uz
Feedback

Firibgarlarga uchmang! Telemetrio bunday kanallarni topadi va belgilaydi 👉 Belgini ko‘rmoqchi bo‘lsangiz, obuna bo‘ling

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Kanalga Telegram’da o‘tish

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Ko'proq ko'rsatish

📈 Telegram kanali Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት analitikasi

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) Amxar til segmentidagi kanali faol ishtirokchi. Hozirda hamjamiyat 16 042 obunachidan iborat bo'lib, Din & Maʼnaviyat toifasida 5 281-o'rinni va Efiopiya mintaqasida 2 239-o'rinni egallagan.

📊 Auditoriya ko‘rsatkichlari va dinamika

невідомо sanasidan buyon loyiha tez o‘sib, 16 042 obunachiga ega bo‘ldi.

28 Oktabr, 2026 dagi oxirgi ma’lumotlarga ko‘ra kanal barqaror faollikka ega. Oxirgi 30 kunda obunachilar soni 512 ga, so‘nggi 24 soatda esa -6 ga o‘zgardi va umumiy qamrov yuqori darajada qolmoqda.

  • Tasdiqlash holati: Tasdiqlanmagan
  • Jalb etish (ER): Auditoriya o‘rtacha 25.18% darajada jalb etiladi. Nashrdan keyingi dastlabki 24 soatda kontent odatda umumiy obunachilar sonining 10.37% ini tashkil etuvchi reaksiyalarni to‘playdi.
  • Post qamrovi: Har bir post o‘rtacha 4 039 marta ko‘riladi; birinchi sutkada odatda 1 663 ta ko‘rish yig‘iladi.
  • Reaksiyalar va o‘zaro ta’sir: Auditoriya faol: har bir postga o‘rtacha 30 ta reaksiya keladi.

📝 Tavsif va kontent siyosati

Muallif resursni shaxsiy fikrni ifoda etish maydoni sifatida ta’riflaydi:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”

Yuqori yangilanish chastotasi (oxirgi ma’lumot 29 Oktabr, 2026 da olingan) sababli kanal doimo dolzarb va katta qamrovli bo‘lib qoladi. Analitika auditoriya kontent bilan faol hamkorlik qilishini, uni Din & Maʼnaviyat toifasidagi muhim ta’sir nuqtasiga aylantirishini ko‘rsatadi.

16 042
Obunachilar
-624 soatlar
+917 kun
+51230 kun
Postlar arxiv
የመስከረም ፲፮ የደመራ በዓል የምሥራቅ አ.አ ሰ/ት/ቤቶችና የማኅበረ ቅዱሳን የበገና የመሰንቆና የዝማሬ ተሰላፊዎች በከፊል ይህንን ይመስላሉ፡፡ በተለይ ውጭ ላላችሁ ባለን ካሜራና አቅም ይህችን ለመዘ
+9
የመስከረም ፲፮ የደመራ በዓል የምሥራቅ አ.አ ሰ/ት/ቤቶችና የማኅበረ ቅዱሳን የበገና የመሰንቆና የዝማሬ ተሰላፊዎች በከፊል ይህንን ይመስላሉ፡፡ በተለይ ውጭ ላላችሁ ባለን ካሜራና አቅም ይህችን ለመዘገብ ጥረት አድርገናል፤ ለወደፊቱ ግን የተደራጀ ነገር እንድንዘግብላችሁ የካሜራና የመቅርፀ ድምፅ ጉዳይን አስቡበት፡፡ /መልካም በዓል/

፠፠፠ #የመስቀል_ክብረ_በዓላት_ #መስከረም_16_የደመራ_በዓል_፤ #መስከረም_17_የመስቀል_በዓል_፤ #መስከረም_10_ተቀጸል_ጽጌ_፤ #መጋቢት_10_መስቀሉ_የተገኘበት_በዓል፤ #ደመራ_፤ ንግሥት እሌኒ በመስከረም 16 ደመራ አስደምራ እጣን አስጢሳ የመስቀሉን ቦታ ያወቀችበት ዕለት ነው፡፡ ጥንተ ታሪኩም፤ ክርስቶስ በሞተ ጊዜ የገነዙት ዮሴፍና ኒቆዲሞስ በጌታ መካነ መቃብር ጎልጎታ ወስደው አኑረውታል፡፡ አበው ሐዋርያት የኢየሩሳሌሙ ኤጲስ ቆጶስ ሐዋርያው ያዕቆብ በኃላፊነት እንዲጠብቀው አድርገው እነርሱም ከየአህጉረ ስብከታቸው ሲመለሱ በእግረ መስቀሉ ሥር እየተሰበሰቡ ይጸልዩ ነበር፡፡ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጠዋትና ማታ በጎልጎታ በመስቀሉ ሥር ትጸልይ ነበር፡፡ ብዙ ሰዎች ታሪኩንና ቦታውን በክርስቶስ ደም የተቀደሰውን ክቡር መስቀሉን ለማየት ያመኑትም በረከት ለማግኘት ከየአቅጣጫው ይመጡ ነበር፡፡ በመስቀሉ ተአምራት ብዙዎች ከተለያዩ ደዌ /በሽታ/ መፈወስ ጀመሩ፤ ይህም በጣም ብዙ ሰዎች ክርስቶስን ወደ ማመን ሳባቸው፡፡ ይህን ድንቅ ሥራ የተመለከቱ የክርስቶስ ሰቃዮች /ሰቃልያነ ክርስቶስ/ በሁኔታው ባለመደሰታቸው መስቀሉን ከጎልጎታ አንስተው ወደ ሌላ ቦታ በመውሰድ ቀብረውት ለ300 ዓመታት ያህል የከተማው ጉድፍና ጥራጊ እየተጣለበት የተቀበረበት ቦታ ኮረብታ እስኪሆን ድረስ ቆየ፡፡ በ4ኛው መ/ክ/ዘመን ለክርስቲያኖች ነፃነት የሚያስብና የሚያስከብር ንጉሥ በሮም ተነሣ፡፡ የንጉሡም ስም ቈስጠንጢኖስ ይባል ነበር፡፡ ይህ ንጉሥ ክርስቲያኖችን ይበልጥ እንዲወድ ያደረገው በጠላቱ በማክሴንዲዩስ (መክስምያኖስ) ላይ በዘመተበት ጊዜ ገና በጕዞ ላይ እያለ ‹‹በዝንቱ ትዕምርተ መስቀል ትመውዕ ፀርከ /በዚህ ምልክት ድል ታደርጋለህ/›› የሚል በመስቀለኛ ቅርፅ የተጻፈ ጽሑፍ በጠፈር ሰማይ አይቶ በመስቀል ምልክት ድል በማድረጉ ነው፡፡ የንጉሥ ቈስጠንጢኖስ እናት ንግሥት እሌኒ የመስቀሉ ፍቅር ያደረባት ቅድስት እናት ነበረች ቈስጠንጢኖስም በዘመነ መንግሥቱ በትዕምርተ መስቀል ብዙ የድል ሥራ ስለሠራ ለመስቀሉ ታላቅ አክብሮትና አድናቆት ነበረው፡፡ ንግሥት እሌኒም መስቀሉን ለማግኘት ሰው ብትጠይቅ የሚያውቅ አላገኘችም፡፡ በመጨረሻ ግን የመስቀሉ መውጣት የእግዚአብሔር ፈቃድ በመኾኑ ኪራኮስ የሚባል አረጋዊና መቃርስ የሚባል ኤጲስ ቆጶስ አገኘች፡፡ ከእነዚህም አረጋዊው ኪራኮስ ዕድሜው የሸመገለና በእስራኤል ባህልና ደንብ ያደገ ነበር፡፡ እሌኒም እሱን ጠይቃ መስቀሉን ለማግኘት እንዲተባበራት ጠየቀችው እርሱም ሦስት ተራሮችን ጠቆማትና ከሦስት ተራሮች የትኛው እንደሆነ ለማወቅ ግን በእግዚብሔር ፈቃድ ሱባኤ እንድትይዝ ነገራት፤ ሱባኤም ያዘች፡፡ ከዚህም በኋላ እግዚአብሔር መልአኩን ልኮ እንዲህ አላት ‹‹አንቺም ሰውም በከንቱ አትድከሙ እንጨት አሰብስበሽ /አስደምረሽ/ ዕጣን አፍስሺበትና በእሳት አያይዥው የዕጣኑ ጢስ ወደ ላይ ወጥቶ ወደ ታች ሲመለስ አቅጣጫውን ተመልክተሽ ጭሽ ያረፈበትን ቦታ አስቆፍሪው›› አላት፡፡ እርሷም መልአኩ እንዳላት እንጨት አሰብስባ ደመራ አስደመረች ዕጣንም አፈሰሰችበት ጭሱም ሰማይ ደርሶ ወደ ምድር ሲመለስ ቦታውን አመለከታት ይህም የሆነው መስከረም 16 ቀን ነው፡፡ እኛ ደመራ ብለን የምናከብረው ይህን አብነት በማድረግ ነው፡፡ ደመራ ማለትም፤ ደመረ፣ ጨመረ፣ አንድ አደረገ፤ ከሚለው የግእዝ ቃል የተወረሰ ሲሆን መቀላቀልን፣ መገናኘትን፣ መሰብሰብን፣ መጣመርን፣ መዋሐድን በአጠቃላይ ሱታፌን፣ አንድነትን እና ኅብረትን ያመለክታል፡፡ #መስቀል_፤ መስከረም 17 ንግሥት እሌኒ በመስከረም 16 ደመራ አስደምራ እጣን አስጢሳ የመስቀሉን ቦታ ካወቀች በኋላ ቁፋሮውን ያስጀመረችበት ዕለት ስለሆነ ነው፡፡ ከቁፋሮውም በኋላ የጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል ዳግመኛ በእግዚአብሔር ፈቃድ፤ በእሌኒ ተነሳሽነት፤ በረዳቶቿ አጋዥነት መስቀሉ እንደቀድሞ ድውያንን ሲያድን፣ ለምጻምን ሲያነጻ፣ ሽቦችን ሲያቀና፣ ሙታንን ሲያስነሳ፣ የማያምኑትን ወደ ማመን ሲመልስ ነበር፡፡ ዛሬም የክርስቶስ መስቀል በዓለም እያበራ ሕሙማንን እየፈወሰ ይገኛል፡፡ #ተቀጸል_ጽጌ_(#መስከረም_10_/#አፄ_መስቀል_/)፤ መስቀሉ ወደ ሃገራችን የገባባት ዕለት ነው፡፡ #መስከረም_21_፤ መስቀሉ መስከረም 10 ቀን ቀን ወደ ሃገራችን ከገባ በኋላ ‹‹መስቀሌን በመስቀለኛ ቦታ አስቀምጥ›› በተባለው ቃል መሠረት ከብዙ ፍለጋ በኋላ መስከረም 21 በግሸን ደብር ከርቤ ያረፈበት ዕለት ነው /ዝርዝሩን መስከረም 21 ይጠብቁ/፡፡ ✤፠ንግስት እሌኒ በመስከረም 16 ቀን ደመራ አስደምራ፤ ፠፠✤✤መስከረም 17 ቁፋሮ አስጀምራ ፠፠፠✤✤✤በመጋቢት 10 ቀን ቁፋሮ ተጠናቅቆ መስቀሉ ተገኝቷል፡፡ (በደብራችን በአ.አ በብቸኝነት ከንግሥት ዘውዲቱ ጀምሮ በደብራችን የመስቀል ክብረ በዓል መስከረም 17ና መጋቢት 10 ይከብራል፤ ላልሰማው ያሰሙ፡፡ እንደየደብራችሁ ይትበሃል ትጠቀሙበት ዘንድ ሙሉ ሥርዐተ ማኅሌቱን (ዘመድኀኔዓለምና ዘአደባባይ ብለን) አቅርበንላችኋል፡፡) እንደ መድኀኔ ዓለም ፈቃድ፤ መስከረም 16ና 17፤ በደመራው (በርጥብ እንጨት ለሚደመረው ደመራ)፣ በዋይዜማው፣ በማኅሌቱ፣ በሰዐታቱ፣ በኪዳኑ፣ በቅዳሴው፣ በዑደተ ታቦተ ሕጉ፣ የመስቀሉን እምነት ግናባራችንን ለመቀባት በቀጨኔ ደብረ ሰላም እንገናኝ፡፡ ፠ እኛንም በመስቀሉ ፈዋሽነት ይማረን፤ የመስቀሉን ፍቅር በልባችን ይሳልብን አሜን፡፡ ፠ "በወንጌሉ ያመናችሁ፤ እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ አደረሳችሁ፡፡" ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡ /ከቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት ሰሌዳ መጽሔት ላይ ባጭሩ የተወሰደ፡፡/

የደመራ በዓል በደብራችን በቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለም (ርጥብ ዛፍ በዕለቱ ተቀቈርጦ የሚደመርበት) በአዲስ አበባ በብቸኝነት የመስቀል ታቦት ክብረ በዓል የሚነግሥበት፡፡ ተወልደናሆ ተወልደ መድኅ
+3
የደመራ በዓል በደብራችን በቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለም (ርጥብ ዛፍ በዕለቱ ተቀቈርጦ የሚደመርበት) በአዲስ አበባ በብቸኝነት የመስቀል ታቦት ክብረ በዓል የሚነግሥበት፡፡ ተወልደናሆ ተወልደ መድኅን፤ መድኅንን ያመነ መድኀኔ ዓለምን፡፡ ተወልደናሆ ተወልደ መድኅን፤ ተወልደናሆ ተወልደ መድኅን፡፡

ከፎቶ ማኅደራችን፤ በመስቀል አደባባይ የመስቀል ደመራ በዓል አቅራቢዎች፤ በ1995፣ በ2004 ና በ2007ዓ.ም.
+4
ከፎቶ ማኅደራችን፤ በመስቀል አደባባይ የመስቀል ደመራ በዓል አቅራቢዎች፤ በ1995፣ በ2004 ና በ2007ዓ.ም.

ለምነና እንደወጡም ከሸዋ ተነሥተው ወደ ትግራይ ክፍለ ሀገር በአኵሱም አቅራቢያ ከሚገኘው ገዳም ደብረ በንኮል ከሚባለው ከአቡነ መድኃኒነ እግዚእ ገዳም ደረሱ፤ ብሉይ ከሐዲስ የጠነቀቁ ናቸውና የአባታቸውን ዙፋን (ልዑልነት) ስለ ፍቅረ ክርስቶስ ንቀውት እየዘመሩ ስለተጓዙ በዚህ ምክንያት 'መናኔ መንግሥት' ይባላሉ፡፡ አቡነ መድኃኒነ እግዚእም አቡነ ያሳይ የእግዚአብሔር ጸጋ ያደረባቸው ሰው መሆናቸውንና ወደ እርሳቸውም እየመጡ መሆኑን በመንፈስ ዐውቀውት ስለነበር በደስታ ተቀበሏቸውና በረድእነት ከወንድሞቻቸው ጋር ጨመሯቸው፡፡ አቡነ ያሳይም የገዳም መነኮሳትን በማገልገል በመንፈሳዊ ተጋድሎ ብዙ ደከሙ፡፡ በደብረ በንኮል ገዳምም ብዙ አስገራሚ ተአምራትን አደረጉ፡፡ ከዚህም በኋላ እግዚአብሔር መልአኩን ልኮ ወደ መካነ ገድላቸው በጣና አካባቢ እንደሆነ ነገራቸው፡፡ ‹‹ወላዴ አእላፍ ቅዱሳን›› የተባሉ አቡነ መድኃኒነ እግዚእም ቀደም ብለን የጠራናቸውን ‹‹ሰባቱን ከዋክብት›› ምግባር ሃይማኖታቸውን፥ ተጋድሎ ትሩፋታቸውንና ገቢረ ተአምራታቸውን አይተው ፈቃደ እግዚአብሔርን ጠይቀው በአንድ ቢያመነኩሷቸው በዚያው ቅጽበት መንፈስ ቅዱስ ወርዶ ገዳሙን በብርሃን አጥለቅልቆት ታይቷል፡፡ ከሰማይም የምስክርነት ድምፅ ተሰምቷል፡፡ አቡነ ያሳይ በረድእነት በቆዩበት ዘመንም ዛፎችን መትከል ይወዱ ነበር:: ከትሩፋት መልስም በልብሳቸው ውሃ እየቀዱ ያጠጡ ነበር:: በተለይ "ምዕራገ ጸሎት" የሚባለው ተአምረኛ ዛፍ ዛሬ ድረስም አለ፡፡ ከዚህም በኋላ ከሰባቱ ቅዱሳን ውስጥ ሦስቱ ቅዱሳን አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ፣ አቡነ ያሳይ እና አቡነ ያፍቅረነ እግዚእ ሆነው ከደብረ በንኮል ገዳም አባታቸውን አቡነ መድኃኒነ እግዚእን ተሰናብተው ወደ ጣና ደሴት መጥተዋል፡፡ አቡነ ሳሙኤል ወደ ‎ዋልድባ፤ አቡነ ያፍቅረነ እግዚእ ወደ ገሊላ ከዚያ ወደ ጐጉቤን ሲሔዱ አቡነ ያሳይ መንዳባ ውስጥ ገቡ:: አቡነ ያሳይ በ13ኛው መ/ክ/ዘመን በአባታቸው የዘመነ ንግሥና መጨረሻ ወደ አርባ ምንጭ ሄደው ከዚያው ሱባኤ ገብተው ፈጣሪያቸውን ቢማጸኑ እግዚአብሔርም ከዚያው አካባቢ የሚኖር አንድ ባሕታዊን የመድኀኔዓለምን ጽላት እንዲያወጣላቸው አዘዘላቸው፡፡ እርሳቸውም ጽላቱን ተቀብለው በጎጃም በኩል አድርገው ወደ ጣና ተመልሰው በዘጌ አከባቢ ሲደረሱ ከጣና ባሕር ዳር ቆመው በየብስ ያለውን ርቀትና በባሕሩ ያለውን ቅርበት አይተው አሁንም ወደ ፈጣሪያቸው በጸሎት ተማጸኑ፡፡ በዚህም ጊዜ ጌታችን ተገልጦላቸው ‹‹ወዳጄ ያሳይ ሆይ አትጨነቅ እኔ ከአንተ ጋር ነኝ፣ ከጎንህ ያለውን ድንጋይ በባሕሩ ላይ ጫነው፤ ድንጋዩም ለልጅ ልጅ እኔ ዓለምን ለማሳለፍ እስከምመጣበት ሰዓት ድረስ መታሰቢያ ትሁንህ›› አላቸውና ተሰወረ፡፡ አቡነ ያሳይም የመድኀኔዓለምን ጽላት ይዘው በድንጋዩ ላይ እንደተቀመጡ ድንጋዩ እንደታንኳ በባሕሩ ላይ ተንሳፈፈ፡፡ ባሕሩም ከማዕበሉ ብዛት የተነሣ ይታወክ ነበር፡፡ አባታችንም ያለ ምንም ቀዘፋ ልብሳቸውም ውኃ ሳይነካው ቁጭ እንዳሉ ማን እንደአባ ወደ ተባለው ቦታቸው ደረሱ፡፡ ከዚህም በኋላ አቡነ ያሳይ ገዳማቸውን ገድመው ወንድሞቻቸውን ሰብስበው በተጋድሎ በመኖር ብዙ ቅዱሳንን አፍርተዋል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ፤ ✣ የጌታችንን እግር ያጠቡት የገዳመ መጕናው አቡነ አብሳዲ፤ ✣ እንደ ነቢዩ ኤልያስ ዝናብንና ነፋስን የከለከሉት አቡነ ያዕቆብ፤ ✣ እሬትን እንደ ማር ያጣፈጡት አቡነ ገብረ ኢየሱስ፤ ✣ እንደ ቅዱስ እስጢፋኖስ ጸጋንና ሞገስን የተሞሉት አቡነ ዳንኤል፤ ✣ እንደ ንጉሥ ሰሎሞን ጥበብን የተሞሉት አቡነ ፊቅጦርና ሌሎችም ብዙዎች ይጠቀሳሉ፡፡ በወቅቱም ብዙ የበቁ ቅዱሳን በአካባቢው ነበሩ፡፡ በአጽፋቸውና በእግራቸው በባሕሩ ላይ የሚሄዱ ነበሩ፣ በጸጋ ክንፍ ተሰጥቷቸውም የሚበሩ ነበሩ፡፡ የአቡነ ያሳይ ተአምራቶቻቸው ተነግረው አያልቁም፡፡ በወቅቱ የነበሩት ቅዱሳን ልጆቻቸው ‹‹ከቅዱሳን ማን እንደ አባ ያሳይ በከባድ ድንጋይ ላይ ተጭኖ በባሕር ላይ የተጓዘ አለና..›› ብለው ይገረሙባቸው ነበር፡፡ ቦታቸውም ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ‹‹ማን እንደ አባ›› ተባለ፡፡ ይህም የአቡነ ያሳይ ገዳም በሰሜን ጎንደር ዞን ሀገረ ስብከት በደንቢያ ወረዳ በጎርጎራ ጣና ሐይቅ አካባቢ ይገኛል፡፡ *** ገዳሙን ልዩ ከሚያደርጉት ነገሮች አንዱ፤ በገዳሙ ውስጥ የሚገኙ መነኰሳት የሚጠሩበት የአባት ስማቸው በጻድቁ በአቡነ ያሳይ ስም ነው፡፡ ምንጭ፤ *የቃል አስረጅ የገዳሙ አበምኔትና የገዳሙ መነኰሳት (በተለይም አባ ኀይለሚካኤል ያሳይ)፤ *የቅዱሳን ታሪክ፣ ገጽ 152፤ *ሐመር 21ኛ ዓመት ቊ.11፣ 2006 ዓ.ም፤ *ከገድላት አንደበት-ke gedilat andebet እና Dn Yordanos Abebe መጽሐፈ ገጽ (Facebook) (ከቦታው ድረስ በመሄድና ከአበውና ከተለያዩ መጻሕፍት ይህንን ጽሑፍ ላዘጋጀልን የሰ/ትቤታችን አባል አቡነ ያሳይ ይስጡልን፡፡) አምላከ አበው(ያሳይ ዘመንደባ) በበረከት ረድኤት ይጠብቀን፤ ፍጻሜያችንን ያሳምረው፡፡ ከአበው በረከት፤ ከሥላሴ ልጅነት አያናውጠን፡፡ /የቀ/ደ/ሰ መድኀኔ ዓለም ወደ/ት/ቅ/ገብርኤል ፍ/ሕ/ሰ/ት/ቤት/

#አቡነ_ያሳይ_ዘማንዳባ_(ድንጋዩን እንደ ጀልባ ተጠቅመው የጣናን ሐይቅ ይጓጓዙ ስለነበር /ማን እንደ አባ የተባለላላቸው፤ ከ7ቱ ከዋክብት ቅዱሳንና ከ7ቱ ከዋክብተ ጣና ከኹለቱም ወገን የሚመደቡ) መስከረም 14 የዕረፍታቸው ዕለት ነው፤ መድኀኔዓለም አምላካችን ከጻድቁ ረድኤት በረከት ይክፈለን፡፡ /ስዕሉ 1ኛ አቡና ያሳይ በጣና ባሕር ላይ እንደሔዱ የሚያሳይ፣ 2ኛ ጻድቁ እንደ ታንኳ ይጠቀሙበት የነበረው ድንጋይ ዛሬ በገዳሙ ቅጽር ግቢ የሚገኝ፣ 3ኛ መንደባ መድኀኔዓለም ገዳም (የጻድቁ አጽም ያረፈበት) 4ኛ የአቡነ ኒቃላዎስ አጽም ያረፈበት ቤት/ 7ቱ ከዋክብት ቅዱሳንን የመላእክትን ሕይወት በምድር የኖሩ ታላላቅ የሀገራችንን ቅዱሳን በአንድ ጊዜ አስተምረውና አመንኵሰው ለጽድቅ ያበቋቸው አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ናቸው፡፡ ‹‹ወላዴ አእላፍ ቅዱሳን›› የተባሉት አቡነ መድኃኒነ እግዚእ የኢትዮጵያ ብርሃኗ በሆኑት በአቡነ ተክለ ሃይማኖት እጅ ከመነኰሱ በኋላና አቡነ ተክለ ሃይማኖትም ለአቡነ መድኃኒነ እግዚእ ‹‹ስፍር ቊጥር የሌላቸው ከዋክብት ቅዱሳንን›› በመንፈስ ቅዱስ እንደሚወልዱ ትንቢት በተናገሩላቸው መሠረት፤ ታላቁን ገዳም ደብረ በንኰልን (አኵሱም አጠገብ) መሥርተው፤ ኍልቈ መሳፍርት የሌላቸውን ቅዱሳንና መነኰሳት አመንኵሰዋል፡፡ ለአብነትም፤ የተንቤኑን አቡነ ዐቢየ እግዚእን፣ የዞዝ አምባውን አቡነ አብሳዲን፣ ሰባቱ ከዋክብትን ጨምሮ አመንኵሰዋል፡፡ አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ሰባቱን ቅዱሳን በአንድ ጊዜ ሲያመነኵሷቸው በዚያው ቅጽበት መንፈስ ቅዱስ ወርዶ (ገዳሙ የተቃጠለ እስኪመስል ድረስ ብርሃን ወርዶ) ገዳሙን በብርሃን አጥለቅልቆት ታይቷል ከሰማይም የምስክርነት ድምፅ ተሰምቷል፡፡ እንዲሁም እነዚሁ ቅዱሳን በአቡነ ተክለሃይማኖት በኋላ መላዋን ኢትዮጵያን በወንጌል ኮከብ ብርሃንነት አብርተዋታልና፤ በእነዚህ ምክንያት አንድ ላይ የመነኰሱት እነዚህ ሰባቱ ቅዱሳን ‹‹ሰባቱ ከዋክብት›› እየተባሉ ይጠራሉ፡፡ ከላይ ካየናቸው ፯ቱ ከዋክብተ ጣና፥ ፯ቱ ቅዱሳንና፥ ፭ቱ ከዋክብት መካከል ባሕሩን በእግራቸውም እየረገጡ ጠቅጥቀው የተሻገሩ አሉ፣ በአጽፋቸው (በልብሳቸው) እንደጀልባ ተጠቅመው የሚጓዙ አሉ፤ በየብስ ላይ ኾነው መጻሕፍቶቻቸውን በአንበሳ ጭነው የተጓዙ አሉ፤ ……. ዛሬ መስከረም 14 ክብረ በዓላቸው የምናከብራለቸው አቡነ ያሳይ ትልቅ ጠፍጣፋ ድንጋይን እንደጀልባ ተጠቅመው በእርሱ ላይ ሆነው እንደ ጀልባ የሚጓጓዙ ናቸው፡፡ አቡነ ያሳይ፤ ቅዱስ ዳዊት ‹‹እግዚአብሔር በቅዱሳኑ ላይ ድንቅ ነው›› (መዝ 67፡35) ብሎ እንደተናገረ ጻድቁ አቡነ ያሳይ ከእግዚአብሔር በተሰጣቸውም ጸጋ ጣና ሐይቅን የሚያቋርጡት በአንድ ትልቅ ጠፍጣፋ ድንጋይ ላይ ተቀምጠው ድንጋዩን እንደ ጀልባ ተጠቅመው ነበር፡፡ ያ ድንጋይ ዛሬም ድረስ በገዳማቸው ውስጥ በክብር ተቀምጦ ይገኛል፤ በዚህም ምክንያት በጣና ከተደረጉት ተዓምራት ማን እን አባ ያሳይ ይኾናል የሚሰጥመውን ድንጋይ ሳይሰጥም እንደ ጀልባ አድርጎ መጓዝ ብለው አበው ገዳሙን ‹‹ማን እንደ አባ ያሳይ /ማንዳባ(መንደባ)/ ብለው ሰየሙት፡፡ ጻድቁ ከአቡነ ሳሙኤል ጋር አብረው ወደዚህ ቦታ መጡ፡፡ ከዚያም የቦታው አቀማመጥ የብስ፥ መሬትና ደሴት መሆኑን አይተው ‹‹እግዚአብሔር ፈቅዶ ይችን ደሴት የጸሎት ቦታችን አድርጎ ቢሰጠን በጸሎት እንጠይቀው›› ተባብለው ሁሉቱም ቅዱሳን ሱባኤ ገቡ፡፡ ለስም አጠራሩ ክብር ምስጋና ይግባውና ጌታችንም ለአቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ በገሃድ ተልጦላቸው ‹‹ወዳጄ ሳሙኤል ሆይ ይህ ቦታ የአንተ አይደለም የወንድምህ የያሳይ ቦታ ነው፡፡ እኔ ወዳዘጋጀሁልህ ቦታ ወደ ዋሊ(ዋልድባ) ሂድ›› ብሎ የዋልድባን ምድር አሳያቸው፡፡ አቡነ ሳሙኤልም የጌታችንን ትእዛዝ ተቀብለው ወንድማቸውን አቡነ ያሳይን ተሰናብተው ወደ ዋልድባ ሄደው ገዳማቸውን አቅንተው ተጋድሏቸውን በዚያ ፈጸሙ፡፡ ጌታችን ዳግመኛም ለአቡነ ያሳይ ተገለጠላቸውና ‹‹ወዳጄ ያሳይ ሆይ የአባትህን መንግሥትና የዓለሙን ክብር ከምኞቱ ጋር ለእኔ ብለህ ስለተውክ ይህንኑ ቦታ በዚህ ዓለም ሳለህ ለአንተ፣ ወደ ዘላለማዊ መንግሥቴ ከወሰድኩህ በኋላም ለልጆችህ ምንዳህ አድርጌ ሰጥቼሃለሁ፤ ምሕረቴንም በቦታህ አዘንባለሁ ቸርነቴም አይለያትም፣ ብዙ የመንፈስ ልጆችንም ታፈራለህ፤ ቦታህም እኔ ለፍርድ እስክመጣ ድረስ ትኖራለች›› በማለት ቃልኪዳኑን አቆመላቸውና ተሰወራቸው፡፡ ‹‹ምንዳህ›› ማለት ደመወዝ ማለት ነውና በዚህም ‹‹ማንዳባ›› ማለት ‹‹የአቡነ ያሳይ ምንዳ-ደመወዝ›› ማለት ነው ሲሉ አባቶች ገዳሙን ‹‹ማንዳባ-ምን እንደ አባ›› ብለው ሰየሙት፡፡ አቡነ ያሳይ የትውልድ ሀገራቸው ሸዋ ተጉለት ነው፡፡ አባታቸው ንጉሡ ዓምደ ጽዮን ቀዳማዊ ነው፡፡ ይኸውም ከ1296-1326 ዓ.ም. የነበረው ነው፡፡ አቡነ ያሳይ በልጅነታቸው በንጉሡ አባታቸው ቤት ሲኖሩ የገዳማት መነኰሳት ለመንፈሳዊ ሥራ ወደ ንጉሡ ዘንድ እየመጡ ደጅ ሲጠኑ ያዩዋቸዋል፡፡ በዚህም ጊዜ አባታችን ገና በልጅነታቸው የመነኰሳቱን እግር ያጥቡ ስለነበር በዚሁ አጋጣሚ መነኰሳቱን ስለምንኩስና ሕይወት ይጠይቋቸው ነበር፡፡ መነኰሳቱም ሕይወታቸውን ያስረዷቸዋል፡፡ አቡነ ያሳይም ብሉያትንና ሐዲሳትን ከልጅነታቸው ጀምሮ የተማሩ ስለነበር የአባቶችን ትምህርትና የወንጌልን ቃል በማገናዘብ የፈጣሪያቸው ፍቅር በልቡናቸው እንደ እሳት ነደደ፤ ይልቁንም ‹‹ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱን ግን ቢያጎድል ምን ይጠቅመዋል›› የሚለውን የጌታችንን ቃል አሰቡ፡፡ ማቴ 16፥26፡፡ ከዚህም በኋላ የንጉሡ አባታቸውን የአልጋ ወራሽነት ማለትም የንጉሥነትን ክብር ፈጽመው በመናቅ ‹‹እኔን መከተል የሚወድ ቢኖር እራሱን ይካድ፣ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ›› (ማቴ 16፡27) ያለውን የጌታችንን ቃል አስበው ንጉሣውያን ቤተሰቦቻቸውን ጥለው ለምነና ወጡ፡፡

ዘመኑን የዋጀ ተከታታይ መንፈሳዊ ትምህርት (Course)፤ ለወጣቶች (በቀንና በማታ) እና ለሕፃናት (በቀን)፤ ለምትፈልጉ ምዕመናን በሙሉ፤ ሰ/ት/ቤታችን የቀ.ደ.ሰ መድኀኔ ዓለም ወደ/ት/ቅ/ገብርኤል
ዘመኑን የዋጀ ተከታታይ መንፈሳዊ ትምህርት (Course)፤ ለወጣቶች (በቀንና በማታ) እና ለሕፃናት (በቀን)፤ ለምትፈልጉ ምዕመናን በሙሉ፤ ሰ/ት/ቤታችን የቀ.ደ.ሰ መድኀኔ ዓለም ወደ/ት/ቅ/ገብርኤል ፍኖተ ሕይወት ለወጣቶችና ሕፃናት ምዕመናን በ2012ዓ.ም. ልዩ ተከታታይ ትምህርቶችን አዘጋጅቶ ይጠብቃችኋል፡፡ የትምህርቶቹ ዓይነቶች፤ በወጣት ክፍል የሚሰጡ፤ ✤ #በቀዳማይ፤ * ትምህርተ ሃይማኖት (መግቢያ ሥነ ፍጥረትና አእማድ) * የቤተ ክርስቲያን ታሪክ መግቢያና በዓለም መድረክ * የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መግቢያና አዋልድ ቅዱሳት መጻሕፍት * ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ✤ #በካልዓይ፤ * ነገረ ማርያም ወነገረ ቅዱሳን * የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ (የቤ.ክ ታሪክ በኢትዮጵያ) * ብሉይ ኪዳን * ተግባራዊ ክርስትና (ክርስቲያናዊ ሕይወት) ✤ #በሣልሳይ * ነገረ ክርስቶስ ወነገረ ድኅነት * ልሳነ ግእዝ * ሐዲስ ኪዳን * ሥርዐት ወምሥጢራተ ቤ.ክ እንዲሁም በሕፃናት ክፍል የአብነት ትምህርትን ጨምሮ የተለያዩ ትምርቶች ይሰጣሉ፡፡ ትምህርቱ የሚሰጠው፤ * ለወጣቶች በቀን (ቅዳሜ ከ9-11 ና እሑድ ከ4፡30-6፡30) * ለወጣቶች በማታ (ሰኞ፣ ረቡዕና ዐርብ ከ12-2)፤ ለ6 ወራት * ለሕፃናት በቀን (ቅዳሜ ከ6፡30-8፡30 ና እሑድ ከ6፡30-8፡30) ✣✣ መመዝገቢያ፤ በሰ/ት/ቤቱ ጽሕፈት ቤትና ትምህርት ክፍል ✣ ከአኀት ሰንብት ትምህርት ቤቶችና ከግቢ ጕባኤ ለመማር የምትመጡ የተማራችኋቸውን ትምህርቶች የሚገልጽ ደብዳቤ (ምስክር ወረቀት /ካርድ (Certeficet)/ ማምጣት ይጠበቅባችኋል፡፡ ✤✤ ትምህርቱ ጥቅምት 1 ይጀመራል፡፡ ‹‹የነፍስ ምግቧ የእግዚአብሔር ቃል ነው፡፡›› ለበለጠ መረጃ፤ 0922 85 13 74 /0921 05 60 56/

?????? አንተ የምትተኛ ንቃ! /ሙሉ ጽሑፉን ሳያነቡ አስተያየት ባይሰጡ ይመከራል!/ ፩ ፨፨፨ ‹‹እስከ መቼ ድረስ በሁለት አሳብ ታነክሳላችሁ?›› ፨ መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ ፲፰፥፳፩ ‹‹ያለ ሥርዓት የሚሄዱትን ገስጿቸው፡፡›› 1ተሰ. 5፥14 በጉለሌ ክፍለ ከተማ የእሬቻን በዓል በማስመልከት በተካሄደው የፓናል ውይይት ላይ /ቀሲስ?????/በላይ በመገኘት ስለ በዓሉ ሃይማኖታዊ???? አከባበር መግለጫና ማብራሪያ ሰጥተዋል፤ በመጨረሻም ቀሲሱ????? በሰጡት ቃለ ምዕዳን የፓናሉ ፍጻሜ ሆኗል፡፡ ፪ ፨፨፨ /#ዋዜማ_ቅኔ_ዘሊቁ_ክፍለ_ዮሐንስ/ #ለመልአክ ኢናከብሮ፣ ለእመ አስረጸ ቈጽለ በመጠነ ነዊኀ ቆሙ፤ ለዖፍ ወለትንንያ እስመ ክንፍ ቦሙ፡፡ ወበሲበቱ ለሰብእ ኢናከብሮ ቀዲሙ፤ ፀዐዳ ሲበት እስመ ሀለወሙ፤ ለዕፀው ወአዕባን ኵሎሙ፡፡ #ትርጕም፤ ፠፠ #በረጅም_ቁመቱ_ክንፍን_ቢያበቅል_በክንፍ_ቢሸፈን_መልአኩን_አናከብረውም_፤ (ቀሲስ በላይ የክህነት ልብስ ስለለበሰ፥ መስቀል ስለያዘ፥ የእግዚአብሔርን ስም ስለጠራ አናከብረውም) ለወፍና ለትንኝ ክንፍ አላቸውና፤ መልአኩን በክንፍ አናከብረውም፡፡ (ለጣዖት ቤት /ለመተተኞች ፥ ለጠንቋዮች፥ ለካዳሚዎች ……/ ልብስ አላቸውና፥ በቅብዐ ሜሮን ያልከበረ መስቀል የሚይዙ አሉና፥ ዲያብሎስም እግዚአብሔርን ያምናልና …..) ፠፠ #ሰውንም በሽበት አናከብረውም፤ (በላይም ስሙ ቀሲስ ስለተባለና ከመንግሥት አካላት ጋር ስለተጠጋ አናከብረውም) ለድንጋይና ለእንጨቶች ሁሉ ነጭ ሽበት አላቸውና፤ ሰውን በእውቀቱ እንጂ በሽበቱ አናከብረውም፡፡ (በስመ ቀሲስ የሚነግዱና የሚያጨናብሩ፤ ቆብ ያደረጉ፥ ጥምጣም የጠመጠሙ አሉና)፨ ፫ ፨፨፨ #ፍቅር ያጌብረኒ ነጊረ ነጊረ ዜናሆሙ ለቅዱሳን፤ የቅዱሳንን ዜናቸውን ለመናገር ፍቅር ግድ ይለኛል ወቅንዐት ያጌብረኒ ከመ እዝልፎሙ ለዕልዋን፤ #ቅናትም_ዝንጉዎችን_እንድሸሻቸው_ግድ_ይለኛል፤ #ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እሰብሖ ለኢየሱስ ክርስቶስ፤ ፍቅር ክርስቶስን እንዳመሰግነው ግድ ይለኛል፤ ወቅንዐት ያጌብረኒ ከመ አውግዞ ለሰይጣን፤ ቅናትም ሰይጣንን አወግዘው ዘንድ ያስገድደኛል፤ #ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እትልዎሙ ለሐዋርያተ ክርስቶስ፤ ፍቅር የክርስቶስን ሐዋርያት እንድከተላቸው ያስገድደኛል፤ ወቅንዐት ያጌብረኒ ከመ አጕይዮሙ ለረሲዓን፤ #ቅንዐትም_ከሀዲዎችን_እነቅፋቸው_ዘንድ_ያስገድደኛል፤ #ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እወድሶሙ ለሰማዕት፤ ፍቅር ሰማዕታትን አውድሳቸው ዘንድ ግድ ይለኛል፤ ወቅንዐት ያጌብረኒ ከመ እጽአሎሙ ለማርያን፡፡ ቅናትም ጠንቋዮችን እንድዘልፋቸው ያስገድደኛል፡፡ /ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ፥ መጽሐፈ ምሥጢር ዘደብረ ዘይት ምንባብ፡፡/ ፬ ፨፨፨ የቄሣርን ለቄሣር፤ የእግዚአብሔርን ለእግዚአብሔር፡፡ ‹‹ነገር ግን ሁሉ በአገባብና በሥርዐት ይሁን፡፡›› 1ቆሮ. 14፥40 #አድኅነኒ እግዚኦ እስመ ሀልቀ ሔር፤ ወውኅደ ሃይማኖት እም እጓለ እመሕያው፡፡

እንኳን ለሰ/ት/ቤታችን #፶፬ኛ#ዓመት_የምሥረታ_በዓል_ለተማሪዎች_ምረቃና_ለዝክረ_ቅዱስ_ያሬድ_አደረሳችሁ_አደረሰን፡፡ ፎቶ 1፤ በ1962 ዓ.ም ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ደብራችንንና ሰ/ት/ቤታችንን በጎጉበት ወቅት፡፡ ‹‹የሰ.ት.ቤት አገልግሎት ለቤ.ክ ሐዋርያዊ ተልዕኮ›› የሰንበት ትምህርት ቤታችን የ54ዓመታት ታሪክ በአጭሩ፤ ፠ ምንም እንኳን አስቀድሞ ብዙ እንቅስቃሴዎች ቢኖሩም፤ ሰንበት ትምህርት ቤታችን ራሱን ችሎ በመዋቅር ተዋቅሮ አካል ገዝቶ፥ ስያሜ አግኝቶ የተዋቀረው የደብራችን አስተዳዳሪ በኾኑት በንቡረ ዕድ በየነ ዓሊ ከፍተኛ ድጋፍ በጥቂት ወንዶችና ሴቶች (ወጣትና ሕፃናት) ነሐሴ ፳፮ና ፳፯/፲፱፻፶፰ ዓ.ም. ነው፤ ፠ ሲመሠረት የሰ/ት/ቤታችን ስያሜ ‹‹የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለም ቤ.ክ. ሰንበት ትምህርት ቤት›› በሚል ነበር፤ ፠ ሲመሠረትም ከነበሩት መሥራች አባላት መካከል ለአብነት (እማሆይ ተስፋዬ (እኅተ ጊዮርጊስ)፣ አቶ አየለ…፣ አርቲስት የሻሽወርቅ በየነ፣ ሐና በለጠ፣ …..….) እዲሁም ከጥቂት ቆይታ በኋላ ከተቀላቀሉት መካከል እነ አርቲስ ችሮታው ከልካይ ተጠቃሾች ናቸው፡፡ በተለይም እማሆይ ተስፋዬ ፀጋ ሰንበት ትምህርት ቤታችንን ከመመሥረት ጀምሮ ለብዙ ዘመናት በሰንበት ትምህርት ቤታችን አገልግሎት ላይ እጅግ ከፍተኛውን አስተዋጽዖ ያደረጉና በሰ/ት/ቤታችን ታሪክ ላይ የአንበሳውን ድርሻ የተወጡ እናታችን ናቸው፡፡ ✤✤ ሰ/ት/ቤታችን መነሻ አድርጎ የተመሠረተበት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ቃልም ‹‹አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥትና ጽድቁንም ፈልጉ፤ ሌላው ኹሉ ይጨመርላችኋል፡፡›› ማቴ. ፮፥፴፫ የሚለው ሲኾን፤ ዋና ዓላማው መጽሐፍ ቅዱስን መማርን ቤተ ክርስቲያንን ማወቅ ሲኾን ዝርዝር ዓለማው ደግሞ ወጣቶች ከሕፃንነታቸው ጀምረው እግዚአብሔርን በፍፁም ልባቸውና በፍፁም ነፍሳቸው እንዲያመልኩት፤ ወላጆቻቸውንና ከእነርሱ በእድሜ ከፍ ያሉትን እንዲያከብሩ፣ በኑሮ ዝቅ ላሉት ወንድሞቻቸውና እኅቶቻቸው በራሳቸው ሊደረግላቸው የሚወዱትን ኹሉ ለእነርሱም እንዲያደርጉላቸው፤ ትምህርተ ሃይማኖትና ለትውልድ እንዲተላለፍ ለማድረግ ነበር፡፡ ፠ ከሰ/ት/ቤታችን ምሥረታ ከ2 ዓመታት በኋላ ጥቅምት 11/1960ዓ.ም. ‹ፍኖተ ሕይወት› (‹‹የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለም ቤ.ክ. ፍኖተ ሕይወት››) የሚል ስያሜን ያገኘችበት ነው፡፡ ‹ፍኖተ ሕይወት› ቃሉ የግእዝ ሲኾን ትርጓሜው የሕይወት መንገድ ማለት ነው፤ ይኸውም እውነተኛ መንገድ የተባለው መድኀኔ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ‹‹እኔ እውነተኛ መንገድና ሕይወት ነኝ፡፡›› እንዲል፡፡ ✤፠✤ በ1962ዓ.ም. የሰንበት ትምህርት ቤታችን ሌላኛው ትልቁ ምዕራፍ፤ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ደብራንችንና ሰንበት ትምህርት ቤታችንን መጎብኘት /ፎቶውን ይመልከቱ …../ ፠ ብፁዕ አባታችን ሰንበት ትምህርት ቤታችንን ባልታሰበ ጊዜ መጎብኘታቸው፤ አዳራሻችን ድረስ መጥተው ማስተማራቸውና አባላቱን ኹሉ እቅፍ አድረገው ማበረታታቸው፤ አዳራሻችንን ለማደስ ተሥፋ መስጠታቸው፤ ማኅበረ ካህናት ለሰንበት ትምህርት ቤት እንዲራዱ መመሪያ መስጠታቸው ከሰንበት ትምህርት ቤቱ ምሥረታ በኋላ ዳግመኛ በአባላቱ ሁሉ ልቡና ላይ እንደ ሰሌዳ ተቀርጾ በብርታትና በፍቅር፤ በንቃትና በትጋት አገልግሎትን እንድናከናውን መሠረት ሆነን፤ ይህችም ቀን ዳግመኛ ሰንበት ትምህርት ቤታችን የተመሠረተችበት ዕለት ሆነች፡፡ ✤✤✤ ሕፃናት ክፍል  መምህር አባ ምክረ ማርያም ሠይፈ ሥላሴ የደብራችን አስተዳዳሪ ከኾኑ በኋላ መጋቢት 29/1965ዓ.ም. ድረስ በመምጣጥ የሕፃናት ክፍል ለብቻቸው እንዲማሩ ወንድ በአንድ ረድፍ ሴቶች በሌላኛው ረድፍ እንዲቀመጡ ባስተላለፉት መመሪያ መሠረት፤ በሳምንቱ ከሚያዝያ 6/1965ዓ.ም. ጀምሮ ሕፃናት ክፍል ራሱን ችሎ መዋቀሩ የመጀመሪያዋ የሕፃናት ክፍል ሰብሳቢም የ13ት ዓመቷ የሻሽ ወርቅ በየነ መኾኗ፡፡  በ1980ዋቹና 90ዎቹ መጀመሪያ ድረስ የሕፃናት ክፍል ‹‹እምነት ተስፋ ፍቅር›› በሚል በተሰየሙ በ3ት ምድቦች የተለያዩ መርሐ ግብሮችን በአዳራሽና በዐውደ ምሕረት ሲያቀረብ መቆየቱ፡፡  በ1990ዎቹ መጀመሪያ የፊልጶስና ናትናኤል ክፍል በሚል ስያሜ ተሰይሞ ለ2ት ተከፍሎ መቆየቱ፤ የሕፃናት ክፍል አባላት ከጊዜ ወደ ጊዜ በመጨመራቸውና በተለያዩ የእድሜ ክልሎች ከፍሎ ማስተማር በማስፈለጉ ተጨማሪ 2ት ክፍሎች ‹‹የታሪክ ሀ›› እና ‹‹የታሪክ ለ›› ክፍል በሚባሉ የተሰየሙ ክፍሎች መጨመራቸው፡፡ ያተሪክ ሀ እና ለ የሚሉት ስያሜዎች አሁን የጳውሎስና የጴጥሮስ ክፍል ተብለው የተሰየሙት ናቸው፡፡  በ2000ዎቹ መጀመሪያ ላይ የመድኀኔዓለም ዝክር (ጽዋ) ስያሜው ‹‹ዝክረ አበው›› በሚል መከበር መጀመሩ፡፡ አንዲሁም የወላጅ ኮሚቴ በሕፃናት ክፍል መዋቀሩ የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ /የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለም ወደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን፤ የፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት፡፡/

#አጋፔ_ ለተማሪዎችና ለአባላት በሙሉ፤ የአጋፔ (የፍቅር ማዕድ) መርሐ ግብር ቅዳሜ መስከረም 10/2012 ዓ.ም. በ12፡00 ሰዐት ይካሄዳል፡፡ /የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱ
+1
#አጋፔ_ ለተማሪዎችና ለአባላት በሙሉ፤ የአጋፔ (የፍቅር ማዕድ) መርሐ ግብር ቅዳሜ መስከረም 10/2012 ዓ.ም. በ12፡00 ሰዐት ይካሄዳል፡፡ /የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት/

ወቅታዊ የቤተ ክርስቲያናችን ፈተናዎች ምንድን ናቸው?፤ የእኛስ ድርሻ? መስከረም 10/2012 ዓ.ም. በ10፡30 በመርካቶ ደብረ ኀይል ቅዱስ ራጕኤል ቤ/ክ በትልቁ ት/ቤት ሰገነት ላይ እንገናኝ፡፡
+2
ወቅታዊ የቤተ ክርስቲያናችን ፈተናዎች ምንድን ናቸው?፤ የእኛስ ድርሻ? መስከረም 10/2012 ዓ.ም. በ10፡30 በመርካቶ ደብረ ኀይል ቅዱስ ራጕኤል ቤ/ክ በትልቁ ት/ቤት ሰገነት ላይ እንገናኝ፡፡

እንኳን ለአቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ (ፀሐየ ዋሊ ፀሐየ ኢትዮጵያ) ፍልሰተ ሥጋ በሰላምና በጤና አደረሳችሁ፡፡ /ስዕሉ/- አቴና(መቃብረ ሳሙኤል)ይባላል፤ በዋሊ(ዋልድባ) የሚገኝ፤ አቡነ ማር ሳሙኤል ዘዋልድባ ለበርካታ ዘመናት በጾም፣ በጸሎት፣ በትህርምት፣………የኖሩበት እና በስተመጨረሻም፤ ማክሰኞ ታኅሣሥ 12 ያረፉበት፤ ጌታችን ከእናቱና ከቅዱሳን መላእክቶች ጋር የወረዱበት ቅዱስ ቦታ፤ ከካረፉም በኋላ ቅዱስ ሥጋቸው ለበርካታ ዘመናት የኖረበት ቦታ ነው፡፡ አቡነ ኣሙኤል በኪደተ እግር በወንጌል ገበሬነት አዲስ አበባንና አካባቢዋን ያስተማሩ ታላቅ አባት ናቸው፡፡ ዛሬ መስከረም 6 የአቡነ ማር ሳሙኤል(ፀሐይ ዘዋሊ፤ ፀሐይ አዚትዮጵያ) ቅዱስ ሥጋ ከአቴና(መቃብረ ሳሙኤል) የፈለሰበት ነው፤ ልክ የእመቤታችን ሥጋ በነሐሴ (14) እንደፈለሰ፤ የሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ ሥጋ (ሚያዝያ 23 አርፎ) በነሐሴ 16 ወደ ልዳ እንደፈለሰ፤ የአቡነ ተክለሃይማኖት ሥጋ (በነሐሴ 24 አርፎ) በግንቦት 12 ከደብረ አስቦ ወደ ደብረ ሊባኖስ እንደፈለሰ ሁሉ፤ ዛሬም የአቡነ ማር ሳሙኤል ሥጋ ከአቴና የፈለሰበት ነው፡፡ አቡነ ማር ሳሙኤል (ፀሐይ ዘዋሊ፤ ፀሐይ አዚትዮጵያ) ከሚታወቁበት ብዙ ነገሮች መካከል ከአቡነ ሳሙኤል ዘደብረ ወገግና ከአቡነ ብንያሚ ጋር ወደ ታላቁ አባት አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ለበረከት በመጡበት ወቅት አዲስ አበባንና አካባቢዋና በወንጌል ገበሬነት አርሰዋታል፤ ለዚህም ምስክሩ፤ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ የተሠራበት/አቡነ ሳሙኤል የኤልክትሪክ ኃይል ማመንጫ በመባል የሚታወቀው/ (ከአቃቂ 30ኪ.ሜ አካባቢ ርቀት ላይ የሚገኘው) በወቅቱ ራሳቸው የመሠረቱት(ያስፋፉት) ገዳም (ደብረ ገነት አቡነ ሳሙኤል የሴቶች አንድነት ገዳም በመባል የሚጠራው) ምስከር ነው፡፡ ሰላም ለከ ኵነነ ሐመረ፤ እንበለ አስጥሞ ኅቡረ፥ ታዕድወነ ባሕረ፡፡ አምላከ አበው(ሳሙኤል) በረድኤት ይጠብቀን፤ ፍጻሜያችንን ያሳምረው፡፡ ከአበው በረከት፤ ከሥላሴ ልጅነት አያናውጠን፡፡ /ከዋልድባ ዋሊ ገጽ የተወሰደ/

‹‹ሁለቱም አንድ አካል ይኾናሉ፤ ይህ ነገር ጥልቅ፤ ረቂቅ ምሥጢር ነው፤ እኔም ለክርስቶስና ለቤተ ክርስቲያን ምሳሌ አድርጌ እናገረዋለሁ፡፡›› ሃይማኖተ አበው ዘስምዓት በወርኀ ነሐሴ ፳፬/፳፻፲፩ ዓ.
+3
‹‹ሁለቱም አንድ አካል ይኾናሉ፤ ይህ ነገር ጥልቅ፤ ረቂቅ ምሥጢር ነው፤ እኔም ለክርስቶስና ለቤተ ክርስቲያን ምሳሌ አድርጌ እናገረዋለሁ፡፡›› ሃይማኖተ አበው ዘስምዓት በወርኀ ነሐሴ ፳፬/፳፻፲፩ ዓ.ም. ጋብቻሽን በዩናይትድ ኪንግደም ሎንዶን ደብረ ገነት ቅድስት ሥላሴ ቤ/ክ የፈጸምሽው የሰ/ት/ቤታችን አባል እኅታችን፤ #ሰላማዊት(ይልፋሸዋ)#ጌታቸው_ከሠራዊት_ወንድማገኘው ጋር የፈጸማችሁትን ጋብቻ፤ የይስሐቅንና የርብቃን ጋብቻ የባረከ አምላክ፤ የትዳር ሕይወታችሁን ይባርክላችሁ፥ ያጣምራችሁ፥ ያዋሕዳችሁ፤ እመብርሃን በአማላጅነቷ አትለያችሁ፤ ቅዱስ ገብርኤል ከፊት ይምራችሁ ከኋላ ይከተላችሁ፡፡ ✤ ‹‹ጌታን እንዲወዱና በአካልም ይሁን በመንፈስ በባሎቻቸው ደስ እንዲሰኙ ለእህቶች ንገራቸው፡፡ ልክ እንደዚሁ ጌታ ቤተ ክርስቲያንን እንደወደደ ሚስቶቻቸውን እንዲወዱ ለወንድሞች በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ንገራቸው፡፡›› ቅዱስ አግናጥዮስ ምጥው ለአንበሳ ለፖሊካርፐስ በላከው መልእክቱ ✤ ከተጋባችሁ በኋላ ባልና ሚስት አንድ አካል ናችሁ እንጂ ሁለት ስላይደላችሁ በፍጹም ልባችሁ እርስ በእርሳችሁ ተፋቀሩ፡፡ ከዛሬ ጀምሮ ሌላ ወንድ ወይም ሌላ ሴት አትፈልጉ ይልቁንም በተቻላችሁ መጠን አንዳችሁ ሌላውን ደስ አሰኙ፤ በመረዳዳትና በፍጹም ፍቅር ኑሯችሁን ሁሉ አሳምሩ፡፡>> ኢትዮጵያዊው ፈላስፋ ዘርአያዕቆብ፡፡ /ከቀጨኔ ደ/ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደ/ት/ቅ/ገብርኤል ቤ/ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት/

#አስቸኳይ_፤ +++ነገ መስከረም 4/2012 ዓ.ም. * ሁላችንም እናስቀድስ፥ አቡነ ዘበሰማያት እናድርስ፤ ሁላችንም፤ የተቻለን 151 መዝሙረ ዳዊት እንጸልይ (በገዳም ያሉ እንዲጸልዩ መልዕክት እናድርስ) * ውዳሴ ማርያም፥ ሰላም ለኪ እንድገም። * ሰላማዊ ሰልፉን ያጨናገፉ 3ቱ .... ከለባትን ሌላ ጊዜ እንመለከታቸዋለን። /shareeeeeeee/