cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

Hijra Tube [Official]

ሒጅራ ቲዩብ ኢስላማዊ ድረገፅ ትኩስ ትኩስ የሙስሊሙን አለም የተመለከቱ መረጃዎች ጠቃሚ ፅሁፎችና ዳእዋዎች ይቀርቡበታል

Ko'proq ko'rsatish
Reklama postlari
10 051
Obunachilar
-424 soatlar
-367 kunlar
-12930 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

Photo unavailableShow in Telegram
የወንድማችን አህመድን ህይወት ለማትረፍ በሚደረገው ትግል ውስጥ በትንሹ ድጋፋችሁም ቢሆን የወንድማችንን ተስፋ ለማለምለም ሰበብ መሆን ትችላላችሁ። ለህክምና ከሚያስፈልገው ብር ውስጥ ሊሞላ የቀረው ውስን ብር ነው፣ የቀረችውን ተባብረን በአቅማችን እንሙላት። ድጋፍ ለማድረግ፦ Account name: muhammed suleiman & or Taju suleiman. Comercial bank 1000632758638 Zemzm bank 0042125420101 Awash bank 014251356745900 ለበለጠ መረጃ 0910373510 ታጁ ሱለይማን ...ወንድም 0921572121 ሙሀመድ ሱለይማን ...ወንድም
Hammasini ko'rsatish...
👍 2
Photo unavailableShow in Telegram
ብዙ አባቶች እነሱ ካለፉ በኋላ የልጆቻቸው እጣፈንታ ያሳስባቸዋል ። ልጆቻቸው ቦታ ቦታ ሳይዙላቸው መሞትም አይፈልጉም ። ይሄ የብዙ ወላጆች ጭንቀት ነው ። ቁርዐን ሱራ አል-ከህፍ ውስጥ ይህን ስጋት የሚያስወግድ መፍትሄ ተቀምጧል ። ሰይዱና ኸድር ከነብዩላህ ሙሳ ጋ በነበራቸው አጭር ቆይታ ካጋጠሟቸው ክስተቶች አንዱ መስተንግዶ የተነፈጉበት መንደር ውስጥ ሊወድቅ ያዘመመ የየቲሞችን የቤት ግድግዳ ሰይዱና ኸድር ማቃናታቸው ያታወቃል ። የዚህንም ምክንያት ለነቢ ሙሳ ሲያብራሩ ‹ከግድግዳው ስር ልጆቹ ማያውቁትና በሷሊህነቱ የሚታወቀው አባታቸው ከመሞቱ በፊት ያስቀመጠላቸው ከንዝ(የወርቅና ብር ድልብ) እንዳለና አላህም በእዝነቱ አውጥተው እንዲጠቀሙበት እንደፈለገ› ገልፀውለት ነበር ። ይህን ይዘው ሙፈሲሮች አላህ በአባት ሰላህ/ደግነት እና ተቅዋ ልጆችን ይጠብቃል ይላሉ ። ተፍሲሩል በغዊ ላይ ደግሞ حُفِظَا بِصَلَاحِ أَبَوَيْهِمَا ‹በወላጆቻቸው ደግነት እነሱ ተጠበቁ› የሚል አሰር ከኢብኑ ዐባስ ይዘው አውርተዋል ። የልጆቹ የወደፊት እጣፈንታ የሚያሳስበው ወላጅ ነፍሱ ላይ ይስራ ፣ አላህን ይጠንቀቅ ፣ ሷሊህ ለመሆን ይጣር ። አላህ ሸኩር የሆነ አምላክ ነው - ካለፈ በኋላ ከሱ በላይ ልጆቹን ይንከባከብለታል ። ✍ አብዱ ሰመድ
Hammasini ko'rsatish...
ሰዎች "እንዴት ነህ"?' ባሉህ ጊዜ 'አልሐምዱ ሊላህ ትልቅ ኒዕማ ዉስጥ ነኝ' ያልክ እንደሆን ትልቅ ኒዕማ እንደሚፈስልህ አትጠራጠር በምንም ዉስጥ ሁን በምን፤ አላህን አብዝተህ አመስግን🙏🙏🙏
Hammasini ko'rsatish...
👍 19 11
የቤት ኪራይ ጨምሩ፣ ወይም "ቤቱን ልቀቁ፣ ወይም እንዲያ ላደርግ እንድህ ላደርገ ፈልጌ ነው" ሚል ግፊት ከደረሰባችሁ ከታች ባለው የስልከ ቁጥሮች ደውላችሁ ጠቁሙ!! +251118722917 +251118553820 አዲስ አበባ የቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ
Hammasini ko'rsatish...
👍 11
እጅግ ጠቃሚ የጁምኣ ኹጥባ " አማናን መወጣት" 8:44 አማርኛው ይጀምራል ሰኔ 14/2016 ዙልሂጃ 15/1445 ኡስታዝ _አብዱልዋሲዕ ሼኽ ነስሮ አዲስአበባ ተንኢም መስጂድ
Hammasini ko'rsatish...
የጁምዓ ኹጥባ 8.mp324.69 MB
👍 1
#የነፍስ_ዓይነቶች 📚ቁርኣን ነፍስን ከጠባዩዋና ከባሕሪዋ አንፃር ለሦስት ይከፍላታል... 1ኛ- "አን-ነፍሱል ዓማረቱ ቢሱእ"፤ በመጥፎ የምታዝ ነፍስ እንላታለን። የዚህች ዓይነት ነፍስ ባለቤት ሰውየውን ሙሉ ለሙሉ የምትቆጣጠረውና የምታዝዘው ሲሆን ሁሌም አላህን ወደ ማመጽ ትገፋዋለች። ይህች ነፍስ ሀጢያትና ወንጀልን ተቀብላ ያለምንም ትግል ታስተናግዳለች። ♦️ነቢዩላህ ዩሱፍን (عليه السلام) ለነፍሷ ፍላጎት ያባበለቻቸው ያቺ የንጉሱ ሚስት ምን ነበር ያለችው... وَمَاۤ أُبَرِّئُ نَفۡسِیۤۚ إِنَّ ٱلنَّفۡسَ لَأَمَّارَةُۢ بِٱلسُّوۤءِ إِلَّا مَا رَحِمَ رَبِّیۤۚ إِنَّ رَبِّی غَفُورࣱ رَّحِیمࣱ «ነፍሴንም (ከስሕተት) አላጠራም፡፡ ነፍስ ሁሉ ጌታዬ የጠበቃት ካልሆነች በስተቀር በመጥፎ ነገር በእርግጥ አዛዥ ናትና፡፡ ጌታዬ በጣም መሓሪ አዛኝ ነው» (አለች)፡፡ [12፥53] 2ኛ- "አን-ነፍሱ ላዋማህ"፤ ዋቃሽ ነፍስ እንላታለን። ይህች ነፍስ ባሕሪዋ ሆኖ አንድ ሁኔታ ላይ አትጸናም። መገለባበጥና መለዋወጥ ታበዛለች። ሲሆንላት አላህን ታወሳለች ደግሞ ትዘነጋለች። አንዴ ወደ አላህ ትገባለች ከዚያ ትመለሳለች። አንዴ በዒባዳ ትደሰታለች ደግሞ ስሜት ታጣበታለች። ትወዳለች ትጠላለች። ሲላት ቀጥ ብላ "አላህ አላህ" ትላለች ደግሞ ወንጀልም ትቀላቅላች። ♦️ይህች ነፍስ አንድ ወንጀል ስትሰራ ሰውየውን ለምን እያለች አንዲያስብ ታደርገዋለች። ወንጀል ላይ በወደቀች ቁጥር አላህን በማሰብ ጥበትና በወንጀሉ ማፈር የሚከተላት ናት። አላህ በዚህች ነፍስ ምሏል። لَاۤ أُقۡسِمُ بِیَوۡمِ ٱلۡقِیَـٰمَةِ ❝(ነገሩ ከሓዲዎች እንደሚሉት) አይደለም፡፡ በትንሣኤ ቀን እምላለሁ፡፡❞ [75፥1] وَلَاۤ أُقۡسِمُ بِٱلنَّفۡسِ ٱللَّوَّامَةِ ❝(ራሷን) ወቃሽ በኾነች ነፍስም እምላለሁ፡፡ (በእርግጥ ትቀሰቀሳላችሁ)፡፡❞ [75፥2] ♦️ይህች ነፍስ ከመጀመሪያዋ ነፍስ የተሻለች ናት። በል እንደውም በጣም ከፍ ያለች ናት። ሁሌም ኣኺራንና ቂያማን ታስታውሳለች። ለተውበትም የቀረበችና የተገራች ናት። በመጥፎ የምታዝን ነፍስ ወደዚህች ራሷን ወቃሽ ወደሆነችው ነፍስ ለመለወጥ አኺራን ደጋግሞ ማስታወስ መድኃኒት መሆኑን ልብ እንበል። ♦️በመጥፎ የምታዘውን ነፍሱን "አላህ ጋር ትገናኛለሽ፣ አላህ ፊት ትቆሚያለሽ..." እያለ አኺራንና ቂያማን በማስታወስ መገሠጽ ፈውስ ይሆናል። ነገሩ ያላሰለሰ ጥረት የሚፈለግና መቋረጥ የሌለበት የመዳን መንገድ ነው። ማወቅ ያለብን ነፍስ መቀየርና መለወጥን የምትቀበል ፍጡር ናት። 3ኛ- "አን-ነፍሱ አል-ሙጥመኢናህ" የተረጋጋች ነፍስ እንላታለን። ይህች ነፍስ አላህን የምትፈራ፣ አላህን የምትናፍቅ፣ አላህን የምትወድ በዚህም የረጋችና የረካች ደግ ነፍስ ናት። ነፍስ በአላህ የረካች እንደሆነ፣ አላህን በማውሳት የጸዳች ከሆነ፣ ወደ አላህም ጠቅልላ የገባች ከሆነ፣ ወደ አላህ በመቅረብ ብቸኝነቷን ያስወገደች ከሆነ፣ አላህን መገናኘት የምትናፍቅ ከሆነ ይህች ነፍስ "ሙጥመኢናህ" የተረጋጋች ናት ማለት ነው። ♦️ይህች ነፍስ ሞት መጥቶ ከሰውነት ስትወጣ እንዲህ ትባላለች (አላህ ያድለንና)፦ یَـٰۤأَیَّتُهَا ٱلنَّفۡسُ ٱلۡمُطۡمَىِٕنَّةُ ❝(ለአመነች ነፍስም) "አንቺ የረካሺው ነፍስ ሆይ! [89፥27] ٱرۡجِعِیۤ إِلَىٰ رَبِّكِ رَاضِیَةࣰ مَّرۡضِیَّةࣰ ❝ወዳጅ ተወዳጅ ኾነሽ ወደ ጌታሽ ተመለሺ..[89፥28] فَٱدۡخُلِی فِی عِبَـٰدِی ❝በባሮቼም ውስጥ ግቢ..[89፥29] وَٱدۡخُلِی جَنَّتِی ❝ገነቴንም ግቢ፤» (ትባላለች)።❞ [89፥30] 💥አንዲት ነፍስ ሦስቱንም ባሕሪ ተላብሳ ልናገኛት እንችላለን። በመጥፎ የምታዝ ሆናም፤ ራሷን ወቃሽ ሆናም፤ የተረጋጋች ሆናም ይስተዋላል። ባሕሪዋ ከአንዱ ወደ አንዱ ሁኔታ ይለዋወጣል። አላህ ነፍሳችንን ይቅጣልን❤ አሚን💚
Hammasini ko'rsatish...
9👍 5
አንድ ሰው አርባ አመት ሲሞላው፦ ”ወደ አኼራ ጎዞህ ተቃርቧልና ስንቅህን አዘጋጅ።˝ ብሎ ከሰማይ☝️ ተጣሪ ይጣራል። 📚ረውደቱ አል ዑቀላእ (52)
Hammasini ko'rsatish...
👍 6
Photo unavailableShow in Telegram
3
📢📢📢 ታላቅ የምስራች ለወላጆች እና ለመምህራን 🌤በብዙዎች ጥያቄ መሰረት በተለያዩ ቦታዎች እንሰጥ የነበረውን  የተርቢያ(ልጆቻችንን በተርቢያ የማሳደግ) ስልጠና በአሏህ ፈቃድ በተቀናጀ እና ቀጣይነት ባለው መልኩ በማእከላችን ልንሰጥ ዝግጅታችንን አጠናቀን ምዝገባ መጀመራችንን  ስንገልፅ በታላቅ ደስታ ነው:: ትውልድን በመልካም ማነፅ የሁሉም ሀላፊነት በመሆኑ እኛም የበኩላችንን ለማበርከት በማእከላችን የሚሰጠውን የመጀመሪያ ዙር የአንድ ወር ስልጠና አሰናድተን  የናንተን መምጣት በመጠባበቅ ላይ ነን:: ይምጡ አበቦቻችንን በጋራ እንኮትኩት:: 🌴 ስልጠና የሚሰጠው ቅዳሜ ጠዋት ከ3:30_6:00 ሰዐት            ወይም ቅዳሜ ከሰአት ከ7:30 _10:00 ሰዐት የሚጀመረው ከአረፋ በኋላ የመጀመሪያው ቅዳሜ(ሰኔ 15/2016) ለምዝገባ እና ለበለጠ መረጃ 👇ይደውሉ :: የምንቀበለው የሰልጣኝ ብዛት ውስን ስለሆነ ቀድመው ይመዝገቡ:: አድራሻ ከጀርመን አደባባይ ከፍ ብሎ ገቢዎች አካባቢ:: ☎️ 0982002437 አል ማሒር የተርቢያ ማእከል 👉ለሴቶች ብቻ
Hammasini ko'rsatish...
👍 4 2
Boshqa reja tanlang

Joriy rejangiz faqat 5 ta kanal uchun analitika imkoniyatini beradi. Ko'proq olish uchun, iltimos, boshqa reja tanlang.