cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ክርስትና

Ko'proq ko'rsatish
Mamlakat belgilanmaganTil belgilanmaganToif belgilanmagan
Reklama postlari
917
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kunlar
Ma'lumot yo'q30 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

የሐዋርያት መልስም "በእርሱ እንድንድን የሚገባን ሌላ ስም ከሰማይ በታች ለስው ልጅ አልተሰጠም።፣፣፣ የሚል ነበረ የሐዋ ስራ4:12።ይህን እውነት ሰምተው ወደ ተሻለ ኪዳን፣እንደ መመለስ ፣ጭራሽ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እንዳያስተምሩ እንዳይመሰክሩ አጥበቀው አዘዝዋቸው።ሓዋርያ ጴጥሮስ እና ዮሐንስ ግን ፣ ★"ያየነው የሰማነው እውነት ልንተወው አንችልም★ "በማለት መለሱ።! እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ሕይወትነው።ህይወትነቱ በዚህ ምድር የሚኖረንን ህይወት በመባረክ ብቻ የሚቀርየሚያልፍ አይደለም። እርሱ ህይወት ስለሆነ በእርሱ የሚያምኑ ቢሞቱእንኳን ህያዋን ናቸው። እርሱ ዘለዓለማዊ ሕይወት ነውና። በእርሱ የሚያምኑ አያፍሩም እንዲል መጽሐፍ በኢየሱስ ክርስቶስ ፍጽም እምነት ያላቸው ሁሉ ቢሞቱ እንኳን ህያዋናን ናቸው እርሱ ትንሳኤና ህይወት ነውና። ራሱ ኢየሱስ ከርስቶስ ሲናገር ዮሐ 11፡25 ኢየሱስም። ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ፤ የሚያምንብኝ ቢሞት እንኳ ሕያው ይሆናል፤ እንዳለ።የሚያምኑበት ይነሳሉ የዘለዓለም ህይወትንም ይወርሳሉ። መነሳትስ ሁሉም ይነሳል ነገር ግን በክርስቶስ የሚያምኑ ለህይወት ለሚሆነው ደስታና ሰላም ላለበት ትንሳኤ ይነሳሉ። ከእርኛቸው ከክርስቶስ ጋርም ይከበራሉ። ነጩንም ልብስ ከለበሱ ህይወታቸውንም ለበጉ አሳልፈው ከስጡ ጋር በአንድነት ይከብራሉ። ✔«★በዋእየ ፍቅርከ ከመ ሥርወ አእዋም የብሰ ውሳጤ ሕሊናየ ነደ ወልብየ ጤሰ★» በፍቅርህ ሙቀት የልቤ ኃጢአት ደረቀ ሕሊናየ ተቃጠለ ልቤም ጤሰ እያሉ አመስግነውታል ★መልከዓ ኢየሱስ★። ለአባቶቻችንን ያቃጠለው የክርስቶስ ኢየሱስ ፍቅር እኛንም ነክቶናል።ገናና ስሙም ለአለም እናውጃለን፣እንመሰክረሰለን።ዳሩ ግን ከአመንበት እውነት ወጥተን የዚህ አለም ፍልስፍና ላይ ትኩረት እንድንሰጥ የሚመክሩን ከአለም የሆኑ ስዎች፣ከመድኃኒታችን፣ከሕይወታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ እንድንለይ የሚዳክሩ ፣ስሙ እንዳንጠራ በስሙ እንዳናስተምር የሚያስጠነቅቁን የዘመናችን አይሁዳዊያን መልሳችን ከቅዱሳን አባቶች የተለየ አይደለም።ዳሩ ግን ★ሠናይ እገሪሆሙ ለእለ ይዜንው ሠናየ ዜና፡፡ መልካሙን የምሥራች የሚናገሩ እግሮቻቸው እንዴት ያማሩ ናቸው፡፡ ሮሜ 10:15★። ተብሎ ተፅፏልና ክርስቶስ በአባቱ ቀኝ ተቀምጦ አለምን በፍቅርና በፍትህ እየገዛ እያስተዳደረ እንዳለ ፃድቃንን በቀኙ፣ኃጥአን በግራው ለማድረግ ለፍርድ እንደሚመጣ ከኢየሩሳሌም እስከ ይሁደ፣ከሰማርያ እስከ አለም የመጨረሻ ደንበር የክርስቶስ ምስክር ነን።ከዚህ እውነት የሚለየን ሓይልም የለም።ሮሜ 8:38–39 ልክ እንድ አባቶቻችን ለእውነት ልንሞት ይገባል።የተሰጠን አላማ የእግዚአብሔር መንግስት ለማስፋፋት ነውና። ፡“የተጠራነው በስሙ ልናምን ብቻ ሳይሆን መከራንም ልቀበል ጭምር ነው”፡፡ፊሊ1፤29 ደቀ መዛሙርቱ « እኛስ ያየነውንና የሰማነውን ከመናገር ዝም ማለት አንችልም» / የሐዋ. ሥራ. 4፣2ዐ/ ስማችን እንዳይጠፋ፣እንዳይሰድቡን፣ በማለት ከአመንበት፣ ቤተ ክርስቲያን ከቆመችለት እውነት ወደ ኃላ ማለት አያስፈልግም።” ★አመ ትመጽእ ለኮንኖ ምስለ ደመ ገቦ አእጋር አማኅፀንኩ ነፍስየ ውስተ እዴከ ክቡር”★/መጽሐፈ ሰዓታት ገጽ ፪፻፵፩/ በዳግመኛ ምጽአትህ ጎንህ በጦር እንደተወጋ እጆችህና እግሮችህም እንደተቸነከሩ ሆነህ ለፍርድ ስትመጣ ነፍሴ በከበረ የእጅህ መዳፍ እረፍት እንድታገኝ አደራ እልሃለሁ/እማፀንሃለሁ/ማቴ 25:31/።ስለ ግርፋትህ፣ሞትህ፣መራብ፣መጠማትህ ሁሉ ብለህ ይቅር እንድትለኝ እለምንሃለሁ እንዲል። ለአዳነን ላፈቀረን፣ከኃጢአታችን በደሙ ላነፃን ለመንግስቱ ወንጌል ካህናት እንድንሆን ላደረገ ኢየሱስ ክርስቶስ ክብርና ስልጣን ለዘለአለም ይሁን አሜን። “እመሂ ስሕትኩ አንትሙ እለ በመንፈስ አርትዕዎ” “የተሳሳትኩትም ቢኖር እናንተ በመንፈስ ያላችሁ አቃኑት”
Hammasini ko'rsatish...
★በሥጋ ያዩት ሰቅለውታል በመንፈስ ያዩት ሰግደውለታል።★ ※ቅዱስ አግናጥዮስ ዘአንፆኪያ ምጥው ለአንበሳ በሮማዊያን ተይዞ እዲገደል ይዘውት እየሄዱ ሳለ ሁል ግዜ የኢየሱስ ክርስቶስ ስም ከአንደበቱ አይለይም ነበር።የሮም ወታደሮችም"ይህ ስም አታሳርፈውም?አይበቃህም?ብለው ጠየቁት።ቅዱስ አግናጥዮም "እንዴት አድርጌ የኢየሱስ ስም ከአንደበቴ ልለይው እችላለሁ በልቤ እኮ ነው የታተመው:የነገሰው አላቸው።በሮም እንደደረሰም በአናብስት ጉድጓድ አስገቡት።አናብስቱም ስጋ እና አጥንቱ ሳይቀር በሉት ነገር በመለኮታዊ ተአምር ልቡ ለብቻው ተረፈች። "የኢየሱስ ስም በልቤ ነው ያለው:የሰፈረው ብሎ የነገራቸው ወታደሮች ልቡ ለብቻዋ ሲመለከቱ"ኑ እንሂድና ኢየሱስ የሚል ስም በልቡ ላይ እንዳለች እንይ?ተባብለው ልቡን በቢላ ለሁለት ሲከፍሉት ""★ኢየሱስ★""የሚል ስም በወርቅ የተሰራ በልቡ ተገኘ ።ስለዚህም ነው ቅዱስ አግናጥዮስ/theophorus/ ተብሎ የሚጠራው።ክብር ለስመ አጠራሩ ይሁን ለዘለዓለም። ጠላት አብዝቶ የሚጠላው ወዳጅም አብዝቶ የሚወደው ቢኖር ኢየሱስን ነው። ኢየሱስ ማለት መድኃኒት፣ፈውስ ማለት ነው።ይህን ምስጢር ያልገባቸው አይሁድና አይሁዳዊያን ግን ለዚህ ስም በመቃወም ክርስቶስ እንዲሰቀል፣እንዲገደል ነገር ግን ለብዙ ዘመናት ሀብት እና ንብረታቸው እየዘረፈ ማስገባት ማስወጣት የከለከላቸውን ሽፍታ የነበረው በርባን እንዲፈታ ለምነዋል።ዳሩ ግን ያሳዝናል። ✔ ዘመናትን ለሁለት የከፈለ፣ለዓለም ሕዝብ ሁሉ ከሞት ወደ ሕይወት፣ከጨለማ ወደ ብርሀን፣ከሲኦል ወደ ገነት ያሸጋገረ፣ለታመሙት ፈውስ፣ ለደከሙ ጉልበታቸው፣ለሞቱት ሕይወት የሚሰጥ ★ኢየሱስ★የሚል ስም ነው።ለዚህ ስም የማይገዛ በዚህ ስም ያልተሸፈነ ፉጡር ሊኖር አይገባም፣አለም የሚጠቀለለው በስሙ ስልጣን በፍቅሩ ብርታት ነውና ኤፌ1:9_10።ምክንያቱም ኢየሱስ ከስም በላይ ስም ስለ ሆነ።ስለዚህም ኢየሱስ ለሚልው ክቡር ስም በሰማይና በምድር ያሉት ፍጥረት ለዘለአለም ሊንበረከክ እና ሊገዛለት እንዲሁም ኢየሱስ ክርስቶስ ታላቅ አባት፣ፈጣሪያችን እያለን እነረዘምራለን።ስሙ ነውና ሰው ያረገን ። የስሙም ጣዕም ዘወትር ከአንደበታችን የማይጠፋ ነው፡፡ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ★“ኢየሱስ ክርስቶስ ጥዑመ ስም ለዘይጼውዖ፣ኢየሱስ ክርስቶስ ጥዑመ ቃል ለዘያጸምዖ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ጥዑመ ሥጋ ለዘይበልዖ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ጥዑመ ደም ለዘይሰትዮ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ጥዑመ ፄና ለዘያፄንዎ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ጥዑመ ዝክር ለዘይነግር ዜናሁ ” “ኢየሱስ ክርስቶስ ለሚጠራው ስሙ የጣፈጠ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ለሚያዳምጠው ቃሉ የጣፈጠ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ለሚበላው ሥጋው የጣፈጠ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ለሚጠጣው ደሙ የጣፈጠ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ዜናውን ለሚነግር መታሰቢያው የጣፈጠ ነው ” ★ ያለው መቼ በከንቱ ሆነና (መጽሐፈ ምሥጢር፣ የዕርገት ምንባብ):: ስለሆነም ቤተክርስቲያን ስመ ክርስቶስን ከመጥራት የምትከለከልበት ጊዜ የለም አይኖርምም:: ✔ኢየሱስ የሚል ስም ከአድማስ እስከ አድማስ፣ከአፅናፍ እሰከ አፅናፍ ዓለም ሲዘረጋ፣በዚህ ስም ሕሙማን ሲፈወሱ፣ሙውታን ሲነሱ፣ለምፃሞች ሲነፁ፣ዕውራን ሲያዩ፣መናገር የማይችሉትን አንደበታቸው ሲፈታ፣መሄድ የማይችሉትን እንደ እንቦሳ ሲዘሉ ፣በዚህ መልካም ስራ የቀኑት አይሁድና አይሁዳውያን ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን እንዴት እንደ ሚገድሉት ፣ለዚህ ከስም በላይ ስም የሆነ ደግሞ እንዴት ከሰው ህሊና እንደ ሚረሳ ማሰብ እና ማብሰልሰል የዘወትር አላማቸው ሆነ።ስለዚህም ከእነ ስሙና ታሪኩ ለማጥፋት የተጠቀሙት ዘዴ እንደ ወንጀለኛ በመስቀል ተሰቅሎ እንዲሞት፣ስሙ ለሚጠሩትም ጌታ ኢየሱስን እንደ መድሓኒታቸው እንደ ንጉሳቸው ፣እንደ አምላካቸው የተቀበሉት እንዲሁም ቅዱስ ስሙን ሲመሰክሩ የተገኙት ደግሞ ሊዘረፉ፣ቤታቸው እንዲቃጠል፣ ሊገርፉ፣ሊሰየፉ፣ወንጌል ሳይሆን ወንጀል በሚሰብኩባት ምኩራብ ደግሞ ለማሳደድ ወሰኑ።ቢሆንም ግን ማንም በማይቀርበው ብርሃናዊ ዙፈን ተቀምጦ ጥልቁን ውቅያኖስ የሚመረምር፣አለምን በፍቅርና በፍትሕ የሚያስተዳድር ዘለአለማዊ ንጉስ እንዲገደል ማሰብ፣ይህን የማይጠፋ ስም ለማጥፋት መጣር ሞኝነት እንጂ ጥበብ አይደለም። ቅዱስ ጳውሎስ “ ★ኦ አብዳን ሰብአ ገላትያመኑ አሕመመክሙ ከመ ኢትእመኑ በጽድቅ ከመ ያስተርኢ ለዓይን ኢየሱስ ክርስቶስ” “እናንተ ሰነፎች የገላትያ ሰዎች ሆይ ለጽድቅ እንዳትታዘዙ ማን አታለላችሁ? ቀድሞስ ኢየሱስ ክርስቶስ በዓይናችሁ ፊት እንደተሰቀለ ሆኖ ተስሎ ነበር” ያለው ከቶ ለማን ሆነና? ነገረ ክርስቶስ በዓይናቸው ፊት ተስሎላቸው ሳለ ላላስተዋሉት አይደለምን★? ክርስትና ህይወት ናት፡ ክርስቶስ የህይወት ባለቤት ስለሆነ በእርሱም ስለተመሰረተች ህይወት ናት። በእውነት በህይወት ሊኖሩ የሚፈልጉ ሁሉ ህይወትና መንገድ እውነትም የሆነውን ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ በህይወትም ይኖሩ ዘንድ ክርስትና ታስፈልጋቸዋለች። ✔ከአንዳ አንዶች ልባቸው በትዕቢት የተወጠረ/እንደ ፈርኦን/ በስተቀር ፣ኩፉ ምኞታቸውን የዋጣቸው ልጓም እንደሌለው ፈረስ ወደ ፊት የሚነዱ፣እምነታቸው በስሜት እንጂ በመረዳት ያልተመረኮዘ፣ትውፊትና መፅሓፍ ቅዱስ ለይተው ያለወቁ ፣የአይሁዳዊያን ባህሪ ያላቸው ሰዎች ካልሆኑ በስተቀር ፣ክርስቶስ ኢየሱስን የማይናፍቅ ለስሙ የማይቀኝ፣ስለ ታላቅ ውለታው ከአእምሮ በላይ ስለሆነ ፍቅሩ የማይመሰክር፣ንጉሴ፣ አምላኬ፣መድኀኒቴ አንተ ነህ እያለ ለስሙ የማይገዛ ፍጥረት በዘመን ሊኖር አይገባም።ምክንያቱም ኢየሱስ ፈውስ መድሓኒት፣የእረፍት ብርሃን፣ሰላም፣ህይወት ስለ ሆነ ።ስለዚህ እርሱጌታ የማይናፍቅ ፣ማራናታ አሜን ጌታ ኢየሱስ ና እያለ የማይዘምር ሊኖር አይገባም። ማር 1፥37 ።1ቆሮ1:23 ★ዕፍረት ምዑዝ ኢየሱስ ክርስቶስ፤ኢየሱስ ክርስቶስ መአዛዉ ያማረ ሽቶ ነዉ”★።ኤፌ 5:2 አንድም ኢየሱስ ክርስቶስ ምዑዘ ባህሪይ ነዉ።”ንዑ ንስግድ ሎቱ፤እንሰግድለት ዘንድ”/ፊል 2:10/ “ወንዕቀብ ትዕዛዛቲሁ፤ትዕዛዙን እንጠብቅ ዘንድ ኑ”።”ከመ ይሥረይ ለነ ኃጣዉኢነ፤ኃጢአታችንን ያስተሰረይልን ዘንድ” ኑ /መጽሐፈ ቅዳሴ ንባቡና ትርጓሜዉ ገጽ ፹፪ ሉቃ 5:24። ✔የገሃንም ደጆች ያፈረስንበት የእሳት ባህር የተሻገርንበት ፣በሞቱ ሞትን ያሸነፍንበት ፣በትንሳኤው ትንሳኤችን ያረጋገጥንበት ፣ነብያት የሚናፍቁት፣መላእክት ያበሰሩት፣ሓወርያት የሰበኩት የእምነታችን ጅማሪና ፍፃሜ ንጉሳችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስሙ እንዳንጠራ እንዳናመሰግን ለስሙ እንዳንገዛ ፣ስለ ዋለልን ውለታ ለአለም እንዳንመሰክር፣በስሙ ሕሙማን እንዳይፈወሱ እንደ ስምኦን ሉቃ 7:36:50 በበራችን ደጅ ቁመው እንዳንገባ እንዳንወጣ የሚከለከሉን ሰዎች :ተስፋ ቆርጠን ወደ ኃላ እንድንመለስ ደካማ ጎናችን የሚፈልጉ ተረፈ ፈሪሳዊያን ብዙ ናቸው።እንዚህ ከአባታቸው ከዲያብሎስ እንጂ ከእግዚአብሔር እንዳልሆኑ ከፍሬያቸው ይታወቃሉ።ታስታውሱ እንደሆነ ከልጅነቱ ጀምሮ ሸባ የነበረ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ሲፈውስት በወቅቱ የነበሩ ሊቀ ካህናትና ፀሓፍት ፈሪሳዊያን "በማን ሓይል ወይም በማን ስም ነው ይህን ያደረጋቹሁት"በለው ጠይቀዋል
Hammasini ko'rsatish...
ጌታዬ መድኃኒቴ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ! አንተን በበደልኩ ጊዜ ዕርቃኔን ወጣኁ፡፡ ጸጋዬ ተገፈፈ፡፡ አፈረኩ፡፡ በበለስ ቅጠልም ዕርቃኔን ሸፈንኩ፡፡ አንተ ግን አንተ ነኅና በማይለካ መውደድን ወደድከኝ፡፡ አዳም ሆይ ወዴት ነኅ ብለኽ ጠራኸኝ፡፡ እኔን ፍለጋም ወደኔ መጣኅ፡፡ ያንተን ትሰጠኝ ዘንድ የኔን ባሕርይ ገንዘብ አድርገኅ ፈለግከኝ፡፡ ዕርቃኔን የሸፈንኩባት ቅጠልንም ለዘላለም የሞት ፍሬ አይገኝብሽ ብለኅ ረገምክልኝ፤ ፈጽመኅም አጠፋኽልኝ /ማቴ.21:19/፡፡ የወይን ተክል ኾነኽም በጥላኅ አሳረፍከኝ /ዮሐ.15:1/፡፡ አባት ሆይ! አኹንም ከጥላኅ በታች ማደርን በየጊዜውም ጣፋጭ ፍሬውን ይኸውም ቅዱስ ሥጋኽን ክቡር ደምኽን እመገብ ዘንድ አድለኝ፡፡
Hammasini ko'rsatish...
“መኑ ይመስለከ፡ እምነ አማልክት እግዚኦ፡ አንተ ውእቱ ዘትገብር መንክረ፡ አርአይኮሙ ለሕዝብከ ኀይለከ፡ ወአድኀንኮሙ ለሕዝብከ በመዝራዕትከ ሖርከ ውስተ ሲኦል፡ ወአዕረገ ጼዋ፡ እምህየ ወጸጎከነ ምዕረ ዳግመ ግዕዛነ እስመ መጻእከ ወአድኀከነ፡፡ በእንተ ዝንቱ ንሴብሐከ፡ ወንጸርሕ ኀቤከ እንዘ ንብል፡ ቡሩክ አንተ እግዚኦ፡ ኢየሱስ ክርስቶስ እስመ መጻእከ ወአድኀንከነ፡፡” (ሥርዓተ ቅዳሴ) አቤቱ ፈጣሪያችን፡ መድኀኒታችን እግዚአብሔር ሆይ፤ “አማልክት” ከተባሉ፡ አማልክት ከሆኑባቸው ከእነ ዜውስ፡ ከእነ አርጤምስ አንተን የሚያህል፡ አንተን የሚተካከል ማነው? አማልክት ከሆኑብን ከስስት፤ ከዝሙት፤ ከሐሰት አንተን የሚመስል፤ አንተን የሚተካከል ማነው? እኒህ ሁሉ አማልክት ሕዝብህን ከክፉ ማዳን አይችሉምና፤ ሕዝብህን ከክፉ በማዳንም ድንቅን አላደረጉምና፡፡ አንተ ግን በከበረች ኀይልህ፡ እኛን ልታከብር፡ እኛ ከገባንበት ደይን (ሲኦል) ለማውጣት፡ ወደ ሲኦል ሄድኽ፡፡ እኛን ለመፈለግ በፍቅርህ ብዛት ወደ ምድር መጣህ፡፡ ፍቅርህ እውነተኛ ናትና “ወደ ምድር መጣሁላቸው፤ እሱ ይብቃቸው” ብለህ ፍቅርህን ሳትቆጥር፤ በደላችን ከምድር በታች (ሲኦል) ወስዳናለችና፡ እዚያም ሄድኽ፡፡ ክቡር እና ልዑል ለሆነ አባትህ ምርኮን ማረክህ፤ እኛን ወደ እርሱ አቀረብከን፡፡ እኛን ከከፋችው ቦታ አወጣኸን፡፡ ለዘለዓለም የሚሆን ነጻነትን (ጸጋን) ዳግመኛ ሰጠኸን፡፡ ጥንት የሰጠኸንን ነጻነት አንተን ላለመውደድ፤ ሕግህንም ላለማድረግ በጥመት ተጠቅመንበት ነበርና፡፡ አሁን ግን ወደን፡ ፈቅደን ለአንተ እንድንገዛ ከሰይጣን ባርነት፤ ያንተን ወደምትመስል ነጻነት መለስከን፡፡ ታዲያ እኛ ምን ብለን፡ ምን አድርገን እንመልስልህ? “የቡሩክ አብ ልጁ፡ ቡሩክ ወልድ” ብለን እናመስግንህ እንጂ፡፡ “እኛን ክፉ ከተባለው ሁሉ ጠብቀን” ብለን እንለምንህ እንጂ፡፡ “እኛን ከራሳችንም ጠብቀን፤ አድነን” ብለን እንለምንህ እንጂ፡፡ አንተ መጥተህ (ሰው ሆነህ) አድነኸናልና፡፡ አሁንም በመምህራን ትምህርት፤ በካህናት መሥዋዕት፤ በምዕመናን ጸሎት መጥተህ ታድነናኽና፡፡ አቤቱ ከአማልክት አንተን የሚመስል ማነው? አቤቱ ማረን!
Hammasini ko'rsatish...
ፍቅር! በፍቅር ውስጥ ሰላም አለ በፍቅር ውስጥ ደስታ አለ በፍቅር ውስጥ እምነት አለ በፍቅር ውስጥ ተስፉ አለ በፍቅር ውስጥ እውነት አለ በፍቅር ውስጥ ትዕግስት አለ በፍቅር ውስጥ ጸጋ አለ በፍቅር ውስጥ እረፍት አለ በፍቅር ውስጥ ጤና አለ በፍቅር ውስጥ መዋሐድ አለ በፍቅር ውስጥ አንድነት አለ። ፍቅር ዘር ብሔር ቋንቋን አይለይም ፍቅር ቀይ ጥቁር ቆንጆ መጥፎ አይልም በፍቅር ውስጥ እንዲሁ መዋደድ እንዲሁ መፋቀር አለ። ፍቅር ሃብት ድኽነት ጥጋብ ረሃብ አይልም። ፍቅር ስሜትን ልቡናን ማንነትን የሚቆጣጠር በቃላት ሊገለጽ የማይችል ረቂቅ ነገር ነው ፍቅር ቀልድ አይደለም ፍቅር ደካማም ጠንካራም የማድረግ ኃይል አለው ፍቅር ከቃላት በላይ ነው ፍቅር ከስጦታ በላይ ነው ፍቅር ሁሌም እውነት ነው ፍቅር የሚከሰት እንጂ ሠው ፈልጎ የሚያመጣው አይደለም ፍቅር በልብ ውስጥ የሚያድግ ስሜት ነው ፍቅር አለምን የሚያሳይ ክስተት ነው ፍቅርን ሳያውቅ ያለፈ ሠው በሕይወት አልኖረም። ፍቅር የጦር መሳሪያ የለውም ግን ሁሉንም ያሸንፋል ፍቅር ባለበት ጭንቀት ተስፋ መቁረጥ ሰላም ማጣት አይታሰብም ዶፍ ዝናብ ቢዘንብ ሐሩር ጸሐይ ቢወጣ መብረቅ ቢወድቅ ፍቅር ካለ ስሜቱ ምንም ነው ምክንያቱም ፍቅር ከሚዳሰሰው ከሚጨበጠው ከሚታየው በላይ ነውና መከራ ቢያጋጥም ጨለማ ነግሶ ብርሃን የጠፋ ቢመስልም ፍቅር ካለ በማይታይ ድቅድቅ ውስጥ ጽልመት የማያሸንፈው አብርሆት ነግሶ ይታያል። ፍቅር ከምንናገረው ከምናወራው መግባቢያ ከሆነው ቃላችን በላይ ነው ፍቅር በሶስት ቃላቶች አጥሮ ነገር ግን ውስጡ ረቂቅ ምስጢራትን የያዘ ድንቅ ምጡቅ ቃል ነው። ፍቅር እንደሁኔታው የሚገለጥ በሰው ልጆች ሁሉ አካል ውስጥ ያለ የተሰወረ አንድ ቀን የሚገለጥ ንዝረት ነው ፍቅር ከምንጽፍለት ከምንናገርለት ከህሊናችን በላይ የሆነ ድንቅ ነው ሰማይ ወረቀት ሆኖ ምድርም ቀለም ሆና ስለፍቅር ጽፈን እንጨርስ ዘንድ አንችልም ምክንያቱም ሰማይና ምድር የማይወስኑት ሰማይና ምድርን የሚወስን ከላይ ጽርሐ አርያም ከስር ጥልቅ በርባሮስን የመላ የርሕቀት ጥግ ወሰኑ የማይታወቅ ጌታ እግዚአብሔር ፍቅር ነውና ፍቅር ባለበት ተስፋ እምነት ሰላም ነጻነት ሁሉም በሁሉም የሆነ ጌታ እግዚአብሔር አብ አለ ፍቅር ባለበት ነጻነት ቤዛ አዳኝ በደሙ የዋጀን በቤዛነቱ የታረቀን በኩረ ትንሳኤ የተባለ ሊቀካህናት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አለ ፍቅር ባለበት አንድ የሚያደርገን በውሃ ጥምቀት በቅብዐ ሜሮን የተቀበልነው የሚያዋሕደን አንድ የሚያደርገን የሚያከብረን ከኃጢአት አርቆ የቤተክርስቲያን አካል ያደረገን ያነጻን የቀደሰን ያከበረን መንፈስ ቅዱስ አለ። ኡፍፍፍፍ በፍቅር ህብረት ውስጥ መኖር ምንኛ መታደል ነው!በአንድነት በሶስትነት የሚመለክ ቅድስት ሥላሴ በእውነተኛው ፍቅር ያጽናን ሰላሙን ያብዛልን አሜን!! DN ሸዋፈራው ይቆየን
Hammasini ko'rsatish...
ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ከወንድሞች ሁሉ የማንስ እኔ ባሪያህ ስለሠርግኽ ሳስብ እጅግ እፈራለኹ ስለ ግርፋትህ ፣ሞትህ ፣ መራብ ፣መጠማትኽ ሁሉ ብለህ ይቅር እንድትለኝ እየለመንኩኽ በደብረ ጽዮን እንድምተኛ ታረገኝ ዘንድ እሻለው!!
Hammasini ko'rsatish...
“ እባክህ፥ መባረክን ባርከኝ፥ አገሬንም አስፋው፤ እጅህም ከእኔ ጋር ትሁን፤ እንዳያሳዝነኝም ከክፋት ጠብቀኝ ብሎ የእስራኤልን አምላክ ጠራ፤ እግዚአብሔርም የለመነውን ሰጠው።” — 1 ዜና 4፥10
Hammasini ko'rsatish...
ፍቅር ቁስል ነው! እውነቱ ይኽ ነው ፣ ፍቅር የሚለካው በልባችን ላይ በተወው ቊስል ልክ ነው። እጅግ የምንወዳቸው ሰዎች አሳምመውን ይሆናል። እኛም እጅግ የሚወዱንን ሰዎች አሳምመን ይሆናል። ምክንያቱም ፍቅር የሚታየው በታገስ ነው ቊስል ውስጥ ነው። ፍቅር የሚታወቀው የተለዋወጥናቸውን ቃላት ሳይሆን በምንታገሠው ቊስል ፣ በተሰማን የውስጥ ሕመም ፣ በከፈልነውን መሥዋዕትነትና በተካፈልነውን ብርሃን ነው። ከትንሣኤው በኋላ በሐዋርያቱ ፊት የተገለጠው ክርስቶስ ኢየሱስ እርሱ የሚወዱት ጌታ እንደሆነ ለማስረዳት ያሳያቸው የትንሣኤው ድል ማብሠሪያ መለከት አይደለም ፣ የፍቅሩ ማስረጃ ቊስሉ ነበር። "ወደ እኔ ኑ ቊስሌን ዳስሱ ፣ እጃችሁንም ስለ እናንተ ፍቀር በቆሰልሁት ቊስል አስገቡ" ነበር ያላቸው። አታስታውሱኝም? አላወቃችሁኝም? እስከ ሞት ድረስ የወደድኳችሁ እኔ ነኝ። ለፍቅሬ ማስረጃ እንዲሆናችኹ ደግሞ ቊስሌን ተመልከቱ! ነው ያላቸው። ፍቅር ቊስል ነው። በእግዚአብሔር መንግሥት ክብርና ምስጋና የምናገኘውም በምድር ሳለን በነበሩ ስኬቶቻችንና ባስገኘናቸው ውጤቶቻችን ሳይሆን በታገሥናቸው መከራዎችና በተሰቃየንባቸው ሕመሞች ልክ ነው። ለዚህም ነው በአበው መጽሐፍ አንድ ቅዱስ አባት ለረጅም ዓመት በሰውነትዋ ላይ ቆስሎ የምትሰቃይን ሴት ሊጠይቁ ሲሔዱ "እዩት ቊስሌን አጎንብሰው ቢያዩት አጥንቴ ይታይዎታል" አለቻቸው። እርሳቸውም ጎንበስ ብለው "ብዙ ዓመት በታገስሽው በቊስልሽ ውስጥ የሚታየኝ አጥንት ሳይሆን ገነት ነው" አሏት። ጌታ በፍቅር ውስጥ ያለውን መከራ ለትዕግስት አድርጎልን መንግስቱን እንዲያወርሰን ቅዱስ ፈቃዱ ይሁን አሜን! ይቆየን
Hammasini ko'rsatish...
ፍቅር ቁስል ነው! እውነቱ ይይኽ ነው ፣ ፍቅር የሚለካው በልባችን ላይ በተወው ቊስል ልክ ነው። እጅግ የምንወዳቸው ሰዎች አሳምመውን ይሆናል። እኛም እጅግ የሚወዱንን ሰዎች አሳምመን ይሆናል። ምክንያቱም ፍቅር የሚታየው በታገስ ነው ቊስል ውስጥ ነው። ፍቅር የሚታወቀው የተለዋወጥናቸውን ቃላት ሳይሆን በምንታገሠው ቊስል ፣ በተሰማን የውስጥ ሕመም ፣ በከፈልነውን መሥዋዕትነትና በተካፈልነውን ብርሃን ነው። ከትንሣኤው በኋላ በሐዋርያቱ ፊት የተገለጠው ክርስቶስ ኢየሱስ እርሱ የሚወዱት ጌታ እንደሆነ ለማስረዳት ያሳያቸው የትንሣኤው ድል ማብሠሪያ መለከት አይደለም ፣ የፍቅሩ ማስረጃ ቊስሉ ነበር። "ወደ እኔ ኑ ቊስሌን ዳስሱ ፣ እጃችሁንም ስለ እናንተ ፍቀር በቆሰልሁት ቊስል አስገቡ" ነበር ያላቸው። አታስታውሱኝም? አላወቃችሁኝም? እስከ ሞት ድረስ የወደድኳችሁ እኔ ነኝ። ለፍቅሬ ማስረጃ እንዲሆናችኹ ደግሞ ቊስሌን ተመልከቱ! ነው ያላቸው። ፍቅር ቊስል ነው። በእግዚአብሔር መንግሥት ክብርና ምስጋና የምናገኘውም በምድር ሳለን በነበሩ ስኬቶቻችንና ባስገኘናቸው ውጤቶቻችን ሳይሆን በታገሥናቸው መከራዎችና በተሰቃየንባቸው ሕመሞች ልክ ነው። ለዚህም ነው በአበው መጽሐፍ አንድ ቅዱስ አባት ለረጅም ዓመት በሰውነትዋ ላይ ቆስሎ የምትሰቃይን ሴት ሊጠይቁ ሲሔዱ "እዩት ቊስሌን አጎንብሰው ቢያዩት አጥንቴ ይታይዎታል" አለቻቸው። እርሳቸውም ጎንበስ ብለው "ብዙ ዓመት በታገስሽው በቊስልሽ ውስጥ የሚታየኝ አጥንት ሳይሆን ገነት ነው" አሏት። ጌታ በፍቅር ውስጥ ያለውን መከራ ለትዕግስት አድርጎልን መንግስቱን እንዲያወርሰን ቅዱስ ፈቃዱ ይሁን አሜን! ይቆየን
Hammasini ko'rsatish...