Birhan Ber School 2026 GC
Kanalga Telegram’da o‘tish
"The children are our future.Teach them well and let them lead the way.Show them all the beauty they possess inside"Whitney Houston
Ko'proq ko'rsatish928
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
+27 kun
+230 kun
Postlar arxiv
በሀገር ደረጃ የሚገኝ ሰላም እንደግለሰብ እና በትምህርት ላይ ያለው ጠቀሜታ በአጭሩ፡
1. እንደ ግለሰብ (ለተማሪዎች፣ መምህራን እና ወላጆች)፦
የአእምሮ ሰላም፦ ከፍርሃትና ስጋት ነፃ ሆኖ ሙሉ ትኩረትን በትምህርትና ማስተማር ላይ ማድረግ ያስችላል።
የማይቋረጥ ትምህርት፦ ትምህርት ሳይቋረጥ በጊዜው አጠናቆ ለተሻለ ደረጃ ለመድረስ ይረዳል።
የወላጆች እረፍት፦ ወላጆች የልጆቻቸውን ደህንነት ሳይሰጉ በስራቸው ላይ እንዲያተኩሩ ያደርጋል።
2. በትምህርት ሥርዓቱ ላይ፦
የመሠረተ ልማት ደህንነት፦ ትምህርት ቤቶች እና ቁሳቁሶች ሳይወድሙና ሳይበላሽ ለረጅም ጊዜ አገልግሎት እንዲሰጡ ያደርጋል።
የትምህርት ጥራት፦ የትምህርት ጊዜና ካሪኩለም ሳይስተጎል በትክክል እንዲፈጸም ያስችላል።
ሀብትን ለትምህርት ጥራት ማዋል፦ ለመልሶ ማቋቋም የሚወጣው ወጪ ቀጥታ ለትምህርት መሳሪያዎችና ስልጠናዎች እንዲወል ያደርጋል።
ዛሬ ካነበብኩት👍👍👍👍
From We Best👍ለነገው ትውልድ ይድረስ! ✨ካነበብኩት አካፈልኩላችሁ! tiktok.com/@webest.19
Repost from Shewa Educational Channel
በፌዴራል_ትምህርት_ሚኒስቴር_የወጣ_የተማሪዎች_አለባበስ_ስነስርዓት_መመሪያ_ሕዳር_2000ዓ:ም_pdf.pdf4.69 KB
💪💪 አይዞህ በርታ፣ ተነስ 💪💪
💪 አፈር ልሰህም ቢሆን ተነስ፦ 'ዓለም' ለደካሞች ቦታ የላትም! ሕይወት አንዳንዴ ትበረታለች፤ ካልጠበቅነው አቅጣጫ መጥታ ዘርራ ትጥለናለች፡፡ ጉልበታችን ይዝላል፣ ተስፋችን ይጨልማል፣ ምድሩም ይከብደናል። ነገር ግን ትልቁ ውድቀት መውደቁ ሳይሆን፣ ወድቆ መቅረቱ ነው፡፡ "አፈር ልሰህም ቢሆን ተነስ" የሚለው ጥሪ፣ የሽንፈትን መራራነት ቀምሰህም ቢሆን መልሰህ እንድትቆም የሚገፋፋ የነፍስ ጩኸት ነው፡፡ መሬት መላስ ማለት የመጨረሻው የውርደትና የስቃይ ጥግ ላይ መድረስ ማለት ሊሆን ይችላል። ነገር ግን አፈር የነካ ሰው ወደ ታች ዝቅ ሊል አይችልም፤ የቀረው አንድ መንገድ ብቻ ነው። እሱም፦
🧗🏽♂️ ወደ ላይ መውጣት! ውድቀትህ የጉዞህ ማብቂያ ሳይሆን፣ ይበልጥ ጠንክረህ እንድትነሳ የሚረዳህ መነሻህ ነው፡፡ ትቢያህን አራግፈህ ስትቆም፣ ካንተ በላይ ብርቱ የለም፡፡ እውነቱ መራራ ቢሆንም፣ ዓለም ለሚያለቅሱና እጅ ለሰጡ ሰዎች የራራችበት ጊዜ የለም። ቆመህ ስትታይ ሁሉም አብሮህ ከጎንህ ይቆማል፤ ወድቀህ ስትቀር ግን ብዙዎች ይረግጡሃል። ዓለም የምታከብረውና ቦታ የምትሰጠው ለታጋዮች፣ ለጽኑዎችና
ለማይበገሩ ሰዎች ነው፡፡ "ደካማ ነኝ' ብለህ ራስህን አትልቀቅ፤ በውስጥህ ያለው አንበሳ እንዲነቃ አድርገው። ከወደቅህበት ስትነሳ የምታገኘው ጠባሳ የውርደት ሳይሆን የጀግንነት ምልክት ነው፡፡ ያ ጠባሳ ምን ያህል ፈተናን እንዳለፍክና ምን ያህል ብርቱ እንደሆንክ ለዓለም የሚናገር ሕያው ምስክር ነው። አፈር የላሰ ሰው የድልን ጣዕም ከማንም በላይ ያውቀዋል። ዛሬ ላይ ያለህበት ሁኔታ ነገህ አይደለም፤ ተነስና ታሪክህን በራስህ እጅ ጻፈው፡፡ እዚህላይ ለናተ አንድ ጥያቄ ሕይወት መሬት ላይ ዘርራ ጥላችሁ ታውቃለች፣ "ተስፋ የለም" ስትላችሁስ ምን አደረጋችሁ? አፈር ልሳችሁ የተነሳችሁበትን ያንን የድል ቀን ታስታውሳላችሁ? ዛሬ ደክሞኛል ለምትሉ ሁሉ የምለው አንድ ነገር ብቻ ነው፦ ተነሱ! ዓለም የእናንተን ዳግም መቆም እየጠበቀች ነው! "ወድቆ መቅረት ሞት ነው፤ አፈር ልሶ መነሳት ግን ዳግም መወለድ ነው!"
💪 ታላቁ መፅሐፍ ሲናገር፦ "ፃድቅ ሠባቴ ወድቆ፣ ሠባቴ ይነሳል"። ይላልና፦ አይዞህ ቢደክምህም ተስፋ አትቁረጥ፣ ተነስ፣ አይዞህ በርታ !!!።
💎 ይህ ግሩፕ እየተመቻችሁ ከሆነ ሌሎች ሠዎችን አድ ያድርጉ። ለተጨማሪ መረጃዎች ማስፈንጠሪያችን፦ https://t.me/Sourceofwisdom2024http
Repost from N/a
ሐሰተኛ ገንዘብ መሥራት፣ መያዝ እና ማዘዋወር የሚያስከትለው የወንጀል ተጠያቂነት
መግቢያ
ሐሰተኛ ገንዘብ መሥራት፣ መያዝ እና ማዘዋወር በአገር ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ጉዳት የሚያደርስ ድርጊት ነው፡፡ ይህንንም ለመከላከል ድርጊቱ በወንጀል የሚያስጠይቅ እንዲሆን ተደንግጓል፡፡ በዚህ ጽሑፍ ሐሰተኛ ገንዘብ መሥራት፣ መያዝ፣ ማስቀመጥ እና ማዘዋወር የሚያስከትለውን የወንጀል ተጠያቂነት በአጭሩ እንመለከታለን።
የገንዘብ ምንነት
በኢትዮጵያ ቋንቋዎች እና ሥነ-ጽሑፍ ጥናት ምርምር ማዕከል መዝገበ ቃላት (1993፣ ገጽ 505) መሠረት ገንዘብ በመግዛትና በመሸጥ ሂደት ውስጥ በሻጭና በገዥ መካከል ተቀባይነት ያለው ለመገበያያ የሚያገለግል ነገር፣ የተወሰነ ልኩ ላዩ ላይ የታተመበት የሳንቲም ወይም የወረቀት መገበያያ ነው፡፡
የሐሰተኛ ገንዘብ ምንነት
ሐሰተኛ ገንዘብ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የወንጀል ሕግ ላይ ትርጉም ያልተሰጠው ቢሆንም ሐሰተኛ ገንዘብን አስመልክቶ ከተደነገጉት የወንጀል ድንጋጌዎች ይዘት በመነሳት ሐሰተኛ ገንዘብ ማለት ሕጋዊ የመገበያያ ገንዘብ ሆነው እንዲያገለግሉ በሕግ የመገበያያ ገንዘቦችን የመሥራት ወይም የማሠራት ሥልጣን ባለው አካል አማካኝነት ወይም ፍቃድ ሰጪነት ከተሠሩት የመገበያያ ገንዘቦች ጋር ተመሳስለው የተሠሩ የብር ኖቶች መሆናቸውን መረዳት ይቻላል፡፡ የአንድ አገር ገንዘብ ሊሠራ የሚችለው በአገሩ መንግሥት ነው፡፡ ለምሳሌ፡- በአገራችን በብሔራዊ ባንክ አዋጅ ቁጥር 1359/2017 አንቀጽ 6(15) መሠረት ገንዘብ የማተም፣ የመቅረጽ፣ የማሰራጨት ወይም የማሳተም፣ የማስቀረጽ እና የማሰራጨት ሥልጣን የተሰጠው ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ነው፡፡
የወንጀል ተጠያቂነት
ሐሰተኛ ገንዘቦችን የመሥራት፣ መያዝ፣ ማስቀመጥ እና የማዘዋወር ድርጊት በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የወንጀል ሕግ ከአንቀጽ 356 እስከ አንቀፅ 362 ባሉት ድንጋጌዎች መሠረት የወንጀል ተጠያቂነትን የሚያስከትል ድርጊት ነው፡፡ በመሆኑም
በኢትዮጵያ ወይም በውጪ አገር እንደእውነተኛ አድርጎ ለማዘዋወር በማሰብ ሕጋዊ መገበያያ የሆኑትን ገንዘቦች ያለ ፈቃድ መሥራት ወይ አስመስሎ መሥራት ከ5 (አምስት) ዓመት በማያንስ ጽኑ እስራት እንደሚያስቀጣ በወንጀል ሕጉ አንቀፅ 356 ተደንግጎ ይገኛል፡፡
ሕጋዊ መገበያያ የሆኑትን ገንዘቦች ከትክክለኛ ዋጋቸው በላይ በሆነ ዋጋ እንዲዘዋወሩ ለማድረግ በማሰብ መልካቸውን መለወጥ፣ እውነተኛ መልካቸው ላይ ሌላ ነገርን መጨመር፣ ቀለማቸውን መለዋወጥ ወይም በሌላ ዓይነት ዘዴ በኢትዮጵያ ወይም በውጭ አገር ወደ ሐሰተኛነት መለወጥ በወንጀል ሕግ አንቀጽ 357 መሠረት ከ15 (አስራ አምስት) ዓመት በማይበልጥ ጽኑ እስራት እንደሚቀጣ ተደንግጓል፡፡ በተመሳሳይ በሜካኒካል፣ በፊዚካል ወይም በኬሚካል ወይም በማንኛውም ሌላ ዘዴ ተጠቅሞ የሕጋዊ ገንዘቦችን ዋጋ ዝቅ ማድረግም ከ10 (አስር) ዓመት በማይበልጥ ጽኑ እስራት የሚያስቀጣ ነው (አንቀጽ 358)፡፡
በወንጀል ሕግ አንቀጽ 359 መሠረት ማንም ሰው ሐሰተኛ የሆኑ ወይም ዋጋቸው ዝቅ እንዲል የተደረጉ ገንዘቦችን እውነተኛ ወይም ሙሉ ዋጋቸውን እንደያዙ አስመስሎ ራሱ እንዲገበያይባቸው ወይም እንዲዘዋወሩ ለማድረግ በማሰብ ወደ አገር ማስገባት፣ ከአገር ማስወጣት፣ መያዝ ወይም ማስቀመጥ ወይም ማቅረብ ከ15 (አስራ አምስት) ዓመት በማይበልጥ ጽኑ እስራት ያስቀጣል፡፡
ከላይ ከአንቀጽ 356 እስከ አንቀጽ 359 የተገለጹት የወንጀሎች ድርጊቶቹ የተፈፀሙት ለማዘዋወር በማሰብ እንደሆነ ግምት እንደሚወሰድ ተደንግጓል (አንቀጽ 360)፡፡
ሐሰተኛ የሆኑትን ወይም ወደ ሐሰተኛነት የተለወጡትን ገንዘቦች እውነተኛ አስመስሎ ወይም ከተወሰነው የበለጠ ዋጋ እንዳላቸው አስመስሎ በኢትዮጵያ ውስጥ ወይም ከአገር ውጭ ማዘዋወር በአንቀጽ 361 መሠረት ከ10 (አስር) ዓመት በማይበልጥ ጽኑ እስራት ያስቀጣል፡፡ እንዲሁም ዋጋቸው የተቀነሰውን ገንዘቦች ሙሉ ዋጋ እንደያዙ አስመስሎ እንዲዘዋወሩ ማድረግ ከ5 (አምስት) ዓመት በማይበልጥ ቀላል እስራት የሚያስቀጣ ይሆናል፡፡
ወንጀል አድራጊው ገንዘቡን እውነተኛ ነው በሚል እምነት ወይም በትክክለኛ ዋጋው ከተቀበለ በኋላ ሐሰተኛ መሆኑን ወይም ዋጋው መቀነሱን እያወቀ ከኪሳራ ለመዳን ሐሰተኛውን ወይም ወደ ሐሰት የተለወጠውን ገንዘብ ማዘዋወር በቀላል አስራት የሚያስቀጣ ሲሆን ዋጋው የተቀነሰውን ገንዘብ ሙሉ ዋጋ እንዳለ በማስመሰል ማዘዋወር በመቀጮ የሚያስቀጣ ይሆናል።
ከላይ የተገለጹት ወንጀሎች የተፈጸሙበት የገንዘብ መጠን ማነሱ ከወንጀል ተጠያቂነት አያስመልጥም፡፡ ይልቁንም ሕጉ ባስቀመጠው መሠረት የገንዘቡ መጠን ትንሽ ከሆነ በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 362 መሠረት ቅጣቱ ቀላል እስራት ይሆናል፡፡
ወንጀል ፈጻሚው የማታለል ሀሳብ ባይኖረውም ገንዘቦችን በማስመሰል መሥራት፣ በማስታወቂያነት አስመስሎ ማውጣት ወይም አምሳያ አድርጎ እንዲዘዋወር ለማድረግ በማሰብ የማሳሳት አደጋ የሚፈጥር ወይም ለመፍጠር የሚችል ከሆነ እንዲሁም እነዚህኑ መስለው የተሠሩትን ገንዘቦች ወደ አገር ማስገባት፣ ከአገር ማስወጣት፣ በአደራ በመቀበል፣ ለሽያጭ ወይም በስጦታ ማቅረብ ወይም እንዲዘዋወሩ ማድረግ በሕጉ አንቀጽ 369 መሠረት በመቀጮ ወይም ሁኔታው ለማሳሳት ወይም ለማታለል በተለይ የሚያሰጋ በሆነ ጊዜ ከሶስት ወር በማይበልጥ ቀላል እስራት ያስቀጣል፡፡
እነዚህን የሐሰት ገንዘቦች ከመሥራት ጋር በተገናኘ ሌላው መታወቅ ያለበት ነገር ማንም ሰው አግባብ ያለው ባለሥልጣን ፈቃድ ሳያገኝ ለገንዘብ ማተሚያ ወይም መሥሪያነት የሚያገለግሉትን መሣሪያዎች፣ ፎርሞች፣ ከውሮች፣ ወረቀቶች፣ ሞዴሎች እና መሰል ዕቃዎች መሥራት፣ በእጅ ማስገባት፣ ወደ አገር ማስገባት ወይም ማስወጣት፣ ለሌላ ሰው ማቅረብ ወይም አሳልፎ መስጠት እንዲሁም እነዚህ ገንዘቦች እንዲሰሩ የሚሰጡ ትዕዛዞችን መቀበል፣ መፈፀም፣ ማስፈፀም፣ ማስረከብ ወይም ለሌላ ሰው እንዲያስረክብ ማድረግ በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 370 መሠረት በቀላል እስራት ወይም በመቀጮ የሚያስቀጣ ነው፡፡
ማጠቃለያ
ሀሰተኛ የገንዘብ ኖቶች በአገር ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ጉዳት የሚያስከትሉ በመሆኑ ማንኛውም አካል የገንዘብ ኖቶችን አስመልክቶ ከሚፈፀም ወንጀል መቆጠብ ይጠበቅበታል፡፡ ይህ ሳይሆን ቀርቶ ወንጀሉን ተፈፅሞ ከተገኘ ግን ፈፃሚው ከላይ በተቀመጠው መሠረት በወንጀል ተጠያቂነት ይሆናል፡፡
በንቃተ ሕግ ትምህርትና ሥልጠና ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ
#NGAT
አገር አቀፍ የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ነሐሴ 20 እና 21/2018 ዓ.ም ይሰጣል፡፡
ተመዝጋቢዎች Username፣ Password እና Entrance Ticket ለማግኘት የኢሜይል አድራሻችሁን መጎብኘት አትዘንጉ።
@tikvahuniversity
✅በህይወታችን ልንማርባቸው የሚገቡ ጠቃሚ #️⃣አባባሎች
1️⃣. ጠንካራ ሰው ሁን ማለት አትወደቅ ማለት አይደለም ወድቀህ መነሳትን ልመድ ማለት እንጂ!
2️⃣. ዝም በል ማለት አትናገር ማለት አይደለም ሌሎችን ለመስማትም ጆሮ ስጥ ማለት እንጂ!
3️⃣. ሆዳም አትሁን ማለት አትብላ ማለት አይደለም በሰዎች ሃቅ ላይ አትለፍ ማለት እንጂ!
4️⃣. ይቅርታ አድርግ ማለት አልተጎዳህም ማለት አይደለም በሆድ ቂም መያዝ ሌላ ጉዳት ስለሆነ እንጂ!
5️⃣ .ጠላትህን ውደድ ማለት ጠላት ጥሩ ነው ማለት አይደለም ከጥላቻ ይልቅ ፍቅር ስለሚያሸንፍ እንጂ!
6️⃣. ደስተኛ ሁን ማለት ሁሉ ይኑርህ ማለት አይደለም ባለህ ነገር ደስ ይበልህ ማለት እንጂ
7️⃣. ስራህን ወደድ ማለት የምትሰራው ስራ ጥሩ ነው ማለት አይደለም ነገ ጥሩ ስራ እንዲኖርህ ዛሬ የምትሰራውን ወደድ ማለት እንጂ!
8️⃣. ወሬኛ አትሁን ማለት አታውራ ማለት አይደለም ምንም ስለማታውቀው ነገር አታውራ ማለት እንጂ!
9️⃣ .ትሞታለህ ማለት አትስራ ማለት አይደለም ምንም ቁም ነገር ሰትሳራ አትሙት ማለት እንጂ!
1️⃣0️⃣. ብቸኛ አትሁን ማለት ሮጠህ ትዳር ያዝ ማለት አይደለም ልብህን ጊዜህን ያለህን ሁሉ አሳልፈህ ለመስጠት ዝግጁ ሁን ማለት እንጂ!
1️⃣1️⃣.አዋቂ ሁን ማለት እንደገና ት/ቤት ሂድ ማለት አይደለም ብልህ ሁን ማለት እንጂ!
🔤🔤🔤🅰️
🔤🔤🔤
✅የተማሪዎች አለኝታ!
⬇️⬇️⬇️⬇️
https://t.me/dam76
ተፈጥሮ በተለያየ መንገድ ታስተምረናለች; እኛም በጥበብ እንኑርባት። ከንስር አኗኗር የምንወስደውን በጥንቃቄ እንመልከት።
🦅🦅 ንስሩ እና አዲሱ ክንፍ 🦅🦅
🦅 በአንድ ረጅም ተራራ ጫፍ ላይ የሚኖር አንድ ታላቅ ንስር ነበር። ይህ ንስር ለብዙ ዓመታት በሰማይ ላይ በነፃነት እየበረረ፣ ማዕበሎችንና ኃይለኛ ነፋሳትን እያሸነፈ የሰማዩ ንጉሥ ሆኖ ኖሯል። ነገር ግን ዕድሜው እየገፋ ሲሄድ አንድ ትልቅ ፈተና ገጠመው። ምንቃሩ በጣም ስለረዘመና ስለታጠፈ ምግብ ማደን አቀተው፤ ጥፍሮቹ ስለደነዘዙ ማናቸውንም ነገር መጨበጥ አልቻለም። ከሁሉም በላይ ደግሞ ክንፎቹ በላባዎች ብዛት ስለከበዱት እንደ ድሮው ወደ ሰማይ መጥቀስ አቅቶት ዝቅ ብሎ መብረር ጀመረ። በዚህ ጊዜ ንስሩ በሕይወቱ ትልቅ ምርጫ ፊት ቆመ፦ ወይ ተስፋ ቆርጦ ሞቱን መጠበቅ፣ ወይም ደግሞ በጣም ከባድና አሳማሚ የሆነውን የምንጭ ማደስ ጉዞ መጀመር።
ንስሩ ሁለተኛውን መረጠ! ወደ ተራራው ጫፍ በመውጣት ማንም በማያየው ዋሻ ውስጥ ተሸሸገ። መጀመሪያ ምንቃሩን በኃይል ከአለቱ ጋር በመምታት ሰበረው። አዲሱና ስለታሙ ምንቃሩ እስኪበቅል ድረስ ለብዙ ቀናት በራብና በሕመም ታገሠ። አዲሱ ምንቃሩ ሲበቅልለት፣ ያንን በመጠቀም የደነዘዙ ጥፍሮቹን አንድ በአንድ ነቃቅሎ ጣላቸው። አዳዲስ ጥፍሮች በቀሉለት። በመጨረሻም፣ በሰውነቱ ላይ የከበዱትንና ያረጁትን የክንፍ ላባዎቹን በሙሉ በምንቃሩ እየነጨ አረገፋቸው። ይህ አሳማሚ ሂደት አምስት ወራትን ፈጀ። ነገር ግን ከአምስት ወራት ከባድ ትግልና ሕመም በኋላ፣ ንስሩ ሙሉ በሙሉ አዲስ ጥፍር፣ አዲስ ምንቃርና ቀላል የሆኑ አዳዲስ ክንፎችን አገኘ! ከዋሻው ውስጥ በታላቅ ኩራት ወጥቶ ክንፎቹን ዘረጋ። ከዚያም ካለፈው በበለጠ ፍጥነትና ኃይል ወደ ሰማይ ጥቆ በመብረር ለተጨማሪ 30 ዓመታት በክብር መኖር ቻለ።
🦅 የታሪኩ መልእክት (Moral of the Story)፦
ሕይወታችን እንዲቀየርና ወደ ላቀ ስኬት ለመድረስ ካለን፣ አሮጌውንና የማይጠቅመንን አስተሳሰብ፣ ተስፋ መቁረጥንና የድሮ ስንፍናችንን አውልቀን መጣል አለብን። ያ አሮጌውን የመቀየር ሂደት ልክ እንደ ንስሩ ሊያምም ወይም መስዋዕትነት ሊጠይቅ ይችላል፤ ነገር ግን ያንን ጊዜ በትዕግሥት ካለፍነው በኋላ በታላቅ ኃይልና በአዲስ ስኬት ወደ ሰማይ እንጠቅሳለን! 🔄
💎 ይህ ግሩፕ እየተመቻችሁ ከሆነ ሌሎች ሠዎችን አድ ያድርጉ። ለተጨማሪ መረጃዎች ማስፈንጠሪያችን፦ @addisTDPoffice
✔️ተማሪዎች ሆይ የ2019 የት/ት ዘመን ጥናት አሁኑኑ ጀምሩ መጽሀፍት ለማግኘት :-
✅የቅድመ 1ኛ መጽሀፍ
⬇️⬇️⬇️
https://t.me/dam76/3693?single
✅የቅድመ አንደኛ የእንግሊዘኛ መጽሀፍ
⬇️⬇️⬇️
https://t.me/dam76/4609?single
✅የ1ኛ ክፍል መጽሀፍ
⬇️⬇️⬇️
https://t.me/dam76/3716?single
✅የ2ኛ ክፍል መጽሀፍ
⬇️⬇️⬇️
https://t.me/dam76/3709?single
✅የ3ኛ ክፍል መጽሀፍ
⬇️⬇️⬇️
https://t.me/dam76/3702?single
✅የ4ኛ ክፍል መጽሀፍ
⬇️⬇️⬇️
https://t.me/dam76/3685?single
✅የ5ኛ ክፍል መጽሀፍ
⬇️⬇️⬇️
https://t.me/dam76/3678?single
✅የ6ኛ ክፍል መጽሀፍ
⬇️⬇️⬇️
https://t.me/dam76/3670?single
✅የ7ኛ ክፍል መጽሀፍ
⬇️⬇️⬇️
https://t.me/dam76/3659?single
➡️የ8ኛ ክፍል መጽሀፍ
⬇️⬇️⬇️
https://t.me/dam76/3641?single
✅Afan Oromo Grade 3-8 text books
⬇️⬇️⬇️
https://t.me/dam76/3099?single
✅ከ9ኛ-12ኛ ክፍል መጽሀፍ ለማግኘት
⬇️⬇️⬇️
https://t.me/dam76/3720
🔐🔐 ገልብጠህ አንብበው 🔐🔐
🔐 አንድ ቀን፣ አንድ ትንሽ ልጅ ከትምህርት ቤት ደብዳቤ ይዞ ወደ ቤት መጣ፣ ለእናቱም "መምህሬ ይህንን ደብዳቤ ለአንቺ ብቻ እንድሰጥሽ ላከኝ" አላት።
እናቱም ከፈተችው፣ በቅድሚያ በፀጥታ አነበበችው... ከዚያም አይኖቿ በእንባ ተሞሉ። እናትም በጥልቀት ካሰላሰለች በኋላ ትንሽ ትንፋሽ ወስዳ ደብዳቤውን ለልጇ ጮክ ብላ አነበበችለት፤ እንዲህም ስትል፡- "ልጅሽ በጣም ሊቅ ነው፣ ትምህርት ቤታችን ለእሱ እውቀት የሚመጥን አይደለም፣ እና የሚገባውን ትምህርት ስለማንሠጠው እባክሽ እራስሽ አስተምሪው።" በልጇ ላይ የተደረገው ነገር እሷንም፣ ልጁንም ቢያሳዝንም እርሷ ግን ልጇን በቤት ውስጥ ለማስተማር ወሰነች።
🔐 ዓመታት አለፉ ...። ልጁም አደገ... እና በክፍለ ዘመኑ ውስጥ ካሉት እጅግ ጎበዝ የፈጠራ ሰዎች መካከል አንዱ ሆነ። በመሆኑም፦ ለዓለም መብራት፣ ለፎኖግራፍ፣ ለቴሌግራፍ፣ ለካሜራ እና ለሌሎችም ፈጠራዎች የመፍትሔ ሠው ነበር።
ልጁም እናቱ ከሞተች ከብዙ ዓመታት በኋላ፣ በቤቱ ውስጥ በማስታወሻዎች የተሞላ አሮጌ ሣጥን አገኘ። በሳጥኑ ውስጥም በጥንቃቄ የተጣጠፈ አንድ ደብዳቤ ተመለከተ። ያኔ በልጅነቱ መምህሩ ለእናቱ ብቻ እንዲሠጥ የሰጠው ደብዳቤ ነበር። አነበበው እንዲህ ይላል “ልጅሽ አቅም የለውም፣ የአዕምሮ ችግር አለበት፣ ወደ እኛም ትምህርት ቤት እንዲመለስ ፈፅሞ አንፈቅድለትም።” የሚል ነበረ።
🔐 ለካንስ እናቱ ደብዳቤውን ገልብጣ ነበር ያነበበችለት። ያ ልጅ የአሁኑ "ቶማስ ኤዲሰን" ነበር።
ደብዳቤውን አንብቦ ሲጨርስ ለረጅም ሰዓት አለቀሰ። ከዚያም በማስታወሻው ላይ እንዲህ ሲል ፃፈ፡- “ቶማስ ኤዲሰን ጉድለት እንዳለበት የሚታሰብ ልጅ ነበር… ለልዩ እናቴ ምስጋና ይግባትና ያ ልጅ ዛሬ ሊቅ ሆነ።”
🔐 የሰው ልጅን (በተለይ ልጆችን) የምንመለከትበት መንገድ ዕጣ ፈንታቸውን ሊለውጥ ይችላል። እናቱ ደብዳቤውን ገልብጣ ባታነብለት፣ በቤቷ ውስጥ አቅሟን አሟጣ ባታስጠናው ኖሮ፤ አንተ አትችል፣ አቅም የለህም፣ ጉድለት አለብህ፣ አርፈህ ቁጭ በል እያለች ብታሳድገው ኖሮ፤ "ቶማስ ኤዲሰን" ዛሬ ማንም፣ ምንም፣ ባልነበረ ነበር።
ከ"ምክረ ትምህርት"
💎 ይህ ግሩፕ እየተመቻችሁ ከሆነ ሌሎች ሠዎችን አድ ያድርጉ። ለተጨማሪ መረጃዎች ማስፈንጠሪያችን፦ @addisTDPoffice
በጣም የሚገርም አስተማሪ ስንፀ ሀሳብ ይዟል።
Repost from Addis Ababa Education Bureau
የመምህርነት የስራ ቅጥር ማስታወቂያ!
(ሀምሌ 21/2018 ዓ.ም) መመዝገቢያ ሊንኮች
1. ለ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች
https://docs.google.com/forms/d/1RRFzFMb2HEoCyRp_ye5E-joooyGYzpAMfEvFBQdbJJs/edit
2. ከቅድመ አንደኛ ደረጃ እስከ 8ኛ ክፍል ላሉ ትምህርት ቤቶች
https://docs.google.com/forms/d/1exSs8OJs3UzYpyzcqQ8e13-JiczbyGR1ohmYFpdHJOY/edit
3. Barnoota Sadarkaa 1ffaan duraa hanga kutaa 8ffaa isa jala jiraniif Bara Barnootaa
https://docs.google.com/forms/d/1UXIAIH736rY4YoENoRNSmNsYkZsOJFrh6o7-G3qz53E/edit
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
