EECSF
Kanalga Telegram’da o‘tish
ይህ በ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የ ህንፃ ኮሌጅ ወንጌል አማኞች ክርስቲያን ህብረት ነው:: #ተቀዳሚ_ዐላማ፤የምንኖርለት:- •ተማሪዎችን በማገልገል የእግዚአብሔርን መንግስት ማስፋት #በዚህ_ቻናል:- ☞ የክርስቶስን አካል የ ሚያንፁ ልዩ ልዩ መልዕክቶች ይቀርባሉ:: ☞ከ ህብረቱ መሪዎችና ከ [ኢቫሱ] የ ሚተላለፉ መልዕክቶችን ያገኛሉ::
Ko'proq ko'rsatish508
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kun
Ma'lumot yo'q30 kun
Postlar arxiv
508
Pray, Care, Share
#PCS Part 1
#Prayer_leads_to_care_opening_ways_to_share_the_gospel
✍️አጭር መግለጫ ስለ PCS
📖የወንጌል የምሥራች የሰውን የዘላለም እጣ ፈንታ የሚወስን ታላቅ መልእክት ነው፡፡ ይሄን ለዘላለም ድኅነት የሆነውን የምሥራች ሊሰሙት የተገባቸው ደግሞ የሰው ልጆች ሁሉ ናቸው፡፡ የምሥራቹ አዋጅ የሚታወጅበት ሥፍራም እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ነው። በወንጌሉ አምነው የዳኑ ቅዱሳን ሁሉ የወንጌልን የምሥራች ለህዝብ ሁሉ እንዲናገሩ ተልዕኮን ተቀብለዋል፡፡
💫የወንጌልን የምሥራች በጥቅሉ በአዋጅ መልክ ( Proclamation)፣ በሙግት መልክ (Confrontational)፣ እንዲሁም ወዳጃዊ ግንኙነትን በመጠቀም ( Relational) ለሰሚዎች ማድረስ ይቻላል፡፡
✨ምንም እንኳ እንደየሁኔታውና አመቺነቱ ከላይ የተጠቀሱትን የወንጌል መናገሪያ መንገዶች ሁሉ የምንጠቀም ቢሆንም፣ በዩኒቨርሲቲና ኮሌጅ አካባቢ በብዛት ወዳጃዊ ወንጌልን የማድረስ መንገድ ጠቀሜታው የጎላ ነው፡፡ መፀለይ-መንክባከብ (መወዳጀት)-መመስከር [PCS : Pray-Care-Share] የምሥራች የሆነውን ወንጌል፣ ወዳጃዊ በሆነ መንገድ ለሰዎች ለማድረስ ዉጤታማ መንገድ ነው፡፡ (ከEvaSUE NMS 2022 Booklet የተወሰደ)
⚡️ለምን PCS?
1. የኢየሱስ ተከታዮች እንደመሆናችን መጠን ለሌሎች እንዴት መጸለይ እንዳለብን፣ እንዴት መውደድና መተሳሰብ እንዳለብን እና ክርስቶስን እንዴት ከእነሱ ጋር መካፈል እንደምንችል ተምረናል።
2. ይህ መንገድ በዓለም ዙሪያ በጣም ውጤታማ ሆኗል በተለይ ደግሞ በUniversity area እና ካምፓሶች ላይ በጣም አዋጭ ነው።
የመፀለይ-መንክባከብ (መወዳጀት)-መመስከር [PCS] ግብ ከሰዎች ጋር ለህይወት የሚሆን ግንኙነቶችን መፍጠር ነው። ህይወታችሁን እና ከዚያም ክርስቶስ እንዴት እንደለወጣችሁ የምትነግሩባቸውን መንገዶች መፈለግ፣ ሂደቱ የሚጀምረው ከክርስቶስ ጋር ለማስተዋወቅ የሚፈልጉትን ሰው በመምረጥ ነው, ከዚያ ለዚያ ሰው መፀለይ-መንክባከብ (መወዳጀት) እና መመስከር።
ለዛሬ በዚ ይብቃ፤ በቀጣዩ ክፍል Biblical Base for PCS እና እንዴት እንደምንጀምር እናያለን!
ተባረኩ!💛
#ወንጌል ስለልጁ ነው!
#ወንጌል ስለክብሩ ነው!
#ወንጌል ስለእግዚአብሄር መንግስት ነው!
እናም
#ወንጌል ኃላፊነታችን ነው!!!
#EiABC_Action_Team
#EiABC_Fellowship
508
የአምልኮ ድግስ
“በእንጨት የሚሰቀል ሁሉ የተረገመ ነው ተብሎ ተጽፎአልና ክርስቶስ ስለ እኛ እርግማን ሆኖ ከሕግ እርግማን ዋጀን፤”
— ገላትያ 3፥13
ከኮሜርስ፣ ከEIABC እና ያሬድ የሙዚቃ ባንዶች ጋር
መጋቢት 15,2016
ኢየሱስ ከፍሎታል በሚል ርዕስ ጌታን አብረን እናምልክ።
ሰዓት፡- 8፡30 ጀምሮ
ቦታ፡- ሬማ ቤተ-ክርስቲያን(https://maps.app.goo.gl/B7MawKeHwXC1MKnp6)
ሁላችሁም ተጋብዛችኃል።
508
Repost from EvaSUE |ኢቫሱ
Day2 #soc24 #Evasue Isaiah 53:5
"But he was pierced for our transgressions, he was crushed for our iniquities; the punishment that brought us peace was on him, and by his wounds we are healed."
508
Repost from EvaSUE |ኢቫሱ
Day2 #soc24 #Evasue Isaiah 53:5
"But he was pierced for our transgressions, he was crushed for our iniquities; the punishment that brought us peace was on him, and by his wounds we are healed."
508
✨✨ሰላም የተወደዳችሁ እግዚአብሔር ረድቶን ዛሬ ጥሩ ጊዜ ነበረን፣ የእግዚአብሔር ስም ይባረክ 🙏🙏🙏
ነገም በተመሳሳይ ሁኔታ ፕሮግራሙ ይቀጥላል ፤
ስለዚህም sharp 2:00 ሰዓት ላይ BUS EiABC በር ላይ ስለሚጠብቃችሁ እንድትዘጋጁ ይሁን።
💥የደርሶ መልስ 60 ብር መያዛችሁንም እንዳትረሱ።
እንወዳችኋለን ❤️❤️❤️
#EiABC_ FELLOWSHIP
