فِي الدُّنْيَا، حَتَّى إِذَا أَفْضَى إِلَى الْآخِرَةِ لَمْ تَكُنْ لَهُ حَسَنَةٌ يُجْزَى بِهَا﴾
“አላህ አማኝን በመልካም ስራው አይበድልም። በዱንያም በሷ ይሰጠዋል። በአኺራም በሷው ይሸልመዋል። ከሃዲ ግን አላህን አስቦ በሰራቸው መልካም ስራዎች ዱንያ ላይ ያበላዋል። ወደ አኺራ ሲሄድ ግን የሚመነዳበት መልካም ስራ የለውም።”
📚 ሙስሊም ዘግበውታል: 2808
السلام وعليكم ورحمة الله وبركاته
هل تعلمون ما معنى
*جزاك الله خيراً* ؟
معاني جميله لكلمه *جزاك الله خيراً*
أغلب الناس حين تقدم لهم معروف يقولون : *جزاك الله خيراً*
كلمة *خير* تدل على
ما هو طيب عند الله تعالى...
*جزاك الله خيراً*
بأن يمن عليك بالجنة ورؤية وجهه الكريم.
*جزاك الله خيراً*
بأن يزحزحك عن النار مثوى الكافرين.
*جزاك الله خيراً*
بأن يهديك إلى الصراط
المستقيم...
*جزاك الله خيراً*
بأن لا يسلط عليك كل شيطان
رجيم..
جزاك الله خيراً*
بأن يبارك في رزقك
رب العالمين...
*جزاك الله خيراً*
بأن يجعلك باراً بوالديك إلى يوم الدين.
*جزاك الله خيراً*
بأن تتبع سنة سيد المرسلين.
*جزاك الله خيراً*
جزاك الله خيراً ....
والخير كثير عند الله ....
ولا أستطيع أن أحصي
كل ما هو خير...
ولا تظن أنك حين تقول
*جزاك الله ( ألف ) خير*
إن هذا أفضل
فأنت حصرت الخير
في كلمة ألف
والخير عند الله أكثر بكثييير
جزاكم الله خيرا ..
في قول المؤمن لأخيه :
*جزاك الله خيراً*
( 1 ) عن أبي هريرة قال : قال رسول الله صلى الله عليه وسلم : إذا قال الرجل لأخيه : جزاك الله خيرا ، فقد أبلغ في الثناء .
( 2 ) حدثنا وكيع عن أسامة بن زيد عن طلحة بن عبيد الله بن كريز قال : قال عمر : لو يعلم أحدكم ما له في قوله لأخيه : جزاك الله خيرا ، لأكثر منها بعضكم لبعض.
من اروع ما وصلنى اليوم فاحببت اهداؤه لكم
فجزاكم الله خيراً
📌 ረመዷን ሊገባ ቀናቶች ቀርተውታል፤ ያለፈው ረመዷን ቀዷእ ያለብዎ ከሆነ ከወዲሁ ፆመው ያካክሱ።
🛑🛑🛑🛑🛑🛑🛑🛑🛑🛑🛑🛑
አላህ ስራቸውን ይውደድላቸውና አቢ ሰለማ እንዳሉት እናታችን ዓኢሻ ረዲየ አላሁ ዓንሀ “ከረመዳን ወር ፆም ቀሪ ይኖርብኝና በሻዕባን ወር ካልሆነ በስተቀር ፆሜ ማካካስ አልችልም ነበር።" ትላለች ብለዋል። (ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።)
አል-ሃፊዝ ኢብኑ ሀጀር አላህ ይዘንላቸውና በዚህ ሀዲስ ላይ ተመርኩዘው በፈትሁል-ባሪ (4/191) ላይ እንዳሰፈሩት
«እናታችን ዓኢሻ (ረዲየ አላሁ ዓንሀ) በሻዕባን ወር የረመዳንን ፆም "ቀዷእ" ለማውጣት ጥረት በማድረጓ ከዚህ የምንገነዘበው ነገር የረመዳንን ወር ፆም "ቀዷእ" ሌላኛው ረመዳን እስኪገባ ድረስ ማዘግየት የማይቻል መሆኑን ነው።» ብለዋል።
ስለዚህ እህትና ወንድሞች ከፊትለፊታችን ያሉት ጥቂት ቀናት ናቸውና ያልተፆመ እዳ ካለብዎት ፈጠን ብለው ይክፈሉና ለቀጣዩ ይዘጋጁ። አላህ ይወፍቀን።
©️ Ahmedin Jebel
