uz
Feedback
Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Kanalga Telegram’da o‘tish

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Ko'proq ko'rsatish

📈 Telegram kanali Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት analitikasi

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) Amxar til segmentidagi kanali faol ishtirokchi. Hozirda hamjamiyat 15 367 obunachidan iborat bo'lib, Din & Maʼnaviyat toifasida 5 600-o'rinni va Efiopiya mintaqasida 2 189-o'rinni egallagan.

📊 Auditoriya ko‘rsatkichlari va dinamika

невідомо sanasidan buyon loyiha tez o‘sib, 15 367 obunachiga ega bo‘ldi.

26 Iyun, 2026 dagi oxirgi ma’lumotlarga ko‘ra kanal barqaror faollikka ega. Oxirgi 30 kunda obunachilar soni 2 ga, so‘nggi 24 soatda esa 2 ga o‘zgardi va umumiy qamrov yuqori darajada qolmoqda.

  • Tasdiqlash holati: Tasdiqlanmagan
  • Jalb etish (ER): Auditoriya o‘rtacha 20.69% darajada jalb etiladi. Nashrdan keyingi dastlabki 24 soatda kontent odatda umumiy obunachilar sonining 10.92% ini tashkil etuvchi reaksiyalarni to‘playdi.
  • Post qamrovi: Har bir post o‘rtacha 3 180 marta ko‘riladi; birinchi sutkada odatda 1 679 ta ko‘rish yig‘iladi.
  • Reaksiyalar va o‘zaro ta’sir: Auditoriya faol: har bir postga o‘rtacha 18 ta reaksiya keladi.

📝 Tavsif va kontent siyosati

Muallif resursni shaxsiy fikrni ifoda etish maydoni sifatida ta’riflaydi:
የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Yuqori yangilanish chastotasi (oxirgi ma’lumot 27 Iyun, 2026 da olingan) sababli kanal doimo dolzarb va katta qamrovli bo‘lib qoladi. Analitika auditoriya kontent bilan faol hamkorlik qilishini, uni Din & Maʼnaviyat toifasidagi muhim ta’sir nuqtasiga aylantirishini ko‘rsatadi.

15 367
Obunachilar
+224 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kunlar
+230 kunlar
Postlar arxiv
፥ የተግባባ በመሆኑ “ማርቆስ አባታችን ፥ እስክንድርያ እናታችን” ማለት በኢትዮጵያውያን ምእመናን ዘንድ የተለመደ ነበር፥ ታሪክ ነውና ዛሬም ቢሆን ቤተክርስቲያናችን ሙሉ በሙሉ ከግብጽ ቤተክርስቲያን ጥገኝነት ተላቃ በኢትዮጵያውያን ጳጳሳት ብትመራም ይህ እውነታ ግን የሚዘነጋ አይደለም፡፡ --------------- ፠ በፎቶ የምትመለከቷቸው አብያተ ክርስቲያናት፤ * ሰላ ድንጋይ ቅዱስ ማርቆስ፤ በአፄ ምኒልክና የተሠራና የአቡነ ማቴዎስ መንበረ ጵጵስና የነበረ፤ በልዩ አሠራር በ42 ቆመ ብእሲ (ዐምድ) የታነጸ፡፡ * መናገሻ ቅዱስ ማርቆስ፤ በአቡነ ማቴዎስ የተሠራና መንበረ ጵጵስና የነበረ፤ ውጭው ክብ ውስጡ ግን ከሌሎች ክብ አብያተ ክርስቲያናት ልዩና ድንቅ በሆነ አሠራርና ሥዕላት የተሞላ፡፡ቀ * ጎጃም ደብረ ማርቆስ፤ * መንበረ ልዑል ቅዱስ ማርቆስ፤ አፄ ኀይለ ሥላሴ ከቤተ መንግሥታቸው ላይ ቦታ ቀንሰው ያነጹት ቤ.ክ.፡፡ /በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ፤ ትምሕርት ዋና ክፍል ፥ ንዑስ ክፍል /ሕትመት እና ሚዲያ/ የተዘጋጀ :: #share Contact: https://t.me/finotehiwot1927 .Facebook... https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool .Telegram... https://t.me/medihanaelem http://tiktok.com/@finotehiwot www.finotehiwotsundayschool.com YouTube https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w Telegram (https://t.me/finotehiwot1927) Telegram (https://t.me/finotehiwot1927) ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ት.ቤት .

#ቅዱስ_ማርቆስ_ወንጌላዊ_ጥቅምት_፴ ማርቆስ የሚለው ስም 3ት ፍቺዎች አሉት ንብ፣ አንበሳና ካህን:: ሀ) *ንብ የሚለው ፍቺ የተሰጠው ንብ አበባ ካለው ተክል ሁሉ ቀስማ ማር እንድትሠራ እርሱም ቀድሞ ከጌታ ኋላም ከጌታ የተማርኩት ይበቃኛል ሳይል ከሐዋርያት ተምሮ ደገኛይቱን ወንጌልን በማስተማሩና በመጻፉ ነው፤ ለ) *አንበሳ መባሉ አንበሳ እንስሳት አራዊትን በክርኑ እንዲሰብር፤ በግብጽ ይመለኩ የነበሩ በእንስሳ አምሳል የተሠሩ ጣዖታትን በወንጌል ቃል ኃይልነት በማጥፋቱ ነው፡፡ ሐ. *ካህን የሚለው ትርጕም ደግሞ በሐዋ. 14፥13 “ወአምጽኡ ማሬ ዘድዮስ” ተብሎ ከተመዘገበው መጽሐፍ ቅዱሳዊ አሳብ የተወረሰ ነው:: ፠ ማርቆስ ከመባሉ በፊት ዮሐንስ ይባል የነበረ ሲሆን ቁጥሩ ከ72ቱ አርድዕት ነው፤ ሐዋ. 12፥12፡፡ አባቱ አርስጦቦሎስ እናቱ ማርያም ይባላሉ፡፡ እናቱ ማርያም በጌታ ትምህርት አምነው ሲከተሉትና ሲያገለግሉት ከነበሩት ደጋግ ሴቶች አንዷ ስትሆን ከጌታ ትንሣኤ በኋላ ቤቷን ለወንጌል አገልግሎት ሰጥታ ሐዋርያት በዚያ ተሰብስበው ለጸሎት ይተጉ ነበር፥ ጌታ ባረገ በ10ኛው ቀን (በተነሣ በ50ኛው ቀን) ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ጋር በአንድነት ሳሉ መንፈስ ቅዱስን የተቀበሉትም በዚሁ በማርቆስ እናት በማርያም ቤት ውስጥ ነው፡፡ ሐዋ. 2፥1 ፤ 12፥12፡፡ ፠ የራሱን ሀገረ ስብከት ይዞ ማስተማር ከመጀመሩ በፊት ቅዱስ ማርቆስ ሐዋርያትን እየተከተለ ይማር ፥ በተልእኮም ይራዳቸው ነበር:: ከቅዱስ ጳውሎስ መጠራት በኋላ ጳውሎስንና አጎቱ በርናባስን ተከትሎ በአንጾኪያ ፤ ቅዱስ ጴጥሮስን ተከትሎ በሮም አስተምሯል፤ እነርሱም በመልእክቶቻቸው “ማርቆስ ሰላም ይላችኋል” እያሉ አንስተውታል:: ሐዋ. 12፥25፣ ቈላ. 4፥10፣ 1ኛ ጴጥ. 5፥13 ፠ በሮም ተልእኮው ከቅዱስ ጴጥሮስ ጋር ሳለ ቅዱስ ጴጥሮስ ከፍጹምነት መድረሱን ዐውቆ ጵጵስና ሾሞ ከሀገረ ስብከቱ ግብጽን ከፍሎ አስተምር ብሎ ሰጠው፡፡ እርሱም ሊያስተምር ሄዶ ወደከተማ ሊገባ ሲቃረብ የጫማው ጠፍር ተበጥሶበት አንያኖስ ወደሚባል ጫማ ሰፊ ሄደና ስፋልኝ ብሎ ሰጠው። አንያኖስ ጫማውን ተቀብሎ ሲሰፋ መስፊያው እጁን ወግቶት “ኢስ ታኦስ” ብሎ ጮኸ “አሐዱ እግዚአብሔር” ማለት ነው፤ የጠራኸውን ታውቀዋለህን? አለው፥ ሲሉ ሰምቼ እንጂ ያስተማረኝስ የለም አለው፡፡ ቅዱስ ማርቆስም ፈቃደኛነቱን አይቶ አስተማረው አንያኖስም ከነቤተሰቦቹ አምኖ ተጠመቀ:: ፠ ከዚህ በኋላ አንያኖስን አስከትሎ በከተማ እየተዘዋወረ ያስተምር ጀመረ፤ ሕዝቡም ትምህርቱን ሰምተው ፥ ተአምራቱን አይተው አመኑ፥ ተጠመቁ፤ አብያተ ጣዖታቱንም አፈራርሰው አብያተ ክርስቲያናትን ሠሩ፡፡ በዚህ ጊዜ የጣዖታቱ አገልጋዮች የለመዱት ቢቀርባቸው በጠላትነት ተነሡበት:: ምእመናኑ ተሰብስበው አባታችን እንድትለየን አንሻም፤ ነገር ግን ገነውተ ጣዖታቱ በጠላትነት ተነሥተውብሀልና ቁጣቸው እስኪበርድ ጥቂት ጊዜ ወደ ሌላ ሥፍራ ሄደህ ቆይ አሉት:: አንያኖስን ኤጲስቆጶስ ልጆቹን ቄስና ዲያቆን አድርጎ ሾሞላቸው፤ በባርቃና በሌሎች 5 አውራጃዎች እየሰበከ ቅዱስ ጴጥሮስን ለመጠየቅ ወደሮም ሄደ፤ በዚያ ሆኖ በስብከቱ ያመኑ የእስክንድርያ ምእመናን የተማሩትን እንዳይዘነጉ የማርቆስ ወንጌል ተብሎ የሚታወቀውን ወንጌል በሮማይስጥ ቋንቋ ጽፎ ልኮላቸዋል:: ዘመኑ ጌታ ካረገ 11ኛው ሲፈጸም 12ኛው ሲጀመር ፥ ቀላውዴዎስ ቄሳር በነገሠ በ4ኛው ዓመት /45-46ዓ.ም. ባለው ጊዜ/ ነው:: ፠ ከጥቂት ዓመታት ቆይታ በኋላ ወደ ግብጽ ተመለሰ፥ ምእመናኑ በቊጥር በዝተው፥ በእምነት ጐልምሰው አግኝቷተቸው ደስ ብሎት እያስተማራቸው አብሯቸው ጥቂት ጊዜ ቆየ:: በዓለ ትንሣኤን በሚያከብሩበት ቀን አምልኮ ጣዖት ከስሞ አምልኮተ እግዚአብሔር በመስፋፋቱ ምቀኝነት ያደረባቸው ጣዖታውያን ሊጣሉት መጡ፤ ምእመናኑ አባታችን ሽሽ አሉት፤ እንግዲህስ በጌታዬና በአምላኬ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ስለ ወንጌል ክብር መከራ ልቀበል እንጂ ልሸሽ አይገባኝም፥ አልሸሽም አለ፡፡ እንደ ላም በአንገቱ ገመድ አስረው በረሀ ለበረሀ ሲጐትቱት ዋሉ ፥ ሥጋው በእሾህ በጋሬጣ ተቀረደደ፡፡ ወደጌታ ቢያመለክት፤ ስለተቀበልኸው መከራ ክብርህን ከ12ቱ ደቀመዛሙርቴ ክብር አንድ አድርጌልሀለሁ፤ በስምህ የተማፀነኝንም እምርልሀለሁ ብሎ ቃልኪዳን ገብቶለት ነፍሱን በቃለ አቅርንት፥ በይባቤ መላእክት አሳርጓታል:: በሞቱ ያልረኩት ጣዖታውያኑ ከሞተም በኋላ ሥጋውን ለማቃጠል ሽተው እንጨት ሰበሰቡ የሚያቀጣጥልላቸውን ዝፍትም በከመሩት እንጨት ላይ አርከፈከፉ፤ ጌታ ግን ይህን እንዲያደርጉ ዕድል አልሰጣቸውም ድንገት ታላቅ ነጐድጓድ ሆነ፥ የተከማቹበት ሥፍራ ተናወጸ፥ የፀሐይም ብርሃን ተሠወረባቸው፤ በዚህ ጊዜ ምን መጣብን ብለው ማቃጠሉን ትተው ሸሽተዋል፡፡ ኋላ ግን ምእመናን በመብረቅ ጸዳል ተከብቦ አግኝተው በክብር ሥጋውን በአሌክሳንድርያ ቀብረውታል:: ፠ በዚህ ቦታ ተቀብሮ ለብዙ ዘመን ከቆየ በኋላ በ820 ዓ.ም ሁለት የቬኑስ ነጋድያን አጽሙን በድብቅ ከተቀበረበት አስወጥተው ወደ ቬነስ ወሰዱት፤ በዚህ ከተማ በሚገኘው በቅዱስ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያን አኑረውት ቦታው የበላይ ቅዱስ ሆኖ በክብር ይኖር ነበር። ስለሆነም የግብጽ ቤተ ክርስቲያን እንዲሰጣት በየጊዜው ከመጠየቅ አልቦዘነችም ነበር፡፡ ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴም የሮማው ርዕሰ ሊቀ ጳጳስ ጳውሎስ 6ኛ ስለፈቀዱ፤ ቅዱሱ ባረፈ በ1900 ፥ በተወሰደ በ1140 ዓመት አጽሙ ሰኔ 17 ቀን 1960 ዓ.ም. ፈልሶ ወደ ጥንተ ቦታው ለመመለስ በቃ፡፡ ሲመለስም ጃንሆይም በስፍራው ተገኝተዋል፡፡ ቅዱስ ማርቆስ በሰማዕትነት ሲያርፍ የ70 ዓመት አረጋዊ ነበረ፡፡ ከ30 ዓመታት በላይ በዘለቀ መዋዕለ ስብከቱ ለዓለም ሁሉ የምስራች የሚሆን የወንጌልን ቃል ከመጻፉ ባሻገር ከሐዋርያዊ ተልዕኳቸው የተነሣ ብርሃናተ ዓለም ከተባሉ ከቅዱስ ጴጥሮስና ከቅዱስ ጳውሎስ ጋር በብዙ አህጉረ ስብከት ተዘዋውሮ በማስተማሩና ይልቁንም የጥንት ግሪክ ሥልጣኔ ተስፋፍቶባትና የሮማ ሥርወ መንግሥት ቁልፍ የፓለቲካና የንግድ መዲና በነበረችው እስክንድርያ በሰማዕትነት እስካረፈባት ቅጽበት ድረስ በአንደበቱም በሕይወቱም በክብሩና በመከራው ሁሉ በማስተማር አይሁድን ከይሁዲነት ወደ ክርስቲያንነት ፥ አረማውያንን ከአምልኮ ጣዖት ወደ አምልኮተ እግዚአብሔር የመለሰ እንዲሁም በጸሎታቸው የሚጠብቁ፥ በትሩፋታቸው የጽድቅን ዋጋ የሚያሰጡ የባሕታውያን አባት አባ ጳውሊን፣ የመነኰሳት አባት አባ እንጦንስን፣ አባ ጳኩሚስ እና አባ ሰራብዮንን፤ መናፍቃንን ተከራክረው የረቱ ፥ ሃይማኖትን ያቀኑ ቅዱስ እለእስክንድሮስን ፥ ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊን ፥ ቅዱስ ቄርሎስ ዘእስክንድርያን፥ ቅዱስ ጢሞቴዎስ ዘአልቦ ጥሪትና ቅዱስ ዲዮስቆሮስን የመሳሰሉ ኦሮቶዶክሳውያን ሊቃውንትንና እስከ ዛሬም መከራ ሳይበግራቸው፥ ሞትና ግርፋታቸውን እንደ ክብር ቈጥረው፥ በሃይማኖታቸው ፀንተው የሚኖሩ የጸኑ ምእመናንን ያፈራች አንፀባራቂ ስም ያላት ኦርቶዶክሳዊትና ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያንን ያቋቋመ ሐዋርያ በመሆኑ ዳግመኛም ከ4ኛ ክ/ዘ/ አባ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን እስከ አቡነ ቄርሎስ 20ኛ ክ/ዘ/ ድረስ የኢትዮጵያን ቤተክርስቲያን በክህነት የመገቡ 111 ጳጳሳት ቅዱስ ማርቆስ ወንጌላዊ ያቋቋማት የዚህችው ቤተክርስቲያን ፍሬዎች በመሆናቸውና ትምህርታችን ከትምህርታቸው ፥ ሥርዐታችን ከሥርዓታቸው የተስማማ

https://youtu.be/R3vAMYdusE0 ቤተ ክርስቲያናችን ካሉ ከ፲፬ቱ ፍሬ ቅዳሴያት በተጨማሪ የተወሰኑ የጒባኤ ሊቃውንት ብቻ የሚያውቋቸው ለምእመናን ዐይን ያልበቁ ሌሎች ፍሬ ቅዳሴያት አሉን፤ ለምሳሌ ያኽል አራት የቅዳሴ ማርያም ፍሬ ቅዳሴያት በብራና በግእዝ ተጽፈው ሲገኙ፡- እነዚኽም ፩ኛ) ቅዳሴ ማርያም ዘናትናኤል ሐዋርያ የሚል (መጽሐፉ በጎጃም ደብረ ማርቆስ የነበረ)፡፡ ፪ኛ) ቅዳሴ ማርያም ዘማርቆስ ወንጌላዊ የሚል (መጽሐፉ በዜና ማርቆስ ገዳም የነበረ)፡፡ ፫ኛ) ቅዳሴ ማርያም ዘጎርጎርዮስ ዘቀጶዶቅያ (መጽሐፉ በጣና በጣሬጣ የነበረ)፡፡ ፬ኛ) ቅዳሴ ማርያም (መዐዛ ቅዳሴ) በአባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ የተደረሰው ነው፡፡

የበዓለ ንግሡን በቀጥታ ሥርጭት በYoutube እና Facebook ገጻችን ይከታተሉ ። ጠዋት ከ3:00 ጀምሮ ሌሊት በሥርዓተ ማኀሌቱ ላይ የተመረጡ ወረቦችን ።
የበዓለ ንግሡን በቀጥታ ሥርጭት በYoutube እና Facebook ገጻችን ይከታተሉ ። ጠዋት ከ3:00 ጀምሮ ሌሊት በሥርዓተ ማኀሌቱ ላይ የተመረጡ ወረቦችን ።

የበዓለ ንግሡን በቀጥታ ሥርጭት በYoutube እና Facebook ገጻችን ይከታተሉ ። ጠዋት ከ3:00 ጀምሮ ሌሊት በሥርዓተ ማኀሌቱ ላይ የተመረጡ ወረቦችን ።

የበዓለ ንግሡን ቀጥታ ሥርጭት በYoutube እና Facebook ገጻችን ይከታተኩ ። ጠዋት 2:30 ሌሊት በሥርዓት ማኅሌት ላይ የተመረጡ ወረቦችን ።