ch
Feedback
Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

前往频道在 Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

显示更多

📈 Telegram 频道 Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት 的分析概览

频道 Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 15 373 名订阅者,在 宗教与灵性 类别中位列第 5 571,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 2 195

📊 受众指标与增长动态

невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 15 373 名订阅者。

根据 05 七月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 30,过去 24 小时变化为 -4,整体触达仍然可观。

  • 认证状态: 未认证
  • 互动率 (ER): 平均受众互动率为 22.23%。内容发布后 24 小时内通常能获得 9.08% 的反应,占订阅者总量。
  • 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 3 418 次浏览,首日通常累积 1 397 次浏览。
  • 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 20

📝 描述与内容策略

作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

凭借高频更新(最新数据采集于 06 七月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 宗教与灵性 类别中的关键影响点。

15 373
订阅者
-424 小时
-197
+3030
帖子存档
✣✤#ገዳመ_ጽጌ_ድንግል_፤ የአቡነ ጽጌ ድንግል ገዳም በ14ኛው ክፍለ ዘመን የተመሠረተው በታላቁ አባት በአቡነ ጽጌ ድንግል ሲኾን፤ እኝህ ታላቅ አባት እጅግ ሰፊ ኾኖ የሚያምረውንና ዕጹብ ድንቅ የሚያሰኘውን ባለሦስት ክፍል (ቅኔ ማሕሌት፣ ቅድስትና መቅደስ) ያለውን የገዳመ ጽጌን ውቅር ዋሻ ቤተክርስቲያን ያነጹ፣ ከሰባቱ ቅዱሳን ዘጋሥጫ (አቡነ በጸሎተ ሚካኤል ዘደብረ ጎል፥ አቡነ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ፥ አቡነ ያዕቆብ ዘቀዳሚት ግሸን ደብረ ከርቤ፥ አቡነ ገብረ እንድርያስ ዘደብረ ቆዘት፥ አቡነ ዘካርያስ ዘወለቃ፥ አቡነ ዮሴፍ ዘወለቃ፥ የዝቋላው አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ዘምስካበ ቅዱሳን ገዘዛ) አንዱ የኾኑና የወርቃማ ዘመን ወርቃማ ደራሲ የኾኑ በዚህም በቤተክርስቲያናችን ከመስከረም ፳፮ እስከ ኅዳር ፮ የምንጸልይበትንና የምናመሰግንበትን ማሕሌተ ጽጌን ባለ ፭ት አርኬና እንደ መዝሙረ ዳዊት በ፻፶ መዝሙር ልክ አድርገው የደረሱና ጸሐፊያቸው በኾኑ ጓደኛቸው አቡነ ገብረ ማርያም ዘደብረ ሐንታ አጽፈው ለትውልድ ያስተላለፉ፤ እንዲሁም ሰቈቃወ ድንግልን ከጓደኛቸው አቡነ ገብረ ኢየሱስ ዘገዳመ መጕና ጋር አብረው የደረሱ ቅዱስ አባት ናቸው፤ እንዲሁም በዘመናቸው ከነበሩት ከጓደኛቸው ከታላቁ አባት አቡነ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ጋር ብዙ ገቢረ ተዓምራትን የሠሩ (የወለቃ ወንዝ ድልድይን ጨምሮ ያነጹ)፥ አሁንም ብዙ ገቢረ ተዓምራትን የሚሠሩ አባት ናቸው፡፡ ገዳሙ የሚገኘው በደቡብ ወሎ ሃገረ ስብከት፥ በወግዲ ወረዳ ልዩ ስሙ ደብረ (ገዳመ) ጽጌ ጫቀታ በሚባል ቦታ፤ ለዐባይ ወንዝ ገባሮች ከኾኑትና በበረሀ ውስጥ ከሚጓዙት አንዱ በኾነው በወለቃ ወንዝ አቅራቢያ ነው፡፡ ገዳሙ ለታላቁ አባት በተሰጠው ቃል ኪዳን መሠረትም አኹንም ድረስ ፈውሰ ሥጋ፥ ፈውሰ ነፍስ እየሰጠ ይገኛል፤ የገዳሙ ፍየሎችና ከብቶችም በአካባቢው ከሚገኙት ነብሮች ጋር አብረው ያለምንም አደጋ ይኖራሉ፡፡ ገዳሙ በግራኝ መሐመድ ወረራ ወቅት 500 መነኰሳት በሰማዕትነት የተሰየፉበት ሲኾን ከዚህ ጀምሮ እስከ 20ኛው ክፍለ ዘመን ድረስ ተዘግቶ ቆይቶ በልዑል ራስ ካሣ ኀይሉ አማካይነት ተከፍቶ አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቷል፤ በድጋሚ በጣሊያን ወረራ ወቅት አደጋ ደርሶበታል፤ በደርግ ዘመንም የገዳሙ 84 ጋሻ መሬት ስለተወሰደበት እንደገና እስከ ከ1995ዓ.ም. ገዳሙ ዘግቷል፤ ነገር ግን በ1995ዓ.ም. በበጎ አድራጊ ምዕመናን ድጋሚ ሊከፈት ችሏል፡፡ ማሕሌተ ጽጌ የተደረሰበት ይህ ገዳም እስከ 2008ዓ.ም. ማሕሌቱ ሳይቆምበት ቆይቶ ከ2009 ዓ.ም. ጀምሮ ማሕሌቱ እየተቆመ ይገኛል፡፡ ለበርካታ ዓመታት የሊቁ የአባ ጽጌ ድንግል በዓለ ዕረፍት መስከረም 27 መከበር አቁሞም ነበር፤ እንደ አምላከ አበው ፈቃድ ከ2011 ዓ.ም. ጀምሮ ክብረ በዓሉ በገዳም ሥርዐት እየተከበረ ይገኛል፡፡ ወደ ገዳሙ ለመሄድ ለሚፈለጉ ምዕመናን፤ (በተለይ ወደ ግሸን ደብረ ከርቤ የተጓዛችሁ በዛው ለመሄድ ቅርብ ነው፡፡) 1ኛ) ከደሴ ከተማ ለምትነሱ ወግዲ በሚል መኪና ከተሳፈሩ በኋላ ከተወሰኑ የእግር ጕዞ በኋላ ይገኛል፤ 2ኛ) ከጎጃም በመካነ ሰላም ለምትነሱ ወግዲ በሚል መኪና ከተሳፈሩ በኋላ ከተወሰኑ የእግር ጕዞ በኋላ ይገኛል፤ 3ኛ) በመርሐ ቤቴ በሚዳ ለምትነሱ ወግዲ በሚል መኪና ከተሳፈሩ በኋላ ከተወሰኑ የእግር ጕዞ በኋላ ይገኛል፡፡ † በዚሁ አጋጣሚ የታለቁ ሊቅ የአባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ በዓለ ጽንሰታቸውም ጥቅምት 3 ስለሚከበር አብሮ ማክበር ይቻላል፡፡ /ከዋልድባ ዋሊ ገጽ የተወሰደ/ (የገዳሙን ኹኔታ የዘገበልንን ወንድማችንን አምላከ አባ ጽጌ ድንግል ወጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ይስጥልን፤ በረድኤት በበረከት ቅዱሳን ሊቃውንቱ ይጎብኙልን፡፡)

#_ቀን _ከሌት_ለምትደክሙ ለደብራችን አገልጋይ ካህናት #_ቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ከተመሰረተበት ጊዜ አንስቶ እስከዛሬ ድረስ #_በማኅሌቱ፣ #_በሰዓታቱ ፣ #_በቅዳሴው፣ #_በሰርክ_ጉባኤው በተለይ ደግሞ ታላላቅ ገዳማት በሚደርሰው ምህላ ሁልጊዜ ወር ከገባ ከ1-7 ባሉት ጊዜዎች #_ለሀገራችን ለቤተክርስቲያናችን ሳትሰለቹ የምትጸልዩ ፣ #_ደብራችንን ታላቅ እንዲሆን ያደረጋችሁ የምታደርጉ አብነት ት/ት ዘወትር ለተተኪዎች የምታስተምሩ አባቶቻችን ስለእናንተ ተናግረን አውርተን አንጠግብም፡፡ ይህ ሁሉ አገልግሎታችሁን ሳታቋርጡ ደግሞ ደብራችን #_ሰላም እንዲሆን፣ #_ቤተክርስቲያን ከግለሰቦች አያያዝ ተላቃ የምዕመናን እንድትሆን ፣ #_ሰላም የምትሰብክ ቤተክርስቲያን ሰላሟ እንዲበዛላት፣ #_ምዕመናን የሚሰጡት አስራት በኩራት ለሰጡበት አላማ ብቻ እንዲውል ጠንክራችሁ የምትሰሩ ፣ #_እውነትን ሳትሰለቹ የምትሰብኩ ለእናንተ ለሊቃውንት አባቶቻችን እጅ እንነሳለን፡፡ ይህ ልፋታችሁ በእኛ በልጆቻቸሁ ዘንድ #_ትልቅ _ዋጋ አለው፡፡ ትልቅ ትምህርት አስተምራችሁናል፡፡ ለእውነት በመቆማችሁ ስትገፉ አይናችን እያየ ዝም አንልም፡፡ #_የአካባቢው ጠንካራ ወጣቶች ማኅበራት (አይደለም ለዚህ ታላቅ ደብር ለሀገር የሚተርፉ) #_የደብሩ ሰንበት ት/ቤት ዛሬም እንደትላንቱ አብረናችሁ ነን፡፡ በኑሯችሁ ሲመጡ፣ በህይወታችሁ ሲመጡ ፣ ካደጋችሁበት ደብር ሊያፈናቅሏችሁ ሲጥሩ፣ ታላቁን ደብር ሊያሳንሱ ሲጥሩ አይቶ እንዳላየ ፣ ሰምቶ እንዳልሰማ መሆን #_አንችልም፡፡ ያን ጊዜ ትላንት እውነትን በመመስከራቸው፣ የእውነት ጥያቄ በመጠየቃቸው ባሳዩት ቁርጠኝነት ተነስተው ለነበሩት #_ለ_3ቱ_አባቶች እንደቆምነው ዛሬም ለሁላችሁም ዘብ እንቆማለን፡፡ ምንም እንኳን በመካከላችን ገብተው የሰ/ት/ቤቱን አባላት እና ካህናት አባቶችን ለማጣላት የሚፈልጉ ጥቂት ግለሰቦች ቢኖሩም እኛ ግን ትላንት መጥተው ነገ ለሚሄዱ ሰዎች ክፍተት አንፈጥርም በማለት በመነጋገር እዚህ ደርሰናል፡፡ ዛሬም ለዚህ ሳንበገር #_በፍቅር #_በአንድነት አገልግሎታችንን እናገለግላለን፡፡ ስለሆነም አሁንም ቢሆን #_አስተዳደራዊ በደል እየደረሰባችሁ ግን ልጆቻችሁንና ቤተሰባችሁን ህይወታችሁን ላለመበተን ስትሉ መናገር እየቻላችሁ መናገር ያልቻላችሁ #_አባቶችም #_ዲያቆናትም እናንተም እየቀረባችሁ የሚገጥማችሁን ፈተና እየተወያየን ከፊታችሁ ቆመን የምንጮህላችሁ መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡ #_ከፊት ተሰልፈን እውነታችሁን እንደግፋለን፡፡ ዛሬም አብረናችሁ ነን፡፡ #_ክብር_ለሚገባው_ክብርን_እንሰጣለን!!! share ያድርጉ ወስብሐት ለእግዚአብሔር

እንኳን ለዘመነ ጽጌ (ከመስከረም ፳፮ - ኅዳር ፭) እና ለጽጌ ጾም በሰላምና በጤና አደረሰን ፥ አደረሳችሁ፡፡ ኀለፈ ክረምት ቆመ በረከት፣ ተሠርገወት ምድር በሥነ ጽጌያት፡፡ ትርጕም፤ የክረምት ዘመን (ከሰኔ 26 - መስከረም 25) አለፈ፥ ሄደ /መኃ.2 11/፡፡ የጽጌ ዘመን (ከመስከረም 26 - ኅዳር 5) ተተካ፡፡ Like እና Share ያድርጉ #ማኅሌተ_ጽጌ #ማኅሌተ ጽጌ ከሁለት የግዕዝ ቃላት ጥምረት የተገኘ ነው፡፡ ማኅሌት ማለት ምስጋና፣ ማወደስ ማለት ሲኾን፤ ጽጌ ማለት ደግሞ አበባ፣ የፍሬ ምልክት፤ ውበት፣ ደም ግባት ያለው ማለት ነው፡፡ ማኅሌተ ጽጌ ተብሎ በአንድነት ሲነገር እና ሲተረጎም ደግሞ የአበባ ምስጋና ማለት ነው፡፡ ይህም ድንግል ማርያም እና የማሕፀኗ ፍሬ ኢየሱስ ክርስቶስ በጎ በጎ መዓዛ ባላቸው አበባዎችና ፍሬዎች እየተመሰሉ በዳዊት መዝሙር መጠን በ150 እንዲሁም እንደ መልክዕ በባለ 5ት መስመር ግጥም ተደርጎ የሚመሰገኑበት ምስጋና ማለት ነው፡፡ ጽጌ የዘመን (የወራት) ስምም ይኾናል፤ ዘመነ (ወርኃ) ጽጌ 40 ቀን ነው ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 5 ነው፡፡ በዚህ ወራት የሚጾመው ጾም ጾመ ጽጌ ሲባል ጾሙም የፈቃድ ጾም ነው፡፡ በሀገራችን ዘመነ ክረምት አልፎ መስከረም 26 ቀን ዘመነ ጽጌ ይጀመራል፡፡ ዘመኑ አበቦች የሚያብቡበት እና ሜዳዎችን እና ተራሮችን የሚስጌጡበት ዘመን ነው፡፡ ፍሬ ከአበባ አበባም ከፍሬ እንደሚገኝ ኹሉ በማኅሌተ ጽጌ እመቤታችንን በአበባ፥ ጌታችን በፍሬ፤ ወይም እመቤታችንን በፍሬ፥ ጌታችንን በአበባ እየተመሰሉ በምሥጢራዊ ግጥም ቀርበዋል፡፡ የማኅሌተ ጽጌ ደራሲ ሊቁ አባ ጽጌ ድንግልም የአበቦችን ነገር ከእመቤታችን ስደት ጋር እያደረገ፣ እጅግ አስደናቂ የሆኑ ታሪኮችን እያጣቀሰ ማኅሌተ ጽጌ (የአበባ ማኅሌት) የተባለውን ጸሎት ደርሷል፡፡ በዘመነ ጽጌ ወቅት ቅዳሜ ለእሑድ አጥቢያ ማኅሌት ይቆማል፤ የሚቆመው ቁመትም አባ ጽጌ ድንግል የደረሱት ማኅሌተ ጽጌና ሰቈቃወ ድንግል ነው፡፡ አባ ጽጌ ድንግል ጓደኛቸው አባ ገብረማርያም የጀመሩትን ማኅሌተ ጽጌ አብነት በማድረግ በተለይም በጎንደር ዘመነ መንግሥት በእቴጌ ምንትዋብ ዘመን በጎንደር ደብረ ፀሐይ ቊስቊም ማርያም የማኅሌተ ጽጌ ቁመት መቆም ተጀምሯል፤ ቆይቶ ግን ይህ ማኅሌት ወደ ዘንሥር ዮሐንስ ማእከላ ለጎንደር ተዛውሮ እስከ ዐፄ ኃይለ ሥላሴ ድረስ ሲቆም ቆይቶ በመምህር ተክሌ ጊዜ ወደ መካነ ነገሥት ግምጃ ቤት ማርያም ተዛውሮ በጎንደር አብያተ ክርስቲያናት በብቸኝነት በዚህችው ደብር የጎንደር አድባራት ሊቃውንት በመሰባሰብ ሲቆም ቆይቷል፤ በሌሎች የሃገራችን ክፍሎች አዲስ አበባን ጨምሮ ባሊ አብያተ ክርስቲያናትም የጽጌ ቁመት ተስፋፍቷል፡፡ ከ1999(2000)ዓ.ም. ጀምሮ በጎንደር ደብረ ፀሐይ ቊስቋምና የተወሰኑ የጎንደር አብያተ ክርስቲያናት የማኅሌተ ጽጌ ቁመት ጀምረዋል፤ ነገር ግን ቢጀምሩም ቅሉ አሁንም ግን የጎንደር አድባራት ሊቃውን በዋነኛነት በመካነ ነገሥት ግምጃቤት እየተሰባሰቡ የሚቆሙት የማኅሌተ ጽጌ ቁመት እጅግ በጣም ልብን የሚማርክና ኅሊናን የሚመስጥ በሃገራችን በኢትዮጵያ ደረጃም ተወዳዳሪ የሌለው ነው፡፡ በሌሎች የሃገራችን ክፍሎችና በመዲናችን በአዲስ አበባ ባሉ አብያተ ክርስቲያናት ደግሞ የአገልጋይ ካህናት እጥረት በሌለባቸው ኹሉ ይቆማል፡፡ #ሰቈቃወ_ድንግል፤ ማለት እመቤታችን ከልጇ ከመድኀኔዓለም፥ ከአረጋዊ ዮሴፍና ከሰሎሜ ጋር በስደቷ ወቅት ያየችውን መከራ፥ ልቅሶ፥ ዋይታ የሚዘከርበት የማኅሌተ ጽጌ አርኬ ነው፡፡ ፎቶዎቹ፤ #ቤተ_ክርስቲያኖች_ *ደብረ ጽጌ ገዳም፤ የአባ ጽጌ ደንግል ገዳም፤ ማኅሌተ ጽጌ የተደረሰበት፤ ወሎ ወግዲ አጠገብ፤ ኅዳር 6 ይከብራል፡፡ *ጎንደር ደብረ ፀሐይ ማርያም፤ ለበርካታ ዘመናት ማኅሌተ ጽጌ ይቆምባት የነበረች ታላቋ ደብር፡፡ *ጎንደር ዘንሥር ዮሐንስ፤ እስከ አፄ ኀይለ ሥላሴ ዘመን የጎንደር የ44ቱ ታቦታት ሊቃውንት አየተሰበሰቡ ማኅሌተ ጽጌ ይቆሙበት የነበረ ደብር፡፡ *ጎንደር መካነ ነገሥት ግምጃ ቤት ማርያም፤ ከአፄ ኃይለ ሥላሴ እስከ አሁን ድረስ የጎንደር የ44ቱ ታቦታት ሊቃውንት አየተሰበሰቡ ማኅሌተ ጽጌ የሚቆሙባት ታላቂቷ ደብር፡፡ #መምህራን_ ✤ #መምህር_ተክለማርያም_፤ የታለቁ ገዳም የማኅበረ ሥላሴ አበምኔት፤ የግምጃ ቤት ማርያም የሐዲሳት መምምህር፤ የድጓና የአቋቋምም መምህር፤ የጎንደር አድባራት በጋራ በመኾን የማኅሌተ ጽጌን ቁመት በአንድ ላይ ይቆሙበት ከነበረው ዘንሥር ማዕከላ ለጎንደር ዮሐንስ ወደ መካነ ነገሥት ግምጃ ቤት ያመጡ ታላቁና ይህ ቀረሽ የሚይባሉ ሊቅ ✤፠ #መምህር_ክፍለ_ማርያም_ይመር_፤ የመጻሕፍት ትርጓሜ ብርሃን፤ የየቀኑን ምሥጢር ከድጓ፣ ከጾመ ድጓ፣ ከዝማሬ መዋሥዕት፣ ከቅዳሴ፣ ከሰዐታት እየተመለከቱና እያውጣጡ ዚቁን ያዘጋጁ፤ ይህ ቀረሽ የማይባሉ የሊቆች ሊቅ፡፡ ✤፠ #ሊቀ_ማዕምራን_ወመጋቤ_ሐዲስ_ወሰንበት_ባይነሳኝ_፤ የጽጌ ዚቅን (የላይ ቤትን) አቀናብረው ያቀረቡ፤ የመጻሕፍተ ሐዲሳት ዋና ምስክርና የመካነ ነገሥት ግምጃ ቤት ማርያም ዋና አስተዳዳሪ፤ የሚያስተምሩት የሚኖሩ፤ ሊቅነትና ከትሕትና የያዙ፤ ከቀደምት ዐበይት ሊቃውንት መካታቻ የሆኑ፤ በቅርቡ ያረፉ፤ ጕባኤ እያሄዱ (እያስተማሩ) የሚያሳይ ፎቶ ✤፠ ሊቀ ማዕምራን ሐዋዝ ጥሩነህ፤ የግምጃ ቤት ማርያም አለቃ፤ ከላይ የተጠቀሱ ሊቃውንት የደረሱትን ዚቅ በእጅ ጽሑፍ ለትውልድ ያቆዩ ብልህ አስተዳዳሪ፡፡ ✤፠ #መምህር_ክፍሌ_ወለደ_ጻድቅ፤ የጽጌ ዚቅን (ዚቅን) (የታች ቤትን) አቀናብረው ያቀረቡ፤ የደብረ ኃይል ወደብረ ጥበብ በዓታ የአቋቋም ዋና ምስክር የነበሩ፡፡ የአሁንን ዝክረ ቃልን በቀድሞ ስሙ አባጃሌ የተባለውን መጽሐፍ ለመጀመሪያ ጊዜ ለሕትመት ያበቁ፡፡ ✤ #መምህር_ላዕከ_ጊዮርጊስ_ደምሴ፤ የግምጃ ቤት ማርያም የሐዲሳት ምክትል መምህር የነበሩና ዜማ አዋቂ ምሁር፤ በወርኃ ጽጌ የዕለቱን ምሥጢር በተመለከተ ዚቅ እያዘጋጁ ለሊቃውንቱ ያቀርቡ የነበሩ ✣✤✣ #መካነ_ነገሥት_ግምጃ_ቤት_ማርያም፤ ለሃገራችን ኢትዮጵያና ለኢ.ኦ.ተ.ቤ.ክ ባለውለታ የኾነች ጥንታዊት ቤ.ክ.፤ በደርቡሽ ወረራ ጊዜ መመህራን ጕባኤያችንን (ማስተማራችንን የታሪክ መዘክርነታችንን) ለቅቀን አንሔድም በማለት ሰማዕት የኾኑባት፡፡ **የብዙ ሊቃውንተ መፍለቂያ፤ እስከ ዐፄ ኀይለሥላሴ ዘመን ድረስ (ከሠለስቱ ምዕትና ከልደታ አብያተ ክርስቲያናት ጕባኤ ቤት በመቀጠል) በሃገራችን ኢትዮጵያ ብቸኛዋ የታች ቤት የመጻሕፍት /አንድምታ ትርጓሜ/ (የ4ቱ ጕባኤያት) ብቸኛ ማስመስከሪያ፡፡ /በአሁኑ ሰዓት በዋነኛነት በኢትጵያ ደረጃ የመጻሕፍተ ሐዲሳት የታች ቤት ትርጓሜ ዋና ማስመስከሪያ መካነ አእምሮ (university)/፡፡ እዲሁም የላይ ቤት የአቋቋም የዜማ የድርሰት ማዕከልና ዋና አብነት ነች፡፡ በውስጧ ተዓምረኛ የኾነች የእምቤታችን ሥዕል ይገኝባተል፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2whttps:/ /t.me/medihanaelem በቅርቡ ደግሞ በ finotehiwotsundayschool.com Like እና Share ያድርጉ