uz
Feedback
Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Kanalga Telegram’da o‘tish

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Ko'proq ko'rsatish

📈 Telegram kanali Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት analitikasi

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) Amxar til segmentidagi kanali faol ishtirokchi. Hozirda hamjamiyat 15 367 obunachidan iborat bo'lib, Din & Maʼnaviyat toifasida 5 600-o'rinni va Efiopiya mintaqasida 2 189-o'rinni egallagan.

📊 Auditoriya ko‘rsatkichlari va dinamika

невідомо sanasidan buyon loyiha tez o‘sib, 15 367 obunachiga ega bo‘ldi.

26 Iyun, 2026 dagi oxirgi ma’lumotlarga ko‘ra kanal barqaror faollikka ega. Oxirgi 30 kunda obunachilar soni 2 ga, so‘nggi 24 soatda esa 2 ga o‘zgardi va umumiy qamrov yuqori darajada qolmoqda.

  • Tasdiqlash holati: Tasdiqlanmagan
  • Jalb etish (ER): Auditoriya o‘rtacha 20.69% darajada jalb etiladi. Nashrdan keyingi dastlabki 24 soatda kontent odatda umumiy obunachilar sonining 10.92% ini tashkil etuvchi reaksiyalarni to‘playdi.
  • Post qamrovi: Har bir post o‘rtacha 3 180 marta ko‘riladi; birinchi sutkada odatda 1 679 ta ko‘rish yig‘iladi.
  • Reaksiyalar va o‘zaro ta’sir: Auditoriya faol: har bir postga o‘rtacha 18 ta reaksiya keladi.

📝 Tavsif va kontent siyosati

Muallif resursni shaxsiy fikrni ifoda etish maydoni sifatida ta’riflaydi:
የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Yuqori yangilanish chastotasi (oxirgi ma’lumot 27 Iyun, 2026 da olingan) sababli kanal doimo dolzarb va katta qamrovli bo‘lib qoladi. Analitika auditoriya kontent bilan faol hamkorlik qilishini, uni Din & Maʼnaviyat toifasidagi muhim ta’sir nuqtasiga aylantirishini ko‘rsatadi.

15 367
Obunachilar
+224 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kunlar
+230 kunlar
Postlar arxiv
#ፎቶዎቹ ፤ እመቤታችን ከልጇ ጋር ያረፈችበት ገዳመ ቊስቋም ማርያም ገጽታ የሚያሳዩ _______________________________ ደብረ ቁስቋም በደቡብ ግብፅ የሚገኝ ተራራ ነው፡፡ ደብረ ቁስቋም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን እንዲሁም ቅዱስ ዮሴፍንና ቅድስት ሰሎሜን ይዛ ከስደት ሲመለሱ ያረፉበት ቦታ ነው፡፡ ይህም ‹‹ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ ግብፅ ሽሽ›› ባለው መሠረት የተፈጸመ ነው፡፡ (ማቴ. ፪፥፲፫-፲፭) የክርስቶስ ስደቱ ቀድሞ በነቢዩ ኢሳይያስ ‹‹. . . እነሆ፥ እግዚአብሔር በፈጣን ደመና ተቀምጦ ወደ ግብፅ ይመጣል፡፡ የግብፅም ጣዖታት በፊቱ ይዋረዳሉ›› ተብሎ በተነገረው መሠረት የተፈጸመ ነው፡፡ ነቢዩ ፈጣን ደመና ያለው ጌታችን በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ጀርባ ላይ ሆኖ ወደ ግብፅ መውረዱን ለመግለጽ ነው፡፡ ፈጣን ደመና የተባለችውም እመቤታችን ነች፡፡ (ኢሳ. ፲፱፥፩) በስደቱም ጣዖታተ ግብፅ እየተሰባበሩ ሲወድቁ፤ በእነርሱም አድረው ሰውን ሲያስቱ የነበሩ አጋንንትም ሲሸሹ ታይተዋል፡፡ ደግሞም ጌታችን ዳግማዊ አዳም ነውና በምክረ ከይሲ (ዲያብሎስ) ምክንያት ተሰዶ የነበረው ቀዳማዊ አዳምን ለመካስ ተሰደደ፤ በዚህም አጋንንትን ከሰው ልቦና አውጥቶ አሳደደ፡፡ እመቤታችንም ልጇን ይዛ ከስደት ስትመለስ ያረፈችበትን ተራራ ደብረ ቁስቋምን ባረከችው ቀደሰችውም፤ ይህ ተራራ የተቀደሰ ተራራ ስለመሆኑ የእስክንድርያው ሊቀ ጳጳስ ቅዱስ ታኦፊሎጎስ በድርሳነ ማርያም እንዲህ አለ፤ ‹‹ይህም ከሀገሮቹ ሁሉ ተራሮች የሚበልጥ (የተለየ) ከፍ ያለ ተራራ ነው፡፡ በውስጡ ቅዱስ አግዚአብሔር ያድራል፡፡ ይህንን ተራራ የእግዚአብሔር ልጅ ወዶታል፤ አክብሮታልምና፤ ከዓለም ሀገሮች ሁሉ ከተቀደሰች እናቱ ጋር አድሮባታልና፡፡ ከመላእክት ቤት ያድር ዘንድ አልወደደም፤ ቢታንያንም አልመረጠም፡፡ ከተራራው ላይ ባለች ገዳም ቤት ውስጥ አደረ እንጂ፤ ነቢዩ ዳዊት፤ የጽዮንን ተራራ ወደደ፤ በአርያምም መቅደሱን ሠራ እንዳለ፡፡›› ‹‹አንተ ተራራ ሆይ የእግዚአብሔር ማደሪያ በሆንህ ጊዜ በኪሩቤልና በሱራፌል መካከል ፍጹም ደስታ ተደረገ፡፡ የመላእክት ሠራዊት ቅዱስ የሆነ ፈጣሪያቸውንና ጌታቸውን ይታዘዙ (ያገለግሉ) ነበር፡፡ አንተ ተራራ ሆይ ያደረብህ ጌታችን ስለሆነ ከተራሮች ሁሉ ከደብረ ሲናም ይልቅ ከፍ ከፍ አልህ፤ ጌታችን በደብረ ሲና ባረፈ ጊዜ ፍጹም ደስታ፣ ታላቅ ብርሃንም በሆነ ጊዜ መቅረብና መመልከት ከሙሴ በቀር የቻለ የለም፡፡ እርሱም ቢሆን ፊቱን ማየት አልቻለም፡፡ ሥጋ ለባሽ ሁሉ እርሱን ዐይቶ በሕይወት መኖር የሚቻለው የለምና፡፡ እኛ ግን አየን፤ ከዚህ ማደሩንም ተረዳን፤ ዳግመኛም ንጽሕት በሆነች በማርያም ዘንድ አየነው፡፡ ቅድስት ከሆነች ከእመቤታችን ማርያም ዘንድ በቤተልሔም ስለ እኛ በተዋሐደው ሥጋ በጨለማና በሞት ጥላ ሥር ያለን እኛን ከቸርነቱና ሰውን ከመውደዱ የተነሣ መጥቶ አዳነን፤ ከዓለም ሁሉ ይልቅ ጣዖትን በማምለክ ሲበድሉም ወደ ግብፅ ሀገር ወርዶ በእነርሱ ላይ የመለኮትነት ብርሃኑን በማብራት ታላቅ የሆነ ክብሩን ገለጠ››፡፡ (ድርሳነ ማርያም) ኅዳር ፮ ቀን የሚነበበው የመጽሐፈ ስንክሳር ክፍል ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግመኛም በኋላ ዘመን ሐዋርያትን በደብረ ቁስቋም ሰብስቦ፤ ታቦትንና ቤተ ክርስቲያኑን አክብሮ የቊርባን መሥዋዕትንም ሠርቶ ቅዱስ ሥጋው ክቡር ደሙን እንደ ሰጣቸው፤ እኛንም ለዚህ ክብር የበቃን እንሆን ዘንድ የእግዚአብሔር አምላክ ቅዱስ ፈቃድ ይሁንልን፤ አሜን፡ ፍቶዎች በመ/ር ልዋም | የቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት :: #share .Facebook... https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool .YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w .Telegram... https://t.me/medihanaelem http://tiktok.com/@finotehiwot www.finotehiwotsundayschool.com

የቊስቋም ክብረ በዓልን በየት ሊየከብሩ ዐስበዋል??? #ኅዳር #፮፤ #በዓለ_ቊስቋም_፡፡ (በግብፅ ሀገር ባለች ደብረ ቊስቋም ዋሻ ከ፫ ዓመት ከ፮ ወር ስደቷ ያረፈችበት)፡፡ #በመላው_ዓለም_የቊስቋም_ክብረ_በዓል_የሚከበርባቸው_ #፲፬ #ገዳማትና_አድባራት፡፡ (ሌሎች ያልጠቀስናቸው አብያተ ክርስቲያናት ካሉ አሳውቁን) #በአዲስ_አበባ_የቊስቋም_ክብረ_በዓል_የሚከበርባቸው_ #፰ #ገዳማትና_አድባራት፡፡ ፩. #መንበረ_ንግሥት_ቊስቋም_ማርያም_ቤ/ክ_፤ (#፫፻፷፭ት #ቀናት_ሙሉ_ዝክር_በማኅበረ_ሰላም_መድኀኔዓለም_የሚዘከርባት_ቤ/ክ) አድራሻው፤ ጉለሌ ክፍለ ከተማ፥ እንጦጦ፥ ቊስቋም፤ ታክሲ፤ ከፒያሳ/ጊዮርጊስ (መርካቶ) (4 ኪሎ) → ሽሮሜዳ (መነን) → ቊስቋም፤ ፪. #ደብረ_ናዝሬት_ቅዱስ_ዮሴፍ_ቤ/ክ፤ አድራሻ፤ ቦሌ ክለ ከተማ፥ ደጃዝማች መርዕድ መንገድ፥ ቀለበት መንገድ፤ ታክሲ፤ ከፒያሳ (መገናኛ) (ከላጋር) (ከ4 ኪሎ) → ቦሌ → ሳሪስ /ቃሊቲ ቀለበት መንገዱ ላይ/ ወይም፤ ከሳሪስ አቦ → ቦሌ /በቀለበት መንገድ/ ፫. #ቃሊቲ_ደብረ_ገነት_ቅዱስ_ሚካኤልና_ደብረ_ቊስቋም_ማርያም_ቤ/ክ፤ (ቃሊቲ ቊስቋም) አድራሻ፤ አቃቂ ቃሊቲ ክለ ከተማ፥ ሰፈረ ገነት፤ ታክሲ፤ ከፒያሳ (መገናኛ) (ከላጋር) (ከ4 ኪሎ) → ቃሊቲ መናኸሪያ → ሰፈረ ገነት ወይም፤ ከሳሪስ አቦ → ቦሌ /በቀለበት መንገድ/ ፠፨፠ #እንዲሁም_በድርብነት_የሚከበርባቸው_፤ ፬. #ኮልፌ_ደብረ_ብርሃን_ቅድስት_ሥላሴ_ቤ/ክ፤ አድራሻ፤ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ፥ ዊንጌት፥ ጠሮ፥ አራት መንታ፡፡ ታክሲ፤ ከፒያሳ/አቡነ ጴጥሮስ ዐደባባይ/ → ዊንጌት → ጠሮ፡፡ ወይም፤ ከመርካቶ ኮልፌ አጣና ተራ → ጠሮ ፭. #ማኅደረ_መለኮት_ወይብላ_ቅድስት_ማርያም_ቤ/ክ፤ አድራሻ፤ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ፥ የሺ ደበሌ፡፡ ታክሲ፤ ከፒያሳ (መርካቶ) → የሺ ደበሌ፡፡ ፮. #ላፍቶ_ደብረ _ኢያሪኮ_መድኀኔ_ዓለምና_መጥምቀ_መለኮት_ቅዱስ_ዮሐንስ_ቤ/ክ፤ አድራሻ፤ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ፥ ላፍቶ ፤ ታክሲ፤ ከመገናኛ → ሜክሲኮ → ላፍቶ፡፡ ፯. #መዝገበ_ምሕረት_ፋኑኤልና_ቊስቋም_ቤ/ክ፤ አድራሻ፤ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ፥ ካራ ፥ አጀንባ፤ ታክሲ፤ ከፒያሳ ሸዋ ዳቦ ቤት (ከሜክሲኮ) → አየር ጤና → ካራ፡፡ ፰. #ጉለሌ_ሸጎሌ_ኪዳነ_ምሕረት_ቤ/ክ፤ አድራሻ፤ ጉለሌ ክፍለ ከተማ፥ አዲሱ ገበያ ፥ ቶታል፥ ጉለሌ ዕፅዋት ማዕከል (ወደ ዊንጌት በቀለበት መንገገዱ ትንሽ ሄደው)፤ ታክሲ፤ ከፒያሳ (አስኮ) → አዲስ ገበያ /ጸዮን ሆቴል/፤ #በኢትዮጵያ_ደረጃ_የሚከብርባቸው_ #፭ #ገዳማትና_አድባራት፡፡ ፩. #ደብረ_ፀሐይ_ፋርጣ_ቊስቋም _ቤ/ክ፤ (በ1254 ዓ.ም. የተመሠረተች) አድራሻው፤ ደቡብ ጎንደር ሀገረ ስብከት፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ደሴ/ወልድያ → ፋርጣ፡፡ ወይም፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ባሕር ዳር → ወረታ → ፋርጣ፤ ፪. #ገዳመ_አባ_ጽጌ_ድንግል_ገዳም_፤ አድራሻው፤ ደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ደሴ → ወግዲ → ገዳመ ጽጌ፤ ወይም፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ጎጃም (በመርጡለ ማርያም) → መካነ ሰላም ወግዲ → ገዳመ ጽጌ፤ ወይም፤ ከአ.አ. ቦሌ መርካቶ አውቶቡስ ተራ → መርሐ ቤቴ ወግዲ → ገዳመ ጽጌ፡፡ ፫. #አምባ_ጽጌ_ድንግል_ገዳም፤ አድራሻው፤ ዋግኽምራ ሀገረ ስብከት፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ላሊበላ → ሰቆጣ (ዋግኽምራ)፡፡ ፬. #ጎንደር_ደብረ_ፀሐይ_ቊስቋም_ማርያም_ቤ/ክ፤ አድራሻው፤ ማዕከላዊ ጎንደር ሀገረ ስብከት፥ ጎንደር ከተማ፥ ቸቸላ (ሆስፒታል አጠገብ)፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ጎንደር ከተማ → ሆስፒታል → ቊስቋም፤ ፭. #ደሴ_ቊስቋም_ማርያም_ቤ/ክ፤ አድራሻው፤ ደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት፥ ደሴ ከተማ፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ደሴ ከተማ፡፡ #ከኢትዮጵያ_ውጭ_የሚከብርባቸው_ #፩ #ጥንታውያን_ገዳማትና_አድባራት፡፡ ፩. #ግብፅ_ቊስቋም _ማርያም_ገዳም_፤ (#እስከ_ቅርብ_ዘመናት_በግብፅ_የኢትዮጵያ_ርስት_የነበረ_) አድራሻው፤ ግብፅ፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ → ግብፅ → ገዳመ ቊስቋም፤

፠ በኢትዮጵያ ደረጃ ኅዳር 6 የሚከበርባቸው ቦታዎች፤ ገዳመ አባ ጽጌ ድንግል፤ ደቡብ ወሎ፤ ወግዲ፡፡ ደብረ ፀሐይ ጎንደር ቋስቋም ማርያም፤ ጎንደር ከተማ ከሆስፒታል አጠገብ፡፡ ፠ በአዲስ አበባ ታቦተ
+6
፠ በኢትዮጵያ ደረጃ ኅዳር 6 የሚከበርባቸው ቦታዎች፤ ገዳመ አባ ጽጌ ድንግል፤ ደቡብ ወሎ፤ ወግዲ፡፡ ደብረ ፀሐይ ጎንደር ቋስቋም ማርያም፤ ጎንደር ከተማ ከሆስፒታል አጠገብ፡፡ ፠ በአዲስ አበባ ታቦተ ሕጉ የሚነግሥባቸው ቦታዎች፤ ፠እንጦጦ መንበረ ንግሥት ቅድስት ቊስቋም ማርያም፡፡ (#365ት_ቀናት_ሙሉ_ዝክር_በማኅበረ_መድኀኔ_ዓለም_አዳራሽ_የሚዘከርባት_ቤ/ክ) ፠ደብረ ናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍ ቤተ ክርስቲያን፡፡ (የቤ/ክርስቲያኑ ዐጸድ እጅጉን ልብን የሚገዛና የሚማርክ) ፠ቃሊቲ ቊስቋም ማርያም ቤ/ክ፡፡ … ሌላም ካለ ይንገሩን..

#ኅዳር_6፤ ደብረ ቊስቋም፤ #እመቤታችን_ከልጇ_ጋርስ_ደትን_የጀመረችበት_ዕለት_ነው፡፡ **ድንግል ማርያም ከልጇና ከአረጋዊ ቅዱስ ዮሴፍ ጋርለ3 ዓመታት ከ6 ወራት (ወይም ለ42 ወራት) (1275 ቀናት) ከተሰደደች በኋላ #ግንቦት_24_ደግሞ_በዓተ_ግብጽ_ (ወደ ግብጽ ወደ ደብረ ቊስቊም ገብታ ያረፈችበት ቀን ነው፡፡ ዖፍኒ ረከበት ላቲ ቤተ፤ ወፍም ቤቷን ሰራች፡፡ መዝ. ፹፫፥፫ ንጉሥ ተወልዷል መባሉን የሰማው ሔሮድስ 144,000 ሕጻናትን ሲፈጅ በቅዱስ ገብርኤል ትዕዛዝ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አንድ አምላክ ልጇን አዝላ፤ በአንዲት አህያ ላይ ተቀምጣ፤ ጥቂት ስንቅ ቋጥራ፤ ከዮሴፍና ከሰሎሜ ጋር ስደት ወጣች፡፡ ከገሊላ ተነሥታ በጭንቅ፣ በመከራ፣ በረሃብና በጥም፣ በሐዘንና በድካም፣ በእንባ ተጕዛ በዚህች ቀን ምድረ ግብፅ ገብታ በሥደት እጅግ ብዙ መከራ ተቀብላለች:: † የአምላክ እናቱ እሳትን አዝላ በብርድ ተንገላታለች:: † ለእኛ የሕይወት እንጀራን ተሸክማ እርሷ ተራበች:: † የሕይወትን ውሃ ተሸክማ ተጠማች:: † የሕይወት ልብስን ተሸክማ ተራቆተች:: † የሕይወት ፍስሐን ተሸክማ አዘነች:: † እመ አምላክ ተራበች፣ ተጠማች፣ ታረዘች፣ ደከመች፣አዘነች፣ አለቀሰች፣ እግሯ ደማ፣ ተንገላታች:: ለሚገባው ይሕ ሁሉ የተደረገው ለእኛ ድኅነት ነው:: በእውነት ይህንን እያወቀ ለድንግል ማርያም ክብር የማይሰጥ ሰይጣን ብቻ ነው:: አራዊት: ዕፀዋትና ድንጋዮች እንኳን ለአመላክ እናት ክብር ይሰጣሉ:: አረጋዊው ቅዱስ ዮሴፍና ቅድስት ሰሎሜ ደግሞ የክብር ክብር ይገባቸዋል:: ከአምላክ እናት ከድንግል ማርያምና ከቸር ልጇ ጋር መከራ መቀበልን መርጠዋልና:: #መድኃኔ_ዓለም_ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ_ለምን_ተሰደደ? #ለምን_ስደቱን_ወደ_ግብፅና_ኢትዮዽያ_አደረገ? 1. ፠ትንቢቱን ይፈጽም ዘንድ:: በፈጣን ደመና ወደ ግብፅ እንደሚወርድ ተነግሯልና(ኢሳ 19፥1፣ ዕን. 3፥7) 2. ፠ምሳሌውን ለመፈጸም፤ የሥጋ አባቶቹ እነ አብርሃም፥ ያዕቆብ (እሥራኤል):፥ ኤርምያስ ወደዚያው ተሰደዋልና:: 3. ከግብፅ ጣዖት አምልኮን ያጠፋ ዘንድ:: (ኢሳ. 19፥1) 4. የግብፅና የኢትዮዽያ ገዳማትን ይቀድስ ዘንድ:: 5. ሰው መሆኑ በአማን (በእውነት) እንጂ ምትሐት እንዳልሆነ ለማጠየቅ:: (ሰው ባይሆን ኑሮ አይሰደድም ነበር:: ሔሮድስ ቢያገኘው ደግሞ ሊገድለው አይችልም:: ያለ ፈቃዱና ያለ ዕለተ ዐርብ ደሙ አይፈስምና:: 6. ስደትን ለሰማዕታት ባርኮ ለመስጠት:: እና 7. የአዳምን ስደት በስደቱ ለመካስ ነው:: እመ ብርሃን ድንግል ማርያም ለ3 ዓመታት ከ6 ወራት (ወይም ለ42 ወራት) (1275 ቀናት) በስደት የቆየችባቸው ቦታዎች አሉ:: ፠ በመጀመርያ ድንግል ማርያም ከርጕም ሔሮድስ ስትሸሽ መጀመሪያ የሔደችው ከገሊላ ወደ ሶርያ ደንበር (ደብረ ሊባኖስ) ነበር:: በዚያም የሸሸጋት ቅዱስ ጊጋር መስፍኑ በሔሮድስ ሲገደል ወደ ምድረ ግብጽ ወረደች፡፡ ፠ በግብጽም ለብዙ ጊዜ ከአንዱ ወደ ሌላው ስትሸሽ ቆየች:: ‹‹እንዘ ከመ በግዕት ግድፍት አመ ሳኮይኪ ውስተ ምድረ በዳ፡፡›› እንዲል:: (እሴብሕ ጸጋኪ) ፠ ቀጥላም በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ገብታ ደብረ ቢዘን ላይ (አሁን ኤርትራ ውስጥ ነው) ዐረፈች፤ ፠ ከደብረ ቢዘን ደብረ ሐዊ፣ በደብረ ዳሞ፣ አኵሱም፣ ደብር ዐባይ፣ ዋልድባ አድርጋ እየባረከች ቆይታለች፤ ፠ በዋልባም ቆይታቸው ልጇ ገዳሙን በኢትዮጵያ በብጨኝነት ራሱ የገደመውን ገዳም መሥርቶ እየባረከ ወደ ጣና ሄደዋል፡፡ ፠ በጣና ገዳማትም፤ በተለይ በጣና ቂርቆስ ለ100 ቀናት ቆይታ ቀጥታ በጐጃም ወደ ሸዋ ሔዳ ደብረ ሊባኖስን ቀድሳለች:: ፠ ቀጥላም እስከ ደብረ ወገግና ደብረ ሐዘሎ ደርሳለች፤ በእግሯ ያልደረሰችባቸውን የሀገራችን ክፍሎች በደመና ተጭና ዐይታ ባርካቸዋለች፡፡ ፠ በደብረ ኤረር ተራራ ላይም ከልጇ ኢትዮጵያን በዐሥራትነት ተቀብላለች፡፡ ሔሮድስ መሞቱን መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል የነገራትም እዚሁ ኢትደዮዽያ ውስጥ መሆኑን ትውፊት ያሳያል:: እመቤታችን የሄሮድስን ሞት ከሰማች በኋላ ቊስቋም ከሚባል ተራራ ላይ ሆና ደስታዋን አብረዋት መከራን ከተቀበሉት ከዮሴፍና ከሰሎሜ ጋር አከበረች፡፡ ከሃገራችን ሰዎች (ከሰብአ ኦፌር) የተቀበለችውን ስንቅና ስጦታ በ5 ግመሎች ጭና ከቅዱሳኑ ዮሴፍና ሰሎሜ ጋር ኅዳር 6 ቀን ቊስቋም ውስጥ ገብተው ከድካም ዐርፈዋል፤ ሐሴትንም አድርገዋል:: #ግብጽ_ደብረ_ቊስቋም_፤ ከክርስቶስ ስደት 400 ዓመታት በኋላ በዚህች ቀን የግብጿ ደብረ ቊስቋም ታንጻ ተቀድሳለች፤ የቅዱሳን ማደሪያም ሆናለች፡፡ ይህስ እንደ ምን ነው ቢሉ፤ ለስም አጠራሩ ጌትነት ይሁንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በ390ዎቹ አካባቢ ድንግል እናቱን፣ ቅዱሳን ሐዋርያትን፣ አእላፍ መላእክትን፣ ጻድቃን ሰማዕታትን፣ አስከትሎ ወረደ፡፡ የወቅቱ የግብጽ ፓትርያርክ ቅዱስ ቴዎፍሎስና ሊቁ ቅዱስ ቄርሎስ ቤተ ክርስቲያኑን አንጸው፤ ሕዝቡን ሰብስበው ይጠብቁት ነበርና ወርዶ ቀድሶላቸው ታላቅ ደስታ ኾኗል:: ይህቺ ቀን ለእኛ ለክርስቲያኖች ሁሉ እጅግ የደስታ ቀን ነውና ሐሴትን እናድርግ፤ የሰማይና የምድር ጌታ ለእኛ ሲል ካደረገው ስደቱ ኅዳር 6 ተመልሷልና:: ስደቷን አስበን ካዘንን: መመለሷን አስበን ደስ ልንሰኝ ይገባልና:: ‹‹አብርሒ አብርሒ ናዝሬት ሃገሩ፤ ንጉሥኪ በጽሐ ዘምስለ ማርያም መጾሩ›› ልንልም ይገባል፡፡ ***ኅዳር 5 ለኅዳር 6 ከዋይዜማው ጀምሮ የሚባለውን ሙሉ ሥርዐተ ማኅሌትም እነሆ ብለናል፤ መልካም የማኅሌት ሌሊት ይሁንልን፡፡ /በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ፤ ትምሕርት ዋና ክፍል ፥ ንዑስ ክፍል /ሕትመት እና ሚዲያ/ የተዘጋጀ :: #share Contact: https://t.me/finotehiwot1927 .Facebook... https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool .Telegram... https://t.me/medihanaelem http://tiktok.com/@finotehiwot www.finotehiwotsundayschool.com YouTube https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w Telegram (https://t.me/finotehiwot1927) Telegram (https://t.me/finotehiwot1927)

#Orthodox_Quotes . ክርስቶስ ሆይ ስለ ስምህ ብለው በመስቀ ህዋ ላይ የበረሩ አሉ ።በአንገታቸውም ሰይፍ ያለፈባቸው አሉ ።
#Orthodox_Quotes . ክርስቶስ ሆይ ስለ ስምህ ብለው በመስቀ ህዋ ላይ የበረሩ አሉ ።በአንገታቸውም ሰይፍ ያለፈባቸው አሉ ።