📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜
Kanalga Telegram’da o‘tish
📚📚እንኳን በደህና መጡ📖📗🧾 ➥ እዚህ ቻናል ላይ የተለያዩ የ አማርኛ እና እንጊሊዘኛ ..... መፅሀፍትን በ 📙 Pdf እና ትረካዎችን እና ሌሎችም ጠቃሚ ነገሮችን ያገኛሉ። 📖 ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል‼️ B-) :-መረዳዳት ቢኖር ሁሉም ቢተባበር 100K ይደርስ ነበር ። For any comment @Meki3
Ko'proq ko'rsatish2 297
Obunachilar
+324 soatlar
+117 kun
+2830 kun
Postlar arxiv
2 297
❤️ የሂባዋ ናርዶስ ❤️
❤️ልብ አንጠልጣይ ታሪክ❤️
ፅሀፊ :ፉዓድ ሙና
ክፍል 4⃣
ያለፉትን ቀናት በተደጋጋማ ሲደውል ስልክ አላነሱለትም ነበር። የሂባን ቤተሰቦች ለመተዋወቅ ቋምጦ ስልኳን በጉጉት ሲጠብቅ ቢውል ቢያድር ህልም ሆኖ ቀረበት። ውስጡ በጣም ተረብሿል። ናርዶስና ሂባ ሺቲያቸውን እንደለበሱ ናርዶስ በነጠላ ፀጉሯን ሸብ አድርጋ ፣ ሂባ ደግሞ ሂጃቧን ራሷ ላይ በደንቡ ጠምጥማ ከሴቶች ዶርም መግቢያ ትንሽ ፈንጠር ብሎ የቆመው ኢምራን ጋ ሄዱ።
ኢምራን ሂባን እንዳየ ፊቱ በፈገግታ ደመቀ። ለሁለት ቀን ዘግታው እንደቆየች ሁሉ ሳይረሳው አልቀረም።
ሂቡዬ" ቢጎርሳት ደስ ይለዋል።
‹‹ኢምሩ ... ›› ሳግ ተናነቃት።
‹‹ናርዲ›› ተቁለጨለጨ።
‹‹እ ሰውየው››
የሂባን የአይን ክዳን እንባዋ አሸነፈው። ተርገበገበ። እንባዋ ጉንጮቿ ላይ ተኛ። አተነፋፈሷ ፈጠነ። ትከሻዋ ከፍ ዝቅ ማለት ጀመረ። ተንሰቀሰቀች። ናርዶስ ሂባን አቅፋ ማባበል ጀመረች። ኢምራን ጨረቃ ላይ የተጣለ መሰለው። ሁሉም ነገር አዲስ ሆኖበታል።
‹‹ሂባዬ? ምን ሆንሽብኝ?›› እንባው ቢታገለውም ወንድ መሆኑን አስታወሰው። ወንድ ሆኖ ሰው ፊት ማልቀስ ከመንጋው ባህል ጋ ይጋጫል ሲል አሰበ።
ናርዶስ ሂባን ትንሽ ካረጋጋቻት በኋላ ማስረዳት ጀመረች።
‹‹ኢምሩ ታፈቅርሀለች ግን ቤተሰቦቿ ከሌላ ሰው ጋር ጋብቻዋን ተዋውለው ጨርሰዋል። ሳትወድ በግዷ ካንተ ተነጥቃለች።›› በአጭሩ አረዳችው።
ኢምራን ጭንቅላቱ ሲከብደው ተሰማው። ቁጢጥ አለ። እሱ እኮ ኒካህ ካሰሩ በኋላ የት መኖር እንዳለባቸው ከእናቱ ጋር ተከራክሯል። እንዲህ ያለ ዱብዳ ይገጥመኛል ብሎ በፍፁም አላሰበም። እህቶቹ ኒካሁ ከታሰረ በኋላ ቶሎ ወደ ደሴ ይዟት እንዲመጣ ቃል አስገብተውታል። ጉጉታቸውን አላበርድም ብሎ ግን ጭራሹን አልገመተም ነበር። የለበሰው ቱታ እና ቲሸርት ሰውነቱ ላይ የሌለ ፣ የተራቆተ የተራቆተ ፤ ልቡ አካባቢ ንፋስ የገባ መሰለው። ሆዱ ተረበሸ። እንባው አሸነፈው። ሂባ እንባውን ስታይ መንሰቅሰቋ በረታ። ሰው እስኪታዘብ ድረስ ረዥም ሰዓት ባሉበት ረግተው አነቡ። ናርዶስም አብራ ታነባለች።
ኢምራን እንባውን ጠራርጎ ከጨረሰ በኋላ ‹‹ሂባዬ የሚለወጥ ነገር ካለ በማንኛውም ሰዓት ንገሪኝ። ሁሌም እወድሻለሁ። የሚያገባሽ ሰው እድለኛ ነው። የምር ... ደሞ እንደሚያስደስትሽም ተስፋ አደርጋለሁ። መልካም ህይወት ሂባዬ ... መልካም ህይወት!›› ትቷቸው ወደ ወንዶች ዶርም ሩጫ በሚመስል እርምጃ ተፈተለከ። ሂባ መንሰቅሰቋ በረታ። ናርዶስ አብራ እያለቀሰች አቅፋ እያባበለቻት ወደ ዶርም ገቡ።
ሂባ ፈጣሪ የቸራትን ውብ እድል ያበላሸች መሰላት።ቤተሰቦቿ አበሳጯት። ፍርሀት ፍርሀት አላት። ‹‹ለምን ሳፈቅረው ይኼን አላሰብኩም? ለምን ሲወደኝ ሁኔታዎች ምቹ አለመሆናቸውን አልተገነዘበም?›› ራሷን ጠየቀች። ፍቅር በምክንያት ይከሰት ፣ በስሌት ይፈጠር ይመስል። መልሱ ለራሷም አልገባትም። የገባት አንድ ነገር የወደደችውን እና የወደዳትን ሰው ለቤተሰቧ ደስታ ብላ መሰዋቷን ነው። ግን ደግሞ ….. ትፈራለች።
ላይኩ 50 ከሞላ አንድ ክፍል ይለቀቃል
.
.
.
.
ይቀጥላል
ክፍል 5⃣
2 297
.
የምርቃታቸው ቀን ደስታ በሂባ ስብራት ተቸልሶ እንደደበዘዘ አለፈ። በቀጣዩ ቀን ከሰዓት በኋላ የሁለቱም ቤተሰቦች ወደ አዲስ አበባ በአንድነት ተመለሱ። ሂባ እና ናርዶስ መጨራረስ ያለባቸውን የመልቀቀያ ፎርም ማስሞላት ስላለባቸውና ጊዜያዊ ድግሪያቸውን (temporary degree – Tempo) መቀበል ስለሚኖርባቸው አብረዋቸው አልሄዱም።
ማክሰኞ ጠዋቱን ኢምራን ሴቶች ዶርም መጥቶ አስጠራቸው። ያለፉትን ቀናት በተደጋጋሚ
.
.
.
.
ይቀጥላል
ክፍል 4⃣
2 297
❤️ የሂባዋ ናርዶስ ❤️
❤️ልብ አንጠልጣይ ታሪክ❤️
ፅሀፊ :ፉዓድ ሙና
ክፍል 3⃣
የሂባ አባት አቶ ጀሚል እና እናቷ ወ/ሮ ዘምዘም የሂባን ታናሽ ወንድም ኢክሪማን አስከትለው ነበር የመጡት። የናርዶስ አባት አቶ ገበየሁ እና እናቷ ወ/ሮ ዘርፌ ደግሞ የናርዶስን የአክስት ልጅ ኤደንን ይዘው መጥተዋል። ሀይሌ ሪዞርት ገብተው ምሳቸውን ከበሉ በኋላ ናርዶስ ዙሪያውን ጠረጴዛውን የከበቡትን ቤተሰቦቿን እና ጎረቤቶቿን እያየች ‹‹የዛሬውን ቀን ልዩ የሚያደርገው ...›› ስትል ሁሉም ትኩረታቸውን ወደሷ አደረጉ። የሂባ እናት ወ/ሮ ዘምዘም ፈገግ ብለው ‹‹ናርዶሴ እስኪ እንደውም እኔን አስቀድሚኝ ለየት የሚያደርገውን እኔ ልናገር›› አሉ።
‹‹እሺ ናንዬ ምን አለ አንቺ ጋ?››
‹‹እኔ ጋ ያለውማ .... የዛሬዋ ተመራቂያችን ቀጣይ ሙሽራ መሆኗ የሚበሰርበት መሆኑ ነው። ከተመለስን በኋላ ለሂባችን ኒካህ እናስራለን።››
ናርዶስ ፈገግታዋን ግራ መጋባት እየወረሰው ፣ ሂባ የኢምራንን ጉዳይ ነግራቸው ይሆን ብላ ግራ እየተጋባች ወደ ሂባ ስትዞር የሂባ ፊት በአንዴ ደም ሲለብስ አስተዋለች። የፊቷን የተፈጥሮ ቅላት ቁጣዋ ሲያግዘው ፍም መሰለ። ናርዶስ ያሰቡት ኢምራንን የማስተዋወቅ እቅድ እየተጨናገፈ እንደሆነ ተሰማት። ድምጿ እየተሰባበረ ‹‹ከማን ጋር ነው የምታስረው?›› አለች። ወ/ሮ ዘምዘም የሂባ መቆጣት ፣ የናርዶስ መደናገጥ ግራ እየገባቸው ‹‹ዚያድ የጋሽ ሳሊም ልጅ ፣ ዋናው መንገድ ጋ መኪና መሸጫ ያለው አወቃችሁት? ባለፈው ሽማግሌ ልኮ ነበር። ያው በምንም አይታማም እሱ! ለነሀሴ ብለነዋል። ትምህርታችሁ ላይ እንድታተኩሩ ብለን ነው ያልነገርናችሁ!›› አሉ። ናርዶስ ሂባ የመናገር አቅሟ መሰለቡን ልብ ካለች በኋላ ለመከራከር ወደ ወ/ሮ ዘምዘም ዞረች፡፡
‹‹ግን እኮ ናንዬ ሂባ የምትወደው ሰው አለ። ዛሬ ልታስተዋውቃችሁ አስባ ነበር።›› አቶ ጀሚል ጣልቃ ገቡ፡፡ ‹‹አይ ናርዶሴ የናንተው ቢጤ ተማሪ ይሆናል እኮ ይኼኔ!››
‹‹አዎ ነው ጋሼ። ሂባ ከወደደችው ተማሪ ይሁን ሌላ ምን ለውጥ አለው? ደሞ ተመራቂ ነው።››
‹‹አይሆንም ገና በእግሩ እስኪቆም ማገዶ ይፈጃል። እስከዛ ደግሞ የሷ እድሜ አይቆምም። ፍቅር ምናምን እያላችሁ ድራማ አትስሩ። እኛ ስንጋባ ጭራሽ የት እንተዋወወቅ ነበር? አይደል እንዴ ገበየሁ? ዘምዘሜ?›› ወደ ግራ እና ቀኝ እየተዟዟሩ ድጋፋቸውን በአይናቸው ለመኑ። ‹‹ልክ ነው ጨዋታ አያስፈልግም። አሁን ልጅ አይደለሽም አግብቶ መሰብሰብ ነው። ቤተሰብ ያመጣው ነው ደሞ ጥሩ!›› ጋሽ ገበየሁ ተደረቡ።
ሂባ ድምጿን ሳግ እያጠረው ‹‹እንዴ ገብሽ አንተም?›› አለች። ኤደን ክርክራቸውን በደምብ ካዳመጠች በኋላ ጥያቄዋን ሰነዘረች። ‹‹እንዴ ሰው ካልወደደው ሰው ጋር እንዴት ይኖራል?›› ወ/ሮ ዘምዘም እና አቶ ገበየሁ ለመልስ ተሽቀዳደሙ። ‹‹ከተጋቡ በኋላ መውደዷ የት ይቀራል?›› ጋሽ ገበየሁ የሰነዘሩት መልሳማ ጥያቄ ነበር።
‹‹ባትወደውስ?››
‹‹ትወደዋለች።›› በአንድነት ጮኹባት።
‹‹የምወደው ልጅስ?›› ሂባ ቀዩ ፊቷ ላይ ካሉት ሁለቱ ትላልቅ አይኖቿ የእንባ ዘለላዎቿ እየተሽቀዳደሙ በመጠኑ ሰልከክ ያለውን አፍንጫዋን አቋርጠው ከእንጆሪ ከንፈሮቿ ላይ እያረፉ ጠየቀች።
‹‹ከአሁን በኋላ ልጅነት የለም ወደድኩ ምናምን አይሰራም። አዲስ አበባ ስንሄድ ትረሺዋለሽ። ደሞ የዘንድሮ ፍቅር!›› ወ/ሮ ዘምዘም እንደመቆጣት እያሉ ተናገሩ።
ወ/ሮ ዘርፌ እና ኢክሪማ ዝም ብለው ከመከታተል ውጪ ቃል አልተነፈሱም። ሁለቱም ውስጥ ተመሳሳይ ስሜት አለ። የምትወደውን ብታገባ ደስ ይላቸዋል። ሆኖም ግን ጉዳዩ ሽማግሌ ተልኮ ቀን የተቆረጠበት ስለሆነ መቃወማቸው ለውጥ እንደሌለው አስበው ዝምታን መርጠዋል። ናርዶስ የፈራችው እንደደረሰ ገባት። ድሮውንም የወ/ሮ ዘምዘምን ፀባይ ስለምታውቅ እንቅፋት እንደምትሆን አስባ ነበር። በዚህ ፍጥነት ይሆናል ብላ ግን አልገመተችም።
.
ሂባ እጅጉን ግራ ገብቷታል። ህልሟ ሁሉ ሲተን ታያት። ሁሌም ከአእምሮዋ የማይጠፋው የኢምራን ንግግር ታወሳት። ‹‹ሳገባሽ አንቺ የኔ ነሽ። እኔም ያንቺ ብቻ ነኝ። ለአካልሽ ብቻ ሳይሆን ለህልምሽ መፋፋት እና መሳካትም አጋርሽ እሆናለሁ። ሁሌም አዕምሮሽን ለማርካት የምታደርጊውን ጥረት አግዝሻለሁ። ከሁሉም በላይ እረዳሻለሁ። የአልጋ ብቻ ሳይሆን የሁሉም ነገር ባልሽ እሆናለሁ።›› ነበር ያላት። ለሱ ያላትን ፍቅር ካፈረጠሙባት ንግግሮቹ ዋነኛው ይኼ ነበር። ህልሟ በትዳር ምክንያት እንደማይጨናገፍ ፣ በኬሚካል ኢንጅነሪንግ መስክ ለመድረስ ያለመችው ከፍታ ላይ ልትደርስ ማረጋገጫ ሰጥቷት ነበር። እንደሱ ማንም ሊረዳት እንደማይችል ታውቃለች። ዛሬ ተራራውን ህልሟን በአንዴ ዱቄት የሚያደርግ ዱብዳ ወድቆባታል። ያላት ምርጫ ሁለት ነው። ቤተሰቦቿን አሊያም ኢምራንን መክዳት። ሁለቱም ከብዷታል።
የሀይሌ ሪዞርት ቆይታቸውን እንደጨረሱ በቀጥታ ያመሩት ወደ ፍቅር ሀይቅ ነበር። ናርዶስም ሂባም ስሜታቸው ቢረበሽም ቤተሰቡን ላለማስቀየም ሲሉ አብረው ለመሆን እየሞከሩ ነው። ፍቅር ሀይቅ ሲደርሱ በርካታ ተመራቂዎች ከቤተሰቦቻቸው ጋር ሆነው ሀይቁ ላይ እየተንሳፈፉ ነበር። ፍቅር ሀይቅ አይን ማየት የሚችለው ያህል ተንጣሎ ፣ ከውስጡ በበቀለው ሳር ተውቦ ፣ አሳ ፣ ጉማሬ ፣ ዘንዶውን አቻችሎ በውስጡ እንደያዘ በጨዋ ደንብ እንግዳዎቹን ያስደስታል።
ለግማሽ ሰዓት ያህል የሚለበልበውን የሀዋሳን ፀሀይ ሀይቁ ዳር ቆመው ካስተናገዱ በኋላ ጀልባው ላይ ወጥተው መንሳፈፍ ጀመሩ። ዳክዬዎች ፣ የተለያየ አይነት ቀለም ያላቸው አሞራዎች ብዙ ብዙ የተፈጥሮ ጥበቦችን ይታዘባሉ። ሂባ እና ናርዶስ ግን የሂባ ደስታ መነጠቅ ብቻ ይታያቸዋል። የጀልባው የመጨረሻው ወንበር ላይ ተቀምጠው ማንሾካሾክ ጀመሩ።
‹‹ሂቡ ምን አሰብሽ?››
‹‹ጨንቆኛል ምንድነው ማድረግ ያለብኝ?››
‹‹በቃ ለኢምራን የተፈጠረውን በእርጋታ አስረጂው!››
‹‹ምን ብዬ? ክጄሀለሁ ብዬ?›› ሳታስበው ድምጿ ከፍ አለ። ቤተሰቦቿ በተፈጥሮ ውበት ተደምመው በጩኸት እያደናነቁ ነበርና አልሰሟትም።
‹‹ድምፅሽን ቀንሺ! አልከዳሽውም እኮ! በቃ የተፈጠረውን ንገሪው። ትሞቻለሽ እንዴ? ወይስ ሌላ ያሰብሽው አማራጭ አለ?››
‹‹እሱ እኮ በጣም ነው የሚወደኝ።››
‹‹እና ይዘኸኝ ጥፋ ልትይው ነው?››
‹‹አላውቅም። ምንም ቢሆን ግን አባዬ እንዲያዝንብኝ አልፈልግም፡፡ እኛን እዚህ ለማድረስ የሆነውን አውቃለሁ፡፡ እሱን መካድ አልችልም፡፡››
ሁለቱም በሀሳብ ሰጠሙ። ኢምራንን እንደበደሉት ተሰማቸው።
‹‹ይዘኸኝ ጥፋ ብለው ራሱ ወዴት ይዞኝ ይጠፋል? ለራሱ ከቤተሰብ ድጎማ አልተላቀቀም። እኔም እንደዛው።››
‹‹ቢችል ኖሮ ናንዬን እና እኛን ትተሽ ልትጠፊ ነበር?›› ናርዶስ ተቆጣች።
‹‹እኔንጃ ናርዲዬ››
‹‹ያን ያህል እንኳ ራስ ወዳድ አይደለሽም።››
ዝምታ ወረሳቸው። ናርዶስ ፊቷ ደመነ። ለወትሮ በፈገግታ የሚሰረጉደው ጉንጯ እንደጨለመ ሰረጎደ። አነባች። ሂባ በድንጋጤ ‹‹ናርዲ እንዴ?›› አይኖቿ በተማፅኖ ተቁለጨለጩ። ተቃቀፈው አነቡ። ይህ ሁሉ ሲሆን ከወ/ሮ ዘርፌ እና ከኢክሪማ በቀር ያያቸው አልነበረም።
2 297
❤️ የሂባዋ ናርዶስ ❤️
❤️ልብ አንጠልጣይ ታሪክ❤️
ፅሀፊ :ፉዓድ ሙና
ክፍል 2⃣
ከቀኝ ወደ ግራ ይዞራል። ተመርቃችኋል ይባላሉ። ከዚህ በኋላ የእውነት ከህይወት ጋር መፋጠጥ የሚጀምሩበት ጊዜ ነው። ናርዶስ የኢምራን እና የሂባ ፍቅር እጅጉን አሳስቧታል። ‹‹ናንዬ ምን ትላት ይሆን?›› እያለች በውስጧ ትብሰለሰላለች። ‹‹ስንት ሰዓት ሆነ?›› ሀሊማ ሰግዳ ጨርሳ መስገጃዋ ላይ ተቀምጣ አውራ ጣቷን በጣቶቿ ክርከሮች ላይ እያርመሰመሰች የምትዘክረውን ሂባን እያየች ጠየቀች። ናርዶስ ቀደም ብላ ‹‹አስራአንድ ከሀያ ሆኗል። በቃ ተነሺ እንዘገጃጅ በጊዜ ቦታችሁን መያዝ አለባችሁ ምናምን እያሉ ሲዘፍኑ ነበር!›› አለች። አራቱም ከአልጋቸው ተነስተው ከተጣጠቡ በኋላ ዶርሙ ውስጥ መኳኳሉ ደራ። አንዷ የአንዷን ፀጉር ማስተካከል ፣ አንዷ አንዷን ማለባበስ ..... ውክብ አሉ። ውክቢያው አንድ ሰዓት ሊሞላው ሲቃረብ ተዘገጃጅተው ጨረሱ። ከተዋበው ቀሚሳቸው ላይ የምርቃት ጋወን ደረቡ ፣ ኮፍያ ደፉ። ከሶስቱ አጠር ያለ ቀሚስ የለበሰችው ሀና ብቻ ነች። ናርዶስን ጨምሮ የቀሩት ቁርጭምጭሚታቸውን የሸፈነ አንድ አይነት ቀሚስ ለብሰዋል። የሀና አጠረ እንጂ ተመሳሳይ ነው። በስልካቸው ፎቶ ለመነሳት የሚረዳቸውን ዱላ (Selfi stick) ከስልካቸው ጋር አጠማምደው በተመሳስሎ እንደነገሱ ወደ ምረቃው ስታዲየም ለመውሰድ ተማሪዎችን ወደሚጠባበቀው አውቶብስ አቀኑ። ለየት ያለ ስሜት ውርር ሲያደርጋቸው ይታወቃቸዋል። ከተደረደሩት አውቶብሶች ፊት በአንድ ከኋላ ክፍት መኪና ላይ የተሰቀለው ስፒከር ‹‹እንኳን ደስ አላችሁ›› የሚለውን ታዋቂውን የምርቃት ዜማ ያስደምጣል። እንባ ሲያንቃቸው ተሰማቸው። አምስት አመታትን ምቹ ባልሆነ ሁኔታ ብዙ መሰናክል አልፈው ያገኟት ቀን ናትና የዛሬው ደስታ የሚያስታውሳቸው ያለፈውን መከራ ነው። አውቶብሱ ውስጥ ገብተው እንደተቀመጡ ኢምራን ከሁለት ጓደኞቹ ጋር ጥቁር ሰማያዊ ሱፉ ላይ የምርቃት ጋወኑን እንደደረበ ሲፍለቀለቅ መጣ። ናርዶስ ከተቀመጡበት የአውቶብሱ የመጨረሻ ወንበር አይኖቿን በወንበሮቹ መሀል ሰንጥቆ ወደ እነርሱ የሚመጣው ኢምራን ላይ ጥላ ‹‹ሚስኪኑ ውድሽ መጣ!›› አለች። ኢምራን ከሂባ አጠገብ ተቀመጠ። ሁለቱ ጓደኞቹ ከፊት ለፊቱ ተቀመጡ። ፎቶ እየተነሱ እየተሳሳቁ ሀዋሳ ስታዲየም ደርሰው ቦታ ቦታቸውን ያዙ። የተለመደው በተማሪው የማይደመጥ ንግግር እየተደረገ እነሱም መድረክ ላይ ሰው መኖሩንም ዘንግተው ፎቶ በመነሳት ከተጠመዱ በኋላ የኢትዮጵያ ህዝብ ብሔራዊ መዝሙርን በአንድነት ሳግ እያነቃቸው ዘምረው የምርቃት ስነ ስርዓቱ ተጠናቀቀ። ተመራቂዎቹ ልብ ሰጥተው ያዳመጡት መነሳነሳቸውን ከቀኝ ወደ ግራ አዙሩ ሲባልና መዝሙር ዘምሩ ሲባል ብቻ ነበር። መነሳነሳቸውም ዞረ። መመረቃቸውም ተበሰረ።
የምርቃት ስነ ስርዓቱ እንደተጠናቀቀ ሁሉም ወደ ቤተሰቡ ተበታተነ። የናርዶስ እና የሂባ ወላጆች በአንድነት እየጠበቋቸው ነበር። አበባው ተበርክቶላቸው ምሳ ሊበሉ ወደ ሀይሌ ሪዞርት ለመሄድ ከስታዲየሙ ሲወጡ ኢምራን ከቤተሰቦቹ ጋር ቆሞ ሂባን ሲጠብቃት ተገናኙ። የስልክ ኔትወርክ እጅጉን ያስቸግር ስለነበር ደውሎ ሊነግራት አልቻለም። አጋጣሚ ሆኖ ባያገኛት ኖሮ ምናልባትም ሊገናኙ የሚችሉት ወደ ግቢ ከተመለሱ በኋላ ነበር። ኢምራን ቀድሞ ሁሉንም ነገር ለቤተሰቦቹ ተናግሮ ነበረና ልክ እንዳገኛት ጠርቶ ከቤተሰቦቹ ጋር አስተዋወቃት። አንገቷን እንደደፋች ተዋውቃቸው ቆመው ወደሚጠብቋት ቤተሰቦቿ ተመለሰች። ሂባ ኢምራንን ማታ እራት ሲበሉ ከቤተሰቦቿ ጋር ልታስተዋውቀው አስባለች። ጎረቤታሞቹ የሂባ እና የናርዶስ ቤተሰቦች ድምቅ እንዳሉ ምሳቸውን ለመብላት እና በዛውም ለመዝናናት ወደ ሀይሌ ሪዞርት አቀኑ።
.
.
.
.
ይቀጥላል
ክፍል 3⃣
2 297
❤️ የሂባዋ ናርዶስ ❤️
❤️ልብ አንጠልጣይ ታሪክ❤️
ፅሀፊ :ፉዓድ ሙና
ክፍል 1⃣
ህይወት ሰንሰለት ናት። ከአንዱ ወደ አንዱ ክስተት በሽግግር የተሞላች፣ ሞት የሚባል መቀስ ብቻ ከሽግግር የሚገታት፣ ህይወት በፍርግርጓ የተሳለች ፣ በመልካም በመጥፎ የተኳለች ፤ አድካሚ ሰንሰለት ናት። ይኸው ትናንት ልጅ ነበሩ። ከሱቅ ደስታ ከረሜላ እኩል የሚገዛላቸው ፣ አላፊ አግዳሚው በየተራ እያነሳ ከንፈሩን እያሞጠሞጠ የሚያጫውታቸው ፣ ለአንዳቸው ብቻ የተደረገ ለሌላቸው አለመደረጉ ነውር የሚመስላቸው ፣ ባለ ንፁህ ልብ ህፃናት ነበሩ።
የህይወት ሰንሰለት ከጨቅላነት ወደ ታዳጊነት ሲያዛውራቸው ፣ የደንብ ልብሳቸውን ለብሰው ትምህርት ቤቶችን ሲያምሱ ፣ በቀለም ዳብረው ከከፍተኛ የትምህርት ተቋም ሲገቡ እና ለዛሬዋ የምርቃት ቀናቸው ሲበቁ የሁለቱ ሰንሰለት አብሮ የተገመደ ነበር።
የአብሮነታቸው ብርታት ያስቀናው የጣሊያን ሰፈር ሰው ሁሉ ‹‹አንድ ወንድ ለሁለት እንዳያፈቅሩ ብቻ!›› እያለ የህብረታቸውን ስር መስደድ ሲመሰክር ፣ ‹‹ምን የባረካቸው ናቸው?›› እያለ ሲቀድሳቸው ይኸው ዛሬም አሉ። ከመልካቸው ውጪ የሚለያዩት በሀይማኖታቸው ብቻ ሳይሆን አይቀርም። ድሮ ድሮ ልጅነት ነገሮችን በመለየት የወጣትነት ቀለም መልኩ ሳይደበዝዝ በፊት ሂባ ከእናቷ ጋር ለጁምዓ ስግደት ወደ መስጂድ ስትሄድ ናርዶስ አብሬ ካልሄድኩ ብላ አልቅሳለች። ናርዶስ የጥምቀት ዕለት ከላይ እስከ ታች በነጠላ እና በሀበሻ ቀሚስ ተውባ ታቦት ለመሸኘት ከእናቷ ጋር ስትሄድ አብሮ ለመሄድ የምትቋምጠው ሂባ በእናቷ ስትከለከል ያነባችውን መቼም አትረሳውም። የሂባ ኡስታዝ የሰፈሩን ሙስሊም ህፃናት ሰብስበው እነሂባ ቤት ቁርዓን ሲያስተምሩ ናርዶስም አብሮ የመማሩን እድል አግኝታለች። መከልከል የደከማቸው ቤተሰቦቿ አረብኛ ቋንቋ እንድታውቅ ይረዳታል ብለው በመልካም ሰበብ ልባቸውን አሳርፈውት ነበርና የአረብኛ ፊደላትና ቁጥሮችን ከማወቅ አልፋ ከቁርዓን አጫጭሮቹ ምዕራፎች ውስጥ ከስድስት ምዕራፍ በላይ ተምራለች።
የከፍተኛ ትምህርት ተቋም ለመግባት የዩኒቨርሲቲ ምርጫ ሲሞሉ የሁለቱም ወረቀት ከግል መረጃቸው በቀር የተለያየ አልነበረም። ፈጣሪ ጥምረታቸውን ይወደዋል መሰል ከአዲስ አበባ 278 ኪሜ ርቃ ወደምትገኘው ሀዋሳ በአንድነት ተመደቡ። የኢንጅነሪንግ ተማሪ ሊባሉ ወደ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አቀኑ። የኋላ የኋላ ምንም እንኳ የትምህርት ክፍላቸው ቢለያይም አብሮነታቸውን የማቆርፈድ አቅም ግን አልተቸረውም። የተገሩበት ዘዬ ተመሳስሎ የበረታ ነውና ስነ–ምግባራቸው እጅጉን የተዋደደ ነበር። እምነታቸው ላይ ያላቸው እውቀት ለተመሳስሎው እጅጉን አስተዋፅኦ አበርክቷል። ዛሬ ሊመረቁ ነው። ለአምስት አመታት የተማሩበትን ግቢ ለቀው ወደ አዲስ አበባ ሊመለሱ የዛሬውን ስነ ስርዓት መታደምና የትምህርት ማስረጃቸውን መቀበል ብቻ ቀርቷቸዋል።
.
የመኝታ ክፍላቸው የተለያየ ቢሆንም ሂባ ክፍል ባዶ አልጋ ስላለ ሰሞኑን አብረው ነበር የሚያድሩት። የንጋት ስግደት መድረሱን የሂባ ስልክ አላርም ሲያበስር ሁለቱም ከእንቅልፋቸው ባነኑ። ሂባ የመኝታ ቱታዋን እንደለበሰች መስኮቱ ጋር ቻርጅ ተሰክቶ የተቀመጠውን ስልኳን አደብ ልታስይዝ ሄደች። ‹‹ሂቡ እስኪ ስልኬን አቀብዪኝ›› ናርዶስ እንቅልፍ ጎሮሮዋ ላይ እንደተኛ አወራች።
‹‹ተነሽ ባክሽ አትጨማለቂ! ዛሬ እኮ...›› አለችና ሳትጨርሰው ስልኳን አቀብላት ልብሷን መቀያየር ጀመረች።
‹‹ቶሎ ስገጂና ፀጉሬን ታለሰልሺልኛለሽ›› ናርዶስ ከወገቧ ቀና ብላ ተቀመጠችና ልብሷን ለባብሳ በሩን ለመክፈት የምትታገለዋን ሂባን እያየች ቀጠለች ‹‹ስሚ ደሞ ውሀ ያለ አይመስለኝም ለማንኛውም ከዚህ የታሸገ ውሀ ይዘሽ ሂጂ›› ሂባ እንደወጣች ናርዶስ አልጋዋ ላይ ተቀምጣ ዶርሙን በአርምሞ ቃኘችው። እሷ ከተቀመጠችበት አልጋ ፊት ለፊት የሂባ አልጋ እንደተዝረከረከ አፍጥጧል። ከሂባ አልጋ በላይ ሀና አቅሏን ስታ ተጋድማለች። እሷ ያለችበት አልጋ የላይኛው ተደራቢ ላይ ሀሊማ ትገላበጣለች። ከእነርሱ አልጋ ወዲያ ያሉት አራት አልጋዎች ባዶ ናቸው። ናርዶስ ስልኳን ከፈተችና የተላከላትን መልዕክት አነበበች። ኢምራን ነበር። መልዕክቱ ‹‹እንኳን ለዚህ ውድ ቀን አበቃን የኔ ማሮች!›› ይላል። ፈገግ አለች። ኢምራን አሳዘናት። እሱ የደሴ ልጅ ነው። እነሱ ደግሞ የአዲስ አበባ! ከዚህ በኋላ የሚገናኙ አልመስልሽ አላት። ኢምራን የሂባ አፍቃሪ! ከጥንፍፍነቷ ፣ ከቁጥብነቷ በፍቅር የተዋደቀ! እሷም ትወደዋለች። የመጋባት እቅዳቸው የመጀመሪያው ጡብ ዛሬ እንደሚጣል ያምናሉ። ቤተሰቦቿ ለምርቃት ስነ ስርዓቷ ስለመጡ ልታስተዋውቀው አስባለች። እሱም እንደዛው። ‹‹ሚስኪን ኢምራን!›› አለች ናርዶስ እያሳዘናት። ለሂባ ደግሞ ምን ብሎ ልኮላት ይሆን? ማወቅ ፈለገች። ጉልበቷ ጋ የማይደርስ ስስ ቁምጣ በቦዲ እንደለበሰች ወደ ሶኬቱ ጋ ተራመደችና የሂባን ስልክ አንስታ ማንበብ ጀመረች። ‹‹ዛሬ ፈጣሪም ደስ ይለዋል። ዛሬ መልአክት አይከፉም። ዛሬ ከነብስሽ የተዋሀደው ነብሴ ህጋዊ እውቅና የሚያገኝበት የመጀመሪያው ጡብ ይቀመጣል። ደስ ይላል። ስወድድድድሽ!›› ይላል። አንብባ ጨርሳ ፈገግ ስትል ሂባ በሩን ከፍታ ገባች። በሩን ዘግታ ስልኳን ይዛ ወደ ፈገገችው ናርዶስ ተጠግታ አብራት ማንበብ ጀመረች። አንብባ ጨርሳ ስትፈግግ ናርዶስ እየሳቀች ‹‹ቆይ ምን ተዓምር ነው በማርያም? ምንም ሳይቀምስ እንዲህ የሚያክለፈልፈው? በስነ ስርዓት እንኳ አግኝተሽ አውርተሽው አታውቂም እኮ! ሰው በስልክ ብቻ እያወራ ተስፋ ካልቆረጠ አሪፍ ነው የምር!›› አለች። ሂባ መስገጃዋን እያነጠፈች ‹‹የራስሽን ማን ጫሪው አለሽ? በኔ ከምትሻፍጂ ይሻልሽ ነበር›› ‹‹ውይ ሂቡ ለካ አልነገርኩሽም። እናቱን! ለምርቃት አብረን እንተኛ ብሎኝ እኮ ነው። እንደ ኢምራን ስለ ትዳር የሚያስብ መስሎሽ ነው? በቃ ለመጋደም ነው የሚሮጠው የሆነ ተንከሲስ ነው። እሱን ብሎ ኪሩቤል! እኔ ደግሞ እኔ ምኔ የምርቃት ኮፍያ ነው ለምርቃትህ የምትደፋኝ? እመብርሀን እዛዉ ትድፋህ ብዬው መጣሁልሽ›› ሳቀች ፣ ናርዶስ ራሷ ተናግራ ራሷ መሳቅ ይቀናታል።
ሀና ከእንቅልፏ እየተነሳች ‹‹ናርዶስ ደሞ አንቺ ከተነሳሽ ሰው አይተኛማ? ስንት ሰዓት ሆኖ ነው ግን?›› አለች። ‹‹ባክሽ ሂቡ ሱብሂ ልትሰግድ ተነስተን ነው።›› ‹‹አንቺ ምን ቤት ነሽ ታዲያ! ደሞ ሀሊማ አትሰግድም እንዴ? አትቀሰቅሷትም?›› ናርዶስ ፈገግ ብላ ‹‹እሷ ሀይድ ላይ ናት ሶላት የላትም።›› አለች። ሀና በናርዶስ አረብኛ እየተወዛገበች ‹‹ሂባን ውጠሻታል እንዴ ምንድነው አይድ ምናምን?›› ‹‹አንቺ አምስት አመት ሙሉ ከሂባ ጋር ተምረሽ ይኼን አታርፊም? ባክሽ ሀይድ ማለት የወር አበባ ማለት ነው። የወር አበባ ያለባት ሴት ሶላት አትሰግድም ገቢቶ?›› አለች። ሀና ውዝግብ እያለች ‹‹እሱማ ሶላት የላትም አይደል እንዴ የሚባለው! ቆይ ሙስሊም ነሽ እንዴ?›› አለች፡፡ ናርዶስ እየሳቀች ‹‹አዎ በጓደኛዬ ሙስሊም ነኝ።›› አለቻት። ‹‹በቃችሁ አሁን ልስገድበት!›› ሂባ ለመስገድ ተመቻቸች። ናርዶስ ወደ አልጋዋ እየሄደች ‹‹ስሚ ሀይላንዱን ሱትራ አድርጊው! ደሞ አቋረጥሽኝ እንዳትዪ መመላለሴ አይቀርም!›› አለች። ሱትራ ከመስገጃው ፊትለፊት የሚቀመጥ መከለያ ነው። ከመከለያው ወደዛ ሰው መተላለፍ እንዲችል ለመርዳት የሚደረግ ነው። ናርዶስ የእስልምናን አብዛኛዎቹን እሴቶች ምናልባትም ከአንዳንድ የእስልምና እምነት ተከታዮች በተሻለ ታውቃለች። ሂባ መስገድ ስትጀምር ቤቱ.
2 297
የሂባዋ ናርዶስ ❤️
❤️ልብ አንጠልጣይ ታሪክ❤️
ፅሀፊ :ፉዓድ ሙና
ነገ ምሽት ጀምሮ በቴሌግራም ቻናላችን ይከታተሉን
Join us:
https://t.me/Ethioleboled
2 297
❤️ ጥላቻ ❤️
❤️ልብ አንጠልጣይ ታሪክ❤️
ክፍል 1⃣8⃣
የመጨረሻው ክፍል
ኤልሳ ስትሮጥ ሄኖክ ሲከተላት መኪናዋን አቁማበት የነበረው ቦታ ደረሰች ወድያውም አስነስታ ልትሄድ ስትል ሄኖክ ደርሶ ኖሮ እያለከለከ ምን ሆነሻል ኤልሳ አትነግሪኝም ሲል በድጋሚ ጠየቃት ኤልሳም እንባዋ በጉንጮቿ እየወረደ ሄኖኬ ጉድ ሆኛለው ልክ እንደናቴ አባቴንም በኔ ምክንያት ላጣ ነው... አለች እሺ ክፈቺልኝ ልግባ ቅድሚያ አለ መደንገጡ እንዳይታወቅበት እየጣረ .... ኤልሳም አይ ሄኒ ብቻዬን ልሂድ ምናልባት አብረን ሲያየን አባቴ ላይ እርምጃ ሊወስድ ይችላል አለችና በፍጥነት መንዳት ጀመረች...
ሄኖክ አላስቻለውም በኮንትራት ታክሲ ይከተላት ጀመር ከዛ ኤልሳ አባቷ ያለበት ቤት ደረሰች ግን በሚያሳዝን ሁኔታ አባቷን ሳታገኛቸው ቀረች ቤት ውስጥ ማንም አልነበረም ግን አንድ ነገር ተመለከተች ቤት ውስጥ ደም ተንጠባጥቧል ይሄኔ ኤልሳ እንደ እብድ አደረጋት መጮህና ማልቀስ የጠፋባት መሰላት... ወድያው ሄኖክ በሩን ከፍቶ ገባ እሩጣ ተለጠፈችበት ሁኔታዋ ግን ቅይርይር አለ ሰውነቷ ይንቀጠቀጣል ... አይዞሽ ውዴ ተረጋጊ አለ ሄኖክ እሱም ልክ እንደሷ ደሙን ሲያይ በጣም ደንግጧል ... ሄኖክ ገብቶ ጥቂት እንደቆዩ ወድያው ፖሊሶች ገቡ ጥቆማ ደርሶን ነበር አሉና ቤቱን መበርበር ጀመሩ ከዛም ወደ ጓሮ ዞሩ የኤልሳ አባት ተዘርረዋል...
ኤልሳና ሄኖክ ፊልም የሚተውኑ እስኪመስላቸው ነገሩ ከበዳቸው ከዛም ጓሮ ከገቡት አንዱ ፖሊስ ወደቤት በመግባት አለቃ አንድ ሰውዬ አግኝተናል ግን በህይወት አሉ ምናልባት ከተረፉ እንሞክር አምቡላንስ ይምጣ አለ እ አባቴ ነው እ ንገረኝ ፖሊስ አባቴ ነው እያለች ለማየት ስትጣደፍ ሁለቱን ተጠርጣሪ ወደ ጣብያ ውሰዷቸው ተባለ ... ምክንያቱ ምንም ሳይገባቸው ሄኖክና ኤልሳ ታሰሩ አባቷ መናገር ችለው ካልተናገሩ በርግጠኝነት እስኪጣራ እየተባለ አይፈቱም ...
ኤልሳ የእስር ቤቱን ህይወት አልችል አለች እንዛ ያልተፈቱ እንቆቅልሾቿን ተፈተው እስክታይ ጓጉታ ታነባለች ልጇን ከዛ ሰውዬ ተቀብላ አባቷን እያስታመመች በሷ ምክንያት ያለፈ ስቃዩ ሳያንስ አሁንም የታሰረውን ፍቅረኛዋን ባሏ አድርጋ መካስ ትፈልጋለች ...
በዚ መልኩ አንድ ወር ሊሞላ 6ቀን ቀረው አባቷ ነቅተው ልጄስ ብለው ጠየቁ የሚያስታምማቸው አንድም ዘመድ ባለመኖሩ ጎረቤታቸው አስካለ ከጎናቸው አትጠፋም ..ልጄስ አሏት ደግመው እሷም እምባዋን በነጠራዋ እየሸሸገች ልጅህ ታስራለች እስኪጣራ ብለው አስረዋታል አለች ተይ አስካለ ልጄ ስቃይ ላይ ሆና ዝም አልሽ አሉ የኤልሳ አባት በደከመ ድምፃቸው ወድያው ፖሊሶች ገብተው ... እግዜር ይማሮት አባት አሉ የኤልሳ አባትም አይናቸውን ቡዝዝ አርገው እያፈራረቁ ተመለከቷቸው... ፖሊሶቹም ቃል መቀበል ጀመሩ
...
በሰአቱ የኤልሳ ባል ሊገላቸው እንደነበርና እሷንም ደውሎ ድረሽልኝ እንድላት ያረገኝ እሱ ነው አሉ ፖሊሶችም ወድያው ሄኖክንና ኤልሳን እንዲፈቱ ትእዛዝ ሰተው ሰውየውን መፈለግ ጀመሩ ... ከ24 ሰአታት ቡሃላ አገኙት ልጇን መልሶ ወደ እስር ቤት ተወሰደ ...
አሁን ሄኖክ ተረጋግቶ ኤልሳን ሚስቱ አርጎ በተማረበት መስክ ስራ ጀምሯል ደስተኛ ቤተሰብ ሆነዋል ልጃቸውን በፍቅርና በስስት ማሳደግ ቀጥለዋል የኤሳ አባትም ደስተኛ ልጃቸው ቤት ህመማቸውን እያስታመሙ ነው።
በሰፈሩት ቁና... እንዲሉ የኤልሳ የቀድሞ ባልም ፍርዱን በመጠባበቅ ላይ ይገኛል...
❤️ ተ❤️ ፈ❤️ፀ❤️ መ
እንደወደዳችሁት እና እንደ ተማራችሁበት እምነታችን ነው።
ሀሳብ አስተያየት ካላችሁ comment ላይ አሳውቁን በቅርቡ በአዲስ ታሪክ አንመለሳለን ሰላም ቆዩን
2 297
❤️ ጥላቻ ❤️
❤️ልብ አንጠልጣይ ታሪክ❤️
ክፍል 1⃣7⃣
ኤልሳ ልትወጣ ስትል ሄኖክ እጇን ያዝ አድርጎ ምንድነው አላት ኤልሳም እየተርበተበተች ባሌ ነው ድምፁ አስፈርቶኛል ምናልባት የሰማው ነገር ይኖራል አለችና ልጇን ና አባይዬ ብላ እጁን ይዛው ወጣች ... ሄኖክም ሁኔታዋ ስላስፈራው ከኋላ ተከተላት እውነትም ባልዋ ውጪ ላይ ይጠብቃት ነበር ገና ሲያያት ከመኪናው ወርዶ እየቀረባት ... አንቺ የድሃ ልጅ እድፍሽን ባጠራልሽ ደሞ ጎረምሳ አማረሽ አለ በሀይለ ቃል እሷም እንዳቀረቀረች አይ አጋጣሚ ነው አለች ፍርሃት በወረረው አንደበት ዝም በይ አለና ያ የሚያሳሳ ጉንጯን በጥፊ አቀላው ቀጥሎም ስሚ ሰው ያገኩሽ እኔ ነኝ አትሸውጅኝ ይሄን ጋጠ ወጥ የማላውቀው ይመስልሻል? አለና ወደ መኪናው ገፈተራት ... በራሴ መኪና እመጣለሁ ስትለው መልስም ሳይሰጣት የራሱ መኪና ውስጥ አስገባት...
ሄኖክ ሁኔታቸውን ሲከታተል ትግስቱ ተፈታትኖታል ግን መታገስ ስለነበረበት ዝም አለ ... የሱ የሆኑ ሰዎች ሁሌም ተፈታኝ ናቸው በዚም እድለቢስ እንደሆነ ይሰማዋል... ኤልሳ መኪና ውስጥ ገብታ ከመቀመጧ ንዴቱ ያልበረደለት ባሏ አንቺን ያገባሁ ቀን ምናለ ቢደፋኝ አለ ይሄኔ የኤልሳም ትግስት አልቆ ኖሮ... ታድያ ለምን አፈታኝም ...እ... ምን ያዘህ አለችና መኪናውን ከፍታ ስትወርድ ቀድሟት ወርዶ እገልሻለው አንቺንም አባትሽንም ልቹቸን ነው የማስገባቹ አለ ይሄኔ ሰብለ ቀዝቀዝ አለች ለአባቷ ስትል ምንም መሆን እንዳለባት አስታወሰች .... ሄኖክ ግን አላስቻለውም ወደመኪናው በመቅረብ አንተ ማን የሚሉህ ገዳይ ነህ ባክህ እስቲ ይብቃህ... እድሜ ልክህን በቁም የገደልከን ይብቃህ አለው ሰውየውም በንዴት ጦፎ አንተ ወጠጤ ማንነቴን አታውቅም አለና ሄኖክን በቦክስ መታው ይሄኔ ግን ስብለ ትግስቷ ተሟጦ እየሮጠች ወደ ሄኖክ በመሄድ በቃህ ከዚ ቡሃላ የኔና ያንተ ጉዳይ አብቅቷል ዳግም ጫፉን እንዳትነካው እኔ የበደልኩት ይብቃ ብላ ከሄኖክ ጎን ቆመች ...ባሏም እሺ ዋጋ ትከፍይበታለሽ ሲል ዝቶ መኪናውን አስነስቶ ሄደ...
በቆሙበት ጥቂት ከቆዩ በኋላ ኤልሳ ዋ...ይ ብላ ጮኸች ለካ ልጇን ይዞባት ሄዷል ሄኖክም እሷን ለማረጋጋት ጥረት እያረገ አይዞሽ የኔ ፍቅር ልጃችንን ይመልሳል አለና ወደቤት ይዟት ገባ... ሁለቱም በዝምታ ተዋጡ የማይተዋወቁ ይመስል የሚነጋገሩበት ርእስ አጡ ይሄኔ ነበር የኤልሳ የስልክ ጥሪ ዝምታውን ያደፈረሰው ... ስልኩን አውጥታ ስታየው አባቷ ናቸው ስልኩን አንስታ ገና ምንም ሳትል እንባዋ ይወርድ ጀመር ሄኖክም የደወለውን ሰው ለማወቅ እንደጓጓ አተኩሮ ይመለከታት ነበር ... አባቷ በታፈነ ድምፅ ልጄ ሊገለኝ ነው አሏት ምን አባዬ ብላወጥታ ስትሮጥ ምንድን ነው ኤልሳ ብሎ ሄኖክም ይከተላት ጀመር...
ላይኩ 100 ከሞላ የመጨረሻውን_ክፍል_አንለቅላችዃለን ካልሞላ ነገ ይለቀቃል
.
.
ይቀጥላል
ክፍል 1⃣8⃣
2 297
❤️ ጥላቻ ❤️
❤️ልብ አንጠልጣይ ታሪክ❤️
ክፍል 1⃣6⃣
ሄኖክ ሲነቃ ራሱን ያገኘው ሆስፒታል አልጋ ላይ ነበር ካጠገቡ ኤልሳ ነበረች አልጋው ጫፍ አቀርቅራ ታለቅሳለች ሄኖክም እዚ ለምን መጣው? አንቺስ እኔጋ ምን ትሰርያለሽ አለ በሚያሳዝን አንደበት ኤልሳም ይበልጥ እንባዋን መቆጣጠር እየተሳናት የፀሎት አባት ነግረውኝ ነው አለች ከዛም መልስ ሳይሰጣት የሆነው ትዝ አለው ፀሎት በህይወት የለችም! ይህን ሲያስታውስ ከመቅፅበት ብድግ አለ ኤልሳም ደንግጣ የኔ ውድ እዛው ተኛ እስኪሻልህ እባክህ አትነሳ አለች ... ሄኖክም እንባው ሳያቆም በምፀት ፈገግ ብሎ አያትና የተሰካለትን ግልኮስ ነቅሎት ካልጋው ወረደ ይሄኔ ኤልሳ አይሆንም ዶክተር ብላ ጮኸች ወድያው ዶክተሮቹ ገቡና ወደ ፀሎት አባት ተደውሎ እንዲመጡ ተደረገ ...
የፀሎት አባት መተው ልክ እንደ ልጃቸው ሲያረጋጉት ለተመለከተ የሱ አባት ነበር የሚመስሉት ሄኖክም ፀሎትን አይኗን ሳላያት ፍቅሬን ሳልገልፅላት አፈር አለበሳችኋት አይደል አባባ እስቲ ንገሩኝ ፀሎትን ለዚ ያበቃኋት አውቄ እንዳልሆነ ገብቷታል ? አለ እንባው ያለማቋረጥ እየወረደ አባትየውም ልጄ ተው በቃ እሷን ፈጣሪ ስለሚወዳት ነው የወሰዳት አይዞህ ደሞ ልጄ አንተንም እንደልጄ እንዳይህ አደራ ብላኛለች አሉ ፀጉሩን አያሻሹ... አይ አባባ ያ ቢሆን ጥላኝ አትሄድም ነበር አለ.... የፀሎትን አባትና ሄኖክን ተመልክቶ ያላነባ አልነበረም ኤልሳም ይህን ማየት ተስኗት ተነስታ ውጪ ቁጭ አለች...
ሁሉም ከተረጋጉ ቡሃላ ዶክተሮቹ ሄኖክን ዳግም እንዳይጨናነቅ አስጠንቅቀውት መውጣት እንደሚችል ገለፁለት ... ኤልሳም በመኪናዋ የፀሎት አባትና ሄኖክን ይዛቸው ሄኖክ የሚኖርበት ቤት ወሰደቻቸው ... ከዛም ልጇን ከትምህርት ቤት ማውጣት እንዳለባት ገልፃ ብቻቸውን ትታቸው ሄደች ...
ሁለቱም በየራሳቸው የትዝታ ማእበል ይዋኙ ጀመር ... ከዛም የፀሎት አባት ከኪሳቸው አንድ የተጣጠፈ ወረቀት አውጥተው ወደ ሄኖክ እየዘረጉ እንካ ይሄ ልጄ የላከችልህ መልክት ነው አንብበው እናም የኔ ልጅ እኔም እንግዲ እዚ መቆየት አልፈልግም ከዚ ቡሃላ ለነብሴ መኖር እጀምራለው ወደ ትውልድ ቦታዬ አምርቼ ገዳም እገባለው ... አሉ ሄኖክ በቅጡ ያደመጣቸው አይመስልም እየተቻኮለ ወረቀቱን ገልጦ ያነብ ጀመር ...
ሄኖኬ እንደምን አለህ እኔኳ ደና አይደለሁም
መሞቴም አይቀርም ግን የኔ ውድ ሁለም ቢሆን
ሞቼም ሳይቀር አፈቅርሃለው ይሄን አትርሳ
የኔ ውድ በመጨረሻዋ ሰአት ደርሰህ ደስታዬን
እጥፍ ድርብ አርገህልኝ ነበር የኔ ውድ ሁሌም
ለኔ እንዲ መሆን እራስህን ተጠያቂ ታደርግ
እንደነበር አውቃለው ግን ተሳስተሃል አንተ ምንም
አላደረክም ወደ ህንድ የመጣሁትም የልብ
በሽታዬን ለመታከም ነበር የልብ ህመም የነበረብኝ
ደግሞ ገና ልጅ ሆኜ ነው እንጂ ባንተ አይደለም!!
ሌላው ውዴ አደራ የምልህ ኤልሳ ታፈቅርሃለች
አንተም እንደዛው በዛ ላይ ልጅ አላቹ ስለዚህ አብራቹ
ሁኑ እሷን ከዛ አስቀያሚ ትዳር አውጣት!!
መላካም ህይወት የኔ ውድ።
ይላል ይሄን ተመስጦ እያነበበ እንባው ይወርድ እንደነበር ያስተዋለው ደብዳቤው በስብሶ ሲያየው ነበር ... ከዛም ቀና ብሎ ሲያይ የፀሎት አባት የሉም ... ኤልሳም ልጇን አውጥታ ቀጥታ ወደ ሄኖክ ተመለሰች ገና ገመግባቷ ስልኳ ጠራ ባሏ ነበር አንስታም ወዬ አለች ነይ ውጪ አንቺ ተራ አላት ልቧ ስንጥቅ አለ የልጇን ምሳቃ በቁሟ ለቀቀችው ይሄኔ ትንሹ ልጇና ሄኖክ በሁኔታዋ ደንግጠው ቆሙ እሷ ልጇን አውጥታ ስትሄድ ባሏ ለካ ይከታተላት ነበር....
.
.
ይቀጥላል
ክፍል 1⃣7⃣
2 297
❤️ ጥላቻ ❤️
❤️ልብ አንጠልጣይ ታሪክ❤️
ክፍል 1⃣5⃣
ሄኖክ ወደተላከለት አድራሻ በፍጥነት መሄድ ጀመረ ማንነቷ አላሳሰበውም ፍሬ ልቶን ትችላለች ብሎ ገምቷል ... ልክ ሲደርስ ኤልሳን ተመለከታት ልክ ሲያያት የደነገጠው መደንገጥ ልብ ድካም ቢኖርበት ፀጥ ያደርግ ነበር እሷም ልክ ስታየው እየሮጠች እግሩ ላይ ወድቃ ልጄ ሊሞትብኝ ነው በግሉኮስ ሀይል ነው ያለው ከወላጅ አባቱ ደም ያስፈልጋል ተባልኩ እናም ውዴ በፍቅራችን ይዤሃለው ልጄን አድንልኝ አለች ስቅስቅ እያለች በሚያሳዝን አንደበት... ሄኖክም በንዴት ጦፎ ... ቆይ አንቺ ምን አይነት እራስ ወዳድ የማይገልፅሽ ሴት ነሽ ለምን በሰው ህይወት ትቀልጃለሽ ማነው ቆይ መለወጤን የሚነግርሽ ሁሌም ባንቺ እቆስላለው ከዛ ልክ ሲሻለኝ ትመጪና ዳግም ታቆስይኛለሽ... አለ ንዴትና ሀዘን ተደምረው አንደበቱ ቃል ለማውጣት እየቸገረው...
ኤልሳ ግን መማፀኗን ቀጠለች ልጄ ልጅህ ነው እባክህ ሄኒ የኔን አትይ አሁን ለልጅህ ስትል ... ብላ ንግግሯን ሳትጨርስ ከዚ ቡሃላ እንዳትደርሺብኝ ህይወቴ ውስጥ ስትፈልጊ መግባት ሳትፈልጊ መውጣት የምትችይ ይመስልሻል ይሄኮ የህይወት ጉዳይ ነው ብሎ ገፍትሯት ሊሄድ ሲል እሺ እውነቱን ልንገርህ ለትንሽ ደቂቃ አድምጠኝ አለች ማልቀሷን ሳታቆም ... ሄኖክም ጀርባውን እንደሰጣት ቆም አለ... እኔ ድሮም ሆነ አሁን ካንተ በቀር ማንንም ማፍቀር አልችልም ባሌም ቢሆን የልጄ አባት እንዳልሆነና እንደማላፈቅረው ያውቃል!! ግን የግድ እኖራለው ይህም የሆነው ... ያኔ ካምፓስ እያለን ካንተ አረገዝኩ ማሶረድ ብፈልግም አልቻልኩም ምክንያቱም ያንተ ስጦታ ልጄ ብቻ ነው...
እናቴ ደግሞ ልጄ ተመርቃ አያለው ብላ በጉጉት ትጠብቅ ነበር ጉዷን አላወቀችም ከዛ አባቴ ባጋጣሚ ባልሰራው ወንጀል ታሰረ ይሄኔ እናቴ በኪራይ ቤት ልጅ ይዛ ተቸገረች ያሁኑ ባለቤቴ ደግሞ ችግራችንን ያውቅ ስለነበር አባዬን ብዙ ገንዘብ ከፍሎ አስፈታው ቤት ገዛልን እኔንም እንድመረቅ ይረዳኝ ጀመር ግን እናቴ ማርገዜን ስትሰማ ደሟ ከፍ ብሎ ላትመለስ አጣኋት... አሁን አባቴ ያለው ባሌ በገዛልን ቤት ውስጥ ነው እኔ አልፈልግም ብዬ ብፈታው አባቴን እንዳስፈታ አርጎ ያሳስርብኛል አባቴ ላይ ይህን መፍረድ አልችልም በእማዬ ይብቃ ...በቃ ከዚ በላይ ምንም አልልህም አሁን ሂድ ግን እንዳትረሳ እኔም ልጄም እኖድሃለን አለች ተስፋ በቆረጠ አስተያየት እያየችው ....
ሄኖክ ጮሆ ቢወጣለት ደስ ባለው ግን አልቻለም ኤልሳም ከሱ ባላነሰ ፈተናዎችን አሳልፋለች ሊያውም ለሰው እንኳ የማይነገር የማይታይ ችግር ... ሄኖክ ግዜ ሳያጠፋ ልጁን ለማዳን ሄደ... ኤልሳንም አቅፎ አባበላት ግን ምንም ሊላት አልፈለገም ... ልጁን ሲያየው ደስታ ይሁን ሀዘን የማያውቀውይ ስሜት ሰውነቱን ይወረዋል ... የኛስ ይሁን ይሄ ህፃን ልጅ አያሳዝንህም እያለ ፈጣሪን መውቀስ ይጀምራል ...
ሄኖክ ልጁን አዳነ ከዛም ለኤልሳ ስለፀሎት ነገራት ለሱ በሱ ምክንያት የሆነችውንና አሁን ሊክሳት እንደሚፈልግ ሲነግራት ኤልሳ ውስጧ በቅናት አረረ ... ግን ሲለያዩ መልካም እድል ከማለት ውጪ ምንም አላለችም እሱም በቀጥታ ፀሎትን ያየበት ቤት ሄደ... ልክ ደርሶ ሲያንኳኳ በር ተከፈተለት አባቷ ነበሩ ገና ሲያዩት ልጄን ልጨርስብኝ ነው አሉ በሄኖክ ድፍረት የተገረሙ በመምሰል...እሱም ገና ፀሎት ከማለቱ ማነው አባዬ አለች ፀሎት ዊልቸሯን እየገፋች ውጪ የቆመውን ሰው ለማየት ጓጉታ...ፀሎት ያባቷን ቁጣ ስትሰማ ይበልጥ ውጪ ቆሞ ፀሎት የሚለውን ሰው ለማየት ጓጓች አባቷ ግን በአይናቸው ሄኖክን እንዲሄድ ይነግሩት ጀመር ሄኖክ ትግስቱ ተሟጠጠበትና አባቷን እስኪ እባኮትን እድል ስጡኝና ያበላሸሁትን ላስተካክል ብሎ በሩን ግፍቶ አባቷን ገፍትሯቸው ገባ ፀሎትም ሄኖክን ስታይ እውን አልመስልሽ አላት ደንግጣ ፈዛ ቀረች ይሄኔ ሄኖክ እግሯ ስር ተደፍቶ ይሄ ላንቺ አይገባሽም ፀሎትዬ እያለ ያለቅስ ጀመር ፀሎት ማመን ትስኗት ፈዛ ቀርታለች ከዚ ቡሃላ ላንቺ እኖራለው እንደንግስት አነግስሻለው እንደ እናት እጦርሻለው የኔ ውድ እንደ ልጅ እንከባከብሻለው አለ ከልቡ እንደተፀፀተ እያስታወቀበት... አባትየውም ለሄኖክ ለመጀመርያ ግዜ አዘኑለት እሱ ሲያወራ እሳቸው አይናቸው እምባ አቅርሮ ነበር...
ከዛ ቀን ቡሃላ ሄኖክ ስራ ለመቀየር ማፈላለግ ጀመረ በፀሎት ግፊትም ትምህርቱን በማታው መርሃግብር ቀጠለ ሁሌም ከስራና ከትምህርት ውጪ ባሉት ሙሉ ሰአቶቹ ፀሎትን ያዝናናታል እሷም ከሷ ውጪ ደስተኛ የሌለ እስኪመስላት ድረስ ደስታዋ ወሰን አጣ... ኤልሳም አካሏ ባሏ ጋር መንፈሷ ሄኖክ ጋር እንደሆነ ህይወቷን ቀጠለች ...
ሄኖክ ትምህርቱን ጨርሶ ተመረቀ ፀሎት ሀኪሞቿ ከግዜ ወደግዜ ተሽሎሽ መራመድ ትችያለሽ ቢሏትም እስካሁን ግን አልቻለችም ስለዚህም ወደ ህንድ አገር ሄዳ እንድትታከም ተደረገ ስትሄድ ሄኖክም ያለችውን በሙሉ አባቷም ቤታቸውን ሳይቀር ሽጠው አልበቃ ብሏቸው ሄኖክ የመጀመርያ ፍቅረኛውን ኤልሳን እንድታግዛቸው ጠይቋት እሷም ያለምንም ማቅማማት ነበር እሺ ያለችው... በዚ መልኩ ፀሎት ከአባቷ ጋር ህንድ ሀገር ሄዳ ህክምና ጀመረች ...
ቀናት ተቆጠሩና ወደ ሳምንታት ተቀየሩ ከዛም ወደ ወራት ሄኖክ ቢጠብቅም ሳይደወልለት ቀረ አባቷ ገና የገቡ ቀን ብቻ ነበር መግባታቸውን የተናገሩት ከዛ ግን ድምፃቸው ጠፋ ...
ሄኖክም ጠንክሮ እየሰራ ነው ፀሎት ድና መታ አንድ ላይ መኖር የሚጀምሩበት ግዜና ሰርጋቸው ተደግሶ ፀሎት የምትመኘውን ሙሽራ ቀሚስ ለብሳ ማየት ይፈልጋል ....
ልክ በስድስተኛው ወር ሄኖክ ከዚ ወዳላከቸው ሆስፒታል አምርቶ መረጃ መጠየቅ ጀመረ ስለፀሎት በጠየቀ ግዜ ሁሉም ደነገጡ ፊታቸው የሀዘን ጥላ አጠላ... የሆነውን መገመት አልፈለገም እስኪሰማ ድረስ ጓጓ ... መዳን አልቻለችም እናም ከሰሞኑ ትመለሳለች ነበር መልሳቸው ሄኖክ ይሄ ቢያሳዝነውም ይሄን ያህል ወር ያለምንም መፍትሄ የመቆየቷ እንቆቅልሽ ሳይፈታለት ይጠብቅ ጀመር ይህ በሆነ በ4ኛ ቀኑ ሄኖክ ስልኩ ጠራ አንስቶ ሀሎ ከማለቱ ኤርፖርት ተቀበለን አሉ አንድ ትልቅ ሰው በደከመ ድምፅ ሄኖክም ደስታና ድንጋጤ ተቀላቅለውበት የፀሎት አባት ፀሎቴ ደና ናት አለ ግን ምላሽ ሳይሰጠው ስልኩ ተቋረጠ....
ግዜ ሳያጠፋ ኤርፖርት ደረሰ እሱ ከደረሰ ከደቂቃዎች ቡሃላ በቁጥር 10 አካባቢ የሚሆኑ ሰዎች ወይኔ ልጄ እኔ አፈሩን ልብላልሽ እያሉ ጥቁር ለብሰውና ነጠላ ዘቅዝቀው ያለቅሳሉ ሲያያቸው በጣም አሳዘኑት ሰው ሊቀበሉ እንደመጡ ያስታውቃሉ ... እያያቸው በልቡ ሲያሳዝኑ በህይወት ሸኝቶ እሬሳ መቀበል ምን ያህል አለመታደል ነው ይላል ... ልክ ከ1ሰአት ቡሃላ የፀሎት አባት ጥቁር በጥቁር ለብሰው ብቅ አሉ ፀሎት የምትባል ልጅ ባካባቢው አትታይም እሳቸው ብቅ ሲሉ ለቅሶው ይበልጥ ይሰማ ጀመር ግራ ገብቶት ማንን ምን መጠየቅ እንዳለበት አያውቅም ይሄኔ የፀሎት አባትም ከለቀስተኛው ጋር ተደምረው ልጄ ልጄ ሲሉ አንዴ ብቻ ሰማቸው ከዛ እራሱን ስቶ ወደቀ
.
.
ይቀጥላል
ክፍል 1⃣6⃣
2 297
❤️ ጥላቻ ❤️
❤️ልብ አንጠልጣይ ታሪክ❤️
ክፍል 1⃣4⃣
ሄኖክ ሲወድቅ ሁሉም ደንግጠው ከበቡት ፀሎት ግን መቆም ስለማትችል እዛው ሆማ ማነው ፍሬ ምንድነው ንገሩኝ ትላለች ፀሎት ሳታየው አፋፍሰው ወደ ሀኪም ቤት ወሰዱት ከረጅም ሰአታት ቡሃላ ሄኖክ ነቃ ዞር ብሎ ሲያይ ፍሬ እጁን በጇ ይዛ አልጋው ጠርዝ ላይ አቀርቅራለች ይሄን ሲያይ እንባው በጆሮው በኩል ይንቆረቆር ጀመር ፍሬም ቀና አለች ስታየው ነቅቷል እኔ አላምንም የኔ ውድ ነቃህ ብላ እጁን እየሳመች የደስታ እንባዋን ዘረገፈችው እሱ ግን ያቺ የሱን ሀዘን የማትሻው ፍልቅልቋ ፀሎት አሁን መራመድ አቅቷት በሰው ስትገፋ ማየቱ ይህ የሆነው ደግሞ በራሱ ጥፋት መሆኑን እያሰላሰለ ነው እንባው የሚወርደው...
ፍሬም እንባዋን እየጠረገች እሱን ማባበል ጀመረች ሄኖክም የተሰካለትን ግልኮስ ነቅሎ እወጣለሁ አለ ፍሬም አይሆንም ሀኪሞቹ ሲሉ ትወጣለህ አለች እንደመቆጣት እያረጋት ሄኖክ ግን ማንንም መስማት አልፈለገም ፍሬም ኮንትራት ታክሲ ጠርታ እሺ ግን እዛ ሆቴል አሎስድህም እኛ ቤት ትቆያለህ አለችው ሆቴል ነው የምሄደው አላት ልዝዝ ባለ አንደበት ... ታክሲው መቶ መንገድ ሲጀምሩ ምን ሆኖ እንደሆነ ለማወቅ የነበራት ጉጉት ጨመረና የኔ ውድ ግን ፓርቲው ላይ ምን አይተህ ነው የደነገጥከው? ስትል ጠየቀች ሄኖክም የሀጥያቴንና የበደሌን ዋንጫ ግቢያቹ ውስጥ አይቼ አላት ...በጣም ግራ ተጋብታ አልገባኝም አለች መቼም አይገባሽም አንቺን አለና ጮክ ብሎ እየውልሽ ፍሬ ስለኔ ምንም አታውቂም ግን ከዚ ቡሃላ ወደራሴ እንድመለስ እርጂኝ ይሄን አስመሳይ ማንነቴን ሳይሆን ትክክለኛ እኔነቴን እፈልገዋለው ... አላት "OMG እኔ ጭንቀት አልችልም በግልፅ ምን እንደተፈጠረ ንገረኝ" አለች... ግዜው ሲደርስ ይገባሻል እስከዛ ግን ከዚ ቡሃላ ከኔጋ ፍቅር ምናምን የሚባል ጨዋታ የለም አለና ገና ሳይደርስ ወራጅ አለ ብሎ ወረደ ፍሬ ነገሮች የሚሆኑት በህልሟ መሰላት እሱ ሲወርድ እሷ በድንጋጤ ፈዛ ስለነበር እዛው ቀረች...
ሄኖክ ስለ ፀሎት ለማሰብና እንዴት ዳግም ሊክሳት እንደሚችል ያስብ ጀመር ሆቴል ውስጥም ገብቶ እንደቀድሞው ሴቶችን ማማለል አይፈልግም እንዲያውም በተቃራኒው ኮስታራ ሆነ ያም ሆኖ ግን ስራውን ቀጥሏል ፍሬም እሱን ብላ መመላለሷን ቀጥላለች ... አንድ ቀን ፍሬ ወደሄኖክ በመቅረብ እየውልክ ሄኒ የቀልድ ብንጀምርም አሁን ከልቤ አፈቅርሃለው ስለዚ እንድትጎዳኝ አልፈቅድልህም አለች እሱም ትከሻዋን ያዝ አድርጎ እኔ የማፈቅራትና የምታፈቅረኝ ሴት አለችኝ አንቺ ለግዜው አሜሪካ እስክትመለሽ የቀረብሽኝ ስለመሰለኝ ልቤን አልከፈትኩልሽም እናም ፍሬ እባክሽ ከዚ ቡሃላ እራቂኝ አለ... ፍሬ ግን አልችልም ነበር መልሷ
አንድ ቀን ታድያ አንዲት ትንሽዬ መናፈሻ ስር ቁጭ ብሎ እንዴት ብሎ ፀሎትን አግኝቶ እንደሚክሳት እያሰላሰለ ስልኩ ጠራ ለማንሳት ብዙም ደስ ስላላለው አይቶ ዝም አለ ስልኩ ግን ደግሞ ጮኸ አንስቶ ገና ሄሎ ሳይል እርዳኝ እባክህ ልጄ ሊሞት ነው አለች አንዲት እያለቀሰች ያለች ሴት ድምፁ አዲስ አልሆነበትም ማነሽ አለ ከተቀመጠበት እየተነሳ... አድራሻ እልክልሃለው አሁኑኑ ድረስልኝ አለች...
.
.
ይቀጥላል
ክፍል 1⃣5⃣
2 297
❤️ ጥላቻ ❤️
❤️ልብ አንጠልጣይ ታሪክ❤️
ክፍል 1⃣3⃣
ሄኖክ በባህር አቋርጦ ከሀገር ለመውጣት ብዙ መንገድ ተጉዞ ነበር ነገር ግን ሳይሳካለት ቀርቶ በ3ወሩ ከሱዳን ተመለሰ እስከዛች ቀን ድረስ ፀሎት ሀኪም ቤት ቤቷ ሆኖ ነበር አባቷም ከልጃቸው ምንም ስለማይበልጥ ስራቸውን መስዋዕት አርገው ከሷ አይጠፉም ሄኖክም ከሀገር ወቷል ብለው በማመናቸው ልጃቸውን ቀስ በቀስ ብትረሳው ብለው ብዙውን ግዜዋን ሄኖክን የሚያስረሳ ነገር ያደርጋሉ ነገር ግን ከሀገር መውጣቱን አልነገሯትም...
ሄኖክ ከሱዳን ከተመለሰ ቡሃላ እጁ ላይ አምስት ሳንቲም አልነበረም የነበረችውንም ብር ለደላላ ከፍሎ ጨርሶታል ይሄኔ ምንም ምርጫ ስላልነበረው 2ቀን ከአንድ ሆቴል በር ላይ አደረ በ3ኛው ቀን ግን እዛ ያዩት የሆቴሉ ባለቤቶች በጥበቃነት እነሱ ጋር እንዲሰራ አነጋገሩት መጀመርያ ላይ እንዴት ተምሬ እንዳልተማረ ጥበቃ እሆናለው ሲል አሻፈረኝ ብሎ ነበር ግን በረንዳ ከማደርና ለሲጋራ ከመለመን ይሻላል ሲል እራሱን በራሱ መከረ ... የሆቴል ጥበቃነት ሲቀጠር ባለቤቱ እንቅልፍ እንዳይዝክ ለሊት እየጠበክ አንብብ ሲል መፅሃፎችን ይሰጠው ጀመር ... ሄኖክ ማንበብ ሲጀምር አስተሳሰቡ መቀየር ጀመረ የመጀመርያ ግዜ (ፀሀፊውን ባላስታውሰውም) #የቢሆን_አለም የሚል አሳዛኝ ልቦለድ ነበር ያነበበው እዛ መፅሀፍ ላይ ብዙ ለፍቅር ተብለው የተከፈሉ መስዋዕቶችን አነበበ ከዛም ግን እራሱን በባለታሪኩ ቦታ አድርጎ ሲያየው የኔ ፈተና ምንም አይደለችም ሲል ያስባል ይመልስና ደግሞ ይሄ ልብ ወለድ ነው እንደኔ በፍቅር የተገፋ የለም ሲል ያማርራል ...
በዚ ሁኔታው ወር ከ15 ቀን ከሰራ ቡሃላ ሰውየው የሄኖክን ቁመናና ውበት አይቶ ስራ ሊቀይርለት ወሰነና ጠራው ሄኖክም ወደ ሰውየው ሄዶ አቤት አለ ሰውየውም ካሁን ቡሃላ የምታጨሰውን ቀንስ ከዛ አለባበስህን ሁሌም አስተካክል እና ሆቴሌን ከኔ ስር ሆነህ ትቆጣጠራለህ (ሱፐር ፋይዘር ) ትሆናለህ አለው ሄኖክም ትንሽ የተስፋ ጭላንጭል ታየው በሀሳቡም ተስማማ ከዛች ቀን ቡሃላም እንደ ሄኖክ ዘናጭ የለም እሱን ብለው የሚመጡ የከተማዋ ቆነጃጂቶች በዙ ሁሌም ቢሆን ከደሞዙ ይልቅ የሚሰጡት ቲፖች ብዙ ናቸው ... ታድያ ሄኖክን ልጋብዝህ የማትለው ሴት የለችም ከታዳጊ እስከ አሮጊት(ሹገር ማሚ) ሄኖክን ይመኙታል እሱም ይሄ ያስደስተዋል ሁሌም አንድ አባባል አለው ሴት ልጅ ስቶዳት ከሀዲ ናት ስትገፋት ደግሞ ፈላጊ ናት ይላል...ይሄ አባባሉ በኤልሳ ከተጎዳ በኋላ የመጣ ነው...
ሄኖክ ገንዘብ ከምትሰጠው ሴት ጋር ግዜ ያሳልፋል ሲሰለቸው አይንሽን አልይሽ ብሎ ያባራታል... ከዛ ብታለቅስም ግድ አይሰጠውም በዚ ሁኔታው ሴቶችን ማማለልና መጉዳቱን ከስራው በላይ ይዘጋጅበት ነበር አንድ ቀን ታድያ አጋጣሚ ከአንዲት ፍሬ የምትባል ቆንጂዬ ልጅ ጋር ይተዋወቃል ልጅቷ ከአሜሪካ ለመዝናናት ነበር የመጣችው ስታየው ወደደችው እሱም ከሌሎቹ የተሻለ ግልፅነቷ ተመችቶት ከስራ በኋላ እሷን ማግኘት ስራው ሆነ ... ሲያገኛት ሁሌም ግጥምና ልብ ወለድ ታሪክ ያነብላታል ከዛም አልፎ እሷ እሱን የምታፈቅርበትን የተለየ ነገር ያደርጋል ... ቀስ በቀስ ከሄኖክ ውጪ ሰው የለም አለች እሱ ግን ፈፅሞ በልቡ ቦታ አልሰጣትም... ሁሌም ስለአንድ የልጅነት ጓደኛዋ ትነግረዋለች ... ጓደኛዋ አሁን ከቤት አትወጣም በድንገት በገጠማት ችግር ማለትም ፍቅረኛዋ ጥሏት ከሀገር መውጣቱን ስትሰማ በንዴት ከፎቅ ላይ ወድቃ እግሮቿ መራመድ እንደማይችሉና እቤት እንደምትውል ስትነግረው ያፈቀረችው ወንድ ታድሎ ይላታል እሷም ፈገግ ብላ አንተ ግን ጥለኸኝ የትም አትሄድም አይደል ትለዋለች እሱም አንቺ ወደ አሜሪካሽ ልትሄጅ አይደል ይላታል ... እሷ ግን ሄኖክን ጥሎ መሄድ ሞት መስሏታል ...
ይህ በንዲህ እንዳለ አንድ ቀን ፍሬ ለሄኖክ ደውላ የዛች አካል ጉዳተኛ ጓደኛዋ ልደት ስለሆነ ቤታቸው ብሮግራም አዘጋጅታ ጠራችው ያ ቀን መሄድ እየቀፈፈው ከላይ እስከታች ዝንጥ ብሎ ሄደ ደርሶ ልክ ሲከፈት ባለልደቷ ያቺ ፍልቅልቋና ማራኪዋ ፀሎት ልደቷን ዊልቸር ላይ ተቀምጣ ስታከብር ደረሰ በሱ ምክንያት መሆኑን ለመገመት ሰከንዶች በቂ ነበሩ በኤልሳ ስራ ልቡ ታውሮ የገፋት የህይወቱ ድንቅ ሴት ... ሄኖክ ምድር ዞረችበትና በቁሙ ተዘረረ...
.
.
ይቀጥላል
ክፍል 1⃣4⃣
2 297
❤️ ጥላቻ ❤️
❤️ልብ አንጠልጣይ ታሪክ❤️
ክፍል1⃣2⃣
ሄኖክ የሰብለን ማግባት አረጋግጦ ሲመለስ ላየው ሰው የአይምሮ ችግር ያለበት ይመስል ነበር ብቻውን እያወራ ብቻውን ይስቃል ኤልሳ ባል እያላት ለምን ወደ ህይወቱ በድጋሚ እንደመጣች ሲያስብ ግራ ይገባዋል ... አሁን ብቸኛ የነበረችው ተስፋ ፀሎትም እርቃዋለች ሄኖክ በድጋሚ ትምህርት አቆመ ሴት ልጅ ሲያይ ይሸሻል ብዙ በፊት የሚያቁት ሰዎች "ሄኖክኮ ነቀለ" እያሉ ያፊዙበታል ... እሱም ቢሆን ምን ቅንጆ ቢሆንምና ያየችው ሴት የምትማለልበት አቋም ቢኖረውም አሁን ላይ ግን ልብሱን እንኳ አይቀይርም ከወር እስከ ወር ይለብሰዋል ማጨስ መቃም መጠጣት የግሉ ሆኑ ቁም ነገር ስራበት ተብሎ የተቀመጠለት ገንዘብ ግማሽ ደረሰ...
አንድ ቀን እንደተለመደው ብቻውን እያወራና እየሳቀ ሲሄድ ፀሎት ከአባቷ ጋር ወክ ታደርግ ነበር ስታየው ማመን አቃታት እንደዚ እራሱን ጥሎ ይሆናል ብላ አስባ አታውቅም ... ሄኖክ ልክ ሲያያት ከት ብሎ ሳቀ ፀሎትም እንባዋን መቆጣጠር አቃታት ወደሱ ስትቀርብ እሱ ግን ጥሏት ሮጠ ይሄኔ ፀሎት እዛው አስፓልት ላይ እራሷን ስታ ወደቀች... አቧቷም ልጄ ብለው በመጮህ መንገደኛውን እርዳታ በመጠየቅ አንስተው ወደ ሆስፒታል ወሰዷት...
ፅሎት የልብ በሽታ ስላለባት መጨነቅና መደንገጥ ከመሳሰሉት ነገሮች መራቅ አለባት ብለዋል ሀኪሞቹ ይሄም የሚሆነውና ፀሎት ደስተኛ መሆን የምትጀምረው ሄኖክን ከጎኗ ስታገኝ ነው ... ይሄም እንዲሆን አባቷ ነገሩ ስላልገባቸው ፀሎት ስታገግም ስለተፈጠረው ጠየቋት ፀሎትም እንባዋ ያለገደብ እየወረደ አባዬ ሄኖክን አፈቅረዋለው እሱ እንደዚ የሆነው እኔ ጥዬው ስለሄድኩ ነው ፈልግና አምጣልኝ ልክሰው እፈልጋለው አለች አባትየውም ልጃቸውን እናትም አባትም ሆነው ስላሳደጓት በሷ መጨከን አይችሉምና ሄኖክን ማፈላለግ ቀጠሉ...
ታድያ አንድ ቀን ሰፈር ውስጥ በተለምዶ ድድ ማስጫ የሚባል አካባቢ ተቀምጦ አገኙት አለባበሱም ሆነ ሁኔታው እንኳን በልጃቸው ሊፈቀር የልጃቸው በር ጠባቂ እንዲ ሆን ባልፈቀዱለት ነገር ግን አሁን ላይ ያን ማሰብ አይችሉም ምክንያቱም ልጃቸው የሞት አፋፍ ላይ ናት እየቀፈፋቸው ተጠጉትና ልጄ ደና ነህ አሉት እሱም ቀና ብሎ ገልመጥ አረጋቸውና ከኪሱ ሲጋራ አውጥቶ ለኮሰ ይሄኔ በንዴት ጦፈው እንዳንተ አይነቱን ጋጠወጥማ ልጄ ፀሎት አታፈቅርም አሉ ሄኖክ ገና ፀሎት የሚለውን ስም ሲሰማ እንባው መንታ መንታ ይወርድ ጀመር ሰውየውም ትተውት ሊሄዱ መንገድ እንደጀመሩ ልጃቸውና ጭንቀቷ ትዝ አላቸው ከዛም መለስ ብለው ልጄን አድንልኝ እባክህ አሉት ሄኖክም እርሶም ጥቅመኛ ኖት? ክክክክ ሆ እርሶም እንደ ኤልሳ ጥቅም ያታልሎታል? ካካካካ ትተውኝ ሊሄዱ መንገድ ጀምረው ሲያበቁ ተመልሰው ይለምኑኛል ? አለና እያነባ ትቷቸው ሄደ
ከዛ ቀን ቡሃላ ሄኖክን አየው የሚል ጠፋ ፀሎት ሄኖክን እያለች ከሆስፒታል ሳቶጣ ድፍን 20 ቀን ሞላት አባትም የልጃቸውን መድሃኒት ሄኖክን ፍለጋ ተያይዘውታል ... ልክ በ24ኛው ቀን ሄኖክን አየው የሚል ሰው ተገኘ በሊቢያ በኩል አድርጎ ከሀገር ሊወጣ መሆኑን የፀሎት አባት አወቁ ለማስቆም ግን ግዜው ረፍዷል ያ ካልሆነ ደግሞ ፀሎት በርግጠኝነት ትሞታለች ምክንያቱም ጥዬው ባልሄድ እንዲ አይሆንም ነበር ብላ ታምናለች...
.
.
ይቀጥላል
ክፍል 1⃣3⃣
2 297
❤️ ጥላቻ ❤️
❤️ልብ አንጠልጣይ ታሪክ❤️
ክፍል1⃣1⃣
ሄኖክ ምን ማድረግና ማንን መምረጥ እንዳለበት ግራ ገባው የልጁን እናት ኤልሳን ወይንስ ከብዙ ፈተናዎች ታድጋ በስተመጨረሻ መልካም መንገድ እንዲጓዝ የረዳችውን ፀሎት ... ይሄን መምረጥ ለሱ ትልቅ ፈተና ነበር ኤልሳን ሲያገኛት በርግጥ ፍቅሩ አገርሽቶበታል በዛ ላይ ልጅ ከሷ አለው ግን ደግሞ ፀሎት ማለት እናቱ ነች ያላትን ፍቅር ሳትሰስት ለግሳ ከመጥፎ መስመር መልሳና መጥፎ ትዝታዎችን አስረስታዋለች... ለዛም ነበር ልጅ እንዳለው እንኳ ነግሯት ቅስሟን መስበር ያልፈለገው...
ሄኖክ በድጋሚ ጭንቀቱን ለመርሳት ሲል ማጨስና መጠጣት ጀመረ ትምህርት ቤት ከሚሄድበት የማሄድበት ቀንይበልጣል ባጭር ቋንቋ ሄኖክ ልክ እንዳለፈው ሱስ ውስጥ ተዘፈቀ ይሄኔ ነበር ፀሎት አንድ ነገር እንድተፈጠረ የጠረጠረችው ... ሄኖክን ከመሸሽ ይልቅ ቀርባ ልትረዳው ሞከረች ፀሎት በተፈጥሮዋ ብዙ ፈተናን መጋፈጥ አትችልም በዛ ላይ የልብ በሽተኛ ነች ትንሽ ጭንቀት ይጥላታል ለዛም ፀሎትን የሚያስደነግጣት ነገር መፈጠር የለበትም ...
አንድ ቀን ሄኖክና ፀሎት ሰፈር ውስጥ ተቀምጠው ፀሎት እንደተለመደው ሄኖክን ለማዝናናት የባጥ የቆጡን ትለፈልፋለች ይሄኔ ኤልሳ ሳያስቡት መጥታ ከፊት ለፊታቸው ቆመች ትንሽዬ የሚያምር ህፃን ይዛለች ሄኖክ በድንጋጤ ከተቀመጠበት ተነሳ ኤልሳም እኔና ልጄ ሰላም ልንልህ ነው የመጣነው አለች ሄኖክም ፀሎት ከዚ በላይ ከሰማች ስለምትደነግጥ የት ታቂኛለሽ እብድ ነሽ እንዴ ሴትዮ ብሎ ፀሎትን እየጎተተ ይዟት ሄደ ግን እንዳሰበው ፀሎትን መሸወድ አልቻለም እውነቱን እንዲነግራት አፋጣ ያዘችው እሱም እንድትረጋጋ ካደረጋት ቡሃላ ስለኤልሳና ሜላት ይነግራት ጀመር...
ፀሎት ኤልሳን ማፍቀሩንና የልጅ አባት መሆኑን አምኖ መቀበል አቃታት በዚም ልትርቀው ወሰነች ሄኖክ በድጋሚ የሚወደውንና የሚያስብለትን ሰው አጣ ... ዶጮም እንደመጀመርያው አያገኘውም ሄኖክ ግን ያለው አማራጭ ዶጮን ፈልጎ ማግኘት ነበርና አገኘው... ስለኤልሳ የነገረውን በማስታወስ ዶጮ ያኔ ስለኤልሳ የሰማኸው ልክ አልነበረም ማለትም ፊዚክስ ቲቸራቹ አጎቷ ነው አለ አይኖቹ እምባ አቀርዝዘው ዶጮም በምፀት ፈገግ ብሎ ጓደኛዬ እኔ ላንተ ያልተጣራ ወሬ አላቀርብልህም ኤልሳን ምን ያህል እንደምታፈቅራት አውቃለው ለዛም አንድ እንድቶኑ ብቻ ነበር የምፈልገው ለዚም ብዬ ብዙ ለማጣራት ጥረት አድርጌአለው ሄኖክ አንተ ማለት ወንድሜ ነህ ማንም ሰው ሲያስከፋህ ማየት አልፈልግም ከፈለክ በዚ አድራሻ ኤልሳ ቤት ሂድ ከዛም ሁሉንም ታያለህ... አለና በትንሽ ወረቀት አድራሻ ፅፎ ሰቶት ይልቅ ወንድሜ ፀሎትን በደምብ ያዛት ላንተ ህይወት መስመር የምቶንህ እሷ ብቻ ናት ብሎ ትቶት ሄደ...
ሄኖክ እውነቱን ሳያውቅ ማደር አልፈለገም በቀጥታ ወደ ኤልሳ ሄደ እንደተባለውም የኤልሳ ግቢ ሲደርስ ማመን አቃተው ኤልሳን ሲያውቃት የድሃ ልጅ ነበረች ፓርቲ ለመሄድ እንኳን ቀሚስ የለኝም ትል የነበረች ልጅ ዛሬ መቼም ከሰማይ አይወርላልትም ይሄ ሁሉ ሀብት አለ በውስጡ የኤልሳ ቤት እጅግ ውብ የሚባል ነው ... በመደመም ካየው ቡሃላ እውነቱን ለማረጋገጥ አንኳኳ አንድ ጎልማሳ የክፍለ ሀገር ሰው ከፈተለት
ማንነቱን ለማወቅ ጥያቄ አያሻውም የግቢው ጥበቃ ነው... ሄኖክ በሩ ሲከፈት ደንግጦ ምን ለመጠየቅ እንደመጣ ጠፋበት ከዛም ሰውየው ምን ፈለክ ጎረምሳው አሉ እ...እ..እ እያለ ሲርበተበት ምናባቱ እ ይልብኛል ምን ፈለክ አሉ እ... ኤልሳን ነው ትኖራለች ሲል ጠየቀ ሰውየውም እትዬ የለችም ባልተቤቷ ግና አሉ አለ ባሏ አለና ቃሉን ደገመው አዎ ልጥራልህ አሉ አይ ተውት ግን የምር ኤልሲ አግብታ ነው? ሲል በድጋሚ ጠየቀ ምን ይላል ይሄ የስንት አመቱን ነው ሲል ድንገት አሸብር ማነው የመጣው አለ አንድ ጎርናና ድምፅ ከወደ ውስጥ ሄኖክም እንደ እብድ ብቻውን እያወራ በመጣበት መመለስ ጀመረ...
.
.
ይቀጥላል
ክፍል 1⃣2⃣
2 297
❤️ ጥላቻ ❤️
❤️ልብ አንጠልጣይ ታሪክ❤️
ክፍል1⃣0⃣
ፀሎት ስትወድቅ ሁለቱም ተደናግጠው አነሷትና ምን ማድረግ እንዳለባቸው ግራ ተጋቡ ይሄኔ የኤልሳ ፀሃፊ ሲጯጯሁ ሰምታ ስለነበር በፍጥነት ወደ ውስጥ በመግባት ፀሎት ላይ ውሃ አፈሰሰችላት ፀሎት ግን አልነቃችም ይሄኔ አምቡላንስ ጠርተው ወደ ሆስፒታል ወሰዷት ዶክተሮቹም ኤልሳንና ሄኖክን ውጪ እንዲቆዩ ነግረዋቸው ስራቸውን ቀጠሉ...
ይሄኔ ሄኖክ ወደ ኤልሳ ተጠግቶ... "ባንቺ ነበር ህይወቴ መስመር መሳት የጀመረችው ከዛም አንቺን አፍቅሬ ታወርኩና የሚወዱኝን ስገፋና ስበድል ኖርኩ ከዛ ፍቅርሽን አግኝቼ መኖር ጀመርኩ ስል ዳግም በራስሽ ላይ መጥፎ ውሳኔን ወስነሽ ልጃችንን አሶርዳለው ስትይ እንዳላጣሽ ፈርቼ ላወራሽ ብመጣ የደከምኩለት ትምህርቴን አጣሁት ለካ አንቺ ከሌላ ወንድ ጉዳይ ስለነበረሽ ነው ያን ያልሽው ..." ሄኖክ ንግግሩን መቋጨት አቅቶት ወንበሩ ላይ አቀርቅሮ እያነባ ተቀመጠ ይሄኔ ኤልሳ በዛ ጣፋጭ አንደበትዋ እንባዋን እያዘነበች "አትሳሳት ካንተ ውጪ ማንንም ወንድ አፍቅሬም ሆነ ወደ ህይወቴ አስገብቼ አላውቅም! ሄኒ ያኔ በኔ ምክንያት ስትባረር እኔ ጋር የቀረው ልጃችን ብቻ ነበር እሱንም ልንመረቅ ጥቂት ወራት ቀርተውን ስለነበር ነው ላሶርደው ብዬክ የነበረው ግን አንተን ሳጣ ካንተ ያገኘሁትን አንድና አንድ ስጦታ ልጄን ማጣት አልቻልኩም በሱ ውስጥ አንተ አለህ ..." ይሄኔ ሄኖክ ማመን አቅቶት የሌላ ሰው ታሪክ ታወራ ይመስል አፉን ከፍቶ ያዳምጣታል አክላም "እድሜ ለአጎቴ እዚው ዩንቨርስቲ ፊዚክስ ያስተምር ስለነበር ብዙ ረድቶኝ ተመረኩ ልጄንም ትምህርቴንም ሳላጣ..." እያለች ንግግሯን በእንባዋ አጅባ ስትቀጥል ሄኖክ ዶጮ የነገረው ትዝ አለው "ከፊዚክስ አስተማሪ ጋር ፍቅር ጀምራለች" ብሎት ነበር
ሄኖክ ማስተዋል ሲጀምር ምላሽ አገኘ ዶጮም ሆነ ሌሎቹ የኤልሳ አጎት ፍቅረኛዋ መስሏቸው ነበር ግን እውነቱ ያ አይደለም ጭንቅላቱን ይዞ "ማመን አልነበረብኝም አንቺን መጠበቅ ነበረብኝ ግን እረፍዷል ሂጂ ኤልሳ ላይሽ አልፈልግም ሂጂ" ብሎ ሲጮህ ኤልሳ ተስፋ በቆረጠ አስተያየት እንባ በሚያጎርፉት አይኖቿ እያየችው ከተቀመጠችበት ተነሳች ይሄኔ "...አዎ ዳግም ህይወቴ ውስጥ አትግቢ ምክንያቱም ያን ያህል ግዜ ስጠፋ አንዴም አልፈለግሽኝም ከሞት አፋፍ ላይ የመለሰችኝ ፀሎት ናት ያኔ ሜላትን ባንቺ ለውጬ እንደጎዳዋት ሁሉ ዳግም መሳሳትና ፀሎትን መጉዳት አልፈልግም!!" አለ ኤልሳም ልትናገር "...እ ግን ለልጃችን የግድ ታስፈልገዋለክ..." ስትል ዶክተሮቹ ወተው የፀሎት ቤተሰብ አሉ ሄኖክም በፍጥነት ወደ ሀኪሙ ቀርቦ ደና ናት ሲል ጠየቀ ሀኪሙም ፈገግ ብሎ ቶሎ ደርሰንላታል ደና ናት ገብተህ ማየት ትችላለህ አለው...
ፀሎት ተሽሏት ከሀኪም ቤት ወጣች እራሷን ስትስት ምን ተፈጥሮ እንደነበር ግን እረስታው ኖሮ ጭርሱን አላነሳችም እንደሁልግዜዋ ደስ የሚል ፍቅር መስጠቷን ቀጠለች ሄኖክ ግን ኤልሳን ካገኘና ልጅ እንዳለው ካወቀ ወዲ እንደ እብድ ያረገው ጀምሯል ባህሪው ቅይርይር ከማለትም ባለፈ አይጨበጥም... ይሄ ያስጨነቃት ፀሎት ታድያ አንድ ቀን ምሽት ራት ጋብዛው ሲገናኙ ከዛ በፊት "መች ነው የምታገቢኝ?" ያላትን አስታውሳ "...ፍቅሬ ጥያቄህ መልስ አግኝቷል አሁን ዝግጁ ነኝ ሽማግሌ ላክ" አለችው ፈገግ ብላ በዚ ግዜ ክው አለ የገዛ ምራቁ አነቀው...
( ማንን መምረጥና ማስቀደም አለበት??? እኔንጃ...)
.
.
ይቀጥላል
ክፍል 1⃣1⃣
2 297
❤️ ጥላቻ ❤️
❤️ልብ አንጠልጣይ ታሪክ❤️
ክፍል 9⃣
ኤልሳ ትከዳኛለች ብሎ አስቦ የማያውቀው ሄኖክ በሰማው ነገር ቅስሙ ተሰበረ ህይወት አስጠላችው ይሄኔ ማጨስና መጠጥ መጠጣት ጀመረ ሄኖክ ሙሉ ለሙሉ ወደ ሱስ ሲገባ በቀን ከሚያገኘው ገቢ ግማሹ ለሱስ ሲሆን የተረፈው ለአጎቱ ሚስት ሀና የቤት ኪራይ ና ለሷ አንዳንድ ነገር መግዣ ይሰጣታል ... በዛ መልኩ ግን ኑሮን መግፋት አልቻለም ሀናም በጣም ትታመም ጀመር ግን በቂ ገንዘብ ስለሌለው በወቅቱ ህክምና አታገኝም ልክ በ7ወሯ ለሊት ላይ ሀና በጣም ታመመች ይሄኔ ሲነጋ በጥዋት ነብስ አባቷን አስጠርታ ሄኖክ ከገባበት መጥፎ መስመር ወጥቶ እንዲማር 100,000ብር ባንክ ያስቀመጠችውን ተናዘዘችለት ... ሀና ገንዘቡን ያገኘችው መንግስት ወረሰን ላለችው ቤት ካሳ ተሰቷት ስለነበር ነው።
ሄኖክ በግርምት እናቴ ይሄ ሁሉ ገንዘብ ካለሽ ታድያ ለምን አልታከምሽም ሲል ጠየቀ ይሄኔ ሀና እንባዋ በጆሮዋ በኩል እየተንቆረቆረ ልጄ አንደኛ ገንዘቡ እንዳለኝ ብነግርህ ለኔ አትልም ነበር ልክ አሁን እንዳልከው በሽታዬ ላይድን ነገር በህክምና እንጨርሰው ነበር ሁለተኛ ተቸግሬና ተጎሳቁዬ እንኳ ከልጅ በላይ እንደምትወደኝና ሳይኖርህ ስትንከባከበኝ ልጄ ደስታዬ ልክ አልነበረውም ለዛም ነው እስካሁን የኖርኩት አለች ሄኖክ ማመን አቃተው የተኛችበት አልጋ ጫፍ ላይ አቀርቅሮ አለቀሰ በቃ ህይወት እንዲ ነው አንዳንዱ እንጥፍጣፊ ፍቅር ሳያስቀር አውጥቶ ይሰጥሃል አንዳንዱ ደግሞ ስትሰጠው ብቻ ይሰጥሃል አንዳንዱ ብትሰጠውም ባትሰጠውም ይነፍግሃል ... ሀና በህይወት መቆየት አልቻለም አረፈች...
ሄኖክ በምድር ላይ ያሉትን የሚወዳቸውን ነገሮች ሁሉ አጥቷል የሚወደውን ለማግኘት ደግሞ የምትወደውን ሜላትን ልብ ሰብሯል ... ለዛም ሀና ባወረሰችው ገንዘብ ምንም ቁም ነገር ሳይሰራበት እዛው ተወውና ሱሱን ገፋበት በዚ ወቅት ሴት ልጅ ቀርባ ስታዋራው ሁሌም ኤልሳና ያ ውብ አስተያየቷ ትዝ ይለዋል ከዛ ወድያው የሌላ ሆና እነዛን ውብ ከንፈሮቿን በሌላ ወንድ ስትሳማቸው ያስበዋል ይሄኔ ሴት ልጅ ከሀዲ ናት አልቀርብም ይላል ...
በዚ አቋሙ ሲኖር አንድ ቀን ፊልም ሊከራይ ፊልም ቤት ይሄዳል ይሄኔ አንዲት እድሜዋ ከሱ አነስ የምትል የቀይ ዳማ ቆንጂዬ ፍልቅልቅ ሴት ገና ሲገባ ከመቀመጫዋ ተነስታ በራሷ ምርጫ ፊልም ትሰጠዋለች በጣም ተገርሞ እኔ መች ገና ጠየኩሽ ይላታል ልጅቷም ቅልጥፍጥፍ ባለ ማራኪ አንደበቷ እኔ መረጥኩልሃ ገና ሳትነግረኝ ምን እንደምትፈልግ አወኩ አለች ለረጅም ግዜ ሴት መቅረብ ፈርቶ የነበረው ሄኖክ ከቀን ወደ ቀን በልጅቷ መሳብ ጀመረ ልጅቷ ፀሎት ትባላለች እስከዛሬ ልብ ብሏት ባያውቅም አሁን ግን ልቡ ደንግጦላታል እሷም ሆን ብላ ይመስል እሱ የሚወደውን ቀድማ ታደርግለታለች... መቀራረባቸው በጨመረ ቁጥር የተሰበረውን ልቡን ትጠግንለት ጀመር ...
ከ1አመት ቡሃላ ሄኖክ ሱስ የሚባል ነገር እርግፍ አድርጎ ተወ ከዛም የቀን በዲግሪ ፕሮግራም ትምህርት ጀመረ እድሜ ለሀና ልክ መለወጡን ሲያረጋግጥ ገንዘቡን መጠቀም ጀመረ ... አንድ ቀን ታድያ አፓረንት ወተው ወደ አንድ ድርጅት ተላኩ የመጀመርያው ቀን ፀሎት አብራው ሄደችና ወደ ዋናው ቢሮ አንኳኩተው ገቡ ይሄኔ ነበር ሄኖክ ተአምር ይመስል ባየው ነገር ደንግጦ የቀረው ... የቢሮው ሃላፊ የመጀመርያ የልጅነት ፍቅሩ ኤልሳ ናት ያየው እውነት ባይሆን ብሎ ተመኝቶ አይኑን ጨፍኖ መልሶ ገለጠው ግን እውነት ኤልሳ ፊትለፊቱ ቆማ እንባዋ ይንቆረቆራል ...
ካንደበቱ ቃል ማውጣት ተስኖት ፈዞ ቀረ ፀሎትም ግራ ገብቷት አንዴ እሱን አንዴ እሷን ታያለች ይሄኔ ኤልሳ "እንዴት ግን አስቻለህ? እኔን ተወኝ በልጅህ እንዴት ጨከንክ?"... አለች ድምጿ እየተቆራረጠ ይሄኔ ሄኖክ ክው አለ ፀሎትም ልጅክ ብላ በድንጋጤ ወደቀች...
.
.
ይቀጥላል
ክፍል 1⃣0⃣
2 297
❤️ ጥላቻ ❤️
❤️ልብ አንጠልጣይ ታሪክ❤️
ክፍል 8⃣
ሄኖክ ከዚ በፊትም ሴት ልጅ መመምታት ተከሶ ስለነበር አሁን የሴቶች ዶርም ሲገኝ በቀጥታ እርምጃ ተወሰደበት ሄኖክ ኤልሳን አግኝቶ በቅጡ እንኳ ሳያወራት ከትምህርት ቤት ተባረረ ... ሄኖክ የሚሄድበት ግራ ገብቶት ባለችው ብር አልጋ እየተከራየ ሁለት ቀን ሆቴል አደረ ከዛ ግን ቁርጡን አውቆ ወደ አዲስ አበባ መምጣትና ስራ እየስራ መኖር እንዳለበት እራሱን አሳመነ ከዛም ባለፈ የሚረዳው ባይኖርም ግን መማር ግዴታው ነው ምክንያቱም ከማንም በታች መሆን አይፈልግም ... ስለፍቅረኛው ኤልሳም እጅግ ይጨነቃል ...
እንዳሰበው ህይወት ቀላል አልሆነችም ምንም ሞያና ዘመድ ሳይኖረው ጥሩ ስራ ማግኘት ይከብዳል ለዛምያገኘው ስራ ቀንስራ ነበርና በ500 ብር ቤት ተከራይቶ ስራ ጀመረ ሄኖክ በርግጥ ውበቱም ሆነ አቋሙ ውብ ነው ይሁንና ይህን ስራ በጀመረ በሳምንቱ ከከለሩ ጀምሮ ሰውነቱ ተቀየረ እንኳን መማር በዚ ስራ ምግብ አቅርቦ መብላት ከበደው ሁሌም ከስራ ተመልሶ የተከራያት ጎጆ ውስጥ ሲገባ እናቱ እንደሞተችበት ህፃን ባለፈ ትዝታው ስቅስቅ ብሎ ያለቅስና ሲደክመው ያንቀላፋል....
በዚ መልኩ እየኖረ ሳለ አንድ ቀን ቤተክርስቲያን ሊሳለም ሲሄድ ያጎቱ ሚስት ሀና በጣም ተጎሳቁላ ያገኛታል ይሄኔ በጣም ደንግጦ ደርቆ ቀረ እሷም አጋጣሚ አይታው ስለነበር ቀርባ ልጄ ብላ ተጠመጠመችበት ... ትንሽ ከተላቀሱ ቡሃላ ወደቤት ላድርስሽ ሲል ፍቃዷን ጠየቀ ተስማምታም ሲሄዱ ያ ሲፈነጥዝ ያደገበት ቤት የለም የወሰደችው ከዛ በተቃራኒ ሲያዩት ሊፈርስ የዘመመ ጠባብ ቤት ነበር በጣም ደንግጦ እናቴ ቤቱስ ሲል ጠየቀ ሀናም እንባ ባቀረሩ አይኖቿ ወደሰማይ አንጋጣ እሱ የስራዬን አይቶ ነጠቀኝ አለች አሁንም እንዳልገባው ለማሳወቅ ማለት? ሲላት "ልጄ አጎትህ መውለድ እንደማልችል ሲያውቅ እላዬ ላይ ሴት ይደርብ ጀመር ከዛም በ2አመት ውስጥ 3 ሴት አስረገዘ ... ከዛ ግን የልጅ አምሮት ሳይሄን ሴሰኝነት ነው እናም ወደ ቀድሞ ማንነትህ ተመለስ ብለው አላርፍ ብሎ ከየት እንዳመጣው ሳይታወቅ የHIV ቫይረስ ተጠቂ ሆንን እናም ብዙ ሳይቆይ እንደምታውቀው ሞተ ... እኔም በንዴት በሀጥያት ተጨማለኩ ፈጣሪ ግን ልክ ስላልነበርኩ አሁን እየቀጣኝ ነው አንተን ልጄን ነጠቀኝ ቤታችንም የመንግስት ነበርና ተወረሰ ልጄ ስራም ስለደከምኩ ተቀነስኩ አሁን ሞቴን እየተጠባበኩ ነው!" አለች እንባዋ መንታ መንታ እየወረደ ሄኖክም በህይወቱ እንደዛ ግዜ አዝኖ አያውቅም ቃል ሳይተነፍስ እያለቀሰ ወጥቶ ሄደ...
ከዛ ለደሞዝ ለሀና ቤት ተከራየላት ከቀን ስራ ከሚያገኛት እየቀነሰ እሷን መርዳት ጀመረ በዛ ኑሮ ትምህርት ቤት ከፍሎ ፍፁም እንደማይሆን አመነ ያዳለፈውን ግዜ ባሰበ ቁጥር ቅስሙ ይሰበራል ሜላት ዶጮ ኤልሳ ሁሉንም አጥቷል ...
ይህ በንዲህ እንዳለ አንድ ቀን ዶጮና ሄኖክ ተገናኙ ዶጮ ሄኖክን ሲመለከተው በጣም አዘነ ለምን እኛ ቤት አልሄድክም ሲል ተቆጣው ሄኖክ ግን ማወቅ የፈለገው ስለ ኤልሳ ጤንነት ነበር ... ዶጮን ስለኤልሳ ሲጠይቀው ሌላ ወሬ ያስቀይስበታል ይሄኔ ዶጮ ስለኤልሳ የማትነግረኝ ለምንድን ነው ወይስ ደና አይደለችም ሲል አፋጠጠው ይሄኔ ዶጮ በጣም እየፈራ ጓደኛዬ የምታፈቅራት ልጅ አሁን ያንተ አይደለችም ከፊዚክስ መምህራችን ጋር የፍቅር ግንኙነት ጀምራ የግቢውን ተማሪ በሙሉ ጉድ አስብላዋለች አለ ይሄኔ ሄኖክ ሰማይ የወረደበት መሰለው ...
.
.
ይቀጥላል
ክፍል 9⃣
