cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

እዉነት ለሁሉ

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
2 466
Obunachilar
+2224 soatlar
+217 kunlar
+39130 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

ማቴዎስ_ወንጌል 28፡19 "በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም" ይላል አይልም..?? አንዳንድ ሰዎች ይህ ጥቅስ ተበርዟል ይላሉ.. በተለይ "ኦንሊ ጂሰስ" በመባል የሚታወቁት አካላት አውሳብዮስ የተባለ የታሪክ ጸሐፊን ንግግር በመያዝ ቃሉ የሚለው "በእኔ ስም አጥምቁ" እንጂ አሁን በመጽሐፍ ቅዱሳችን ባለው መልኩ "በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም" አይልም ይሉናል። በእርግጥ እንደው "ኦንሊ ጂሰሶችስ" ለእምነታቸው መደገፊያ ብለው ይህንን ይላሉ ይህንኑ የሚደግሙት አንዳንድ ሙስሊሞች አሁን እስቲ ጥምቀት በኢየሱስ ስም ቢሆን ከእስልምና ጋር ምን ያገናኘዋል..?? እንደው ሰው ያለው ነገር አይቅርብኝ አትበሉ.. ለማንኛውም እስቲ ይህንን ለመመለስ ከአውሳብዮስ በፊት የነበሩ አባቶችን ብቻ ከራሳቸው ከሃዋርያት ከተማሩ አባቶች ጀምረን ስለዚህ ቃል(ማቴዎስ 28፡19) የተናገሩትን እንመለከታለን፤  ከዛም ደግሞ በስተመጨረሻም ራሱን እነሱ የጠቀሱትን አውሳብዮስን እንደማስረጃነት እንጠቀመዋለን። ከዚያም ደግሞ ጥንታውያኑን እደ ክታባት(Manuscripts) ምን እንደሚሉ እንመለከታቸዋለን። 👇👇👇👇👇👇 "ነቢያት እንዲህ ሲሉ ተናገሩ፡ 'ለእርሱ የሚጠብቀውን እስኪያገኝ ድረስ የአህዛብ ተስፋቸው እርሱ ነውና'(ዘፍ 49፡10) ይህም ያወጁት ቃል በወንጌል ውስጥ ጌታችን 'ሂዱ አህዛብን ሁሉ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችሁ አስተምሯቸው' ባለ ጊዜ ተፈጸመ።" [St Ignatius: to philadelphians, chap 9] ሦስት አብ ወይም ሦስት ወልዶች ወይም ሦስት መንፈስ ቅዱሶች ያሉ አይደሉም ይልቁንም ጌታችን አህዛብን ደቀመዛሙርት ያደርጉ ዘንድ ሃዋርያትን ሲልክ 'በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችሁ' ብሎ በማዘዝ ነው። ስለዚህም አንዱ አካል ሦስት ስም እንደኖረው አይደለም ወይም ደግሞ ሦስቱ አካላት ሥጋ ሆነው እንደመጡ አይደለም ይልቁንም እኩል ክብር ባላቸው በሦስቱ እንጂ። [St Ignatius: to philipians, chap. 1] "(ጌታ) እርሱም (ሃዋርያትን) እንዲህ አላቸው 'ሂዱ አህዛብን ሁሉ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችሁ አስተምሯቸው'" [St Irenaeus: against heresies 3:17:1] "የጥምቀት ህግ ተደንግጓልና፤ ፎርሙላውም(እንዴት እንደምንጠመቅ) ተቀምጧልና፣ 'ሂዱ' አላቸው 'አህዛብን ሁሉ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችሁ አስተምሯቸው'" [tertulian: on baptism, chap 13] "ጌታም ከትንሳኤው በኋላ ሃዋርያቱን ሲልክ በምን መልኩ ማጥመቅ እንዳለባቸው እንዲህ ሲል አስተማራቸው 'ሥልጣን ሁሉ በሰማይና በምድር ተሰጠኝ፤ እንግዲህ ሂዱ አህዛብን ሁሉ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችሁ አስተምሯቸው'" [St Cyprian: epistle 72:5] "እንዲህም ሲል ሃላፊነትን ሰጣቸው 'ሥልጣን ሁሉ በሰማይም በምድርም ተሰጠኝ፤ እንግዲህ ሂዱ አህዛብን ሁሉ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችሁ አስተምሯቸው'" [Lucius of Castra Gilba on The Seventh Council of Carthage under Cyprian] "አምላክንና ጌታችን ኢየሱስ በራሱ አንደበት ደቀመዛሙርቱን እንዲህ ሲል አዘዛቸው 'ሂዱ አህዛብን ሁሉ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችሁ..'” [Euchratius of Thena on The Seventh Council of Carthage under Cyprian] "እኛ በእርግጥም የእውነት ህግ አለን ይህም ጌታ በመለኮታዊው ትእዛዙ ሃዋርያቱን 'ሂዱ አህዛብን ሁሉ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችሁ አስተምሯቸው' ያለው ነው።" [Vincentius of Thibaris on The Seventh Council of Carthage under Cyprian] አርጌንስ የማቴዎስ ወንጌል 28፡19ን ቀጥታ አሁን እኛ ጋር ባለው መልኩ ይጠቅሰዋል [origen: Homilies on Genesis, hom. 13] 🔥ሰዎቻችን የሚጠቅሱትም አውሳብዮስ "በእኔ ስም አጥምቁ" በማለት እንደተናገረ አድርጎ የጻፈው መቼስ ከእነዚህ ሁሉ አባቶች ዘንድ ከነበረ መጽሐፍ ቅዱስ ለእሱ ለብቻው ሌላ ወርዶለት ሳይሆን "በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አጥምቁ" የሚለው መለኮታዊ ትእዛዝ የጌታችን የኢየሱስ ትእዛዝ ነውና "በእኔ ስም" ብሎ አውሳብዮስ መናገሩ.. ወይም ደግሞ አንዳንድ አባቶች "በኢየሱስ ስም" ቢሉ በኢየሱስ ትእዛዝ ለማለት እንጂ ሌላ አይደለም። ቃሉን ቀጥታ "በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም" በማለት ራሱ አውሳብዮስ ሲጠራው እንዲህ አለ፡ "ጌታችን ኢየሱስ ደቀመዛሙርቱን 'እንግዲህ ሂዱ አሕዛብን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችሁ አስተምሯቸው' በማለት እንዳዘዘ.." [letter of Eusebius concerning the council of nicea, 3] እደክታባቱስ ምን ይላሉ..?? ኮዴክስ ሳይናይቲከስ, ቫቲካነስ፣ አሌክሳንድሪያነስ እንዲሁም ሌሎችም ጥንታውያን የመጽሐፍ ቅዱስ እደክታባት ይህንን የሥላሴን የጥምቀት ፎርሙላ የያዙ ናቸው።
Hammasini ko'rsatish...
👍 6
የፕሮቴስታንት አምስቱን ሶላ እናውቃቸዋለን ያው አምስቱንም ሶላ እንቀበላለን ፣ ዳኛችንም ቃሉ ነው ተብሎ ግን የተለያየ ትምህርት በመዳን ላይ ቢኖርም ማለት ነው ። ለማንኛውም የክርስትናው የመዳን ትምህርት እንደዚ ነው። ድነናል ፣ እየዳንን ነው ፣ እንድናለን መዳን የቅጽበት ጉዳይ ሳይሆን ሂደታዊ ነው። መዳን ማለት የእግዚአብሔርን መንግስት መውረስ ማለት ነው። 1.ድነናል:- ስንል ያለ እኛ ሥራ እግዚአብሔር ራሱ ከራሱ ጋር አስታረቀን እያልን ነው። እንዴት አስታረቀን ሲባል ከሶስቱ አካል አንዱ አካል ወልድ የዘመኑ ፍጻሜ ሲደርስ ከድንግል ማርያም ተወልዶ ደሙን በመስቀል ላይ አፍሶ አድኖናል(ገላ 4:4 ፣ ዮሐ 3:16 ) ይሄም የቸርነቱ ስጦታ (በጸጋው) ነው ያዳነን ይሄንን በጸጋ የሰጠንን መዳንም የምንቀበለው በእምነት ነው ከዛም በመጠመቅ ነው። (ማር 16:16 ፣ ማቴ 28:19፣ ሮሜ 6)  ለዛ ነው በተደጋጋሚ ከዚ የኤፌሶን መልእክት ጋር የሚመሳሉ ቃላት በመጽሐፍት ላይ የተጻፉልን ኤፌሶን 2 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ⁴ ነገር ግን እግዚአብሔር በምሕረቱ ባለ ጠጋ ስለ ሆነ፥ ⁵ ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩ የተነሣ በበደላችን ሙታን እንኳ በሆንን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ሕይወት ሰጠን፥ በጸጋ ድናችኋልና፥ ⁶-⁷ በሚመጡ ዘመናትም በክርስቶስ ኢየሱስ ለእኛ ባለው ቸርነት ከሁሉ የሚበልጠውን የጸጋውን ባለ ጠግነት ያሳይ ዘንድ፥ ከእርሱ ጋር አስነሣን በክርስቶስ ኢየሱስም በሰማያዊ ስፍራ ከእርሱ ጋር አስቀመጠን። ⁸ ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤ ⁹ ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለም። ስለዚህ ይሄንን የዘለዓለም ህይወት ስጦታ እግዚአብሔር ሰጠን የእኛ ድርሻም በነጻ ፈቃዳችን አሜን ብለን ተቀብለን ማመን ነው። ለዛ ነው "ጸጋው በእምነት አድኗችኋልና" የሚለው። 2. እየዳንን ነው:- ይሄ ደግሞ በጸጋው የሰጠንን መዳን እስከ መጨረሻው አጽንተን ለመጠበቅ ተጋድሎ የምናደርግበት እና መዳናችንን የምንፈጽምበት ነው። ይሄም በእለት ተእለት ህይወታችን የምንኖረውን በሃጢአት መውደቅ እና በንስሐ መነሳት የያዘ እስከ ህይወታችን ፍጻሜ ድረስ ያለውን ጊዜ የሚመለከት ነው ። ይሄንንም ሐዋርያው “ስለዚህ፥ ወዳጆቼ ሆይ፥ ሁልጊዜ እንደ ታዘዛችሁ፥ በእናንተ ዘንድ በመኖሬ ብቻ ሳይሆን ይልቁን አሁን ስርቅ፥ በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ የራሳችሁን መዳን ፈጽሙ፤”     ፊልጵስዩስ 2፥12  እንዳለው የራሳችንን መዳን የምንፈጽምበት ነው። ይሄም ጌታ "እስከ መጨረሻ የጸና ይድናል"፣"በእኔ ያለው ፍሬ የማያፈራው ዛፍ ይቆረጣል" ያለውን እና ሌሎችንም የጌታ ትምህርቶች እና የሐዋርያትንም የቱንም ሳንመርጥ ስለምንቀበል እምነታችን በተግባር የሚገለጥበት ነው። ቅዱስ ጳውሎስም ከባርነት ነጻ ከወጣን በኋላ ድጋሚ እንዳንያዝ የነገረን ጽናት ስለሚያስፈልግ ነው።   “በነጻነት ልንኖር ክርስቶስ ነጻነት አወጣን፤ እንግዲህ ጸንታችሁ ቁሙ እንደ ገናም በባርነት ቀንበር አትያዙ።”     ገላትያ 5፥1 በክርስቶስ አምኖ ወደ ቤተክርስቲያን የተጨመረ እና ጌታ ራሱ የሆነለት ሰው ፍሬ ማፍራት እና መልካም ሥራ መስራት አለበት። “ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤ አሮጌው ነገር አልፎአል፤ እነሆ፥ ሁሉም አዲስ ሆኖአል።”    2ኛ ቆሮ 5፥17 ይሄ በክርስቶስ አዲስ ፍጥረት የሆነ አማኝ እንደ አዲስ የተፈጠረው መልካሙን ሥራ ለማድረግ እና የተቀደሰ ህይወት እንዲኖር ነው። “እኛ ፍጥረቱ ነንና፤ እንመላለስበት ዘንድ እግዚአብሔር አስቀድሞ ያዘጋጀውን መልካሙን ሥራ ለማድረግ በክርስቶስ ኢየሱስ ተፈጠርን።”     ኤፌሶን 2፥10 በጣም ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ላይ ምን አይነት ህይወት ልንኖር እንደሚገባ እና ምን ብናደርግ የእግዚአብሔርን መንግስት እንደማንወርስ በግልጽ ይናገራሉ ፣ማስጠንቀቂያም ይሰጣሉ። 3.እንድናለን:- ይሄ ማለት ጌታ ለፍርድ መጥቶ ለሁሉም የመጨረሻ ፍርድ ሰጥቶ መንግስቱን ያወርሰናል ብለን ተስፋ የምናደርግበት ነው። መዳናችን የሚፈጸመው የእግዚአብሔርን መንግስት ስንወርስ ስለሆነ ይሄ በመዳን መንገድ ውስጥ የመጨረሻው ነው። ጌታ ሲመጣም ፍርድ የሚሰጠው እያንዳንዳችን በሰራነው መልካም ሥራ እና ክፉ ሥራ ነው። ይሄንንም ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ላይ ጌታም ሲያስተምር ሐዋርያትም ሲያስተምሩ የምናገኘው እውነት ነው። በብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ላይ ራሱ በተደጋጋሚ የተነገረ ነው። እስኪ የተወሰኑትን እንይ  “እግዚአብሔር ሥራን ሁሉ የተሰወረውንም ነገር ሁሉ፥ መልካምም ቢሆን ክፉም ቢሆን፥ ወደ ፍርድ ያመጣዋልና።”    መክብብ 12፥14 “እኔም በልቤ፦ በዚያ ለነገር ሁሉና ለሥራ ሁሉ ጊዜ አለውና በጻድቅና በኃጢአተኛ ላይ እግዚአብሔር ይፈርዳል አልሁ።”    መክብብ 3፥17 “መልካም ቢሆን ወይም ክፉ እንዳደረገ፥ እያንዳንዱ በሥጋው የተሠራውን በብድራት ይቀበል ዘንድ ሁላችን በክርስቶስ በፍርድ ወንበር ፊት ልንገለጥ ይገባናልና።”     2ኛ ቆሮ 5፥10 “ባሪያ ቢሆን ወይም ጨዋ ሰው፥ እያንዳንዱ የሚያደርገውን መልካም ነገር ሁሉ ከጌታ በብድራት እንዲቀበለው ታውቃላችሁና።”    ኤፌሶን 6፥8 “የሰው ልጅ ከመላእክቱ ጋር በአባቱ ክብር ይመጣ ዘንድ አለውና፤ ያን ጊዜም ለሁሉ እንደ ሥራው ያስረክበዋል።”    ማቴዎስ 16፥27 ቆላስይስ 3 ²⁴ ከጌታ የርስትን ብድራት እንድትቀበሉ ታውቃላችሁና፤ የምታገለግሉት ጌታ ክርስቶስ ነውና። ²⁵ የሚበድልም የበደለውን በብድራት ይቀበላል፥ ለሰው ፊትም አድልዎ የለም። 1ኛ ጴጥሮስ 1 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹⁵-¹⁶ ዳሩ ግን፦ እኔ ቅዱስ ነኝና ቅዱሳን ሁኑ ተብሎ ስለ ተጻፈ የጠራችሁ ቅዱስ እንደ ሆነ እናንተ ደግሞ በኑሮአችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ። ¹⁷ ለሰው ፊትም ሳያደላ በእያንዳንዱ ላይ እንደ ሥራው የሚፈርደውን አባት ብላችሁ ብትጠሩ በእንግድነታችሁ ዘመን በፍርሃት ኑሩ። “አንተም በወንድምህ ላይ ስለ ምን ትፈርዳለህ? ወይስ አንተ ደግሞ ወንድምህን ስለ ምን ትንቃለህ? ሁላችን በክርስቶስ ፍርድ ወንበር ፊት እንቆማለንና።”     ሮሜ 14፥10 ራእይ 22 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹¹ ዓመፀኛው ወደ ፊት ያምፅ፥ ርኵሱም ወደ ፊት ይርከስ፥ ጻድቁም ወደ ፊት ጽድቅ ያድርግ፥ ቅዱሱም ወደፊት ይቀደስ አለ። ¹² እነሆ፥ በቶሎ እመጣለሁ፥ ለእያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን እከፍል ዘንድ ዋጋዬ ከእኔ ጋር አለ። ዕብራውያን 10 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ²⁶ የእውነትን እውቀት ከተቀበልን በኋላ ወደን ኃጢአት ብናደርግ ከእንግዲህ ወዲህ ስለ ኃጢአት መሥዋዕት አይቀርልንምና፥ ²⁷ የሚያስፈራ ግን የፍርድ መጠበቅ ተቃዋሚዎችንም ሊበላ ያለው የእሳት ብርታት  አለ።  ድነናል ፣ እየዳንን ነው ፣እንድናለን 🙏🙏 ለመዳን የሚያስፈልጉን እነዚህ ናቸው። 1.በጸጋ የተሰጠንን መዳን በእምነት መቀበል 2.ምሥጢራትን  መፈጸም (ጥምቀት+ሜሮን+ቁርባን) 3.መዳናችንን መፈጸም(ተጋድሎ) 4.እስከ መጨረሻ መጽናት(በጸጋ የተቀበልነውን መጠበቅ) 5.ተግባራዊ ክርስትናን እየኖርን ፍሬ ለማፍራት የቻልነውን ሁሉ ማድረግ እና በንስሐ ህይወት መመላለስ ኦርቶዶክሳዊው የመዳን ትምህርት "እግዚአብሔርን ወደመምሰል ማደግ" (Theosis) ነው። ፍቅረ ማርያም
Hammasini ko'rsatish...
🥰 5👍 4🙏 1
‹‹የመዳንን መንገድ የሚነግሯቹ›› ሐዋ 16፡17 ከሁለት ዓመት በፊት ለመናፍቃን የሰጠሁት መልስ ነው!! አሁን አሁን የመናፍቃን እና የተሐድሶ አራማጆች በቤተክርስቲያን ላይ ያላቸውን ጭፍን ዲያብሎሳዊ ጥላቻ ሳስበው ይደንቀኛል፡፡ለምን ይሆን ቤተክርስቲያንን ባገኙት መድረክ እና ቦታ የሚያጣጥሏት የሚል ጥያቄ ውስጤ ይፈጥርብኛል ይህ ሁሉ ሆኖ የጌታን ቃልኪዳን ሳስታውስ እፅናናለው ‹‹የገሀነብ ደጆች አይችሏትም›› ማቴ 16፡18 የጌታ ቃል እንዴት ያፅናናል እንዴትስ ሀይል እና ብርታትን ይሰጣል ወልድ ዋሕድ/የእግዚአብሔር አንድያ ልጅ/ ብላ በክርስቶስ ዐለትነት ላይ የተመሰረተችው ቤተክርስቲያን ዲያብሎስ እና ግብረ አበሮቹ ስም የማጥፋት እና የማፍረስ ዘመቻ ቢከፍቱባትም አትጠፋም ማንም ሊያጠፋት እና ከዐለቱ ክርስቶስ አላቆ ሊያሸንፋት የሚችል ኃይል የለም ይኽንን እንድታውቁ እና እንድትገነዘቡ እፈልጋለው፡፡ይኽ ሁሉ መከራ እና ፈተና እንዲሁም ዘለፋ በቤተክርስቲያኒቱ ላይ እየደረሰ ያለው ምክንያቱ በክርስቶስ ደም ተመስርታለችና በዓለም ሳላቹ መከራ አለባቹ የሚለው የአምላካችን የመስቀል ጉዞ ተከታይ ናትና ከመከራ ተለይታ የማትታይ የመስቀሉ ተከታይ የመከራው ተሳታፊ ወርቅ ወርቅነቱ እንዲታወቅ በእሳት እንደሚፈተን ቤተክርስቲያንም የክርስቶስ መሆኗ የሚታወቀው የክርስቶስን አብነት ተከትላ በመከራ ስታልፍ ነው፡፡እንደ መግቢያ ይህንን ካልኩኝ የዚህን ፅሁፍ መነሻ የሆነኝን ነገር ላንሳ በዚህ በማህበራዊ ድኅረገፅ በፌስ ቡክ ስማቸው ‹‹ሔቨን ናሆም ፤አዲስ አለም ብሩክ እና ሌሎች የፕሮቴስታንት ሰዎች››የእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም የልደት መታሰቢያ በዐልን ተንተርሶ በቤተክርስቲያን ላይ ከአባታቸው ከዲያብሎስ የተማሩትን የሐሰት ክስ ሲያቀርቡ በመመልከቴ ነው መጋደላችን ከሥጋና ከደም ጋር ሳይሆን ከእነርሱ ጋር ካለው የዲያብሎስ የሐሰት መንፈስ ጋር ቢሆንም እውነት ከሆነው ከኢየሱስ በተማርነውን እውነት ለእውነት ፈላጊ ያለሐሰት እናቀርባለን፡፡ከላይ በስም ያነሳዋቸውም ሆኑ ስማቸውን ያልገለፅኳቸው የፕሮቴስታንት አማኞች ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የእመቤታችንን የልደት በዐል መታሰቢያ አስመልክታ ጥቁር በግ ለአጋንንት እንደምትሰዋ በዚህም ሴጣንን እንደምታመልክ እንዲሁም ፈንዲሻ የተወቀጠ ኑግ እና አረቄ እየረጫጨች ባዕድ አምልኮ እንደምትፈፅም አድርገው በፅሁፎቻቸው አቅርበዋል እንደውም ልደቷ መከበር እንደሌለበትም አክለዋል፡፡ ለመሆኑ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያናችን መዋእዕት ሆኖ ደሙን አፍሶ የዋጃትን ጌታ ሳታቅ ቀርታ ነው ለአጋንንት መዋእዕት የምትሰዋው ? ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን መፈተት ትታ?በጭራሽ ቤተክርስቲያናችን ለአጋንንት ጥቁር በግ ፈንዲሻ አረቄን ጨምሮ ሰውታ አታውቅም ወደፊትም አትሰዋም ሰዉም ብላ አታስተምርም ፡፡እርግጥ አንድ የማይካደው ሐቅ በስመ ኦርቶዶክስ የሚመላለሱ ግማሽ አካላቸው ጠንቋይ መተተኛ ጋር ግማሹን ቤተክርስቲያን ያደረጉ ከእግዚአብሔር ቃል ይልቅ አጋንንትን የሚያደምጡ እምነታቸውን ከባዕድ አምልኮ ጋር ያዳቀሉ በእግዚአብሔር ላይ ሙሉዕ እምነት የሌላቸው የአጋንንት ባሮች የሆኑ ሰዎች የቤተክርስቲያን በዐላትን አስታከው የእናት የአባታቸውን የዲብሎስ መንፈስ የሚቀሰቅሱ ለመንፈሱም ጥቁር በግ የሚሰዉ ፈንዲሻ እና አረቄን የሚረጫጩ ከኦሪት መዋእዕት ያልተላቀቁ ሰዎች መኖራቸው እሙን ነው፡፡እነዚህ ሰዎች ይህንን ያደርጋሉ ማለት ቤተክርስቲያን ፈቅዳላቸው ሰዉ ብላ አዛቸው ነው ማለት ግን አይደለም ይህንን ዲቃላ እምነታቸውን ከሲወርድ ሲዋረድ ከእናት አባት የዛር መንፈስ የወረሱት እንደሆነ እንጂ ቤተክርስቲናችን ይህንን አጥብቃ ትቃወማለች በስብከትም በቅዳሴም ይህንን የሚያደርጉትን ሰዎች ስትገስጽ ከዚህ ድርጊታቸው እንዲታረሙ እግዚአብሔርን ወይም በአልን እንዲመርጡ ስታስተምር ነው የምትውለው፡፡ለምን ከንፅህይት ድንግል እመቤታችን ልደት ጋር አያይዘው ይህንን ሰይጣናዊ ድርጊት ያደርጋሉ ከተባለ የአጋንንት ፀባይ መመሳሰል ተመሳስሎም ህዝቡን ከእግዚአብሔር መንግስት መለየት አላማው እንደሆነ ሊረዳ ያስፈልገዋል፡፡ከላይ ለፅሁፌ መነሻ የሆነኝን ቃል እዚህ ላይ ላነሳው ግድ ይለኛል ቅዱስ ጳውሎስ እና የሐዋርያት ስራ ፀሐፊው ቅዱስ ሉቃስ ምናልባትም ሌሎቹም ደቀመዛሙርት ጨምሮ ወደፀሎት ስፍራ በሚጓዙበት ጊዜ ለጌቶቿ እየጠነቆለች ብዙ ትርፍ ታመጣ የነበረች የአጋንንት መንፈስ ያደረባት ሴት እነ ቅዱስ ጳውሎስን ለህዝቡ እያመላከተች ‹‹የመዳንን መንገድ የሚነግሯቹ እነዚህ ሰዎች የልኡል አምላክ ባሪያዎች ናቸው ››እያለች አብዝታ እየደጋገመች በተለያየ ጊዜ ትጮህ ነበር ይህንንም ብዙ ቀን ታደርግ ነበር ተብሎ ተፅፏል ልብ በሉ ሐዋ16፡16-20‹‹የመዳንን መንገድ የሚነግሯቹ የልኡል ባሪያዎች ስላለች ይህች ሴት ከቤተክርስቲያን እና ከእግዚአብሔር ተልካ ነው ጥንቆላን የምትጠነቁለው ማለት እንደማይቻል ሁሉ እነዚህም ሰዎች በቤተክርስቲያን ሃይማኖታዊ በዐላት ምክንያት ለሚሰሩት የባዕድ አምልኮ ቤተክርስቲያን አዛቸው ነው ማለት አይቻልም ይህንን ባዕድ አምልኮ ቤተክርስቲያን አጥብቃ ትቃወማለች ፡፡በብሉይ ኪዳንም በተለያዩ ታሪኮች እንደተገለፀው እስራኤላውን ከእግዚአብሔር ጋር ደርበው ጣኦትን ያመልኩ እንደነበር እግዚአብሔር ይህንን አጥብቆ እንደተቃወማቸው ማምለክ ያለባቸው መዋእዕትም መሰዋት ያለባቸው ለእርሱ እንደሆነ በነብያቱ እና በካህናቱ አማካኝነት አሳስቧቸዋል እግዚአብሔርን ያመልኩ የነበሩ ህዝቦች ለጣት መሥዋዕት በመሰዋታቸው እርሱንም በማምለካቸው ተጠያቂው እግዚአብሔር የሰጣቸው የኦሪት እምነት እንዳልሆነ ሁሉ የቤተክርስቲያኒቱን በዓላት አስታከው ሴጣናዊ ምኞታቸውን የሚፈፅሙ አጋንንትን የሚያመልኩ ጥቁር በግ አርደው ደሙን የሚረጫጩ ነጭ አረቄን ለጠቋር ወሰን ገፊ አውልያ መተተኛ ……….እያሉ ለአጋንንት መንፈስ ግብር የሚገብሩ ሰዎች የአምልኮ ችግር እንጂ የቤተክርስቲያኒቱ ትዕዛዝ ወይም ትምህርት እንዳልሆነ አንባቢው ሊያስተውል ያስፈልጋል፡፡የቆሮንቶስ ምዕመናንም በዝሙት በመውደቃቸው ምክንያት ቅዱስ ጳውሎስ በመልዕክቱ እንደገሰፃቸው በ1ኛ ቆሮንቶስ መልዕክቱ እናነባለን እነዚህ ክርስቲያኖች ይህንን ድርጊት በመፈፀማቸው ሰዎቹ የራሳቸው ችግር እንጂ የክርስትና እምነት ችግር እንዳልሆነ ሁሉ በቤተክርስቲያን በዓላት ሰበብ የገዛ ምኞታቸውን የሚፈጽሙትም ሰዎች ችግር የራሳቸው እንጂ የቤተክርስቲያናችን እንዳልሆነ ልትገነዘቡ እወዳለው ፡፡ ስለዚህም መናፍቃን ሆይ ቤተክርስቲያንን በሐሰት ክስ እየወነጀላቹ አማኝ ያበዛቹ እየመሰላቹ በኃጢአት ላይ ኃጢአት ባትጨምሩ መልካም ነው ቤተክርስቲያንን የሚጠብቅ ልዑል አምላክ እግዚአብሔር ነው የተመሰረተችውም በደሙ እንጂ በሰው ሀሳብ በዓለም ፍልስፍና እና ቋንቋ አይደለም ስለዚህም እንኳን በሐሰት እየከሰሳችሁ እውነት እንኳን ቢኖራቹ ቤተክርስቲያንን ልታፈርሱ አትችሉም አምላካችን እግዚአብሔር በባዕድ እና በአጋንንት አምልኮ ውስጥ ያሉትን ወገኖቻችንን በምሕረት ያስብልን ይህንን ክፉ መንፈስ እና አሰራር በልጁ በኢየሱስ ስም ይገስጽልን በመናፍቃን ላይ አድሮ በሐሰት ክስ ቤተክርስቲያንን የሚከሰውን እርኩስ መንፈስ ያስታግስልን የእመቤታችን በረከቷ እና ምልጃዋ ይደርብን አሜን ፡፡ ዲያቆን ሸዋፈራው አለነ ይቆየን
Hammasini ko'rsatish...
👍 6
‹‹የእግዚአብሔር የሰውን ዘር የማዳኑ ዘለዓለማዊ ዕቅድ የኾነው ንጉሱ መሲሑ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ይቤዠን ያድነን ይታደገን ነጻ ያወጣን ሰው ይሆን ዘንድ ንግስቷ እመቤታችን ድንግል ማርያም ተወለደች ፤ እርሷ ተወልዳ አዳኙን ጌታ ወለደችው ስለዚህም ድንግል ኾይ ልደትሽ ልደታችን ነው እንላለን ቅድስት ኾይ ለምኝልን›› https://t.me/orthodoxawitewahdo ቻናሉን ተቀላቅለው ኦርቶዶክሳዊ ወንጌል ይማሩ!
Hammasini ko'rsatish...
👍 3🙏 2
በጣም መደመጥ ያለበት ቪዲኦ ኢሆ ለኦርቶዶክስም ለፕሮቴስታንትም ይሁንልኝ አዳምጡት ??😳 * ፕሮቴስታንቲዝም ክርስትና እንዲወድቅ ብዙ ሚና ተጫውቶል * የ ቤ ክ ራስ የሆነውን ክርስቶስን ሳይሆን የፖስተሮቹ የግል ምልከታ የግል ፍቺ በማስቀመጥ የግል አመለካከታቸውን በመጫን ብዙ ነገር እንዳበላሹ ይታወቃል ግን መምህራችን ዲ ን ያረጋል ያስረዳውን አዳምጡት ማንም እንዳያሳልፈው ተመልከቱት 😢❤️❤️❤️❤️
Hammasini ko'rsatish...
11🆒 1
‹‹ልባችን ይቃጠልብን አልነበረምን? ሉቃ 24፡32 ጊዜው የዛሬ ሁለት ሺህ ዓመት ገደማ ነበር፡፡ መንገዶች ሁሉ እንደተከበበ ከተማ ጭር ብለዋል፤አልፎ አልፎ ሰዎች በመንገድ በሹክሹክታ እየተነጋገሩ በፍርሃት ተውጠው ይጓዛሉ፡፡በጊዜው ወሬው ሁሉ በአይሁድ እና በሮማናውያን በግፍ ያላንዳች ወንጀል እና ኃጢአት ተገርፎ ስለተሰቀለው መሲሕ ኢየሱስ ነበር፡፡ህዝቡ ሁሉ በፍርሃት ተውጦ በጭንቀት ተስፋ በመቁረጥ ውስጥ ሆኖ ይቅበዘበዝ ነበር፡፡ያ ሶስት ዓመት ከሶስት ወር ዕውራናቸውን ያበራ ፤ ሙታናቸውን ያስነሳ፤ ለምጻቸውን ያነጻ፤ ጎባጣውን ያቀና ፤ሽባውን የተረተረ፤እንጀራ እና ዓሳን አበርክቶ ያበላ፤ ከአጋንንት እስራት የፈታቸው፤ ተስፋ በቆረጡ ጊዜ ተስፋቸውን የቀጠለላቸው፤በሞት ፍርሃት ውስጥ ሳሉ ተገልጦ ከዚህ ፍርሃት ያላቀቃቸው፤ ጠላቶቹ ሆነው ሳለ የወደዳቸው በፍቅር የቀረባቸው ፤ከአባትም በላይ አባት ሆኖ በዕቅፉ የሰበሰባቸውን ጌታ ሰቅለው በመቃብር ጥለው ብቻቸውን በፍርሃት ውስጥ ነበሩ፡፡ በዚህ ጊዜ ሁለት ደቀመዛሙርት ሉቃስ እና ቀለዮጳ ጭር ባለው ከኢየሩሳሌም ስድሳ ምዕራፍ ያህል ወደሚርቅ ኤማሁስ መንገድ ላይ መሬት ላይ ተበትኖ የደረቀውን የዛፍ ቅጠሎች እየረገጡ ቅጠሎቹ ሲረገጡ ድምጽ እያሰሙ በግፍ ስለሞተው ስለ መሲሑ ኢየሱስ እያወሩ ይቋዙ ነበር፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመካከላቸው ተገኝቶ የሚነጋገሩትን እየሰማ አብሯቸው ሲጓዝ እንኳ ሶስት ዓመት ከሶስት ወር አብሯቸው የነበረውን መልኩን ማወቅ ተስኗቸው እርሱ መሆኑን መረዳት ሳይችሉ ቀሩ፡፡ዓለም እንደዚህ ናት ትላንት ያበላናቸው ያጠጣናቸው፤ የወደድናቸው ያፈቀርናቸው፤ራሳችንን የሰጠንላቸው ሰዎች ስናጣ ፤ስንገረጣ እናደርግላቸው የነበረውን ነገር ማድረግ ሳንችል ስንቀር ይረሱናል ውለታችንን ይዘነጉታል፡፡ እነዚህም ደቀመዛሙርት ትላንት ያደረገላቸውን ረስተው ውብ መልኩን ዘንግተው እርስ በርሳቸው እየተነጋገሩ እንዳያውቁት ዓይናቸው ተይዞ ስለነበር መንገዳቸውን ቀጠሉ፡፡የአይን መያዝ መጥሮ ነገር ነው ብዙዎቻችን መንፈሳዊ ነገርን እንዳናይ ለመንፈሳዊ ነገር እንዳናደላ ዓይኖቻችን ተይዘው በመከራ እና በስቃይ ውስጥ እንገኛለን፡፡አይን ከተያዘ ምንም ነገር ማየት አይቻለም በጠራራ ጸሐይ በብርሃን ውስጥ እንኳ ብንሆን አይነ ልቡናችን ከተያዘ መመልከት ይሳነናል፡፡ ደቀመዛሙርቱ ሉቃስ እና ቀለዩጳም የገጠማቸው ነገር ይኸው ነው ያበላቸውን ያጠጣቸውን ጌታ አይናቸው ስለተያዘ ብቻ ማየት አልቻሉም ፡፡ የእምነት ልባቸው ስላልተከፈተ፤ ተጠራጣሪዎች ስለነበሩ፤ከሞቱ አስቀድሞ የነገራቸውን ትንሳኤውን መቀበል አቅቷቸው በሶስተኛው ቀን እነሳለው ብሎን አልነበረምን ታድያ ምነው ሳይነሳ ቀረ ? በሚል መጠራጠር ውስጥ ስለነበሩ ዓይናቸው ተያዘ፡፡ብዙዎቻችን እንዲህ ነን የለመንነው ሳይሳካ ሲቀር የጠየቅነው ሳይመለስልን ከቀረ ጌታ እውነት አለግን እያልን እንጠራጠራለን ምን አልባትም እግዚአብሔር የለመንነው ነገር የማይጠቅመን ወይም በግሞ ሊጎዳን የሚችል ሆኖ ሳይሰጠን ቀርቶ ቢሆንስ ብለን ናስብም ፤ አልያም እግዚአብሔር የራሱ ጊዜ አለው በራሱ ጊዜ እርሱ የወደደውን በወደደው ጊዜ ያደርግልኛል ብለን ልባችንን በእርሱ ላይ አሳርፈን በእምነት መጠባበቅ ያቅተናል፡፡ የነዚህም ደቀመዛሙርት ነገር እንዲሁ ነበር ጌታ በመካከላቸው ተገልጦ ስለምን እንደሚወያዩ ሲጠይቃቸው ‹‹በእግዚአብሔርና በሕዝቡ ሁሉ ፊት በሥራና በቃል ብርቱ ነቢይ ስለ ነበረው ስለ ናዝሬቱ ስለ ኢየሱስ፤እርሱንም የካህናት አለቆችና መኳንንቶቻችን ለሞት ፍርድ እንዴት አሳልፈው እንደ ሰጡትና እንደ ሰቀሉት ነው።እኛ ግን እስራኤልን እንዲቤዥ ያለው እርሱ እንደ ሆነ ተስፋ አድርገን ነበር፤ ደግሞም ከዚህ ሁሉ ጋር ይህ ከሆነ ዛሬ ሦስተኛው ቀን ነው።ደግሞም ከእኛ ውስጥ ማልደው ከመቃብሩ ዘንድ የነበሩት አንዳንድ ሴቶች አስገረሙን፤ሥጋውንም ባጡ ጊዜ። ሕያው ነው የሚሉ የመላእክትን ራእይ ደግሞ አየን ሲሉ መጥተው ነበር።ከእኛም ጋር ከነበሩት ወደ መቃብር ሄደው ሴቶች እንደ ተናገሩት ሆኖ አገኙት፥ እርሱን ግን አላዩትም።›› ብለው ነበር መለሱለት ጌታም ‹‹እናንተ የማታስተውሉ፥ ነቢያትም የተናገሩትን ሁሉ ልባችሁ ከማመን የዘገየ፤ክርስቶስ ይህን መከራ ይቀበል ዘንድና ወደ ክብሩ ይገባ ዘንድ ይገባው የለምን? አላቸው።ከሙሴና ከነቢያት ሁሉ ጀምሮ ስለ እርሱ በመጻሕፍት ሁሉ የተጻፈውን ተረጐመላቸው።›› ከጥንት ጀምሮ ስለርሱ የተነገረውን ተርጉሞ አብራርቶ አለማመናቸውን አራቀላቸው ፡፡ ሉቃስ እና ቀለዮጳ ወደ ማደሪያ ስፍራቸው በደረሱ ጊዜ ቀኑ መሽቶ ስለነበር ያላወቁትን ጌታ አብረኸን እደር ሲሉት እሺ ብሎ ገብቶ በማዕድ ከነሱ ጋር ተቀመጠ እንጀራውን ባርኮ ቆርሶ ሲሰጣቸው ዓይናቸው ተከፍቶ አዩት እርሱ በአይሁድ እጅ በግፍ ተገርፎ ተሰቀለው ፤ በፈቃዱ ሞተው ወደ መቃብር የወረደው የትንሳኤው ጌታ በኩረ ትንሳኤ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መሆኑን አወቁ ፡፡እግዚአብሔርን የምናውቀው ልባችንን ከፍተን በእምነት ስንቀበለው ወደ ልባችን ስናስገባው የርሱ መሆን ስንችል ነው ፡፡በየዋሕነት በቅን ልቡና በመንፈስ ቅዱስ ሙላት በቃሉ መታደስ ስንቀርበው ራሱን ገልጥልናል ያነጻናል ይቀድሰናል ከክፉ ነገር ሁሉ ሰውረናል ፤ ጋሻ መከታ ጥላ ከለላ ይሆነናል፡፡ደቀመዛሙትቱ ጌታን ባወቁት ጊዜ ተሰወረባቸው ፡፡ በዚህ ጊዜ ነበር ‹‹በመንገድ ሲናገረን መጻሕፍትንም ሲከፍትልን ልባችን ይቃጠልብን አልነበረምን?›› እርስ በርሳቸው የተባባሉት ፡፡ ልብ በሉ ልባቸው ይቃጠልባቸው ነበረው ከአንደበቱ ከሚወጣው ቃል የተነሳ ነው ፤ የእግዚአብሔር ቃል ልባችን እስከሚቃጠልብን ድረስ በሐሴት ይሞላናል ፤ ምድራዊውን ነገር አስትቶ ሰማያዊውን ነገር እንድናስብ ያደርገናል ፤ ሐላፊ ጠፊውን ትተን የማያልፈውን መንግስቱን እንድንሻ ያደርገናል ለዚህ ነው ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹የእግዚአብሔር ቃል ሕያው ነውና፥ የሚሠራም፥ ሁለትም አፍ ካለው ሰይፍ ሁሉ ይልቅ የተሳለ ነው፥ ነፍስንና መንፈስንም ጅማትንና ቅልጥምንም እስኪለይ ድረስ ይወጋል፥ የልብንም ስሜትና አሳብ ይመረምራል››ዕብ 4፡12 ሲል ተናገረው ማነው በእግዚአብሔር ቃል ልቡ ያላረፈው? ማነው በእግዚአብሔር ቃል ያላረፈው?ማነው በእግዚአብሔር ቃል ያልተጽናናው?ማነው በእግዚአብሔር ቃል ልቡ ያልተቃጠለበት?የእግዚአብሔር ቃል ዘማውን ከዝሙቱ ይመልሳል፤ሙታንን ያስነሳል፤ያዘለውን ያጽናናን፤ልብን ያሳርፋል፤ ሰላም እረፍት እፎይታ እና መጽናናትን ይሰጣል፡፡ቅዱስ ቃሉ የተጻፈበት አላማ እኛ እንድናምንበት ፤ እንድንጽናናበት እንድንመለስበት ፤ ልባችን በፍቅሩ እንዲቃጠልብን ነው፤ቃሉን መሸሽ ከቃሉ መራቅ ራስን ያለ መልህቅ በመርከብ ላይ ማግኘት ነው የሚሆነው፡፡ ስለዚህ በቃሉ ልባችን ይቃጠልብን ፤ ለቃሉ እንገዛ ፤ቃሉን ዘወትር ቸል አንበል፡፡ በቃሉ እንድንገዛ ልባችን እንዲቃጠልብን እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ይርዳን አሜን! ዲያቆን ሸዋፈራው አለነ የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ የነገረ መለኮት ምሩቅ! ይቆየን
Hammasini ko'rsatish...
👍 8 2🔥 1🙏 1
የእምነት ስራ" "ሲያያት በሕይወት ይኖራል" ዘኁ21:8 ክፍል ሁለት ሲያያት በሕይወት ይኖራል አይቶ ሕይወት ማግኘት መታደል ነው! አለም ክፉ ናት በወደደን ቅዱስ ስጋውን ክቡር ደሙን በሰጠን ላይ እንድናጎራጉር ታደርጋለች አላማዋም በመርዛማ እባቦች እንድንነደፍና እንድንሞት ነው እርሱ ግን ለእኛ አይታችሁ በሕይወት ኑሩ አለ! ማየት ሁሉ ማየት አይደለም በእምነት ማየት ይለያል ። ብዙዎች በእምነት አይን ተመልክተው ድነዋል ኃጢአት የእምነትን አይን ይይዛል "ኃጢአቶቼ ያዙኝ ማየትም ተሳነኝ" መዝ39:12 በእምነት ማየት እና መዳን ከእምነት ስራዎች ውስጥ አንዱ ነው። አይተው በሕይወት የኖሩት በሙሴ በትር ላይ የተሰቀለውን የነሃስ የእባብ ነው ዘኁ21:8-9 ፨ የነሃስ እባብን አይቶ መዳን እንዴት ይችላል? ፨ እግዚአብሔርስ እንዲሁ ማዳን ሲቻለው ይህን የናስ እባብ እንዲሰራ ለምን አዘዘ? እነዚህ ጥያቄዎች በእምነት ስራ ውስጥ መልስ የሚያገኙ ናቸው "የነሃሱ እባብ ምሳሌነት" የእዚአብሔር በምክንያትም ያለምክንያትም ያድናል። የእግዚአብሔርን ማዳን በእምነት የእግዚአብሔር በሆኑ ነገሮች ውስጥ ሁሉ እናገኛለን ።የእርሱ በሆኑት ሁሉ ማዳኑ መገለጹ የእግዚአብሔር ማዳን ስፉህ ምሉዕ መሆኑን ያሳያል እንጂ አይሸፍነውም። በእምነት ስራ ስንመረምረው መርዝ የሌለው የነሃሱ እባብ የጌታ ስነስቅለት ምሳሌ ነው "ሙሴ .. እባብን እንደሰቀለ .. እንዲሁ የሚያምን ..ሕይወት እንዲኖረው የሰው ልጅ ይሰቀል ዘንድ ይገባዋል" ዮሐ3:15 ስለዚህም የዳኑት በስነ ስቅለቱ ምሳሌነት ነው ።ድንቅ ምስጢር ገና ሳይሰቀል በስቅለቱ ምሳሌነት ካዳነ ከስቅለቱም በኋላ በስቅለቱ ስዕል መስቀሉን አይተን እንድናለን ። ዲያቆን ሸዋፈራው አለነ ይቀጥላል
Hammasini ko'rsatish...
👍 4
የእምነት ስራ ክፍል አንድ የእምነት ስራ ማለት በእምነት ከእግዚአብሔር ኃይልን ማዳንን እና በረከትን የምንቀበልባቸው መንገዶች ናቸው። እግዚአብሔር የህሊና ዳኛ ነው ሰው በአፍአ ያለውን እያየ እንዲህ እንዲያ ነው እያለ ግምታዊ ሃሳቡን ይሰነዝራል። እግዚአብሔር ግን በሰው ልብ ምን እና ለምን እንደሚደረግ እንደፍጡር ግር አይለውም ስለዚህም ሰው በእምነት ለሚያደርጋቸው ነገሮች ኃይሉና ማዳኑን ሲገልጽ በረከቱን ሲያድል በብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች እናነባለን ። አስራ ሁለት አመት ደም ሲፈሳት የነበረችው ሴት ከጌታ መዳንን ኃይልን ለመቀበል የፈጸመችው የእምነት ስራ ነበር የእምነቷ ቃል እንዲህ ይላል "ልብሱን ብቻ ከዳሰስሁ እድናለሁ"ማር5:28 ግሩም የእምነት ቃል! አናግሬው አላለችም ዳሶኝም አላለችም የእምነት ሥራዋን የገለጠችው የልብሱን ጫፍ በመዳሰስ ብቻ ነበር። ለስም አጠራሩ አምልኮትና ስግደት የሚገባው ከህሊና አስቀድሞ የሚያውቅ የእምነትን ስራ የሚቀበል የኛ ጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ የአስራ ሁለት አመቱን እንቆቅልሽ በአይን ጥቅሻ ውስጥ ፈታው። *ለካ እርሱን በእምነት ለማናገር የልብሱም ጨርቅ ይበቃል ! *ለካ መዳንን ከእርሱ ለማግኘት የእርሱ የሆነውን ሁሉ በእምነት መንካት ይበቃል ! *ለካስ ከእርሱ በርዕቀትም ኃይል ይገኛል ! ♦️እውነት ነው ልብሱን ጨርቅ ዳስሼ ከዳንኩኝ እርሱ የምትሆን እናቱን ጠርቼ አልድንምን? ♦️እውነት ነው ለጊዜው የለበሰውን ደሙ ያልነጠበበትን ልብሱን ነክቼ ከዳንኩ የወርቅ ደሙ ዙፋን የሆነውን መስቀሉን ነክቼ እንዴት አልድንም? "ልጄ እምነትሽ አድኖሻል" ማር5:34 የሚያድነንን እምነታችን ነው አዎን የጌታ ፍጹም የሆነ ኃይሉ የእርሱ በሆኑት እንደሚገለጽ ብናምን ዳሰንም እንድናለን ይህም የእምነት ስራ ነው!! ዲያቆን ሸዋፈራው አለነ ይቀጥላል ይቆየን
Hammasini ko'rsatish...
👍 7 1🙏 1
MK TV || ልዩ የትንሣኤ መርሐ ግብር || በጌታ መቃብር ላይ የሚገለጠው ቅዱሱ እሳት
Hammasini ko'rsatish...
Hammasini ko'rsatish...
MK TV || ልዩ የትንሣኤ መርሐ ግብር || በጌታ መቃብር ላይ የሚገለጠው ቅዱሱ እሳት

Subscribe and share

https://www.youtube.com/user/EOTCMK?s......

https://www.youtube.com/user/EOTCMK?s......

#MKTV #MahibereKidusan #EOTCMK