Grade 7-8 Info & Materials
Kanalga Telegram’da o‘tish
🎒 🏫 ለ7ኛ እና ለ8ኛ ክፍል ተማሪዎች: 📖 መፅሀፎች | 📝 መልመጃዎች | 📑 Worksheets 🤖 በNotebookLM የታገዙ: 💻 Short notes, 🎙Audio, 🎥 Video & 🗂 Flash Cards 🌟 ለ8ኛ ክፍል:- 🎯 Models | ⏳ Ministry Exams | 🧠 የአጠናን ስልቶች ◉ የቂያማ እለት ከምንጠየቀው ጥያቄ አንዱ ❝በአወቅከው ነገር ምን ሰራህበት❞ ነው❗️
Ko'proq ko'rsatish2 243
Obunachilar
+624 soatlar
+247 kun
+7730 kun
Postlar arxiv
የ31 ዓመቷ ኢንጂነር በChatGPT የተሰጣትን ምክር ተከትላ የሚጥል በሽታ መድኃኒቷን ከቀነሰች በኋላ ሕይወቷ አለፈ።
በአሜሪካ ሲያትል ከተማ የአማዞን ኩባንያ የሶፍትዌር ኢንጂነር ሆና የምትሠራው የ31 ዓመቷ ቦዌን ዋን፣ የሚጥል በሽታ ለመቆጣጠር የምትወስደውን መድኃኒት በChatGPT የተሰጣትን ምክር ተከትላ ከቀነሰች በኋላ መሞቷ የተነገረ ሲሆን ወላጆቿ የChatGPT ፈጣሪን OpenAIን ከሰዋል።
ከ14 ዓመቷ ጀምሮ በሚጥል በሽታ የምትሠቃየው ዋን ለሦስት ዓመታት ከChatGPT ጋር የቀረበ ግንኙነት ከፈጠረች በኋላ የጤና ምክር ለማግኘት ቴክኖሎጂው ላይ መተማመን መጀመሯን በክሱ ላይ ተጠቅሷል።
በተለይም በ2025 መጨረሻ በአማዞን የሥራ ቦታዋን በ90 ቀናት ውስጥ እንደምታጣ ከተነገራት በኋላ፣ መድኃኒቷ የማሰብ ችሎታዋንና በሥራ ላይ እንግሊዝኛ የመናገር ችሎታዋን እየጎዳ እንደሆነ በማመን ወደ AI መሣሪያው ምክር መጠየቋ ተገልጿል።
በወላጆቿ የቀረበው ክስ እንደሚያመለክተው፣ ChatGPT ሐኪም ያዘዘላትን ላሞትሪጂን የተባለ የሚጥል በሽታ መድኃኒት ቀስ በቀስ እንድታቆም የሚያስችል የቅነሳ ዕቅድ ሰጥቷታል።
በየቀኑ 400 ሚሊግራም የምትወስደውን መድኃኒት ወደ ዜሮ እንድታወርድ መመሪያ እንደሰጣትም ክሱ ይገልጻል።
ዋን፣ በ25 ቀናት ውስጥ መድኃኒቷን መቀነስ መቀጠሏን በዚህም ሂደት የሚጥል በሽታዋ ተባብሶ በብዛት እየጣላት መሆኑ፣ ግራ መጋባትና የእንቅልፍ ችግር እንዳጋጠማት የወላጆቿ ክስ ያመለክታል።
ወጣቷ መድኃኒቷን መቀነስ ከጀመረች ከአንድ ወር በታች ባለው ጊዜ ሕይወቷ አልፏል።
የሕክምና ምርመራው ለሞቷ ምክንያት በሚጥል በሽታ ምክንያት የሚከሰት ድንገተኛ ያልተጠበቀ ሞት (SUDEP) መሆኑን አረጋግጧል።
የዋን ወላጆች OpenAI እና የኩባንያውን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሳም አልትማንን በቸልተኝነትና በልጃቸው ሞት ኃላፊነት አለበት በሚል ከሰዋል።
ኩባንያው በበኩሉ በተፈጠረው ክስተት እንዳዘነ ገልጾ፣ ከሐኪሞችና ከሌሎች ባለሙያዎች ጋር በመሥራት ChatGPT ለጤና አደጋ በሚያጋልጡ ሁኔታዎች ላይ የሚሰጠውን ምላሽ ጥንቃቄ የተሞላበት እንዲሆን እያጠናከረ መሆኑን አስታውቋል።
OpenAI በተጨማሪም ChatGPT የባለሙያን የሕክምና ክትትል፣ ትዕዛዝና እንክብካቤን ሊተካ እንደማይችል ገልጾ፣ ዋን በተለይ ትጠቀምበት የነበረው GPT-4o ሞዴል ከአገልግሎት መወገዱን አስታውቋል።
ሟቿን ወጣት በተመለከተ የሚደረገው ሙሉ ምርመራ በሚቀጥለው ዓመት ይካሄዳል መባሉን ከኒውዮርክ ታይምስ አንብበናል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ጥቅምት 22 ቀን 2019
+3
Grade 8 - CTE
Project-Based Learning (PBL)
Topic: Undertaking Enterprise Activity
Project Title: Paln Your Own Small Business!
With Teacher's Assessment Guide
የሰሌዳው ማስታወሻ: ከታች ለቅቄላችኋለሁ። ከደቂቃዎች በኋላአጠፋዋለሁ። 👇👇👇👇
Ethiopian Traditional Music
Date: Thursday, October 29, 2025
2. Central Ethiopian
This region is known for its lively and energetic music, with fast rhythms and intricate melodies. The masenqo, a single-stringed bowed instrument, is a popular instrument in this region.
3. Southern Ethiopian
The music in this region is heavily influenced by traditional tribal music and incorporates a variety of instruments, such as flutes, drums, and lyres. The melodies are often complex and feature call-and-response vocals.
4. Eastern Ethiopian
This region is known for its unique vocal style, which involves high-pitched singing and yodeling. The music also features a variety of percussion instruments, including the kebero drum.
5. Western Ethiopian
Music incorporates the use of the washint (a bamboo flute) and the kebero drum. The melodies are often upbeat and lively, with fast rhythms and complex arrangements. The vocals are typically high-pitched and often feature call-and-response patterns.
Overall
Ethiopian music is characterized by its diversity and rich cultural heritage, with each region contributing its own unique styles and traditions.
GRADE 8 Review Questions
📚 500 multiple choice questions in each
══════════════
✅ አላህ ይርዳችሁ!! በርቱ
✅ አላህ በፈቀደልኝ ልክ ሁሉ አግዛችኋለሁ። ኢንሻአላህ!! ብቻ እናንተ በርቱ!!
🚀 አሁኑኑ ተለማመዱት! (የዛሬ ፈተናችሁ)
ይህን ልጥፍ አንብባችሁ ብቻ እንዳታልፉት፤ ዛሬውኑ ወደ ተግባር ቀይሩት!
➊ NotebookLM ክፈቱ (https://notebooklm.google.com/)።
➋ የምትፈልጉትን አንድ የትምህርት ማስታወሻ ወይም PDF መጽሐፍ ጫኑ።
➌ Chat በመጠቀም ወይም Studio በመግባት የምትፈልጉትን የጥናት ውጤት (ሰንጠረዥ፣ ማጠቃለያ ወይም ጥያቄ) አመንጩ (generate አድርጉ)።
➍ የሰጣችሁን ውጤት ከዋናው ምንጭ ጋር አነጻጽሩ!
➎ 💬 ሞክራችሁ ከጨረሳችሁ በኋላ በኮመንት አካፍሉን፦ ምን ዓይነት ሰነድ ተጠቀማችሁ? የ Chat እና የ Studio አጠቃቀሙስ እንዴት አገኘችሁት?
➏ 📌 ይህን ልጥፍ ለአንድ መምህር፣ ተማሪ ወይም የትምህርት ይዘት አዘጋጅ አጋሩት።
♦️📚 ዕውቀትን ማካፈል ብቻ ሳይሆን፣ በተግባር መጠቀምም እንጀምር!
♦️📚 የAI ኃይል የሚገለጠው ስለ እሱ በማውራት ሳይሆን፣ በትክክለኛ ዓላማ ስንጠቀምበት ነው! 🚀
#NotebookLM #Gemini #ArtificialIntelligence #AIinEducation #DigitalLearning #ICT #EducationTechnology #FutureOfLearning
🚀 Gemini Notebook (NotebookLM)፡ የዕውቀት ብርሃን በእጃችሁ!
ከመረጃ ማከማቸት ወደ እውነተኛ ዕውቀት መፍጠር!
════════════════
“አእምሮ ሊሞላ የሚገባው ዕቃ ሳይሆን፣ ሊቀጣጠል የሚገባው እሳት ነው!” (ፕሉታርክ)
የተከበራችሁ የነገ ተስፋዎች፣ የዕውቀት ፈላጊዎችና የለውጥ አምጪዎች!
ዓለማችን በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) እና በዲጂታል ቴክኖሎጂ ፍጥነት እየተለወጠች ነው። በዚህ የመረጃ ዘመን ትልቁ ጥያቄ ምን ያህል መረጃ እንደምናከማች ሳይሆን፤ የምናገኘውን መረጃ ምን ያህል ተረድተን፣ ተንትነንና በተግባር እንደምንጠቀምበት ነው።
ብዙ ገጾችን በቃል መያዝ፣ ሰሌዳ ላይ ያለውን ጽሑፍ ብቻ መገልበጥና ማስታወሻ በደብተር መሙላት ብቻውን በቂ አይደለም። ዋናው ዓላማ የተማርነውን መረዳት፣ መጠየቅ፣ ማሰብ፣ ችግር መፍታት እና አዲስ ሐሳብ ማመንጨት ነው።
ለዚህም ከሚረዷችሁ እጅግ ዘመናዊ የAI መሣሪያዎች አንዱ Google NotebookLM ነው። ይህ መሣሪያ የጥናት ምንጮቻችሁን በማደራጀት፣ በመተንተንና በተለያዩ የመማሪያ መንገዶች በማቅረብ ጊዜያችሁን በብቃት እንድትጠቀሙ ያደርጋል። ከሌሎች AI መሣሪያዎች የሚለየው ደግሞ ከእናንተ ውጭ ከሌሉ የጥናት ሰነዶችና መጻሕፍት ተነስተው ብቻ መልስ እንዲሰጥ መደረጉ ነው።
🚀 1. NotebookLM ምን ሊሠራላችሁ ይችላል?
🎧 Audio Overview — ትምህርትን በድምፅ መማር: ረጅም የጥናት ሰነዶችን ወደ ማራኪ የድምፅ ውይይት ቀይሩ። በጉዞ ላይ እያላችሁ ወይም ዕረፍት ላይ ሆናችሁ ጭብጦችን ማዳመጥ ቀላል ይሆንላችኋል።
🎬 Video Overview — ትምህርትን በቪዲዮ መልክ: ከምንጮቻችሁ ተነስቶ የቪዲዮ ማብራሪያ ማዘጋጀት ይቻላል፤ ለግል ጥናትና ለቡድን ውይይት ፍጹም ተስማሚ ነው።
📊 Data Tables — የመረጃ ሰንጠረዦች ከተለያዩ ምንጮች: ከተለያዩ የጥናት ሰነዶችና መጻሕፍት የተበታተኑ መረጃዎችን በጥቂት ሰኮንዶች ውስጥ ወደ ንጹህና የተደራጁ ሰንጠረዦች (Spreadsheets) ቀይሩ። መረጃዎችን እርስ በእርስ ለማወዳደር፣ ለመተንተን እና በቀጥታ ወደ Google Sheets በመውሰድ ለፈተና ዝግጅት ወይም ለምርምር ሥራ መጠቀሚያ አድርጉ!
🃏 Flashcards — ፈጣን የዕውቀት መለማመጃ: ቁልፍ ቃላትን፣ ትርጓሜዎችንና ጠቃሚ ነጥቦችን በጥያቄና መልስ ካርዶች መልክ አዘጋጅታችሁ ለፈተና ዝግጅት ተጠቀሙባቸው።
🧠 Mind Maps — የሐሳብ ካርታዎች: የአንድን ትምህርት ዋና ሐሳብ፣ ንዑስ ርዕሶችና ግንኙነቶች በሥዕላዊ መልክ አደራጁ።
📊 Slide Deck — የአቀራረብ ስላይዶች: ለክፍል ገለጻ እና ለቡድን ስራዎች የሚሆኑ ስላይዶችን ፈጥናችሁ አዘጋጁ።
📝 Quizzes — የራስን ዕውቀት መፈተሽ: ከምንጮቻችሁ በመነሳት ጥያቄዎችን በማዘጋጀት የተረዳችሁትንና እንደገና ማጥናት የሚያስፈልጋችሁን ክፍል ለዩ።
📚 Study Guides & Reports — የጥናት መመሪያዎች: ማጠቃለያዎችንና የምንጭ ንጽጽሮችን በማዘጋጀት የጥናት ሥራችሁን ቀልብሱት።
🪜 2. NotebookLM-ን እንዴት ትጠቀማላችሁ? (የደረጃ በደረጃ መመሪያ)
ደረጃ 1፦ ድረ-ገጹን ክፈቱ 👉 https://notebooklm.google.com/ (በGoogle መለያችሁ ግቡ)
ደረጃ 2፦ New Notebook ፍጠሩ
ለምሳሌ፦Grade 7 ICT, Biology Chapter 1, ወይም Exam Preparation ብላችሁ ስም ስጡ።
ደረጃ 3፦ የጥናት ምንጮቻችሁን ጨምሩ የPDFመጽሐፍትን፣ የGoogle Docsማስታወሻዎችን፣ የድረ-ገጽ ሊንኮችን ወይም ተስማሚ የYouTube ቪዲዮዎችን ማስፈንጠሪያ (Link) ጫኑ።
💡 ልብ ይበሉ (የአጠቃቀም ምስጢር)፦ የጥናት ምንጮቻችሁን ከጫናችሁ በኋላ መተግበሪያውን በሁለት ዋና ዋና መንገዶች መምራት ትችላላችሁ፦
💬 Chat: የሚፈልጓቸውን ጥያቄዎች በጽሑፍ እየጻፉ በቀጥታ መልስ ለማግኘት።
🛠️ Studio: ከላይ የዘረዘርናቸውን ድንቅ ይዘቶች (የድምፅና የቪዲዮ ማብራሪያዎችን፣ የጥናት ካርዶችን፣ የሐሳብ ካርታዎችን፣ የመረጃ ሰንጠረዦችን እና የጥናት መመሪያዎችን) በአንድ ጠቅታ ለማመንጨትና ለማስተዳደር Studio ውስጥ መግባት ልብ ይበሉ!
ደረጃ 4፦ ብልህ ጥያቄዎችን ጠይቁ ወይም Data Table ፍጠሩ
“ይህን ርዕስ ለተማሪ በቀላል አማርኛ አብራራልኝ።”
“ከእነዚህ የትምህርት ምንጮች በመነሳት ቁልፍ ርዕሶችን፣ ፍቺዎችንና ልዩነቶቻቸውን የሚያሳይ ሰንጠረዥ (Data Table) አዘጋጅልኝ።”
“ከዚህ ምንጭ (ለምሳሌ 2.3) 10 የብዙ ምርጫ ጥያቄዎችን አዘጋጅልኝ።” ከፈለጋችሁ “ከመልሶቻቸው ጋር ስጠኝ” ማለትም ትችላላችሁ።
ደረጃ 5፦ ውጤቱን አረጋግጡና ተግብሩ የAI መልሶችን ከዋናው ምንጭ ጋር አነጻጽሩ፤ በራሳችሁ ቃላት ግለጹት።
👩🏫 3. ለመምህራን፦ የዝግጅት ሥራችሁን አቀልሉ!
NotebookLM ከተወሰነ የትምህርት ምንጭ ተነስታችሁ የሚከተሉትን በአጭር ጊዜ ውስጥ እንድትሰሩ ይረዳችኋል፦
የትምህርት ማጠቃለያዎችና የክፍል ማስታወሻዎች።
የትምህርት ይዘቶችንና ጽንሰ-ሐሳቦችን የሚያወዳድሩ ሰንጠረዦች (Data Tables)
የጥንድና የቡድን ሥራ እንቅስቃሴዎች።
ከቀላል እስከ ውስብስብ የሚሄዱ የግምገማ ጥያቄዎችና የፈተና መለማመጃዎች።
⚠️ ማሳሰቢያ፦ የAI ውጤትን ያለ ማረጋገጥ በቀጥታ ወደ ክፍል ማስገባት አይመከርም። የትምህርቱን ዓላማ፣ የተማሪዎችን ደረጃ እና የምንጩን ትክክለኛነት ሁልጊዜ መምህሩ መፈተሽ አለበት።
🎓 4. ለተማሪዎች፦ ብልህ ተጠቃሚ ሁኑ!
የተሻለ ተማሪ ለመሆን ቴክኖሎጂን ማግኘት ብቻ በቂ አይደለም፤ በትክክል መጠቀምም ያስፈልጋል እንጂ፡
በመጀመሪያ ራሳችሁ ለመረዳት ጥረት አድርጉ።
ያልገባችሁን ነገር ለAI በጥልቀት ጠይቁ።
የምትወስዷቸውን መልሶች ከመጽሐፋችሁ ጋር አረጋግጡ።
የAI መልስን በቀጥታ ከመገልበጥ ይልቅ በራሳችሁ ቃላት አብራሩ።
🎯 ዓላማችሁ AI-ን ተጠቅማችሁ መልስ ማግኘት ብቻ ሳይሆን፣ ያለ AI እንኳን ማሰብ፣ መተንተንና ችግር መፍታት የሚችል አእምሮ መገንባት ነው!
🔍 5. የNotebookLM ታማኝነትና ገደቦች
የAI መሣሪያዎች ድንቅ ረዳቶች ቢሆኑም ፍጹም አይደሉም። አንዳንዴ የተሳሳተ ማብራሪያ ሊሰጡ ይችላሉ። ስለዚህ፦
የምንጭ ማጣቀሻዎችን (Citations) ሁልጊዜ ተከታተሉ።
ዋና ዋና መረጃዎችን ከመጽሐፉ ጋር አረጋግጡ።
የግል መረጃዎችንና ሚስጥራዊ ሰነዶችን ሲያስገቡ ጥንቃቄ አድርጉ።
ቴክኖሎጂ ዕድል ይፈጥራል፤ ጥበብ ግን በትክክል ከመጠቀም ይመጣል!
🔥 6. የለውጥ ጥሪ፦ ዛሬውኑ ጀምሩ!
📍 ለተማሪዎች፦ የጥናት ምንጮቻችሁን አደራጁ፤ NotebookLM-ን ተጠቅማችሁ Data Tables ፍጠሩ፤ የተማራችሁትን በራሳችሁ ቃላት ግለጹ።
📍 ለመምህራን፦ የAI መሣሪያዎችን በመጠቀም የዝግጅት ጊዜያችሁን አቀልሉ፤ ተማሪዎችን በማሰብና በመፍጠር ላይ አበረታቱ።
የወደፊቱ ዓለም መረጃ ያላቸውን ብቻ ሳይሆን፣ መረጃን መረዳት፣ መገምገም እና በጥበብ መጠቀም የሚችሉትን ይፈልጋል።
ዛሬ ተማሩ። ነገ ፍጠሩ። ወደፊት ዓለምን በእውቀት ቀይሩ!
═════════════════
✍️ ረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል
ክፍል 7፦ የወላጆችና የመምህራን ፍቅር — ጫና ወይስ ጥበቃ?
ብዙ ጊዜ ወላጆቻችሁ "አጥኑ፣ ቁርዓን ቅሩ፣ ከጫወታ ተቆጠቡ፣ እንቅልፍ ቀነሱ" ሲሏችሁ እንደሚያጨናንቋችሁ ሊሰማችሁ ይችላል። ነገር ግን እውነታው የወላጅና የመምህር ቁጣ፣ ገሰጻና መመሪያ እናንተን ከህይወት ውጣ ውረድና ቁስል ለመጠበቅ የሚደረግ ጋሻ ነው።
ሰው የተሳሳተውን እናንተ እንዳትሳሳቱ፣ በህይወት ውጣውረድ እንትታመሙ ሲነግራችሁ በትዕግስትና በበሰለ አእምሮ ማየት አለባችሁ።
📖 “ለእነሱም ከእዝነት የተነሳ የዝቅተኝነትን ክንፍ ዝቅ አድርግላቸው፤ «ጌታዬ ሆይ! በህፃንነቴ እንዳሳደጉኝ እዘንላቸው» በል።” (ሱረቱል ኢስራእ 17:24)
ክፍል 8፦ የጓደኛ መረጣና የመንጋ አስተሳሰብን መታገል
በትምህርት ጉዟችሁ ውስጥ ስኬታችሁን ከሚወስኑት ዋና ዋና ነገሮች አንዱ አብራችኋቸው የምታሳልፉአቸው ጓደኞቻችሁ ናቸው። ትምህርትን እንደ ቀልድ የሚያዩ፣ መምህራንን የማይከብሩና ጊዜአቸውን የሚያባክኑ ጓደኞች ጋር መዋል ወደ እነሱ መስመር ይስባችኋል።
የራሳችሁ ሕልም ይኑራችሁ፤ የመንጋ አስተሳሰብ ተከትላችሁ አትበላሹ። ጠንካራ፣ ለትምህርቱ ቦታ የሚሰጥና ወደ አላህ የሚቀርብ ጓደኛን መምረጥ የነገው ስኬታችሁ መነሻ ነው።
ክፍል 9፦ ስህተትን አለመፍራት እና ከተሞክሮ መማር
በህይወትና በትምህርት ጉዞ ውስጥ መሳሳት ወይም በፈተና ዝቅተኛ ውጤት ማምጣት የውድቀት ማብቂያ አይደለም። ትልቁ ውድቀት ከስህተት አለመማርና እጅ መስጠት ነው።
ጎበዝ ከሆናችሁ፦ በአላህ ዘንድ ትሁት ሁኑ፤ አትኩሩ፤ ሌሎችንም አግዙ።
ትምህርት ከከበዳችሁ፦ በፍጹም ተስፋ አትቁረጡ! ማንም ሰው ተወልዶ አዋቂ አልሆነም። በየቀኑ የምታደርጓት ትንሽ ጥረት ነገ ትልቅ ቦታ ታስይዛችኋለች (ስኬትን ታጎናፅፋችኋለች)።
🎤 ኢማም ማሊክ (ረሂመሁላህ) እንዲህ ይላሉ፦
"ዕውቀትን መፈለግ ውበትና ግርማ ሞገስ ነው፤ ነገር ግን የሚጠቅመው በተግባር ሲተረጎምና በትህትና ሲያዝ ብቻ ነው።"
ክፍል 10፦ ወደ ተግባር የሚቀይር የስኬት መንገድ
ይህ መልዕክት በንባብ ብቻ እንዲቀር አይፈለግም። ከዛሬ ጀምሮ በዕለታዊ ህይወታችሁ ልትተገብሯቸው የሚገቡ ዋና ዋና እርምጃዎች የሚከተሉት ናቸው፦
የመጀመሪያው እርምጃ፦ የተመጣጠነ የጊዜ ሰሌዳ ማዘጋጀት
በየቀኑ ለጥናት፣ ለሶላት፣ ለእረፍትና ለቤተሰብ የሚሆን የተመጣጠነ የጊዜ ሰሌዳ (Timetable) አዘጋጁ። ጊዜውን በአግባቡ የሚመራ ተማሪ በየትኛውም ፈተና አይሸነፍም።
ሁለተኛው እርምጃ፦ ንቁ አጠናን (Active Recall) መጠቀም
ደብተራችሁን ወይም መጽሐፋችሁን ዝም ብላችሁ በዓይን ከመቃኘት ይልቅ፣ ያነበባችሁትን ሳታዩ በራሳችሁ ቋንቋ ለማብራራት፣ ማስታወሻዎችን በአጭሩ ለመፃፍና ጥያቄዎችን ለመስራት ሞክሩ።
ሦስተኛው እርምጃ፦ ቴክኖሎጂን ለትክክለኛ ዓላማ ማዋል
ሰው ሰራሽ አስተዋይነትን (AI) መጽሐፍትን ወደ አጫጭር ማስታወሻዎች (Teacher-written version notes)፣ የአእምሮ ካርታዎች (Mind-maps) እና ክለሳ ጥያቄዎች (Quizzes) በመቀየር ለጥናት ረዳት አድርጉት።
አራተኛው እርምጃ፦ ሁሉንም ትምህርቶች እኩል ዋጋ መስጠት
እንደ CTE፣ ICT ያሉ ተግባር ተኮር ትምህርቶች ለነገው እውነተኛ ዓለም የሚያዘጋጁአችሁ ድንቅ የክህሎት ማዕከላት መሆናቸውን ተረድታችሁ በትኩረት ተከታተሉ።
አምስተኛው እርምጃ፦ ታዛዥነትና ትህትናን ማጎልበት
ለመምህራኖቻችሁና ለወላጆቻችሁ ፍጹም ታዛዥ ሁኑ፤ የእነሱን በረካና አዎንታዊ ዱዓ ማግኘት የትምህርታችሁ ብርሃንና የስኬታችሁ ቁልፍ ነው።
ክፍል 11፦ ማጠቃለያና የነገው ጥሪ
ውድ ተማሪዎች! እናንተ የነገው ሀገር ተስፋ፣ የወላጆቻችሁ ኩራት፣ የህብረተሰባችሁ አለኝታ ናችሁ። ዛሬ ተነሱ፤ አእምሯችሁን በእውቀት፣ ልባችሁን በተስፋ፣ ተግባራችሁን በትጋት አስጊጡ።
የተኙበት ሕልም ሳይሆን የነቁበት ተግባር ነገአችሁን ይወስናል!
✨ አላህ እውቀታችሁን፣ ጊዜያችሁንና ስራችሁን ይባርክላችሁ! ✨
✍️ ረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል
📢 የነገው መሪነት ቀመር፦ ሕልምን ከእውነት፣ ጥረትን ከተስፋ ጋር ማያያዝ!
መግቢያ፦
ውድና የተወደዳችሁ ተማሪዎች! ይህ መልዕክት የተዘጋጀው በውስጣችሁ ትልቅ አቅም፣ ሊቀየር የማይችል የታመቀ ችሎታና የነገ ብሩህ ተስፋ እንዳለ ሙሉ በሙሉ በመተመኑ (እምነት በመጣል) ነው። ይህ ወቀሳ ወይም ጥፋተኛ የማድረግ ጥሪ አይደለም፤ ይልቁንም አመለካከታችሁን፣ አስተሳሰባችሁን፣ የአኗኗር ዘይቤያችሁንና ለትምህርታችሁ ያላችሁን ቦታ እንድታድሱና እንድታስተካክሉ የተዘረጋ የእውነትና የተስፋ እጅ ነው።
ክፍል 1፦ ሕልም እና እውነታ:- "መመኘት" ወይስ "መኖር"?
ብዙ ሰዎች ሕልም ያልማሉ፤ ነገር ግን ጥቂቶች ብቻ ናቸው ለሕልማቸው የሚኖሩት። ሕልም ማለት በተኙበት አልጋ ላይ የሚታይ ምናባዊ ምስል ሳይሆን፣ እንቅልፍ የሚነሳ፣ ወደ ተግባር የሚያንቀሳቅስና በየቀኑ መስዋዕትነትን የሚጠይቅ የህይወት ግብ ነው።
ዛሬ የምታሳልፏት እያንዳንዷ ደቂቃ፣ የምታነቧት አንዲት ገጽና የምትሰሩት አንድ የሂሳብ ጥያቄ ነገ ለምትሆኑት ትልቅ ሰው መገንቢያ መሰረት ናቸው። ሕልማችሁ የዝሆን ያህል ትልቅ ሆኖ፣ ጥረታችሁ ግን የጭልፊት ያህል ትንሽ ከሆነ ውጤቱ ተስፋ መቁረጥ ብቻ ይሆናል።
🎤 ታላቁ ሊቅ ኢማም አሽ-ሻፊዒይ (ረሂመሁላህ) እንዲህ ይላሉ፦
"የዕውቀትን ድካም ለጥቂት ጊዜ እንኳ ያልተለማመደና ያልታገሰ፣ የድንቁርናን ውርደት እድሜ ልኩን ይጎነጫቸዋል።"
⁉️ የነፍስ ጥያቄ፦ እኔ በእርግጥ ለሕልሜ እየኖርኩ ነው ወይስ በምኞት ዓለም ውስጥ ተሸውጄ ነው ያለሁት? ዛሬ የሰራሁት ስራ ለነገው ሕልሜ ያቀርበኛል ወይስ ያርቀኛል?
🔶 የተግባር እርምጃ፦ ዛሬ ማታ ትልቅ ሕልማችሁን በወረቀት ላይ ፃፉ፤ ከዚያም ያንን ሕልም ለማሳካት በየቀኑ ልታደርጓቸው የሚገቡ 3 አነስተኛ ተግባራትን ለዩ።
ክፍል 2፦ ትምህርት ቤት — የዕድል ማዕከል ወይስ የእስር ቤት ደጅ?
ትምህርት ቤት መሄድ፣ ክፍል ውስጥ መቀመጥና የመምህራንን ምክር መስማት እንደ እዳና እንደ እስር ቤት የሚታያችሁ ከሆነ፣ አስተሳሰባችሁን ዛሬውኑ ማደስ አለባችሁ። ትምህርት ቤት ማለት አእምሮአችሁን የምትቀርፁበት፣ የነገውን ዓለም የምትጋፈጡበትን መሳሪያ የምትታጠቁበት ትልቅ የእድል ደጅ እንጂ የእስር ቤት ግንብ አይደለም።
ጥፋት ስታጠፉ የሚቆጧችሁ፣ ጠንክራችሁ እንድታጠኑ የሚገፋፉአችሁ መምህራንና አካላት በደለኛ ወይም ጠላት አይደሉም። በእጃቸው ላይ ያለው የነገው ሀገርና ህብረተሰብ መሪ እናንተ በመሆናችሁ፣ ለእናንተ ካላቸው ትልቅ ፍቅርና ተስፋ የተነሳ የሚከፍሉት መስዋዕትነት ነው።
📖 “«ጌታዬ ሆይ! እውቀትን ጨምርልኝ» በል።” (ሱረቱ ጣሃ 20:114)
⁉️ የነፍስ ጥያቄ፦ መምህራኖቼ ሲቆጡኝ የበደሉኝ ይመስለኛል ወይስ ለወደፊት ህይወቴ ብርሃን ሊያበሩልኝ እንደሆነ አስተውላለሁ?
🔶 የተግባር እርምጃ፦ ነገ ትምህርት ቤት ስትገቡ መምህራኖቻችሁን በፈገግታና በታላቅ ክብር ሰላም በሉ፤ ለሚያደርጉላችሁ ድካምም የልብ ምስጋና አቅርቡላቸው።
ክፍል 3፦ የወደፊቱ የውድድር ዘመን እና የዛሬው ዝግጅት
ዓለማችን በከፍተኛ ፍጥነት እየተቀየረች ነው። ነገ የምትቀላቀሉት ዓለም የእውቀት፣ የክህሎትና የጠንካራ ስነ-ምግባር ውድድር ያለበት ነው። አላህ (ሱ.ወ) የሰጣችሁን አቅም አውጥታችሁ ካልተጠቀማችሁና ራሳችሁን ካላዘጋጃችሁ፣ ባላችሁበት ቦታ መቆም እንኳ ይከብዳችኋል።
ዛሬ የምትለማመዱት ጫናና የምታሳልፉት ድካም፣ ነገ በሚገጥማችሁ ማዕበል ውስጥ ጠንካራ ሆናችሁ እንድትቆሙ የሚያደርጋችሁ ልምምድ ነው። አእምሮ ልክ እንደ ጡንቻ ነው፤ ፈተናና ከባድ ነገር ሲገጥመው ነው የሚጠነክረው።
💎 የአላህ መልክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
❝ጠንካራ ምእመን ከደካማ ምእመን ይበልጥ በአላህ ዘንድ የተወደደና ጥሩ ነው። በሁሉም ላይ መልካም ነገር አለ። ለስጋህና ለዲንህ የሚጠቅምህን ነገር ላይ ጉጉ ሁን፤ በአላህም ተገዝ፤ አትሸነፍ (አትድከም)።❞
(ሶሂህ ሙስሊም 2664)
⁉️ የነፍስ ጥያቄ፦ እኔ ለነገው ከባድ ውድድር ራሴን እያዘጋጀሁ ነው ወይስ ጊዜዬን በማባከን ላይ ነኝ?
ክፍል 4፦ የመሰረት ጥንካሬ — "ገና ጊዜ አለኝ" የሚለው ወጥመድ
"ከ9-12 ስደርስ ጠንክሬ እማራለሁ" ወይም "ለብሔራዊ ፈተና (Entrance Exam) ገና ብዙ ጊዜ አለኝ" የሚል አስተሳሰብ ትልቅ የሽንገላ ወጥመድ ነው። ህንፃ የሚቆመው ባለው ጠንካራ መሰረት ላይ እንደሆነ ሁሉ፣ የከፍተኛ ደረጃ ስኬታችሁም የሚወሰነው ከአንደኛ እስከ ስምንተኛ ክፍል ባላችሁ መሰረት ነው።
ከ12ኛ ክፍል Entrance Exam የሚወጣው ከ9-12 በተማራችሁት ቢሆንም፣ ያንን ትምህርት በቀላሉ የመረዳት አቅማችሁ ግን ከአንደኛ ደረጃ ጀምሮ ባዳበራችሁት የማንበብ፣ የማሰብና የመተንተን ልማድ ላይ የተመሰረተ ነው። ከአሁኑ ጫናን ካለመዳችሁ ነገ ጫናው ሲመጣ መቋቋም ይከብዳችኋል።
🎤 ታላቁ ሊቅ ኢብኑል ቀይም (ረሂመሁላህ) እንዲህ ይላሉ፦
"የጊዜን ዋጋ ያወቀ ሰው፣ ጊዜውን አላስፈላጊ ነገሮች ላይ በማጥፋት አያባክንም፤ ምክንያቱም ጊዜ ማለት ህይወትህ እራሷ ነች።"
⁉️ የነፍስ ጥያቄ፦ ዛሬ የምጥለው መሰረት ነገ የሚያቆመኝ ህንፃ ነው ወይስ የሚደረመስ (የሚፈርስ)?
ክፍል 5፦ ቴክኖሎጂን ለዕውቀት ማሳደጊያ መጠቀም
በአሁኑ ዘመን የተፈጠሩ የቴክኖሎጂ ውጤቶች (እንደ ChatGPT፣ Gemini NotebookLM እና የመሳሰሉት) ለአእምሯችሁ ማሳደጊያ የተሰጡ ድንቅ መሳሪያዎች ናቸው። ነገር ግን ቴክኖሎጂን እንዴት ትጠቀሙበታላችሁ?
የተሳሳተ መንገድ፦ ደብተራችሁን ሳትገልጡ፣ ሳታስቡና ሳታነቡ ሁሉንም ነገር AI ብቻ እንዲሰራላችሁ ማድረግ አእምሯችሁን ያሰንፈዋል።
ትክክለኛ መንገድ፦ የከበዳችሁን ነገር አቅልሎ በምትረዱት ቋንቋ እንዲያስረዳችሁ ማድረግ፣ የመጽሐፍትን ጭብጥ ወደ አጫጭር ማስታወሻዎች (Teacher-written version notes)፣ ጥያቄዎች (Quizzes)፣ የአእምሮ ካርታዎች (Mind-maps)፣ Summaries እና Data-tables እንዲቀይርላችሁ መጠየቅ ነው።
⁉️ የነፍስ ጥያቄ፦ ቴክኖሎጂን አእምሮዬን የሚያጎለብት ረዳቴ አድርጌዋለሁ ወይስ ማሰቢያዬን የሰረቀኝ ጥገኛ?
🔶 የተግባር እርምጃ፦ ዛሬውኑ የከበዳችሁን ምዕራፍ Gemini NotebookLM ወይም ChatGPT ላይ በመጫን አጫጭር የክለሳ ጥያቄዎችን (Quizzes) በማውጣት ራሳችሁን ፈትሹ።
ክፍል 6፦ የትምህርቶች ሁሉ እኩል ዋጋ — Real-World Application
ትምህርት ሲባል ለፈተናና ለሚኒስትሪ የሚወጡትን ብቻ አድርጋችሁ አታስቡ። ክህሎታችሁን የሚያሳድጉ፣ ለነገው እውነተኛ ዓለም (Real-world Application) የሚያዘጋጃችሁን እንደ CTE፣ ICT እና የመሳሰሉትን ትምህርቶች ግዴታ ስለሆነ ብቻ ሳይሆን፣ ህይወታችሁን የሚቀይሩ መሳሪያዎች መሆናቸውን ተረድታችሁ ተማሩ።
እውቀትና ክህሎት አስተሳስረው የያዙ ተማሪዎች በየትኛውም የመስክ ውድድር ውስጥ ቀደምት ይሆናሉ።
🎤 ሸይኩል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ (ረሂመሁላህ) እንዲህ ይላሉ፦
"እውቀት ማለት መረጃን መደርደር ሳይሆን፣ አላህ በልብ ውስጥ የሚጥለውና ወደ ተግባር የሚመራ ብርሃን ነው።"
