uz
Feedback

Firibgarlarga uchmang! Telemetrio bunday kanallarni topadi va belgilaydi 👉 Belgini ko‘rmoqchi bo‘lsangiz, obuna bo‘ling

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Kanalga Telegram’da o‘tish

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Ko'proq ko'rsatish

📈 Telegram kanali Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት analitikasi

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) Amxar til segmentidagi kanali faol ishtirokchi. Hozirda hamjamiyat 16 042 obunachidan iborat bo'lib, Din & Maʼnaviyat toifasida 5 281-o'rinni va Efiopiya mintaqasida 2 239-o'rinni egallagan.

📊 Auditoriya ko‘rsatkichlari va dinamika

невідомо sanasidan buyon loyiha tez o‘sib, 16 042 obunachiga ega bo‘ldi.

28 Oktabr, 2026 dagi oxirgi ma’lumotlarga ko‘ra kanal barqaror faollikka ega. Oxirgi 30 kunda obunachilar soni 512 ga, so‘nggi 24 soatda esa -6 ga o‘zgardi va umumiy qamrov yuqori darajada qolmoqda.

  • Tasdiqlash holati: Tasdiqlanmagan
  • Jalb etish (ER): Auditoriya o‘rtacha 25.18% darajada jalb etiladi. Nashrdan keyingi dastlabki 24 soatda kontent odatda umumiy obunachilar sonining 10.37% ini tashkil etuvchi reaksiyalarni to‘playdi.
  • Post qamrovi: Har bir post o‘rtacha 4 039 marta ko‘riladi; birinchi sutkada odatda 1 663 ta ko‘rish yig‘iladi.
  • Reaksiyalar va o‘zaro ta’sir: Auditoriya faol: har bir postga o‘rtacha 30 ta reaksiya keladi.

📝 Tavsif va kontent siyosati

Muallif resursni shaxsiy fikrni ifoda etish maydoni sifatida ta’riflaydi:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”

Yuqori yangilanish chastotasi (oxirgi ma’lumot 29 Oktabr, 2026 da olingan) sababli kanal doimo dolzarb va katta qamrovli bo‘lib qoladi. Analitika auditoriya kontent bilan faol hamkorlik qilishini, uni Din & Maʼnaviyat toifasidagi muhim ta’sir nuqtasiga aylantirishini ko‘rsatadi.

16 042
Obunachilar
-624 soatlar
+917 kun
+51230 kun
Postlar arxiv
በአዲስ አበባ በዋነኛነት የመስከረም 21 (የብዙኃን ማርያም) ክብረ በዓል የሚከበርባት፤ ግማደ መስቀሉ ለተወሰኑ ጊዜያት ያረፈበት፥ ለጥቂት ዓመታት የሃገራችን ኢትዮጵያ ርዕሰ መዲና የሆነችው፤ ርዕሰ
+1
በአዲስ አበባ በዋነኛነት የመስከረም 21 (የብዙኃን ማርያም) ክብረ በዓል የሚከበርባት፤ ግማደ መስቀሉ ለተወሰኑ ጊዜያት ያረፈበት፥ ለጥቂት ዓመታት የሃገራችን ኢትዮጵያ ርዕሰ መዲና የሆነችው፤ ርዕሰ አድባራት መንበረ ፀሐይ እንጦጦ ማርያም፡፡ ሌሊቱን በማኅሌት አሸብርቃ አድራለች፤ በእንጦጦ ብቻ ከሚወረቡ ወረቦች መካከልም፤ እትአመን ባቲ እስመ አርአያ መስቀል ይእቲ፤(፪) አክሊለ ተቀጺላ ታንሶሱ፡፡(፪) የሚለውን ወረብ ልቡናን በሚመሰጥ አወራረብ ሲወረብ አድሯል፡፡ የአዲስ አበባና የሱሉልታ ምዕመን በቤቱ አለ ወይ? በሰፈሩስ ቀርቷል ወይ በሚያስብል ሁኔታ ሁሉም ወደ እንጦጦ በእግር በመኪና በፈረስ ሳይቀር ይተምማል? /መልካም በዓል/

#ዛሬ_በአሁኑ_ሰዐት_ክብረ_በዓሉ_በግሸን_ደብረ_ከርቤ_ይህን_ይመስላል፡፡ በክብረ በዓሉም ላይ ከ3 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ይገኛል ተብሎ ይገመታል፡፡ ፠ በዐውደ ምሕረቱ ላይም የግሸን ደብረ ከርቤና ከኢት
+6
#ዛሬ_በአሁኑ_ሰዐት_ክብረ_በዓሉ_በግሸን_ደብረ_ከርቤ_ይህን_ይመስላል፡፡ በክብረ በዓሉም ላይ ከ3 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ይገኛል ተብሎ ይገመታል፡፡ ፠ በዐውደ ምሕረቱ ላይም የግሸን ደብረ ከርቤና ከኢትዮጵያና ከመላው ዓለማት የተውጣጡ ሊቃውንት ከዚህ በታች ያሉውን ወረብ እየወረቡ ገኛሉ፡፡ ሃሌ ሃሌ ሉያ፤ (፪) ወረከበ ደብረ ከርቤ ዕፀ መስቀሉ ለክርስቶስ፡፡(፪) ትርጕም፤ እውነት በእውነት የክርስቶስ ዕፀ መስቀሉ በደብረ ከርቤ ተቀመጠ፡፡ ፠ ቀጥለውም ከጌታችን ዕፀ መስቀል ጋር አብረው በግሸን በክብር ከተቀመጡት ንዋያተ ቅድሳት መካከል አይሁድለ ለጌታችን ያለበሱትን ከለሜዳ (ቀይ ግምጃ ልብስ) ወጥቶ ሕዝቡን እየባረከ ይገኛል፡፡ ሊቃውንቱም ለዚሁ ተስማሚ የሆነውን ከዚህ በታች ያለውን ወረብ እየዘመሩ ይገኛሉ፡፡ ዘአልበስዎ አይሁድ ከሌሜዳ ዘለይ፤ (፪) ከለሜዳ ዘለይ፡፡ (፫) ትርጕም፤ አይሁድ ከሌማዳና ዘለይ /ለመድኀኔዓለም ክርስቶስ/ አለበሱት፡፡ ፠ የሰንበት ትምህርት ቤት አባላትም የሚከተለውን ወረብ እየወረቡ ይገኛል፤ አይ ይእቲ ዛቲ ደብረ ከርቤ መድኀኒት እንተ ኀሠሥዋ ወዖድዋ ነቢያት፤ (፪) እትአመን ባቲ (፪) እስመ አርአያ መስቀል ይእቲ፡፡ (፪) ****ትመስል ኢየሩሳሌም በአርአያ ልዑል ፤ ደብረ ከርቤ ግሸን ማርያም፡፡ ፠፠ አሁን ደግሞ ጸሎተ ምሕላ እየደረሰ ነው ቀጥሎ ትምህርት ይኖራል፡፡ ፎቶዎቹ፤ አይሁድ መድኀኔ ዓለም ክርስቶስን ያለበሱት ከሌዳ ዘለይ የሚባለው ቀይ ግምጃ ልብስ፤ በክብረ በዓሉ ከተገኙ ሕዝቦች በጨረፍታና፤ ሊቃውንቱና ሰ/ት/ቤት ተማሪዎች ወረብ ሲያቀርቡ፡፡

✤እንኳን ለመስከረም 21፤ #ብዙኃን_ሊቃውንት_ሌሰበሰቡበት_ብዙኃን_ማርያም_፤ #ክቡር_መስቀሉና_ሌሎችም_ንዋያተ_ቅድሳት-በግሸን_ደብረ_ከርቤ_አምባ_ላይ_በክብር_ላረፉበት_ዕለት፤( …….ዝረዝርሩን በስተመጨረሻ ይመልከቱ)፤ #ለቅዱስ_ቆጵርያኖስ_(ኃይለኛ ሥራየኛ ጠንቋይ የነበረውና በኋላም አምኖ ለክርስቶስ ምስክር ሆኖ አንገቱን የተሰየፈው )ና ፡ ቆጵርያኖስን ያሳመነችውና ስሟ በተጠራበት ቦታ ሰይጣናት እንደ ትቢያ በነው የጠፉት ታላቋ ቅድስት ድንግሊቱ ዮስቴና በሰማዕትነት ላረፉበት ዕለት፤ #ሃይማኖታቸው_ለቀና_ለ318ቱ_አበው_ሊቃውንት (#በ325 ዓ.ም #አርዮስን_አስተምረው_ለመመለስ_በኒቅያ_የተሰበሰቡባት_ዕለት )፣ /የጉባኤውም ፍጻሜ ኅዳር ዘጠኝ ነው/ እንዲሁም #ከ72ቱ_አርድእት_አንዱ_ለሆነው_ለሐዋርያው_ቅዱስ_ጢባርዮስ_ዕረፍት በሰላምና በጤና አምላከ አበው መድኀኔዓለም አደረሳችሁ አደረሰን፡፡ ፠፠፠ #ብዙኃን_ማርያም፤ /ከቀ.ደ.ሰ መድኀኔ ዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት ሰሌዳ መጽሔት ባጭሩ የተወሰደ፡፡/ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም በዓሏ መስከረም ፳፩ ቀን መከበሩ ስለ ሁለት ነገር ነው፡፡ ፠1ኛ) አንዱ ጉባኤ ኒቅያን ይመለከታል፤ ለ፲፰ኛው የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳስ ለተፍጻሜተ ሰማዕት ቅዱስ ጴጥሮስ ካሉት ደቀ መዛሙርት መካከል አርዮስ፣ አኪላስና እለእስክንድሮስ የሚባሉት ዋነኞቹ ነበሩ፡፡ አርዮስ እውቀቱ በመምህሩ የተመሠከረለት ሊቅ ነበር፡፡ ነገር ግን “እጅግ ጥበብ ያደርሳል ከሞት” እንዳለ ሰሎሞን የተጻፈውን ትቶ ባልተጻፈው ላይ ፍልስፍና ጀመረ፡፡ በምሳ. ፰÷፳፪ ላይ ያለውን ቃል በተሳሳተ መንገድ ፈታው፤ ነገር ግን ተፍጻሜተ ሰማዕት ቅዱስ ጴጥሮስ ጠርቶ ቢመክረው ቢገስጸው እንቢ በማለት የክህደት ትምህርቱን ቢቀጥልበት ከሹመቱ አውርዶ አወገዘው፡፡ ተፈጻሜተ ሰማዕት ከደቀመዛሙርቱ መካከል አኪላስን ተክቶ ኅዳር ፲፱ ቀን በሰማዕትነት አረፈ፡፡ አኪላስም የጓደኝነት ፍቅር አድልቶበት አርዮስን ከውግዘት ቢፈታው በመቅሠፍት ሞት ሞተ፡፡ በመንበሩም እለእስክንድሮስ ተተካ፡፡ በዚህ ጊዜ የአርዮስ የክህደት ትምህርት በሀገሪቱ ሞላ፡፡ ይህ ነገርም እየተባባሰ በመሔዱ በንጉሥ ቈስጠንጢኖስ ዘንድ ተሰማ፡፡ ንጉስ ቈስጠንጢኖስም ይህን ሲሰማ ለአርዮስ ጥያቄ መልስ ይሠጥበት ዘንድ የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ጕባኤ እንዲደረግ ሰኔ ፳፩ ቀን አዋጅ አስነገረ፡፡ ይህንን አዋጅ የሰሙት ሊቃውንት ሁሉ መስከረም ፳፩ ቀን የእመቤታችን እለት ተሰባሰቡ፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ “ለምን ቈስጠንጢኖስ መልዕክት ከላከበት ጊዜ በኋላ ወዲያውኑ ለምን አልመጡም? ለምን ዘገዩ?” የሚለው ጥያቄ ይነሳል፡፡ ምክንያቱም፤ *አንደኛ መጓጓዣ ችግር ስለነበር፤ *ሁለተኛ ሁሉም ሊቃውንት አስተማሪዎች በመሆናቸው ለምዕመናኑ (ለተማሪዎቻው) ሌላ መምህር ማዘጋጀት ስለነበረባቸው፤ *ሦስተኛ ደግሞ በእድሜ የገፉ ስለነበሩ አንድም ሊቃውንቱ ሲያስተምሩ በአላውያን ነገሥታት ባላመኑ ሰዎች ግፍ ይድርስባቸው ስለነበር ነው፡፡ ለምሳሌ ቶማስ ዘመርዓስ በእነዚህ ሰዎች በግፍ እግሩና እጁ ተቆርጦ ስለነበር ለማስተማር በቅርጫት ይዘውት ነበር የሚጓዘው፡፡ ወደ ጕባኤውም ሲመጣ ደቀ መዛውርቱ ያመጡት በቅርጫት ይዘውት ነበር፡፡ ከዚህ በኋላ 2,340 ሊቃውንት መስከረም ፳፩ ቀን ተሠባሰቡ፡፡ ከእነዚህ መካከል ግን 318ቱ ሊቃውንት ‹‹ዘእሩይ ምስለ አብ በመለኮቱ ›› በማለት በሃይማኖታቸው የጸኑ ነበሩ፡፡ ጉባኤውን ከመጀመራቸው በፊት አርባ (፵) ቀን ሱባኤ እስከ ኅዳር ዘጠኝ (፱) ቀን ይዘውና ጕባኤውን አድርገው በአንዲት ቀን ያንን ታላቅ መናፍቅ አርዮስን ድል ነሥተውታል፡፡ ከዚህ ጋር አያይዘውም የኃይማኖታችን መሠረት የሆነውን ጸሎተ ሃይማኖትን አዘጋጅተዋል፡፡ #ብዙኃን_ማርያም_የተባለበት_ምክንያት_ብዙኃን_ሊቃውንት_የተገኙበት_እለት_በመሆኑ_ነው፡፡ ፠፠ 2ኛ) መስከረም ፳፩ የምናከብርበት ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ መስቀልን አስመልክቶ ነው፡፡ መስቀሉ በመስቀልኛ ቦታ በግሸን ደብረ ከርቤ በክብር ያረፈበት ዕለት ነው፡፡ ለዚህም በቂ ማብራሪያ በመስከረም 17 (የመስቀል ክብረ በዓለት የሚለውን ገጽ ይመለከቱ)፡፡ ከበዓሉ ረድኤት በረከት ይክፈለን እመቤታችን ጣዕሟን ፍቅሯን ታሳድርብን አሜን፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር (በሁሉም የእመቤታችን አብያተ ክርስቲያናት በላይ ቤትና በታች ቤት ይትበሃል የሚቆመውን ሥርዐተ ማኅሌቱን አቅርበንላችኋል፡፡ ላልደረሰው በ Facebook, twitter, instagram, telegram, Email, Viber, Xender, whatsup, imo, Bluetooth, ….. በማድረስ ይተባበሩ፡፡) መልካም ማኅሌት፡፡ የቤ/ኑ ፎቶዎቹ፤ ግማደ መስቀሉ ካረፈባቸው ቅዱሳን መካናት የ3ቱ (የመናገሻ አምባ ማርያም፣ የእንጦጦ ማርያምና የግሸን ማርያም) ናቸው፡፡

#ፎቶ_ክምችት_11፤ የደመራ በዓል በአፍሪካ (በኡጋንዳ፣ በግብጽ)፣ በኢየሩሳሌም፣ በዱባይ፡፡
+5
#ፎቶ_ክምችት_11፤ የደመራ በዓል በአፍሪካ (በኡጋንዳ፣ በግብጽ)፣ በኢየሩሳሌም፣ በዱባይ፡፡

#ፎቶ_ክምችት_10፤ የደመራ በዓል በምሥራቃዊት ኢትዮጵያ፤ መቄት፣ ራያ፣ ሰቆጣ፣ ከሚሴ፣ ከምቦልቻ፣ ወልድያ፣ ባቲ፣ ደሴ፡፡ እና በሰሜን ሸዋ (ጅሩ)
+9
#ፎቶ_ክምችት_10፤ የደመራ በዓል በምሥራቃዊት ኢትዮጵያ፤ መቄት፣ ራያ፣ ሰቆጣ፣ ከሚሴ፣ ከምቦልቻ፣ ወልድያ፣ ባቲ፣ ደሴ፡፡ እና በሰሜን ሸዋ (ጅሩ)

#ፎቶ_ክምችት_9፤ የደመራ በዓል በምዕራባዊት ኢትዮጵያ፤ አሶሳ፣ ወለንጪቲ፣ ወሊሶ፣ ጅማ፡፡
+3
#ፎቶ_ክምችት_9፤ የደመራ በዓል በምዕራባዊት ኢትዮጵያ፤ አሶሳ፣ ወለንጪቲ፣ ወሊሶ፣ ጅማ፡፡

#ፎቶ_ክምችት_8፤ የደመራ በዓል በደቡባዊት ኢትዮጵያ፤ ሆሳዕና፣ ሻሸመኔ፣ አርባ ምንጭ፣ ወላይታ፣ የም ደሪ ከተማ፣ ጂንካ፣ ዲላ፣ ደራሼ ጊዴሎ፡፡
+8
#ፎቶ_ክምችት_8፤ የደመራ በዓል በደቡባዊት ኢትዮጵያ፤ ሆሳዕና፣ ሻሸመኔ፣ አርባ ምንጭ፣ ወላይታ፣ የም ደሪ ከተማ፣ ጂንካ፣ ዲላ፣ ደራሼ ጊዴሎ፡፡

#ፎቶ_ክምችት_6፤ የደመራ በዓል በምሥራቅ ደቡባዊት ኢትዮጵያ፤ በድሬደዋና በሐረር፣ በቁልቢና በአሰበ ተፈሪ፡፡
+4
#ፎቶ_ክምችት_6፤ የደመራ በዓል በምሥራቅ ደቡባዊት ኢትዮጵያ፤ በድሬደዋና በሐረር፣ በቁልቢና በአሰበ ተፈሪ፡፡

#ፎቶ_ክምችት_6፤ የደመራ በዓል በማዕከላዊ ደቡባዊት ኢትዮጵያ፤ በናዝሬት /አዳማ/፣ አሰላና አርሲ፡፡
+6
#ፎቶ_ክምችት_6፤ የደመራ በዓል በማዕከላዊ ደቡባዊት ኢትዮጵያ፤ በናዝሬት /አዳማ/፣ አሰላና አርሲ፡፡

#ፎቶ_ክምችት_5፤ የደመራ በዓል በማዕከላዊ ኢትዮጵያ፤ በአዲስ አበባ፤ ዕለቱን ርጥብ ዛፍ ተቈርጦ ደመራ በሚደመርበት በቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለም፡፡ (በአረጓዴ ቢጫ ቀይ አምፑል የሚታየው መስቀ
+8
#ፎቶ_ክምችት_5፤ የደመራ በዓል በማዕከላዊ ኢትዮጵያ፤ በአዲስ አበባ፤ ዕለቱን ርጥብ ዛፍ ተቈርጦ ደመራ በሚደመርበት በቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለም፡፡ (በአረጓዴ ቢጫ ቀይ አምፑል የሚታየው መስቀል በማዕጠንት እየታጠነ የሚንቀሳቀስ መስቀል ሲሆን፤ የመጨረሻው ፎቶ፤ ከምሽቱ 3፡19 ደቂቃ ላይ ደመራው ወደ ደወል ቤቱ /በቀድሞ የደጀ ሰላም በር/ ሲወድቅ የሚያሳይ ነው፡፡)

#ፎቶ_ክምችት_4፤ የደመራ በዓል በማዕከላዊ ኢትዮጵያ፤ በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ::
+7
#ፎቶ_ክምችት_4፤ የደመራ በዓል በማዕከላዊ ኢትዮጵያ፤ በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ::

#ፎቶ_ክምችት_3፤ የደመራ በዓል በማዕከላዊ ኢትዮጵያ፤ በአዲስ አበባ ለመስቀል አደባባይ ተሰላፊዎች (የሰሜንና የደቡብ አዲስ አበባ ሰ/ት/ቤት ተማሪዎች፣ የማኅበረ ቅዱሳን ዘማሪያንና በገና ደርዳሪዎች
+7
#ፎቶ_ክምችት_3፤ የደመራ በዓል በማዕከላዊ ኢትዮጵያ፤ በአዲስ አበባ ለመስቀል አደባባይ ተሰላፊዎች (የሰሜንና የደቡብ አዲስ አበባ ሰ/ት/ቤት ተማሪዎች፣ የማኅበረ ቅዱሳን ዘማሪያንና በገና ደርዳሪዎች፤ እንዲሁም ነጋሪት ጐሳሚና መለከት ነፊዎች፤ በጕዞ ወቅት፡፡)

#ፎቶ_ክምችት_2፤ የደመራ በዓል በማዕከላዊ ኢትዮጵያ፤ በአዲስ አበባ በተለያዩ ቦታዎች (በ6 ኪሎ፣ በአፍንጮ በር አካባቢ፣ በሐመረ ኖኅ ኪዳነ ምሕረትና በአዲስ ከተማ መርካቶ)
+6
#ፎቶ_ክምችት_2፤ የደመራ በዓል በማዕከላዊ ኢትዮጵያ፤ በአዲስ አበባ በተለያዩ ቦታዎች (በ6 ኪሎ፣ በአፍንጮ በር አካባቢ፣ በሐመረ ኖኅ ኪዳነ ምሕረትና በአዲስ ከተማ መርካቶ)

በሃገራችን የደመራ ክብረ በዓል እንደየአካባቢው መስከረም 16 ለ17 ማታ ላይና በ17 ቀን ቀትር ላይ ይደመራል፡፡ ፠ ወደ ሰሜኑ ክፍል ያሉት በ17 ቀትር ላይ ዋናውን ሲደምሩ፤ በየቤታቸው ደግሞ ሌሊት
+8
በሃገራችን የደመራ ክብረ በዓል እንደየአካባቢው መስከረም 16 ለ17 ማታ ላይና በ17 ቀን ቀትር ላይ ይደመራል፡፡ ፠ ወደ ሰሜኑ ክፍል ያሉት በ17 ቀትር ላይ ዋናውን ሲደምሩ፤ በየቤታቸው ደግሞ ሌሊት ያበራሉ፡፡ (ለአብነትም ያህል፤ ጎንደር፣ ሞጣ፣ እስቴ መካነ ኢየሱስ፣ ገንዳ ውኃ፣ ደባርቅ፣ ደብረ ታቦር፣ ሰቆጣ ይጠቀሳሉ፡፡) ፠ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ (አዲስ አበባን ጨምሮ)፣ ምዕራብ፣ ምሥራቅና ደቡባዊት ኢትዮጵያ ደግሞ በ16 ለ17 አጥቢያ ምሽት ላይ ይደምራሉ፡፡ #ፎቶ_ክምችት_1፤ የደመራ በዓል በሰሜናዊት ኢትዮጵያ (በመቀለ፣ በጎንደር፣ በባሕር ዳርና በደብረ ማርቆስ)

መስከረም 18/2012 ዓ.ም. እንኳን ለአቡነ ኤዎስጣቴዎስ ከፋሌ ባሕርና ለአቡነ አኖሬዎስ ክብረ በዓል አደረሰን። +**ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን።*+ ፠፠፠ በደርቡሽ ተቃጥሎ ጠፍ ሁኖ የቆየው፥ ከ44
+5
መስከረም 18/2012 ዓ.ም. እንኳን ለአቡነ ኤዎስጣቴዎስ ከፋሌ ባሕርና ለአቡነ አኖሬዎስ ክብረ በዓል አደረሰን። +**ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን።*+ ፠፠፠ በደርቡሽ ተቃጥሎ ጠፍ ሁኖ የቆየው፥ ከ44ቱ ታቦታተ ጎንደር አንዱ የሆነውና ጽላቱ በደብረ ብርሃን ሥላሴ የቆየው የዳረገንዳ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ወደ ቀድሞ ርስቱ ቤተ ክርስቲያኑ ታንፆ ታቦተ ሕጉ ገብቶ ክብረ በዓሉ ተከብሮ ውሏል። ፠፠፠ እንዲሁም #የመስቀለ_ኢየሱስ_ቤተ_ክርስቲያን_(ትግራይ ከአዲግራት 80 ኪ.ሜ. ርቀት ላይ ኢሮብ ወረዳ አሲምባ ተራራ ላይ የሚገኝ) ቅዳሴ ቤቱ ተከብሯል፡፡ +**ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን።*+ /ከዋልድባ ዋሊ ገጽ የተወሰደ/

እንኳን ለአቡነ ኤዎስጣቴዎስ ከፋሌ ባሕርና ለአቡነ አኖሬዎስ ክብረ በዓል አደረሰን። +**ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን።*+ በደርቡሽ ተቃጥሎ ጠፍ ሁኖ የቆየው፥ ከ44ቱ ታቦታተ ጎንደር አንዱ የሆነውና ጽላቱ በደብረ ብርሃን ሥላሴ የቆየው የዳረገንዳ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ወደ ቀድሞ ርስቱ ቤ/ኑ ታንፆ ታቦተ ሕጉ ገብቶ ክብረ በዓሉ ተከብሮ ውሏል። +**ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን።*+ /ከዋልድባ ዋሊ ገጽ የተወሰደ/

***12ኛ ክፍልን በ2011 ዓ.ም. ላጠናቀቃችሁ አባላቶቻችንና ወጣት ምዕመናን በሙሉ፤ እሑድ መስከረም 18/2012 ዓ.ም. በ10 ሰዐት ከደብረ ነጎድግዋድ ቅዱስ ዮሐንስ ፍቁረ እግዚእ ሰ/ት/ቤት ጋራ በመተባበር የውይይት መርሐ ግብር ስለተዘጋጀ በሰዐቱ እንድትገኙ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን። ቦታ፤ በቅዱስ ዮሐንስ ቤ.ክ. አዳራሽ። እሑድ መስከረም 18/2012 ዓ.ም. በ10 ሰዐት

የመስከረም ፲፯ በዓለ አስተርእዮተ መስቀልን የት ሊያከብሩ አስበዋል????? አዲስ አበባ ላላችሁ በማኅሌት፣ በሰዐታት፣ በኪዳን፣ በቅዳሴ፣ በዑደተ ታቦተ ሕግ፣ በሰርክ ጕባኤ በአዲስ አበባ የሚከብርባቸ
+3
የመስከረም ፲፯ በዓለ አስተርእዮተ መስቀልን የት ሊያከብሩ አስበዋል????? አዲስ አበባ ላላችሁ በማኅሌት፣ በሰዐታት፣ በኪዳን፣ በቅዳሴ፣ በዑደተ ታቦተ ሕግ፣ በሰርክ ጕባኤ በአዲስ አበባ የሚከብርባቸውን ቦታዎች እንጠቁማችሁ፡፡ ፠ ቀጨኔ ደብረ ሰላም፤ ከንግሥት ዘውዲቱ ጀምሮ የመስቀል ክብረ በዓል የሚከበርበት፤ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ አገልጋይ ካህናቱ እንኳን ሳይቀር የመድኀኔ ዓለም አገልጋይና የመስቀል አገልጋይ ተብለው ምድብ የነበሩና፤ የመስቀል አገልጋዮች ደመወዝም ከቤተ ክሕነት የሚከፈልበት፡፡ ፠ ደብረ ዕንቊ ልደታ ለማርያም፤ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የመስቀል ክብረ በዓል ይከብራል፡፡ ፠ ደብረ ከዋክብት አቡነ አረጋዊና ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ፤ የመስቀል ክብረ በዓል ይከብራል፡፡