uz
Feedback
በማስተዋል ዘምሩ

በማስተዋል ዘምሩ

Kanalga Telegram’da o‘tish

⚠️ Contact us through our bot: 💬 @zemeru_bot

Ko'proq ko'rsatish
7 846
Obunachilar
+824 soatlar
+497 kunlar
+21230 kunlar
Postlar arxiv
ሳምንታዊ ተከታታይ ትምህርት የተራራው ስብከት 📍ክፍል 6 "የሚምሩ ብፁዓን ናቸው፥ ይማራሉና።" (ማቴ 5፥7) Via: ACE Bole Hermon @zemeru

ኤልሻዳይ ነህና ተመስገን ሁሉንቻይ ነህና ተመስገን መሃሪ ነህና ተመስገን ኢየሱስ ሆይ እያልኩ ልጥራህ አንተ የፍቅር ጌታ ነህ

የእምነት አባታችን ቄስ ኤልያስ ጉዲሶ ረጅም እድሜ ከጤና ጋር ተመኘን፣ እንዎዶታለን 🩷
የእምነት አባታችን ቄስ ኤልያስ ጉዲሶ ረጅም እድሜ ከጤና ጋር ተመኘን፣ እንዎዶታለን 🩷

#ምስጋና በዚህ ክረምት በሀገረስብከት ደረጃ ከሐምሌ ወር ጀምሮ በየአጥቢያው እየተደረገ ባለው የወንጌል ስርጭት ፕሮግራም ብዙ አዳዲስ ነፍሳትን ወደ እግዚአብሔር መንግስት እየጎረፉ ይገኛሉ። ይህ ወንጌል ከአንድ ነፍስ አልፎ ሙሉ ቤተሰብን እየማረከ ስለሆነ አምላካችንን እጅግ አድርገን እናመሰግናለን። ክብር ለኢየሱስ ይሁን! @zemeru

ኖሬ ኖሬ በቤትህ አገልግዬ በፊትህ ሳላይ አንተን እንዳልቀር ፍፃምዬን አሳምር እንቅፋት ብዙ ነው ፈተናው ብዙ ነው ከሰማይ ሊያስቀረኝ የሚፈልገው እንቅፋት ብዙ ነው ፈተናው ብዙ ነው ፊትህን እንዳላይ የሚሟገተው እጄን ያዝ ይኸው እጄን ያዝ አልችልም ብቻዬን ረዥም መንገድ ልጓዝ እጄን ያዝ ይኸው እጄን ያዝ አልችልም በራሴ ረዥም መንገድ ልጓዝ

ካንተ በላይ አምላክ የለም ካንተ ውጭ ሁሉም ከንቱ ነው ተመስገን እኔስ እልሃለሁ ሰላሜ የበዛው ባንተ ነው ተባረክ እኔስ እልሃለሁ መውጣቴ መግባቴ ባንተ ነው

#Doctrine የእግዚአብሔር ልጅ ማለት ? መጽሐፍ ቅዱስ ራሱን በራሱ ስተረጉም 1.ከሞት የተነሳው ከሙታን ልጁን አስነሳ(1ኛ ተስ 1፥9) ከሙታን የሥጋ ሰውነት አስነሳ(ዮሐ 2፥20) 2.የታረቅንበት ከእግዚአብሔር ጋር በልጁ ሞት ታረቀን(ሮሜ 5፥10) ከእግዚአብሔር ጋር በሥጋው ሰውነት ታረቅን(ቆላ 1፥20) 3.ለዓለም ሕይወት የተሰጠው ዓለም ሕይወት የሰጠው አንዲያ ልጁን ነው(ዮሐ 3፥16) ለዓለም ሕይወት የሰጠው ሥጋዬን ነው (ዮሐ 6፥51) 4.የሚፈርደው አብ በአንድ ስንኳ አይፈርድም ፍርድን ለወልድ(ለልጁ) ሰጥቶታል።(ዮሐ 5፥23) እግዚአብሔር ባዘጋጀው ሥጋ ማለትም በሰውነት ይፈርዳል ሐዋ 17፥31 ዕብ 10፥5 5.ወደዓለም የተላከው ወደዓለም የተላከው ልጁ ነው (1ኛ ዮሐ 4፥14) ወደዓለማ የገባው የተዘጋጀው ሥጋ ነው ዕብ 10፥5 6.ወደአብ መግባት ወደአብ የገባነው በክርስቶስ(በልጁ) ሥራ ኤፌ 2፥18 ወደቅድስት ማለትም ወደአብ የገባነው በመጋረጃው(በሥጋው ሰውነት) ነው ዕብ 10፥19 7.የኢየሱስ የብርቱ ጸሎት ወራት ልጁ ወደአብ ጮኾ ጸለየ(ሉቃ 23፥47) በሥጋው ወራት በብርቱ ጩኸት ጸለየ(ዕብ 5፥7) የሥጋው ወራት ማለት የልጅነት የድካም ወራት ማለት ነው። 8.የሞተው የሞተው ልጁ ነው ሮሜ 5፥10 የሞተው ሥጋው ነው(በሥጋ ሞተ) 1 ጴጥ 3፥18 👉በልጁ ሞት በሥጋው ሰውነት ሞት 👉ልጁን አስነሳ ሰውነትን አስነሳ 👉በልጁ ይፈርዳል በሰውነቱ ይፈርዳል 👉ልጁን ላከ ሥጋን አዘጋጀ 👉ልጁን ሰጠ ሥጋውን ሰጠ የእግዚአብሔር ልጅ ማለት የእግዚአብሔር አብ የሥጋ ሰውነት ነው። በወ/ም ሕዝቅኤል ጴጥሮስ @zemeru

ከአእላፋት ይልቅ ከወርቅ ከእንቁ የሚበልጥ በቤትህ ደጆች መኖር የቃልህን ክብር ማየት ማደሪያዎችህ ውቦች ናቸው በቤትህ ያሉ የታደሉ መልካም የበረከት ቀን ይሁንላችሁ!

ዛሬም ጌታን ላክብር በአዲስ ሕይወት ወደ ቤቱ ልግባ በእርሱ ምህረት በመንፈሱ ጸጋ ይታደስ ህይወቴ ፊቱንም ያብራልኝ ይርዳኝ መድኃኒቴ

የዋህነትን በ3 መንገዶች ልናይ እንችላለን። 1. ክፉን በመልካም ማሸነፍ 2. ክፉ ለሚያደርጉብን ሰዎች መጸለይ/መባረክ 3. በሕይወታችን ላይ የሚመጣውን ፈተና መሰሪያዬ ነው (እንደ ወርቅ ተፈትኜ የሚወጣበት ነው) በማለት በጸጋ መቀበል “የዋሆች ብፁዓን ናቸው፥ ምድርን ይወርሳሉና።” (ማቴ 5፥5) @zemeru

#ተከታታይ_ትምህርት የተራራው ስብከት 📍ክፍል 5 “የዋሆች ብፁዓን ናቸው፥ ምድርን ይወርሳሉና።” (ማቴ 5፥5) Via ACE Bole Hermon @zemeru

ምህረትህ ስለበዛልኝ ጥበቃህ ስላልተለየኝ ቸርነት ስላረክልኝ በፍቅር ስለመራኸኝ አለሁ ዛሬም በቤትህ አለሁ ኢየሱስ አለሁ ዛሬም በፊትህ አለሁ ጌታዬ

ውለታህን እያሰብኩኝ ያደረክልኝ እየቆጠርኩኝ ላመስግንህ ኢየሱስ ላመስግንህ ላመስግንህ ጌታ ሆይ ላመስግንህ

ማሰማሪያህ ውሃ ዳር እጅግ ከጥም ያረካልደስ እያለኝ በቤትህ እኖራለሁ በእቅፍህየሱስ ፍጹም ደስታዬ መንፈስህ እርካታዬለንሮዬ ጣዕም ነህ ለደስታዬ ምንጭ ነህ

ወርሃ ሐምሌ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት! ዘዳ ፲፯:፲፱፤ "አምላኩን እግዚአብሔርን መፍራት ይማር ዘንድ፥ የዚህን ሕግ ቃል ሁሉ ይህችንም ሥርዓት ጠብቆ ያደርግ ዘንድ፥ ልቡ በወንድሞቹ ላይ እንዳይኰራ ከትእ
ወርሃ ሐምሌ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት! ዘዳ ፲፯:፲፱፤ "አምላኩን እግዚአብሔርን መፍራት ይማር ዘንድ፥ የዚህን ሕግ ቃል ሁሉ ይህችንም ሥርዓት ጠብቆ ያደርግ ዘንድ፥ ልቡ በወንድሞቹ ላይ እንዳይኰራ ከትእዛዙም ቀኝና ግራ እንዳይል፥ እርሱም ልጆቹም በእስራኤል ልጆች መካከል ረጅም ዘመን ይነግሡ ዘንድ መጽሐፉ ከእርሱ ጋር ይኑር፥ ዕድሜውንም ሁሉ ያንብበው።" ይህንን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ማጥናት ከጀመርን ወዲህ ጌታ ኢየሱስ በቃሉ በኩል እየባረከን፣ እያደሰን፣ እየለወጠን ስላለ አምላካችንን እጅግ አድርገን እናመሰግናለን። ይህንን Manual ያዘጋጁትን ጌታ ኢየሱስ አብዝቶ ይባርክልን። ያልጀመራችሁ እንድትጀምሩ ከታላቅ አክብሮት ጋር ልናሳስባችሁ እንወዳለን። የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ከሁላችንም ጋር ይሁን! @zemeru

#ተከታታይ_ትምህርት የተራራው ስብከት ክፍል 4 “የሚያዝኑ ብፁዓን ናቸው፥ መፅናናትን ያገኛሉና።” (ማቴ 5፥4) Via: ACE Bole Hermon @zemeru

#የቀጠለ... "የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕግሥት፥ ቸርነት፥ በጎነት፥ እምነት፥ የውሃት፥ ራስን መግዛት ነው።" (ገላ 5፥22) 8⃣ የውሃት 9⃣ ራስን መግዛት ስለ እነዚህ ዘጠኙ የ
+1
#የቀጠለ... "የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕግሥት፥ ቸርነት፥ በጎነት፥ እምነት፥ የውሃት፥ ራስን መግዛት ነው።" (ገላ 5፥22) 8⃣ የውሃት 9⃣ ራስን መግዛት ስለ እነዚህ ዘጠኙ የመንፈስ ቅዱስ ፍሬዎች የተወሰነ መሰረታዊ ትምህርት እንዳገኛችሁ ተስፋ እናደርጋለን፤ ስለተከታተላችሁ እጅግ አድርገን እናመሰግናለን፣ ጌታ ኢየሱስ ጸጋውን ያብዛላችሁ። @zemeru

#ተከታታይ_ትምህርት የተራራው ስብከት 📍ክፍል ሶስት "በመንፈስ ድሆች የሆኑ ብፁዓን ናቸው፥ መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና።" (ማቴ 5:3) Via ACE Bole Hermon @zemeru @ACEBoleHermon

photo content

"የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕግሥት፥ ቸርነት፥ በጎነት፥ እምነት፥ የውሃት፥ ራስን መግዛት ነው።" (ገላ 5፥22) 5⃣ ቸርነት 6⃣ በጎነት 7⃣ እምነት @zemeru
+2
"የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕግሥት፥ ቸርነት፥ በጎነት፥ እምነት፥ የውሃት፥ ራስን መግዛት ነው።" (ገላ 5፥22) 5⃣ ቸርነት 6⃣ በጎነት 7⃣ እምነት @zemeru