uz
Feedback
ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

Kanalga Telegram’da o‘tish

ጤና ነክ ጥያቄ ካለዎት፣ በጽሑፍ በቴሌግራም ብቻ ይሄንን➡️  t.me/Dr_Sofonias በመጫን ያስቀምጡልኝ ሙያዊ ምላሽ ለመስጠት ጊዜ ሊወስድብኝ ስለሚችል፣ በትዕግስት ይጠብቁኝ ​📢 ለማስታወቂያ/ስፖንሰርሺፕ: ​ለስፖንሰርሺፕና ምርትዎ በሙያዊ ምክር እንዲተዋወቅ ከፈለጉ፣ ይሄንን ➡️ t.me/MASTAWKIYA በመጫን ያናግሩን

Ko'proq ko'rsatish

📈 Telegram kanali ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias analitikasi

ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias (@drsofonias) Amxar til segmentidagi kanali faol ishtirokchi. Hozirda hamjamiyat 19 989 obunachidan iborat bo'lib, Tibbiyot toifasida 1 154-o'rinni va Efiopiya mintaqasida 1 680-o'rinni egallagan.

📊 Auditoriya ko‘rsatkichlari va dinamika

невідомо sanasidan buyon loyiha tez o‘sib, 19 989 obunachiga ega bo‘ldi.

25 Iyun, 2026 dagi oxirgi ma’lumotlarga ko‘ra kanal barqaror faollikka ega. Oxirgi 30 kunda obunachilar soni -558 ga, so‘nggi 24 soatda esa -23 ga o‘zgardi va umumiy qamrov yuqori darajada qolmoqda.

  • Tasdiqlash holati: Tasdiqlanmagan
  • Jalb etish (ER): Auditoriya o‘rtacha 22.78% darajada jalb etiladi. Nashrdan keyingi dastlabki 24 soatda kontent odatda umumiy obunachilar sonining 5.94% ini tashkil etuvchi reaksiyalarni to‘playdi.
  • Post qamrovi: Har bir post o‘rtacha 4 556 marta ko‘riladi; birinchi sutkada odatda 1 188 ta ko‘rish yig‘iladi.
  • Reaksiyalar va o‘zaro ta’sir: Auditoriya faol: har bir postga o‘rtacha 11 ta reaksiya keladi.

📝 Tavsif va kontent siyosati

Muallif resursni shaxsiy fikrni ifoda etish maydoni sifatida ta’riflaydi:
ጤና ነክ ጥያቄ ካለዎት፣ በጽሑፍ በቴሌግራም ብቻ ይሄንን➡️  t.me/Dr_Sofonias በመጫን ያስቀምጡልኝ ሙያዊ ምላሽ ለመስጠት ጊዜ ሊወስድብኝ ስለሚችል፣ በትዕግስት ይጠብቁኝ ​📢 ለማስታወቂያ/ስፖንሰርሺፕ: ​ለስፖንሰርሺፕና ምርትዎ በሙያዊ ምክር እንዲተዋወቅ ከፈለጉ፣ ይሄንን ➡️ t.me/MASTAWKIYA በመጫን ያናግሩን

Yuqori yangilanish chastotasi (oxirgi ma’lumot 26 Iyun, 2026 da olingan) sababli kanal doimo dolzarb va katta qamrovli bo‘lib qoladi. Analitika auditoriya kontent bilan faol hamkorlik qilishini, uni Tibbiyot toifasidagi muhim ta’sir nuqtasiga aylantirishini ko‘rsatadi.

19 989
Obunachilar
-2324 soatlar
-1207 kunlar
-55830 kunlar
Postlar arxiv
7 የወይራ ዘይት ጥቅሞች በጥንት ጊዜ የወይራ ዘይት ፈሳሹ ወርቅ ይባል ነበር። ከወይራ ፍሬ ነው የሚሰራው። ታዲያ የወይራ ዘይት ከኩሽና አልፎ የውበት ሳሎን ድረስ ሰተት ብሎ በመግባት በርካታ ምትሃታዊ ጥቅሞችን እየሰጠ ይገኛል። ☑️ ውድ የኢትዮጤና ቤተሰቦች እስኪ የተወሰኑትን አብረን እንመልከት:- 1. ለሜካፕ ማስለቀቂያነት ያገለግላል ጥቂት የወይራ ዘይትና ጥጥ ብቻ ነው የሚያስፈልግዎ። ታዲያ የወይራን ዘይት ለየት የሚያደርገው ከሌሎች የሜካፕ ማስለቀቂያዎች በተለየ መልኩ ሜካፕ እያስለቀቁ በተመሳሳይ ሰዓት ቆዳዎ እርጥበትን እንዲላበስ ማድረግ ማስቻሉ ነው። 2. ቆዳን እርጥበት ለማላበስ የወይራ ዘይት በከፍተኛ ሁኔታ በአንቲኦክሲዳንት የበለፀገ ስለሆነና በውስጡም ቫይታሚን ኢ ስላካተተ ገላዎን በሚታሹበት ጊዜ ቢጠቀሙት ቆዳዎን ዘልቆ በመግባት እርጥበት እንዲኖረው ማድረግ ይችላል። በተለይ ደረቅ ያለ ቆዳ ላላቸው ሰዎች የወይራ ዘይት ተመራጭ ነው። 3. የተቆራረጠ ሰውነትንና ለማለስለስና ጥፍርን ለማሳደግ አንዳች ቦታ ሰውነታችን ተቆርጦ የመሻከር ስሜት ካለው በወይራ ዘይት ማሸት እንዲለሰልስ ያደርገዋል። በተለይ በመደበኛነት ማታ ማታ ይህን አካባቢ በዚህ ዘይት ማሸት ትልቅ ለውጥን ያስገኛል። በተጨማሪም ጥፍርን ለማሳደግ የወይራ ዘይት ተመራጭ ነው። በቫይታሚን ኢ የበለፀገ ስለሆነ በቆዳችን በቶሎ የመመጠጥ ባህር ይኖረዋል። ይህ ደግሞ ለጥፍር እድገት ወሳኝ ነው። የተሰባበረ የተጎዳ ጥፍር ካልዎት በወይራ ዘይት ቢያንስ በሳምንት አንድ ጊዜ ለ20 ደቂቃዎች ቢያሹት ትልቅ ለውጥ ማየት ይችላሉ። 4. ቆዳን ይመግባል የወይራ ዘይት በአንቲአኮሲዳንት የበለፀገ በመሆኑ እርጅናን ይዋጋል። ይህም ሲባል የወይራ ዘይትን መጠቀም ቆዳዎን በመመገብ መጨማደድን ለማዘግየትና አንዳንድ እርጅናን ተከትለው በቆዳ ላይ የሚከሰቱ መስመሮችን ለማስወገድ አይነተኛ መፍትሄ ነውም ይባልለታል። በተጨማሪም በወይራ ዘይት የበለፀገ የሰውነት ማጽጃ መጠቀም የሞቱ የቆዳ ሴሎችን ለማስወገድ እና ቆዳዎን ከውስጥ ለመመገብ ይረዳል። 5. ፀጉርን ይጠቅማል የወይራ ዘይት መቀባት ፀጉርን አንፀባራቂና ጤናማ አንዲሆን ያስችለዋል። የወይራ ዘይት ተፈጥአዊ ኮንዲሽነር ስለሆነ ሁሌም ቢሆን ከሻምፖ በፊት በመቀባት በፀጉር ላይ ትልቅ ለውጥን መመልከት ይችላሉ። 6. በታይፕ 2 የስኳር በሽታ type (2 Diabetes) የመያዝ እድልን ይቀንሳል ጥናቶች እንደሚያሳዩት የወይራ ዘይት ታይፕ 2 ተብሎ በሚጠራው የስኳር በሽታ የመጠቃት እድልን በእጅጉ ይቀንሳል። የወይራ ዘይትን በእለት ተዕለት ምግብዎ ውስጥ ቢያካትቱት በደምዎ ውስጥ የሚገኘው ስኳር ጤናማ መጠኑን እንደጠበቀ እንዲቆይ ሊያደረግው ይችላል። በ The American Journal of Clinical Nutrition የታተመ አንድ ጥናት እንዳመላከተው ከሆነ የወይራ ዘይት ሴቶች በስኳር ህመም አንዳይጠቁ ይከላከላል ብሏል። 7. ከልብ በሽታ ይከላከላል ለጤናማ ህይወትና ለጤናማ ልብ ሲሉ በእለት ተእለት ምግብዎ ዝርዝር ውስጥ የወይራ ዘይትን እንዲያካትቱ ይመከራሉ። በአንድ ጥናት ላይ የወይራ ዘይት ለልብ ህመም ምክንያት ከሆኑት መካከል ከፍተኛ የደም ግፊትን በመቀነስ ልብን ጤናማ አድርጎ እንደሚያቆይ መጠቀሱን ልብ ይሏል። ምንጭ: ሄልዝካርት መልካም ጤንነት!! ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ የጤና መረጃ ለማግኘት፤ @DrSofonias

የጉበትን ጤንነት ለመጠበቅ የሚጠቅሙ መንገዶች 💎 ጤናማ ክብደት ይኑርዎት ከመጠን በላይ ከፍተኛ ውፍረት ያላቸው ሰዎች ለጉበት ላይ ስብ መከማቸት ተጋላጭ ሊሆኑ ይችላሉ። ክብደትን መቀነስ የጉበት ስብን ለመቀነስ ትልቅ ሚና ይጫወታል። 💎 ጤናማ አመጋገብ ይከተሉ ከፍተኛ የካሎሪ፣ የስኳር እና የቅባት ይዘት ያላቸውን ምግቦች ያስወግዱ። 💎 አዘውትረው የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ያድርጉ በሳምንት ለ5 ቀናት ለ30 ደቂቃ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ የጉበት ስብን በመቀነስ ጉበቶዎ ጤናማ እንዲሆን ይረዳዎታል። 💎 ተጓዳኝ በሽታዎችን ይቆጣጠሩ እንደ የስኳር ህመም፣ የደም ግፊት እና ከፍተኛ ኮሌስትሮል ያሉ የጤና ሁኔታዎች ለጉበት በሽታ ዋና ዋና ምክንያቶች ናቸው። በአመጋገብ እና በመዳኒቶች መቆጣጠር የጉበት ጉዳትን ለመከላከል ያስችላል። 💎 አልኮል መጠቀምን ያስወግዱ ወይም ይቀንሱ አልኮል ከመጠን በላይ መጠጣት የጉበት ህዋስ ሊጎዳ ወይም ሊያጠፋ እና ጉበትዎን ሊጎዳ ይችላል። 💎 ማጨስ ያቁሙ ማጨስ ከጉበት ካንሰር ጋር የተያያዘ ሲሆን አንዳንድ መድሃኒቶች በጉበት ላይ የሚያደርሱትን መርዛማ ተጽእኖ ሊያሳድግ ይችላል። 💎 ጥንቃቄ ከጎደለው የግብረ ሥጋ ግኑኝነት ይቆጠቡ ከብዙ አጋሮች ጋር ጥንቃቄ የጎደለው የግብረ ሥጋ ግንኙነት ማድረግ ለሄፐታይተስ ቢ እና ለሄፐታይተስ ሲ የመጋለጥ እድልን ይጨምራል። 💎 መዳኒት ከመውሰድዎ በፊት ባለሙያ ያማክሩ መድሃኒቶችን በተሳሳተ መንገድ ሲወስዱ ወይም ከመጠን በላይ በመውሰድ ጉበትዎን ሊጎዱ ይችላሉ። መልካም ጤንነት!! @DrSofonias

የሴት ብልት የፈንገስ ኢንፌክሽን >>>>>>>>>>>>>>>>>>>(Vulvovaginal yeast infection) የሴት ብልት የፈንገስ ኢንፌክሽን ምንድን ነው? የሴት ብልት የፈንገስ ኢንፌክሽን በሴት ብልት የውጨኛው ቆዳ ላይ የመቆጣት እና የማሳከክ ስሜት የሚያስከትል ኢንፌክሽን ነው። ይህ ኢንፌክሽን የሚከሰተው ካንዲዳ(candida) በመባል በሚጠራው የፈንገስ ዝርያ ነው። የሴት ብልት የፈንገስ ኢንፌክሽን ምልክቶችና የህመም ስሜቶች ምንድን ናቸዉ? ምልክቶቹ የሚከተሉትን ያካትታሉ ● የሴት ብልት የውጨኛው ቆዳ ማሳከክ ● የሽንት ማቃጠል ● የሴት ብልት እና የሴት ብልት የውጨኛው ቆዳ ማቃጠል፣ መቅላት ወይም መቆጣት ● በወሲብ ወቅት ህመም ● የሴት ብልት ፈሳሽ አንዳንድ የሴት ብልት የፈንገስ ኢንፌክሽን ያላቸው ሴቶች ከሴት ብልት ውስጥ ትንሽ ፈሳሽ ሊኖራቸው ይችላል። ይህ ፈሳሽ በአብዛኛው ነጭና እንደ አይብ የሚበጣጠስ ነው። ነገር ግን ቀጭን እና እንደ ውሃም ሊሆን ይችላል። ምልክቶቼ በፈንገ ኢንፌክሽን ምክንያት መሆኑን እንዴት አውቃለሁ? አብዛኛዎቹ ሴቶች የምልክታቸው መንስኤ የሴት ብልት የፈንገስ ኢንፌክሽን ይሁን ወይም ሌላ ነገር ይሁን ሊያውቁ አይችሉም ። የሴት ብልት የፈንገስ ኢንፌክሽን ምልክቶች ከሌሎች የሴት ብልት ኢንፌክሽን ምልክቶች ጋር ተመሳሳይ ናቸው ፤ ስለዚህ ምርመራ ሳያደርጉ በዚህ ምክንያት ነው ብሎ ለመናገር በጣም አስቸጋሪ ነው። እርግጠኛ ለመሆን ሃኪም ወይም ነርስጋ ቀርቦ መታየት እና ከማህጸን ፈሳሽ ናሙና ተወስዶ የላቦራቶሪ ምርመራ ማድረግ ያስፈልጋል። የሴት ብልት የፈንገስ ኢንፌክሽን እንዴት ነው የሚከሰተው? የሴት ብልት የፈንገስ ኢንፌክሽን የሚያመጣው ፈንገስ አብዛኛውን ጊዜ በአንጀት ውስጥ እና በሴት ብልት ውስጥ ይኖራል። ይሁንና የፈንገሱ ቁጥር አነስተኛ በመሆኑ አብዛኛውን ጊዜ የበሽታ ምልክቶች አይኖርም። የተወሰኑ መድሃኒቶች (በተለይም አንቲባዮቲክስ) ፣ ጭንቀትና ሌሎች ምክንያቶች ፈንገሶቹ እንዲባዙ ሊያደርጉ ይችላሉ። ይህ በሚሆንበት ጊዜ የማህጸን የፈንገስ ኢንፌክሽን ምልክት መታየት ይጀምራ። ከስር የተዘረዘሩት ለሴት ብልት የፈንገስ ኢንፌክሽን የሚያጋልጡ ሁኔታዎች ናቸዉ ●የአንቲባዮቲክስን መጠቀም ●የወሊድ መቆጣጠሪያ እንክብሎች መጠቀም ●የስኳር በሽታ ●እርግዝና ●የተዳከመ የሰውነት የበሽታ መከላከያ ስርዓት (የኬሞቴራፒ ሕክምና፣ኤች አይ ቪ) የሴት ብልት የፈንገስ ኢንፌክሽን እንዴት ይታከማል? ለሴት ብልት የፈንገስ ኢንፌክሽን የሚሆኑ መድኃኒቶች ​​ሊወስዱ ይችላሉ። መድኃኒቶች የሚዋጡ ወይም በሴት ብልት ውስጥ የሚቀመጡ ሊሆኑ ይችላሉ። በሴት ብልት ውስጥ የሚቀመጡት መድሃኒቶች በክኒን ወይም በክሬም መልክ ሊመጡ ይችላሉ። ለሴት ብልት የፈንገስ ኢንፌክሽን የሚወሰዱ ሁሉም መድሃኒቶች ኢንፌክሽኑን የሚያስከትሉ ፈንገሶችን በመግደል ይሰራሉ። ጥሩ ስሜት የሚሰማኝ መቼ ነው? ሕክምና እንደጀመሩ በጥቂት ቀናት ጊዜ ውስጥ ጥሩ ስሜት ሊሰማዎት ይችላል። ህክምናን ካጠናቀቁ በኋላ ካልተሻለዎት ​​ዶክተርዎን ወይም ነርስዎን እንደገና ማየት አለብዎት ፤ ተጨማሪ መድሃኒት መውሰድ ወይም ሌላ መድሃኒት መውሰድ ይኖርብዎት ይሆናል። ባለቤቴስ ህክምና ማድረግ ይጠበቅበታል? የሴት ብልት የፈንገስ ኢንፌክሽን በግብረ ስጋ ግንኙነት የሚተላለፍ አይደለም ። አልፎ አልፎ ከአንዱ ወደ አንዱ የመጋባት ሁኔታ ቢስተዋልም ፤ ባለሙያዎች የወሲብ ጓደኛ ህክምና እንዲያደርግ አይመክሩም። @DrSofonias

አዲስ ልብስ ከመለበሱ በፊት መታጠብ አለበት? በፋሽን ኢንዱስትሪው የተደረገ ጥናት እንደሚያሳየው ከሆነ አዲስ ልብሶችን ሳያጥቡ መልበስ በባክቴሪያ ለሚተላለፉ በሽታዎች ሊያጋልጥ ይችላል፡፡ በኒውዮርክ ዩንቨርሲቲ የማይክሮ ባዮሎጂና የሴል ባለሙያ የሆኑት ፕሮፌሰር ፕሊፕ ቴርኖ እንደሚሉት አዲስ ልብሶች አገልግሎት ላይ ከመዋላቸው በፊት መታጠብ አለባቸው። ብዙ ጊዜ ልብሶች ለሽያጭ ሲቀርቡ በሳምንታት ውስጥ በርከት ያሉ ደንበኞች እንደሚሞክሯቸውና ሳይገዟቸው እንደሚሄዱ ነው የተገለጸው። ፕሮፌሰር ፕሊፕ ቴርኖ በአልባሳት መደበሮች ላይ ባካሄዱት ጥናት ልብሶቹ የሚሸጡበት ጊዜ ፍጥነት፣ የልብሱ ማቆያ ጥበትና ስፋት ሌሎች ሁኔታዎችም የራሳቸው አስተዋጽኦ ቢኖራቸውም የአልባሳት ደንበኞች ልብሶችን በመለካትና ሳይገዙ በመሄድ ባክቴሪያና ጀርሞችን ልብሶቹ ላይ ትተው እንደሚሄዱ አረጋግጠዋል። በጥናቱ ለተለያዩ በሽታዎች መነሻ የሆኑ ባክቴሪና በልብሶች ላይ እንደተገኙ ፕሮፌሰር ቴርኖ አረጋግጠዋል። ሰዎቹ በጀርም ና ባክቴሪያ የተበከሉ ልብሶችን በመነካካት አፍ፣ አፍንጫ፣ ቆዳና ሌሎች የሰውነት ክፍሎችን በመንካት ልብሶቹ ለበሽታ መተላለፊያ መንገዶች እንደሆኑ በጥናቱ ተጠቅሷል። በዚህ መንገድ የሚከሰተው አደጋ ቀለል ያለ ቢሆንም የመቁስልና የቆዳ መሰንጠቅ ችግር ባለባቸው ሰዎች ላይ ጉዳቱ ከፍ ሊል እንደሚችል ፕሮፌሰሩ ገልጸዋል። ከዚህም ሌላ በልብሶች ምርት ሂደት አገልግሎት ላይ የሚውሉ የቀለምና ሌሎች ኬሚካሎችም ቆዳን የማቃጠል ስሜት ስልሚኖራቸው ልብሶችን አጥቦ መልበስ አስገዳጅ ከሚያደርጉት ምክንያቶች አንዱ እንደሆነ ነው ጥናቱ የሚጠቁመው። በኒውጀርሲ የቆዳ ሃኪም የሆኑት ዶክተር መጋሀን ፈለይ አንዳንድ የልብስ ንጽህና መስጫዎች የሚጠቀሟቸው የማጽጃ ኬሚካሎች ውህድ ንጥረ ነገሮችና ቀለሞች ለተወሰነ ጊዜ ቆዳን ማቃጠልና ሽፍታ የሚያጋልጡ መሆኑን ነው የሚገልጹት። ከኮፍያ ጀምሮ አዲስ ልብሶችን እንደየ ስሪታቸው ባህሪ በማጠብ ማድረቅና መጠቀም የእራስንና የሌሎችን ጤና መጠበቅ አስፈላጊ እንደሆነ ነው የተገለጸው። ውድ የኢትዮጤና ቤተሰቦች ከመልበሻ ክፍል እንደወጣን ከመመገብ፣ መጠጣትና ሌሎች ተግባራትን ከማከናዎናችን በፊት እጃችንን በመታጠብ በልብሶች ሊተላለፉ የሚችሉ በሽታዎችን በቀላሉ መከላከል እንደሚያስችል ልብ ይሏል፡፡ @DrSofonias

የአይን እይታን የሚጎዱ 10 ልምዶች 1. ሲጋራ ማጨስ - በሲጋራ ውስጥ ከ7 ሺህ በላይ ኬሚካሎች አሉ። እነዚህን ኬሚካሎች አይናችንን በከፍተኛ ሁኔታ ይጎዳሉ። 2. ተንቀሳቃሽ ምስሎችን በላፕቶፕ፣ ስልክ ወይም ታብሌቶች ላይ ለረጂም ሰአት መመልከት - ማንናውንም ነገር ወደ ፊታችን በጣም አቅርበን መመልከት ለአይናችን መጥፎ ነው። ለረዥም ጊዜ ቴሌቪዥን መመልከትም የእይታ ችግር ይፈጥራል ነው የተባለው። 3. የጸሀይ ብርሃን ጨረር መከላከያ መነጸር አለማድረግ (Solar Eye Glass) - ለጸሀይ ብርሀን ጨረር በምንጋለጥባቸው አካባቢዎች የጨረር መከላከያ መነጸር ማድረግ አልትራቫዮሌት ጨረር (Ultraviolet Light) በቀጥታ አይናችንን እንዳይጎዳን ይረዳል። 4. ደማቅ ቀለም ያላቸው ምግቦችን አለመውሰድ - በፔክቲን የበለጸጉ እንደ ካሮት ያሉ እና ለአይን ጤና የሚመከሩ ምግቦችን አለመውሰድ ለውዱ አይናችን መስጠት የሚገባንን ማጓደል ነው። 5. በተሽካርካሪ ውስጥ እየተጓዙ ማንበብ - አድካሚ እና አሰልቺ ጉዞ ስናደርግ ከድብርት ለመውጣት ስንል መጽሃፍት እናነባለን፤ ይሁን እንጂ ይሄ ልማድ ለአይናችን ጤና መልካም አይደለም ተብሏል። 6. በቂ እንቅልፍ አለማግኘት። 7. ኮምፒውተር ላይ ረጅም ጊዜ የሚያጠፉ ሰዎች አይናቸውን በተወሰነ ደቂቃ ልዩነት ማርገብገብ እንዳለባቸው ይመከራል። ይሁን እንጂ ባለማወቅም ይሁን በመርሳት አይናችንን ካለማርገብገብ የተነሳ አይናቸው ሊጎዳ ይችላል። 8. አጥብቦ መመልከት - የተለያዩ አጋጣሚዎች አይናችንን አጥብበን እንድንመለከት ይጋብዙናል፤ ነገር ግን ይህ ነገር እየተደጋገመ ሲመጣ እና ልማድ ሲሆን ለአይናችን በርካታ ጠንቆች ይዞ እንደሚመጠ ነው የሚነገረው። 9. በቂ ብርሃን በሌለው ቦታ ማንበብ። 10. መነጸር እንዳደረግን መተኛት ለተለያዩ የአይን ኢንፌክሽኖች ያጋልጣል። @DrSofonias

የወር አበባ እየታየ እርግዝና ይፈጠራል? ስለ እርግዝና ሲነሳ የተለመደው እና ብዙ ጊዜም የሚነገረው በወር አበባ ወቅት እርግዝና አይፈጠርም የሚለው አፈ ታሪክ (myth) ነው። ምንም እንኳን በወር አበባ ወቅት የእርግዝና የመፈጠር እድል እጅግ ያነሰ ቢሆንም ዜሮ በሚባል ደረጃ ግን አስተማማኝ አይደለም። በወር አበባ ወቅት ስለሚደረግ ወሲባዊ ግንኙነት እና ስለ እርግዝና ጉዳይ የሚከተለውን ማወቅ ለግንዛቤ ይረዳል እና እነሆ:- ☑️ ለመሆኑ እርግዝና እንዴት ነው የሚከሰተው? እርግዝና የሚፈጠርበት ሂደት እና እድል አስገራሚ ነገር አለው። እርግዝና ለመፈጠር የሴቷን እንቁላል እና የወንዱን የዘር ፍሬ መገናኘት የሚፈልግ ሲሆን የሴቷ እንቁላል ከኦቫሪ ከተለቀቀ ብኋላ ያለው እድሜ ከ12-24 ሰዓት ብቻ ነው። የወንዱ የዘር ፍሬ ግን እስከ ሶስት ቀን የመቆየት አቅም አለው። ስለዚህ እርግዝና ሊከሰት የሚችለው የሴቷ እንቁላል ተለቆ በህይወት በሚቆይበት እድሜ የወንዱን የዘር ፍሬ የሚያገኝበት እድል ሲፈጠር ነው ማለት ነው። በነገራችን ላይ መደበኛው የሴት ልጅ የወር አበባ ኡደት 28 ቀን ሲሆን የሴቷ እንቁላል የሚለቀቀው (ovulation) በ14ኛው ቀን ገደማ ነው። ይህም ማለት በ12,13 ወይም በ14ኛው ቀን ሊሆን ይችላል። ይሁንና ሁሉም ሴቶች በተመሳሳይ የ28 ቀን የወር አበባ ዑደት የላቸውም ። አንዳንድ ሴቶች እስከ 35 ቀን የሚደርስ ረዘም ያለ ዑደት ሲኖራቸው ፣አንዳንዶቹ ደግሞ 21 ቀን ብቻ ሊኖራቸው ይችላል። ይህ የወር አበባ ዑደት ልዩነት ደግሞ ኦቩሌሽን የሚፈጠርበትንም ቀን የተለያየ እንዲሆን ያደርገዋል። በዚህም መሰረት ባለ 21 ቀኖቹ በ7ኛው ቀን ገደማ፣ ባለ35 ቀኖቹ ደግሞ በ21ኛው ቀን ገደማ ኦቩሌሽን (የእንቁላል መለቀቅ) ይኖራቸዋል። ☑️ ታዲያ አንዲት ሴት በወር አበባዋ ወቅት እንዴት ልታረግዝ ትችላለች? አንዳንዴ ከሴት የመራቢያ አካል የሚወጣን ደም ከወር አበባ ጋር የማሳሳት ነገር ይፈጠራል። ይህም ማለት አንዲት ሴት ለእርግዝና ዝግጁ ሆና ሳለ የወር አበባዋ እንደመጣ ልታስብ ትችላለች። ይህ አንዱ ምክንያት ሊሆን ቢችልም ዋነኛው ግን ከወንድ ልጅ የዘር ፍሬ እድሜ ጋር የሚያያዝ ነው። የወንድ ልጅ የዘር ፍሬ እስከ 72 ሰዓታት በሴቷ አካል ውስጥ የመቆየት አቅም ስላለው አንዲት ሴት በወር አበባ መገባደጃ አከባቢ ወሲብ ብትፈጽም የማርገዝ እድል ይኖራታል። የአብዛኞቹ ሴቶች የኦቩሌሽን ሳይክል ከ28-30 ቀን ነው። ይህም ማለት በወር አበባ ጊዜ ወሲብ ቢፈጸም ለብዙ ቀናት እርግዝና ላይከሰት ይችላል። ይሁንና አጭር የኦቩሌሽን ሳይክል ያላቸው ሴቶች በኦቩሌሽን እና በወር አበባ መካከል በቂ ቀን ላይኖራቸው ይችላል። ☑️ በወር አበባ ወቅት የእርግዝና መከሰት እድሉ ምን ያህል ነው? አንዲት ሴት የወር አበባ ማየት በጀመረችበት ሁለት ተከታታይ ቀናት ወሲብ ብትፈጽም የማርገዝ እድሏ ዜሮ ነው ማለት ይቻላል። ይሁንና ከሶስተኛው ቀን ጀምሮ የማርገዝ እድሏ ቀስ በቀስ እያደገ ይሄድና ልክ 13ኛው ቀን ላይ 9% ይደርሳል። ይህ ቁጥር ቢቀንስ እንኳን መቶ ፐርሰንት እርግዝና እንደማይከሰት እርግጠኛ ሆኖ መናገር አይቻልም። 💎 ሲጠቃለል የሴቶች የኦቩሌሽን ሳይክል የተለያየ ነው። ስለዚህ በስታቲስቲክስ አንዲት ሴት የወር አበባ ላይ ሆና የምታረግዝበት እድል ሊፈጠር ይችላል። ምንም እንኳን በወር አበባ የመጀመሪያዎቹ ቀናት እርግዝና የመከሰት እድሉ እጅግ ያነሰ ቢሆንም ቀን እየገፋ በሄደ ቁጥር ግን እያደገ ይሄዳል። ወቅታዊ እና የተሟሉ የጤና መረጃ ለማግኘት፤

የሰውነት ሎሽን ጥቅሞች የሰውነት ሎሽን መቀባት ውድ ዋጋ የማያስከፍል ሰዎች እራሳቸውን ለመንከባከብ ከሚያደርጓቸው መንገዶች አንዱ ነው። ለወንድም ለሴትም የሚሆኑ እንደየቆዳዎች አይነትም የተለያዩ የሰውነት ሎሽኖች በአለማችን ዙሪያ ይገኛሉ፡፡ ታዲያ እነዚህን ሎሽኖች በየቀኑ ሰውነታቸውን የሚቀቡ ሰዎች በርካታ ጠቀሜታዎችን እንደሚያገኙም ይታመናል፡፡ 1. የደረቀ ቆዳን ያለመልማል አንዳንድ ሰዎች የትኛውም አይነት የአየር ሁኔታ ያለበት ቦታ ላይ ቢኖሩም ቆዳቸው ከመድረቅ ወደኋላ አይልም፡፡ በቤት ውስጥ ብቻ ተወስነው እየዋሉ እንኳን የቆዳ ድርቀት የሚያጋጥማቸው ብዙ ናቸው፡፡ ደግሞም የስራ ሁኔታ ይሆንና በርካታ ሰዎች ከባድና አስቸጋሪ የአየር ንብረት ያለበት ቦታ ይሰራሉ፡፡ ታዲያ በቅዝቃዜ፣ በሙቀት፣ በንፋስ እና በተለያዩ ነገሮች የተቆራረጠ የተቆጣ እንዲሁም የደረቀን ቆዳ በኮስሞቲክስ መልሶ ማስተካከል አይቻልም፡፡ ሰውነትዎን ከታጠቡ በኋላ ግን ደረጃውን የጠበቀ የሰውነት ሎሽን ቆዳዎን ቢቀቡት ስር ድረስ ዘልቆ በመግባት ቆዳዎ እንዲለመልም እርጥበትም እንዲኖረው ማድረግ ይችላሉ፡፡ 2. ሸካራ ቦታዎችን ያለሰልሳል ምንም እንኳን ቆዳዎ ወዛምና የተለመደ አይነት ቢሆንም ክርኖችዎ ወይም ጉልበቶችዎ አካባቢ ሸካራ ቦታዎች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ እነዚህን ቦታዎች በመደበኛ ሁኔታ የሰውነት ሎሽን ቢቀቧቸው ለስላሳና ማራኪ መሆን ይችላሉ፡፡ 3. የሞቱ ቆዳዎችን ያስወግዳል በእግርዎ ሲንቀሳቀሱ የማያስደስትና የሚያሰቃይ አይነት የህመም ስሜት ሲሰማዎ እርጥበታማ ሎሽን ቢጠቀሙ ሎሽኑ ስቃይ የሚያመጣብዎ ቦታ ላይ ያለውን የሞተ ቆዳ በማስወገድ ከህመምዎ እንዲያገግሙ ቆዳዎም ጤነኛ እንዲሆን ማድረግ ይችላል፡፡ 4. ጥሩ ስሜት እንዲሰማዎ መልካም መዓዛ እንዲኖርዎ ያደርጋል ብዙ ሰዎች እጆቻቸውን ክሬም ሎሽን መቀባት ይወዳሉ፡፡ እርስዎም ጣትዎን፣ ክንድዎን፣ እግርዎን ዘና የሚያደርጉ ሎሽኖችን በመቀባት መፍታታት ይችላሉ፡፡ ደግሞም ሎሽኖች በተለያዩ መዓዛም ጭምር ስለሚገኙ ከጥሩ ስሜት ጋር መልካም መዓዛ ያለውን ሎሽን በመጠቀም ውሎዎ ላይ ጥሩ ስሜትን ማካተት ይችላሉ፡፡ 5. ቆዳን አንፀባራቂ ያደርጋል በቆዳው ላይ የሚያንፀባርቁ ጥቃቅን ብልጭታዎችን የሚያሳዩ የሚያብረቀርቁ ባህሪያት አንዳንድ ጊዜ በሎሽን ውስጥ ይካተታሉ፡፡ ታዲያ እነዚህ ሎሽኖች የሞቱና የደነዘዙ የቆዳ ህዋሶችን ቀርፎ በማስወገድ ከሥር ያሉ ሕብረ ሕዋሶችን በማደስ ቆዳን አንፀባራቂ ባህርይን እንዲላበስ ያስችሉታል።

ቋቁቻ( pityriasis versicolor) ቋቁቻ malassezia በሚባል የፈንገስ(fungus) አይነት የሚመጣ ሲሆን ብዙ ግዜ ወጣቶችን የሚያጠቃ በሽታ ነዉ።ይህ የ fungus አይነት በሁላችንም ሰዉነት የሚገኝ ሲሆን ለምን አንዳንድ ሰዎች ላይ ብቻ በሽታዉን እንደሚያመጣ በሳይንስ የተረጋገጠ ነገር የለም። እሱም ገርጣ ገርጣ ወይም ጠቆር ጠቆር በሚሉ የቆዳ ለዉጥ ይታወቃል። አብዛኛዉን ግዜ ደረትና ጀርባን የሚያጠቃ ሲሆን አልፎ አልፎ ፊት ፣ እጅና እግርን ልያጠቃ ይችላል። ቋቁቻ ብዙ ግዜ በሞቃታማ የአየር ሁኔታ የሚከሠት ሲሆን የበለጠ ወንዶችን ያጠቃል። አብዛኛዉን ግዜ ምልክት ባይኖረዉም አንዳንድ ግዜ ግን ልያሳክክ ይችላል። ይሁንና ቋቁቻ ከሰዉ ወደ ሰዉ አይተላለፍም። ቋቁቻ በብዛት ሊከሰት የሚችል ከሰዉ ወደ ሰዉ የማይተላለፍ በፈንገስ ምክንት የሚመጣ የቆዳ ላይ ችግር ነዉ:: ፈንገሱ የቆዳ ተፈጥሮዊ መልክን በማሳጣት ትናንሽ፣ነጣ ወይም ጠቆር ያሉ መልካቸዉን የለወጡ ነገሮች በቆዳ ላይ እንዲወጡ ያደርጋል፡፡ ሞቃታማና እርጥበታማ የአየር ፀባይ ፣ወዛማ ቆዳ ካለዎት፣· የሆርሞን መለዋወጥ የበሽታ መከላከል አቅማችን መዳከም ቋቁቻ እንዲከሰት ወይም የሚያደርጉ ነገሮች ሲሆን ቋቁቻን በተለያዩ የሚቀቡና የሚዋጡ መዳንቶች ማከም ይቻላል።ሆኖም ግን ሁኔታዎች ሲመቻቹለት የመመላለስ ፀባይ አለው። ቋቁቻ በፈንገስ ምክንት የሚመጣ የቆዳ ችግር ስለሆነ የሚከተሉት መድሃኒቶች ሊታዘዙ ይችላሉ፡፡ የተወሰኑት መድሃኒቶች በቆዳ ላይ ሊቀቡ የሚችሉ ሲሆን ቀሪዎቹ የሚዋጡ ናቸዉ፡፡ 1.የፍሉኮናዞል እንክብል ወይም ፈሳሽ መድሃኒት 2. ኢትራኮናዞል( እንክብል፣ካፕሲዩል ወይም ፈሳሽ) 3. ኬቶኮናዞል( ክሬም፣ ጄል ወይም ሻንፖ) ናቸዉ፡፡ ምንም እንኳ ህክምናዉን በደንብ ቢከታተሉትና ህመሙ ቢሻሎትም ለሳምንታት ወይም ለወራት የቆዳዎ ቀለምዎ ሳይለወጥና እንደሻከረ ሊቀጥል ይችላል፡፡ አንዳንዴ ደግሞ ህመሙ ተመልሶ ሊመጣ ይችላል( በተለይ በሞቃታማና እርጥበታማ የአየር ፀባይ ወቅት)፡፡ ስለሆነም ኢንፌክሽኑ ተመልሶ እንዳይመጣ መድሃኒት በወር አንዴ ወይም ሁለቴ መዉሰድ ሊስፈልግ ይችላል፡፡ @DrSofonias

ቪያግራና የፍቅር ጨዋታ በፍቅር ጨዋታ ጊዜ አልጋ ላይ ብዙ መቆየት ባለመቻልዎ ደስተኛ አይደሉም? የፍቅር አጋርዎ የእርካታን ጣሪያ ሳይነኩ በፊት ገና ጨዋታውም በድንብ ሳይጀመር ድንገት ብልትዎ ዝልፍልፍ በማለት አሸማቅቆዎት አልያም ስራየን ጨርሻለሁ ጌታየ ብልዎት ደንግጠው ያውቃሉ? የዘርፉ ባለሙያዎች አይጨነቁ ይህ የእርስዎ ችግር ብቻ አይደለም በአለም ላይ 39% ወንዶች ተመሳሳይ ቶሎ የዘር ፍሬን የመርጨት ችግር ሰለባዎች ናቸው። ግን መፍትሄ አለን እንዲች ብለው እንዳያስቡ። ይሉዎታል። ☑️ ቪያግራ ቪያግራ ውስጥ የሚገኘው ንጥረ ነገር ወደ ብልት የሚሄደውን የደም ፍሰት በመጨመር ብልትን ለወሲብ ዝግጁ ሆኖ ረዘም ላለ ሰዓት እንዲቆይ ያደርገዋል። በርግጥ ቪያግራ እንዲሁ ዝም ብሎ አይወሰድም ይላሉ ባለሙያዎቹ። ለምሳሌ ከ18-64 የእድሜ ክልል የሚገኙ ሰዎች 50 ግራም ቪያግራ እንዲወስዱ ሲመከር ከ65 ዓመት በላይ የሆኑ ደግሞ 25 ግራም ቪያግራ ቢጠቀሙ የተሻለ ነው። በእርግጥ እንደየሁኔታው እስከ 100 ግራም ድረስ ሊወስድ ይችላልም ይላሉ የዘርፉ ባለሙያዎች። ☑️ መቼ ይወሰድ ታዲያ? ቪያግራን ከወሲብ አንድ ሰዓት ቀደም ብሎ መውሰድ ተመራጭ ጊዜ ነው። ☑️ ከምግብ በፊት ነው በኋላ? ቪያግራ ከምግብ በፊትም በኋላም መወሰድ ይቻላል። ነገር ግን በሚወስዱበት ጊዜ ከፍተኛ ፋት (Fat) ያለው ምግብ መመገብ ቪያግራው በቶሎ ከሰውነትዎ ጋር እንዳይዋሃድና ስራውን እንዳይሰራ እክል ስለሚሆንበት ቀለል ያለ ምግብ እንዲመገቡ ይመከራል። ☑️ ማስታወሻ ቪያግራ ልክ በወሰዱበት ቅጽበት ወዲያው ወደጉዳይዎ እንዲያስገባዎት አይጠብቁ። ☑️ አልኮል ብቀማምስስ? ከወሲብ በፊት ወይን ወይንም አንዳች አልኮል የመጠጣት ልምድ ካልዎትና ቪያግራ የሚወስዱ ከሆነ ከአንድ ብርጭቆ በላይ አልኮል እንዳይጠጡ ይመከራሉ። ምክንያቱም ቪያግራ ከአልኮል ጋር በሚቀላቀልበት ጊዜ ወደብልት የሚሄደውን የደም መጠን በእጅጉ ሊቀንሰውና ነገርየው እንደሀረግ እየተልፈሰሰ ሊያስቸግርዎት ይችላል። 🦋 ሙድ ውስጥ ይግቡ 🦋 ቀድሞውንም እርስዎ የወሲብ ሙድ ውስጥ ካልገቡ ቪያግራ በራሱ ምንም የሚፈጥረው ነገር የለም። ስለዚህ የወሲብ ሙድ ውስጥ ይግቡ። ☑️ በምን ያክል ፍጥነት ስራውን ሊጀምር ይችላል? እርስዎ የወሲብ ሙድ ውስጥ ከሆኑ ቪያግራ በአብዛኛው ከ30 እስከ 60 ደቂቃ ሊወስድበት ቢችልም አንዳንዴ ግን ከ2 ሰዓታት በኋላ ስራውን መስራት ይጀምራል። ☑️ ለምን ያክል ጊዜ ወሲብ እየፈፀሙ መቆየት ያስችላል? በርግጥ ይህ እንደግለሰቡ እድሜ፣ የጤና ሁኔታና ቪያግራውን በወሰደበት ወቅት እንደተመገበው የምግብ አይነት ቢወሰንም እስከ 4 ሰዓት ይቆያል ይባላል። አንዳንዶቹ ግን ከ2 እና 3 ሰዓታት በላይ መቆየት እንዳላስቻለቸው ገልፀዋል። በርግጥ ለ5 ሰዓታት የቆዩም መገኘታቸው ሳይዘነጋ። በርግጥ በእነዚህ ሁሉ ሰዓቶች ወሲብ መፈፀም አለብኝ ብለው ማሰብ የለብዎም ምክንያቱም የቪያግራ ሌላው ጥቅም የዘር ፍሬዎን ከረጩ በኋላም እንኳን ቢሆን ብልትዎ ለወሲብ ዝግጁ እንደሆነ ረዘም ላለ ጊዜ መቆየቱ ነው። ይህም እንደባለሙያዎቹ አባባል የተጓዳኝን ስሜት ለማስጨረስ ይረዳል። ዋው ምናልባትም ቪያግራ በወሲብ ህይወቴ ላይ አንዳች ነገር ሊጨምር ይችል ይሆናል ነገር ግን እንዴት ነው የጎንዮሽ ጉዳት አለው? ብለው ከጠየቁ የባለሙያዎቹ መልስ ምንማለትዎ ነው ግጥም አድርጎ ነው ያለው ይሆናል። በመጀመሪያ ደረጃ ቪያግራ ማንኛውም ሰው እንዲሁ እንዲወስደው አይመከርም። የህክምና ታሪካችሁን የሚያውቅ ባለሙያ ካላዘዘላችሁ በቀር ባትወስዱ ይመከራል። ☑️ የጎንዮሽ ጉዳቶቹ 💎 ራስ ምታት 💎 ድብርት 💎 የጀርባና የጡንቻ ህመም 💎 የእይታ ችግር (ለምሳሌ ነገሮች የተጥበረበሩ ሁነው ሊታዩን ይችላሉ) 💎 መጨነቅ 💎 ከአፍንጫ የሚወጣ ፈሳሽ(ንፍጥ) መብዛት እና ሌሎች። @DrSofonias

ሽንት በምንሸናበት ጊዜ የማቃጠል ስሜት መንስኤውና መፍትሄው ሽንት በምንሸናበት ጊዜ የህመም ወይም የማቃጠል ስሜት መሠማት በህክምና ቋንቋ ዲስዮሪያ (Dysuria) ይባላል። ይህ የማቃጠል ስሜት በምንሸናበት ጊዜ ወይም ከሸናን በኋላ ይከሰታል። ይህ ችግር በተፈጥሮአዊ የመራቢያ አካል አቀማመጥ ምክንያት በሴቶች ላይ በብዛት ይከሰታል። ሴቶች አጭር የሽንት ፊኛ ቱቦ አላቸው (ሽንትን ከሽንት ፊኛ ወደ ውጪ የሚያወጡ)። እና የሽንት ቧንቧ ሥርዓት ከሰገራ መውጫ ቀዳዳና ከሴት አባላዘር በጣም በቅርብ እርቀት ተጠጋግተው ይገኛሉ። ☑️ ሽንት ከሸናሁ በኋላ ለምን የማቃጠል ስሜት ይሰማኛል? ይህ የማቃጠል ስሜት ከኢንፌክሽን ጋር የተያያዘ ነው። ኢንፌክሽኑ በማንኛውም የሽንት ቧንቧ ሥርዓት ክፍል ውስጥ ሊከሰት ይችላል። በአንድ ክፍል ላይ ከጀመረን በኋላ ካልታከምነው ወደተለያዮ ክፍሎች ይዛመታል። በዚህም ኢንፌክሽን ዩሬትራ፣ የሽንት ፊኛ፣ ዩሬተር እና ኩላሊት የመጠቃት ዕድል አላቸው። ሽንት ከሸኑ በኋላ የማቃጠል ስሜት የሚሰማዎት ከሆነ በሚከተሉት ምክንያቶች ሊሆን ይችላል፦ 1. የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን ይህ በጣም ከተለመድት ምክንያቶች ውስጥ አንድ ነው። ይህ የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን መነሾ ወደ ሽንት ሥርዓት የመግባት ዕድል ባገኙ ባክቴሪያዎች ምክንያት ይከሰታል። ከዚያም ወደተያያዙ የሰውነት ክፍሎችና ዩሬትራ ይዛመታል። የታችኛው የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን ሌሎች ምልክቶች የሚከተሉት ናቸው:- 🔹 የሆድ ህመም ወይም በሚሸኑበት ጊዜ ህመም። 🔹 ፒንክ ወይም ቀይ ቀለም ያለው ሽንት። 🔹 ከወትሮው ለየት ያለ ጥሩ ያልሆነ ሽታ ያለው ሽንት። 🔹 የሽንት ፊኛቸው ባዶ ቢሆን እንኳን ለመሽናት መጣደፍ/መቸኮል። 🔹 የጀርባ ህመምና አጠቃላይ የህመም ስሜት መሰማት። 🔹 በዳሌ አካባቢ የምቾት ማጣት ስሜት። ይህ ኢንፌክሽን ከሽንት ቧንቧ መስመር ካለፈ ለምሳሌ ወደ ኩላሊት ከተዛመተ ምልክቶቹ በደንብ ይወጣሉ ከነዚህም ምልክቶች መካከል ፦ 🔹 ትኩሳት 🔹 የጀርባ ህመም 🔹 የጎን ወይም ዳሌ አካባቢ ህመም 🔹 ማቅለሽለሽ 🔹 ማስመለስና 🔹 ተቅማጥ ናቸው። ☑️ ለሽንት ቧንቧ የሚያጋልጡ ምክንያቶች የሚከተሉት ናቸው:- 🔸 በዕድሜ የገፉ ሰዎች 🔸 የስኳር በሽተኞች 🔸 ሴቶች 🔸 የኩላሊት ጠጠር ያለባቸው ሰዎች 🔸 እርጉዝ ሴቶች 🔸 በመጠን ትልቅ የሆነ ፕሮስቴት ዕጢ ያላቸው ሰዎች (በተለይ በዕድሜ የገፉ ሰዎች) 🔸 የሽንት መሽኒያ ቱቦ ወይም ካቲተር የተገጠመላቸው ሰዎች። 2. በግብረ - ሥጋ ግንኙነት የሚተላለፉ በሽታዎች ባክቴሪያዎች በምንሸናበት ጊዜ የማቃጠል ስሜት ለመከሰቱ ቀጥተኛ ተሳታፊዎች ናቸው። ይህም የብልት ኸርፐስ፣ ክላሚዲያ እና ጨብጥ ይጠቀሳሉ። ሌሎች ከግብረ - ሥጋ ግንኙነት ኢንፌክሽን ጋር የሚያያዙ ምልክቶች እነሆ:- 🦋 ያልተለመደ የብልት ፈሳሽ 🦋 ከማቃጠል ስሜት በተጨማሪ የማሳከክ ምልክት 3. የብልት ኢንፌክሽን የብልት ኢንፌክሽን ለምሳሌ እንደ ይስት ኢንፌክሽን (Yeast Infection) የማቃጠል ስሜት ከማስከተላቸው በተጨማሪ በብልት አካባቢ ማሳከክና መቅላት (Redness) ምልክቶች ያስከትላሉ። ሌሎች የይስት ኢንፌክሽን ምልክቶች የሚከተሉትን ይመስላሉ:- 🍀 ያልተለመደ ነጭ አይብ የመሰለ የብልት ፈሳሽ 🍀 በግብረ ሥጋ ግንኙነት ወቅት የህመምና የማቃጠል ስሜት መሰማት 🍀 በውጫዊ የብልት አካባቢ የህመምና የማሳከክ ስሜት መሰማት። 4. የዩሬትራ አቀማመጥ (Urethral structure) ይህ ችግር በብዛት ወንዶችን የሚያጠቃ ሲሆን በዙሪያው ያሉ ስጋዎች ቀልተው በሚያብጡበት ጊዜ ወይም ጠባሳ በሚኖርበት ጊዜ ይፈጠራል። ከዚያም ሽንት ከሰዉነታችን በነፃነት መወገድ ስለሚሳነው በሚሸኑበት ጊዜ የማቃጠል ስሜት ይሰማዎታል። 5. ሌሎች ምልክቶች ጠንከር ያለ የግብረ ሥጋ እንቅስቃሴ ዩሬትራ እንዲቆጣ ያደርገዋል። ሌሎች አካላዊ እንቅስቃሴዎች ለምሳሌ፦ ብስክሌት ወይም ፈረስ መጋለብ በውጫዊው የብልት አካባቢ ሰበቃና (ፍጭት) ቁጣ እንዲፈጠር ያደርጋሉ። ለተለያዩ ሳሙናዎች፣ የሽንት ቤት ወረቀቶች፣ አረፋማ መታጠቢያዎችና የውበት መጠበቂያዎች አለርጂ ካለብዎ ከሸኑ በኋላ የማቃጠል ስሜት ሊያስከትሉ ይችላሉ። ☑️ ሃኪምዎን ማናገር ያለብዎት መቸ ነው? 🗣 ከወንድ ወይም ሴት የመራቢያ አካል ውስጥ ያልተለመደ ፈሳሽ የሚወጣ ከሆነ 🗣 ከህክምና በኋላ የህመሙና የማቃጠል ስሜት የማያቆም ከሆነ 🗣 በጎን ወይም በጀርባ የሰውነት ክፍልዎ ላይ የህመምና የትኩሳት ስሜት ከተሰማዎ 🗣 የሽንት ፊኛ ወይም የኩላሊት ጠጠር በሚወጣዎ ጊዜ ከባድ ህመም ካለዎ 🗣 በሽንትዎ ውስጥ ደም ካዩ ናቸው ☑️ ይህን ችግር በራስዎ እንዴት ማከም ይችላሉ? 💥 በዛ ያለ ውሃ ይጠጡ 💥 ሽንትዎ ሲመጣ ቶሎ ይሽኑት 💥 በጠርሙሱ ላይ በታዘዘው መሠረት አላካላይን ግራኒውልስ ይጠቀሙ። 💥 ፓርስሊ ውሃ ይጠጡ 💥 ኩከምበር ይመገቡ 💥 ክሬይንቤሪ ጭማቂ ይጠጡ 💥 ብሉቤሪስ ይመገቡ 💥 ሆርስ ራዲሽ ይመገቡ። @DrSofonias