uz
Feedback

Firibgarlarga uchmang! Telemetrio bunday kanallarni topadi va belgilaydi 👉 Belgini ko‘rmoqchi bo‘lsangiz, obuna bo‘ling

Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa

Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa

Kanalga Telegram’da o‘tish

Ko'proq ko'rsatish
1 321
Obunachilar
+224 soatlar
+87 kun
+15130 kun
Postlar arxiv
የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ከተለያዩ ኢንዱስትሪዎች ጋር በጋራ መስራታቸው የቴክኒክና ሙያ ዘርፉ ለውጥ ማምጣት እንዲችል አድርጎታል ተባለ፡፡ Hope Enterprise ከ SEED Project፣MasterCard foundation እንዲሁም ከ EDI ጋር በመተባበር ለድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለአሰልጣኝ መምህራኖች እና ለሃሮማያ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አሰልጣኝ መምህራኖች ለተከታታይ 3 ቀናት ሲሰጥ የነበረውን የ ToT ስልጠና በዛሬው ተጠናቀቀ። በዛሬው እለት የተጠናቀው ይህ ስልጠና በዋናነት ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች በገበያ መር አጫጭር ስልጠና ለዜጎች ተደራሽ መሆን እንዴት እንደሚቻል ግንዘቤ ለመፍጠርና ስልጠናዎችን ኢንዱስትሪ መር ለማድረግ ታልሞ የተዘጋጀ ስልጠና እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል ። በተጨማሪም ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች አካታች እንደመሆናቸው መጠን ስልጠናቸውን ሲሰጡ ሴቶችንና አካል ጉዳተኞችን ያማከለ ማድረግ እንዳለባቸው በስልጠና በቂ ግንዛቤ መፍጠር ተችሏል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ በስልጠናው ማብቂያ እለት ከኢንዱስትሪዎችና ባለድርሻ አካላት ጋር የፓናል ውይይት የተደረገ ሲሆን የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ተሞክሮ የቀረበ ሲሆን ኢንዱስትሪዎች ከኮሌጁ ጋ ባላቸው ቅርብ ግንኙነት የተመዘገቡ ለውጦች እጅግ አበረታችና ሌሎች ኮሌጆች በድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ያለውን ምርጥ ተሞክሮ ሊካፈሉት ይገባል ተብሏል። የሶስቱን ቀን ስልጠና እና የዛሬውን የፓናል ውይይት ያዘጋጀው ከኮሌጁ ጋር ቀደም ብሎ የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ ያለው እንዲሁም የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ከኢንዱስትሪዎች ጋር የማቀራረብ ስራ የሚሰራው Hope Enterprise ሲሆን በቀጣይም በርካታ ስራዎችን ከድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ጋር በጋራ እንደሚሰራ ለማወቅ ተችሏል ፡፡ የኮሌጁ ኮምኒኬሽን ጥር 21/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ

የቦንጋ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ አመራሮችን ያቀፈ ልዑካን ቡድን በኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የስራ ልምድ ልውውጥ ጉብኝት አካሄደ፡፡ የቦንጋ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የEASE ፕሮጀክት ከሚተገበርባቸው 24 የሚሆኑ የሀገሪቱ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች አንደኛው ሲሆን በዚህም የኮሌጁን ዲኖች ጨምሮ የተለያዩ የስራ ሀላፊዎችን ያካተተ የልዑካን ቡድን በኮሌጃችን ያለውን የስራ እንቅስቃሴ ለመመልከት እንዲሁም በEASE ፕሮጀክት ትግበራ ያለውን ተሞክሮ ለመውሰድ የሚያስችላቸውን የስራ ልምድ ልውውጥ በኮልጁ ማካሄድ ችለዋል:: ልዑካን ቡድኑ በኮሌጃችን በነበረው የልምድ ልውውጥ መርሃ-ግብር ወቅትም የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ የEASE ፕሮጀክት ትግበራን ጨምሮ ጠቅላላ በተቋም የተመዘገቡ የአፈፃፀም ውጤቶችን በዝርዝር የተመለከቱ ሲሆን በተጨማሪም ኮሌጁ ከምስረታው አንስቶ አሁን እስከደረሰበት ደረጃ የነበረውን ሂደት እና ያከናወናቸውን ዘርፈ ብዙ የለውጥ እንቅስቃሴዎችን በኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ አማካኝነት ሰፋ ያለ ገለፃና ማብራሪያም ተደርጎላቸዋል:: ልኡካን ቡድኑ በኮሌጁ በተደረገላቸው አቀባበልና በተመለከቱት የኮሌጁ እንቅስቃሴ መነሻ በማድረግ የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጁ እያከናወናቸው የሚገኙ ዘርፈ ብዙ የስራ እንቅስቃሴዎች አስደናቂ መሆናቸውን ገልፀው በተለይም ኮሌጁ በEASE ፕሮጀክት ትግበራ ካሳየው የስራ አፈፃፀም ብዙ ልምዶችን መቅሰም መቻላቸውንም ገልፀዋል:: በተጨማሪም ልኡካን ቡድኑ በኮሌጁ የሚገኙ የተለያዩ የስልጠና ዎርክ ሾፖችን ተዘዋውረው የተመለከቱ ሲሆን በነበራቸው የልምምድ ልውውጥ መርሃ-ግብርም የተሳካ ቆይታን በኮሌጃችን ማድረግ ችለዋል:: የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ጥር 21/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ

የመላ ኢትዮጵያውያን የሕልውና ጉዳይ የሆነው የባሕር በር ጥያቄ ** የኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ ተገቢውን ምላሽ ያገኝ ዘንድ ሁሉም ኢትዮጵያውያን በጋራ የቆሙ መሆኑን የዓለም አቀፍ ግንኙነት እና የዲፕሎማሲ ባለሙያው አቶ ጥላሁን ሊበን ገልጸዋል። የባሕር በር ጥያቄው የአንድ መንግሥት ወይም የፖለቲካ ድርጅት ፍላጎት ብቻ ሳይሆን፣ የመላው ኢትዮጵያውያን የሕልውና ጥያቄ መሆኑን ባለሙያው ከኢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል። ኢትዮጵያ የባሕር በር በማጣቷ በየዓመቱ የምትከፍለው የወደብ ኪራይ በሀገር ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ጫና እያሳደረ እንደሚገኝ አቶ ጥላሁን አንስተዋል። ለወደብ ኪራይ የሚወጣው ከፍተኛ ወጪ ለውጥ ሊያመጣ የሚችል ትልቅ ሀብት መሆኑን የጠቀሱት ባለሙያው፤ የባሕር በር ማጣት በዲፕሎማሲና በሀገር ሉዓላዊነት ላይም የራሱ የሆነ አሉታዊ ተፅዕኖ እንዳለው አስረድተዋል። በአዲስ አበባ የጉለሌ ክፍለ ከተማ አርሶ አደሮች ለኢቢሲ በሰጡት አስተያየት፥ የባሕር በር አለመኖር በኑሯቸውና በሥራቸው ላይ ከፍተኛ ጫና እንደፈጠረባቸው ተናግረዋል። አርሶ አደሮቹ እንዳሉት፥ ከውጭ ለሚገባው ማዳበሪያ ዋጋ መናር እንዲሁም ያመረቱትን ምርት በጥሩ ዋጋ ለውጭ ገበያ ማቅረብ ያልቻሉበት ዋነኛው ምክንያት የባሕር በር ማጣት ነው። "የባሕር በሩ ቢገኝልን አርሶ አደሩም፣ ነጋዴውም ሆነ ሸማቹ ተጠቃሚ ይሆናል" ሲሉ አርሶ አደሮቹ ተስፋቸውን ገልጸዋል። የባሕር በር ጥያቄው ተገቢ መሆኑን በመጥቀስ፣ ለስኬቱ አስፈላጊውን መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል። የባሕር በር ጥያቄው ውጤት እንዲያመጣ ወጣቱ ትውልድ እና ሚዲያዎች የሀገርን ብሔራዊ ጥቅም በማስቀደም ግንዛቤ የመፍጠር ሥራ እንዲያከናውኑ ጥሪ ቀርቧል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ ባሕር በር ጥያቄ በሰላማዊ መንገድ እና በድርድር ምላሽ እንዲያገኝ መንግሥት በጽኑ እንደሚሠራ መግለፃቸው ይታወሳል።

#ዜና | የኢትዮ ጣሊያን ፖሊቲክኒክ ኮሌጅ በሙያ ደህንነት እና ጤንነት (occupational Safty and Health) ዙሪያ ሲያስለጥናቸው የቆየውን ከአስር ስድስት(16) በላይ የኢንዱስትሪ አንቀሳቃሽ ባለሞያዎችን አስመርቋል:: ኮሌጁ ይህን ስልጠና ሲያከናውን ለመጀመሪያ ጊዜ ሲሆን ከሽንብሮ ፕላስቲክ ፋብሪካ ጋር በመዋዋል የፋብሪካውን ከአስራ ስድስት (16 ) በላይ የሆኑ ሰራተኞችን አሰልጥኖ ማስመረቁን በወቅቱ ተጠቅሷል ። በወቅቱ ንግግር ያደረጉት የስራና ክህሎት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊና የቴክኒክና ሞያ ኤጀንሲ ዳሬክተር ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ ቢሮው በስሩ ዘርፈብዙ ስራዎችን እንደሚሰራ ጠቅሰው ከስራዎቹም መካከል የፋብሪካን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ የሞያ ክፍተቶችን በመሙላት ደህንነታቸው የተጠበቀ የበቁ ዜጎችን ማብቃት ነው ብለዋል :: ቢሮው የሞያ ክፍተትን በስልጠና ማጠናከር ብቻ ሳይሆን በሁለቱ የመንግስት ኮሌጆች በኩል በአስተዳደሩ ለሚገኙ የተለያዩ ፋብሪካዎች መለዋወጫዎችን በማምረት የውጭ ምንዛሬን ከማስቀረት ባሻገር ከውጪ ግብዓቱ የሚመጣበትንም ጊዜ እንዲቆጠብ እያደረገ ይገኛልም በማለት ሀላፊዋ አክለው ተናግረዋል :: የኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ በበኩላቸው ይህ የፋብሪካ ውስጥ የሞያ ደህንነትና የጤና አጠባበቅ ስልጠና እንደ ሀገር ያለ ክፍተት መኖሩን ጠቅሰው ኮሌጁ ይህን ችግር ለመቅረፍ ለመጀመሪያ ጊዜ ከሽንብሮ ፕላስቲክ ፋብሪካ ጋር በመዋዋል የፋብሪካውን ከአስር ስድስት (16) በላይ ሰራተኞች ማሰልጠናቸውን ተናግረዋል :: ስልጠናውን ተከታትለው የተመረቁት ስልጣኖች በበኩላቸው የወሰዱት የሞያ ደህንነትና የጤና ስልጠና ከፋብሪካ ውስጥ ስራችን ውጪም የግል ሕይወታችንን ለምን መራበት አካባቢም የሚጠቅመን ነው ብለዋል :: በምረቃና ማጠቃለያ መርሃ ግብሩ ላይም ስልጠናቸውን ላጠናቀቁ ሰልጣኖች የእውቅና ስርተፊኬት ተሰጥቷል :: #DireTvአማርኛ |ጥር 16 ፥ 2018 ዓ.ም | ድሬዳዋ

የ2017 ዓ.ም ቅድመ ሞዴልና የ2018 ዓ.ም ሞዴል ኢንተርፕራይዞች በኢንተርፕርነርሽፕ እና በቢዝነስ ዴቨሎፕመንት ላይ ሰልጠና ተሰጠ። በዚህም ስልጠና የኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾችን ባገኙት ዕውቀትና ክህሎት ምርትና ምርታማነታቸውን ለማሳደግና ያላቸውን ልምድ እርስ በእርሳቸው እንዲለዋወጡ ለቀጣይም የዕድገት ደረጃ ለማብቃት አቅማቸውን የሚገነባ ይሆናል። በመሆኑም ኢንተርፕራይዞቹ በቀጣይ በሞዴል መመዘኛ መሰረት ተመዝነው ከዛ ውስጥ የተሻለ የሚባሉትን ምርጥ ተሞክሮ የሚቀመር ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ ታዳጊ መካከለኛ በየአመቱ የሚሸጋገሩትን በመስፈርቱ መሰረት የመለየት ስራ ተጠናክሮ የሚሰራ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የኢንተርፕራይዞች ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሙሉጌታ ሀ/ማርያም ገልጸዋል፡፡ የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ጥር 15/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ

በድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የአሰሪና ሰራተኛ ዳይሬክቶሬት ለአገር ውስጥ ስራና ሰራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አዘጋጀ። በመድረኩም ከተለያዩ በአስተዳደሩ ከሚገኙ የአገር ውስጥ ስራና ሰራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች ለተወጣጡ አሰሪና ሰራተኞች በሁለትዮሽ ማህበራዊ ምክክር ዝርጋታ እና በአሰሪና ሰራተኞች አዋጅ ቁጥር 1156/2011 ላይ ማብራሪያ ተሰጥቷቸዋል። በዚህም አዋጁን በመረዳት የአሰሪውንና ሰራተኛውን ግንዛቤ ማሳደግ ዓላማው አድርጎ ከዚህ ጎን ለጎን የሚኖሩ አለመግባባቶችን በመቀነስ የስራ ክርክሮችን በምክክር መፍታት የሚያስችላቸው ይሆናል። የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ጥር 15/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ

የድሬዳዋ አስተዳደር ኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ድጋፍን ለማሻሻልና ለማዘመን መነሻ የሚሆን የአምስት አመታት ትግበራ አፈጻጸም ጥናት ቀርቦ ውይይት ተደረገ፡፡ በቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች የሚተገበረው ኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ድጋፍ አስመልክቶ ከ2013-2017 ዓ.ም ድረስ በኢንተርፕራይዞች ላይ ያመጣው ለውጥ ምን ይመስላል የሚለውን የሚያሳይ የተጠና ጥናት ለባለድርሻ አካላት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡ በዚህም የሚሰጠውን ድጋፍ ለማሻሻልና ለማዘመን የሚያግዙ ሃሳቦች በመድረኩ የተነሱ ሲሆን የኢንተርፕራይዞች የብቃት ማረጋገጫ ምዘና በሁሉም ባለ ድርሻ አካላት ተሳትፎ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተመላክቷል፡፡ በመድረኩ የግል ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ድጋፍ ላይ ያላቸው ተሳትፎ ምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የተገመገመ ሲሆን ቀጣይ የስራ አቅጣጫ በድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ም/ኃላፊና በቢሮው የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኤጀንሲ ኃላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ ተሰጥቷል፡፡ የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ጥር 15/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ

የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት የስራ አፈፃፀም ግምገማ እና የመውጫ ግብረ-መልስ ተሰጠ፤ የሥራና ክህሎት ቢሮ  የስድስት ወር የስራ አፈፃፀም በድሬደዋ አስተዳደር ምክር ቤት የበጀት ኢኮኖሚ፣ ንግድና ኢንዱስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ተገምግሟል። በግምገማው መድረክ  ቢሮው የ2018 በጀት አመት ስድስት ወራት  ያከናወናቸውን ተግባራት ቋሚ ኮሚቴው ለተከታታይ ቀናት ያካሄዷቸውን የመደበኛ እና የካፒታል  ፕሮጀክቶች በተመለከተ መስክ ምልከታ የተለዩ ጉዳዮች እና የተዘጋጀውን ቼክ ሊስት መነሻ በማድረግ ከቋሚ ኮሚቴ አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች እና ግልፅነት የሚፈልጉ  ስራዎች ላይ በቢሮው አመራሮች ሀሳብ አስተያየት ተሰጥቶባቸዋል። የሥራና ክህሎት ቢሮ ም/ኃላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ ከቋሚ ኮሚቴው  ከተነሱ ጥያቄና ማብራሪያ የሚያስፈልጋቸው ለቢሮው የተስጡ  ግብረ መልሶች፣ የውክል አወጣጥ መድረኮች የተነሱ ጥያቄዎች በገጠርና ከተማ የተፈጠሩ  ስራ ዕድሎች፣  የኢንተርፕራይዞች ልማት እንቅስቃሴ፣ የ100 ቀን ዕቅድ  የሪፎርም ስራንም ጨምሮ በ6 ወራት ታቅደው የተከናወኑ ተግባራት፣ የተገኙ ውጤቶችና  ሊፈቱ የሚገቡ ተግዳሮቶች ላይ ሰፋ ያለ ማብራርያ የሰጡ ሲሆን የቢሮው የማኔጅመንት አባላትም በሚመለከታቸው ጉዳዮች ላይ ምላሽ ሰጥተዋል። የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ወ/ሮ አይናለም ተዘራ በበኩላቸው የዝግጅት ምዕራፍ አፈፃፀማቸው፣ የቢሮው ስትራቴጂክ ግቦች ዋና ዋና እና በዝርዝር የታቀዱ  ተግባራት የተፈፀሙ መሆናቸው  በስራቸው ያሉ ተቋማት ጋር ያላቸው ቅንጅታዊ አሰራር በመጠናከሩ የተቋሙ የ6 ወር የስራ አፈፃፀም ጥሩና የሚበረታታ መሆኑን በመግለጽ ጥንካሬዎችን በማስቀጠል እና የስራ ክህሎት ምክር ቤት መደበኛ ግዜውን ጠብቆ  መድረክ በማዘጋጀትና ባለድርሻ አካላት ኃላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ በማድረግ በመስክና በመድረክ የተገመገሙ  ውስንነቶችን በሚገባ ማረም እንደሚያስፈልግ  ገልፀው የቢሮውን የመውጫ ግብረ መልስ ሰጥተዋል። የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ጥር 14/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ

የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት የስራ አፈፃፀም ግምገማ እና የመውጫ ግብረ-መልስ ተሰጠ፤ የሥራና ክህሎት ቢሮ  የስድስት ወር የስራ አፈፃፀም በድሬደዋ አስተዳደር ምክር ቤት የበጀት ኢኮኖሚ፣ ንግድና ኢንዱስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ተገምግሟል። በግምገማው መድረክ  ቢሮው የ2018 በጀት አመት ስድስት ወራት  ያከናወናቸውን ተግባራት ቋሚ ኮሚቴው ለተከታታይ ቀናት ያካሄዷቸውን የመደበኛ እና የካፒታል  ፕሮጀክቶች በተመለከተ መስክ ምልከታ የተለዩ ጉዳዮች እና የተዘጋጀውን ቼክ ሊስት መነሻ በማድረግ ከቋሚ ኮሚቴ አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች እና ግልፅነት የሚፈልጉ  ስራዎች ላይ ቡቢሮው አመራሮች ሀሳብ አስተያየት ሰጥቶባቸዋል። የሥራና ክህሎት ቢሮ ም/ኃላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ ከቋሚ ኮሚቴው  ከተነሱ ጥያቄና ማብራሪያ የሚያስፈልጋቸው ለቢሮው የተስጡ  ግብረ መልሶች፣ የውክል አወጣጥ መድረኮች የተነሱ ጥያቄዎች በገጠርና ከተማ የተፈጠሩ  ስራ ዕድሎች፣  የኢንተርፕራይዞች ልማት እንቅስቃሴ፣ የ100 ቀን ዕቅድ  የሪፎርም ስራንም ጨምሮ በ6 ወራት ታቅደው የተከናወኑ ተግባራት፣ የተገኙ ውጤቶችና  ሊፈቱ የሚገቡ ተግዳሮቶች ላይ ሰፋ ያለ ማብራርያ የሰጡ ሲሆን የቢሮው የማኔጅመንት አባላትም በሚመለከታቸው ጉዳዮች ላይ ምላሽ ሰጥተዋል። የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ወ/ሮ አይናለም ተዘራ በበኩላቸው የዝግጅት ምዕራፍ አፈፃፀማቸው፣ የቢሮው ስትራቴጂክ ግቦች ዋና ዋና እና በዝርዝር የታቀዱ  ተግባራት የተፈፀሙ መሆናቸው  በስራቸው ያሉ ተቋማት ጋር ያላቸው ቅንጅታዊ አሰራር በመጠናከሩ የተቋሙ የ6 ወር የስራ አፈፃፀም ጥሩና የሚበረታታ መሆኑን በመግለጽ ጥንካሬዎችን በማስቀጠል እና የስራ ክህሎት ምክር ቤት መደበኛ ግዜውን ጠብቆ  መድረክ በማዘጋጀትና ባለድርሻ አካላት ኃላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ በማድረግ በመስክና በመድረክ የተገመገሙ  ውስንነቶችን በሚገባ ማረም እንደሚያስፈልግ  ገልፀው የቢሮውን የመውጫ ግብረ መልስ ሰጥተዋል። የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ጥር 14/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ