cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

مذهب السلف الصالح

Reklama postlari
517
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
-37 kunlar
-730 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

# ቀልድ በኡለሞች መካከል ሸይኽ ሙሀመድ ረምዛን ከሸይኽ ሷሊህ አልፈውዛን ጋር ﺣﺪّث ﺍﻟﺸﻴﺦ ﻣﺤﻤﺪ ﺑﻦ ﺭﻣﺰﺍﻥ ﻗﺎﻝ: كان‎ﺍﻟﺸﻴﺦ ﺍﻟﻔﻮﺯﺍﻥ ﻳﻤﺎﺯﺣﻨﻲ ﻭﻳﻘﻮﻝ: ﻳﺎ ﻣﺤﻤﺪ ﻣﺎﻳﻜﻔيك ﺭﻣﺰﻭﺍﺣﺪ ،ﻻﺯﻡ"ﺭﻣﺰﺍﻥ"؟‏ ﻗﺎﻝ: ﻓﺄﺟﻴﺒﻪ: ﻳﺎﺷﻴﺨﻨﺎ ، ﻭﺃﻧﺖ ﻣﺎ ﻛﻔﺎﻙ ﻓﻮﺯ ﻭﺍﺣﺪ ، ﻻﺯﻡ "ﻓﻮﺯﺍﻥ" ؟ ﻓﻴﻀﺤﻚ ﺍﻟﺸﻴﺦ ﺍﻟﻔﻮﺯﺍﻥ ﻭﻳﻘﻮﻝ ﻟﻪ : ﻳﺎﺷﻴﺦ ﻣﺤﻤﺪ ، ﺩﺍﺋﻤﺎ ﺟﻮﺍﺑﻚ ﺣﺎﺿﺮ. ﻗﺎﻝ: ﺃﻗﻮل ﻟﻪ: ﻣﻨﻜﻢ ﺗﻌﻠﻤﻨﺎ ﺷﻴﺨﻨﺎ."...‏ 📒المصدر : ذكرها الشيخ محمد بن رمزان الهاجري - حفظه الله - عند زيارته الموقع الرسمي لمدينة الرياض. https://t.me/abuabdurahmen
Hammasini ko'rsatish...
📝Abu abdurahman«አብዱልቃዲር ኢብኑ ሐሰን»

هدفنا الذب عن السنة ይህ ቻናል የአቡ አብዱረህማን አብዱል ቃድር ሀሰን ደርሶች ሙሓደራዎች እና ጠቃሚ የሆኑ ፈዋኢዶች የሚለቀቁበት ቻናል ነው ይቀላቀሉ ➘➘➘➘➘➘➘➘

https://t.me/abuabdurahmen

https://t.me/abuabdurahmen

https://t.me/abuabdurahmen

ካሚል ሸምሱ፣ ኢልያስ አህመድ እና ሳዳት ከማል ============> ↪️ ❝ ተመዩዕ ዳር የሌለው ባህር ነው ! ❞ ↩️ ❞ التمييع بحر لا ساحل له! ❝ ♻️ የተመይዕ ቢድዓ ልክ ዳር እንደሌለው ባህር ነው ከገባህበት በኋላ ለመውጣት ብትሞክር አትችልም ምክንያቱም ባህሩ ዳርቻ የለውምና። ወደ ተመዩዕ Ideology የተነከሩ ሰዎች በቆዩ ቁጥር ባህሩን ያንቦጫርቃሉንጂ አይሻሻሉም። ➲ ከታች በቅደም ተከተል የምንጠቅሳቸው ሰዎች በተለዬ እርከን የሚገኙና የተለያዩ ስህተቶችን የሚፈፅሙ ናቸው። እንመልከት፦ ❶ኛ 🎙 ካሚል ሸምሱ፦ ➲ ❝ሱፊይ ሰለፍይ የሚለው በእስልምና አስተምህሮት ጥንት ያልነበረ አሁን የመጣ ቢሆንም ሱፍይ ነን ከሚለው ቡድንም በፊደራልም በአድስ አበባም በተለያዩ ክልል መጅሊሶችም የተካተቱበት የተወከሉበትም ተጨባጭ ነው ያለው።❞ ➘➴➘ ማዳመጥ ይችላሉ https://t.me/AbuImranAselefy/7523 ✅ መልስ፦ እጅግ በጣም ሰቅጣጭ ሀሳብ ነው። እንደት ሰው «...ሰለፍይ የሚለው በእስልምና አስተምህሮት ጥንት ያልነበረ አሁን የመጣ ቢሆንም...» ብሎ በድፍረት ይናገራል!? በእርግጥ ኢኽዋንዮች ምንም ለማለት የማይጨንቃቸው በተለያዩ አጋጣሚዎች የሻቸውን የሚናገሩ ሸይኽ እንዳሻዎች መሆናቸውን በደንብ እናውቃለን። ቢሆንም ግን እንዲህ አይነት ግልፅ ጥፋት እንግዳ ሊሆን ይችላል። ካሚል ሸምሱ ሰለፍይ ስለሚለው ፅንፀ-ሀሳብ ምንም አይነት ግንዛቤ እንደሌለው መገንዘብ ይቻላል። ለመሆኑ ሰለፍይ ማለት የሰለፎች (የደጋግ ቀደምቶች) ተከታይ አይደለምን!? ሰሃቦችን እና እነሱን በመልካም የተከተሉትን መከተል አይደለምን!? ነውንጂ ወሏህ وَالسَّابِقُونَ الْأَوَّلُونَ مِنَ الْمُهَاجِرِينَ وَالْأَنصَارِ وَالَّذِينَ اتَّبَعُوهُم بِإِحْسَانٍ رَّضِيَ اللَّهُ عَنْهُمْ وَرَضُوا عَنْهُ وَأَعَدَّ لَهُمْ جَنَّاتٍ تَجْرِي تَحْتَهَا الْأَنْهَارُ خَالِدِينَ فِيهَا أَبَدًا ۚ ذَٰلِكَ الْفَوْزُ الْعَظِيمُ ከስደተኞቹና ከረዳቶቹም ሲኾኑ የመጀመሪያዎቹ ቀዳሚዎች እነዚያም በበጎ ሥራ የተከተሏቸው አላህ ከእነሱ ወዷል ከእርሱም ወደዋል፡፡ በሥሮቻቸውም ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች በውስጣቸው ዘለዓለም ነዋሪዎች ሲኾኑ ለእነርሱ አዘጋጅቶላቸዋል፡፡ ይህ ታላቅ ዕድል ነው፡፡   [ሱረቱ አል-ተውባህ - 100] ♻️ ሰለፍያን መጤ ማለት ከባድ አደጋ እንደሆነ ብንገነዘብ ኖሮ ምን ያክል በጨነቀን ነበር። ለማንኛውም ይህ ለሱና ሰዎች ግልፅ ስለሆነ መደጋገም አልፈልግም። ካሚል ቀጥሎ እንዲህ ይላል፦ ➲ ❝አሁን ያለው መጅሊስ መውሊድን ኮሚቴ አዋቅሮለት በጀት በጅቶለት መውሊድ እንዲከበር እያደረገ ያለ መጅሊስ ነው።❞ ✅ መልስ፦ አዎ እንዲህ ሰዎች ማንነቱን እንዲገነዘቡ በዚህ መልኩ መናገሩ ጥሩ ነው። ለመውሊድ ይሄን ያክል ቦታ ከሰጡ የታለ ቢድዓን መቃወም እ? መጅሊሱን አስተካክለናል የሚሉት ሰወችስ ምን እየሰሩ ነው!? ❷ኛ 🎙 ኢልያስ አህመድ፦ ➲ ❝ይህ (መጅሊስ) የተለያዩ አመለካከት ያሏቸው ከተለያዩ background የመጡ ስብስቦች በአንድ ... የሚመሰርቱት ህብረት ነው❞ ✅ ማዝገንዘቢያ፦ ኢልያስ እንዳለው መጅሊስ የተለያዩ ሰዎች ስብስብ ነው። በህብረቱ ድብን ያሉ ከባባድ ልዩነቶች ያሏቸው አካላት የተጠራቀሙበት ነው። በዚህ መጅሊስ የተለያዩ የቢድዓ ባለቤቶች ተከማችተዋል። ከንግግሩ እንደምንገነዘበው እነዚህ የቢድዓ ሰዎች በጋራ እየሰሩ ነው። ታዲያ የሱና ሰው ነኝ የሚል አካል እንደት ከነዚህ አጥፊዎች ጋር በጋር ለአመታት ይቀጥላል!? የባሰው ደግሞ ከነዚህ የጥፋት አካላት ጋር በመሆን የሀቅ ሰዎችን መዋጋት ነው። 🎞 ቀጥሎም የሚከለክለውን መልዕክት ያዘለ ንግግር ያስተላልፋል፦ ➲ ❝ሌሎችን የምንገፋ ከሆነ ለሌሎች እውቅና የማንሰጥ ከሆነ....❞ ✅ ጉድኮ ነው! አሉ በኢልያስ ሙግት ከሆነ ሌሎች መገፋት የለባቸውም እውቅና መሰጠት አለበት ማለት ነው። አይይይ ሰው አውቆ ያላወቁትን ያህል ሲያጠፋ ይሰቀጥጣል። እርግጥ ነው ሰዎች ከንግግሩ የሚረዱት በዚህ መልኩ የተናገረው ለሆነ አላማ ሲባል ነው በማለት ነው። አላማውም መጅሊስ ገብቶ አንዳንድ ጥቅሞችን ማስገኘት ነው በማለት ይሞግታሉ! ⁉️ የኛ ጥያቄ የታለ ጥቅሙ? ⁉️ ለመውሊድ ከተበጀተ ሰለፍያ ልክ እንደሱፍያ መጤ ከተደረገ የታለ ጥቅሙ!? ⁉️ የሚገኘው ጥቅም በግልፅ የሚታየው መች ነው!? ⁉️ የአሁኑ መጅሊስ ከድሮው በምን ይለያል!? እንደውም እነ ኡመር ገነቴ ሰለፍይ ነኝ ያላለ ይከፍራል አሉንጅ ሰለፍያህ መጤ ነው አላሉም። ትክክለኛውን ሱና የፈለገ ይፁምንጅ እየበላ እየጠጣ መውሊድ ማክበር የለበትም ነው ያሉት! የነኢልያስ ካሚሎች ግን ለመውሊድ አብይ ኮሚቴና ከመጅሊሱ በጀት አውጥተው ይደግሱና በድፍረት ተግባራቸውን ይነግሩናል። የታለ የድሮውና የአሁኑ መጅሊስ ልዩነት!??? ❸ኛ 🎙 ሳዳት ከማል፦ ➲ ❝የመጅሊሱ ሰዎች ከእኛ በእድሜ የጠገቡ ናቸው❞ ✅ መልስ፦ ሳዳት ከማል ከተመዩዕ በሽታ በፊት የመጅሊስ ሰዎችን ጥፋቶች እየለቃቀመ ማስተካከያ ያደርግ ነበር። ያኔ ጥፋታቸውንጅ እድሚያቸው አልታየውም ነበር። በጥፋታቸው ሙስሊሙን የሚጎዱ እንጂ ጥቅማቸው አልተገለፀለትም ነበር። ምክንያቱም ያኔ በሹብሃ ሳይበከል በንፁህ አስተሳሰብ ላይ ነበር። ሰው ካጠፋ ትልቅ ነው ጠቃሚ ነው ወዘተ እየተባለ ጥፋቱ አይሸፍንም። መነገር ባለበት ልክ መነገር አለበት። ግን ሳዳት ዳርቻ ወደሌለው የተመዩዕ ባህር ከሰመጠ በኋላ ሀሳቡን ቀየረ። እንዲህም ይላል፦ ➲ ❝እንዳንተ ልጅ አይደሉም ጅል አይደሉም፤ ልጅና ጅል ቶሎ አይበስልም❞ ✅ መልስ፦ በዚህ ንግግሩ ምክንያት አንድ ድምፅ ትዝ አለኝ። ዶክተር ጀይላን በአንድ ወቅት ስለነሳዳትና መሰሎቹ እንዲህ ብሎ ነበር «ተዋቸው ልጅ ስለሆኑ ነው ይመለሳሉ ታገሱ» በማለት እስኪበስሉ ጠብቁ ብሎ ነበር እናም ዛሬ ሳዳት በስለናል እያለ መሆኑ ነው። አይ ጨዋታ ጉድ! ➲ ❝ስትሸብት መብት እያለህ እንደሌለህ ሆነህ መንግስት ቤት ሆነህ ትለምናለህ። ፈሪነት ግን አይደለም።❞ ✅ መልስ፦ ስንትና ስንት ሰዎች ሸብተው ሀይማኖታችንን ለመበረዝ ጥረት ያደርጋሉ። ተፈላጊው ነገር በትክክለኛው መንገድ መሆን እንጂ መሸበት አይደለም። ሳጠቃልል ♻️ እነዚህ ሰዎች ተሳስረው እየተጓዙ ነው። ከመንጫጫታችሁ በፊት ነገሮችን ለአላህ ብላችሁ ለማስተዋል ሞክሩ! እነ ኢልያስም ሆነ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ እነሳዳትም በኢክዋኖች ላይ ደራርበው ተኝተዋል። ይህ የሚካድ አይደለም። በዚህ አመት ብቻ የሀገራችን ኢኽዋኖች ስንቱን ቀባጠሩት ማነው ትንፍሽ ያለው!? የሳዳት ወዳጆች ረድ የምትመስል ነገር ካገኙ ይሄው ረድ አደረገ ይሄው ዝም አላለም በማለት ይንጫጫሉ። ይህ የሚያሳየው ረዱ ብርቅ ሆኖባቸዋል። በቃ እንደበፊቱ አይደለም። ወደድክም/ሽም ጠላህም/ሽም 📝 ➷➘➴ https://t.me/AbuImranAselefy
Hammasini ko'rsatish...
Abu Imran Muhammed Mekonn

ካሚል ሸምሱ፣ ኢልያስ አህመድ እና ሳዳት ከማል ============> 🎙 ካሚል ሸምሱ፦ ➲ ❝ሱፊ ነን የሚሉት በፊደራልም በአድስ አበባም በተለያዩ ክልል መጅሊሶችም እንዲካተት አድርገናል።❞ ➲ ❝አሁን ያለው መጅሊስ መውሊድን ኮሚቴ አዋቅሮለት በጀት በጅቶለት መውሊድ እንዲከበር እያደረገ ያለ መጅሊስ ነው።❞ 🎙 ኢልያስ አህመድ፦ ➲ ❝ይህ (መጅሊስ) የተለያዩ አመለካከት ያሏቸው ከተለያዩ background የመጡ ስብስቦች በአንድ ... የሚመሰርቱት ህብረት ነው❞ ➲ ❝ሌሎችን የምንገፋ ከሆነ ለሌሎች እውቅና የማንሰጥ ከሆነ....❞ 🎙 ሳዳት ከማል፦ ➲ ❝የመጅሊሱ ሰዎች ከእኛ በእድሜ የጠገቡ ናቸው❞ ➲ ❝እንዳንተ ልጅ አይደሉም ጅል አይደሉም፤ ልጅና ጅል ቶሎ አይበስልም❞ ➲ ❝ስትሸብት መብት እያለህ እንደሌለህ ሆነህ መንግስት ቤት ሆነህ ትለምናለህ።❞ ጊዜ ሳገኝ በማብራሪያ እመለሳለሁ 📝 ➷➘➴ ጠብቁኝ!!!

https://t.me/AbuImranAselefy

ሸይኹ ለኡማው ካበረከቱት ኪታቦች መካከል በጥቂቱ እነሆ፡ [1]: ኪታብ አት-ተውሒድ [2]: ኪታብ አል-ከባኢር [3]: ከሽፍ አሽ-ሹብሃት [4]: ሙኽተሰር ሲረት አር-ረሱል [5]:መሳኢል አል-ጃሂሊየህ [6]: ኡሱል አል-ኢማን [7]: ፈዳኢል አል-ቁርኣን [8]: ፈዳኢል አል-ኢስላም [9]: መጅሙዕ አል-አ'ሃዲስ [10]: ሙኽተሰር አል-ኢንሳፍ ወ-አሽ-ሸርህ አል-ከቢር [11]: አል-ኡሱል አስ-ሰላሰህ [12]: ኣዳብ አል-መሻኢል አስ-ሶላት....የመሳሰሉ ኪታቦችን አበርክተው ከዚህ ዓለም ተለይተዋል። ሸይኹል ኢስላም ሙሐመድ ብን ዐብዱል-ወ'ሓብ (ረሂመሁላሁ ተዓላ) እስከመጨረሻው አስትንፋሳቸው ደረስ ከደርዒያው አስተዳደር እንዲሁም ከሙሐመድ ብን ሰዑድና ልጁ...ከሸይኹ ጎን በመቆም ለተውሒድ ትልቅ የሆነን ዋጋ ከፍለዋል። በመጨረሻም፣ሸይኹል ኢስላም ሙሐመድ ብን ዐብዱል-ወ'ሓብ (ረሂመሁላሁ ተዓላ) ከዚች ዓለም በመሞት የተለዩት በሒጅራው ቀመር አቆጣጠር፣በዙል ቀዕዳ በመጨረሻው ዕለት፣1206 ዓመተ ሒጅራ ላይ ነበር። ባጭሩ የሸይኹል ኢስላም ሙሐመድ ብን ዐብዱል-ወ'ሓብ (ረሂመሁላሁ ተዓላ) አጭር የሕይወት ታሪክ ይህን ይመስል ነበር። አላህ ተጠቃሚዎች ያድርገነ!!!!!!! @semirEnglish @semirEnglish
Hammasini ko'rsatish...
የሸይኹል ኢስላም ሙሐመድ ብን ዐብዱል-ወ'ሓብ (ረሂመሁላሁ ተዓላ) አጭር የሕይወት ታሪክ:
ክፍል-1 አል-ሙጀዲድ ሸይኹል ኢስላም ሙሐመድ ብን ዐብዱል-ወ'ሓብ (ረሂመሁላሁ ተዓላ) በሒጅራው ቀመር አቆጣጠር በ'1115 ኡነይዛ ከተሰኘች ከተማ ተወለዱ። ኡነይዛ የተሰኘችው ከተማ፣ ከሳዑዲ አረቢያ ዋና ከተማ ከሪያድ በስተ ሰሜን-ምእራብ 70 ኪሎሜትር ያክል እርቀት ላይ ትገኛለች። የሸይኹ ቤተሰቦች የተከበሩና ዑለማኦች ነበሩ። አባቱ ሸይኽ ዐብዱል-ወ'ሓብ ብን ሱለይማን (ረሂመሁላህ) ጥልቅ እውቀት እንዳላቸውና እንዲሁም አጅግ ትሁትና መልካም ሰው እንደነበሩ ይነገራል። የሙሐመድ ዐብዱል-ወ'ሓብ አባት እውቀትን የቀሰሙት፣ ከአባታቸው ከሸይኽ ሱለይማን ብን ዐሊይ እንደሆነ ታሪክ ይዘክራል። ይህ በንዲህ እንዳለ፣ሸይኽ ሱለይማን ብን ዐሊይ (ረሂመሁላህ) በጊዜው ከነበሩ ዑለማኦች፣ዋና ሊቀመንበርና ፈትዋ ሰጪ እንደሆኑ ታሪክ ያስረዳል። አል-ሙጀዲድ ሸይኹል ኢስላም ሙሐመድ ብን ዐብዱል-ወ'ሓብ (ረሂመሁላሁ ተዓላ) የመጀሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን የተማሩት ከአባታቸው ነው። ይህም የሆነው እዛው በትውልድ ስፍራቸው ላይ ነበር። ሸይኹል ኢስላም ሙሐመድ ብን ዐብዱል-ወ'ሓብ (ረሂመሁላሁ ተዓላ) ታንፀው ያደጉትም በአባታቸው ነበር። ሸይኹ ቁርኣንን የሃፈዙት ገና በለጋ እድሜያቸው ላይ ነበር። ይህም የሆነው 10 አመት ሆኗቸው ሳለ ነበር። ሸይኹ ተፍሲር፣ሐዲስ፣ፊቅህ...ተምረዋል። ይህ በንዲህ እንዳለ፣ ሸይኹ የሰለፎችን ኪታብ በብዛት እንደማያነቡ ይነገራል፣በተለይም የሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያና ብርቅዬ የሆነው የተማሪያቸው የኢብኑል ቀይምን ኪታቦች ማንበብ ያጓጓቸው እንደነበር የታሪክ መዛግብት ያስረዳሉ። ሸይኹ እድሜያቸው ለጉርምስና በደረሰ ጊዜ፣ከአምስቱ የኢስላም ማዕዘናት የሆነውን ሐጅን ለመፈፀም ወደ መካ አቀኑ፤ከዚያም መካ ከሚገኙ ዑለማኦች እውቀትን ቀሰሙ። ሸይኹ ከመካ ቆይታ በኃላ፣እውቀትን ለመቅሰም ወደ መዲና አቀኑ፤እዛው መዲና ጥልቅ እውቀት ያላቸው እንደነ፡ ሸይኽ ዐብዱሏህ ቢን ኢብራሂም ብን ሰዒድ ነጅዲ እና ሸይኽ ሙሐመድ ሐያት ሲንዲ የመሳሰሉ ከታላላቅ ሙሁሮች ጋር ለረጅም ጊዜ ተማሪ ሆነው አሳለፉ። ሸይኹ እውቀትን (ዒልም) ፍለጋ በመካና መዲና ላይ አላበቁም። ሸይኹ ለዒልም ከነበራቸው ከፍተኛ ጉጉትና ፍላጎት ፣መዲና ላይ ለረጅም ጊዜ ከተማሩ በኃላ፣ ወደ ኢራቅና በስራ ጉዞ አቀኑ። ይሁን እንጂ፣ በዚህን ጊዜ የነጅድ ሁኔታ በጣም አስቸጋሪ ነበር፤ማለትም የተለያዩ ሺርክያቶች፣ ኢስላማዊ ያልሆኑ ድርጊቶች ይፈፀሙ ነበር። ሙሉበሙሉ በሚባል ደረጃ ነጅድ በሺርክ ማዕበል ተጥለቅልቃ ነበር። መቃብሮች፣ ዛፎች፣ ድንጋዮች፣ዋሻዎች፣መጥፎ መንፈሶች፣ከአላህ ውጭ ይመለኩ ነበር። መሰረት የሌላቸው አፈታሪኮችና ትንበያዎች በጊዜው ተንሰራፍቶ ነበር። በጊዜው የነበሩ ዑለማእ ተብዮችም ስሜታቸውን በመከተል ህዝቡን ከትክክለኛው መስመር ኢንዲስት አደረጉት። ይህ በንዲህ እንዳለ፣ጠንቋዮችና ትንቢት ተናጋሪዎች በጊዜ በህብረተሰቡ ላይ ተፅኖ ፈጣሪ የሚባሉት እነሱ ነበሩ። እነኝህን አካለት፡ ማለትም ጠንቋዮችን፣ትንቢት ተናጋሪዎች፣አጋሪዎች...በጊዜው ደፍሮ ሚጋፈጣቸው ሰው አንነበረም። በተመሳሳይም ይህ ሁኔታ በመካ፣በመዲና እንዲሁም በየመን ላይ ይስተዋል ነበር። ሸይኹ ትልቅ የዳዕዋ ተልእኮና ዓላማ አንግበው ተነሱ። በርግጥ ለሸይኹ ትልቅ ፈተና ነበር። በርግጥም፣ ይህንን ተለዕኮ መፈፀም ከባድ ፈተና እንደሆነ ለሁሉም ግልፅ ነው። ሸይኹ በቁርጠኝነት ጥሪያቸውን አንግበው ተነሱ።  ሰዎችን ወደ ተውሒድ ጥሪ አደረጉላቸው፤ ወደ ቁርኣንና ሱንናም ጥሪ አደረጉላቸው፤ በጊዜው የነበሩ ዑለሞችንም ወደ ቁርኣንና ወደ ሱንና እንዲመጡ አነሳሷቸው። ሸይኹ በዚህ ብቻ አላቆሙም፤ጭፍን ተከታይነትን አጥብቀው ተቃወሙ። ከጭፍን ተከታይነት ወጥተን ቁርኣንና ሱንናን እንከተል የሚል ጥሪም አቀረቡ። ሸይኹ ጥሪያቸው አጥብቀው ባለማቋረጥ ቀጠሉ፤ ሸይኹ ለተለያዩ በጊዜው ለነበሩ ዑለሞች ይህንን አስከፊ ሺርክ ለማጥፋት ከጎናቸው እንዲቆሙ ጥሪ አቀረቡ። ይህንን የሸይኹን ጥሪ አያሌ የሆኑ ዑለማኦች...ከመካ፣ከመዲና እንዲሁም ከየመን የሸይኹን ጥሪ በመቀበል ሸይኹንም በመደገፍ ከሸይኹ ጎን ተሰለፉ፤ ረዱትም ጭምር። ከፊሎች ደግሞ፣ ዳር በመያዝ ሸይኹን መተቸትና ማብጠልጠል ጀመሩ። ልብ ይበሉ! እንደዚህ የሚያደርጉት ዓለማዊ ጥቅም ፈላጊ ዑለማእ ተብየዎች ናቸው። በዚህ ብቻ አላበቃም ሌሎችን በሸይኹ ላይ በማነሳሳት ዳዕዋውን ለማኮላሸት መሞከራቸው የሚዘነጋ አይደለም። ሸይኹን የነዚህ ጥቅመኛ ዑለማእ ተብየዎች አመፅና ትችት ከዳዕዋው ዝንፍ አላደረጋቸውም፤በል እንዳውም ሸይኹ የተውሂድን ጥሪ ለማድረስ ወደተለያዩ ስፍራዎች አቀኑ። ለምሳሌ፡ "ዘቢር፣ አሕሳ፣ሁረይመለ..." ከዚያም ዑወይነህ ደረሱ። ዑወይነህ ከደረሱ በኃላ፣የገጠማቸው መልካም ነገር ነበር። በጊዜው የነበረው የዑወይነህ አስተዳደር፡ ዑስማን ብን ሐምድ ብን መ'ዕመር ይባላል። ይህ አስተዳደር ሸይኹን በደስታ ተቀበላቸው፤እንዲሁም  ከሸይኹ ጎን እንደሆነና ሸይኹ ደዕዋቸውን ማስኬድ እንደሚችሉ አረጋገጣላቸው። ሸይኹም እራሳቸውን ይበልጥ ለተውሂድ ተልዕኮ አዘጋጁ። ኢንሻአላህ ይቀጥላል.... https://t.me/semirEnglish https://t.me/semirEnglish
Hammasini ko'rsatish...
የሸይኹል ኢስላም ሙሐመድ ብን ዐብዱል-ወ'ሓብ (ረሂመሁላሁ ተዓላ) አጭር የሕይወት ታሪክ:
ክፍል-2 (የመጨረሻው ክፍል) ክፍል-1ን ለማግኘት⬇️ https://t.me/semirEnglish/2914 ፡ ፡ ፡ ሸይኹል ኢስላም ሙሐመድ ብን ዐብዱል-ወ'ሓብ (ረሂመሁላሁ ተዓላ) የዑወናው አስተዳደር አቀባበል ካደረገላቸው በኃላ፣ሸይኹ በከፍተኛው ሞራልና ትግል ዳዕዋቸውን በቁርጠኝነት ቀጠሉ። ዑወይነህ ላይ ሲፈፀሙ የነበሩ አስቀያሚ ሽርኪያቶች ሸይኹ ሰበብ በማድረሳቸው በአላህ ፍቃድ ሊጠሩ ችለዋል። እዛው ዑወይነህ ከተማ ውስጥ ሸይኹ ከመሄዳቸው በፊት፣ መቃብሮች፣ዋሻዎች፣ዛፎች...በሙስሊም ተብዬዎች ይመለኩ ነበር፤ሆኖምግን በዑወይነህ አስተዳደር አሚር ዑስማን ቢን መ'ዕመር...ከሸይኹል ኢስላም ሙሐመድ ብን ዐብዱል-ወ'ሓብ (ረሂመሁላሁ ተዓላ) ጎን በመሰለፍ የተለያዩ የባዕድ አምልኮ ተግባራትን በአላህ ፍቃድ ሊያስወግዱ ችለዋል። ይህ ደግሞ የሆነው፣ዑወይነህ ከተማ ብቻ ሳይሆን ዙሪያውን ጭምር ነው። ይህ በንዲህ እንዳለ፣በዑወይነህ ከተማ ውስጥ የእስልምና ህግጋት ተግባራዊ መሆን ጀመሩ። ለአብነት ያክልም...አንዲት ባለትዳር ሆና ዝሙት የፈፀመች ሴት ኢስላማዊ ህግጋት በሷ ላይ ተግባራዊ አንዲሆን ሸይኹን መጥታ ጠይቃለች። ዝሙት የፈፀምችው ሴትዮዋ ኢስላማዊ ህግጋት በሷ ላይ ተግባራዊ ኢንዲሆን መጠየቋን ተያይዞ፣ ስለ ሁኔታዋ፣ማለትም ጤነኛ ነች ወይ? ተገዳ ነው ወይ? የሚሉ ምርመራዎች ከተካሄዱ በኃላ፣እንዲሁም ወንጀሉ ከተረጋገጠ በኃላ፣ ሸይኹ ተወግራ እንድትገደል አዘዙ። የሸይኹ ዝናና ጀብድ በተለያዩ ከተሞች እየተስፋፋና እየተሰራጨ መሄድ ጀመረ። ሸይኹል ኢስላም ሙሐመድ ብን ዐብዱል-ወ'ሓብ (ረሂመሁላሁ ተዓላ) "የዑወይነህ" ቆይታቸውን ካጠናቀቁ በኃላ፣ "ደርዒየህ" ወደ ተሰኘች ከተማ አቀኑ። ሸይኹ ወደ "ደርዒየህ" ማቅናታቸውን ከታወቀ በኃላ፣የአል-አህሳ አስተዳደርና እንዲሁም ብን ሱለይማን የሸይኹን ገናናነት እና ተፅኖ-ፈጣሪ መሆናቸውን ለመለየት በህዝብ መካከል ሆኖ ይከታተል ነበር። ሁኔታው አጅግ በጣም አስፈራው፤ምክንያቱም ስልጣኔ ይነጠቃል የሚል ስጋትም ጭምር አደረበት። ይህ ሱለይማን የተባለው ግለሰብ፣ለአሚር ዑስማን ስጋቱን በመግለፅ ሸይኹን እንዲገላቸው ጥያቄ አቀረበ፤ይሁንእንጂ አሚር ዑስማን የሱለይማንን ጥያቄ ለመቀበል ፍቃደኛ አንነበሩም። ሱለይማን የአሚር ዑስማንን አቋም ከተረዳ በኃላ ተሸበረ፣ተጨነቀ፣ምድር ሰፊ ከመሆኗም ጋር ጠበበችው....አሚር ዑስማን ሸይኹን ተቀበሏቸው፤ በግዛቱ የፈለጉበት ቦታ መንቀሳቀስ እንደሚችሉ አስረግጦ አሳውቋቸው። የደርዒየህ ነዋሪዎችና ህዝቦች የሸይኹን የተውሂድ ተልእኮ ተረዱ። የደርዒያው አስተዳዳሪ አሚር ሙሐመድ ብን ሰዑድ፣ ሸይኹ ወደ ግዛቱ ስለገቡ በእጅጉን ተደሰተ። አስተዳዳሪው ቀጥታ ሸይኹ የሚገኝበት ድረስ በመሄድ ጉብኝት አድርጓል። በሸይኹ የተውሒድ ጥሪም ተደስቷል። ከሸይኹም ጋር የሃሳብ ልውውጥ አድርጓል። አሚር ሙሐመድ ብን ሰዑድ ለሸይኹ ድጋፍ እንደሚያደርግላቸው ቃል ገባላቸው። ሸይኹም ለአሚሩ ዱዓ አደረጉለት። ሸይኹ ይህንን ወርቃማ የሆነውን አጋጣሚ በመጠቀም፣አያሌ የሆኑ ህዝቦችን ማስተማር ጀመሩ። የደርዒየህ እና አካባቢዋ በተውሂድ ተናወጠች፤የተውሂድ ሰንደቅዓላማ መውለብለብ ጀመረ... ምን ይሄ ብቻ የደርዒያው ዋና አስተዳዳሪ አሚር ሙሐመድ እራሱን እና ቤተሰቦቹን ይዞ እንደተማሪ ሆኖ በመቅረብ፣ ከህዝቡ ጋር በመታደም የሸይኹን ትምህርቶችን መከታተል ጀመረ። ይህ ዜና በተለያዩ አከባቢዎች ተሰራጨ። ዜናውን የሰሙ ሰዎችም ከበረከቱ ለመቋደስ፣እውቀት ለመቅሰም ወደ ደርዒየህ መሰደድ ጀመሩ። ደርዒየህ የተውሂድ ማዕከል ሆነች። ይህ በንዲህ እንዳለ፣የሸይኹ ጠላቶች በሸይኹ ላይ የተለያዩ ቅጥፈቶችን መንዛት ጀመሩ። ምን ይሄ ብቻ?! ጠንቋይ፣ ድግምተኛ፣ ሙናፊቅ (ዚንዲቅ)...በመሳሰሉ ቃላቶች በሸይኹ ላይ መንዛት ጀመሩ። በተለያዩ የውሸት ቅጥፈቶች ሸይኹን ለማሸማቀቅና ከዳዕዋው ለማሰናከል በሚክሩም፣ሙከራቸው ሳይሳካ ቀርቷል። ሸይኹ የተቺ ተቺዎች ሴራ ሳይበግራቸው ተልዕኮውን ቀጠሉ። በል እንዳውም ተቃራኒ ከሆኑ አካላቶች ጋር ጨዋነት በተሞላበት ስልት ተከራክረዋል። ከዚህም በተጨማሪ፣ከተለያዩ ከአረብ ደሴት (Arabian peninsula) የመጡ የተለያዩ ልዑካን ቡድኖችን ትክክለኛው የተውሒድ ጥሪ ካደረጉላቸው በኃላ፣ወደ ሀገራቸው ሲመለሱ ህዝባቸውን ወደ ተውሒድ እንዲጠሩ አጥበቀው መክረዋል። ሸይኹ በዚህም ብቻ አላቆሙም ለአረብ ደሴት መሪዎችና ሊቃውንቶች ደብዳቤዎችነ ፃፉ። የደብዳቤው ዋና መልእክት ሽርክን እንዲሁም ኢስላም የማያውቀው ባዕድ የሆኑ አምልኮዎችን ህዝባቸውን እንዲታደጉ ነበር። ሸይኹ ደብዳቤዎችን የፃፉት ለነጅድ፣ ሪያድ፣ኸርጅ፣ ቀሲም፣ሀዬል፣ወሽም፣ ሱደይር፣አህሳ፣ መካ፣ መዲና፣ የመን...ለመሳሰሉት ሀገራቶች ፅፈው ነበር። ልብ ይበሉ! ደብዳቤው የተፃፈው በሀገሩ ለሚገኙ አስተዳደር እና ዑለማች ነው። ሸይኹ አሁንም በዚህ አላበቁም፤ከአረብ ደሴት ውጭ ለሆኑ ሀገራትም ደብዳቤዎችን ፅፈዋል፤ለምሳሌ፡ ለነ ሶሪያ፣ ኢራቅ፣ሕንድ...ለመሳሰሉት ሃገራት በደብዳቤ የዳዕዋ ጥሪ አቅርበዋል። ሸይኹ ቁርኣንና ሱንናን አብራርተዋል። ምስጋና ለአላህ የተገባ ይሁንና ዳዕዋቸው ግብ መቷል። የሸይኹን ዳዕዋ ከተቀበሉ ሀገራቶች መካከል፡ ሕንድ፣ኢንዶኔዥያ፣አፍጋኒስታን፣አፍሪካ፣ሞሮኮ፣ግብፅ፣ሶሪያ...የመሳሰሉ ሀገራቶች የሸይኹን ዳዕዋ በመቀበል ትልቅ ተፅዕኖ አድሮባቸዋል። ይህም ብቻ ሳይሆ ከሸይኹ ጎንም ጭምር ተሰልፈዋል። ሸይኹ በሒጅራው ቀመር አቆጣጢ ከ"1158" እስከ "1206" ባሉት ጊዜያት ውስጥ ትልቅ የሆነ ተግል በማድረጋቸው አመክንዮ፣ በነጅድ ሙሉበሙሉ በሚባል ደረጃ አላህ ሸይኹን ድል አጎናፀፋቸው። ሰዎች ዶሪህን፣ ቀብርን፣ እንጨትን፣ዛፍን...ማምለክ ተው። ጭፍን ተከታይነት ሚባል ነገር ጠፋ። ይህ ባህል ነው፣የአባቴ መንገድ ነው፣የአያቴ መንገድ ነው...ከማለት ሰዎች ተወገዱ። ጥርት ወዳለው እስልምና ገቡ። አላሁ አክበር ዲን እንደገና ሕያው ሆነ። ቁርኣንና ሱንና በሰዎች ላየ ተንፀባረቀ። በመልካም ማዘዝ ከመጥፎ መከልከል ተግባራዊ ስራ ሆኖ ቀጠለ፤ መስጂዶች ውስ ሰዎች ሞልተው መስገድ ጀመሩ። በሀገሪቷ ሰላምና መረጋጋት ሰፈነ። ገጠሬዎችም ከተሜዎች...በሰላም መኖር ጀመሩ። የተውሒድ ሰንደቅዓላማ ተውለበለበ። ከሸይኹ እወቀትን የቀሰሙ አካላቶች በመላው ዓረቢያ ደሴት የተውሒድ ተልዕኮን ይዘው ተሰሬጩ። ሸይኹ በሕይወት ካለፉ በኃላም ልጆቻቸው እና ተማሪዎቻቸው ዳዕዋውን በአላህ ፍቃድ ማስቀጠል ችለዋል። ከልጆቻቸው መካካል ዳዕዋውን ካስቀጠሉ እንደነ፡ ሸይኽ ኢማም ዐብዱሏህ ብን ሙሐመድ፣ ሸይኽ ሑሰይን ብን ሙሐመድ፣ ሸይኽ ዐሊይ ብን ሙሐመድ፣ሸይኽ ኢብራሂም ብን ሙሐመድ....ይገኙበታል። ከሸይኹ ከልጅ ልጆቻቸው መካከል ደግሞ፣ሸይኽ ዐብዱር-ረሕማን ብን ሐሰን፣ሸይኽ ዐሊይ ብን ሑሰይን፣ሸይኽ ሱለይማን ብን ዐብዱሏህ... ይገኙበታል። ከተማሪዎቻቸው መካከል ደግሞ፡ እንደነ ሸይኽ ሐምድ ብን ናሲር...የመሳሰሉ ይገኙበታል። ሸይኹል ኢስላም ሙሐመድ ብን ዐብዱል-ወ'ሓብ (ረሂመሁላሁ ተዓላ) ለዚህ ኡማ ትልቅ የሆነን አሻራ ጥለው አልፈዋል። ለዚህም ነው ሰዎች በሺርክና በተለያዩ ባዕድ በሆኑ አምልኮ ተጨማልቀው ሳለ፣ በአላህ ፍቃድ ሸይኹ ትግል አድርገው፣የአንበሳውን ድርሻ ተጫውተው ነው ከዚች ዓለም ያለፉት።
Hammasini ko'rsatish...
أركان الكفر أربعةٌ: الكبرُ والحسد والغضب والشهوة فالكبر يمنعه الانقيادَ والحسد يمنعه قبولَ النصيحة وبذلها والغضبُ يمنعه العدلَ والشهوة تمنعه التفرُّغَ للعبادة. فإذا انهدم ركنُ الكبر سَهُلَ عليه الانقياد، وإذا انهدم ركنُ الحسد سهل عليه قبول النصح وبذله، وإذا انهدم ركن الغضب سهل عليه العدل والتواضع، وإذا انهدم ركن الشهوة سهل عليه الصبرُ والعفافُ والعبادةُ. وزوال الجبال عن أماكنها أيسر من زوال هذه الأربعة عمن بُلِي بها. الفوائد لابن القيم - (٢٣١ )
Hammasini ko'rsatish...
13:50
Video unavailableShow in Telegram
كلام منهجي يوزن بالدهب / للشيخ العلامة محمد بن هادي المدخلي حفظه الله
Hammasini ko'rsatish...
كلام_منهجي_يوزن_بالدهب_للشيخ_العلامة_محمد_بن_هادي_المدخ_glJIi_mR9p8.mp48.50 MB
03:57
Video unavailableShow in Telegram
جديد| تلاوة مبكية لآيات من سورة المطففين| بصوت الشيخ د. محمد بن هادي المدخلي 10-2-1443
Hammasini ko'rsatish...
جديد_تلاوة_مبكية_لآيات_من_سورة_المطففين_بصوت_الشيخ_د_م_TAcFjUSSjsk.mp42.86 MB
Boshqa reja tanlang

Joriy rejangiz faqat 5 ta kanal uchun analitika imkoniyatini beradi. Ko'proq olish uchun, iltimos, boshqa reja tanlang.