fa
Feedback

فریب کلاهبرداران را نخورید! تل‌متریو این کانال‌ها را شناسایی و برچسب‌گذاری می‌کند 👉 برای مشاهده برچسب، اشتراک تهیه کنید 👈

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

رفتن به کانال در Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

نمایش بیشتر

📈 تحلیل کانال تلگرام Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

کانال Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) در بخش زبانی امهری بازیگری فعال است. در حال حاضر جامعه شامل 15 622 مشترک است و جایگاه 5 362 را در دسته دین و مذهبی و رتبه 2 204 را در منطقه أثيوبيا دارد.

📊 شاخص‌های مخاطب و پویایی

از زمان ایجاد در невідомо، پروژه رشد سریعی داشته و 15 622 مشترک جذب کرده است.

بر اساس آخرین داده‌ها در تاریخ 08 اکتبر, 2026، کانال فعالیت پایداری دارد. در ۳۰ روز گذشته تغییر اعضا برابر 67 و در ۲۴ ساعت گذشته برابر 14 بوده و همچنان دسترسی گسترده‌ای حفظ شده است.

  • وضعیت تأیید: تأیید نشده
  • نرخ تعامل (ER): میانگین تعامل مخاطب 8.25% است و در ۲۴ ساعت نخست پس از انتشار، محتوا معمولاً 4.62% واکنش نسبت به کل مشترکان کسب می‌کند.
  • دسترسی پست‌ها: هر پست به طور میانگین 1 288 بازدید دریافت می‌کند. در اولین روز معمولاً 721 بازدید جمع‌آوری می‌شود.
  • واکنش‌ها و تعامل: مخاطبان به‌طور فعال حمایت می‌کنند؛ میانگین واکنش به هر پست 12 است.

📝 توضیح و سیاست محتوایی

نویسنده این فضا را محل بیان دیدگاه‌های شخصی توصیف می‌کند:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”

به لطف به‌روزرسانی‌های پرتکرار (آخرین داده در تاریخ 09 اکتبر, 2026)، کانال همواره به‌روز و دارای دسترسی بالاست. تحلیل‌ها نشان می‌دهد مخاطبان به‌طور فعال با محتوا تعامل دارند و آن را به نقطه اثرگذاری مهم در دسته دین و مذهبی تبدیل کرده‌اند.

15 622
مشترکین
+1424 ساعت
+867 روز
+6730 روز
آرشیو پست ها
ጥር_7_በዓለ_ሥላሴ_የሰናዖርን_ግንብ_ያፈራረሱበትና_ቋንቋ_የደባለቁበት_ዕለት፡፡ ✤✤ #በአዲስ_አበባ_የቅድስት_ሥላሴ_በዓል_የሚከበርባቸው_ #፲፭ #ገዳማትና_አድባራት_ከታች... ✤✤✤✤✤ “#ንዑ_ንረድ_ወንዝርዎ_ ከመ_ኢይሳምዑ_ነገሮሙ_አሐዱ_ምስለ_ካልኡ፤›› “ኑ ፥እንውረድ ፤ አንዱ የአንዱን ነገር እንዳይሰማ ቋንቋቸውን እንደባልቅባችው”ዘፍ 11፥7 #በባቢሎን የነበሩት በሰናዖር ሰፊ ሜዳ አግኝተው ‹ሳንሞት ስም ማስጠሪያ ግንብ እንገንባ› አገር እናቅና እስከ ሰማይ የመሚደርስ ግንብ እንስራ ተባባሉ ፤ማይ አይኀ በወረደ ጊዜ እንዳያጠፋን የምንጠጋበት ግንብ እንስራ ብለው ሥራ ጀመሩ ፤ አንድም ሞትን የሚያመጡብን ሥላሴ ናቸውና እርሱን ገለን ሞትንም እናጠፋለን ሲሉ፡፡ ✤ይህንን ግንብ #43 ዓመት ሰርተውታል ቁመቱም #5433 ከ2 ስንዝር ነው፤ በፀሐይም እያበሰሉ ይበሉ ጀምረው ነበር ፡፡ ✤ከዚያም ሆነው ጦር እየሰበቁ ይወረውሩ ጀመር ሰይጣን ከደመና በምትሀት ደም እየቀባ ይልክላቸዋል እነርሱም ደሙን እያዩ ‹‹ አሁን አብን ወጋነው አሁን ወልድን ወጋነው ….›› ይሉ ጀመር እግዚአብሔርም የሰናዖርን ግንብ ይጥልባችው ዝንድ ‹‹ንዑ ንረድ ወንዝርዎ ✤ ከመ ኢይሳምዑ ነገሮሙ አሐዱ ምስለ ካልኡ፤›› አሉ የአንዱን ቋንቋ አንዱ እንዳይሰማው ወርደን ቋንቋቸውን እንለያየው ፡፡ ሥላሴ ፍጥረት ሁሉ ቢጎዳ አይወዱምና #72_ቋንቋ አመጡባቸው፤ አንዱ እሣት አምጣ ሲለው አንዱ ውሃ ያመጣል አንዱ ጭቃ ሲል ደግም እንጨት ያመጣለታል፡፡ ✤ከዚያም ትተው ወረዱ ነገር ግን ግንቡን እንደ ጣዖት አርገው ማምልክ ሲጀምሩ ሥላሴ ጽኑ ነፋስ አስነስተው በትነውታል፡፡ #ምሥጢረ_ሥላሴን ሲያስረዳ ( “እግዚአብሔርም አለ” አንድነታቸውን ሲያጠይቅ ድግሞም ኑ እንውረድ አለ ፤ ሶስትነታቸውን ሲያጠይቅ፤) (ዘፍ 11) #ባቢሎን ማለት ዝርው (ዝሩት) ሲሆነ ቋንቋ እና በቦታ ስለተለያዩበት ስያሜውን አግኝቷል (እግዚአብሔር ቋንቋን በትኗልና፣ አህዛብንም በዓለም ሁሉ በትኗልና፡፡ ‹‹…ሥላሴ ሕጸበኒ ወአንጽሐኒ እምአበሳየ በሐሊበ ምሕረትከ ›› ሰይፈ ሥላሴ ዘዓርብ /በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ትምህርት ክፍል ፥ ሕትመት እና ሚዲያ ንዑስ ክፍል የተዘጋጀ ::/ #share .YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w .Telegram... https://t.me/medihanaelem http://tiktok.com/@finotehiwot www.finotehiwotsundayschool.com #churches_and_monastries #ገዳማትና_አድባራት #ክብረ_በዓላት #Feasts #holy_trinity #ቅድስት_ሥላሴ

/በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሕትመት እና ሚዲያ ንዑስ ክፍል የተዘጋጀ ::/ #share .YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w .Telegram... https://t.me/medihanaelem http://tiktok.com/@finotehiwot www.finotehiwotsundayschool.com #churches_and_monastries #ገዳማትና_አድባራት #ክብረ_በዓላት #Feasts #holy_trinity #ቅድስት_ሥላሴ

በአዲስ_አበባ_የቅድስት_ሥላሴ_በዓል_የሚከበርባቸው_ #፲፭ #ገዳማትና_አድባራት፡፡ ፩. #መካነ_ሥላሴ ( #መንበረ_ፀባዖት_ቅድስት_ሥላሴ_ቤ.ክ.)፤ (አዲስ አበባ ላይ በ1883 ዓ.ም. የተመሠረተ፤ ነገር ግን ታቦቱ ቀድሞ የነበረና ከ600 ዓመታት በላይ ታሪክ ያለው) አድራሻው፤ አራዳ ክፍለ ከተማ፥ 4 ኪሎ፤ ታክሲ፤ ከፒያሳ → 4 ኪሎ፤ ፪. #መንበረ_ስብሐት_ቅድስት_ሥላሴ አድራሻ፤ ጉለሌ ክፍለ ከተማ፥ ሽሮ ሜዳ፤ ታክሲ፤ ከፒያሳ(ከአራዳ ጊዮርጊስ)(ከመርካቶ)(ከቦሌ)(ከካዛንቺስ)(ከስታዲየም) → ሽሮ ሜዳ፡፡ ፫. #ደብረ_ሲና_ቅዱስ_እግዚአብሔር_አብ፤ (በድርብነት ይከበራል) አድራሻ፤ ጉለሌ ክፍለ ከተማ፥ በአዲሱ ገበያ በቀጨኔና በእንጦጦ መሃል ላይ የሚገኝ፤ ታክሲ፤ ከፒያሳ(ከመርካቶ) → አዲሱ ገበያ(ቀጨኔ) → ቅዱስ እግዚአብሔር አብ፡፡ ፬. #መሪ_ምሥራቀ_ፀሐይ_ቅድስት_ሥላሴ አድራሻ፤ የካ ክፍለ ከተማ፥ አያት መሪ፤ ታክሲ፤ ከፒያሳ → መገናኛ → መሪ/አያት/፡፡ ፭. #ካራ_አሎ_ቅድስት_ሥላሴ አድራሻ፤ የካ ክፍለ ከተማ፥ ካራ አሎ ፥ አባዶ አጠገብ፤ ታክሲ፤ ከፒያሳ → መገናኛ → ካራ አሎ፡፡ ፮. #ጠሮ_ደብረ_ብርሃን_ቅድስት_ሥላሴ አድራሻ፤ ኮልፌ ቀራንዮ ከተማ፥ ጠሮ፤ ታክሲ፤ ከፒያሳ አራዳ/መርካቶ/ → ኮልፌ፡፡ ፯. #ጀሞ_ፈለገ_ኮሬብ_ቅድስት_ሥላሴና_ቅድስት_ማርያም አድራሻ፤ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ፥ ጀሞ፤ ታክሲ፤ ከፒያሳ አራዳ ሸዋ ዳቦ ቤት /ሜክሲኮ/ → ጀሞ፡፡ ፰. #ደብረ_ቀራንዮ_መድኀኔ ዓለም፤ (በድርብነት ይከበራል) አድራሻ፤ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ፥ ቀራንዮ፤ ታክሲ፤ ከፒያሳ → ጦር ኃሎች → ቀራንዮ፡፡ ፱. #አየር_ጤና_አንቀጸ_ብርሃን_ቅድስት_ኪዳነ_ምሕረት፤ (በድርብነት ይከበራል) አድራሻ፤ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ፥ አየር ጤና፤ ታክሲ፤ ከፒያሳ → ጦር ኃሎች → አየር ጤና፡፡ ወይም፤ ከፒያሳ ሸዋ ዳቦ ቤት → አለም ባንክ/ኤር ጤና/፡፡ ፲. #ሰፈረ_ገነት_ቅድስት_ሥላሴ አድራሻ፤ ነፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ፥ ወረዳ 4፤ ታክሲ፤ ከሜክሲኮ → ላፍቶ፡፡ ፲፩. #ፈለገ_ብርሃን_ቅድስት_ሥላሴ አድራሻ፤ ነፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ፤ ታክሲ፤ ከሜክሲኮ → ላፍቶ፡፡ ፲፪. #ቂሊንጦ_ቅድስት_ሥላሴ አድራሻ፤ አቃቂ ቃሊቲ ላፍቶ ክፍለ ከተማ፥ ወረዳ 9 ፤ ታክሲ፤ ከመገናኛ → /በጎሮ/ ቂሊንጦ ወይም ከፒያሳ → ቃሊቲ → ቂሊንጦ፡፡ ፲፫. #ኤረር_ጽርሐ_አርያም_ቅድስት_ሥላሴ አድራሻ፤ ቦሌ ክፍለ ከተማ፥ ወረዳ 9፥ ጎሮ ሰፈር፤ ታክሲ፤ ከመገናኛ → ጎሮ፡፡ ፲፬. #መሪ_ቅድስት_ሥላሴ አድራሻ፤ ቦሌ ክፍለ ከተማ፥ መሪ አያት፥ ወረዳ 13፤ ታክሲ፤ ከመገናኛ → መሪ/አያት/፡፡ ፲፭. #ቦሌ_ኆኅተ_ብርሃን_ቅድስት_ማርያም፤ (በድርብነት ይከበራል) አድራሻ፤ ቦሌ ክፍለ ከተማ፥ ገርጂ፤ ታክሲ፤ ከመገናኛ → ገርጂ፡፡ #በሃገራችን_በኢትዮጵያና_በዓለም_አቀፍ_ደረጃ_የቅድስት_ሥላሴ_በዓል_የሚከበርባቸው_ #፲ #ገጥንታውያን_ገዳማትና_አድባራት፡፡ ፩. #ማኅበረ_ሥላሴ_ገዳም፤ (ከ2014 ዓመታት በላይ ያስቈጠረ፤ የብዙ ቅዱሳን /የአባ ዐምደ ሥላሴ፣ የአባ ክፍለ ማርያም፣ የ7ቱ ዘሥላሴ፣ የአባ አርከ ሥሉስ ቅዱስ፣ …….. ) መፍለቂያ፡፡ አድራሻ፤ ምዕራብ ጎንደር ሃገረ ስብከት፥ ቋራ (መተማ)፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ጎንደር/አዘዞ/ → ሸዲ/መተማ/ → በእግር፡፡ ፪. #ዱጉም_ሥላሴ_ገዳም፤ አድራሻ፤ ትግራይ፥ ገርዓልታ፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ → በመቀለ (በጎንደር) → ገርዓልታ፡፡ ፫. #ደብረ_ወገግ_አሰቦት_ቅድስት_ሥላሴና_አቡነ_ሳሙኤል፤ (በ13ኛው ክ/ዘመን በታላቁ ጻድቅ በአቡነ ሳሙኤል ዘደብረ ወገግ የተስፋፋ፥ ቅዱስ ዑርኤል የጌታን ደም በጽዋው የመጨረሻውን እንጥፍጣፊ ያፈሰሰበት፥ በርካታ ቅዱሳን የተሰወሩበት፥ አሁንም የሚሠወሩበት፥ የምሥጢር ቦታ) አድራሻ፤ ሐረርጌ፥ አሰበ ተፈሪ፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ቃሊቲ አውቶቡስ ተራ → ናዝሬት/አዳማ/→ አሰበ ተፈሪ → አሰቦት፡፡ ፬. #ሰሜን_ሸዋ_ደብረ_ብርሃን_ሥላሴ_፤ (በ14ኛው ክፍለ ዘመን በዓፄ ዘርዐ ያዕቆብ ዘመን የተመሠረተ፡፡) አድራሻ፤ ሰሜን ሸዋ ሃገረ ስብከት፥ ደብረ ብርሃን ከተማ፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ደብረ ብርሃን ከተማ፡፡ ፭. #መካነ_ሥላሴ_ደቡብ_ወሎ_ወረኢሉ፤ (በ1500ዓ.ም. በዐፄ ናዖድ የተመሠረተና በልጁ በዐፄ ልብነ ድንግል ሥራው የተጠናቀቀ፤ ባለ 16 መንበር፥ በዕንቊና በወርቅ የታነጸ የነበረ፤ /ኋላ በግራኝ የፈረሰ/፤ ነገር ግን ጽላቱ በዐፄ ምኒልክ ወደ አዲስ አበባ መጥቶ ቀድሞ 4 ኪሎ መካነ ሥላሴ አሁን መንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ በመባል የሚጠራው)፤ ጊዜ ገቢር ለእግዚአብሔር ነውና በቀድሞው ቅርጹ በባለ 16 መንበር ተደርጎ 2009 ዓ.ም. አካባቢ የመሠረት ድንጋይ ተጥሎ በመገንባት ላይ ይገኛል፤ (ለሕንፀታ ቤቱ ሁላችንንም ያብቃን)፡፡ አድራሻ፤ ደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት፥ ወረኢሉ፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ደሴ → ወረኢሉ፡፡ ፮. #ፀዓዳ_አምባ_ቅድስት_ሥላሴና_አቡነ_ሰይፈ_ሚካኤል_ገዳም፤ (በ1669 ዓ.ም. የተገደመ፤ መሄጃ መንገዱ እጅግ አስደናቂና በ2ቱም በኩል ገደል የኾነ) አድራሻ፤ ኤርትራ፥ ዞባ አንሰባ፥ ከረን፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ (በአውሮፕላን)→ ኤርትራ → ከረን → /25ኪ.ሜ/ ፀዓዳ አምባ፡፡ ፯. #ጎንደር_ደብረ_ብርሃን_ሥላሴ_፤ (በጥር 26 ቀን 1683 ዓ.ም. በዓፄ አድያም ሰገድ የታነጸ፤ በጎንደር ከተማና ዙሪያ ከሚገኙ 44ቱ ታቦታተ ጎንደር በአሠራሩ ልዩ የኾነ፤ በ1880ዎቹ ድርቡሽ ጎንደር ከተማን ሲያጠፋ ከ44ት አብያተ ክርስቲያናት በተአምራት ሳይቃጣል የቀረ፤ የታላላቅ ሊቃወንት /የእነ ሊቁ ክፍለ ማርያም/ መፍለቂያ፡፡ አድራሻ፤ ማዕከላዊ ጎንደር ሃገረ ስብከት፥ ጎንደር ከተማ፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ጎንደር፡፡ ፰. #ናርጋ_ሥላሴ_ገዳም፤ (በጣና ሐይቅ ላይ ካሉ ደሴቶች ትልቁ በሆነው በደቅ(7ት ደብር ሃገር) ደሴት ከሚገኙ 7 ገዳማት አንዱ)፡፡ (በአፄ በካፋ ባለቤት በበእቴጌ ምንትዋብ /1730-1755 ዓ.ም./ የተሠራ፤ ግድግዳዎቹ በሚያስደንቁና ልቡናና መንፈስን በሚመስጡ ሥዕላት ያሸበረቁ፡፡) አድራሻ፤ ደቡብ ጎንደር ሃገረ ስብከት፥ ጣና ሐይቅ (ከባሕር ዳር ከተማ ሰሜናዊ 37 ኪ.ሜ ርቀት ላይ /በጀልባ 3 ሰዓት/፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ባህር ዳር/ጎንደር → በጀልባ/በታንኳ/ /በመርከብ/ ናርጋ ሥላሴ፡፡ ፱. #ጨለቆት_ሥላሴ_ትግራይ፤ መቀለ አጠገብ፡፡ (በ1787 ዓ.ም. የተመሠረተ ሲኾን ተካዩ ደጃዝማች ወልደ ሥላሴ ክፍለ ኢየሱስ ሃገረ ገዢ ናቸው) (የታላላቅ ሊቃውንት መፍለቂያ ነው፤ ለአብነትም በዐፄ ዮሐንስ /1864 – 1881ዓ.ም./ ዘመነ መንግሥት አራት ጳጳሳትን እንዲያመጡ ከተላኩት መካከል አንዱ ሊቅ አለቃ ዐሥራት ዘውጉ ዘጨለቆት ሥላሴ ናቸው፡፡) (የእንግሊዝ ጦር ዐፄ ቴዎድሮስ በመቅደላ ሰብስቦት የነበረውን ዘርፈው ሲወስዱ የበዛባቸውን ለዚህ ደብር ሰጥተው ሄደዋል፡፡) አድራሻ፤ ትግራይ ሀገረ ስብከት ፥ እንደርታ አውራጃ፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → መቀለ /እንደርታ/፡፡ ፲. #ሐረር_ሐድሬ_ጥቆ_መካነ_ሥላሴ፤ አድራሻ፤ ምሥራቅ ሐረርጌ ሃገረ ስብከት፥ ሐረር ከተማ፥ ሐድሬ ጥቆ ወረዳ፤ (በአፄ ኀይለ ሥላሴ በ1941-43 ዓ.ም. የተሠራ) ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ቃሊቲ አውቶቡስ ተራ → ሐረር፡፡የአድባራት አቅጣጫ ምንጭ፤- ከ ገዳማትና አድባራት ገጽ