💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
Kanalga Telegram’da o‘tish
💎ሀያዕ ሲወሳ ለሴት ልጅ ጌጧ ነውና ሁሌም አብራ ትወሳለች፣ #ሴት ልጅና #ሀያዕ አብረው የሚኖሩ መቼም የማይነጣጠሉ ጥምሮች ናቸው። 👉 ሴት ልጅ ስትፈጠርም በሀያዕ ዘውድ አሸብርቃ ነው። 💎ይህንን ዘውድ ከራሷ የገፈፈች ሴት ግን ህያው ከሆኑ ሰዎች መሀል እንደምትንቀሳቀስ በድን ትሆናለች።
Ko'proq ko'rsatish8 754
Obunachilar
-524 soatlar
-367 kun
-7330 kun
Postlar arxiv
አንዳንድ ጊዜ ምንም እንደማያገባን ነገር ሆነን፣ ሳንሸበር ሳንጨነቅ፣ ምን ጉዳዬ ምን አገባኝ ብለን ሕይወትን ዝምብለን ስንኖራትም ደስ ይላል።
~
t.me/https_Asselfya
👉⭕️ተከታታይ ፅሁፍ ስለረመዷን አህካም ዳሰሳ
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
【ክፍል አንድ 0⃣1⃣】
〰〰〰〰〰〰〰
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
👉ረመዷንን ግዴታ የሚሆንባቸው ሰዎች
ረመዷን በገባ ወቅት በትኩሱ (ቀዷ ሳያደርጉ) መፃም ግዴታ የሚሆንባቸው አካላቶች
⭕️👉ከታች የተዘረዘሩትን መስፈርት ያሟላ ማንኛውም ሰው ረመዷንን መፃም ግዴታ ይሆንበታል። ፃሙንም አላህ ዘንድ ተቀባይነት ያገኛል። ከወቅቱ ማዘግየት ግን አይፈቀድለት። እነዚህ መስፈርቶች፦
▪️ሙስሊም የሆነ👉 ካፊር ይወጣል
▪️ለአቅመ አዳም የደረሰ👉 ህፃን ይወጣል
▪️አቅሉ ጤነኛ የሆነ👉 እብድ ይወጣል
▪️መንገደኛ ያልሆነ👉 ሙሳፊር ይወጣል
▪️መፆም የሚችል👉 የማይችል ሰው ይወጣል
▪️ጾምን ከልካይ ከሆኑ ነገሮች ሰላም የሆነ▪️ ፃም ከልካይ ምክንያት ያለበት ይወጣል
✅ ይህንን መስፈርት ያሟላ ሰው ወዳው በግዜው መጾም እንዳለበት የቁረአንና የሀድስ መረጃ እንዲሁም የሙስሊሞች ስምምነት ያመላክታል።
◾️ شَهْرُ رَمَضَانَ ٱلَّذِىٓ أُنزِلَ فِيهِ ٱلْقُرْءَانُ هُدًۭى لِّلنَّاسِ وَبَيِّنَٰتٍۢ مِّنَ ٱلْهُدَىٰ وَٱلْفُرْقَانِ ۚ فَمَن شَهِدَ مِنكُمُ ٱلشَّهْرَ فَلْيَصُمْهُ ۖ
➀(እንድትጾሙ የተጻፈባችሁ) ያ በርሱ ውስጥ ለሰዎች መሪ ከቅን መንገድና (ሀቅና ከባጢል) ከሚለዩም ገላጮች (አንቀጾች) ሲኾን ቁርኣን የተወረደበት የረመዳን ወር ነው፡፡ ከእናንተም ወሩን ያገኘ ይፁም።
✅ قال النبيﷺ: ((إذا رأيْتُمُ الهلالَ فصُومُوا))
➁【ጨረቃን ባያችሁ ግዜ ረመዷንን ጹሙ】
📚 مُتَّفَقٌ عَليْهِ
➂ ከላይ የጠቀስናቸው መስፈርቶች ያሟሉ ሰዎች ረመዷንን ያለ ቀዷእ ወዳው በትኩሱ እንደገባ መፃም ግዴታ በመሆኑ ላይ የሙስሊሞች ስምምነት እንዳለ ኢብኑ ኡሰይሚን ገልፀዋል።
📚 مجالس شهر رمضان (٤٦)
🔘 ክፍል ሁለት ይቀጥላል ኢንሻአላህ
፧ ፧
፧ ፧
t.me/https_Asselfya
~ስህተቴን ፊት ለፊቴ ለነገረኝ፣ በመልካም ስራዬን ፊትለፊቴ ላላሞገሰኝ! የአላህ እዝነት ይውረድ!!
~
አላህ መልካም ምንዳቸዉን ይክፈላቸዉ
በጣም አሪፍ አፕ ነዉ አዉርዳችሁ እንደፈለጋችሁ ተጠቀሙ ለዘመድ አዝማድ ላኩላቸዉ ያዉርዱት
.
―ክፍል (②)
📚الوسائل المفيدة للحياة السعيدة
«ደስተኛ ሕይዎት ለመኖር የሚያግዙ ነጥቦች!»
ዒልም ፈላጊ - የሞባይል መተግበሪያ
• መተግበሪያው ከያዛቸው በጥቂቱ፦
- ከ40 በላይ የሱና ኡስታዞችን ደርሶች፣
- የዐቂዳ፣ የተውሒድ፣ የመንሀጅ ኪታቦችን፣
- እያንዳንዱ የድምፅ ቅጂ ከሶፍት ኮፒ ጋር
- የቀን እና የማታ ገፅታ ያካተተ፣
- የፅሁፍ መጠን መጨመርና መቀነስ፣
- የጀማሪ ኪታቦችን ለብቻ የሚያሳይ፣
- የደርስ ሰአት እና ቀን አስታዋሽ ያለው፣
- ደርሱን ብናቋርጠው ሌላ ጊዜ ካቆመበት የሚጀምር፣
- አድስ ደርስ ሲጫን መልእክት የሚቀበል ነው።
• መተግበሪያውን በሚከተለው ሊንክ ያውርዱ፦
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.aj.islamic_online_learning
بـــسم اللهِ الرَّحمنِ الرَّحـيم
وبـه نَستعين عونَك يا كريم
• ዒልም ፈላጊ:
ይህ የሞባይል መተግበሪያ፦
- ከ40 በላይ የሱና ኡስታዞችን ደርሶች፣
- ዘርፈ ብዙ ፈኖችን: የዐቂዳ፣ የተውሒድ፣ የመንሀጅ፣ የተፍሲር፣ የሲራ፣ የአደብ፣ የተርቢያ፣ የሐዲሥ፣ የፊቅህ፣ የነሕው፣ የሶርፍ እና የተጅዊድ ኪታቦችን፣
- እያንዳንዱ የድምፅ ቅጂ ከሶፍት ኮፒ ጋር
- ከ150 በላይ የኪታብ ቅጅዎችን፣ በአንድ ላይ አካቶ ይዟል።
• አፑን ለአጠቃቀም ምቹ ከሚያደርጉት ነገራቶች፦
- የፈለጉትን ደርስ በቀላሉ ለማግኘት ምልክት ማድረግ የሚያስችል፣
- ከቅጅዎቹ መካከል መርጠው ለሌሎች ማጋራት የሚያስችል፣
- ለእይታ አመቺ ይሆን ዘንድ የቀንና የማታ ገፅታ ያካተተ፣
- የፅሁፍ መጠን መጨመርና መቀነስ የሚያስችል፣
- የፈለጉትን ደርስ ‘ሰርች’ ማድረጊያ ያለው፣
- የአፑን አጠቃቀም የሚያሳይ፣
- የጀማሪ ኪታቦችን ለብቻ የሚያሳይ፣
- የደርስ ሰአት እና ቀን አስታዋሽ (alarm) ያለው፣
- ደርሱን አቋርጠን በሌላ ጊዜ ማዳመጥ ብንፈልግ ካቆመበት የሚጀምር፣
- አድስ ደርስ ሲጫን መልእክት የሚቀበል ነው።
• በመጨረሻም፦
ይህ ስራችን የላቀው አላህን ፊት ብቻ ተፈልጎበት የተሰራ እንዲሆን፣ ደርሶችን ከተለያዩ የቴሌግራም ቻናሎች ላሰባሰበው፣ አፑን ላዘጋጀው፣ በዚህ ስራ ለተባበሩ፣ ይህንን ስራ ለሚያሰራጩትም፣ ለሁላችንም - አላህ: "ከኋለኞቹ ህዝቦች ዘንድ መልካም ዝናን እንዲያደርግልን" እማፀነዋለሁ። ረበና ተቀበል ሚና!!
አፕልኬሽን ስራ፡ አብዱረሕማን ጀማል
አፑን በሚከተለው ሊንክ ይጫኑ፦
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.aj.islamic_online_learning
🛑👉በጉጉት ሲጠበቅ የነበረ ፕሮግራም ሊጀመር ነዉ
ገባ ገባ በሉ➘➘➘➘➘➘➘➘➘
https://t.me/Ye_kombolcha_Ansuar_Mesjid_Jemea?videochat
VID_20210528_213317_315_٢٠٢١٠٥٢٨٢١٤٢١٨٥٤٨_a01.mp32.51 MB
* [ ታላቅ የዳዕዋ ፕሮግራም ] *
••••••••••••••••••••••
ነገ
ጁመአ በኮምቦልቻ አንሷር መስጅድ የቴሌግራም ግሩፕ የሚቀርብ ከምሽቱ 2:30 ጀምሮ የሙሀደራ ፕሮግራም በቀጥታ(live) ተደግሶላችኋል ።በዕለቱም የተጋበዙ ውድ ወንድሞቻችን ➧ ወንድም አቡ ኡበይዳ ሰኢድ ➧ወንድም አቡ ሂበቲላህ ሁሴን ኢስማኢል ➧ወንድም አቡ አዩብ ሙሐመድ ሰኢድ ➧ ወንድም አቡ ሐፍሷ ኢማም ➧ ወንድም አቡ ሀሳን ዐልይ እና ሌሎችም ተጋባዥ እንግዶች ይሳተፋሉ። ➧ በሰአቱ የጥያቄ እና መልስ ውድድር አለ ለአሸናፊውም ለየት ያለ ሽልማት ተዘጋጅቷል:: ➧ የጨረታ ፕሮግራምም አለ የመስጅዳችን ጉዳዬ አሳሳቢና አንገብጋቢ ስለሆነ
እንዳትቀሩ አደራ ጠርቻችኋለሁ።ፕሮግራም መሪ አቡ ማሒ ሙሐመድ بن ኢድሪስ ቀን - የካቲት 8- 2016 ሰዓት -ከምሽቱ 2:30 ቦታ - በኮምቦልቻ መስጅደል አንሷር የቴሌግራም ግሩፕ https://t.me/Ye_kombolcha_Ansuar_Mesjid_Jemea
⭕️👉የሒጃብ ጥፍጥና እና ስለሒጃብ የተሣሣቱ ግንዛቤዎች መነበብ ያለበት ስለሒጃብ ጠቃሚ ተከታታይ ፁሑፍ።
➡️ክፍል. ➀
t.me/https_Asselfya/7930
t.me/https_Asselfya/7930
➡️ክፍል .➁
t.me/https_Asselfya/7940
t.me/https_Asselfya/7940
➡️ክፍል .⓷
t.me/https_Asselfya/7956
t.me/https_Asselfya/7956
➡️ክፍል .➃
t.me/https_Asselfya/7975
t.me/https_Asselfya/7975
➡️ክፍል .➄
t.me/https_Asselfya/7992
t.me/https_Asselfya/7992
➡️ክፍል .➅
t.me/https_Asselfya/8006
t.me/https_Asselfya/8006
➡️ክፍል .➆
t.me/https_Asselfya/8028
t.me/https_Asselfya/8028
➡️ክፍል .➇
《ሒጃብሽን ልበሽ!》
ሂጃብሽን ለብሰሽ ቅርፅሽን ሸፍኚ:
አንች ውድ ሴት ነሽ እርካሽ አትሁኚ:
ሒጃቡን ስትለብሽ መስፈርቱን እወቂ:
ሣታውቂ ብትለብሽ አይሆንም ዘላቂ:
ታሪኳን ስሚላት ያችን ጀግና እንስት :
ሒጃቧን አውልቂ ብሎ ሲመጣባት :
ጦሯን ያነገበች ሰይፏንም የሳለች:
ሒጃቤ ከሚወልቅ ደሜ ይፍሰስ ያለች:
ስንት ጀግና አለች ለሒጃብ የቆመች:
ይች ሴት እያለች ብርታት አስተማሪ :
በሒጃብ ተውባ ወደ ኢስላም ጠሪ :
እህቴ ነይ ስትል ሒጃብሽን ልበሽ:
አንች አፈንግጠሽ ይሄው ተራቆትሽ:
ኩፋርን በፋሽን እየተከተልሽ:
እህት ይበቃሻል አሁን ግን ተመለሽ:
መስፈርቱን አሟልተሽ ሒጃብሽን ልበሽ:
~
~አላህ ሆይ!!
〰️〰️〰️
የማያልቅ ሶብር ስጠን፣
የማያረጅ ኢማን አልብሰን፣
የማይደክም ተስፋ ለግሰን፣
የማይዘነጋ ቀልብ ሸልመን፣
የማይሰንፍ ጉልበትም ቸረን፣
ከባዱን ሁሉ አግራልን፣
መልካሙን ሁሉ ወፍቀን።
ጠግነን፣ ጠግነን፣ ጠግነን ...ያ ረብ።
~
𝐓𝐞»t.me/https_Asselfya
⭕️👉 የመጨረሻ ክፍል ስምንት‼️
ውድ እህቴ ! አላህን ለማስደሰት ምን
ማድረግ አለብን? እንግድህ እስካሁን በዘረዘር ናቸው ሂጃብን አስመልክቶ በየቦታው የሚገኙ የተሳሳቱ እሳቤወች (misconception) ካስወገድን የብዙ እህቶቻችንንም የተለያዩ ግላዊ( ከነፍሲያ) የሆኑ ፍላጎቶችን ካጋለጥንና እየመረመርን ከተቸን ቡኋላ!
⭕️👉ጉዳዩን ሲጠቃለል ውዷ እህቴ! ወኔ የተሞላበት ውሳኔ በማድረግሽ ህይወትሽ ወዲያውኑ የሚለወጥ ሲሆን ይህም ለውጥ የተሻለና ያማረ መሆኑ እርግጥ ነው ።ይህን ውሳኔ ስታደርጊ ልብሽን ንፁህ እውነተኛ መሆኑን ቀድመሽ እርግጠኛ ሁኝ ያኔ አላህ ለመወሰን የሚገጥምሽን ማመንታትና ፈተና ገር ያድርግልሻል።
~ከዚህ ቡሃላ ሂጃብ ለመልበስ መወሰን የሚኖርብሽ ትክክለኛው ጊዜ አሁን ነው ። ይህን በስብዕናሽ ላይ ታላቅ ለውጥ የሚያመጣት ውሳኔ ለሚቀጥለው ረመዳን፣ ለአድስ አመት ወይ ትዳር ስይዝ እያልሽ እንዳታራዝሚው አደራ‼️ እነዚህ ሁሉ ሰበቦች ራስሽን የምታታልይባቸው ምክንያቶች ከመሆን ያልዘለሉና የሸይጧን ጉትጎታ ውጤቶች ብቻ ናቸው። ይህን ወርቃማ ውሳኔ ከማሳለፍ ወደ ኋላ የምትጎተችበት ሁኔታ ህይወትሽ የሚሻሻልበት እንቅስቃሴዎች በመሙላቱ ስኬት የሚያገኝበትና በመጠቃቀሚያዋ(መደሰቻዋ) ጀነት ደረጃሽ የሚያድግበት እድልን አበላሽቶ በምትኩ ለሸይጧን ጉትጎታ እጂ እንድትሰጭ በማድረግ ቀደምት ሙስሊም እንስቶች ከሚያገኙት ምንዳ እጣ እንዳይኖርሽ ያደርጋል። ይህ ዛሬ ነገ ማለት እጅግ አደገኛ የሆነ የድብብቆሽ ጨዋታ መሆኑን ተረድተሽ በጊዜ ካላስወገድሽው መጨረሻሽ የማያምርና የታላቅ ፀፀት ባለቤት ሆነሽ መቅረትሽ የማይቀር መሆኑን ተረጂው።
✅ እህቴ ሆይ ! ፍጠኝ ! እድሱን ህይወትሽን በጠራ መነሳሳት (ኒያ) በመጀመር በልቦናሽ ውስጥ ሸይጧን አንዳች መዕክት እንዳያኖር ቦታ ንፈጊው። #ሒጃብ_ማለት_!አዎ!እርሱ #የአሸናፊነት_አክሊልና_የመመራት_ብርሃን ነው። ልበሽው !ከዚያም በቅርቢቱ ዓለም ክብርና መታፈርን ለራስሽ አድርገሽ ለመጭው አለምም በመንደላቀቂያዋ ጀነት ቦታሽን ታስከብሪያለሽ ። አዎ እህቴ ሆይ ያለ ማመንታት ሒጃብሽን ልበሽው ጨርሻለሁ።
⭕️👉ወደ አላህ ተመልሰን ለሁላችንም ይቅርታ እንድያደርግልን ስንጠይቅ የሚከተለውን የቁርአን አንቀፅ ታላቅ ግምት ሰጥተን በማጤን በማስተንተን ነው ። አላህ ﷻ በተከበረው ቃሉ በሱረቱል ዙመር ከአንቀፅ 54_58 እንድህ ይለናል፦
قُلْ يَٰعِبَادِىَ ٱلَّذِينَ أَسْرَفُوا۟ عَلَىٰٓ أَنفُسِهِمْ لَا تَقْنَطُوا۟ مِن رَّحْمَةِ ٱللَّهِ إِنَّ ٱللَّهَ يَغْفِرُ ٱلذُّنُوبَ جَمِيعًا إِنَّهُۥ هُوَ ٱلْغَفُورُ ٱلرَّحِيمُ۞
በላቸው «እናንተ በነፍሶቻችሁ ላይ ድንበር ያለፋችሁ ባሮቼ ሆይ! ከአላህ እዝነት ተስፋ አትቁረጡ፡፡ አላህ ኃጢኣቶችን በመላ ይምራልና፡፡ እነሆ እርሱ መሓሪው አዛኙ ነውና፡፡
وَأَنِيبُوٓا۟ إِلَىٰ رَبِّكُمْ وَأَسْلِمُوا۟ لَهُۥ مِن قَبْلِ أَن يَأْتِيَكُمُ ٱلْعَذَابُ ثُمَّ لَا تُنصَرُونَ۞
«ቅጣቱም ወደእናንተ ከመምጣቱና ከዚያም የማትርረዱ ከመኾናችሁ በፊት ወደ ጌታችሁ (በመጸጸት) ተመለሱ፡፡ ለእርሱም ታዘዙ፡፡
وَٱتَّبِعُوٓا۟ أَحْسَنَ مَآ أُنزِلَ إِلَيْكُم مِّن رَّبِّكُم مِّن قَبْلِ أَن يَأْتِيَكُمُ ٱلْعَذَابُ بَغْتَةً وَأَنتُمْ لَا تَشْعُرُونَ۞
«እናንተ የማታውቁ ስትኾኑም ቅጣቱ በድንገት ሳይመጣባችሁ በፊት ከጌታችሁ ወደናንተ የተወረደውን መልካሙን (መጽሐፍ) ተከተሉ፡፡»
أَن تَقُولَ نَفْسٌ يَٰحَسْرَتَىٰ عَلَىٰ مَا فَرَّطتُ فِى جَنۢبِ ٱللَّهِ وَإِن كُنتُ لَمِنَ ٱلسَّٰخِرِينَ۞
(የካደች) ነፍስ «እኔ ከሚሳለቁት የነበርኩ ስኾን በአላህ በኩል ባጓደልኩት ዋ ጸጸቴ» ማለቷን (ለመፍራት)፤
أَوْ تَقُولَ لَوْ أَنَّ ٱللَّهَ هَدَىٰنِى لَكُنتُ مِنَ ٱلْمُتَّقِينَ۞
«አላህ በመራኝ ኖሮ ከሚጠነቀቁት እኾን ነበር» ማለቷን (ለመፍራት)፡፡
أَوْ تَقُولَ حِينَ تَرَى ٱلْعَذَابَ لَوْ أَنَّ لِى كَرَّةً فَأَكُونَ مِنَ ٱلْمُحْسِنِينَ۞
ወይም ቅጣቱን በምታይ ጊዜ «ለእኔ (ወደ ምድረ ዓለም) አንድ ጊዜ መመለስ በኖረኝና ከበጎ አድራጊዎቹ በኾንኩ» ማለቷን (ለመፍራት መልካሙን ተከተሉ)፡፡
⭕️👉በዚህ ተጠናቋል!!
〰️〰️〰️〰️〰️
ቅድሚያ ይችን አጠር መጠን አድርጋ ላዘጋጀችልን ዉዷ እህቴ በዱኒያም በአኼራም መልካሙን ሁሉ ይግጠማት እያልኩ።የተወሰኑ ነገሮችን በማስተካከል ስታቀርብላችሁ ለነበረችዉ እህታችሁ በዱአችሁ አትርሷት። ስለተከታተላችሁን እናመሰግናለን።እናንተም ባነበባችሁት እኛም ባስተላለፍነዉ አላህ ተጠቃሚዎች ያድርገን።
👉ኢንሻአላህ ትሠበሰባለች!
𝐓𝐞»t.me/https_Asselfya