uz
Feedback
ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

Kanalga Telegram’da o‘tish

ጤና ነክ ጥያቄ ካለዎት፣ በጽሑፍ በቴሌግራም ብቻ ይሄንን➡️  t.me/Dr_Sofonias በመጫን ያስቀምጡልኝ ሙያዊ ምላሽ ለመስጠት ጊዜ ሊወስድብኝ ስለሚችል፣ በትዕግስት ይጠብቁኝ ​📢 ለማስታወቂያ/ስፖንሰርሺፕ: ​ለስፖንሰርሺፕና ምርትዎ በሙያዊ ምክር እንዲተዋወቅ ከፈለጉ፣ ይሄንን ➡️ t.me/MASTAWKIYA በመጫን ያናግሩን

Ko'proq ko'rsatish

📈 Telegram kanali ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias analitikasi

ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias (@drsofonias) Amxar til segmentidagi kanali faol ishtirokchi. Hozirda hamjamiyat 19 989 obunachidan iborat bo'lib, Tibbiyot toifasida 1 154-o'rinni va Efiopiya mintaqasida 1 680-o'rinni egallagan.

📊 Auditoriya ko‘rsatkichlari va dinamika

невідомо sanasidan buyon loyiha tez o‘sib, 19 989 obunachiga ega bo‘ldi.

25 Iyun, 2026 dagi oxirgi ma’lumotlarga ko‘ra kanal barqaror faollikka ega. Oxirgi 30 kunda obunachilar soni -558 ga, so‘nggi 24 soatda esa -23 ga o‘zgardi va umumiy qamrov yuqori darajada qolmoqda.

  • Tasdiqlash holati: Tasdiqlanmagan
  • Jalb etish (ER): Auditoriya o‘rtacha 22.78% darajada jalb etiladi. Nashrdan keyingi dastlabki 24 soatda kontent odatda umumiy obunachilar sonining 5.94% ini tashkil etuvchi reaksiyalarni to‘playdi.
  • Post qamrovi: Har bir post o‘rtacha 4 556 marta ko‘riladi; birinchi sutkada odatda 1 188 ta ko‘rish yig‘iladi.
  • Reaksiyalar va o‘zaro ta’sir: Auditoriya faol: har bir postga o‘rtacha 11 ta reaksiya keladi.

📝 Tavsif va kontent siyosati

Muallif resursni shaxsiy fikrni ifoda etish maydoni sifatida ta’riflaydi:
ጤና ነክ ጥያቄ ካለዎት፣ በጽሑፍ በቴሌግራም ብቻ ይሄንን➡️  t.me/Dr_Sofonias በመጫን ያስቀምጡልኝ ሙያዊ ምላሽ ለመስጠት ጊዜ ሊወስድብኝ ስለሚችል፣ በትዕግስት ይጠብቁኝ ​📢 ለማስታወቂያ/ስፖንሰርሺፕ: ​ለስፖንሰርሺፕና ምርትዎ በሙያዊ ምክር እንዲተዋወቅ ከፈለጉ፣ ይሄንን ➡️ t.me/MASTAWKIYA በመጫን ያናግሩን

Yuqori yangilanish chastotasi (oxirgi ma’lumot 26 Iyun, 2026 da olingan) sababli kanal doimo dolzarb va katta qamrovli bo‘lib qoladi. Analitika auditoriya kontent bilan faol hamkorlik qilishini, uni Tibbiyot toifasidagi muhim ta’sir nuqtasiga aylantirishini ko‘rsatadi.

19 989
Obunachilar
-2324 soatlar
-1207 kunlar
-55830 kunlar
Postlar arxiv
መጥፎ የሰውነት ጠረንን እንዴት ማስወገድ ይቻላል? የሰው ልጅ የራሱ የሆነ የተለየ የሰውነት ጠረን አለው። ይህ የሰውነት ጠረን ጤናማ ቢሆንም በአንዳንድ ሰዎች ዘንድ ግን ከመጠን ያለፈ ይሆንና ከራስ አልፎ ሌሎችንም ሊረብሽ ይችላል። ሰውነታችን ኤክሶክራይን (Exocrine) እና አፖክራይን (Apocrine) የተሰኙ ሁለት አይነት ላብ አመንጪ እጢዎች አሉት። ኤክሶክራይን የተባሉት እጢዎች በሁሉም የሰውነታችን ክፍል የሚገኙ ሲሆን የአፖክራይን እጢዎች ደግሞ ጉርምስና እና ኩርድናን በሚያመላክቱና ፀጉር በሚወጣባቸው አካባቢዎች የሚገኙ ናቸው። የአፖክራይን እጢዎች ፕሮቲንና ስባማ ንጥረ ነገሮችን ያመነጫሉ፤ ይህም ነው ለሰውነት ጠረን መፈጠር ምክንያት የሚሆነው። ☑️ የመጥፎ የሰውነት ጠረን መንስኤዎች 💥 ቅመም የበዛባቸው ምግቦችን እንደ ነጭ ሽንኩርት፣ ዝንጅብል እና ማጣፈጫዎችን አዘውትሮ መመገብ 💥 ከላብ ጋር ተያይዞ የሚፈጠሩ ባክቴሪያዎች ☑️ መፍትሄዎች 🔹 ንፅህናን መጠበቅ፤ በየቀኑ ሻወር መውሰድ በተለይም ካላበን በኋላ በቀዝቃዛ ውሃ መታጠብ 🔸 ሻወር መውሰድ ባንችል እንኳን ሰውነታችንን ማደራረቅ 🔹 ሙቀት በበዛባቸው ስፍራዎች የአየር ማቀዝቀዣዎችን መጠቀም 🔸 እንደ አየር ሁኔታው ሳሳ ያሉ ልብሶችን መልበስ፤ ሙቀት አፍነው የሚይዙ ኮተን ልብሶችን አለማዘውተር 🔹 ልብሶቻችን በተለይም የውስጥ ልብሶቻችን በአጭር ጊዜ ልዩነት መቀየር 🔸 ቅመም የበዛባቸውን ምግቦችን ከመመገብ መቆጠብ 🔹 ፀረ ባክቴሪያ የሆኑ ሳሙናዎችንና ጄሎችን መጠቀም 🔸 ዲዮድራንት ወይም የላብ ማጥፊያ ከመጠቀማችን በፊት ብብታችን ደረቅ መሆኑን ማረጋገጥ። 👉 ከላይ የጠቀስናቸውን ሁሉ ተግባራዊ አድርገው የሰውነትዎ ጠረን የማይቀየር ከሆነ ግን ባለሙያዎችን ማማከር ተገቢ ነው። 👉 ከሁሉም በላይ ግን ዘወትር ንፅህናችንን መጠበቅ ካልተፈለገ የሰውነት ጠረን ያድናል። @DrSofonias

የልብ ድካም ህመም የልብ ድካም በአለማችን ቁጥር አንድ ገዳይ በሽታ ነው። በአለማችን ላይ በአመት ወደ ሰባት ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች በልብ ድካም ሳቢያ ህይወታቸውን የሚያጡ ሲሆን በሃገራችንም ቁጥሩ ከጊዜ ወደ ጊዜ በአሳሳቢ መልኩ እየጨመረ ይገኛል። የልብ ድካም ሲከሰት ወደ ልብ ጡንቻ የሚዘዋወረው ደም በከፊል ወይም ሙሉ ለሙሉ የሚቋረጥ ሲሆን ወደ ልብ ህዋሳት መሄድ ያለበት ኦክስጅንና ሌሎች ጠቃሚ ንጥረ ነገሮች ስለማይደርሱ የልብ የመምታት ስራ ይስተጓጉላል ማለት ነው። የልብ ድካም በዋነኝነት መንስኤው የልብ ደም ስር መጥበብ ሲሆን በተጨማሪም የኦክስጅን እጥረት፣ የልብ ደም ስር መኮማተርና የልብ ቀዶ ህክምና ሌሎች የልብ ድካም መነሻ ሊሆኑ ይችላሉ። ☑️ የልብ ደም ስር መጥበብ እንዴት ይመጣል? የልብ ጡንቻዎች ደም በተገቢው መልኩ ወደ ሰውነታችን ለማድረስ ያልተቋረጠ ኦክስጅንና ሌሎች እንደ ግሉኮስ ያሉ ንጥረ ነገር ያስፈልጋቸዋል፤ ይህንንም ለማግኘት ቀጫጭን የሆኑ የልብ የደም ስሮች በልብ ጡንቻዎች መሃል ተዘርግተው ይገኛሉ። አዘውትረን ቅባትና ስብ የበዛበት ምግቦችን የምንጠቀም ከሆነ እንደ ኮሌስትሮል ያሉ መጥፎ ስቦች በልብ ደም ስር ውስጥ መከማቸት ይጀምራሉ ፤ በጊዜ ሂደትም (እስከ 10 አመታት) የልብ የደም ስር መጥበብን ያስከትላል። ከልክ ያለፈ ውፍርት፣ የደም ግፊት፣ ሲጋራ ማጨስ፣ የአካል እንቅስቃሴ አለማድረግ፣ የስኳር በሽታ ለልብ ድካም ተጋላጭነትን ይጨምራሉ። ☑️ የልብ ድካም ምልክቶች በልብ የደም ስር የተከማቸው ስብ በድንገት ተላቆ የደም ዝውውሩን ሲገታ የልብ ድካም ምልክቶች ይከሰታሉ። ምልክቶቹም ከሰው ሰው ሊለያዩ ይችላሉ፤ እንዲሁም በሴቶችና ወንዶች መካከል ሊለያይ ይችላል። የልብ ድካም ያጋጠመው ሰው የሚከተሉትን ምልክቶች ያሳያል። 🍀 የደረት ህመም፡ የህመሙ ደረጃ ከትንሽ እስከ ከባድ ሊሆን ይችላል፤ 🍀 ታማሚው ደረቱ ላይ መክበድ፣ መጨምደድ፣ መግፋት ሊሰማው ይችላል፤ 🍀 ህመሙ ከ3 እስከ 5 ደቂቃ የሚቆይ ወይም ሄድ መለስ የሚል ይሆናል ነገር ግን ህመሙ ከ10 ደቂቃዎች በላይ ከቆየ አስጊ ደረጃ የመድረሱ ማሳያ ነው። 🍀 የልብ ድካምን ህመም ከቃር ጋር ሊመሳሰል ይችላል። ህመሙ የአቀማመጥ ቦታን በመቀያየር አይጠፋም። 🍀 የህመሙ ስሜት ወደ ትከሻ፣ የግራ እጅ፣ አገጭና አንገት መሰራጭት ሊኖረው ይችላል። 🍀 ለመተንፈስ መቸገር፣ ትንፋሽ መቆራረጥ፣ ቶሎ ቶሎ መተንፈስ፤ 🍀 በላብ መዘፈቅ፣ ማዞርና ድንግዝግዝ ማለት፤ 🍀 ማቅለሽለሽና ማስመለስ፤ 🍀 ድካም ድካም ማለት፤ 🍀 የሰውነት መገርጣት፣ ከንፈርና ጣቶች አካባቢ መጥቆር፤ 🍀 ራስን መሳት ሌሎች የልብ ድካም ምልክቶች ናቸው። የልብ ድካም ምልክቶች በሴቶች፣ በአዛውንቶች እና በስኳር ታማሚዎች ላይ የተለየ ምልክቶች ወይም ከነ ጭራሹም ምልክት ላያሳዩ ይችላሉ። ☑️ የልብ ድካም እንዴት እንከላከል? 💥 የደም ግፊት በትክክል መቆጣጥርና የታዘዘን መድሃኒት በትክክል መውሰድ፣ 💥 የተመጣጠነ የአመጋገብ ስርአት መከተል (ፍራፍሬ፣ ጥራጥሬ፣ የእጽዋት ተዋጽኦ ዘይቶችን…) 💥 የኮሌስትሮል መጠን መቀነስ፤ 💥 ስኳር ህመም ካለ በአግባቡ ክትትል ማድረግ፣ 💥 አደንዛዥ ዕፅ ከመጠቀም፣ ሲጋራ ከማጨስ፣ አልኮል ከመጠቀም መቆጠብ 💥 ከመጠን ያለፈ ውፍረት ማስወገድ እንዲሁም አካላዊ እንቅስቃሴ ማድረግ ያስፈልጋል። @DrSofonias

የማቀፍ የጤና ጥቅሞች 💎 የኦክሲቶሲን መጠን እንዲጨምር ያደርጋል። የኦክሲቶሲን (Oxytocin) መጨመር የብቸኝነት፣ የመለየት እና የንዴት ስሜትን ለማስወገድ ይረዳል። 💎 ረዘም ላለ ጊዜ ተቃቅፎ
የማቀፍ የጤና ጥቅሞች 💎 የኦክሲቶሲን መጠን እንዲጨምር ያደርጋል። የኦክሲቶሲን (Oxytocin) መጨመር የብቸኝነት፣ የመለየት እና የንዴት ስሜትን ለማስወገድ ይረዳል። 💎 ረዘም ላለ ጊዜ ተቃቅፎ መቆየት የሴሪቶኒን (Serotonin) መጠን እንዲጨምር ያደርጋል። ይህም ሙድን በመጨመር የደስታ ስሜትን ያጎናጽፋል። 💎 የሰውነትን በሽታ የመከላከል አቅምን ከፍ ያደርጋል። 💎 ጡንቻዎቻችን ዘና እንዲሉ ያደርጋል። 💎 ህመም ወይም በሽታ ከእርስዎ እንዲርቅ ያደርጋል። 💎 ወደ ለስላሳ የሰውነት አካሎች የደም ፍሰትን በመጨመር ህመምዎን ያስታግሳል። 💎 የነርቭ ሥርዓትን ያመጣጥናል። 💎 መተቃቀፍ መመሰጥ እና ሳቅን ይተካል። 💎 ግጭትንና ውጥረትን (ጥልን) ያረግባል። (ጥል ከመጀመሩ በፊት ቢሆንም እንኳን)። 💎 በልጅነት ወቅት መታቀፍ እና ፍቅር፤ ልጆች ጤናማ ሆነው እንዲቆይ ያደረጋል። 💎 ከአንድ በላይ በሆነ መንገድ ለልብዎ ጤንነት አስፈላጊ ነው። መልካም ጤንነት!!

ወንዶች የመራባት እድላቸውን እንዴት መጨመር ይችላሉ? 💥 ጭንቀት፣ ውጥረት እና ድካምን መቀነስና መቆጣጠር። 💥 ሲጋራ እና የአልኮል መጠጦችን ያቁሙ። 💥 ጤናማ እና የተስተካከለ የሰውነት ክብደት
ወንዶች የመራባት እድላቸውን እንዴት መጨመር ይችላሉ? 💥 ጭንቀት፣ ውጥረት እና ድካምን መቀነስና መቆጣጠር። 💥 ሲጋራ እና የአልኮል መጠጦችን ያቁሙ። 💥 ጤናማ እና የተስተካከለ የሰውነት ክብደት ይኑርዎ። 💥 ከፍተኛ የዚንክ መጠን ያላቸው ምግቦች (ሥጋ፣ እንቁላል፣ ጥራጥሬዎችና የባህር ውስጥ ምግቦች) እንዲሁም ሰሊኒየም (የባህር ውስጥ ምግቦች፣ እንጉዳይ፣ ስጋና ለውዝ) እንዲሁም ቫይታሚን ኢ ይመገቡ። 💥 በቻሉት መጠን የሃፍረተ ስጋ ፍሬዎ (Testicles) እንዲቀዘቅዙ ያድርጉ። ከዛሬ ጀምሮ ረዘም ላለ ጊዜ ሙቅ ሻወር እና ሳውና ባዝ አይውሰድ ምክንያቱም የስፐርም (Sperm) ሴሎችን ቁጥር ስለሚቀንስ ነው። መልካም ጤንነት!! ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ የጤና መረጃ ለማግኘት፤

በቂ ፋት እያገኙ እንዳልሆነ የሚያሳዩ ምልክቶች ፋት ያለባቸው ምግቦች ብዙውን ግዜ በመልካም ጎኑ ስማቸው ሲነሳ አይሰማም። ነገሩ እንዳለ ሆኖ ግን ፋት ያለበት ምግብ መመገብ ብቻውን የሰውነት ክብደታችን ያለመጠን እንዲጨምር አያደርግም። በአግባቡ እስከተመገብን ድረስ። ሰውነታችን በተፈጥሮው ፋት ይፈልጋል። ሰውነታችን የሚፈልገውን የፋት መጠን በአግባቡ ካልሰጠነው በጤናችን ላይ የራሱ የሆነ አሉታዊ ተጽዕኖ ያስከትላል። ሰውነታችን በቂ መጠን ያለው ፋት ሳያገኝ ሲቀር የሚከሰቱ ምልክቶች አሉ። ከእነዚህ ምልክቶች መካከል የሚከተሉት አምስቶቹ ዋነኞቹ ናቸው። 1. የቫይታሚን እጥረት (Vitamin deficiencies) እንደ ቫይታሚን ኤ፣ ዲ፣ ኢ እና ኬ (A, D, E & K)የመሳሰሉ የቫይታሚን አይነቶች በፋት የሚሟሙ (fat soluble vitamins) ይባላሉ። ሰውነታችን እነኚህን ቫይታሚኖች መጦ ለመጠቀም የፋት ይዘት ያላቸው ምግቦችን ማግኘት ይፈልጋል። ይህ በማይሆንበት ግዜ የእነዚህ ቫይታሚኖች እጥረት ሰውነታችን ይገጥመውና ለሚከተሉት የጤና እክሎች ልንጋለጥ እንችላለን:- 🔸 በምሽት ለማየት መቸገር (night blindness) 🔸 የጸጉር ድርቀት (dry hair) 🔸 መሃንነት (infertility) 🔸 የጡንቻ ህመም (muscle pain) 🔸 ድብርት (depression) 2. የቆዳ መቆጣት (Dermatitis) የኤን ሲ ቢ አይ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ፋት የቆዳ ጤንማነት ላይ ትልቅ ድርሻ አለው። በቂ የሆነ ፋት ካላገኘን ሰውነታችን ዴርማቲቲስ ለተባለው ለቆዳ መቆጣት በሽታ የመጋለጥ እድላችን ሰፊ ነው። 3. የቁስል በቶሎ ያለመዳን በፋት እጥረት ምክንያት እንደ ቫይታሚን ኤ እና ዲ የመሳሰሉ ቫይታሚኖች እጥረት ሊከሰት ይችላል። ይህም እነኚህ ቫይታሚኖች በቁስል በቶሎ መዳን ላይ ያላቸውን ሚና ስለሚያሳጣን የቁስል በቶሎ ያለመዳን ችግር ሊከሰት ይችላል። 4. የጸጉር መነቃቀል ፕሮስታግላንዲንስ (Prostaglandins) የተባሉ የፋት ሞለኪውሎች በጸጉር እድገት እና ጤናማነት ላይ ትልቅ ድርሻን ይጫወታሉ። በቂ ፋት ያለመመገብ ይህን ፋቲ ሞሎኪውል በበቂ መጠን እንዳናገኝ ስለሚያደርግ ለጸጉር ወዝ ማጣት እና የመነቃቀል ችግር ሊያጋልጠን ይችላል። 5. ተደጋጋሚ ህመም በበቂ መጠን ፋት ያለማግኘት ሰውነታችን ሊኖረው የሚገባውን የበሽታ መከላከል አቅም (Immunity) ይጎዳል። ሰውነታችን በሽታን የመከላከል አቅሙን ለማደበር ከሚፈልጋቸው ነገሮች ውስጥ አንዱ ፋት ነው። ይህም በመሆኑ በቂ ፋት አለመመገብ ደካማ የበሽታ መከላከል ስረዓትን በማዳከም በቀላሉ ለበሽታዎች የምንጋለጥበትን እድል ይፈጥራል። ☑️ ጤናማ ፋት ያላቸው ምግቦች የትኞቹ ናቸው? ፋት መመገብ ሲባል የግድ ጮማ ስጋ መቁረጥ ማለት አይደለም። በቀላሉ የፋት ይዘት ልናገኝባቸው ከምንችልባቸው ምግቦች መካከል የሚከተሉት ይጠቀሳሉ:- 🍀 አቮካዶ 🍀 እንቁላል 🍀 አሳ 🍀 ለውዝ 🍀 እርጎ 🍀 ኦሊቭ ኦይል @DrSofonias

ክብደት ለመጨመር ምን ላቁም? ምንስ ልመገብ? ክብደት መጨመር ክብደት ለመቀነስ ከሚደረገው ተግባር እኩል ተመሳሳይ ትጋት ይፈልጋል። ትክክለኛውን አመጋገብ በመምረጥ ደግሞ ምንም የማናሳካው ግብ አይኖርም። እርግጠኛ መሆን የሚቻለው ዝቅተኛ ክብደት ያላቸው ሰዎች ተጨማሪ ክብደት የሚያገኙባቸውን አማራጮች ለማወቅ ከፍተኛ ጉጉት ያድርባቸዋል። ውፍረት ከሽብር አደጋ ባልተናነሰ የዓለማችን ስጋት በሆነበት ዘመን የተስተካከለ አቋም እንዲኖረን በርካታ ጥረቶችን እናደርጋለን። በተመሳሳይ ሁኔታ ከልክ ባለፈ ሁኔታ ዝቅተኛ ክብደት ያላቸው ሰዎችም፣ ለበሽታ ሊኖራቸው የሚችለውን ተጋላጭነት ለመቀነስ፣ ለብሰው እንዲያምርባቸውና በሂደቱ ሊከሰትባቸው የሚችለውን ምቾት ማጣት ለማስወገድም እንዲሁ፣ ተጨማሪ ክብደት በሰውነታቸው ላይ ለመጨመር የመፍትሄ በሮችን ሁሉ ያንኳኳሉ። ባለሙያዎች ታዲያ ከመፍትሄ አቅጣጫዎች የምናገኘው ስብ ወይስ ጡንቻ የሚለውን ቀድመን መለየት እንዳለብን ያስገነዝቡናል። አንዳንዶቹ በሰውነታቸው ላይ ስለሚጨምሩት ክብደት ትኩረት አይሰጡም። ጡንቻ፣ ስብ ወይም የሁለቱ ጥምረት፤ እነዚህ ሰዎች ከብዶና ወፍሮ መታየት ብቻ ስለሆነ ዓላማቸው ወደ ባሰ ሁኔታ ሊሸጋገሩ ይችላሉ። ለወንዶችም ሆነ ለሴቶች በተሻለ ሁኔታ ክብደት በሰውነታቸው ላይ መጨመር ስለሚችሉበት መንገድ፣ ከምርምር ውጤቶች የተገኙትን እነዚህ መመሪያዎች በተቻለ መጠን ለመተግበር እንሞክር፡፡ 💎 በቀን 5-6 ጊዜ መመገብ ክብደት ለመጨመር በቀን ከ5 እስከ 6 ጊዜ መመገብ መጀመር ይኖርብናል፡፡ ታዲያ የመመገቢ ሰዓታችን በሚገባ መከፋፈል ይኖርብናል፡፡ ምክንያቱም በአንድ ጊዜ በምንወስደው ከፍተኛ ምግብ ሳቢያ ጨጓራችንም በስርዓት መፍጨት እንዳይችልና ሰውነታችን ሁሉንም ካሎሪዎች መቀበል እንዳይችል ምክንያት ይሆናል። እርግጥ ነው በየ3 ሰዓታት ልዩነት የምግብ ፍላጎታችን ላይነሳሳ ይችላል፡፡ ነገር ግን ጫን ብለን መመገባችንን መቀጠል ይኖርብናል፡፡ በየዕለቱም የምግብ ፍላጎታችን እያደገ ስለሚመጣ፣ መቸገራችን ይቀንሳል፡፡ በተቻለ መጠን ታዲያ በአመጋገባችን ውስጥ ጤናማ ምግቦችን መምረጣችንን እርግጠኛ መሆን ያስፈልጋል፡፡ 💎 ክብደት የማንሳት ልምምዶችን በሳምንት ሶስት ጊዜ ማድረግ በክብደቶች በመታገዝ እንቅስቃሴዎችን ማድረግ ስንጀምር ጡንቻዎቻችንን ማሳደግ እንችላለን፡፡ በሂደትም የክብደቶቹን ሚዛን መጨመር ያስፈልጋል፡፡ ይሄ በተለይ ከሰውነት ክብደታችን ባሻገር ጥንካሬያችንን ማሳደግ እንድንችል የሚረዳን ነው፡፡ 💎 ከ300-500 ካሎሪዎችን ማከማቸት ቀደም ሲል እንደተገለፀው፣ ከ300-500 የካሎሪ መጠን ማከማቸት የምንፈልገውን የክብደት መጠን እንድናገኝ የሚያደርገን ከሆነ መሞከሩ አይከፋም፡፡ ይሄንን የካሎሪ መጠን ደግሞ ሥጋ፣ ዕንቁላል፣ ቺዝ እና ተያያዥ ምግቦችን በመውሰድ ነው ማግኘት የምንችለው፡፡ 💎 ሁሉንም የሰውነት ክፍል ማሰራት በጂም ወይም በቤት ውስጥ ስፖርት የምንሰራ ወይም ክብደት የምናነሳ ከሆነ ሁሉም የሰውነት ክፍላችን በሚገባ እየሰራ መሆኑን ነው በቅድሚያ ማረጋገጥ ያለብን። ምክንያቱም ብዙዎቻችን ትኩረት የምናደርግባቸው ብዙ የጡንቻ ክፍሎች አሉንና ስፖርቱን የሚጀምሩ ብዙ ሰዎች በአንገታቸው፣ ደረታቸው ወይም ማጅራታቸው አካባቢ ብቻ ትኩረት በመስጠት ልምምድ በማድረግ ትልቅ ስህተት ይፈጽማሉ። ይሄ አካሄድ የሰውነታችን ሚዛን እንዲበላሽ በማድረግ ሰዎች የማይወዱትን ሰውነት እንድንላበስ ምክንያት ይሆናል። 💎 በፕሮቲን የበለፀጉ ምግቦችን ማዘውተር ቀደም ሲል እንደተገለፀው ከ300-500 የካሎሪ መጠን ማከማቸት፣ የምንፈልገውን የክብደት መጠን እንድናገኝ የሚያደርገን ከሆነ ይሄንን የካሎሪ መጠን ደግሞ ሥጋ፣ ዕንቁላል፣ ቺዝ እና ተያያዥ ምግቦችን በመውሰድ ነው ማሳካት የምንችለው፡፡ 💎 ካሎሪዎች መጠጣት የተጠየቅነውን ካሎሪ በመብላት ብቻ ሟሟላት አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል፡፡ ስለዚህ ወተትና የወተት ተዋፅኦዎችን፣ እንዲሁም አነስተኛ ስኳር ጋር በፕሮቲን የበለፀጉ መጠጦችን ነው ማዘውተር ያለብን፡፡ 💎 በፍጥነት መመገብ ይሄ ምክር በተቃራኒ ውፍረታቸውን መቀነስ ለሚፈልጉ ሰዎች የሚታዘዝ ነው። ሰውነታችን በቂ ምግብ ስለማግኘቱ ምላሽ እንዲሰጠን የተወሰኑ ጊዜዎችን ይፈልጋል። ስለዚህ በፍጥነት መመገባችን ከሰውነታችን የጥጋብ ምልክት ከማግኘታችን አስቀድመን ብዙ እንድንመገብ ያደርገናል። 💎 ለማገገሚያ የተለያዩ አማራጮችን መከተል የማፍታቻ እንቅስቃሴዎች፣ ሻወር፣ በካርቦ-ሃይድሬት የበለፀጉ ምግቦች ሰውነታችን በፍጥነት እንዲያገግም ያደርጋሉ። ታዲያ የ8፡00 ሰዓት እንቅልፍ እንዳይዘነጋ። 💎 በራሳችን ላይ ትዕግስት ይኑረን ጤናማ ባልሆነ አካሄድ በፍጥነት ተጨማሪ ክብደትን ማግኘት ተጨባጭ አይደለም። የተቀመጡ መመሪያዎችን በመከተል በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ከ1-2 ኪሎ ብቻ ነው ማግኘት የሚቻለው። ባለሙያዎች ፈጣን ለውጥ ካላገኘን በቀላሉ ስሜታችን ሊጎዳብን አይገባም ይሉናል። ምክንያቱም የሁሉም ሰው ሰውነት ልዩነት ስላለው። 💎 በራስ መተማመን ክብደት ለመጨመር ያወጣነው ዕቅድ ክብደት የሚለካው ለስኬታማነቱ በራሳችን ላይ ያለን መተማመን ነው። ከጠንካራ ሥራ በኋላ ለውጥ ማየት ባንችልም፣ ሌላና እጅግ ጠንካራ ወደ ሆነ ልምምድ መግባት ይኖርብናል። ተጨማሪ ምግብ መመገብ፣ ተጨማሪ ክብደቶችን ማንሳት፣ የውስጥ ጥንካሬን አስጠብቆ መቆት ናቸው፣ ክብደት መጨመር ከሚፈልግና በራሱ ከሚተማመን ሰው የሚጠበቀው፡፡ 💎 ረዥም ርቀት መሮጥ ውጤት የለውም መሮጥ ግዴታ ከሆነ አጫጭር ርቀቶችን እና አቀበቶችን መውጣት ነው ተመራጩ። ለዚህ ጥሩ ማሳያ የአጭር እና ረዥም ርቀት ሯጮችን ሰውነት መመልከት ነው። የትኛውን ነው መሆን የምፈልገው? በማለት ራስን መጠየቅ ደግሞ መሰረታዊ ነው። 💎 መተኛት ከፍተኛ ክብደት ለመጨመር በቀን ቢያንስ 8 እና 9 ሰዓት መተኛት ጥሩ አማራጭ ነው። ሰውነታችን ምንም ስራ እንዳይሰራ በማድረግ በተኛበት ጡንቻ እንዲገነባ እናስችለዋለን። በቀን ውስጥ ከ6 ሠዓት እና ከዚያ በታች እንቅልፍ እያገኘን ከሆነ፤ በአመጋገባችንና በስፖርት እንቅስቃሴዎች ያመጣናቸውን ለውጦች ማስጠበቅ አንችልም። @DrSofonias

በዘር የሚተላለፉ በሽታዎች የተወሰኑ በሽታዎች በዘር ወደ ልጅ ወይም ወደ የልጅ ልጅ እየተላለፉ ይሄዳሉ። አንዳንዶቹ በሽታዎች በተፈጥሮ የሰውነት አወቃቀር ምክንያት የሚመጡ፤ አንዳንዶች ደግሞ ተመሳሳይ የመኖሪያ ቦታን በመጋራት፣ ተመሳሳይ ምግብ ሁሌ በመመገብ እና በመሳሰሉት ምክንያቶች ሊይዝዎት ይችላሉ፡፡ ከእነዚህ በዘር ከሚተላለፉ በሽታዎች ውስጥ የተወሰኑትን ከዚህ ቀጥሎ በአጭሩ እንመለከታለን፡፡ 1. የስኳር በሽታ ሁለቱም ዓይነት 1 አይነት እና 2 የሚባሉት የስኳር በሽታ አይነቶች በዘር ይተላለፋሉ፡፡ በየትኛውም ዓይነት የስኳር በሽታ ተጠቂ የሆነ የቤተሰብ አባል ካሎት ከጊዜ ወደ ጊዜ የደሞን የስኳር መጠን እየተመረመሩ ይከታተሉት። ምንም እንኳን ዓይነት 1 የስኳር በሽታን እንዳይዘን ማስቀረት ባይቻልም፤ ዓይነት 2 ግን እንችላለን፡፡ ይህም የሚሆነው በጤናማ አመጋገብና ስፖርትን በመሥራት ነው፡፡ 2. የጡት ካንሰር የጡት ካንሰር ጂን 1 እና የጡት ካንሰር ጂን 2 በመባል የሚታወቁ በዘር የሚተላለፉ የሰውነት መዋቅሮች (ጂኖች) አሉ፡፡ የቤተሰብዎ አባላት በተለይም እናትዎ፣ እህትዎ ወይም ሴት ልጅዎ የጡት ካንሰር ተጠቂ ከሆኑ በቶሎ እርስዎም መመርመር ይኖርብዎታል፡፡ 3. የማህፀን ካንሰር ይህን ዓይነት ካንሰር የጡት ካንሰር ጂኖች እራሳቸውን በመለወጥ ሊያመጡት ይችላሉ፡፡ እናቶ፣ የሴት ልጅዎ ወይም እህትዎ የማህፀን ካንሰር ተጠቂ ከሆኑ እርስዎም በህይወትዎ የ 5 በመቶ በዚህ በሽታ የመያዝ ዕድል አለዎት፡፡ በሽታው ሳይባባስ በጊዜ ለማወቅ መመርመር ይበጃል፡፡ 4. ከፍተኛ የደም ግፊት ከፍተኛ የደም ግፊትን ተመርምሮ የታዘዘን መድሃኒት በተገቢው መልክ በመከታተል፣ ጤናማ አመጋገብ በመመገብና የሰውነት እንቅስቃሴ (ስፖርትን) በመሥራት ልንቆጣጠረው እንችላለን። ነገር ግን ብዙ ሰዎች በሽታው በጣም እስኪባባስ ድረስ እንዳለባቸው አያውቁትም፡፡ ከወላጆች አንዳቸው የደም ብዛት ተጠቂ ከሆኑ፤ በየጊዜው በመመርመር ጤናዎን መከታተል ይኖርብዎታል፡፡ 5. ከፍተኛ ኮሌስትሮል ኮሌስትሮል የምንለው በቀይ የደም ሴሎች (በደምዎ) ውስጥ የስብ ብዛትን ነው፡፡ በበዛ ቁጥር ለጤና በጣም አደገኛ ነው፡፡ የኮሌስትሮል መጠንዎን ጤናማ አመጋገብን በመከተልና ስፖርት በመስራት ሊቆጣጠሩት ይችላሉ። ነገር ግን የኮሌስትሮል መጠንዎን የማይቆጣጠሩት ከሆነና ወላጅዎ ወይም ልጅዎ ከ55 ዓመታቸው በፊት ለልብ ህመም የተጋለጡ ከሆነ አደጋ ላይ እንደሆኑ ይወቁ፡፡ የኮሌስትሮል መጠነንዎን በየጊዜው ይከታተሉ፡፡ 6. ግላኮማ ግላውኮማ በዘር የሚተላለፍ የዓይን በሽታ ነው፡፡ በቤተሰብዎ ውስጥ የግላውኮማ ችግር ካለ ጨርሶ እንዳይዝዎት ማድረግ ባይቻልም በህክምና ማዳን ግን ይቻላል፡፡ 7. ድብርት በድብርት ምክንያት የመጣ የአእምሮ ህመም በቤተሰብዎ ውስጥ ካለ ያ የታመመ ሰው በዘር ተላልፎበት ሊሆን ይችላል፡፡ አንድ ነገር ግን ልብ ይበሉ። ይህ በሽታ ሁሌ በዘር ብቻ ተላልፎ አይዝም፡፡ በቤተሰብዎ ውስጥ ይህ በሽታ ባይኖርም እርስዎ በራሶ ሊይዝዎት ይችላል፡፡ 8. አለርጂ እና የአስም በሽታ አለርጂ የምንለው ለምሳሌ የአበባ የወንዴ አባላዘር ብናኝ ሲሸተን ዓይናችንን የመቆጥቆጥ እና የመቅላት፣ የመተንፈሻ አካሎቻችን ማሳከክ እና ለመተንፈስ መቸገር ዓይነት ምልክት ካሳየን አለርጂ ብለን እንጠራዋለን፡፡ ይህም አለርጂ በዘር ይተላለፋል፡፡ ከወላጅዎ አንዳቸው በአለርጂ ከተጠቁ እርስዎም 50 በመቶ የመያዝ ዕድል አሎት፡፡ ሁለቱም ወላጆቾ ደግሞ ካለባቸው የ75 በመቶ የመያዝ ዕድል አለዎት ማለት ነው። አስምም ብዙ ጊዜ ከአለርጂ ጋር በአብዛኛው ዝምድና አለው ተብሎ ይታመናል። አብዛኛዎቹ አስም ያላቸው ህፃናት አለርጂም አለባቸው። ሁለቱም ደግሞ በዘር ይተላለፋሉ፡፡ @DrSofonias

ለቶንሲል በሽታ አሪፍ መፍትሄ

#የስኳር በሽታ ያለበት ሰው በተቻለው መጠን ጤናማ ሆኖ እንዴት መኖር ይችላል? በዶ/ር ተመስገን ደጀኔ አየለ 👇👇👇 የስኳር በሽታ ታማሚ ጤንነቱን ጠብቆ ለመቆየት መከወን ያለበት ዋና ቁልፍ የሆኑ
#የስኳር በሽታ ያለበት ሰው በተቻለው መጠን ጤናማ ሆኖ እንዴት መኖር ይችላል? በዶ/ር ተመስገን ደጀኔ አየለ 👇👇👇 የስኳር በሽታ ታማሚ ጤንነቱን ጠብቆ ለመቆየት መከወን ያለበት ዋና ቁልፍ የሆኑ ነገሮችን እንደ ሚከተሉት አስቀምጬያቸዋለው{በጣም ብዙ የሚወሱ ቢኖሩም ዋናዎቹ እነዚህ ናቸው ለበለጠ ማብራርያ መልክት ላኩልን በተቻለ ፍጥነት ከጊዜ ጋር ተዛምጄ መልስ ለመስጠት ሞክራለው } #🔸1 በደመችን ዉስጥ ያለውን የA1C የተባለዉን የደም ምርመራ በወቅቱ ማድረግ ላለፉት ጥቂት ወራቶች{3-4 ወር} በአማካይ በደማችን ዉስጥ የነበረዉን የስኳር መጠን ይነገረናል በተዘዋዋሪም መድሀኒት ሚጠቀሙ ከሆነ ምን ያህል መድሀኒቱ የስኳር መጠኑን በተፈለገው መንገድ እየተቆጣጠረ እንደነበርም መልስ ይሆናል ከዚህም በመነሳት ማስተካከል የነበሩ ነገሮ ካሉ ለምሳሌ 🔹አመጋገብ 🔹መድሀኒት አወሳሰድ 🔹የህይወት ዘይቤ ይበልጥ ማስተካከል ካለብን ለማስተካለ እንዲሁም መልካም ከሆነ አበጀ ብለን ለመቀጥል ይረደናል #🔸2 የስኳራ በሽታ ታካሚ የስኳር መጠኑን በየጊዜ እንደሚቆጠጠረው ሁሉ የደም ግፊቱንም መቆጣጠር ይኖርበታል ከፍተኛ የሆነ የደም ግፊት 🔹ለልብ ህመም 🔹ስትሮክ እንዲሁም 🔹ለኩላሊት ህመም ያጋልጣል በእንቅርትላይ ጆሮ ደግፍ ይል የሀገሬ ሰው #🔸3 የኮሌስትሮል መጠንን መቆጣር ሌላው ቁልፍ ጤናማ ሆኖ ለመኖር ከሚረዱ ያንበሳዉን ቦታ ይይዛል ቢባል ማጋነን አደለም

ከሰው ጋር በጥሩ ሁኔታ ለመግባባት አስፈላጊ 10 ችሎታዎች /TOP 10 ESSENTIAL SKILLS FOR EFFECTIVE COMMUNICATION ======================== ውጤታማ በሆነ መንገድ መግባባት መቻል አስፈላጊ ክህሎት ነው። በንግድ ህይወታችንም ይሁን በግል ግንኙነታችን ውስጥ ፣ ውጤታማ ግንኙነት ለስኬታችን ቁልፍ ነው። ውጤታማ የግንኙነት ሕይወት ማሰልጠን ይህንን ችሎታ ለመማር እና ለመድረስ አስደናቂ መንገድ ነው። በበርካታ የመገናኛ ሞዴሎች በኩል ፣ እንዴት ወደፊት እንደሚሄዱ እና ወደፊት እንደሚቆዩ አሳያችኋለሁ። ውጤታማ የሐሳብ ልውውጥ ለማድረግ የእኔ አሥር ዋና ዋና ክህሎቶች እዚህ አሉ። እነዚህን ክህሎቶች አሁን ይቆጣጠሩ ፣ እና እነሱ ለረጅም ጊዜ በደንብ ያገለግሉዎታል! 1. ማዳመጥ ውጤታማ የግንኙነት በጣም አስፈላጊ ገጽታዎች አንዱ ጥሩ አድማጭ መሆን ነው። ሰዎች ሊነግሩዎት የሚፈልጉትን ለመናገር ብቻ ፍላጎት ካላቸው ከሌሎች ጋር መገናኘት አይወዱም ፣ እና እርስዎ የሚሉትን አይሰሙ። ውጤታማ ግንኙነት ንቁ ማዳመጥን ይጠይቃል ፣ ስለዚህ ሁለተኛ ተፈጥሮዎ እስኪሆን ድረስ ንቁ ማዳመጥን ይለማመዱ። ስለዚህ ንቁ ማዳመጥ ምንድነው? ንቁ ማዳመጥ አንድ ሰው የሚነግርዎትን መስማት እና መረዳትን ያካትታል። አንድ ሰው የሚነግርዎትን በግልፅ እስካልተረዱ ድረስ ተገቢ ምላሽ መስጠት አይችሉም። ለእርስዎ የሚነገርለትን መልእክት ሙሉ በሙሉ እንደሚረዱት እርግጠኛ ለመሆን ጥያቄዎችን በመጠየቅ ወይም የሚናገሩትን እንደገና ይድገሙ። ለምሳሌ ፣ “ስለዚህ ፣ እርስዎ የሚሉት ነው…” ማለት ይችላሉ 2. የቃል ያልሆነ ግንኙነት እኛ የምንመርጣቸው ቃላት የሚያስተላልፉት መልእክት 7% ብቻ ነው ፣ ይህም የቃል ያልሆነ ግንኙነትን የበለጠ አስፈላጊ ያደርገዋል። የሰውነት ቋንቋ አስፈላጊ የግንኙነት መሣሪያ ነው። የሰውነት ቋንቋዎ ቃላትዎን ለማስተላለፍ መርዳት አለበት። ሊታሰብባቸው የሚገቡ ሌሎች ምክንያቶች እንደ የድምፅዎ ድምጽ ፣ የእጅ ምልክቶች እና የዓይን ንክኪነትን የመሳሰሉ ነገሮች ናቸው። ዘና ካላችሁ እና ወዳጃዊ ቃና ካላችሁ አንድ ሰው ከእርስዎ ጋር በግልፅ እንዲናገር ይበረታታል። ዘና ባለ እግሮች እና በተከፈቱ እጆችዎ ክፍት አቋም አቋም ይውሰዱ። ከሚገናኙበት ሰው ጋር የዓይን ንክኪ ማድረጉ አስፈላጊ ነው ፣ ግን ይህ በቀላሉ የማይመች ስለሆነ እንዳያዩዋቸው ይጠንቀቁ። በሌላ ሰው የሚታየውን የቃላት ያልሆኑ ምልክቶችን መገንዘብ እንዲሁ አስፈላጊ ነው። እነዚህ ምልክቶች ያ ሰው ምን እንደሚሰማው ግንዛቤ ይሰጡዎታል። 3. ግልጽ ይሁኑ እና ትክክለኛ ይሁኑ በተቻለ መጠን ጥቂት ቃላትን በመጠቀም መልእክትዎን ያስተላልፉ። በአካል ፣ በስልክ ወይም በኢሜል መልእክትዎን በግልጽ ፣ በአጭሩ እና በቀጥታ ያስተላልፉ። በቃላትዎ ከመጠን በላይ ከሆኑ አድማጩ ትኩረቱን ያጣል ወይም ምን እንደፈለጉ እርግጠኛ አይሆንም። ከመናገርዎ በፊት ማስተላለፍ የሚፈልጉትን መልእክት በተመለከተ ትንሽ ያስቡ። ይህ እርስዎን ከመጨናነቅ እና ግራ መጋባት እንዳይፈጥሩ ይከላከላል። 4. ሰው ሁን ከአንድ ሰው ጋር ፊት ለፊት በሚገናኙበት ጊዜ ፣ ​​በቀላል ፈገግታ ወዳጃዊ ቃና ይጠቀሙ እና የግል ጥያቄን ይጠይቁ። እነዚህ ነገሮች ሌላኛው ሰው በሐቀኝነት ፣ በግልፅ ግንኙነት ውስጥ እንዲሳተፍ ያበረታታሉ። የጽሑፍ ግንኙነትን (ለምሳሌ ኢሜል) ሲጠቀሙ ቀለል ያለ የግል መልእክት በመጨመር ይህንን ማሳካት ይችላሉ ፣ ለምሳሌ ፣ “ቅዳሜና እሁድዎ እንዴት ነበር?”። 5. በራስ መተማመን በራስ መተማመን ሁሉንም ውጤታማ ግንኙነትን ያጠቃልላል። በራስ መተማመን የሚሰማዎት ከሆነ እርስዎ እንደሚሉት ሌሎች ሰዎች ያምናሉ። የዓይንን ግንኙነት ማድረግ ፣ ጠንካራ ግን ወዳጃዊ ቃና (በጭራሽ ጠበኛ) በመጠቀም ፣ በራስ መተማመንን ማሳደግ የሚችሉበት ሁሉም መንገዶች ናቸው። ያስታውሱ ሁል ጊዜ የሌላውን ሰው ማዳመጥ እና እነዚያን የንግግር ያልሆኑ ፍንጮችን መፈለግ። 6. ርኅራኄ ርህራሄ የሌላውን ሰው ስሜት የመረዳትና የማካፈል ችሎታ ነው። እርስዎ ከሚገናኙበት ሰው ጋር ባይስማሙ እንኳን ፣ የእነሱን አመለካከት መረዳትና ማክበሩ በጣም አስፈላጊ ነው። ለዚያ ሰው “የምትናገረውን ተረድቻለሁ” ማለቱ ፣ እርስዎ እንደሰሟቸው እና የእነሱን አመለካከት እንደሚያከብሩ ያሳውቃቸዋል። 7. ሁል ጊዜ ክፍት አእምሮ ይኑርዎት ውጤታማ ግንኙነት አድራጊ መሆን እያንዳንዱ ውይይት በተለዋዋጭ ፣ ክፍት አእምሮ መቅረብን ይጠይቃል። ይህ ሁልጊዜ ለማሳካት ቀላል አይደለም ፣ ግን ውጤታማ በሆነ መንገድ መግባባት በጣም አስፈላጊ ነው። ሁል ጊዜ በንቃት ማዳመጥ ውስጥ ይሳተፉ ፣ እና የሌላው ሰው አመለካከት ምን እንደ ሆነ በመገንዘብ ርህራሄን ማሳየትዎን ያረጋግጡ። ይህንን አካሄድ መከተል ሁል ጊዜ ሐቀኛ ፣ ውጤታማ ግንኙነትን ያረጋግጣል። 8. አክብሮት ያስተላልፉ እርስዎ እና ሀሳቦቻቸውን ካከበሩ ሌሎች ሰዎች ከእርስዎ ጋር የመግባባት ዕድላቸው ሰፊ ይሆናል። በቀላሉ ስማቸውን በመጠቀም ለሌላ ሰው መናገር ፣ አድናቆት እንዲሰማቸው ያደርጋል። በስልክ የሚገናኙ ከሆነ ሁል ጊዜ በውይይቱ ላይ ያተኩሩ እና በማንኛውም መንገድ እንዳይዘናጉ ያድርጉ። በኢሜል ሲገናኙ ፣ ተቀባዩን በስም ለማነጋገር ጥንቃቄ በማድረግ መልእክትዎን ለመገንባት እና ለማረም ጊዜ ይውሰዱ። 9. ግብረመልስ ይስጡ እና ይቀበሉ ተገቢ ግብረመልስ መስጠት እና መቀበል አስፈላጊ የግንኙነት ክህሎት ነው ፣ በተለይም የእኛ ሚና ሌሎች ሰዎችን ማስተዳደርን ያጠቃልላል። ገንቢ ግብረመልስ መስጠት ፣ እንዲሁም ለአንድ ሰው ውዳሴ መስጠት ፣ ተነሳሽነትን በእጅጉ ከፍ ሊያደርግ እና ሞራልን መገንባት ይችላል። የሌሎችን አስተያየት መቀበል እና ማበረታታት እንዲሁ አስፈላጊ ነው። ሁል ጊዜ ግብረመልስ ያዳምጡ እና በእሱ ላይ አዎንታዊ እርምጃ ይውሰዱ። ስለማንኛውም የግብረመልስ ገጽታ እርግጠኛ ካልሆኑ ፣ ከሌላ ሰው ማብራሪያ ለማግኘት በቀላሉ ጥያቄን ይጠይቁ። 10. ለሥራው በጣም ጥሩውን መካከለኛ ያስቡ! በዝርዝሬ ላይ ያለው የመጨረሻው ንጥል በጣም ጥሩው የመገናኛ ዘዴ ምን እንደሚጠቀም ማወቅ ነው። በጣም ጥሩውን የመገናኛ ዘዴን ለመጠቀም መታሰብ ምላሽዎ አዎንታዊ እንዲሆን ያደርገዋል። እንደ እርስዎ ከማን ጋር ለመገናኘት እየሞከሩ እንደሆነ ፣ ርዕሰ ጉዳዩ ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ እና ያ ሰው ምን ያህል ስራ እንደሚበዛባቸው ያሉ ነገሮችን ያስቡ። ለምሳሌ ፣ አለቃዎን የደመወዝ ጭማሪ መጠየቅ በጭራሽ በጽሑፍ ካደረጉት በጭራሽ በጭራሽ አይታሰብም - ስለዚህ ተገቢውን ያስቡበት! @DrSofonias

የአንጎል ጥቃት (stroke ) ምልክቶች ዋነኛ የስትሮክ ምልክቶች FAST በሚለው ቃል ሊታወሱ ይችላሉ- F - face - ፊት - ፊት በአንድ ጎን መውደቅ ወይም ማዘንበል፣ ፈገግ ማለት አለመቻል፣ ወይም አፋቸው ወይም ዐይናቸው በአንድ በኩል ሊያዘነብል ይችላል። A arm - ክንድ - በ ክንድ ውስጥ ባለው ድክመት ወይም የመደንዘዝ ስሜት የተነሳ ግለሰቡ ሁለቱንም እጆች ማንሳት እና እዚያ ላይ ማቆየት ላይችል ይችላል። S- speech ንግግር - ንግግራቸው ጠፍቶ ወይም ተጎድቶ ሊሆን ይችላል ፣ ወይም ግለሰቡ ንቁ ሆኖ ቢታይም በጭራሽ ማውራት አይችል ይሆናል ፡፡ አንዳንዴ ደግሞ የመረዳት ችግሮች ሊያጋጥማቸው ይችላል፡፡ T - Time ጊዜ - ከእነዚህ ምልክቶች ወይም ምልክቶች መካከል ማንኛውንም ካስተዋሉ ወዲያውኑ ለህክምና ለመደወል ጊዜው አሁን ነው። በተለይ በአደጋ ተጋላጭ በሆነ ቡድን ውስጥ ካሉ አዛውንት ወይም የስኳር ህመም ወይም ከፍተኛ የደም ግፊት ካለበት ሰው ጋር የሚኖሩ ከሆነ ወይም ለእንክብካቤዎ ሁሉም ሰው ማወቁ አስፈላጊ ነው ፡፡ በ ‹FAST› ምርመራ ውስጥ ያሉ ምልክቶች አብዛኛዎቹ የአንጎል ምልክቶች ይታያሉ ፣ ግን አልፎ አልፎ ቁስል የተለያዩ ምልክቶችን ያስከትላል ፡፡ ሌሎች የስትሮክ ምልክቶች የሚከተሉትን ሊያካትቱ ይችላሉ- - የሰውነት 1 ሙሉ አካል መስነፍ - ድንገተኛ ዕይታ ወይም ብዥታ መፍዘዝ -ግራ መጋባት -ሌሎች የሚሉትን ለመገንዘብ አስቸጋሪ ነው -ችግሮች ሚዛን እና ቅንጅት -የመዋጥ ችግር (dysphagia) -ከዚህ በፊት ከነበረው ከማንኛውም ሁኔታ በተለየ ሁኔታ ድንገተኛ እና በጣም ከባድ ራስ ምታት ያስከትላል -የንቃተ ህሊና ማጣት - የድምጽ ችግር -የሚዛን እና ቅንጅት ችግር - የመረዳት ችግር - የማውራት ችግር -የማንበብ እና መጻፍ ችግር የእነዚህ ምልክቶች ሌሎች ምክንያቶች ሊኖሩ ይችላሉ ፡፡ እባክዎን ይህን ጠቃሚ መረጃ ለወገኖ እንዲደርስ Share በማድረግ ይተባበሩን! @DrSofonias

የወንዶች የወሊድ መከላከያ እንክብል የወንዶች የወሊድ መከላከያ እንክብል 99 በመቶ ውጤታማ ሆኗል ተባለ በሚዋጥ እንክብል መልክ የተዘጋጀው የወሊድ መከላከያው እርግዝናን በመከላከል ረገድ ውጤታማ ነው ተብሏል አዲሱ የወሊድ መከላከያ በሴቶች ላይ ብቻ የነበረውን ጫና ያቃልላል የሚል ተስፋ ተጥሎበታል አዲስ እየተዘጋጀ ያለው የሚዋጥ የወንዶች የወሊድ መከላከያ እንክብል እርግዝናን በመከላከል ረገድ 99 በመቶ ውጤታማ መሆኑ ተገለፀ። የወሊድ መከላከያ እንክብሉ በአይጥ ላይ በተደረገ ሙከራ እርግዝናን ለመከላከል ውጤታማ መሆኑ እንደተረጋገጠ ስካይ ኒውስ ዘግቧል። በቅርቡ በአሜሪካ ኬሚካል ሶሳይቲ ስብሰባ ላይ ግኝታቸውን ያቀረቡት ተመራማሪዎች፤ አዲሱ የወንዶች የወሊድ መከላከያ እንክብል ውጤታማ መሆኑን ገልጸዋል። አዲሱን ግኝት ያቀረቡት ዶክተር በአብደላ አል-ኖማ፤ ተመራማሪዎች ለአስርት ዓመታት ያክል በአፍ የሚወጥ የወንዶች የወሊድ መከላከያ እንክብል ለመፍጠር ሲጥሩ ቆይተዋል፤ ሆኖም ግን እስካሁን እውቅና የተሰጠው መድሃኒት በገበያ ላይ የለም ብለዋል። የወንዶች የወሲብ ሆርሞን ቴስቴስትሮንን ኢላማ ያደረጉ በርካታ ክሊኒካል ሙከራዎች እየተደረጉ መሆኑን ያነሱት ዶክተር አብደላህ፤ ሆኖም ግን ከልክ ያለፈ የሰውነት ውፍረትን፣ ድብርትን እና ሌሎች የጎንዮሽ ጉዳቶችን የሚያስከትሉ ናቸው ብለዋል። አሁን የተሰራው የወንዶች የወሊድ መከላከያ እንክብል ግን ከሆርሞን ጋር ግንኙነት የሌለው መሆኑን በመጥቀስ፤ በቅርቡ በሰዎች ላይ ሙከራ ማድረግ እንደሚጀመር አስታውቀዋል። አዲሱ የወሊድ መከላከያ በሴቶች ላይ ብቻ የነበረውን ጫና ያቃልላል የሚል ተስፋ እንደጣለበት ተነግሯል። ምክንያቱም ሴቶች እርግዝናን ለመከላከል የተለያዩ መድሃቶችን ከመዋጥ ጀምሮ ማህፀን ውስጥ የሚገቡ መሳሪያዎችን እስከመጠቀም ይገደዳሉ። በተቃራኒው ወንዶች ግን ኮኖዶምን የሚጠቀሙ ሲሆን፤ ከዚህ ከዘለለ “ቫሴክቶሚ” የተባለ እና በቋሚነት እንዳይወልዱ የሚያደርገውን የቀዶ ጥገና አማራጭ ብቻ ነው ያለው። በወንዶች ላይ ለወሊድ መከላከያ የሚደረገው “ቫሴክቶሚ” የተባለው ቀዶ ጥገና ህክምና በዋጋው ውድ ሲሆን፤ ብዙም ስኬታማ እንዳልሆነ ይነገራል።