uz
Feedback
የጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት ጎላ ቅዱስ ሚካኤል የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት (Official Channel)

የጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት ጎላ ቅዱስ ሚካኤል የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት (Official Channel)

Kanalga Telegram’da o‘tish

ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።

Ko'proq ko'rsatish
2 636
Obunachilar
+324 soatlar
+187 kunlar
+5730 kunlar
Postlar arxiv
በዓለ -ጥምቀት (በዓለ-ኤጲፋንያ) ጥር አስራ አንድ በዚች ቀን የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከአጥማቂው ዮሀንስ ዘንድ በዮርዳኖስ ወንዝ ውኃ ተጠመቀ። ይችም እለት በዮናኒ ቋንቋ ኤጲፋንያ ትባላለች ትርጓሜውም "መለኮት የተገለጠበት ማለት ነው። "ልዩ የሆነች የሶስትነቱን ምስጢር ገልጦባታልና አብ ከሰማይ ሆኖ የምወደው በርሱ ደስ የሚለኝ ልጄ ይህ ነው እርሱን ስሙት እያለ ሲመሰክር ወልድም በዮርዳኖስ ወንዝ ቁሞ ሳለ መንፈስ ቅዱስም በነጭ ርግብ አምሳል በወልድ ራስ ላይ ሲቀመጥ ይህ አጥማቂው ዮሀንስ እንደመሰከረ። እንዲህ ሲል ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተጠምቆ ከውኃ በወጣ ጊዜ ወዲያውኑ ሰማይ ተከፈተ መንፈስ ቅዱስም በርግብ አምሳል ወረዶ በጌታችን ራስ ላይ ተቀመጠ ከሰማይም እንዲህ የሚል ቃል መጣ ይህ የምወደው በእርሱ ደስ የሚለኝ ልጄ ነው እርሱንም ስሙት። በዚች እለት ጌታችን ራሱን ገልጦአልና ከዚህ በፊት ሰላሳ አመት ያህል ራሱን አልገለጠም ነበር ግን በዚች እለት ለእስራኤል ልጆች ራሱን ገለጠ እነሆ የእግዚአብሔር በግ የአለምን ኃጢአት የሚያስወግድ ብሎ መጥምቁ ዮሀንስ እንደገለጠው የከበረ ወንጌል ምስክር ሆነ። እኔ አላውቀውም ነበር ነገር ግን እስራኤል ያውቁት ዘንድ በውኃ ላጠምቅ ስለዚህ መጣሁ አለ። በዚህም በዓል የእግዚአበሄር ልጅ የክርስቶስ የጌትነቱ ክብር ተገልጧል እርሱም የአለሙን ሁሉ ሀጢአት ለማስወገድ የሚሰዋ የእግዚአብሔር አማናዊ በግ ነው። ስለዚህም ይህ በዓል በክርስቲያን ወገኖች ሁሉ ዘንድ የከበረና ከፍ ከፍ ያለ ሆነ በርሱም የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በጥምቀቱ በአከበረው ውኃ ይነፁበታል የተቀበሉትንም ንፅህና ጠብቀው ቢኖሩ በውስጡ የኃጢአታቸውን ስርየት ያገኛሉ። ስለዚህም ከክፉ ነገር ሁሉ ተጠብቀን የፈጣሪያችንና የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን የቸርነቱን ብዛት ልናመሰግን ይገባናል እርሱ ስለ እኛ ሰው ሆኖ ከኃጢአታችን አድኖናልና። ለእርሱም ከቸር አባቱ ሕይወት ከሆነ መንፈስ ቅዱስም ጋር ክብር ምስጋና ስግደትም ይሁን ዛሬም ዘወትርም ለዘላለሙ አሜን። ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው። https://t.me/finotebirhan12 የዩቲዩብ ቻናላችን https://youtube.com/@finotebirhan12 የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ።     ለሰ/ት/ቤታችን አባላትና ተባባሪዎቻችን በሙሉ   ዘመኑ በሚጠይቀው የአገልግሎት ደረጃ ለሰው ልጆች በሙሉ ተደራሽ መሆን የቅድስት ቤ/ክ እና የሰንበት ት/ቤት ድርሻ ጉልህ እንደመሆኑ መጠን ቴክኖሎጂን ተጠቅሞ ወንጌልን ለማዳረስ አሁን የምንሰጠው አገልግሎት በቂ አይደለም ከዚህ በተሻለ ለማገልገል ይረዳን ዘንድ የሰ/ት/ቤቱን ሚዲያ ክፍል ማደራጀት የሁላችንም ግዴታ ነው ስለዚህ እርስዎም ለዚህ የወንጌል አገልግሎት የበኩልዎን ድርሻ ይወጡ አሻራዎትን ያሳርፉ እያልን ለተሳትፎት  የምስጋና ትኬቶች አዘጋጅተናል   ባለ 100 ብር   ባለ 200 ብር   ባለ 500 ብር  እነዚህን ትኬቶች አቅማችሁ በቻለው መጠን እየገዛችሁ በተጨማሪ የሰ/ት/ቤቱን ሚዲያ ክፍል ይጠቅማል ብላችሁ የምታስቡትን ማቴሪያል በማምጣት   - በገንዘብ እና  በሃሳብ እንዲሁም በጸሎት ይደግፉን። በገንዘብ ለመደገፍ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000197609269 አካውንት ቁጥር ሩት ሞገስ፣ካሳሁን እሸቱ፣ደረጄ ኤቢሳ  በሚል የአቅሞትን በመለገስ ሚዲያ ክፍሉን ያደራጁ    ስለምታደርጉልን ነገር ሁሉ አስቀድመን በእግዚአብሔር ስም እናመሰግናለን የአባቶቻችን አምላክ ሃሳባችሁን ይሙላላችሁ በሰጣችሁት! አስባችሁ ባወጣችሁት ሁሉ ክብር ይስጥልን ቅዱስ እግዚአብሔር ቤታችሁን በፍቅር  በበረከት ይሙላ ። መልካም የጥምቀት በዓል ይሁንላችሁ። ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው። https://t.me/finotebirhan12 የዩቲዩብ ቻናላችን https://youtube.com/@finotebirhan12 የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1

የተከበራችሁ የጥምቀት ዘማርያን በሙሉ አገልግሎት የፈጸምንበትን ልብሰ ስብሐት (የአገልግሎት ልብስ) የቃና ዘገሊላ በዓል ከተጠናቀቀ በኋላ ከእለቱ ጀምሮ እስከ አንድ ሳምንት እሑድ (ከ12/05/16 - 19/05/16) ድረስ ንብረት ክፍል በመምጣት እንድትመልሱ እናሳስባለን። ሒሳብና ንብረት አስተዳደር ክፍል ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው። https://t.me/finotebirhan12 የዩቲዩብ ቻናላችን https://youtube.com/@finotebirhan12 የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1

ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው። https://t.me/finotebirhan12 የዩቲዩብ ቻናላችን https://youtube.com/@fino
ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው። https://t.me/finotebirhan12 የዩቲዩብ ቻናላችን https://youtube.com/@finotebirhan12 የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1

በዓለ ከተራ ከተራ ምንድን ነው? ከተራ 'ከበበ' ካለው የግእዝ ግሥ የወጣ ነው፡፡ ፍችው ውኃ መከተር፣ መገደብ ማለት ነው፡፡ በጥምቀት ዋዜማ ታቦተ ሕጉ ከቤተ መቅደስ ወጥቶ ውኃ ባለበት አካባቢ ስለሚያድር የየአጥቢያው ሕዝብ እየተሰበሰቡ በወንዝ ዳር ወይም በምንጭ አካባቢ ድንኳን ይተከላሉ፡፡ ድንኳንም ከሌለ ዳስ ሲጥሉ ይውላሉ፡፡ የምንጮች ውኃ እንዲጠራቀም ይከተራሉ (ይገድባሉ) ጉድጓድ እየተቆፈረ ውኃው እንዳይሄድ በመገደብ ለመጠመቂያ (ለጥር 11) ዝግጁ የሚያደርጉበት ዕለት ነው፡፡ በተጨማሪ  በአቅራቢያ የሚገኙት ቤተክርስቲያናት ተሰብስበው ከዚሁ ከተቆፈረው ገንዳ ወይም ከተገደበው ጅረት  አጠገብ ባለው ዳስ ወይም ድንኳን ታቦቶቻቸውን ያሳድራሉ ሊቃውንቱም በዚያው እግዚአብሔርን በማህሌት ሲያመሰግኑ ያድራሉ። በበዓለ ጥምቀት የታቦታቱ ወደ ወንዝ መውረድ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ በእደ ዮሐንስ ለመጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ የመሄዱ ምሳሌ ነው፡፡ ታቦቱ የጌታችን፣ ምሳሌ ሲሆኑ ካህናቱ የመጥምቁ ዮሐንስ ምሳሌ ናቸው፡፡ መዘምራኑና ሕዝቡ ደግሞ ዮሐንስ ያጠመቃቸው ሕዝቦች ምሳሌዎች ናቸው፡፡ መልካም የከተራ በዓል ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው። https://t.me/finotebirhan12 የዩቲዩብ ቻናላችን https://youtube.com/@finotebirhan12 የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1