uz
Feedback

Firibgarlarga uchmang! Telemetrio bunday kanallarni topadi va belgilaydi 👉 Belgini ko‘rmoqchi bo‘lsangiz, obuna bo‘ling

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Kanalga Telegram’da o‘tish

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Ko'proq ko'rsatish

📈 Telegram kanali Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት analitikasi

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) Amxar til segmentidagi kanali faol ishtirokchi. Hozirda hamjamiyat 15 948 obunachidan iborat bo'lib, Din & Maʼnaviyat toifasida 5 316-o'rinni va Efiopiya mintaqasida 2 234-o'rinni egallagan.

📊 Auditoriya ko‘rsatkichlari va dinamika

невідомо sanasidan buyon loyiha tez o‘sib, 15 948 obunachiga ega bo‘ldi.

21 Oktabr, 2026 dagi oxirgi ma’lumotlarga ko‘ra kanal barqaror faollikka ega. Oxirgi 30 kunda obunachilar soni 408 ga, so‘nggi 24 soatda esa 1 ga o‘zgardi va umumiy qamrov yuqori darajada qolmoqda.

  • Tasdiqlash holati: Tasdiqlanmagan
  • Jalb etish (ER): Auditoriya o‘rtacha 25.79% darajada jalb etiladi. Nashrdan keyingi dastlabki 24 soatda kontent odatda umumiy obunachilar sonining 10.92% ini tashkil etuvchi reaksiyalarni to‘playdi.
  • Post qamrovi: Har bir post o‘rtacha 4 113 marta ko‘riladi; birinchi sutkada odatda 1 742 ta ko‘rish yig‘iladi.
  • Reaksiyalar va o‘zaro ta’sir: Auditoriya faol: har bir postga o‘rtacha 29 ta reaksiya keladi.

📝 Tavsif va kontent siyosati

Muallif resursni shaxsiy fikrni ifoda etish maydoni sifatida ta’riflaydi:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”

Yuqori yangilanish chastotasi (oxirgi ma’lumot 22 Oktabr, 2026 da olingan) sababli kanal doimo dolzarb va katta qamrovli bo‘lib qoladi. Analitika auditoriya kontent bilan faol hamkorlik qilishini, uni Din & Maʼnaviyat toifasidagi muhim ta’sir nuqtasiga aylantirishini ko‘rsatadi.

15 948
Obunachilar
+124 soatlar
+1627 kun
+40830 kun
Postlar arxiv
እንኳን አደረሳቹህ #ታኅሣሥ_፲፱ #በዓለ_ቅዱስ_ገብርኤል፤ #ወሥርዐተ_ማኅሌት፡፡ ቅዱስ ገብርኤል፤ #ሊቀ_መላእክት_በመላእክት_ሁሉ_ላይ_የተሾመ_ነው_ሄኖክ_10፥14 #የአርባብ_የ10ሩ_ነገደ_መላእክት_አለቃ_ነው #ከከበሩ_መላእክት_አንዱ_ነው_ሄኖክ_6፥7፤ #አካሉ እንደ ቢረሌ የሚመስል (ጽሩይ የሆነ) ፥ ፊቱም እንደ መብረቅ አምሳያ የሆነ፤ ዐይኖቹም እንደሚንበለበል ፋና፣ ክንዶቹና እግሮቹም እንደ ጋለ ናስ፣ የቃሉም ድምፅ እንደ ብዙ ሕዝብ ድምፅ ነው፡፡/ዳን.10፥5-9/ #መልአከ_ራማ_ዘራማ_ልዑል_ነው፤ (የራማ ልዑል ነው) #አብሣሬ_ትስብእት_ነው፤ #መጋቤ_ሐዲስ_ነው፤ #በእግዚአብሔር_ፊት_የሚቆም_መልአክ_ነው_ሉቃ_1፥19፤ #ለቅዱሳን_እውቀትን_የሚገልጽላቸውና_ከአላውያን_የሚታደጋቸው_ነው_ /ድርሳነ_ገብርኤል/ #መልአከ_ሰላሞሙ_ወመልአከ_ኪዳኖሙ_መልአከ_አድኅኖ_መልአከ_ኀይል_መልአከ_ፍስሐ (የሰላም መልአክ ፥ የኪዳን መልአክ፥ አዳኝ መልአክ፥ ኀያል መልአክ ፥ የደስታ መልአክ ነው) #ከሣቴ ጥበብ (ጥበብን የሚገልጽ ነው) /ት.ዳን./ #ናዛዜ_ኅዙናን_ (ያዘኑትን_የሚያጽናና_) መልአክ_ነው፨ ✤ ገብርኤል ማለት የእግዚአብሔር ልጅ ማለት ነው፤ የወልደ እግዚአብሔርን መወለድ አብሥሯልና፨ አንድም የሁለት ቃለት ጥምር ነው እነዚህም ገብር እና ኤል ሲሆኑ ትርጕማቸውም ገብር አገልጋይ ማለት ሲሆን ኤል ማለት ደግሞ አምላክ ማለት ነው፤ በተገናኘ ገብርኤል ማለት የአምላክ አገልጋይ /የእግዚአብሔርን ልጅ የሚመስል የአምላክ አገልጋይ/ ማለት ነው፡፡ ✼ ነቢዩ ዳንኤል “ዐይኖቼንም አነሣሁ” አለና አስከትሎ “እነሆም በፍታ የለበሰውን ጥሩም የአፌዝን ወርቅ በወገቡ ላይ የታጠቀውን ሰው አየሁ፡፡ አካሉም እንደ ቢረሌ ይመስል ነበር፤ ፊቱም እንደ መብረቅ አምሳያ ነበረ፤ ዐይኖቹም እንደሚንበለበል ፋና፣ ክንዶቹና እግሮቹም እንደ ጋለ ናስ፣ የቃሉም ድምፅ እንደ ብዙ ሕዝብ ድምፅ ነበረ፡፡… ይህንንም ታላቅ ራእይ አየሁ፤ ኃይልም አልቀረልኝም፤ ክብሬም ወደ ውርደት ተለወጠብኝ ኃይልም አጣሁ፡፡ የቃሉንም ድምፅ ሰማሁ፤ የቃሉን ድምፅ በሰማሁ ጊዜ ደንግጬ በምደር ላይ በግምባሬ ተደፋሁ” አለ፡፡(ዳን.10፥5-9) ነቢዩ ዳንኤል እንዲህ ብሎ የተናገረው የመላእክት አለቃ የቅዱስ ገብርኤልን አስፈሪ ግርማ በተመለከተ ጊዜ ነበር፡፡ ፠ “እነሆ ከዋነኞቹ አለቆች” አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ”(ዳን.10፥13) ብሎ በተናገረው ንግግሩ በመላእክት ላይ የተሾሙ ሌሎች አለቆች እንዳሉ ማስተዋል እንችላለን፡፡ ቅዱስ ጳውሎስም በቅዱሳን መላእክት ዘንድ ስላሉት ነገዶች ሲገልጽ “… በሰማይ ያለውን በምደር ያለውን የሚታየውንና የማይታየውን መናብርትም ቢሆኑ አጋእዝትም ቢሆኑ መኳንንትም ቢሆኑ ቀደምትም ቢሆኑ ሁሉም በእጁ ሆነ፤ ሁሉም በእርሱ ለእርሱ ተፈጠረ” (ቈላ.1፥16) በማለት ይዘረዝራቸዋል፡፡ ከዚህ ተነሥተን መላእክት በተለያዩ ዐበይት ነገዶች የተከፈሉና ለእያንዳንዱም ነገድ የራሱ የሆነ አለቃ እንዳለው ማስተዋል እንችላለን፡፡ ቅዱስ ገብርኤልም ከእነዚህ ዐበይት የመላእክት ነገዶች መካከል አንዱ በሆነው አርባብ በሚባለው ዐቢይ ነገድ ላይ የተሾመ ሲሆን ከ100ው ነገደ መላእክት መካከል ከበታቹ የሚመራቸው ዐሥር ነገደ መላእክት አሉት፤ ከተማቸውም በሰማየ ራማ ነው፡፡ ✼ ቅዱሳን መላእክት በቅዱስ ሚካኤል ፊት አውራሪነት የሰው ልጆች ጠላት የሆነውን ዲያብሎስን ተዋግተው ድል ከመንሳታቸው አስቀድሞ፤ እንደ አምላክ ሊመለክ የወደደውን ሳጥናኤልን ቅዱስ ገብርኤል በመቃወም ‹‹ንቁም በበህላዌነ እስከ ንረክቦ (ነአምሮ) ለአምላክነ “አይዟችሁ ፈጣሪያችን እስክናገኘው፣ እስክናውቀው ድረስ በያለንበት ጸንተን እንቁም፡፡” (አክሲማሮስ ገጽ.35) በማለት መላእክትን ያረጋጋ መልአክ ነው፡፡ ✼ ቅዱስ ገብርኤል በተወዳጁ መልአክ በቅዱስ ሚካኤል መሪነት የሰው ልጆች ጠላት የሆነውን ዲያብሎስን ተዋግተው ድል እንዲያደርጉ ወደ ጥልቁ እንዲጣል አድርጓል ራእ12፥7፤ ነቢዩ ኢሳይያስ በሰማያት የሳጥናኤል ትዕቢትና ውድቀት ምን እንደሚመስል ሲጽፍልን “አንተ በንጋት የሚወጣ አጥቢያ ኮከብ ሆይ እንዴት ከሰማይ ወደቅህ! ወደ አሕዛብ መልእክትን የላክ አንተ ሆይ እንዴት እስከ ምድር ድረስ ተቀጠቀጥህ! አንተም በልብህ ወደ ሰማይ ዐርጋለሁ ዙፋኔንም ከእግዚአብሔር ከዋክብት በላይ ከፍ ከፍ አደርጋለሁ፤… በልዑልም እመሰላለሁ አልህ፡፡ ዛሬ ግን ወደ ሲኦል ትወድቃለህ፤ ወደ ምድር ጥልቅም ትወርዳለህ” (ኢሳ.14፥16) በማለት ገለጠልን፤ ወደ ምድር የጣሉት በመላእክት አለቃ በቅዱስ ሚካኤል መሪነት እነ ቅዱስ ገብርኤል ናቸው፡፡ ✼ ቅዱስ ገብርኤል ወንጌላዊው ቅዱስ ሉቃስ ከሊቃነ መላእክት አንዱና በእግዚአብሔር ፊት የሚቆመው ታማኝ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ነው ብሏል (ሉቃ 1፥19)፤ ✼ ታላቁ ነቢይ ሄኖክም ስለ ነገረ መላእክት በተናገረበት አንቀጽ እንዲህ ሲል መስክሯል ‹‹በአበቦች ላይ በገነትም በጻድቃን ላይ በኪሩቤልም ላይ የተሾሙ ከከበሩ መላእክት አንዱ ገብርኤል ነው፡፡›› ሄኖክ 6፥7፤ ‹‹በሦስተኛውም በመላእክት ሁሉ ላይ የተሾመ ቅዱስ ገብርኤል ነው›› ሄኖክ 10፥14 እያለ የመልአኩን ክብር ተናግሯል፡፡ ** ቅዱስ ገብርኤል መንፈሳዊ እውቀቱን የሚያካፍላቸው መልአክ ብቻ አይደለም፤ ለእግዚአብሔር በመገዛታቸው ምክንያት ከአላውያን ገዢዎች ከሚደርስባቸው መከራም የሚታደጋቸው መልአክም ነው፡፡ ነገር ግን ያደረጋቸው ተዓምራቶች በመጽሐፍ ቅዱስ፣ በመልክኡ፣ በድርሳኑ፣ በተአምሩ፣ …. የተጻፉ ቢሆንም፤ ✤✼ #ታኅሣሥ_19 #ካደረጋቸው_ተራዳኢነት_ዋናውን_እንደከሚተለው_እናያለን_፤ ፠ አናንያና(ሚሳቅ)፣ አዛርያ(ሲድራቅ) እና ሚሳኤል(አብደናጎ) ያዳናቸው ያዳነበት ቀን ነው፡፡ አናንያና(ሚሳቅ)፣ አዛርያ(ሲድራቅ) እና ሚሳኤል(አብደናጎ) የፋርስ ባቢሎን ንጉሥ የነበረው ናብከደነፆር በዱራ(አዱራን) በሚባል ስፍራ ላይ ላቆመው ጣየዖት ምስል ስገዱ ሲላቸው …. የምናምነው አምላክ ያድነናል፤ ባያድነን እንኳን (አምላካችን በእሳት ሰማዕት እንድንሆን ፈቃዱ ቢሆነረ አንኳን) አንተ ላቆምከው ምስል አንሰግድም ብለውታል፡፡ ንጉሡም ወደ እቶን እሳት እንዲጣሉ አድርጓቸዋል፤ በመልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ተራዳኢነት ግን ከእቶን እሳቱ የልብሳቸው ዘርፍ እንኳን እሳት ሳይነካው ከእሳቱ ድነዋል፡፡እኛንም ያድነን አሜን:: እንዲሁም ታኀሣሥ 19፤ #ቅዱስ_ዮሐንስ_ዘሀገረ_ቡርልስ_በዓለ_ዕረፍቱ_ እንዲሁም #ኢትዮጵያዊው_አቡነ_ስነ_ኢየሱስ_ (#ገዳማቸው_በሰሜን_ጎንደር_ትክል_ድንጋይ_አካባቢ_የሚገኘው_) #በዓለ_ዕረፍታቸው_ነው_፡፡ የቀጨኔ ደ/ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደ/ት/ቅ/ገብርኤል ቤ/ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት Facebook https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool YouTube https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w Telegram https://t.me/medihanaelem

35 የሚሆኑ በመናገሻ ከተማችን በአዲስ አበባ #የሊቀ_መላእክት_ቅዱስ ገብርኤል ክብረ በዓል የሚከብርባቸው ገዳማትና አብያተ ክርስቲያናት (ያልጠቀስናቸውን ጨምሩበት፤ ፎቶም ካላችሁ ላኩልን ወይም ለጥፉልን፡፡) ፠ መ.መ.ገ. መንበረ መንግሥት ግቢ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም፤ በ1889 ዓ.ም. የተመሠረተ፤ ፠ ቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ፠ አስኮ ቅዱስ ገብርኤል፤ ፠ ጎፋ መካነ ሕያዋን ቅዱስ ገብርኤል፤ ፠ ደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል (ብሥራተ ገብርኤል) ፠ ደብረ ገነት ቅዱስ ገብርኤል ቤ.ክ. ፠ ኮተቤ ዳግማዊ ቁልቢ ደብረ ልዑል ቅዱስ ገብርኤል በ.ክ. ፠ ደብረ ገነት ፉሪ ዕንቊ ቅዱስ ገብርኤል ቤ.ክ. ፠ ምሥራቀ ፀሐይ ቅዱስ ገብርኤል ቤ.ክ. ፠ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ገብርኤል ቤ.ክ. ፠ መካነ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤ.ክ. ፠ አለም ባንክ ደብረ ራማ ቅዱስ ገብርኤል ቤ.ክ. ፠ አየር ጤና አንቀጸ ብርሃን ኪዳነ ምሕረት ቤ.ክ. (በድርብነት ይከብራል) ፠ ደብረ በረከት ቅዱስ ገብርኤል ቤ.ክ. ፠ ዕንቊ ቅዱስ ገብርኤል ቤ.ክ. ፠ ጋራ ኦዳ ቅዱስ ገብርኤል ቤ.ክ. ፠ አንቆርጫ ቅዱስ ገብርኤል ቤ.ክ. ፠ ጉራራ ምሥራቀ ፀሐይ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤ.ክ. (በድርብነት ይከብራል) ፠ ፈረንሣይ ደብረ ፀሐይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤ.ክ. (በድርብነት ይከብራል) ፠ አቃቂ ፈለገ ግዮን ቅዱስ ገብርኤል ቤ.ክ. ፠ ኤረር ጎሮ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ገብርኤል ቤ.ክ. ፠ ቦሌ ሃራብሳ ቅዱስ ገብርኤል ቤ.ክ. ፠ ቦሌ ቡልቡላ ቅዱስ ገብርኤል ቤ.ክ. ፠ መካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤ.ክ. (በድርብነት ይከብራል) ፠ ብርሃናተ ዓለም ቅዱስ ጴጥሮስ ወጳውሎስ (የቅዱስ ገብርኤል ቤ.ክ. በድርብነት በውስጥ አለ) ፠ ቦሌ ደብረ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስና ቅዱስ ገብርኤል ቤ.ክ. ፠ ቦሌ ኆኅተ ብርሃን ቅድስት ማርያም ቤ.ክ. (በድርብነት ይከብራል) ፠ ቦሌ መንበረ ብርሃን ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ቤተ ክርስቲያን (በድርብነት ይከብራል) ፠ ደብረ ገሊላ አማኑኤል ቤ.ክ. (በድርብነት ይከብራል) ፠ ጀሞ ሦስት ቅዱስ ገብርኤልና ቅድስት አርሴማ ቤ.ክ. ፠ አቃቂ ጃቲ ኪዳነ ምሕረት ቤ.ክ. (በድርብነት ይከብራል) ፠ ቃሊቲ መካነ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤ.ክ. ፠ ኮልፌ አጠና ተራ ደብረ ምጥማቅ ቅዱስ ፊልጶስ ቤ.ክ. (በድርብነት ይከብራል) ፠ የካ አባዶ ገብርኤል ቤ.ክ. ፠ደብረ ገሊላ ቅዱስ ዐማኑኤል ካቴድራል (በድርብነት ይከብራል) #share https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w https://t.me/medihanaelem

‹‹ወንድሞቻችን እኛስ እንደ ይሰሐቅ የተስፋ ልጆች ነን ፡፡›› ገላ 4 ፥ 28 በመጋቤ ሐዲስ ምስጢረ ሥላሴ ፤የታኅሣሥ 9 የዓርብ ጕባኤ በyoutube ገጻችን ይመልከቱ https://youtu.be/5sQdCht3JZc

#እንደ አበባ የሚያስደስት ባለሟልነትን ለተመሉ ከንፈሮችህና ፈጽሞ ከንቱን ለአልተናረ አፍህ ሰላምታ የሚገባህ አራቱን መዓዘነ ዓለም በአማላጅነትህ የምታስምር ጻድቅ አባታችን #አረጋዊ ሆይ ቅን ልቦናን አድለኝ የማይጎድል ምሉ ዕዉቀትንም ስጠኝ፡፡ #መልክአ_አቡነ_አረጋዊ https://youtu.be/3o4wj7Qqcaw

እንኳን አደረሳቹህ ፤ታኅሣሥ 13 ቅዳሴ ቤቱ ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል ::
+1
እንኳን አደረሳቹህ ፤ታኅሣሥ 13 ቅዳሴ ቤቱ ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል ::

አዲሱ የአ.አ ሐገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ #_ብጹእ_አቡነ_መልከጸዴቅ እና #_መምህር_አካለወልድ_ተሰማ የአ.አ ሐገረ ስብከት ዋና ስራ አስኪያጅ ፤ የሰንበት ት/ት ቤታችንን ውሳኔ አጸኑ ፡፡ ከዚህ በፊት
+1
አዲሱ የአ.አ ሐገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ #_ብጹእ_አቡነ_መልከጸዴቅ እና #_መምህር_አካለወልድ_ተሰማ የአ.አ ሐገረ ስብከት ዋና ስራ አስኪያጅ ፤ የሰንበት ት/ት ቤታችንን ውሳኔ አጸኑ ፡፡ ከዚህ በፊት መስከረም 28/01/2013 ዓ.ም በ1 ወር ጊዜ ውስጥ የሰ/ት/ቤቱ መማርያ ቦታ 600 ካሜ ቦታ እንዲሰጣቸው ተብሎ ውሳኔ ተወስኖ ወደ ደብራችን የተላከው ደብዳቤ አፈጻጸሙ ላይ ክፍተት በማሳየቱ ምክንያት በዛሬው ዕለት ታኅሳስ 12 / 2013 ዓ.ም በፍጥነት ወደ አፈጻጸም ገብተው በ #1_ሳምንት ጊዜ ውስጥ ሪፖርት እንዲያደርጉ ደብዳቤ ልከዋል፡፡ ጉዳዩ በፍጥነት ወደ አፈጻጸም እንዲገባ መመርያ ለሰጣችሁት ለአ.አ ሐገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ #_አቡነ_መልከጼዴቅ ፣ #_መምህር_አካለ ወልድ_ተሰማ እንዲሁም #_ለ_መምህር_ዳዊት ፤ሰንበት ት/ት ቤታችን ልባዊ ምስጋናውን ያቀርባል፡፡ #share ያድርጉ

#ታኅሣሥ_12_የአቡነ_ሳሙኤል_በዓለ_ዕረፍት ✤✤ #ፀሐይ_ማር_አቡነ_ሳሙኤል_ዘዋልድባ_(#ዘገዳመ_ዋሊ_) ✤✤ ፠ በሃገራችን በኢትዮጵያ በብቸኝነት በጌታችን የተመሠረተው ገዳመ ዋልድባ፤ ኋላ በአሕዛብ ጠፍቶ ነበርና በ13ኛው ክፍል ዘመን እንደ መሶብ ከፍ አድርገው በ4ቱም አቅጣጭ በ4 ወንዞች (በሰሜን ተከዜ፥ በምስራቅ እንስያ፥ በምዕራብ ዛሪማ ፥ በደቡብ እንዞና ወይቦ) ዙሪያውን ከልለውና አጥረው ያስባረኩ አባት ናቸው፡፡ ፠ አዲስ አበባና አካባቢውን ከ700ዓመታት በፊት በአንበሳ እየተጓጓዙ በስብከተ ወንጌል እርሻነት፥ በሥነ ምግባር ማለስለሻነት ያረሱ አባት ናቸው፡፡ ፠ ወላዴ አእላፍ ቅዱሳን፣ ወላዴ መምህራን ወሊቃውንት የኾኑ ናቸው፤ ይህንንም ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ በ40ቀን ዕረፍታቸው በመካነ መቃብራቸው ተገኝተው መልክዓቸውን ደርሰውላቸዋ፤ ሊቁ አባ ጽጌ ድንግል በማኅሌተ ጽጌ ድርሰታቸው አውስተዋቸዋል፤ እንዲሁም በርካታ ቅዱሳን ደራስያን በየድርሰታቸው አንስተዋቸዋል፡፡ #ክቡር_መምህር፥ #የከበረ_መምህር፤ #መልአክ_ዘበምድር፥ #የምድር_መልአክ፤ #ካህን_ወድንግል፥ #ካህንና_ድንግል፤ #ፍጹም_ንጹሕ_ወልዑል፥ #ፍጹም_ንጹሕና_ልዑል፤ #ትጉህ_ወኅሩይ፥ #ትጉህና_ኅሩይ_የተመረጠ)፤ #ብእሴ_እግዚአብሔር፥ #የእግዚአብሔር_ሰው፤ #ለባሴ_ንጽሕና፥ #ንጽሕናን_የተላበሰ፤ #ወለብሰ_ብርሃናዌ፥ #ብርሃንን_የለበሰ፤ #ዘፈጸመ_ገድሎ_በሠናይ፨ #ገድሉን_በመልካም_ተጋድሎ የፈጸመ፨/ገድለ አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ/ ፠ ከረድአቸው አባ ብንያሚና፤ ከጓደኞቻቸው ከአባ አንበስ ዘሐዘሎና ከአቡነ ዘርዐ ቡሩክ ጋር በመኾን በወቅቱ ከነበሩት ርዕሰ አበው አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ዘንድ ለመባረክ ወደ ዝቋላና ምድረ ከብድ የመጡና በረከትን የተቀበሉ ከሰሜን እስከ ደቡብ ኢትዮጵያ ያስተማሩ ናቸው፡፡ ፠ አናታቸው በሥጋ ሞት በሕፃንንታቸው ቢለይዋቸውም፤ በሕፃንነታቸው ጌታችን አውራ ጣቱን አትብቷቸዋል፡፡ ‹‹እንዘ ይተግህ ለጸልዮ ወያስተበርክ ለስኢል፤ መንኰብያቲሁ አጠበዎ ወልደ ማርያም ድንግል፡፡ ሳሙኤል፥ ሳሙኤል፥ ሳሙኤል ዘዋልድባ መነኮስ ኀያል፡፡›› /እንዲል ነግሥ/ ፠ የተከዜ ወንዝ ሞልቶ የማያሻግራቸው ቢሆን ውሃውን በትዕምርተ መስቀል ባርከው በአንድ እጃቸው መጽሐፍ ፥ በአንድ እጃቸው መብራት እንደያዙ ወደ ወንዙ ገብተው መብራቱ ሳይጠፋ መጽሐፉም ሳይበላሽ ተሸግረዋል፡፡ ፠ ገባሬ ተዓምራት ወመንክራት የኾኑ፤ ⴲ ዝናብ በኾነ ጊዜ ዝሆኖች መጥተው እንደ ጥላ የሚያስጠልሉት፤ ‹‹ሳሙኤል አቡነ ሠረገላ ጸሎት፤ ጊዜ ርደቶሙ ለዝናማት፤ ዘከለሉከ ነጌያት፡፡›› እንዳለ መጽሐፈ ሰዐታት፤ ⴲ ከ24ቱ ካህናተ ሰማይ (ከአቡነ ተክለ ሃይማኖት) ጋር መንበረ ጸባዖትን ለ12 ዓመታት አጥነዋል፤ በዚህም በጎንደር ደባርቅ አካባቢ የመሠረቱት ገዳማቸው አብ ጠራ(ህ) በሚል ተሰይሟል፡፡ ......................................የቀጨኔ ደ/ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደ/ት/ቅ/ገብርኤል ቤ/ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት ‹‹ሳሙኤል አቡነ ትሩፈ ምግባር፤ ዐምድ ጽኑዕ ፀወነ ሃገር፤ ወመልአክ ዘበምድር፡፡›› እንዲል መጽሐፈ ሰዐታት፣ ⴲ በዋልድባ ምድር ላይ ቀድሞ ውኃ የለም ነበርና፤ ፸ የሚጠጉ ምንጮችን በተለያዩ ቦታዎች አፍልቀዋል፡፡ ⴲ ቅዳሴ ማርያምን ወደ መሃል ሃገር ያመጡ፤ ⴲ ቅዳሴ ወውዳሴ ማርያምን ሲደግሙ ከመሬት ክንድ ከስንዝር ያህል ከፍ የሚሉ፡፡ ⴲ በአናብስት ዘባን ላይ የሚጫኑ፤ መጻሕፍቶቻችውንም በአናብስት ላይ የሚጭኑ፡፡ ⴲ እመቤታችን ነጭ ዕጣን (ስለ ምዑዝ ክህነታቸው) እንዲሁም ዕንቊ (ስለ ንጽህናቸው፣ ቅድስናቸውና ድንግልናቸው) የሰጠቻቸው። ⴲ በሰኔ 21 ቀን በቀደሱበት ጊዜ ቤተ ክርስቲያኑ አንድ ክንድ ከስንዝር ከምድር ለቆ እንደ ደመና በአየር ላይ ቆሞ የታየላቸው፡፡ ⴲ ውኃውን ወደ ኀብስት የቀየሩና ከነ ደቀመዛሙርቶቻቸው የተመገቡ፤ ‹‹ሶበ አተቦ ለማይ በቅዳሴኪ እንዘ ይጼሊ፤ ረሰዮ ኅብስተ ጽጌ ሃይማኖት ሳሙኤል ዘሐቅለ ዋሊ፡፡ ምሕረተ ወፍትሐ ለተአምርኪ እኅሊ፤ ሥረዪ ኀጢአትየ ወዕፀብየ አቅልሊ፤ አስመ ኵሎ ገቢረ ማርያም ትክሊ፡፡›› /ማኅሌተ ጽጌ/ ‹‹ …አርአዮሙ ለመምህራን ዐበይተ ኀይላተ፤ እንዘ ይገብር ተአምረ ወመንክረ በኀበ ተአኵተ፥ ወለማይኒ ረሰዮ ኅብስተ፡፡›› /ማኅሌተ ጽጌ/ የምንኵስና ተወረዱም፤ አባት አባትን ሲወልድ፤ መምህር መምህርን ሲተካ፥ ቅዱስ ቅዱስን ሲያፈራ፥ ገዳም ገዳምን ሲወልድ ነውና ቅሉ፤ የምንኵስና ተዋረዱም፤ ፠ ….. ፀሐይ አቡነ ተክለ ሃይማኖት አቡነ መድኃኒነ እግዚእን፤ ፠ አቡነ መድኃኒነ እግዚእ 7ቱን ከዋክብት /ፀሐይ አቡነ ሳሙኤልንና ሌሎች ቅዱሳንን/፤ ፠ ከ7ቱ ከዋክብት አንዱ ፀሐይ አቡነ ሳሙኤል ደግሞ ደቀ መዛሙርቶቻቸውን (አባ ተሥፋ ሐዋርያትን፥ አባ ዘሩፋኤልን፥ አባ ብንያሚን፥ አባ በኪሞስን፥ …… ሌሎች እልፍ አእላፋት መነኰሳትን አምንኵሰዋል፣ ሊቃውንትን አስተምረዋል፤ መምህራንና ደራስያንን ተክተዋል ….፤ በዚህም ወላዴ አእላፍ ቅዱሳን ፥ ወላዴ መምህራን ወሊቃውንት አባ ሳሙኤል በመባልም ይታወቃሉ፡፡ #አቡነ_ሳሙኤል_፤ በአኵስም ከተማ አካባቢ በ1295 ዓ.ም ተወለዱ፡፡ አባታቸው እስጢፋኖስ እናታቸው ዓመተ ማርያም ይባላሉ፡፡ በአኵስም ጽዮን ከነበሩት መምህራን ከፊደል ጀምረው የቅዱስ ያሬድን ጸዋትወ ዜማና ሥርዐተ ቤተ ክርስቲያንን ተምረዋል፡፡ ወላጆቻቸው በልጅነታቸው በሞት ተለይተዋቸዋል፡፡ ከወላጆቻቸው ሞት በኋላ ወደ ታላቁ ኢትዮጵያዊ ጻድቅ አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ዘንድ ሔደው ደብረ በንኰል ገዳም ገቡ፡፡ በዚህም ገዳም እያገለገሉ በወቅቱ ከነበሩት ሊቃውንት የብሉያትና የሐዲሳትን ትርጓሜ እንዲሁም ሥርዐተ ምንኵስናን ተምረው ከገዳሙ አባት በአቡነ መድኃኒነ እግዚእ እጅ ከሌሎች 11ድ ወንድሞቻቸው ጋር አብረው መነኰሱ፤ ቆባቸውም እንደ አቡነ አረጋዊ የድንጋይ ቆብ ነበር፡፡ በዚህም ገዳም እህል ሳይበሉ ቅጠል ብቻ እየተመገቡ ይኖሩ ነበር፡፡ እግራቸው እስኪያብጥም ድረስ ይሰግዱ ነበር፡፡ **ኋላ ወደ ጣና ገብተው ከቆብ ወንድማቸው ከአቡነ ያሳይ ጋር ለ12 ዓመታት በሱባኤ ቆዩ፤ **በስተመጨረሻም ጌታችን ወደ መሠረተውና በመሃልም ጠፍ ሆኖ ወደ ነበረው ብዙ ቅዱንን፣ መምህራንን፣ ሊቃውንትንና መናንያንን ወደ ወለዱበት ዋልድባ ገዳም ገብተው ለ70 ዓመታት ያህል ከዚህ ዓለም በምናኔ ተለይተው፣ ግርማ ሌሊቱን፥ ፀብአ አጋንንቱን ፥ ድምፀ አራዊቱን፥ የሌሊቱን ቊር፥ የቀኑን ሐሩር ታግሠው፣ ረሃቡንና ጽሙን ችለው፣ መላ ዘመናቸውን በጽድቅ ጎዳና ተጕዘው በ1395ዓ.ም ታኅሣሥ 12 ቀን በዋልድባ አቴና ገዳም ዐርፈዋል፡፡ #ባርከኒ አባ እንሣእ ጸሎተከ፤ በእንተ ሰላማ ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን፤ አባ ሳሙኤል ባርከኒ እንሣእ በረከተከ፨ /ጸሎተ መሐረነ አብ/ #በታኅሣሥ ፲፪ በበዓለ ዕረፍታቸው ጊዜም፤ ሮም በጴጥሮስና በጳውሎስ ዕረፍት እንዳለቀሰች፤ ቅድስት ገዳማቸው ገዳመ ዋልድባ (ዋሊ) አልቅሳለች፨ ‹‹በከየት ወለሀወት ገዳምከ በሞትከ ዮም፤ ሃሌ ሉያ፥ ሃሌ ሉያ፥ ሃሌ ሉያ፤ ምድረ ዋልድባ ቅድስት ሰሚዓ ዜና ሞትከ፤ እንዘ አንተ ሰብእ ምድራዊ ወመልአክ ተሠመይከ፤ ካህነ አርያም ሳሙኤል መንበረ ሥላሴ ዘአጠንከ፤ አንበሳ ወነምር ይሰግዱ ለከ፤ ወይልህሱ ጸበለ እግርከ፤ ዕንቈ ወዕጣነ ማርያም አምጽአት ለከ፤ በቅዳሴሃ ሶበ ጸለይከ፤ በከየት ወለሐወት ገዳምከ።>> እንዲል ዚቅ፨ (ሥርዐተ ማኅሌቱን ላልደረሰው ያድርሱ)

#የመስቀል ወረብ (በቀራንዮ መካን ….) ፤ በደብረ ሰላም ሊቃውንት በዩቲዩብ ገጻችን ያድምጡ:: https://youtu.be/2QR7BR2Emg8