ar
Feedback

لا تقع ضحية للمخادعين! تيليمتريو يكتشف ويُميّز هذه القنوات 👉 إذا كنت تريد رؤية العلامة، اشترك 👈

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

الذهاب إلى القناة على Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

إظهار المزيد

📈 نظرة تحليلية على قناة تيليجرام Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

تُعد قناة Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) في القطاع اللغوي Amharic لاعباً نشطاً. يضم المجتمع حالياً 15 622 مشتركاً، محتلاً المرتبة 5 362 في فئة الدين والقيم الروحية والمرتبة 2 204 في منطقة Ethiopia.

📊 مؤشرات الجمهور والحراك

منذ تأسيسه في невідомо، حقق المشروع نمواً سريعاً وجمع 15 622 مشتركاً.

بحسب آخر البيانات بتاريخ 08 أكتوبر, 2026، تحافظ القناة على نشاط مستقر. خلال آخر 30 يوماً تغيّر عدد الأعضاء بمقدار 67، وفي آخر 24 ساعة بمقدار 14، مع بقاء الوصول العام مرتفعاً.

  • حالة التحقق: غير موثّقة
  • معدل التفاعل (ER): يبلغ متوسط تفاعل الجمهور 8.25‎%. وخلال أول 24 ساعة من النشر يحصد المحتوى عادةً 4.62‎% من ردود الفعل نسبةً إلى إجمالي المشتركين.
  • وصول المنشورات: يحصل كل منشور على متوسط 1 288 مشاهدة. وخلال اليوم الأول يجمع عادةً 721 مشاهدة.
  • التفاعلات والاستجابة: يتفاعل الجمهور بانتظام؛ متوسط التفاعلات لكل منشور يبلغ 12.

📝 الوصف وسياسة المحتوى

يصف المؤلف القناة بأنها مساحة للتعبير عن الآراء الذاتية:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”

بفضل وتيرة التحديث المرتفعة (أحدث البيانات بتاريخ 09 أكتوبر, 2026) تحافظ القناة على حداثتها ومستوى وصول مرتفع. وتُظهر التحليلات تفاعلاً نشطاً من الجمهور، ما يجعلها نقطة تأثير مهمة ضمن فئة الدين والقيم الروحية.

15 622
المشتركون
+1424 ساعات
+867 أيام
+6730 أيام
أرشيف المشاركات
ጥር 6 በዓለ ግዝረት፥ ዕረገተ ኤልያስ ዕረፍተ ኖኅ፥ ልደተ ቅድስት አርሴማ፥ ዕረፍተ ዐቢይ ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሣርያ፥ አቡነ ኖኅኖኅ አባ ሙሴ ገዳማዊ፥ አባ ወርክያኖስ፥ ወአባ ሙሴ፡፡ #ግዝረተ_እግዚእነ_ኢየሱስ_ክርስቶስ ፠ ጌታችን በተወለደ በ8ኛ ቀኑ ዕጉለ ማዕነቅ ይዞ ወደ ቤተ ግዝረት በመግባት የኦሪትን ሕግ የፈጸመበት ዕለት ነው፡፡ ፠ ‹‹ጌታ ክርስቶስ በሥጋ ግዝረትን ተቀበለ፣ ለአባቶች የተሰጠውን ቃልኪዳን ይፈጽም ዘንድ›› /ሮሜ.፲፭፥፰/፡፡ ፠ በቅዱስ ወንጌል እንደ ተጻፈ በስምንተኛው ቀን እንደ ኦሪቱ ሥርዓት ግዝረት ይፈጸምለት ዘንድ ሕፃኑ ጌታችንን ወደ ቤተ መቅደስ ወሰዱት፡፡ መጥምቁ ዮሐንስ ሲገረዝ የሊቀ ካህን ልጅ ነው ብለው ሊገርዙት ወደ እርሱ መጡ፡፡ ጌታችን ግን ወደ ምድር የመጣው፡፡ ለትሕትና ነው እንጂ ለልዕልና አይደለምና ወሰዱት አለ /ትርጓሜ ወንጌለ ሉቃስ/፡፡ ፠ የእመቤታችን ድንግልናዋ ሳይለወጥ ከድንግል ማኅፀን እንደመውጣቱ የጌታችን ግዝረቱም የማይመረመር ሆነ፡፡ እንዲሁ በተዘጋ ቤት መግባቱና መውጣቱ እንደማይመረመር እነዲሁ እንደፈቀደ ከረቀቀ ጥበቡ ችሎታውን በመገረዝ ከሥጋው ምንም ምን ሳይቆረጥ ገለጠ፡፡ #ቅዱስ_ኤልያስ_በእሳት_ሰረገላ_ወደ_ብሔረ_ብፁዓን_ያረገበት_ዕለት_ነው፡፡ **በቅዱስ መጽሐፍ ውስጥ ካሉት ቅዱሳን ነቢያት ዝናም በማቆም ብቸኛ ነቢይ ነው፡፡ ✤ የሰማርያው ነቢይ ቴስቢያዊው ኤልያስ ከቅዱሳን አበው ነቢያት አንዱ ሲኾን አባቱ ኢያሴዩ እናቱ ደግሞ ቶናህ(ቶና) ሲባሉ ሲወለድ መላእክት በእሳት ሰፋድል (መጠቅለያ መጐናጸፊያ) ጠቅልለውት ነው፡፡ የስሙ ትርጉምም ‹‹እግዚአብሔር አምላክ ነው›› ማለት ነው፡፡ ** ኤልያስ ብዙ ነገር ስለሚያስተምር የቀና እምነቱን ውጤት ጥቂት መመልከት እኔ ማነኝ? ለሚሉት እጅ ይዞ ይመራል፡፡ ✤ 1. ለሦስት ዓመት ከመንፈቅ ሰማይ ዝናም ለዘር፥ ጠል ለመከር ከመስጠት እንዲከለከል ምድርም የተከሉባትን ✤ 2. አመጸኞች አክአብንና ኤልዛቤልን ምንነታቸውን ካሳወቀ በኋላ የዘጋውን ለመክፈት ወደ ፈጣሪው በመጸለይ ዝናም አዝንሟል፡፡ ✤ 3. በተፈጥሮ የማይመስላቸው በቋንቋም የማይግባባቸው እንኳን ለሰው ሥጋ ሊያመጡ ከሰው ሥጋ የሚነጥቁ አሞራዎች እንጀራና ሥጋ ለምግብ እንዲያመላልሱለት አደረገ 1ኛ ነገሥ. 17፥6-7፡፡ እነዚህ አሞራዎች ለሦስት ዓመት ከመንፈቅ በጋ ከክረምት የለምንም እረፍት ኤልያስን ሲያገለግሉ ኖረዋል፡፡ እምነት ካለ ተአምር መሥራት አይገድም ይህንም ከኤልያስ ይማሯል፡፡ ✤ 4. ለአንዲት መበለት ዱቄትና ዘይት አበረከተ፤ ኤልያስ ቁራሽ እየለመነ ያደረገውን ተአምር ልብ ይሏል፡፡ 1ኛ ነገሥ. 17፥16-24፡፡ ✤ 5. ዱቄትና ዘይት ያበረከተላት የሰራፕታዋ ሴት ልጇ /ኋላ ዮናስ ነቢይ የሆነው/ ቢሞት ከሞት አስነሳው 1ኛ ነገሥ. 17፥20-23 ✤ 6. ለብዙ ጊዜ በቤተ መንግሥት ተሰግስገው አክአብና ኤልዛቤልን በሐሰት ሲደልሉ፥ ግብዝ ሕብረተሰቡን ሲያታልሉ፥ ለፍቶ ያገኘው ገንዘቡን ሲሸልጉ፥ በኀጢአት ሊያስወጉ የነበሩ ነቢያተ ሐሰትና ካህናተ ጣዖትን በሕብረተሰቡ ፊት እስከ መምህራቸው ሰይጣን በቅሌት አከናንቦ ሲያስቅባቸው ውሏል፤ ሐሰቶች የነበሩትን 850 የሚጠጉ የጣዖት ካህናትንም ወደ ቂሶን ወንዝ አውርዶ ፈጅቷቸዋል፡፡ 1ኛ ነገሥ. 18 20 -29 ✤ 7. ወደ ፈጣሪው በጸሎት በማመልከት ያቀረበው ንጹሕ መሥዋዕቱን ከሰማይ እሳት ወርዶ በሰው ፊት በላለት (ተቀበለለት) 1ኛ ነገሥ. 18፥30-40፡፡ በዚህም ማንነቱን በሰይጣንና በሰይጣን አቀንቃኞች ፊት አስመስክሯል፡፡ ✤ 8. እሳት ከሰማይ በማዝነም ሊጣሉት የመጡትን መምለኪያነ ጣኦት፥ ምሉአነ ኀጢአት፤ የሰይጣን ሠራዊት በሰው ደም የሰከሩ፥ በዲያብሎስ የሚመሩ ጠላቶቹን አጋይቷል 2ኛ ነገሥ 1 9-13 ✤ 9. ምግብና መጠጥ መልአክ ከሰማይ አመጣለት ያንን ተመግቦ ለአርባ ቀን ያለምንም ምግብና መጠጥ እስከ እግዚአብሔር ተራራ እስከ ኮሬብ ድረስ 40 ቀንና 40 ሌሊት ተጉዟል 1ኛ ነገሥ. 19፥5-7፡፡ ✤ 10. በመጎናጸፊያው የዮርዳኖስን ባሕር ከፍሎ ከነ ደቀመዝሙሩ በደረቅ ተሻግሯል 2ኛ ነገሥ. 2፥11፡፡ ለደቀመዝሙሩም ሀብተ መንገፈስ ቅዱስን አድሎታል፡፡ ✤ 11. በትህትናው ‹‹ይበቃኛል፤ አሁንም አቤቱ እኔ ከአባቶቼ አልበልጥምና ነፍሴን ውሰድ›› ብሎ እንዲሞት ለመነ፡፡ እግዚአብሔር ግን ቅድመ ልደተ ክርስቶስ በ918 ዓመተ ዓለም ሳይሞት በሕይወቱ መራራውን ሞት ዕያየው በብርሃን ሠረገላ ወደሰማይ አሳርጎታል፡፡ 2ኛ ነገሥ. 2፥6-9 ✤ 12. እንደ አስፈላጊነቱ ከፈጣሪው ጋር ለብዙ ጊዜ ተነጋግሯል፡፡ ✤✤#ከአንድ እስከ አስራ አንድ ያደረጋቸውን ተአምራት የፈጸመለት ታማኝ ፈጣሪው ሰው በሆነበት ወራት በተራራ ከጓደኞቹ ጋር ብርሃነ መለኮቱን ገለጠለት ማቴ 17፥3፡፡ #ዳግመኛም ዛሬ የአባቶችን ኖኅ መታሰቢው ነው፡፡ ኖኅ ግን በእግዚአብሔር ፊት ሞገስን አገኘ …ኖኅም በትውልዱ ጻድቅ፥ ፍጹምም ሰው ነበር፡፡ ኖኅ አካሔዱን ከእግዚአብሔር ጋር አደረገ፡፡ /ዘፍ. 6፥7/ #ዳግመኛም በዚህች ዕለት በበረሃ ስልሳ ዘመናት የኖረ የቅዱሳንን ልቡና ከማየቱ የተነሣ ያደነቀ፤ ፊቱም ተለውጦ እንደእሳት ፍሕም ሆነ አባ ሙሴ በዓለ ዕረፍቱ ነው፡፡ #በአዲስ_አበባ_የጌታችን_በዓለ_ግዝረት_የሚከበርባቸው_ #፪ #ገዳማትና_አድባራት፡፡ ፩. ገነተ ኢየሱስና ገነተ ማርያም ቤ/ክ፤ አድራሻው፤ የካ ክፍለ ከተማ፥ ፈረንሳይ፤ ታክሲ፤ ከአራዳ ጊዮርጊስ ሞቢሉ ጋር (4 ኪሎ) (6 ኪሎ) → ፈረንሳይ/ኢየሱስ/፤ ፪. ገዳመ ኢየሱስ ቤ/ክ አድራሻ፤ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ፤ #በሃገራችን_በኢትዮጵያና_በዓለም_አቀፍ_ደረጃ_የጌታችን_በዓለ_ግዝረት_የሚከበርባቸው_ #፬ #ገዳማትና_አድባራት፡፡ ፩. ምዕራፈ ቅዱሳን በልበሊት ኢየሱስ ገዳም፤ አድራሻ፤ ሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት፥ እንሳሮ ወረዳ፥ ጀማ በረሃ፤ ፪. ለብቃ ኢየሱስ፤ (ተአምረኛ የኾነ ፍልውሃ ጠበል የሚፈልቅበት፤ በቆዳ በሽታ በአካል፥ ደዌ የፈራረሰን ሰውነት ሳይቀር የሚጠግን)፡፡ ከገናናነቱ ተነሣ የሚከተለው ግጥሞች ተገጥሞለታል፡፡ ፨ የለብቃው ኢየሱስ፥ የለብቃው፤ የፈረሰ ገላ ትጠቅማለህ አሉ፡፡ እየተባለ የሚዘመርለት፡፡ አድራሻ፤ ሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት፥ መርሐ ቤቴ፥ ሚዳና ወረሞ ወረዳ፤ ወይም፤ ከደቡብ ወሎ (ደሴ ወይም ወግዲ) → መርሃ ቤቴ /አለም ከተማ/ → ለብቃ ኢየሱስ፡፡ ፫. በለስ ዋሻ ኢየሱስ ገዳም፤ (ጥንታዊና የቅዱሳን መናኸሪያ፤ በተጕለት ከሚገኙ ከ5ቱ የቅዱሳን መናኸሪያ ገዳም አንዱ፡፡) አድራሻ፤ ሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት፥ ተጉለትና ቡልጋ፥ አይዞሽ አሞራ፤ ወይም ከአዲስ አበባ ላምበረት አውቶቡስ ተራ → ደብረ ብርሃን → በኩክ የለሽ መንገድ → ዘንባባ ኢየሱስ → በለስ ዋሻ ፬. አማኑኤል ኢየሱስ ቤ.ክ.፤ አድራሻ፤ ምሥራቅ ጎጃም ሃገረ ስብከት፥ ደንበጫ፥ አማኑኤል ከተማ፤ /በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሕትመት እና ሚዲያ ንዑስ ክፍል የተዘጋጀ ::/ #share .YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w .Telegram... https://t.me/medihanaelem http://tiktok.com/@finotehiwot www.finotehiwotsundayschool.com #ጾም #አጽዋማት #fasting's #ክብረ_በዓላት #Feast_of_the_lord #በዓለ_እግዚእነ

#ጥር_4_ተዝካረ_ፍልሰቱ (በዓለ ስዋሬው ) #ለቅዱስ_ዮሐንስ_ሐዋርያ ፤ ዮሐንስ ወንጌላዊ ፤ ፍቁረ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ዮሐንስ ሐዋርያ በተለያዩ ቅጽል ስሞች የሚጠራ፤ ጌታቸችንን ሥነ ስቅለት የሳለ፡፡ ከ81ዱ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች 5ቱንና ሌሎች መጻሕፍትን (ነገረ ማርያምን ..) የደረሰ፤ #ብዙ ደቀ መዛሙርትን ያስተማረ፤ ጌታ እናቱንም እነሆ ልጅሽ ያላት እርሱን ደቀ መዝሙሩንም እነኋት እናትህ ያለው ነው፡፡ ✤ዮሐንስ ንጹሕ በአምሳለ ትጉሃን፤ (#ዮሐንስ_እንደ_መላእክት_ንጹሕ_ነው፤) ✤ዮሐንስ ድንግል ምክሐ ቅዱሳን፤ (#ዮሐንስ_ድንግል_የቅዱሳን_መመኪያ_ነው፤) ✤ዮሐንስ ስርግው በቀጸላ ሥን በሜላተ ብርሃን፤ (#ዮሐንስ_በብርሃን_መጐናጸፊያና_ሻሽ_የተጌጠ_ነው፤) ✤ዮሐንስ አርጋኖነ ዘቤተ ክርስቲያን፤ (#ዮሐንስ_የቤተ_ክርስቲያን_በገና_ነው፤) ✤ወበቃለ ቀርን ዘይኬልህ በኤፌሶን፥ ይስአል ለነ ስርየተ ለኀጥኣን፡፡ (#በኤፌሶን_ዐዋጅ_የሚናገር_ዮሐንስ_ኀጥኣን_ለምንሆን_ለኛ_ይቅርታን_ይለምንልን፡፡ /መጽሐፈ ሰዐታት/ ፨#100_አካባቢ_ከሚጠጉ_ስሞቹ_ጥቂቶቹን_21ዱን_ስሞች_እነኾ፤ #ሐዋርያው_ቅዱስ_ዮሐንስ፤ ዮሐንስ #ፍቁረ እግዚእ፥ (የቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጐድጓድ ለጌታ በጣም ቀራቢ ከነበሩት ሦስት የምሥጢር ሐዋርያት (ጴጥሮስ ፣ ናያዕቆብ ) ዮሐንስ ቀዳሚዉ ነዉ፡፡ ጌታችን ምሥጢረ ተአምራትን በኢያኢሮስ ቤት ፣ ምሥጢረ መንግስትን (መለኮትን) በደብረ ታቦር፣ ምሥጢረ ምጽአትን በደብረ ዘይት ፣ ምሥጢረ ጸሎትን በጌቴ ሴማኒ ሲገልጽና ሲያሳይ አብሮ የተመለከተ በመሆኑና ለጌታ በጣም ቀራቢ በመሆኑና በወንጌልም ‹‹ጌታ ይወደዉ የነበረ ደቀ መዝሙር ››ተብሎ ስለ ተጠቀሰ የጌታ ወዳጅ ፍቁረ እግዚእ ይባላል፡፡ዮሐ 13፡ 23 ፡፡ ወልደ #ዘብድዮስ ፥ ዮሐንስ #ነባቤ መለኮት ፥ ዮሐንስ #ቦኦርኔጌስ ፥ ዮሐንስ #አብቀለምሲስ ፥ (ፍጥሞ በምትባል ደሴት ላይም ወደ ፊት የሚሆነዉን ነገር በራእይ ስለተገለጸለት በግሪክ ቋንቋ አቡቀለምሲስ ተብሏል፡፡ትጉሙም የራዕይ አባት ማለት ነዉ፡፡) ዮሐንስ #ወንጌላዊ ፥ ዮሐንስ #ድንግል ዮሐንስ #ታዎሎጎስ ቅዱስ ዮሐንስ ምሥጢረ ሥላሴንና ምሥጢረ ሥጋዌን አስፍቶ በመጻፉ (ታዎሎጎስ) ተብሏል፡፡ትርጉሙም ነባቤ መለኮት (የመለኮትን ነገር የሚናገር)ማለት ነዉ፡፡ 1. #ዮሐንስ_ብፁዕ (ብፁዕ ዮሐንስ) ፣ 2. ዮሐንስ ድንግል ፣3. #ዮሐንስ_ፍንው፣4. #ዮሐንስ_ካህን ፣ 5. #ዮሐንስ_ኅሩይ ፣ 6. ዮሐንስ ሥርግው፣7. #ዮሐንስ_ምዑዝ8. ዮሐንስ ቅኑይ ፣ 9. #ዮሐንስ_ማኅቶት ፣ 10. ዮሐንስ ቤዛ ሰማይ ፣ 11. #ዮሐንስ_ክቡር12. ዮሐንስ ጻድቅ ፣ 13. #ዮሐንስ_ረድእ፣ 14. ዮሐንስ ማኅቶት፣ 15. #ዮሐንስ_ድንግል፣ 16. ዮሐንስ ንጹሕ ፣ 17. #ዮሐንስ_ለባዊ ፣18. ዮሐንስ መረግድ፣ 19. #ዮሐንስ_ዕንቈ ፣ 20. ዮሐንስ መልአክ ፣21. #ዮሐንስ_ኪሩብ ፣22. #ቁጽረ ገጽ #ስዋሬው፤ ቅዱስ ዮሐንስ እስከ መስቀል ድረስ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተቀበለዉን መከራ በማየቱ ከዚያ ዕለት ጀምሮ 70 ዘመን ሙሉ ፊቱ በኅዘን የተቋጠረ በመሆኑ (ቁጽረ ገጽ) ሆኖ ኖሯል፡ ቅዱስ ዮሐንስ ብዙ ተጋድሎን አርገጐ ዓለምን ሁሉ ዞሮ ካስተማረ ቦኃላ በመጨረሻም ደቀ መዝሙሩ አብሮኮስን ከወንድሞችም ሌሎች ሁለትን መርጦ መቆፈሪያ ይዘው ይከተሉት ዘንድ አዘዘ ፡፡ ጕድጓድም እንዲቆፍሩ አዘዘ ከዚያም ወረዶ ቆመ ልብሱንም አስወገደ የበፍታ ቀሚስ በቀር ሌላ አላረገም ነበር ፡፡ እየጸለየ ወደ ከተማም አሰናበታቸው፡፡ በክርስቶስ ሃይማኖት ይጸኑ ዘንድ ለሕዝብ ይነግሩአቸው ዘንድ አዘዘ ሁሉም እንደየ ስራቸው ጌታ እንደሚከፍላቸው ነገራቸው ፡፡ካዛም እንዲህ አለ እኔ ከሁላችሁም ደም ንፁሕ ነኝ ከእግዚአብሔር ትእዛዝና ሕግ ሳልነግራቹ የተውኩት ምንም ምን የለምና እናንተም ከእንግዲህ ከቶ ፊቴን አታዩም አላቸው ፡፡ እነርሱም እጅና እግሮቹን ስመውት ትተውት ሄዱ ሲመለሱም ልብስና ጫማ እንጂ ምንም አላገኙም እግዚአብሔርንም አመሰገኑት፡፡ ወልደ ነጐድጓድ ቅዱስ ዮሐንስ ዘጠና ዓመትም ኖረ፤ እንደባላሟሎቹ ሐዋርያት በመሰየፍ ሞትን አለቀመሰም፡፡ ‹‹ያ ደቀ መዝሙር አይሞትን እንዲል ›› ዮሐ 21 ስለ ድንግልናውና ስለንጽሕናው ይህ ሁሉ ሆነ፡፡ በዚህ በከበረ ሐዋርያ ጸሎት ይማረን አሜን #share እና #Like ማድረግ እንዳይረሱ በሃገራችን በኢትዮጵያ ጥር 4 የቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጐድጓድ ዓመታዊ ክብረ በዓል የሚከበርባቸውን አድባራትና ገዳማት /በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሕትመት እና ሚዲያ ንዑስ ክፍል የተዘጋጀ ::/ #share .Facebook... https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool .YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w .Telegram... https://t.me/medihanaelem http://tiktok.com/@finotehiwot www.finotehiwotsundayschool.com #ክብረ_በዓላት #feasts #ቅዱሳን_ሐዋርያት #Apostles

#በአዲስ_አበባ_የሚከብርባቸው_፪ #ገዳማትና_አድባራት፡፡ ፩. እንጦጦ ሐመረ ኖኅ ኪዳነ ምሕረት ገዳም አድራሻ፤ ጉለሌ ክፍለ ከተማ፥ እንጦጦ፤ ትራንስፖርት፤ ከፒያሳ ጊዮርጊስ (4 ኪሎ) (ከመርካቶ) → ሽሮ ሜዳ → እንጦጦ ኪዳነ ምሕረት፡፡ #ለቅምሻ_በአጭሩ፤ #እንጦጦ_ሐመረ_ኖኅ_ኪዳነ_ምሕረት_ገዳም ፠ እንጦጦ ሐመረ ኖኅ ኪዳነ ምሕረት በ485 ዓ.ም. የሸዋ አባቶች የዐብዩ መድኀኔዓለምንና የበረከት ኪዳነ ምሕረት ታቦትን ይዘው ለ3 ወራት የተሰባሰቡባት ስትሆን፤ ታቦተ ኪዳነ ምሕረትን እንጦጦ ላይ አስቀምጠውና ገዳሟን መሥርተው፤ ታቦተ መድኀኔ ዓለምን ደግሞ ይዘው ወደ ዋልድባ በመሄድ ቀድሞ ጌታችን የገደመውን ገዳም ለ2ኛ ጊዜ አስፋፍተውታል፡፡ ፠ ከ16 ዓመታትት በኋላ በ500 ዓ.ም. ደግሞ አቡነ ሊባኖስ ዘመጣዕ ከአኵሱም ወደ ሸዋ ሲመጡ ሐመረ ኖኅን በገዳምነት ገድመው፥ ጠበሏን አፍልቀው፥ ሕሙማንን ፈውሰው ተመልሰዋል፡፡ ፠ በ1967 ዓ.ም. አንድ ምዕመን ለፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለሃይማኖት አስፈቅደው፤ ገድላቸውን ከአኵሱም አጽፈው በማምጣት ማኅሌቱ እንዲቆም፣ ገድላቸው እንዲነበብ፤ 50 ብር እየከፈሉ የጻድቁን ዝክር እንዲገለገል አስደርገዋል፡፡ ፠ ባለውለታዋን ዘንግታ የቆየችው እንጦጦ ሐመረ ኖኅ ኪዳነ ምሕረት ገዳምም ከ በኋላ በዕለተ እሑድ ጥር 3/2012 ዓ.ም. ለመጀመሪያ ጊዜ ታቦተ ሕጉን አውጥታ አክብራለች፨ ፪. አያት ጣፎ መካነ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤ/ን፡፡ (በድርብነት ይከበራል) አድራሻ፤ የካ ክፍለ ከተማ፥ አያት 2 ኮንዶሚንየም ትራንስፖርት፤ ከመገናኛ → አያት(በሲኤምሲ) አደባባይ ወደ ጣፎ በሚወስደው መንገድ ወይም ከመገናኛ በኮተቤ ጣፎ /አባ ኪሮስ ጋር ወርደው/ በባጃጅ (በታክሲ) ያገኙታል፡፡ #በኢትዮጵያና_በዓለም_አቀፍ_ደረጃ_የሚከብርባቸው_፱ #ገዳማትና_አድባራት፡፡ ፩. ደብረ ወርቅ ገዳመ መጣዕ አቡነ ሊባኖስ፤ (በ523 ዓ.ም. በጻድቁ በአቡነ ሊባኖስ የተገደመና በአፄ ገብረ መስቀል የታነጸ፥ ገደል ወገብ ላይ የታነፀና የሚያስደንቅ፡፡) (የጻድቁ የከበረ አጽም የሚገኝበት፥ ሙት ያስነሳበት፥ ዕውር ያበራበት ገዳም ነው) አድራሻ፤ ደቡብ ኤርትራ፥ አካለ ጉዛይ አውራጃ፥ ሃም ታርካ፡፡ ትራንስፖርት፤ ከአዲስ አበባ (በአውሮፕላን) → ኤርትራ → አካለ ጉዛይ → ሃም ታርካ፡፡ ፪. አኵሱም አጠገብ የሚገኝ አባ ሊባኖስ፤ (ጻድቁ የዋሻ በዓት ሠርተው የጸለየበት፥ 7ት ዓይነት ጠበል ያፈለቀበት፤ አንዲት እናት ውኃ ነው ብላ ብትዳፈር ልጇ ሞቶባት እንደ ኤልያስ ያስነሳበት፥ የአከባቢው ካህናት ቢያድሙበት እንደ ኤልያስ በዚህ አካባቢ ላይ ለ3ት ዓመት ዝናብ እንዳይዘንብ የከለከለበት ኋላ ደግሞ በይቅርታ ቢጠይቁት ዝናብ ያዘነበበት ነው) (ልጅ ያጡ የሚወልዱበት መታሻ ደንጊያ ያለበት፥ ከዐለት ላይ የሚፈልቅ ተአምረኛ ጠበል ያለበት) (ገዳሙ ዋሻና ለእኅቶች ደግሞ ክብ ሕንፃ ቤ/ን አለ) አድራሻ፤ አኵስም ሃገረ ስብከት ትራንስፖርት፤ ከአዲስ አበባ መርካቶ አውቶቡስ ተራ በጎንደር/በሽሬ/ → አኵስም → የ10 ብር ትራንስፖርት(የ2ሰዐት የእግር መንገድ) ወይም ከአዲስ አበባ ላምበረት አውቶቡስ ተራ በደሴ/ወልድያ/መቀለ/ → አኵስም → የ10 ብር ትራንስፖርት(የ2ሰዐት የእግር መንገድ) ፫. ተንቤን አምበራ አቡነ ሊባኖስ (በአፄ ገብረ መስቀል የታነፀ) አድራሻ፤ ትግራይ ትራንስፖርት፤ ከአኵሱም → ተንቤን ፬. ላስታ ላሊበላ ቤተ አባ ሊባኖስ (ቅዱስ ላሊበላ ለ23ት ዓመታት ካነጻቸው አንዱ፥ በላስታ ከሚገኙት 11ዱ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ደግሞ አንዱ የኾነና ከ11ዱ ሙሉ ለሙሉ ከተራራ ላይ ተፈልፍሎ ባለመውጣቱ በአሠራሩ ልዩ የኾነ) አድራሻ፤ ሰሜን ወሎ ሃገረ ስብከት፥ ላስታ፥ ላሊበላ ከተማ፡፡ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ላምበረት አውቶቡስ ተራ በደሴ/በጋሸና/ → ላሊበላ ወይም ከአ.አ. (በአውሮፕላን) → ላሊበላ ወይም ከጎንደር (ባህር ዳር) /በወረታ/ /ደብረ ታቦር/ /ጋሸና/ → ላሊበላ ወይም ከመቀለ በወልድያ መስመር/ጋሸና/ → ላሊበላ ፭. ዛራ ሐሙሲት አካባቢ የሚገኘው አባ ሊባኖስ (ቅዱስ ላሊበላ ለ23ት ዓመታት ካነጻቸው አንዱ) አድራሻ፤ ደቡብ ጎንደር ሃገረ ስብከት ትራንስፖርት፤ ከባህር ዳር /በጎንደር መስመር/ → ሐሙሲት ፮. ጎንደር ግራርጌ (ቆላ ድባ) ፈለገ ሕይወት አቡነ ሊባኖስ፤ (በአፄ ገብረ መስቀል እንደተመሠረተ የሚነገርለት፥ አጸዱ እጅግ በጣም የሚማርክ /ዕድሜ ጠገብና አርስ በእርሱ የገጠመ 4 ትላልቅ ወርካና 4 ጽድ የሚገኝበት፤ ወርካውን ፈልፍለው መነኰስ ይኖሩበት የነበረው ለምስክር ቆሞ የሚገኝበት፥ 1ዱ ጽድ በ1880 አካባቢ ወድቆ እስካሁን ዝናብና ፀሐይ እየፈራረቀበት ሳይበሰብስ የሚገኝበት)፤ ውሎ ቅዳሴ የሚቀደስበት፤ የአከባቢው ገበሬ እህሉን ወደ ጎታው ከቅዳሴ በኋላ የሚያስገባበት የበረከት ቃል ኪዳን የተሰጠው ምድር፡፡ አድራሻ፤ ማዕከላዊ ጎንደር ሃገረ ስብከት፥ ደንቢያ ወረዳ፥ ቆላ ድባ ከተማ፡፡ ትራንስፖርት፤ ከጎንደር (አዘዞ) → ወደ ጎርጎራ መስመር (በደረስጌና በቆላ ድባ መሃል ላይ ያገኙታል) (በ25 ኪ.ሜ አስፓልቱ ዳር) ፯. በመንዝ ቀያ ሀገረ ገራዴ አባ ሊባኖስ አፅመ ቅዱሳን ዋሻ (ፈዋሽ ጠበልና አስገራሚ ዋሻ ያለበት)፡፡ አድራሻ፤ ሰሜን ሸዋ ሃገረ ስብከት፥ መንዝ ቀያ ገብርኤል ወረዳ፥ ዘመሮ ከተማ፥ በንዲ ቀበሌ፡፡ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ዘመሮ → 9 ኪ.ሜ ያህል እንደተጓዙ በንዲ ቀበሌ (ከአዲስ አበባ 328 ኪ.ሜ. ርቀት ላይ ይገኛል) ፰. መንዝ ላሎ አንጀትላ አቡነ ሊባኖስ ገዳም፤ አድራሻ፤ ሰሜን ሸዋ ሃገረ ስብከት፥ መንዝ፥ ዘብር፥ ላሎ፥ አንጀትላ፡፡ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ዘብር(247 ኪ.ሜ.) → የ2ት ሰዐት የእግር መንገድ → የአንጀትላ አቡነ ሊባኖስ ገዳም፡፡ ፱. *** ነገር ግን የመሠረቱት፥ ለ40 ዓመታት በዓት ሠርተው የኖሩበትና፥ በስማቸው የሚጠራው ታላቁ ገዳም ደብረ ሊባኖስ ግን ባለፉት 10ር ዓመታት ውስጥ ገድላቸውን በግእዝና በአማርኛ ከማሳተም የዘለለ የሚጠበቅበትን ሥራ አልሠራም፡፡ (ያልጠቀስናቸውን አሳውቁን) /በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሕትመት እና ሚዲያ ንዑስ ክፍል የተዘጋጀ ::/ #share .Facebook... https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool .YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w .Telegram... https://t.me/medihanaelem http://tiktok.com/@finotehiwot www.finotehiwotsundayschool.com

ጥር 3 የደብረ_ሊባኖስ_ገዳምን_የመሠረቱና_በስማቸው_የተሠየመላቸው እና የእንጦጦ_ሐመረ_ኖኅ_ኪዳነ_ምሕረት_ገዳምን_ጸበል_ያፈለቁ የታላቁ አባት አባ_ሊባኖስ_ዘመጣዕ በዓለ ዕረፍት ነው ። #ጥር ፫፤ #የአቡነ_ሊባኖስ_ዘመጣዕ_በዓለ_ዕረፍት_ክብረ_በዓል_የሚከብርባቸው ፲፩ ገዳማትና አድባራት (ከታች)፡፡ #በአ.አ. #እንጦጦ_ሐመረ_ኖኅ_ኪዳነ_ምሕረት ቀድሞ በቅዳሴና በውዳሴ ታቦተ ሕጋቸው ሲከበር የቆየው የአቡነ ሊባኖስ ዘመጣዕ ታቦተ ሕጋቸው #ረቡዕ_ጥር 3/2015 ዓ.ም. አራተኛ ጊዜ_ታቦተ_ሕጋቸው_ወጥቶ_ይከብራል፡፡ (ሁላችሁም እንድትገኙ ገዳሟ ጥሪዋን አስተላልፋላች)፡፡ አባ ሊባኖስ #የደብረ_ሊባኖስ_ገዳምን_የመሠረቱና_በስማቸው_የተሠየመላቸው፤ ፠ ቅዱስ ላሊበላ ከ11ዱ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት አንዱን በስማቸው ያነፀላቸው፡፡ ፠ #ከደረቅ_ዐለት_ላይ_ውሃ_እያፈለቁ_ድውያንን_የሚፈውሱ_ተአምረኛ_አባት ፠ በኤርትራ አካለ ጉዛይ ገዳመ መጣዕ፣ በአኵሱም ከተማ አጠገብ፣ በላስታ ላሊበላ፣ ደብረ ወርቅ አቡነ ሊባኖስ ገዳም፣ እንዲሁም ከ2012 ዓ.ም. ጀምሮ በአ.አ. እንጦጦ ሐመረ ኖኅ ገዳም ክብረ በዓል የሚከበርላቸው። ፠ አባታቸው አብርሃም እናታቸው ንግሥት ሊድሯቸው ሲሉ መመነን በመፈለጋቸው መልአክ በሌሊት መጥቶ ወደ ታላቁ አባት አባ ጳኩሚስ ዘንድ አደረሳቸው፡፡ ፠ አባ ጳኩሚስም ሥርዐተ ገዳምን፥ አስኬማ መላእክትን፥ ቅናተ ዮሐንስን አስተማሯቸው፤ አመነኮሷቸውና ከ8ቱ ቅዱሳን ጋር እንዲገናኙ አደረጓቸው፡፡ ፠ ቀድሞ የመራቸው መልአክ ከአባ ጳኩሚስ ‹‹ወደ ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ ሂድና ተጋድሎህን በዚያ ፈጽም ዝናህ በስፋት ይነገራል፣ ለብዙዎችም አባት ትሆናቸዋለህ›› አላቸው፡፡ ቀጥሎም ራሱ መልአኩ ወደ ኢትዮጵያ አመጣቸውና በአኵሱም ተቀመጡ፡፡ ፠ በዚያም ብዙ ከተጋደሉ በኋላ ወደ ሸዋ መጡና ወንጌልን ዞረው አስተምረው ብዙ ድውያንን ፈውሰው (ቀድሞ የዋልድባን ገዳም ባስፋፉ አባቶች የተመሠረተችውን #የእንጦጦ_ሐመረ_ኖኅ_ኪዳነ_ምሕረት_ገዳምን እስፋፍተው፡፡) ተመልሰው ወደ አኵሱም ሄዱ፡፡ ፠ በአኵሱምም 7 የተለያዩ ጸበሎችን ከድንጋይ ላይ በተአምራት አፍልቀው ድውያንን ፈውሰው ፥ ዕውራንን አበሩ፡፡ በዓታቸውንም ከአኵሱም ጽዮን ፊት ለፊት አድርገው ሲኖሩ ከዕለታት በአንደኛው ቀን አባታችን በተአምራት ከጭንጫ ካፈለቁት ጸበል ‹‹ተራ ውሃ ነው›› ብላ አንዲት ሴት ልጇን አዝላ ልትቀዳ መጣች፡፡ ወዲውም ከቦታው ስትደርስ አድጧት ወደቀችና ልጇም አምልጥጧት ልቡን ድንጋይ መቶት ሞተ፡፡ ሴትዮዋም ስትጮህ አባ ሊባኖስ ፈጥነው ወጡና በልጁ ላይ ጸልየው በመስቀል ምልክት አማትበው ከሞት አስነሥተውታል፡፡ ሕፃኑ ልጅ ከሞት እንደተነሣ ‹‹አምላከ አባ ሊባኖስ›› ብሎ አመሰገነ፡፡ (ስዕላቸው የሚገልጸው ይህንን ተአምር ነው፡፡) ፠ ይህንንም ደግ ሥራቸውንና ተአምራታቸውን ያዩ አንዳንድ እኩይ ካህናት በቅናት ተመልተው ‹‹ምትሃት ነው የሚያሳየው›› ብለው በጻድቁ ላይ ሕዝቡን አሳደሙባቸው፡፡ አባታችንም ካህናቱን ለመምከር ቢሞክሩም አላስቀምጥ አሏቸው፡፡ ይልቁንም ጦር ጦራቸውን ይዘው አሳደዷቸው፡፡ ፠ አባታችንም በዚህ እጅግ አዝነው ከአኵሱም ተነሥተው ደርቃ ወደምትባል ቦታ ሄዱ፡፡ በዚያም በጾም በጸሎት እየተጋደሉ ሲኖሩ፤ በእነዚያ በጠሏቸውና በክፋት በተነሡባቸው ካህናት አገር ግን ለ3 ዓመት ምንም ዝናብ ሳይዘንብ ቀረ፡፡ አባታችን በተሰደዱባት በደርቃ አገር ግን ብዙ ዝናብ ይዘንብ ነበር፡፡ አባታችን በዚያችም አገር እንደልማዳቸው ከዐለት ላይ ውኃ አፍልቀው በውኃው ብዙ ድውያንን ፈውሰውበታል፡፡ በዚያም ትልቅ በዓት መሥርተው በተጋድሎ ሲኖሩ በክፉ የተነሡባቸው እኩይ የሆኑ ካህናት መጥተው ‹‹አባታችን በከንቱ አምተንሃል በድለንሃልና ይቅር በለን፣ በድርቅ ማለቃችን ነውና ዝናብም እንዲዘንብልን ጸልይን›› ብለው ከእግራቸው ሥር ወደቁ፡፡ አባታችንም ይቅር ብለው ከፈጣሪ አማለዷቸው፡፡ ዝናቡም ወዲያው ዘነበላቸውና በአገሪቱ ጥጋብ ሆነ፡፡ ፠ ከዚህም በኋላ አባታችን አስቀድመው ወዳዩአት ወደ ሸዋ ምድር ግራርያ (የአሁኗ ደብረ ሊባኖስ) መጡና በዓታቸውን በአሰቦት ጫካ አደረጉ፡፡ ነገር ግን መልአኩ ተገልጦላቸው ‹‹ሊባኖስ ሆይ! ከዚህ ቦታ የአንተ መኖሪያ አይደለም፣ በዚህ ቦታ ላይ እግዚአብሔርንና ሰውን የሚያገናኝ የሚያስታርቅ ታላቅ ጻድቅ (አቡነ ተክለ ሃይማኖት) ይወጣበታልና ይህ ቦታ የእርሱ ርስት ነው፣ የብዙ መነኮሳትም መንደር ይሆናል ነገር ግን የቦታው ስም በአንተ ስም ይጠራልሃል›› አላቸው፡፡ በኋላ አባታችን ተክለ ሃይማኖት ተወልደው በዓታቸውን በዚያ ቦታ ላይ ሲያጸኑ ቦታው ግን ‹‹ደብረ ሊባኖስ›› ተብሎ በመጀመሪያው አባት ስም ተሰየመ፡፡ ፠ መልአኩም በሌሊት እየመራ ወደ አኵሱም ወሰዳቸው፡፡ ከዚያም ‹‹ታሪክ ወደምትሠራበት ዕጣ ክፍልህ ወደሆነው ቦታ አደርስሃለሁ›› አላቸውና ወደ ኤርትራ አካለ ጉዛይ አውራጃ ልዩ ስሙ መጣዕ ወደተባለው ቦታ ወሰዳቸው፡፡ በዚያም አባታችን ድውያንን እየፈወሱ፣ ለምፃሞችን እያዳኑ፣ ሙታንን እያስነሡ ብዙ ተአምራትን እያደረጉ ወንጌልን እየሰበኩ ‹‹ሊባኖስ ዘመጣዕ›› የሚባለውን ትልቁን ገዳማቸውን መሠረቱ፡፡ በወቅቱ የነበረው አፄ ገብረ መስቀልም የመጀመሪያውን ቤተ ክርስቲያን አሠራላቸው፡፡ ፠ ቅዱስ ላሊበላ 23 ዓመት ሙሉ ካነጻቸው እጅግ ድንቅ 11 ቤተ መቅደሶች ውስጥ አንደኛውን በአባ ሊባኖስ ስም ሰይሞላቸዋል፡፡ አፄ ገብረ መስቀል ያሠራላቸው ሌላኛው ገዳማቸው ትግራይ ተንቤን ውስጥ ይገኛል፡፡ እጅግ ድንቅ ድንቅ ተአምራትን በማድረግ የሚታወቁት አባታችን እንደ ተስዓቱ ቅዱሳን ከሮም በመምጣት በሀገራችን ላይ ብርሃንን አብርተዋል፡፡ ፠+፠ በመጨረሻም ጥቅምት 2 ቀን ተፀንሰው ፤ ፠+፠ ሐምሌ 3 ቀን ተወለደው፤ ፠+፠ በ140 ዓመታቸው ጥር 3 ቀን በክብር ዐርፈዋል፡፡ ፠+፠ ቅዳሴ ቤታቸው ደግሞ ሐምሌ 3 ነው፡፡ ይኸውም ለመጀመሪያ ጊዜ በዐፄ ገብረ መስቀል ጊዜ በስማቸው ቤተ ክርስቲያን ተሠርቶ የተመረቀበት ዕለት ነው፡፡ * እኛም ለክብረ በዓሉ የሚሆነውን ከዋይዜማው ጀምሮ ሙሉውን ሥርዐተ ማኅሌት እነሆ ብለናል፡፡ #እንጦጦ_ሐመረ_ኖኅ_ኪዳነ_ምሕረት_ገዳም ፠ እንጦጦ ሐመረ ኖኅ ኪዳነ ምሕረት በ485 ዓ.ም. የሸዋ አባቶች የዐብዩ መድኀኔዓለምንና የበረከት ኪዳነ ምሕረት ታቦትን ይዘው ለ3 ወራት የተሰባሰቡባት ስትሆን፤ ታቦተ ኪዳነ ምሕረትን እንጦጦ ላይ አስቀምጠውና ገዳሟን መሥርተው፤ ታቦተ መድኀኔ ዓለምን ይዘው ወደ ዋልድባ በመሄድ ቀድሞ ጌታችን የገደመውን ገዳም ለ2ኛ ጊዜ አስፋፍተውታል፡፡ ፠ ከ16 ዓመታትት በኋላ በ500 ዓ.ም. ደግሞ አቡነ ሊባኖስ ዘመጣዕ ከአኵሱም ወደ ሸዋ ሲመጡ ሐመረ ኖኅን በገዳምነት ገድመው ጠበሏን አፍልቀው ሕሙማንን ፈውሰው ተመልሰዋል፡፡ ፠ በ197 ዓ.ም. አንድ ምዕመን ለአቡነ ተክለሃይማኖት አስፈቅደው፤ ገድላቸውን ከአኵሱም አጽፈው በማምጣት ማኅሌቱ እንዲቆም፣ ገድላቸው እንዲነበብ፤ 50 ብር እየከፈሉ የጻድቁን ዝክር እንዲገለገል አስደርገዋል፡፡ ፠ የአባቶቻችን አምላክ መድኀኔ ዓለም ክርስቶስ ይመስገን፨ #ጥር ፫፤ #የአቡነ_ሊባኖስ_ዘመጣዕ_በዓለ_ዕረፍት_ክብረ_በዓል_የሚከብርባቸው ፲፩ ገዳማትና አድባራት፡፡ (አባ ሊባኖስ በሃገራችን ላይ 80 ገዳማትን መሥርተዋል) በ79 ገዳማትና አድባራት ላይ ሲከበሩ ዐበይቶቹ የሚከተሉት ናቸው፤

አድራሻ፤ ጉራጌ ሃገረ ስብከት፥ ማፌድ፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. አየር ጤና አውቶቡስ ተራ → ሆሳዕና → ማፌድ፡፡ ፳፩. እዣ ስራይ ቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጐድጓድ ቤ/ክ፤ አድራሻ፤ ጉራጌ ሃገረ ስብከት፥ እዣ፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. አየር ጤና አውቶቡስ ተራ → ሆሳዕና → እዣ፡፡ ፳፪. ደብረ ዘይት ቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ፤ አድራሻ፤ ምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት፥ አድአ ወረዳ → ደብረ ዘይት፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ቃሊቲ አውቶቡስ ተራ → ደብረ ዘይት፡፡ ፳፫. አለም ገና ቤ/ን (ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ በድርብነት ይከብራል)፤ አድራሻ፤ ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት፥ አለም ገና፤ ትራንስፖርት፤ ከፒያሳ → ጀሞ → አለም ገና፡፡ /በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሕትመት እና ሚዲያ ንዑስ ክፍል የተዘጋጀ ::/ #share .Facebook... https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool .YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w .Telegram... https://t.me/medihanaelem http://tiktok.com/@finotehiwot www.finotehiwotsundayschool.com