uz
Feedback

Firibgarlarga uchmang! Telemetrio bunday kanallarni topadi va belgilaydi 👉 Belgini ko‘rmoqchi bo‘lsangiz, obuna bo‘ling

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

Kanalga Telegram’da o‘tish

💎ሀያዕ ሲወሳ ለሴት ልጅ ጌጧ ነውና ሁሌም አብራ ትወሳለች፣ #ሴት ልጅና #ሀያዕ አብረው የሚኖሩ መቼም የማይነጣጠሉ ጥምሮች ናቸው። 👉 ሴት ልጅ ስትፈጠርም በሀያዕ ዘውድ አሸብርቃ ነው። 💎ይህንን ዘውድ ከራሷ የገፈፈች ሴት ግን ህያው ከሆኑ ሰዎች መሀል እንደምትንቀሳቀስ በድን ትሆናለች።

Ko'proq ko'rsatish
8 754
Obunachilar
-524 soatlar
-367 kun
-7330 kun
Postlar arxiv
⭕️👉ተከታታይ ስለ ረመዷን አህካም ዳሰሳ 〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰 ↪️ ክፍል ሶስት《0⃣3⃣》 #ህፃን (ለአቅመ አዳም) ያልደረሰ ልጅና ፃም ✅ ህጻን ልጅ ብሉግ (አቅመ አዳም) እስኪደርስ ድረስ ፃም ግደታ አይሆንበትም። ምክንያቱም የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋልና። رُفِع القلم عن ثلاَثَةٍ عَنِ النَّاءِم حتَّ يَستيْقِظ وعنٍِ الصغيرِ يكبُرَ وعنِ المجنُونِ حتَّ يُفِيق ⭕️👉 ከሶስት ሰዎች ላይ ቀለም ተነስቷል። 🔹የተኛ ሰው እስኪነቃ ድረስ 🔹ህጻን ልጅ ብሉግ (አቅመ አዳም) እስኪደርስ 🔹እብድ እስኪነቃ ድረስ 📚ኢማሙ አህመድ፣ አቡ ዳውድ፣ ነሳኢይና ዘግበውታል። ⭕️👉 ስለዚህ በዚህ ሀዲስ መሰረት አቅመ አዳም ያልደረሰ ልጅ ቀለም ስለተነሳለት ለምን አልፃምክም ተብሎ ስለማይጠየቅ ፃም በሱ ላይ ግዴታ አይሆንበትም ማለት ነው። ✅ ነገር ግን ህፃኑ ቢፃም የሚችልና ጉዳት የማያመጣበት ከሆነ አስተዳዳሪዎቹ እንዲጾም ያዙታል። ይህ በማድረጋቸው ልጁ ነገ ትልቅ ሲሆን እንዳይከብደውና እንዳይቸገር ይረዳዋል። ✅ ሶሀቦች የአላህ ሱብሀነሁተአላ ውዳሴ በነርሱ ላይ ይሁንና  ልጆቻቸውን ትንሽ ሁነው ሳለ እንዲጾሙ  ያደርጉዋቸው ነበር። በዚህ መልኩ ከፃሙ በኋላ ወደ መስጅድ ይዘዋቸው ይሄዱና ምግብ ትዝ ብሏቸው ማልቀስ ሲጀምሩ መጫወቻ ነገር በመስጠትና በማጫወት ምግብ እንዲረሱና እንዲዘናጉ ያደርጉዋቸው ነበር። 👉ስለዚህ በዚህ መሰረት ህፃናቶች እንዲፃሙ ማድረግና በዚህ ላይ ማለማመድ የሰለፎችን መንገድ ከመከተል ውስጥ አንዱ ነው። 🚫ስህተት 🚫 〰〰〰〰〰 ◾️ብዙ ወላጆች ልጆቻቸውን ዲንን አያስተምሩም። የወላጅ ትልቁ ሀላፊነት ማብላት፣ ማጠጣትና ማልበስ ብቻ ይመስላቸዋል። ይህ ሊቀረፍ የሚገባ ትልቅ ስህተት ነው። ልጆች ከምግብ ከመጠጥ ከሌላም ነገር በላይ ዲን ያስፈልጋቸዋል። በዘመናችን ብዙ ሙስሊም ወጣቶች አጫሽ፣ ቃሚ፣ ጠጪ፣ ዱርዬ እየሆኑ ያሉት ከቤተሰብ ክትትልና ዲንን ካለማስተማር የተነሳ ነው። ብዙ ወጣቶች ጎልማሳነት እድሜ ላይ ሆነው አርካኑል ኢስላም አያውቁም፣ እስልምና የሚያበላሸውን አይለዩም። የነብያቶችና የሶሀባዎች ምንነትም ሆነ ስም አያውቁም። በተቃራኒው የካፊር ፊልም አክተርና ኳስ ተጫዋች አድናቂ በመሆን የመልእክተኛውን ሱና ትተው በፈረንጆች ፋሽንና ዲዛይን ተሸውዶ ይታያሉ። በአብዘሀኛው የዚህ ሁሉ መንስኤ ገና በልጅነታቸው ዲን ያለማሰረተመሰራችን ውጤት ነው። ◾️አንዳንድ ልጆች ለዲናቸው ካላቸው ፍቅርና ለኢባዳ ካላቸው ውዴታ የተነሳ መፃም ይፈልጋሉ። ነገር ግን አንዳንድ ወላጆች በግድ እንዲያፈጥሩ ሲያደርጓቸው ይታያል። ይህም ሌላኛው ሊቀረፍ የሚገባው ጥፋት ነው። በመፃማቸው ግልፅ የሆነ ጉዳት የማይደርስባቸው ከሆነና አቅሙ እስካላቸው ድረስ ቢፃሙና ቢለማመዱ የተሻለ ነው። ምናልባትም አንዳንድ ወላጆች ይህን በማድረጋቸው ለልጆቻቸው ያዘኑ መስሏቸው ሊሆን ይችላል። ሀቂቃው ግን ይህ ድርጊት ለነሱ ማዘን ሳይሆን እነሱን መበደል ነው። እውነተኛ የልጅ እዝነት ማለት፦ 🔹ቁርአን ማቅራት 🔹ሀዲስን ማስተማር 🔹ሸሪአን ማሳወቅ 🔹በኢስላማዊ ተርብያ ማሳደግና 🔹ኢባዳን ማለማመድ ነው። ◾️ክፍል አራት ይቀጥላል ኢንሻአላህ                ፧              ፧                ፧              ፧      t.me/https_Asselfya      t.me/https_Asselfya

✅ አግባ! ብዙዎች አግብተው ሀብታሞች ሆነዋል፤ ድህነትን #ፈርተህ አንተ ግን ፈዝዘሃል። =

✅ ኢማሙ ኢብኑል ቀይም ረሒመሁሏህ እንዲህ ይላሉ፡- በተወኩል ላይ ተረከዞቹን ያፀና እራሱንም ወደ አላህ ያስጠጋ እንዲሁም እራሱን ታዛዥ ያደረገ ሰው እርካታን ማግኘቱ ቅሮት የለውም።❞              📚مدارج السالكين ٢ / ١٧٣"] t.me/https_Asselfya

―ክፍል (④) 📚الوسائل المفيدة للحياة السعيدة «ደስተኛ ሕይዎት ለመኖር የሚያግዙ ነጥቦች!» የኪታቡ pdfለማገኘት👇 t.me/https_Asselfya/8029

                      ⭕️👉'"ብዙ ነገር ለመማር መሞከር እይታህን ያሰፋል ። የዕይታህ አድማስ ሲሰፋ ደግሞ አንተ እያነስክ ነው የምትሄደው። ...ሰፊ ከሆነው ዓለም ውስጥ አንተ ምን ያህል ኢምንት እንደሆንክ ትረዳለህ። እያወክ ስትሄድ ትልቅነትህን ሳይሆን ትንሽነትህን ነው ምትረዳው። እያወክ ስትሄድ በአለም ዙሪያ በተፈጠረው እውቀት ውስጥ አንተ ትንሽ መሆንህ ይገባሀል።" ~ስኬታማ ሰዎች አዳዲስ ነገሮችን ከህይወትና ከንባብ ለመማር ዝግጁ ናቸው! ~ስኬታማ ያልሆኑ ሰዎች በአንጻሩ እራሳቸውን በጣም ብልሆች እንደሆኑና ሁሉንም እንደሚያውቁ ስለሚያስቡ አዳዲስ ነገሮችን ለመማር ዝግጁ አይደሉም። ⭕️👉ስለዚህ በህይወትህ መድረስ የምትፈልግበት ቦታ ለመድረስ ሁሌ አዳዲስ ነገሮችን እና ሃሳቦችን ለማወቅ አእምሮህን ክፍት አድርገው። ~ እና ..አንብብ!      t.me/https_Asselfya

﴿أَقِمِ الصَّلاةَ لِدُلوكِ الشَّمسِ إِلى غَسَقِ اللَّيلِ وَقُرآنَ الفَجرِ إِنَّ قُرآنَ الفَجرِ كانَ مَشهودًا﴾ هزاع البلوشي

⭕️👉ተከታታይ ስለ ረመዷን አህካም ዳሰሳ                ➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖ 【ክፍል ሁለት 0⃣2⃣】 〰〰〰〰〰〰 ◾️ካፊር እና ፃም 〰〰〰〰〰〰 ↪️ 【ነጥብ አንድ】👉 ካፊር ቢፃም ፃሙ ተቀባይነት ያገኛልን⁉️ 〰〰〰〰 ◾️ካፊር የሆነ ሰው በኩፍሩ እስካለ ድረስ ረመዷንን መጾም ግዴታ አይሆንበትም። ቢፃም ራሱ ረሀብና ጥማት ከማትረፍ ውጪ ተቀባይነት አይኖረውም። ነገር ግን ይህ ማለት ነገ አላህ ፊት አይጠየቅበትም ማለት አይደለም። ምክንያቱም ማንኛውም ስራ አላህ ዘንድ ተቀባይነት ይኖረው ዘንድ እነዚህ ሶስት መስፈርቶች የግድ መሟላት አለባቸው። ① ኢስላም ② ኢኽላስ ③ ሙታበአ ስለዚህ ካፊር የተውሂድ ባለቤት ስላልሆነ ማንኛውም መልካም ስራ ቢሰራ ተቀባይነት አያገኝም ውድቅ ይሆናል። ↪️ 【ነጥብ ሁለት】👉 ካፊር የነበረ ሰው በረመዷን በቀኑ ክፍለ ጊዜ ቢሰልም⁉️ ✅ አንድ ሰው ረመዷን ከመግባቱ በፊት ቢሰልም ከመስለምሙ በፊት ያሳለፋቸው ያልፃማቸው አመታቶች ቀዷ አውጣ ወይም ፁም አይባልም። 📍አንድ ሰው ረመዷን ወር ላይ የተወሰኑ ቀናቶች ካለፋ በኋላ ቢሰልም እነዛ የሰለመበት ወር ላይ ከመስለሙ በፊት ሳይፃም ያሳለፋቸው የተወሰኑ ቀናቶች ቀዷ አውጣ አይባልም። ⭕️👉 አንድ ሰው ረመዷን ላይ በቀኑ ክፍለ ጊዜ ቢሰልም ከዛ ከሰለመበት ሰአት ጀምሮ ከምግብ ከመጠጥ መታቀብ ግድ ይለዋል። ምክንያቱም ልክ እንደሰለመ ረመዷን መፃም ግዴታ ከሆነባቸው ሰዎች ቁጥር ውስጥ ይገባል። ነገር ግን የዛን ቀን ቀዷ አውጣ በምትኩ በሌላ ቀን ፁም አይባልም። ምክንያቱም ይህ ሰው ፃም መያዝ ግዴታ በሆነበት ሰአት (ፈጅር) ላይ ሙስሊም ባለመሆኑ ቀዷ ማውጣት ግደታ ከሚሆንባቸው ሰዎች ውስጥ አይመደብም። ◾️ለዚህ መረጃው የአላህ ሱብሀነሁ ተአላ ንግግር ነው 〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰 ◾️قُل لِّلَّذِينَ كَفَرُوٓا۟ إِن يَنتَهُوا۟ يُغْفَرْ لَهُم مَّا قَدْ سَلَفَ ለነዚያ ለካዱት በላቸው፡- ቢከለከሉ (ቢቶብቱ) ለእነሱ በእርግጥ ያለፈውን (ሥራ) ምሕረት ይደረግላቸዋል፡፡ 🔘 ክፍል ሶስት ይቀጥላል ኢንሻአላህ                ፧              ፧                ፧              ፧ t.me/https_Asselfya t.me/https_Asselfya

―ክፍል (③) 📚الوسائل المفيدة للحياة السعيدة «ደስተኛ ሕይዎት ለመኖር የሚያግዙ ነጥቦች!» የኪታቡ pdfለማገኘት👇 t.me/https_Asselfya/8029

~በሕይወት  ትልቁ  ቁም  ነገር  ትምህርት  መውሰድ  ነው፡፡ መቼም በስለንም አውቀንም አንጨርስም። ባወቅን ቊጥር ብዙ ቀዳሚ አላዋቂነታችን  ይታወሰናል፡፡  ሁሌም  እንማር፣  ሁሌም  ለመለወጥ ዝግጁ  እንኹን፣  ሁሌም  ብሩሕ  ተስፋ  ይኑረን፡፡  ብልህ  ሰው  ዛሬ  ላይ ዐዋቂ  ነኝ፣  ትክክል  ነኝ፣  እኔ  ብቻ  የሚል  ሳይኾን  ዛሬ  ላይ የሕይወትን  ትምህርት  ከሕፃናት  ሳይቀር  ለመማር  የተዘጋጀ  ነው፡፡"        ~                   t.me/https_Asselfya

القارئ_ياسر_الدوسري_|_وأتموا_الحج.mp32.67 MB

📍በቁርአን እንተዋወስ!      〰️〰️〰️〰️〰️〰️ ▪️وَيَوْمَ يُحْشَرُ أَعْدَآءُ ٱللَّهِ إِلَى ٱلنَّارِ فَهُمْ يُوزَعُونَ የአላህም ጠላቶች ወደ እሳት የሚሰበሰቡበትን ቀን (አስታውስ)፡፡ እነርሱም የሚከመከሙ ኾነው ይነዳሉ፡፡ ▪️حَتَّىٰٓ إِذَا مَا جَآءُوهَا شَهِدَ عَلَيْهِمْ سَمْعُهُمْ وَأَبْصَٰرُهُمْ وَجُلُودُهُم بِمَا كَانُوا۟ يَعْمَلُونَ ጀሀነምን በመጧትም ጊዜ ጆሮዎቻቸው፣ ዓይኖቻቸውና ቆዳዎቻቸውም ይሠሩት በነበሩት ነገር በእነርሱ ላይ ይመሰክሩባቸዋል፡፡ ▪️وَقَالُوا۟ لِجُلُودِهِمْ لِمَ شَهِدتُّمْ عَلَيْنَا ۖ قَالُوٓا۟ أَنطَقَنَا ٱللَّهُ ٱلَّذِىٓ أَنطَقَ كُلَّ شَىْءٍۢ وَهُوَ خَلَقَكُمْ أَوَّلَ مَرَّةٍۢ وَإِلَيْهِ تُرْجَعُونَ ለቆዳዎቻቸውም «በእኛ ላይ ለምን መሰከራችሁብን?» ይላሉ፡፡ «ያ አንዳቹን ነገር ሁሉ ያናገረው አላህ አናገረን፡፡ እርሱም በመጀመሪያ ጊዜ ፈጠራችሁ፡፡ ወደእርሱም ትመለሳላችሁ» ይሏቸዋል። ▪️وَمَا كُنتُمْ تَسْتَتِرُونَ أَن يَشْهَدَ عَلَيْكُمْ سَمْعُكُمْ وَلَآ أَبْصَٰرُكُمْ وَلَا جُلُودُكُمْ وَلَٰكِن ظَنَنتُمْ أَنَّ ٱللَّهَ لَا يَعْلَمُ كَثِيرًۭا مِّمَّا تَعْمَلُونَ ጆሮዎቻችሁ ዓይኖቻችሁና ቆዳዎቻችሁም በእናንተ ላይ ከመመስከራቸው የምትደበቁ አልነበራችሁም፡፡ ግን አላህ ከምትሠሩት ብዙውን አያውቅም ብላችሁ ጠረጠራችሁ፡፡ 📚(ሱረቱል ፉሲለት 19_22)     t.me/https_Asselfya

የወደክበትን ቦታ ሳይሆን ያንዳለጠህን ቦታ አብዝተህ እየዉ ነገ መልሶ እንዳያንዳልጥህ  ትጠነቀቃለህ !! = http://t.me/https_Asselfya

አንዳንድ ጊዜ ምንም እንደማያገባን ነገር ሆነን፣ ሳንሸበር ሳንጨነቅ፣ ምን ጉዳዬ ምን አገባኝ ብለን ሕይወትን ዝምብለን ስንኖራትም  ደስ ይላል። ~ t.me/https_Asselfya

👉⭕️ተከታታይ ፅሁፍ ስለረመዷን አህካም ዳሰሳ ➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖ 【ክፍል አንድ 0⃣1⃣】 〰〰〰〰〰〰〰 〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰 👉ረመዷንን ግዴታ የሚሆንባቸው ሰዎች ረመዷን በገባ ወቅት በትኩሱ (ቀዷ ሳያደርጉ) መፃም ግዴታ የሚሆንባቸው አካላቶች ⭕️👉ከታች የተዘረዘሩትን መስፈርት ያሟላ ማንኛውም ሰው ረመዷንን መፃም ግዴታ ይሆንበታል። ፃሙንም አላህ ዘንድ ተቀባይነት ያገኛል። ከወቅቱ ማዘግየት ግን አይፈቀድለት። እነዚህ መስፈርቶች፦ ▪️ሙስሊም የሆነ👉 ካፊር ይወጣል ▪️ለአቅመ አዳም የደረሰ👉 ህፃን ይወጣል ▪️አቅሉ ጤነኛ የሆነ👉 እብድ ይወጣል ▪️መንገደኛ ያልሆነ👉 ሙሳፊር ይወጣል ▪️መፆም የሚችል👉 የማይችል ሰው ይወጣል ▪️ጾምን ከልካይ ከሆኑ ነገሮች ሰላም የሆነ▪️ ፃም ከልካይ ምክንያት ያለበት ይወጣል ✅ ይህንን መስፈርት ያሟላ ሰው ወዳው በግዜው መጾም እንዳለበት የቁረአንና የሀድስ መረጃ እንዲሁም የሙስሊሞች ስምምነት ያመላክታል። ◾️ شَهْرُ رَمَضَانَ ٱلَّذِىٓ أُنزِلَ فِيهِ ٱلْقُرْءَانُ هُدًۭى لِّلنَّاسِ وَبَيِّنَٰتٍۢ مِّنَ ٱلْهُدَىٰ وَٱلْفُرْقَانِ ۚ فَمَن شَهِدَ مِنكُمُ ٱلشَّهْرَ فَلْيَصُمْهُ ۖ ➀(እንድትጾሙ የተጻፈባችሁ) ያ በርሱ ውስጥ ለሰዎች መሪ ከቅን መንገድና (ሀቅና ከባጢል) ከሚለዩም ገላጮች (አንቀጾች) ሲኾን ቁርኣን የተወረደበት የረመዳን ወር ነው፡፡ ከእናንተም ወሩን ያገኘ ይፁም። ✅‏ قال النبيﷺ: ((إذا رأيْتُمُ اله‍لالَ فصُومُوا)) ➁【ጨረቃን ባያችሁ ግዜ ረመዷንን ጹሙ】 📚 مُتَّفَقٌ عَليْهِ ➂ ከላይ የጠቀስናቸው መስፈርቶች ያሟሉ ሰዎች ረመዷንን ያለ ቀዷእ ወዳው በትኩሱ እንደገባ መፃም ግዴታ በመሆኑ ላይ የሙስሊሞች ስምምነት እንዳለ ኢብኑ ኡሰይሚን ገልፀዋል። 📚 مجالس شهر رمضان (٤٦) 🔘 ክፍል ሁለት ይቀጥላል ኢንሻአላህ                ፧              ፧                ፧              ፧ t.me/https_Asselfya