uz
Feedback

Firibgarlarga uchmang! Telemetrio bunday kanallarni topadi va belgilaydi 👉 Belgini ko‘rmoqchi bo‘lsangiz, obuna bo‘ling 👈

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Kanalga Telegram’da o‘tish

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Ko'proq ko'rsatish

📈 Telegram kanali Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት analitikasi

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) Amxar til segmentidagi kanali faol ishtirokchi. Hozirda hamjamiyat 15 626 obunachidan iborat bo'lib, Din & Maʼnaviyat toifasida 5 373-o'rinni va Efiopiya mintaqasida 2 216-o'rinni egallagan.

📊 Auditoriya ko‘rsatkichlari va dinamika

невідомо sanasidan buyon loyiha tez o‘sib, 15 626 obunachiga ega bo‘ldi.

09 Oktabr, 2026 dagi oxirgi ma’lumotlarga ko‘ra kanal barqaror faollikka ega. Oxirgi 30 kunda obunachilar soni 72 ga, so‘nggi 24 soatda esa 0 ga o‘zgardi va umumiy qamrov yuqori darajada qolmoqda.

  • Tasdiqlash holati: Tasdiqlanmagan
  • Jalb etish (ER): Auditoriya o‘rtacha 8.45% darajada jalb etiladi. Nashrdan keyingi dastlabki 24 soatda kontent odatda umumiy obunachilar sonining 4.64% ini tashkil etuvchi reaksiyalarni to‘playdi.
  • Post qamrovi: Har bir post o‘rtacha 1 319 marta ko‘riladi; birinchi sutkada odatda 725 ta ko‘rish yig‘iladi.
  • Reaksiyalar va o‘zaro ta’sir: Auditoriya faol: har bir postga o‘rtacha 12 ta reaksiya keladi.

📝 Tavsif va kontent siyosati

Muallif resursni shaxsiy fikrni ifoda etish maydoni sifatida ta’riflaydi:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”

Yuqori yangilanish chastotasi (oxirgi ma’lumot 10 Oktabr, 2026 da olingan) sababli kanal doimo dolzarb va katta qamrovli bo‘lib qoladi. Analitika auditoriya kontent bilan faol hamkorlik qilishini, uni Din & Maʼnaviyat toifasidagi muhim ta’sir nuqtasiga aylantirishini ko‘rsatadi.

15 626
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
+907 kun
+7230 kun
Postlar arxiv
#ጥር ፬፤ #በዓለ_ስዋሬሁ_ለዮሐንስ_ወልደ_ነጐድጓድ_፡፡ #በአዲስ_አበባ_በኢትዮጵያና_በዓለም_አቀፍ_ደረጃ_የቅዱስ_ዮሐንስ_ወልደ_ነጐድጓድ_በዓለ_ስዋሬ_ክብረ_በዓል_የሚከብርባቸው #ገዳማትና_አድባራት፡፡ #በአዲስ_አበባ_የሚከብርባቸው_፫ #ገዳማትና_አድባራት_፡፡ ፩. ደብረ ነጐድጓድ ቅዱስ ዮሐንስና መካነ ጎልጎታ ማርያም ቤ.ክ. ታቦተ ሕጉ ከኢየሩሳሌም የመጣ፥ ከዐፄ ዮሐንስ ጋር በመቀለ፤ ከራስ ጉግሳ ወሌ ጋር በደብረ ታቦር፤ ንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ ከደብረ ታቦር ወደ አዲስ አበባ መናገሻ ገተ ጽጌ ያመጣችው፤ አፄ ኀይለ ሥላሴ ደግሞ አሁን ያለውን ሕንፃ ያሠሩት፤ በአዲስ አበባ በወልደ ነጐጓድ ቅዱስ ዮሐንስ ስም በመሰየም ብቸኛው ቤ.ክ.፤ አድራሻ፤ አራዳ ክፍለ ከተማ፥ ሰባራ ባቡር፥ አባ ኮራን፥ ራስ ደስታ ዳምጠው ሆስፒታል ታክሲ፤ ከፒያሳ ጴጥሮስ ዐደባባይ → ዊንጌት አስኮ በሚለው ታክሲ ተሳፍረው ቤተ ክርስቲያኑን ያገኛሉ፡፡ ወይም ከመርካቶ ጎጃም በረንዳ → አዲሱ ገበያ (ቀጨኔ) በሚሉ ታክሲዎች ተሳፍረው ቤተ ክርስቲያኑን ያገኛሉ፡፡ ፪. ብሔረ ጽጌ መካነ ሰላም ቅድስት ማርያምና መድኀኔዓለም ቤ/ክ (የሐዋርያው ዮሐንስ ወልደ ነጐድጓድ ታቦት ቤተ ክርስቲያኑ ከተመሠረተበት ከ፲፱፻፹፮ ዓ.ም ጀምሮ በድርብነት ይከብራል) አድራሻ፤ ነፋስ ስልክ፥ ብሔረ ጽጌ፤ ከብሔረ ጽጌ መናፈሻ 100 ሜትር ያህል ገባ እንዳሉ፡፡ ታክሲ፤ ከፒያሳ (ሰታዲየም)(መርካቶ)(መገናኛ)→ አደይ አበባ/ሳሪስ/ → ብሔረ ጽጌ፡፡ ፫. ምስካየ ኅዙናን መድኀኔዓለም ገዳም (ታቦተ ሕጉ ወጥቶ ባይከብርም፥ ከቀድሞ ጀምሮ በኪዳንና በሰዐታት፤ በውዳሴ፥ በቅዳሴ ይከበራል፡፡) አድራሻው፤ ጉለሌ ክፍለ ከተማ፥ 6 ኪሎ ታክሲ፤ ከፒያሳ(4 ኪሎ) → ሽሮሜዳ በሚለው ታክሲ (ምስካየ ኅዙናን ጋር) ወይም ከመርካቶ ራጕኤል (ከጊዮርጊስ)→ ሽሮሜዳ በሚለው → መነን (የካቲት 12 ት/ቤት) ተወርዶ → ምስካየ ኅዙናን፡፡ #በኢትዮጵያና_በዓለም_አቀፍ_ደረጃ_የሚከብርባቸው_፳፫ #ገዳማትና_አድባራት_፡፡ ፩. መአቁዲ ዮሐንስ ወልደ ነጐድጓድ (ጥንታዊው ደብር፤ ለአንድ ቀን ብቻ ጠበል የፈለቀበት)፤ አድራሻ፤ ትግራይ፤ ትራንስፖርት፤ ከአዲስ አበባ ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ደሴ → ወልድያ → መአቁዲ፡፡ ፪. ደቡብ ወሎ ዮሐንስ ወልደ ነጐድጓድ (ጥንታዊው ደብር፤ ከመካነ ሥላሴ አጠገብ የሚገኝ)፤ አድራሻ፤ ደቡብ ወሎ ሃገረ ስብከት ትራንስፖርት፤ ከአዲስ አበባ ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ደሴ → መካነ ሥላሴ፡፡ ፫. ሐይቅ ደብረ ነጎድጓድ ቅዱስ ዮሐንስ አድራሻ፤ ደቡብ ወሎ ሃገረ ስብከት፥ ሐይቅ ትራንስፖርት፤ ከአዲስ አበባ ላምበረት አውቶቡስ ተራ → ደሴ → በወልድያ መስመር (ሐይቅ ከተማ) ፬. ደብረ በንኰል ገዳም አጠገብ ዮሐንስ ወልደ ነጐድጓድ አድራሻ፤ ትግራይ፥ ሰለኽላኻ፥ ከታላቁ ገዳም ደብረ በንኰል አጠገብ ትራንስፖርት፤ ከመቀለ(አኵሱም) → ሽሬ → ሰልኽላኻ → ደብረ በንኰል መስመር የቅ/ዮሐንስን ደብር ያገኙታል፡፡ ወይም ከጎንደር በሊማሊሞ ሽሬ (ዳንሻ፤ ሁመራ፤ ሽሬ) መስመር → ሰልኽላኻ → ደብረ በንኰል መስመር የቅ/ዮሐንስን ደብር ያገኙታል፡፡ ፭. አደቁዋረክ ዮሐንስ ወልደ ነጐድጓድ፤ አድራሻ፤ አኵስም (ማዕከላዊ ትግራይ) ሃገረ ስብከት፥ ማኅበረ ዴጎ አጠገብ/፤፡፡ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ላምበረት አውቶቡስ ተራ → በደሴ → ወልድያ → መቀለ → አኵስም → ማኅበረ ዴጎ → አደቁዋረክ፤ ወይም ከአ.አ. (በአውሮፕላን ) → አኵስም → ማኅበረ ዴጎ → አደቁዋረክ፤ ወይም ወይም ከአዲስ አበባ መርካቶ አውቶቡስ ተራ → በቡሬ/በሞጣ/ ባህርዳር → ጎንደር → ከጎንደር በሊማሊሞ ሽሬ (ዳንሻ፤ ሁመራ፤ ሽሬ) መስመር → ሽሬ → አኵስም → ማኅበረ ዴጎ → አደቁዋረክ፤ ፮. ገደፈና_ዮሐንስ /ማይጨው አጠገብ/፤ አድራሻ፤ ትግራይ፥ ማይጨው ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ላምበረት አውቶቡስ ተራ → በደሴ → ወልድያ → ማይጨው → ገደፈና፤ ፯. መንዝ ማማ ሞላሌ ደዋ ዮሐንስ (900 ዓመታት በላይ ያስቈጠረ) አድራሻ፤ ሰሜን ሸዋ ሃገረ ስብከት፥ መንዝ፥ ሞላሌ፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ላምበረት አውቶቡስ ተራ → ሞላሌ → ደዋ፤ ፰. ዣት ደብረ ፀሐይ ዮሐንስ ወልደ ነጐድጓድ፤ አድራሻ፤ ሰሜን ሸዋ ሃገረ ስብከት፥ ጅሩ፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ላምበረት አውቶቡስ ተራ → በደብረ ብርሃን በኩል → ጅሩ ፥ እነዋሪ → ዣት፤ ወይም ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → በሙከጡሪ (መርሐ ቤቴ መስመር) → ለሚ → ጅሩ ፥ እነዋሪ፤ ፱. ዘንስር ደብረ ተድላ ዮሐንስ ማዕከላ ለጐንደር፤ /ከ44ቱ ታቦታተ ጎንደር አንዱና ዋነኛው፤ በጎንደር ከተማ የማኅሌተ ጽጌ ቁመት ወደ ግምጃ ቤት ማርያም ከመዛወሩ በፊት በብቸኝነት የጎንደርና የመላው ኢትዮጵያ ሊቃውንት የማኅሌተ ጽጌን ቁመት ለመቆም የሚተሙት ታላቅ ደብር/፤ አድራሻ፤ ማዕከላዊ ጎንደር ሃገረ ስብከት፥ ጎንደር ከተማ፥ አራዳ፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → በቡሬ /በሞጣ/ መስመር → ባህር ዳር → ወረታ → ጎንደር ከተማ፡፡ ወይም ከመቀለ /አኵሱም/ → ሽሬ → በሊማሊሞ (በሁመራ ዳንሻ) → ጎንደር ከተማ፤ ወይም ከደሴ → ወልድያ → ደብረ ታቦር → ወረታ → ጎንደር ከተማ፤ ፲. ሞያሌ ደጋ ዮሐንስ ወልደ ነጐድጓድ፤ አድራሻ፤ ሞያሌ፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. → ሞያሌ፤ ፲፩. ደምበጫ አጠገብ ዮሐንስ ወልደ ነጐድጓድ፤ አድራሻ፤ ምዕራብ ጎጃም ሃገረ ስብከት፥ ደምበጫ፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → /በባህር ዳር መስመር/ ደምበጫ፤ ፲፪. ቦኮሙራ ወልደ ነጐድጓድ ቅዱስ ዮሐንስ ቤ.ክ.ን፤ አድራሻ፤ ሀዲያና ስልጤ ሀገረ ስብከት፥ ሚሻ ወረዳ፥ ቦኮሙራ ቀበሌ፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. አየር ጤና አውቶቡስ ተራ → ስልጤ → በኮሙራ፤ ፲፫. ናዝሬት(አዳማ) ደብረ ፍስሐ ቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ቤ/ክ፤ አድራሻ፤ ምሥራቅ ሸዋ ሃገረ ስብከት፥ ናዝሬት(አዳማ)፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ቃሊቲ አውቶቡስ ተራ → በደብረ ዘይት (በፈጣን መንገድ) → ናዝሬት (አዳማ) ከተማ፤ ፲፬. ደሴ ዩኒቨርሲቲ ደብረ ነጎድጓድ ቤ/ክ፤ አድራሻ፤ ደቡብ ወሎ ሃገረ ስብከት፥ ደሴ ከተማ፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ላምበረት አውቶቡስ ተራ → ደሴ ከተማ፤ ፲፭. መቱ ደብረ ሳሌም ወነጎድጓድ ቅዱስ ዮሐንስ ቤ/ክ፤ (በ1915 ዓ.ም. የተመሠረተ) አድራሻ፤ ም.ወለጋ ሃገረ ስብከት፥ መቱ፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. አስኮ አውቶቡስ ተራ → ወለጋ/መቱ፤ ፲፮. ጨንቻ ዶርዜ አይራ ቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጐድጓድ፤ አድራሻ፤ ጋሞ ጎፋ ሃገረ ስብከት ፥ ጨንቻ ወረዳ፥ ዶርዜ አይራ፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. አስኮ አውቶቡስ ተራ → ወለጋ/መቱ፤ ፲፯. ፎገራ ቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጐድጓድ፤ አድራሻ፤ ደቡብ ጎንደር ሃገረ ስብከት ፥ ፎገራ ወረዳ፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → በቡሬ /በሞጣ/ መስመር → ባህር ዳር → ወረታ → ፎገራ፡፡ ወይም ከመቀለ /አኵሱም/ → ሽሬ → በሊማሊሞ (በሁመራ ዳንሻ) → ፎገራ፤ ወይም ከደሴ → ወልድያ → ደብረ ታቦር → ወረታ → ፎገራ፤ ፲፰. ሐዋሳ ሰአሊተ ምሕረት ቅድስት ማርያምና ዮሐንስ ወልደ ነጐድጓድ፤ አድራሻ፤ ሐዋሳ ሃገረ ስብከት ፥ ሐዋሳ ከተማ፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ቃሊቲ አውቶቡስ ተራ → ሐዋሳ፡፡ ፲፱. ሆሳዕና ዮሐንስ ወልደ ነጐድጓድ፤ አድራሻ፤ ጉራጌ ሃገረ ስብከት፥ ሆሳዕና፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. አየር ጤና አውቶቡስ ተራ → ሆሳዕና፡፡ ፳. ማፌድ ጓረባ ጠብረሪ ደብረ ዕንቊ ቅድስት ልደታ ወዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ፤

#ታኅሣሥ 29 ልደታቸው ከጌታችን ልደት ጋር የተባበረላቸው ቅዱሳን፤ #አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ፤ #ቅዱስ ላሊበላ፤ #ቅዱስ ነዓኵቶ ለአብ፤ #አቡነ አብሳዲ ዘደብረ መጕና #ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ፤ #ቅዱሳን ነገሥታት አብርሃ ወአጽብሃ፤ #አቡነ አካለ ክርስቶስ፤ #አቡነ መዝራእተ ክርስቶስ፤ #መስፍኑ ኢያሱ፤ #የገርአልታው አቡነ ዳንኤል፤ #ዳግማዊ ቂርቆስ ዘቡልጋና ሌሎችም ቅዱሳን አሉ፤ ነገር ግን ከቅዱሳን በዓል በላይ የጌታ በዓል መከበር ስለሚገባው የቅዱሳኑ ዋና በዓላቸው በሌላ ቀናት /በዕረፍታቸው…../ ቀን ይታሳባል፡፡ በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሕትመት እና ሚዲያ ንዑስ ክፍል የተዘጋጀ ::/ #share .Facebook... https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool .YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w .Telegram... https://t.me/medihanaelem http://tiktok.com/@finotehiwot www.finotehiwotsundayschool.com #ጾም #አጽዋማት #fasting's #ክብረ_በዓላት #Feast_of_the_lord

✤✤ #እቲሣ_ገዳም ( የአቡነ ተክለሃይማኖት የልደት ሥፍራ ) እቲሳ ገዳም (ዞረሬ /ጽላልሽ/ /ምስካየ ኅዙናን/፡፡ ክርስትናን በመላዋ ኢትዮጵያና እስከ ጎረቤት ሀገሮች መዳረሻ ድረስ በስፋት የሰበኩ ፥ ገዳማትና አድባራት የተከሉ ፤ ከዋክብት ሰማይን በብርሃናቸው እንደሚያደምቁት ፥ እንዳስጌጡት ሁሉ፤ በጽድቃቸው፥ በትሩፋታቸው ለቤተ ክርስቲያን ፋና የሆኑ፤ የ99 ቅዱሳን፥ የ566 መናንያን ቅዱሳን መፍለቂያ፤ 17 የጥንት ዋሻዎች፣ 31 አዳዲስ ዋሻዎች የሚገኙበት ነው እቲሳ ገዳምና ዙሪያው፡፡ ገዳሙ ከአዲስ አበባ ከተማ በቅርብ ርቀት በደሴ በር (በደብር ብርሃን መስመር) በ38 ኪ.ሜ ላይ ፤ ከአሌልቱ በስተቀኝ በመታጠፍ ….. ይገኛል፡፡ ✤✤ #ይህ_ታላቅ_ገዳም #በቅዱሳን ነገሥታት አብርሃ ወአጽብሃና አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን የተመሠረተ፤ ሲመሠረትም በታቦተ ኢየሱስና አርባዕቱ እንስሳ ነው፤ #ሊቀ ካህናት አበይድላ ከአኵስም 300 ታቦታትና 300ካህናት ይዞ መጥቶ በጽላልሽ የተቀመጠባት ናት፤ #ፀሐይ አቡነ ተክለሃይማኖት የተወለዱባት (የተወለዱባት ጠፍጣፋ ደንጊያ አሁንም በቦታው አለች)፣ #አባታቸውና ጸጋ ዘአብና እናታቸው እግዚእኀረያ የተወለዱበት፤ ኋላም ክብሩ አጽማቸው ያረፈበት ነው፡፡ #ቅዱስ ያሬድ 3 ዓመት ጸልዮባታል፤ #ቅዱስ ላሊበላ 7 ዓመት ጸልዮባታል፤ #ተሰዓቱ ቅዱሳን 20 ዓመት የጸለዩበት፤ #ሐርቤ በሚባለው ቦታ ላይ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ 7 ዓመት ጸልየውበታል፤ #ታቦተ ጽዮን 12 ዓመት (ከ9ሺህ ሕዝብ) ጋር መጥታ ኖራበታለች፤ #በአምሳለ ሲዖል የተሠራ አስደናቂ የጨለማ ዋሻ ያለበት ነው፤ #ብዙ የታሪክ ቅርስ ያለበት ነው፤ #በቅዱስ ሚካኤልና ጸጋ ዘአብ ቤተ ክርቲያን ውስጥ ካየን በኋላ፤ እዚሁ ቦታ በሚገኘው ፈዋሽ ጠበል ተጠምቀንና ጠጥተን ጕዟችንን ወደ ቦታው ከአ.አ በቅርብ ርቀት በደብረ ብርሃን መንገድ አሌልቱ ከተማ ላይ በመታጠፍ ይገኛል፡፡ #ሥርዐተ_ማኅሌቱን እንደየደብራችሁ ይትበሃል እንድትጠቀሙበት (በላይ ቤትና በታች ቤት) (#ዘአባጃሌ_ተክለ_ሃይማኖትና_ዘአደባባይ_ተክለሃይማኖት) አዘጋጅተነዋል፡፡ ጸሎትና በረከታቸው፤ ረድኤትና ምልጃቸው በመላው ሕዝበ ክርስቲያንና በቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች ሁሉ አድሮ ይኑር ለዘለዓለሙ አሜን፡፡ /በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሕትመት እና ሚዲያ ንዑስ ክፍል የተዘጋጀ ::/ #share .Facebook... https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool .YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w .Telegram... https://t.me/medihanaelem http://tiktok.com/@finotehiwot www.finotehiwotsundayschool.com #ኢትዮጵያውያን_ቅዱሳን

#ከኢትዮጵያ_ውጭ_የሚከበርባቸው_ #፲፯ #ገጥንታውያን_ገዳማትና_አድባራት፡፡ ፩. ኢየሩሳሌም ምስካበ ቅዱሳን ተክለ ሃይማኖት ገዳም (ኢየሩሳሌም፤ በአላዓዛር) ፪. ቨርጂኒያ ምሥራቀ ፀሐይ ተክለ ሃይማኖት (አሜሪካ) ፫. ብሪታንያ ሊቨርፑል መካነ ቅዱሳን ተክለ ሃይማኖት (እንግሊዝ) ፬. ስቶክሆልም ምዕራፈ ቅዱሳን ተክለ ሃይማኖት (ስዊዲን) ፭. ክላርክስተን ዳግማዊ ቁልቢ ደብረ ብሥራት ገብርኤልና ተክለ ሃይማኖት ፮. ግብጽ እስክንድርያ ተክለ ሃይማኖት፤ ፯. ግብጽ እስክንድርያ አል አጋሚ ተክለ ሃይማኖት፤ ፰. ግብጽ እስሙናይ (እል መኖፊያ) ተክለ ሃይማኖት፤ ፱. ግብጽ ኤል ዛግዚክ ተክለ ሃይማኖት፤ ፲. ግብጽ ኤል ሙሐራቅ አስዩት ተክለ ሃይማኖት፤ ፲፩. ኬንያ ማሴኖ ተክለ ሃይማኖት (የግብጽ) ፲፪. ሎስ አንጀለስ ተክለ ሃይማኖት (የግብጽ) ፲፫. ኦታዋ ኦንታሪዮ ተክለ ሃይማኖት (የግብጽ) ፲፬. ብራምፕተን ኦንታርዮ ተክለ ሃይማኖት (የግብጽ) ፲፭. ፐርዝ አውስትራልያ ተክለ ሃይማኖት (የግብጽ) ፲፮. ሲድኒ አውስትራልያ ዳርዊን ተክለ ሃይማኖት ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ /በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሕትመት እና ሚዲያ ንዑስ ክፍል የተዘጋጀ ::/ #share .Facebook... https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool .YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w .Telegram... https://t.me/medihanaelem http://tiktok.com/@finotehiwot www.finotehiwotsundayschool.com

፶፫. አምስትያ ተክለ ሃይማኖት ገዳም፤ (ደቡብ ጎንደር፥ እብናት) ፶፬. አጣ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ጠበል (ደቡብ ጎንደር፥ ፋርጣ፥ ጋሳይ ከተማ (ከደ/ታቦር ከተማ በ18ኪሜ ርቀት) አካባቢ የሚገኘው ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ

#በሃገራችን_በኢትዮጵያና_በዓለም_አቀፍ_ደረጃ_የሚከበርባቸው_ #፶፬ #ገጥንታውያን_ገዳማትና_አድባራት፡፡ (፩-፫) ✣፫ቱ ደብረ ሊባኖሶች፥ ፪ቱ በእጨጌዎች የሚመሩ ፩. ደብረ ሊባኖስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ገዳም፤ (የበርካታ ቅዱሳን መፍለቂያና አጽማቸው በክብር ያረፈበት) አድራሻ፤ ሰሜን ሸዋ ሰላሌ ሀገረ ስብከት፥ ደብረ ሊባኖስ ትራንስፖርት፤ ከአዲስ አበባ መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ደብረ ሊባኖስ (ገዳም) የሚል ትራንስፖርት ያገኛሉ፡፡ ወይም ከአዲስ አበባ መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ፍቼ(ባህር ዳር) በሚሄድ ትራንስፖርት  ደብረ ጽጌን እንዳለፉ ጫገል የምትባል መንደር ላይ ወርደው በታክሲ(በባጃጃ) (በእግር) በመጓዝ ያገኙታል፡፡ ፪. ጎንደር፥ አዘዞ ደብረ ሊባኖስ፤ የኢትዮጵያ ርዕሰ መዲና ከ300 ዓመታት በላይ ጎንደር ላይ በነበረበት ወቅት ዳግማዊት ደብረ ሊባኖስ ሆኖ በእጨጌ እየተመራ የቆየ ታላቅ ገዳም፡፡ አድራሻ፤ ማዕከላዊ ጎንደር ሀገረ ስብከት፥ ጎንደር ከተማ፥ አዘዞ፡፡ ትራንስፖርት፤ ከአዲስ አበባ (ባሕር ዳር) → በጎንደር መስመር → ጎንደር ከተማ ሊገቡ ሲሉ አዘዞ ከተማ መግቢያ ላይ  ወደ ደንቢያ፥ ቆላ ድባ መታጠፊያ ላይ ያኙታል፡ ፫. ኤርትራ ሺምዛና ደብረ ሊባኖስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ገዳም፡፡ አድራሻ፤ ኤርትራ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ቦሌ አየር ማረፊያ → ኤርትራ → ሺምዛና፡፡ ፭. ኮራ ተክለ ሃይማኖት፤ (ጻድቁ የጸለዩበት) አድራሻ፤ ሰሜን ሸዋ ሰላሌ ሀገረ ስብከት፥ ሰላሌ፡፡ ትራንስፖርት፤ ከደብረ ሊባኖስ ገዳም ወደ ቆላው በእግር በመሄድ ያገኙታል፡፡ ፮. ወይንጌ(ዬ) ተክለ ሃይማኖት፤ አድራሻ፤ ሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት፥ ደብረ ብርሃን፡፡ ትራንስፖርት፤ ከጉርድ ሾላ መናኸሪያ → ደብረ ብርሃን ከተማ → በባጃጅ (በእግር) በመጓዝ ያገኙታል፡፡ ፯. አጆራ ተክለ ሃይማኖት፤ (አቡነ ተክለ ሃይማኖት በኢትዮጵያ በባለ መንታ ፏራቴነት ብቸኛ በሆነው አጆራ ላይ ከእጨጌ ዮሐንስና ከሌሎችም ደቀ መዛሙርቶቻቸው ጋር መቶሎሚ በቀፎ አድርጎ የወረወረበት፥ ሊቀ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ያዳናቸው ቦታ፡፡ ታሪክን ታሪክ ደግሞት 3ኛው የኢትዮጵያ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት በቦታው ላይ ሱባኤ በመግባት በግራኝ መሐመድ ጊዜ ጠፍ ሆኖ የነበረውን ቤተ ክርስቲያንና ንዋያተ ቅድሳት ያገኙበት) አድራሻ፤ ደቡብ፥ ሌሾ፥ አጆራ፡፡ ትራንስፖርት፤ ከአዲስ አበባ አየር ጤና መናኸሪያ → ደቡብ (ሌሾ፥ አጆራ) ፰. ደብረ ገሪዛን (ገርዜን) ጕንዳጕንዶ ማርያም፤ (የአቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤ/ክ ለብቻው አለ) አድራሻ፤ ትግራይ ሀገረ ስብከት ፥ አዲግራት ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. → አዲግራት → በእዳጋ ሐሙስ መስመር → ወደ አሲምባ የሚወሰደውን መንገድ በመተው ወደ ጕንዳጕንዶ በመሄድ ያገኙታል፡፡ ፱. አንጋራ ተክለ ሃይማኖት፤ (ከጣና ገዳማት አንዱ) አድራሻ፤ ማዕከላዊ ጎንደር ሀገረ ስብከት፥ ጣና ደሴት ትራንስፖርት፤ ከአ. መርካቶ መናኸሪያ → ጎንደር → ጎርጎራ (ወይም ከባሕር ዳር) → አንጋራ (በደንገል (በመርከብ /በጀልባ/) በመጓዝ ያገኙታል፤ ፲. አባ ጃሌ ተክለ ሃይማኖት፤ (ከ44ቱ ታቦታተ ጎንደር አንዱ) አድራሻ፤ ማዕከላዊ ጎንደር ሀገረ ስብከት፥ ጎንደር ከተማ ትራንስፖርት፤ ከአ. መርካቶ መናኸሪያ → ጎንደር → ፒያሳ ፲፩. አደባባይ ተክለ ሃይማኖት፤ (ከ44ቱ ታቦታተ ጎንደር አንዱ) አድራሻ፤ ማዕከላዊ ጎንደር ሀገረ ስብከት፥ ጎንደር ከተማ ትራንስፖርት፤ ከአ. መርካቶ መናኸሪያ → ጎንደር → አራዳ በሚል ታክሲ ፲፪. መቀለ ተክለ ሃይማኖት፤ አድራሻ፤ ትግራይ ሀገረ ስብከት፥ መቀለ ትራንስፖርት፤ ከአ. ጉርድ ሾላ መናኸሪያ → መቀለ ፲፫. ግሸና ተክለ ሃይማኖት፤ አድራሻ፤ ደቡብ ጎንደር ሀገረ ስብከት፥ ግሸና ትራንስፖርት፤ ከጎንደር → ደቡብ ጎንደር (ደብረ ታቦር) → ግሸና ተክለ ሃይማኖት፡፡ ፲፬. ሚጣቅ ተክለ ሃይማኖት ገዳም፤ አድራሻ፤ ሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት፥ አንኮበር፥ ሚጣቅ፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ መናኸርያ → ደብረ ብርሃን ፥ በአንኮበር መስመር ሚጣቅ፡፡ ፲፭. ጎንድ ተክለ ሃይማኖት ገዳም፤ አድራሻ፤ ማዕከላዊ ጎንደር ሀገረ ስብከት፥ ጎንድ፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. መርካቶ መናኸርያ → በጎንደር መስመር ማክሰኚት → ጎንድ፡፡ ፲፮. ደብረ ድማኅ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ገዳም፤ (በ352 ዓ.ም. በአቡነ ሰላም ከሣቴ ብርሃን በታቦተ መድኃኔዓለምና ማርያም የተመሠረተ) አድራሻ፤ ደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት፥ ደላንታ፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ መናኸርያ → ደሴ /ደላንታ/፡፡ ፲፯. ወላይታ ሶዶ ደብረ መንክራት አቡነ ተክለ ሃይማኖት ገዳም፤ አቡነ ተክለ ሃይማኖት 12 ዓመት ቆመው የጸለዩበት፤ ከሞተሎሜ ቤተ መንግሥት ዳሞት ተራራ ግርጌ የሚገኝ፤ የሀገረ ስብከቱ መንበረ ጵጵስና ያለበት፡፡ አድራሻ፤ ወላይታ ሀገረ ስብከት፥ ወላይታ ከተማ፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. አየር ጤና መናኸርያ → ወላይታ፡፡ ፲፰. አኵስም ተክለ ሃይማኖት፤ (ከደብረ ጽዮን አኵስም አጥር ለአጥር የተያያዘ ቤ/ን) አቡነ ተክለ ሃይማኖት ከጸለዩበት የአኵስም ጽዮን ቤ/ን አጠገብ የተሠራ፡፡ አድራሻ፤ አኵሰም ሀገረ ስብከት፥ አኵስም ከተማ፥ ጽዮን፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. → አኵስም፡፡ ፲፱. ጣራ ዋሻ ተክለ ሃይማኖት፤ አድራሻ፤ ማዕከላዋ ጎንደር ሀገረ ስብከት፥ ጣራ ገዳም፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. መርካቶ መናኸሪያ → በጎንድር መስመር (ጣራ ገዳም)፡፡ ፳. ጥዑመ ግራራ አጆራ ተክለ ሃይማኖት፤ (አቡነ ተክለ ሃይማኖት ከእጨጌ ዮሐንስ ጋራ ሆነው በሞተለሜ ትእዛዝ በአጆራ ባለ 2ት ፏፏቴ በንብ ቀፎ የተወረወሩበትና ቅዱስ ሚካኤል ያዳናቸው) አድራሻ፤ ወላይታ ሶዶ ሀገረ ስብከት፥ ጣራ ገዳም፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. አየር ጤና መናኸሪያ → ወላይታ /አጆራ/ → ጥዑመ ግራርያ፡፡ ፳፩. መርጠሉ ማርያም ደብረ ቢታንያ ተክለ ሃይማኖት (ደቡብ ወሎ፤ ንጉሥ አብርሃና አጽብሃ ከአባ ሰላማ ጋር በ333 ዓ.ም. የመርጡለ ማርያምን ገዳም ሲገድሙ ሱባኤ ከያዙባቸው አንዷ ተራራ) ፳፪. ቈየፃ ተክለ ሃይማኖት ፳፫. አንኮበር ተክለ ሃይማኖት (ሰሜን ሸዋ) ፳፬. ወግዲ ተክለ ሃይማኖት (ሰሜን ሸዋ) ፳፭. መንዝ ኮረብቲት ተክለሃይማኖት (ሰሜን ሸዋ) ፳፮. ራዛ ተክለ ሃይማኖት (ትግራይ) ፳፯. እምባይቶ ተክለ ሃይማኖት (ትግራይ) ፳፰. አራሮ ተክለ ሃይማኖት (ትግራይ) ፳፱. አፈር ባይኔ ተክለ ሃይማኖት ፴. ደጋ ዳሞት ተክለ ሃይማኖት (ምዕራብ ጎጃም) ፴፩. ባሕር ዳር ተክለ ሃይማኖት (ምዕተራብ ጎጃም፥ ባሕር ዳር ከተማ) ፴፪. ሰነቦ ተክለ ሃይማኖት (ምዕራብ ጎጃም) ፴፫. ቆላድባ ተክለ ሃይማኖት (ጎንደር፥ ደምቢያ፥ ቆላድባ) ፴፬. ደብረ ታቦር አንቀጸ አድኅኖ ዑራኤል ወተክለ ሃይማኖት (ደቡብ ጎንደር ) ፴፭. ሽና ተክለ ሃይማኖት ፴፮. ጉባ ላፍቶ ተክለ ሃይማኖት (ወሎ) ፴፯. ደሴ አቡነ ተክለ ሃይማኖት (ሰሜን ወሎ፥ ደሴ) ፴፰. ዳቦት ተክለ ሃይማኖት ፴፱. የጁ ከረዩ ተክለ ሃይማኖት ፵. ጃናሞሬ ተክለ ሃይማኖት ፵፩. ገሬኖ ተክለ ሃይማኖት ፵፪. ቃሊቲ ገላን ጎሮ ተክለ ሃይማኖትና ኪሮስ ፵፫. ደብረ ዘይት (ቢፍቱ) ተክለ ሃይማኖት ፵፬. ሻሸመኔ ተክለ ሃይማኖት ፵፭. ሐዋሳ ተክለ ሃይማኖት ፵፮. ወንጂ ደብረ ፀሐይ ተክለ ሃይማኖት ፵፯. ሆሳዕና ደብረ ፀሐይ ተክለ ሃይማኖት ፵፰. አርባ ምንጭ ተክለ ሃይማኖት ፵፱. ሐረር ተክለሃይማኖት ፶. ጅግጅጋ ተክለ ሃይማኖት ፶፩. ባሌ ጎባ ደበረ ሰላም ተክለ ሃይማኖት ገዳም ፶፪. ወጠቅ ደብረ አሚን ተክለ ሃይማኖት፤

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት - Telegram kanali @finotehiwott statistikasi va tahlili