uz
Feedback
EEP Communication

EEP Communication

Kanalga Telegram’da o‘tish

EEP Communication

Ko'proq ko'rsatish

📈 Telegram kanali EEP Communication analitikasi

EEP Communication (@eepcommuication) Amxar til segmentidagi kanali faol ishtirokchi. Hozirda hamjamiyat 15 692 obunachidan iborat bo'lib, Texnologiyalar & Aralashmalar toifasida 8 014-o'rinni va Efiopiya mintaqasida 2 155-o'rinni egallagan.

📊 Auditoriya ko‘rsatkichlari va dinamika

невідомо sanasidan buyon loyiha tez o‘sib, 15 692 obunachiga ega bo‘ldi.

30 Avgust, 2026 dagi oxirgi ma’lumotlarga ko‘ra kanal barqaror faollikka ega. Oxirgi 30 kunda obunachilar soni 145 ga, so‘nggi 24 soatda esa 2 ga o‘zgardi va umumiy qamrov yuqori darajada qolmoqda.

  • Tasdiqlash holati: Tasdiqlanmagan
  • Jalb etish (ER): Auditoriya o‘rtacha 31.28% darajada jalb etiladi. Nashrdan keyingi dastlabki 24 soatda kontent odatda umumiy obunachilar sonining 16.96% ini tashkil etuvchi reaksiyalarni to‘playdi.
  • Post qamrovi: Har bir post o‘rtacha 4 909 marta ko‘riladi; birinchi sutkada odatda 2 661 ta ko‘rish yig‘iladi.
  • Reaksiyalar va o‘zaro ta’sir: Auditoriya faol: har bir postga o‘rtacha 10 ta reaksiya keladi.

📝 Tavsif va kontent siyosati

Muallif resursni shaxsiy fikrni ifoda etish maydoni sifatida ta’riflaydi:
EEP Communication

Yuqori yangilanish chastotasi (oxirgi ma’lumot 31 Avgust, 2026 da olingan) sababli kanal doimo dolzarb va katta qamrovli bo‘lib qoladi. Analitika auditoriya kontent bilan faol hamkorlik qilishini, uni Texnologiyalar & Aralashmalar toifasidagi muhim ta’sir nuqtasiga aylantirishini ko‘rsatadi.

15 692
Obunachilar
+224 soatlar
+187 kunlar
+14530 kunlar
Postlar arxiv
ፕሮጀክቱ በአካባቢው ያለውን የኃይል ጥያቄ በአግባቡ ለመመለስ ያግዛል …….///……. በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በአርባ ምንጭ ዙሪያ ተገንብተው በመጠናቀቅ ላይ የሚገኙ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር
+7
ፕሮጀክቱ በአካባቢው ያለውን የኃይል ጥያቄ በአግባቡ ለመመለስ ያግዛል …….///……. በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በአርባ ምንጭ ዙሪያ ተገንብተው በመጠናቀቅ ላይ የሚገኙ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር እና ማከፋፈያ ጣቢያ ፕሮጀክቶች በአካባቢው አስተማማኝ ኃይል ለማቅረብ እንደሚያስችሉ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የአርባ ምንጭ ሪጅን ገለፀ። የሪጅኑ ዳይሬክተር አቶ ገረመው ወንድምሁነኝ እንደገለፁት አሁን ላይ የአርባ ምንጭ ከተማን ጨምሮ የጋሞ ዞን የተለያዩ አካባቢዎች በከተማው ውስጥ ከሚገኘው የነባሩ የባለ 132 ኪሎ ቮልት የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ኃይል በማግኘት ላይ ይገኛሉ። የማከፋፈያ ጣቢያው በዞኑ ለሚገኙ ኢንዱስትሪዎች፣ ለአገልግሎት ሰጭና መንግስታዊ ተቋማት እንዲሁም ለነዋሪው ኃይል የማቅረብ አቅም ቢኖረውም በአንድ አቅጣጫ ብቻ ኃይል የሚያገኝ በመሆኑ መስመሩ በተለያዩ ምክንያቶች ችግር ሲያጋጥመው የኃይል መቋረጥ ይስተዋልበት እንደነበር አስታውሰዋል። ተጨማሪ ለማንበብ… https://www.eep.com.et/?amh-news=ፕሮጀክቱ-በአካባቢው-ያለውን-የኃይል-ጥያ&lang=am 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et የካቲት 27 ቀን 2018 ዓ.ም

በተቋሙ የዉስጥ አቅም በተከናወነ ሥራ 60 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ማዳን ተችሏል …..….///…….. በኢትዮ-ኬንያ ኢንተር ኮኔክሽን የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ የችግር ጠቋሚ (fault l
+4
በተቋሙ የዉስጥ አቅም በተከናወነ ሥራ 60 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ማዳን ተችሏል …..….///…….. በኢትዮ-ኬንያ ኢንተር ኮኔክሽን የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ የችግር ጠቋሚ (fault locater) መሳሪያን ተግባራዊ ለማድረግ በውስጥ አቅም በተከናወነ የማስተካከል ሥራ 60 ሺህ የሚደርስ የአሜሪካ ዶላር ማዳን መቻሉን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ። በተቋሙ የኢንጅነሪንግ ቢዝነስ ዘርፍ ሬዚደንት ኢንጂነር አቶ ቴዎድሮስ አያሌው እንዳስታወቁት በከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመሩ ላይ ችግር ሲፈጠር የሚጠቁመው መሳሪያ ከአራት ዓመታት በላይ ሥራ ሳይሰራ ቆይቷል። በተደጋጋሚ ተሞክሮ ዉጤታማ ያልሆነውን የችግር ጠቋሚ መሳሪያ የገጠመውን ችግር ለመለየት በተደረጉ ምርመራዎች እና ፍተሻዎች መሳሪያው በግንባታ ወቅት የቴክኒክ ችግር እንዳለበት መረጋገጡን ገልጸዋል። ተጨማሪ ለማንበብ… https://www.eep.com.et/?amh-news=በተቋሙ-የዉስጥ-አቅም-በተከናወነ-ሥራ-60-ሺህ&lang=am 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et የካቲት 27 ቀን 2018 ዓ.ም

የኃይል ማስተላለፊያ መስመሮቹ የፍተሻ እና ሙከራ ሥራ ተጠናቀቀ .…….///……. የብሔራዊ ኤሌክትሪክ ደቡባዊ ግሪድ ማስፋፊያ ፕሮጀክት አካል የሆኑት የወላይታ ሶዶ ቁጥር 2 - አርባ ምንጭ ቁጥር 2
+8
የኃይል ማስተላለፊያ መስመሮቹ የፍተሻ እና ሙከራ ሥራ ተጠናቀቀ .…….///……. የብሔራዊ ኤሌክትሪክ ደቡባዊ ግሪድ ማስፋፊያ ፕሮጀክት አካል የሆኑት የወላይታ ሶዶ ቁጥር 2 - አርባ ምንጭ ቁጥር 2 ባለ 230 ኪሎ ቮልት እና የአርባ ምንጭ ቁጥር 2 - አርባ ምንጭ ቁጥር 2 ባለ 132 ኪሎ ቮልት የኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች የሙከራ እና ፍተሻ ሥራ መጠናቀቁን ፕሮጀክት ጽ/ቤቱ አስታወቀ። የፕሮጀክቱ ተወካይ ሥራ አስኪያጅ አቶ አንዱዓለም መላኩ እንዳስታወቁት የመስመር ዝርጋታዎቹ አዲስ የተገነቡትን የወላይታ ሶዶ ቁጥር 2 ባለ 230 ኪሎ ቮልት የማስፋፊያ እና የአርባ ምንጭ ሁለተኛ ባለ 230 ኪሎ ቮልት አዲስ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ እንዲሁም የአርባ ምንጭ ቁጥር 1 ባለ 132 ኪሎ ቮልት ማስፋፊያ ግንባታዎችን ለአገልግሎት ዝግጁ ለማድረግ የሚያስችሉ ናቸው። ተጨማሪ ለማንበብ… https://www.eep.com.et/?amh-news=የኃይል-የማከፋፈያ-ጣቢያው-የማስፋፊያ-ሥ&lang=am 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et የካቲት 27 ቀን 2018 ዓ.ም

የኃይል የማከፋፈያ ጣቢያው የማስፋፊያ ሥራ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ …..///….. የወላይታ ሶዶ ቁጥር 2 ባለ 400/230 ኪሎ ቮልት ማከፋፈያ ጣቢያ የማስፋፊያ ግንባታ ሥራ በተያዘለት የጊ
+4
የኃይል የማከፋፈያ ጣቢያው የማስፋፊያ ሥራ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ …..///….. የወላይታ ሶዶ ቁጥር 2 ባለ 400/230 ኪሎ ቮልት ማከፋፈያ ጣቢያ የማስፋፊያ ግንባታ ሥራ በተያዘለት የጊዜ ገደብ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የብሔራዊ ኤሌክትሪክ ደቡባዊ ግሪድ ማስፋፊያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት አስታወቀ። የፕሮጀክቱ ተወካይ ሥራ አስኪያጅ አቶ አንዱዓለም መላኩ እንደገለፁት በማከፋፈያ ጣቢያው ተጨማሪ 230 ኪሎ ቮልት የኤሌክትሪክ ኃይል ማቅረብ የሚያስችል የማስፋፊያ ሥራ በማከናወን በዛሬው ዕለት ለአገልግሎት በቅቷል። በማስፋፊያ ሥራው እያንዳንዳቸው 250 ሜጋ ቮልት አምፒር የመጫን አቅም ያላቸው ሁለት ትራንስፎርመሮች ተከላ መከናወኑንም ነው የተናገሩት። ተጨማሪ ለማንበብ… https://www.eep.com.et/?amh-news=የኃይል-የማከፋፈያ-ጣቢያው-የማስፋፊያ-ሥ&lang=am 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et የካቲት 26 ቀን 2018 ዓ.ም

ማከፋፈያ ጣቢያዎቹ በከተማዉ አስተማማኝ ኃይል እንዲኖር አስችለዋል …….///…… በወላይታ ሶዶ ከተማ አገልግሎት እየሰጡ የሚገኙት ሁለቱ የኤሌክትሪክ ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎች በሶዶ ከተማ እና በዙሪያ
+7
ማከፋፈያ ጣቢያዎቹ በከተማዉ አስተማማኝ ኃይል እንዲኖር አስችለዋል …….///…… በወላይታ ሶዶ ከተማ አገልግሎት እየሰጡ የሚገኙት ሁለቱ የኤሌክትሪክ ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎች በሶዶ ከተማ እና በዙሪያው አስተማማኝ የኃይል አቅርቦት እንዲኖር ማስቻላቸውን የከተማዋ ከንቲባ አስታወቁ። ከንቲባዋ ወይዘሮ እታገኝ ኃይለማሪያም እንዳስታወቁት ለከተሞች እና ለኢንቨስትመንት መስፋፋት፣ ለሥራ ዕድል ፈጠራ እንዲሁም ለቱሪዝም ዕድገት የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ከፍተኛ ድርሻ አለው። በከተማዋ የሚገኙ ማከፋፈያ ጣቢያዎች ለኢንዱስትሪዎች እና ለአገልግሎት ሰጪ ተቋማት በቂ ኃይል እያቀረቡ እንደሚገኙ በማንሳት የኃይል አቅርቦቱ ለከተማዋ መስፋፋት፣ በኢንቨስትመንት፣ በአገልግሎት አሰጣጥ እና በነዋሪዎች የዕለት ተዕለት ኑሮ ላይ አዎንታዊ ለውጥ እያመጣ መሆኑንም ተናግረዋል። ተጨማሪ ለማንበብ… https://www.eep.com.et/?amh-news=ማከፋፈያ-ጣቢያዎቹ-በከተማዉ-አስተማማኝ&lang=am 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et የካቲት 26 ቀን 2018 ዓ.ም

ማከፋፈያ ጣቢያዎቹ በከተማዉ አስተማማኝ ኃይል እንዲኖር አስችለዋል …….///…… በወላይታ ሶዶ ከተማ አገልግሎት እየሰጡ የሚገኙት ሁለቱ የኤሌክትሪክ ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎች በሶዶ ከተማ እና በዙሪያ
+6
ማከፋፈያ ጣቢያዎቹ በከተማዉ አስተማማኝ ኃይል እንዲኖር አስችለዋል …….///…… በወላይታ ሶዶ ከተማ አገልግሎት እየሰጡ የሚገኙት ሁለቱ የኤሌክትሪክ ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎች በሶዶ ከተማ እና በዙሪያው አስተማማኝ የኃይል አቅርቦት እንዲኖር ማስቻላቸውን የከተማዋ ከንቲባ አስታወቁ። ከንቲባዋ ወይዘሮ እታገኝ ኃይለማሪያም እንዳስታወቁት ለከተሞች እና ለኢንቨስትመንት መስፋፋት፣ ለሥራ ዕድል ፈጠራ እንዲሁም ለቱሪዝም ዕድገት የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ከፍተኛ ድርሻ አለው። በከተማዋ የሚገኙ ማከፋፈያ ጣቢያዎች ለኢንዱስትሪዎች እና ለአገልግሎት ሰጪ ተቋማት በቂ ኃይል እያቀረቡ እንደሚገኙ በማንሳት የኃይል አቅርቦቱ ለከተማዋ መስፋፋት፣ በኢንቨስትመንት፣ በአገልግሎት አሰጣጥ እና በነዋሪዎች የዕለት ተዕለት ኑሮ ላይ አዎንታዊ ለውጥ እያመጣ መሆኑንም ተናግረዋል። ተጨማሪ ለማንበብ… https://www.eep.com.et/?amh-news=ማከፋፈያ-ጣቢያዎቹ-በከተማዉ-አስተማማኝ&lang=am 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et የካቲት 26 ቀን 2018 ዓ.ም

የማከፋፈያ ጣቢያውን አቅም የማሳደግ ሥራ እየተከናወነ ነው …….///………. በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በሰሜን ምዕራብ ሪጅን ሥር የሚገኘውን የአዘዞ ባለ 230 ኪሎ ቮልት የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ አ
+4
የማከፋፈያ ጣቢያውን አቅም የማሳደግ ሥራ እየተከናወነ ነው …….///………. በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በሰሜን ምዕራብ ሪጅን ሥር የሚገኘውን የአዘዞ ባለ 230 ኪሎ ቮልት የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ አቅም ለማሳደግ የሚያስችል ሥራ እየተከናወነ መሆኑን የጣቢያው ሥራ አስኪያጅ አስታወቁ። ሥራ አስኪያጁ አቶ ይገርማል ማሩ እንደገለፁት ጣቢያው አገልግሎት መስጠት ከጀመረበት 1995 ዓ.ም. ጀምሮ የአካባቢውን የኃይል ፍላጎት በማሟላት ረገድ ከፍተኛ ሚና ሲጫወት ቆይቷል፡፡ በአሁኑ ወቅት የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያውን የኦፕሬሽን አቅም ለማሳደግ በባለ 33 ኪሎ ቮልት ወጪ መስመሮች የዘመናዊ መቆጣጠሪያ ብሬከር ቅየራ ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ተጨማሪ ለማንበብ… https://www.eep.com.et/?amh-news=የማከፋፈያ-ጣቢያውን-አቅም-የማሳደግ-ሥራ-2&lang=am 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et የካቲት 25 ቀን 2018 ዓ.ም

በኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች ዘመናዊ የአሰራር ሥርዓቶችን ለጥገና ሥራዎች መተግበር ይገባል .......///….… በኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች ዘመናዊ የአሰራር ሥርዓቶችን ለጥገና ሥራዎች ተግባራዊ ማድረግ እ
+5
በኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች ዘመናዊ የአሰራር ሥርዓቶችን ለጥገና ሥራዎች መተግበር ይገባል .......///….… በኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች ዘመናዊ የአሰራር ሥርዓቶችን ለጥገና ሥራዎች ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የጀነሬሽን ቢዝነስ ዘርፍ አስታወቀ። በዘርፉ ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢንጂነር ኤፍሬም ወልደኪዳን የተመራ የባለሙያዎች ቡድን በአዳማ አንድ እና ሁለት የንፋስ ኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች የመስክ ምልከታ አድርጓል። የመስክ ምልከታው ተቋሙ የኃይል ማመንጫ ጣቢያዎቹን ውጤታማነት፣ ደህንነት እና ዘመናዊ የአሰራር ሥርዓት ለማሳደግ የጀመረው ስትራቴጂካዊ የክትትል አካል መሆኑ ተገልጿል። ተጨማሪ ለማንበብ… https://www.eep.com.et/?amh-news=በኃይል-ማመንጫ-ጣቢያዎች-ዘመናዊ-የአሰራ&lang=am 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et የካቲት 24 ቀን 2018 ዓ.ም

ለመላው ኢትዮጵያውያን በሙሉ እንኳን ለ130 ኛው የአድዋ ድል መታሰቢያ በሠላም አደረሳችሁ! ጀግኖች አያት ቅድመ አያቶቻችን ህይወታቸውን ገብረው ነፃነት እንዳቀዳጁንና ጀግንነት እንዳወረሱን ሁሉ ተቋማችን ለሀገራችን እድገት አስተማማኝ የኃይል አቅርቦት እንዲኖር ለማድረግ በርካታ መስዋዕትነት የሚጠይቁ ሥራዎችን እያከናወነ ይገኛል። ከእነዚህም መካከል በመላው ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ድጋፍ እውን የሆነው የመላ አፍሪካውያን ኩራት ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ይጠቀሳል። በህዳሴ ግድብ ላይ የተጀመረውን የድል አድራጊነት ስኬት በሌሎች ፕሮጀክቶቻችንም ላይ በመድገምና አስተማማኝ የኤሌክትሪክ አቅርቦት እንዲኖር በማድረግ ለሀገራችንን ዕድገት የበኩላችንን ድርሻ መወጣታችንን እንደምንቀጥል እምነቴ የፀና ነው። በዓሉ በሁሉም ዘርፍ የምናሸንፍበትና የአንድነት እንዲሆንልን ከልብ እመኛለሁ፡፡ አሸብር ባልቻ፣ ዋና ሥራ አስፈፃሚ

image_2026-03-01_14-50-18.png6.10 KB

ዐድዋ እና ሕዳሴ፦ ትናንት በደም፣ ዛሬ በላብ የተገነባ የሉዓላዊነት ድልድይ! 🇪🇹 በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ሁለት ታላላቅ "የማይቻል" የሚመስሉ ድሎች አሉ። አንደኛው በጠመንጃ ወራሪን ድል ያደረግንበት የዐድዋ ድል ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ በገንዘባችን፣ በዕውቀታችንና በላባችን ድህነትንና ኢፍትሐዊነትን ድል ለማድረግ በቁርጠኝነት የሰራንበት የታላቁ ኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ላይ ያስመዘገብነው ድል ነው። 🇪🇹 አባቶቻችን በዐድዋ ተራሮች ላይ ለዓለም ያስተማሩት ትምህርት "ለነፃነት ዋጋ መክፈል!" የሚል ነበር። ያ ድል ኢትዮጵያን በአፍሪካ ብቻ ሳይሆን በመላው ዓለም የተጨቆኑ ሕዝቦች ተስፋ አደረጋት። ዐድዋ ባይኖር ኖሮ ዛሬ ስለ ሉዓላዊነትና ስለ ኢኮኖሚ ነፃነት የምናወራበት የጸና ሀገር ባልኖረን ነበር። 🇪🇹 የኢኮኖሚ ነፃነት ማማ ተምሳሌት ተደርጎ የሚወሰደው የታላቁ ኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ደግሞ የዐድዋ ድል የ21ኛው ክፍለ ዘመን ቀጣይነት ማሳያ ነው። ትናንት "ቅኝ አልገዛም" እንዳልን ሁሉ፣ ዛሬ ደግሞ በሕዳሴው ግድብ አማካኝነት "የተፈጥሮ ሀብቴን በራሴ ፈቃድና ፍላጎት እንጂ በሌሎች ይሁንታ አልጠቀምም" ብለን የመልማት መብታችንን ለዓለም አረጋግጠናል። የግድቡ ኃይል ማመንጨት መጀመር ኢትዮጵያ ከድህነት ቀንበር ለመውጣትና የአፍሪካ የኢኮኖሚ ብርሃን (Economic Beacon) ለመሆን የጀመረችው ጉዞ ስኬት ነው። 🇪🇹 ትናንት አባቶቻችን አጥንታቸውን ከስክሰው ደማቸውን አፍሰው ይህችን ሀገር አቆይተውልናል፡፡ የዛሬው ትውልድ ደግሞ ላቡን አፍሶ ግድቡን በመገንባት ለኢትዮጵያ ብሩህ የተስፋ አድማስ ፈንጥቋል። የታላቁ ኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የዐድዋ ድል ባለቤት የሆነችውን ኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ባለድል እና የመጪው ጊዜ ኃያል የማድረግ ቃል ኪዳን ነው። ስለሆነም ዐድዋን ማክበር ማለት የአባቶችን ጀግንነት ማድነቅ ብቻ አይደለም፤ እንደ አባቶቻችን ለሀገር የሚጠቅም አሻራ ማሳረፍም ጭምር ነው። የሕዳሴው ግድብ የሁላችንም ኩራትና የዐድዋ መንፈስ በተግባር የገለጽንበት የታሪካችን አዲሱ ምዕራፍ ነው! የዐድዋ የድል መንፈስ በሕዳሴው ግድብ ላይ ተደግሟል! 🇪🇹 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et የካቲት  22 ቀን 2018 ዓ.ም

photo content

ከዐድዋ እስከ ህዳሴ - የክብርና የሉዓላዊነት ቀጣይነት! 🇪🇹🛡🌊 "ዐድዋ የአፍሪካ ድል ነው። አፍሪካውያን ቅኝ ግዛት ፈጽሞ እንደማይቀበሉ ያሳዩበት ድል ነው።" (የመደመር መጽሐፍ፣ ገጽ 266) የዘንድሮው የዐድዋ ድል በዓል “ከአኩሪ ታሪክ ወደ ብሩህ አድማስ" በሚል ታላቅ መሪ ቃል ይከበራል። ይህ መሪ ቃል ትናንት በጀግኖች ደምና አጥንት የተጠበቀችውን ሀገር ዛሬ በዘላቂ ሰላምና በልማት ወደ ሁለንተናዊ ሉዓላዊነትና ከፍታ ለማሻገር ያለንን ፅኑ ቁርጠኝነት የሚገልጽ ነው። ዐድዋ እና ህዳሴ፦ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች 📌 የዐድዋ ድል ወታደራዊ ድል ብቻ ሳይሆን፣ ኢትዮጵያውያን ለፍትሕና ለእኩልነት ያላቸውን ጽኑ አቋም ለዓለም ያሳዩበት ነው። ዛሬም ይህ የዐድዋ መንፈስ በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ላይ በደመቀ ሁኔታ ተደግሟል። 🇪🇹 አባቶቻችን በዐድዋ ምድር በ"ቅኝ አልገዛም!" ብለው ወራሪን እንዳሳፈሩ ሁሉ፣ ዛሬም የታላቁ ኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅና ኃይል ማመንጨት መጀመሩ ኢትዮጵያ በሀብቷ የመጠቀም ተፈጥሯዊ መብቷን ለማስከበር ያሳየችው "የዘመኑ ዐድዋ" ነው። ይህ ግድብ ኢትዮጵያ ኢፍትሐዊነትን እና የኢኮኖሚ የእጅ አዙር ቅኝ አገዛዝን የማትቀበል ሀገር መሆኗን ዳግም ለዓለም ያረጋገጠችበት ትልቅ ሀገራዊ ድል ነው። 🇪🇹 ጀግኖች አባቶቻችን ነፃ ሀገር አውርሰውናል፤ እኛ ደግሞ የበለፀገችና በብርሃን የተሞላች ሀገር ለልጆቻችን ለማውረስ በሕዳሴው ግድብ መሠረት ጥለናል። ይህ ጉዞ ከአኩሪ ታሪክ የተነሳና ወደ ብሩህ አድማስ የሚያመራ የድል ሰንሰለት ነው። ትናንት በጦር ሜዳ ሉዓላዊነታችንን አስከብረን እንዳልተንበረከክን፣ ዛሬ ደግሞ በልማትና በኢኮኖሚ ነፃነታችንን በማረጋገጥ ወደ ሁለንተናዊ ከፍታ እየተጓዝን ነው። የሕዳሴው ግድብ የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን፣ ልክ እንደ ዐድዋ ሁሉ የጥቁር ሕዝቦችና የመላው አፍሪካውያን የልማት ተስፋና ኩራት ነው። 🇪🇹 ስለሆነም ዐድዋ የነፃነታችን መጀመሪያ እንደሆነው ሁሉ የታላቁ ኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብም የኢኮኖሚ ከፍታችን እና የመቻላችን ማረጋገጫ ነው። ትናንት በጥይት ድል አደረግን፤ ዛሬ በዕውቀትና በሀብታችን ድል እያደረግን ነው! ክብር ለዐድዋ ጀግኖች! ሞገስ ለሕዳሴ ግድብ ገንቢዎች! 🇪🇹 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et የካቲት  22 ቀን 2018 ዓ.ም

photo content

የተግባር ፈተና ጥሪ ማስታወቂያ ..........///.......... የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በቧንቧ ጥገና ሰራተኛ (Plumber Technician) የስራ መደብ ሰራተኞችን አወዳድሮ ለመቅጠር ጥ
የተግባር ፈተና ጥሪ ማስታወቂያ ..........///.......... የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በቧንቧ ጥገና ሰራተኛ (Plumber Technician) የስራ መደብ ሰራተኞችን አወዳድሮ ለመቅጠር ጥር 15 ቀን 2018 ዓ.ም የውጭ ማስታወቂያ ማውጣቱ ይታወቃል፡፡ ስለሆነም መስፈርቱ አሟልታችሁ ከተመዘገባችሁት ተወዳዳሪዎች መካከል የፅሁፍ ፈተና ተፈትናችሁ የማለፊያ ነጥብ ያመጣችሁ ከተራ ቁጥር 1 እስከ 19 የስም ዝርዝራችሁ የተገለጸው ተወዳዳሪዎች የካቲት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 የተግባር ፈተና ስለሚሰጥ በሰው ኃይል ቅጥርና ምደባ ቢሮ እንድትገኙ እናሳውቃለን፡፡ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et የካቲት  19 ቀን 2018 ዓ.ም

photo content

የፈተና ጥሪ ማስታወቂያ ..........///.......... የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በኤሌክትሪክ መኪና ቻርጅ አድራጊ ቴክኒያሽን (Technician-I EV Battery Charger) የስራ መደ
የፈተና ጥሪ ማስታወቂያ ..........///.......... የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በኤሌክትሪክ መኪና ቻርጅ አድራጊ ቴክኒያሽን (Technician-I EV Battery Charger) የስራ መደብ ሰራተኞችን አወዳድሮ ለመቅጠር ጥር 08 ቀን 2018 ዓ.ም የውጭ ማስታወቂያ ማውጣታችን ይታወቃል፡፡ በዚሁ መሰረት ከዚህ በታች ስማችሁ የተገለጸው አመልካቾች በሙሉ የካቲት 26 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት ማንነታችሁን የሚገልጽ የታደሰ መታወቂያ በመያዝ ኮተቤ ብረታ ብረት ፊትለፊት በሚገኘው በዋናው መ/ቤት የስብሰባ አዳራሽ የጽሁፍ ፈተና የሚሰጥ በመሆኑ ለፈተና እንድትገኙ እናሳስባለን፡፡ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et የካቲት 19 ቀን 2018 ዓ.ም

የታሪፍ ድርድር ማዕቀፍን ለማዘመን የሚያስችል የጥናት ማስጀመሪያ ፕሮግራም ተካሄደ ….///…. የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከደቡብ ኮሪያ ሪፐብሊክ መንግሥት ጋር የኤሌክትሪክ ታሪፍ ድርድር ማዕቀፍን ለማዘመን የሚያስችል የጥናት ማስጀመሪያ መርሀ ግብር በዛሬው ዕለት አካሂዷል፡፡ በጥናት ማስጀመሪያ መርሀ ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር አሸብር ባልቻ ኢትዮጵያና ደቡብ ኮሪያ የኃይል ልማት ዘርፍን ለማሳደግና ለማዘመን በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ በትብብር ሲሰሩ መቆየታቸውን ተናግረዋል፡፡ ኢትዮጵያ ከታዳሽ ኃይል ኤሌክትሪክ ለማመንጨት የሚያስችል ሰፊ ሀብት ቢኖራትም አሁን ላይ የኃይል ተደራሽነት ሽፋኑ 54 በመቶ ብቻ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ ተጨማሪ ለማንበብ… https://www.eep.com.et/?amh-news=የታሪፍ-ድርድር-ማዕቀፍን-ለማዘመን-የሚያ&lang=am 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et የካቲት 17 ቀን 2018 ዓ.ም

photo content
+2

photo content
+9