uz
Feedback

Firibgarlarga uchmang! Telemetrio bunday kanallarni topadi va belgilaydi 👉 Belgini ko‘rmoqchi bo‘lsangiz, obuna bo‘ling

Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa

Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa

Kanalga Telegram’da o‘tish

Ko'proq ko'rsatish
1 316
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
+287 kun
+14730 kun
Postlar arxiv
የአዲስ ሰልጣኝ ተማሪዎች ምዝገባ መቼ ነው?...ማንኛውም የ12ኛ ክፍል አጠናቃቂ ከጥቅምት 6-20 ድረስ በአስተዳደሩ የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች መመዝገብ የሚችል ይሆናል፡፡

የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ    ዶ/ር ፍቃዱ በየነ በቢሮው የኢንተርፕራይዝ ልማት ዳይሬክቶሬት ሥር የሚደገፉ ኢንተርፕራይዞች ወደሚንቀሳቀሱባቸው የሥራ ቦታዎች በመሄድ የሥራ ሁኔታቸውን፣ ያሉባቸውን ተግዳሮቶችና የማደግ ፍላጎታቸውን በቀጥታ ጎብኝተው ተመልክተዋል። በጉብኝቱ ወቅት የኢንተርፕራይዞቹ አንቀሳቃሾች የሚያነሷቸው የተለያዩ ጥያቄዎችና ለቀጣይ እድገታቸው ያላቸው ከፍተኛ ፍላጎት በቀጥታ የተመለከቱ ሲሆን፣ የኢንተርፕራይዞቹን አሁናዊ ሁኔታ በመረዳት ለልማታቸው የሚያስፈልጉ ድጋፎችን በተቀናጀ መንገድ ለማሟላት ያለውን አስፈላጊነት አጉልቶ አሳይቷል። ዶ/ር ፍቃዱ በየነ በበኩላቸው፣ በጉብኝቱ የተነሱ ጥያቄዎችን በተመለከተ ቢሮው ከሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ጋር በመናበብና በመቀናጀት ተገቢውን ምላሽ ለመስጠት እንደሚሠሩ ገልጸዋል። የጉብኝቱ ዋና ትኩረትም የኢንተርፕራይዞችን የሥራ እውነታ በቅርበት በመረዳት፣ የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች ለመፍታትና የእድገት አቅማቸውን ለማጎልበት የተቋማዊ ትብብርን ማጠናከር ነው። የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ – የሕዝብ ግንኙነት ድሬዳዋ | ጥቅምት 5/2019 ዓ.ም

#ዜና /በድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አብዱላሂ አደም የተመራ ልኡካን ቡድን የኢትዮ-ጣሊያን ኮሌጅን የሥልጠና ክፍሎች ጎበኘ በአስተዳደሩ ከንቲባ አቶ አብዱላሂ አደም የተመራ ልኡክ በኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በመገኘት የተግባር ክህሎት ሥልጠና የሚሰጥባቸውን የተለያዩ የትምህርት ክፍሎች ተዘዋውሮ ጎብኝቷል። ኮሌጁ በሥሩ በሚገኙ ዘጠኝ የትምህርት ክፍሎች አማካኝነት በድሬዳዋ አስተዳደር ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ መነቃቃት ላይ ለሚገኘው ለአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ በክህሎት የዳበረና ብቁ የሆነ የሰው ኃይል ለማፍራት የበኩሉን ከፍተኛ ድርሻ እየተወጣ ይገኛል። ከንቲባው በጉብኝታቸው ወቅት ኮሌጁ ለአስተዳደሩ የኢንዱስትሪ ዕድገት እያበረከተ ያለውን አስተዋፅዖ የተመለከቱ ሲሆን፣ ተቋሙ ብቁ ባለሙያዎችን በማፍራት ረገድ ያለውን ሚና አጠናክሮ እንዲቀጥልም መልዕክት አስተላልፈዋል። አስተዳደሩ ለቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ልዩ ትኩረት መስጠቱን የጠቆሙት ከንቲባው በኮሌጁ የሚሰለጥኑ ወጣቶች የንድፈ-ሀሳብ ዕውቀታቸውን ከተግባር ልምምድ ጋር በማዋሃድ በቀጥታ ወደ ሥራው ዓለም እንዲገቡና የራሳቸውን የሥራ ዕድል እንዲፈጥሩ ጥሪ አቅርበዋል። መንግሥትም ለተቋሙ ማጠናከሪያና ለሰልጣኞች ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አመላክተዋል።

በድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ሥር የሚገኘው የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ ከኮሌጆች ጋር በመሆን የቴክኖሎጂ ሽግግርና የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት የ2019 ዓ.ም የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸምን ገምግሟል። በግምገማው የዕቅድ አፈጻጸሙን ሁኔታ በመገምገም፣ የተከናወኑ ሥራዎችን በመፈተሽና ቀጣይ ሥራዎችን በተቀናጀ መንገድ ለማስፈጸም በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ውይይት ተካሂዷል። በተጨማሪም በ2019 ዓ.ም የሚካሄደውን የቴክኖሎጂና የክህሎት ውድድር ዕቅድ በተመለከተ ዝግጅቱን በተቀናጀና ውጤትን ባማከለ መንገድ ለማከናወን ያስችላሉ በተባሉ ጉዳዮች ላይ ምክክር ተደርጓል። የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ምክትል ኃላፊና የኤጀንሲው ኃላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ በግምገማው ወቅት በዕቅድ አፈጻጸሙና በቀጣይ የሥራ አቅጣጫዎች ላይ መመሪያ ሰጥተዋል። የቴክኖሎጂ ሽግግርን ማጠናከር፣ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎትን ማሳደግና የኮሌጆችን ተሳትፎ ማጠናከር በዘርፉ የሚጠበቁ ውጤቶችን ለማሳካት ወሳኝ መሆናቸው በውይይቱ ላይ ትኩረት የተሰጣቸው ጉዳዮች ናቸው። የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ – የሕዝብ ግንኙነት ድሬዳዋ | ጥቅምት 4/2019 ዓ.ም

የሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ፍቃዱ በየነ በሁለቱ የመንግሥት ፖሊቴክኒክ ኮሌጆች የትውውቅና የሥራ ጉብኝት አካሄዱ የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ፍቃዱ በየነ በድሬዳዋ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅና በኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በመገኘት የትውውቅና የሥራ ጉብኝት አካሂደዋል። በጉብኝቱም የኮሌጆቹን አጠቃላይ የሥራ አፈጻጸም በሪፖርት በመገምገምና በመስክ በመዘዋወር አሁናዊ ሁኔታቸውን ተመልክተዋል። በድሬዳዋ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ባለፉት ሰባት ዓመታት በEASTRIP ፕሮጀክት የተከናወኑ የሰው ኃይል ልማትና የመሠረተ ልማት ግንባታ ሥራዎችን አፈጻጸም ገምግመዋል። በተጨማሪም የSIFA ፕሮጀክትን አፈጻጸም በመስክ ተገኝተው ጎብኝተዋል። በኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በኩል ደግሞ የEASE ፕሮጀክት አፈጻጸምን በመገምገም፣ ፕሮጀክቱ ለተቋሙ አቅም ግንባታና የሥራ ትስስር ምጣኔን ለማሳደግ እያበረከተ ያለውን አስተዋጽኦ ተመልክተዋል። በጉብኝቱ የታዩ የሥራ አፈጻጸም ውጤቶች የሚበረታቱ መሆናቸው ተጠቁሞ፣ ክፍተቶች በታዩባቸው ዘርፎች በማካካሻ ዕቅድ ላይ ተመሥርቶ ውጤትን የማሳደግ ሥራ እንዲጠናከር አስፈላጊነቱ ተነስቷል። በተለይም በኮሌጆቹ የተፈጠረውን ውስጣዊ አቅም በተሟላ ሁኔታ በመጠቀም የሥራ አፈጻጸምን ማሻሻልና የተገኙ ውጤቶችን ማስቀጠል ላይ ትኩረት ተደርጓል። የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ – የሕዝብ ግንኙነት ድሬዳዋ | ጥቅምት 4/2019 ዓ.ም

የሥራ ማዕከላት የአፈጻጸም ግምገማና የወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ ምዝገባን ለማፋጠን አቅጣጫ ተሰጠ የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ፍቃዱ በየነ ከአስተዳደሩ የሥራ ማዕከላት አመራሮች ጋር የትውውቅና የወቅታዊ የሥራ አፈጻጸም ውይይት አካሂደዋል። በውይይቱም የሥራ ማዕከላቱ ወቅታዊ አፈጻጸምና በቀጣይ ትኩረት ሊሰጣቸው በሚገቡ ተግባራት ላይ ተወያይተዋል። በተለይም የአራተኛው ዙር “ብቃት” የወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ ፕሮግራም የምዝገባ ሂደት አፈጻጸም በዝርዝር ተገምግሟል። ፕሮግራሙ በታቀደው መሠረት እንዲተገበርና የምዝገባ ሂደቱ በትኩረትና በተከታታይ ክትትል እንዲመራ አቅጣጫ ተቀምጧል። ዶ/ር ፍቃዱ የምዝገባ ሂደቱ እስኪጠናቀቅ ድረስ የሥራ ማዕከላት አመራሮች በቅንጅትና በተጠያቂነት እንዲሠሩ፣ ተግባሩንም በተገቢው ትኩረት እንዲያስፈጽሙ አሳስበዋል። የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ድሬዳዋ | ጥቅምት 3/2019 ዓ.ም

የሙያ ብቃትን ከሥነ-ምግባርና ከሥራ ፈጠራ ጋር ለማቀናጀት ያለመ የመሪ አሰልጣኞች ስልጠና በድሬዳዋ ተጀመረ ብቁ የሰው ኃይል ለማፍራት የቴክኒክና ሙያ እውቀትና ክህሎትን ከሥነ-ምግባር፣ ከዜግነት ኃላፊነት፣ ከሰው ተኮር ክህሎቶችና ከሥራ ፈጠራ አስተሳሰብ ጋር ማቀናጀት ወሳኝ መሆኑ ተገለጸ። ይህንን ዓላማ ያነገበ የመሪ አሰልጣኞች ስልጠና በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አዘጋጅነት፣ በድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ አስተባባሪነትና በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ማዕከልነት ለ10 ቀናት የሚካሄድ ይሆናል። ስልጠናው የሥነ-ምግባርና የዜግነት ኃላፊነት፣ Human Edge Skills እና የሥራ ፈጠራ ትምህርትን ያካትታል። በመክፈቻው ላይ የቢሮው ምክትል ኃላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ፣ የሙያ ብቃት በቴክኒክ እውቀት ብቻ አይወሰንም፤ እውቀትን በሥነ-ምግባር፣ በኃላፊነትና በሥራ ፈጠራ አስተሳሰብ ማጠናከር ይጠይቃል የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል። በስልጠናው ከምሥራቅ ኦሮሚያ፣ ከሐረሪና ከሶማሌ ክልሎች እንዲሁም ከድሬዳዋ አስተዳደር የመንግሥትና የግል ቴክኒክና ሙያ ተቋማት መምህራን ተሳታፊ ሆነዋል። ተመሳሳይ ስልጠና በሐዋሳና በጎንደር ዩኒቨርሲቲዎችም እየተካሄደ ሲሆን፣ ቀደም ሲል በጅማ፣ በባህር ዳርና በወሎ ዩኒቨርሲቲዎች ተካሂዷል። የሥራና ክህሎት ቢሮ — ሕዝብ ግንኙነት ድሬዳዋ | ጥቅምት 3/2019 ዓ.ም.

"ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ መግባባትና ለአንድነታችን!" በሚል መሪ ቃል የሰንደቅ ዓላማ ቀን ተከበረ፡፡ በዚህም 19ኛውን ብሔራዊ የሰንደቅ አላማ ቀን በዓል የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ እንዲሁም የድሬዳዋ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ አመራሮችና ሰራተኞች በጋራ አክብረዋል፡፡ በበዓሉ ማጠናቀቂያ በአንድነት ለሰንደቅ ዓላማ  ክብር በሰጠና የብሔራዊ አንድነታችን መገለጫ ምልክት መሆኑን በሚያሳይ በኢትዮጵያ ህዝብ መዝሙር የታጀበ የባንዲራ መስቀል ስነ-ሥርዓት ተካሂዷል፡፡ የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ጥቅምት 2/2019 ዓ.ም ድሬዳዋ

19ኛው ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን በኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ተከበረ:: #EIPC ጥቅምት 02. 2019 ዓ.ም ድሬዳዋ የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ አመራሮች፣ ሰራተኞችና ሰልጣኝ ተማሪዎች
+9
19ኛው ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን በኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ተከበረ:: #EIPC ጥቅምት 02. 2019 ዓ.ም ድሬዳዋ የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ አመራሮች፣ ሰራተኞችና ሰልጣኝ ተማሪዎች ዘንድሮ ለ19ኛ ጊዜ "ሠንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ መግባባትና አንድነትታችን" በሚል መሪ ቃል በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚከበረውን ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን በደማቅ ሁኔታ እክብረዋል:: በክብረ በዓሉ ላይ በመገኘት መልዕክት ያስተላለፉት የኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ በንግግራቸው እንደገለፁት ሠንደቅ ዓላማ የአንድ ሀገር የሉዓላዊነትና የነፃነት ምልክት መሆኑን ገልፀው ይህን ቀን ስናከብር እውነተኛ የሀገር ፍቅር መገለጫ በሆነው በተሰማራንበት በየትኛውም ዘርፍ በጀግንነት ለማገልገል ለራሳችን ቃል በመግባት ሊሆንም ይገባል ብለዋል:: "ሠንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ መግባባትና አንድነትታችን" ተጨማሪ መረጃዎችን በሚከተሉት አማራጮች ያግኙ፡- በፌስቡክ -https://www.facebook.com/share/19wDiZAD7x/?mibextid=wwXIfr በቴሌግራም -https://t.me/EIPC2001 በቲክቶክ -https://www.tiktok.com/@ethioitaly2001?_t=ZM-90MxIrBN8qe&_r=1 በዌብሳይት - https://ethioitalypolytechniccollege.com/

ወጣቶች ሲማሩ ከንድፈ ሀሳብ ትምህርት ባሻገር ዓለም አቀፍ የሥራ ስነ-ምግባርን በተግባር በመማር ለአገርና ለዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት፣ ለተፈላጊነት እንዲሁም ለሥራ ፈጣሪነት ብቁ መሆን እንዳለባቸው ተጠቆመ። ​ኦልብራይት ኢንተርናሽናል ኮሌጅ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 166 ተማሪዎች አስመርቋል። ኦልብራይት ኢንተርናሽናል ኮሌጅ ከተመሠረተበት 2015 ዓ.ም ጀምሮ ለሁለተኛ ጊዜ ባካሄደው በዚህ የምረቃ መድረክ በአካውንቲንግና ፋይናንስ፣ በሃርድዌርና ኔትወርኪንግ አገልግሎት፣ እንዲሁም በማርኬቲንግና ሴልስ ማኔጅመንት ያሰለጠናቸውን 94 ሴት እና 72 ወንድ በድምሩ 166 ተማሪዎችን አስመርቋል። ​በመድረኩ በክብር እንግድነት የተገኙት የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ ባስተላለፉት መልእክት ተማሪዎች ከምረቃ በኋላ በተማሩት ትምህርት ሥራ ፈጣሪ መሆን እንዳለባቸው አሳስበዋል። ቢሯቸው ክህሎት መር የሥራ ዕድል ፈጠራን በማስፋፋት ሰፊ እድሎችን ይዞ እየመጣ በመሆኑ ወጣቶች ለሥራ ያላቸውን አመለካከትና ፍላጎት ማሻሻል እንዳለባቸው አክለው ገልጸዋል። ​የኦልብራይት ኢንተርናሽናል ኮሌጅ ምክትል ዲን አቶ ዮናስ መሐመድ በበኩላቸው "ዓለማችን በቴክኖሎጂና በሰው ሰራሽ አስተውሎት እየተለወጠች እንደመሆኗ ኮሌጁም ከዚህ ለውጥ ጋር አብሮ ለመራመድ ዝግጁ ነው" ብለዋል። ኮሌጁ ተማሪዎቹን በእውቀት፣ በቴክኖሎጂ፣ በፈጠራና በሙያ ብቃት የጎለበቱ ተወዳዳሪ ዜጎች አድርጎ ለማፍራት አልሞ እየሰራ እንደሚገኝም አስረድተዋል። ​ኮሌጁ ከመደበኛ ትምህርት በተጨማሪ ከተለያዩ ተቋማት ጋር በመቀናጀት በአስተሳሰብ ልህቀት፣ በትምህርት ቤቶች ድህረ-ገጽ ግንባታና በዲጂታል ክህሎት ዘርፍ ለአካባቢው ማህበረሰብ ሥልጠናዎችን መስጠቱና በማህበረሰብ ልማት ዘርፎች በርካታ ተግባራትን ማከናወኑ በዝግጅቱ ላይ ተገልጿል። ​በስነ-ስርዓቱ ማጠቃለያ ላይ ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተመራቂዎች የሜዳሊያና የዋንጫ ሽልማት የተበርክቶላቸዋል። ©️ DireTvአማርኛ | መስከረም 30 ፥ 2019 ዓ.ም | ድሬዳዋ