uz
Feedback
Benishangul Gumuz Education Bureau

Benishangul Gumuz Education Bureau

Kanalga Telegram’da o‘tish

ይህ ቻናል የቤኒሻንጉል-ጉሙዝ ክልል ትምህርት ቢሮ የቴሌግራም ቻናል ሲሆን ከክልል እስከ ትምህርት ቤቶች ድረስ የተከናወኑ እንዲሁም ሀገራዊ ፣ አህጉራዊ እና አለማቀፋዊ የትምህርት መረጃዎች ተደራሽ የሚደረጉበት ነው፡፡

Ko'proq ko'rsatish
7 330
Obunachilar
+424 soatlar
+287 kun
+27530 kun
Postlar arxiv
ከመማር ማስተማር ጎን ለጎን የውስጥን ገቢ በራስ አቅም ማሳደግ !የግልገል በለስ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ የበለስ ወንዝን በመጠቀም እያለማ ያለው የመስኖ ልማት ስራ አበረታች በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተገለፀ። ​(ግልገል በለስ:- መስከረም 25/2019) የግልገል በለስ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ የበለስ ወንዝን በመጠቀም አበረታች የሆኑ የልማት ስራዎችን እያከናወነ መሆኑ ተገለጸ። ኮሌጁ እያለማ ያለውን የመስኖ ልማት የክልል፣ የዞንና የወረዳ አመራሮችን ጨምሮ የዘርፉ ባለሙያዎች ተዘዋውረው ጎብኝተዋል። የግልገል በለስ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ዲን አቶ ብዙዓየሁ ሳንቢት፤ የበለስ ወንዝን በመጠቀም የሙዝ እና ሽንኩርት ሰብሎችን በስፋት በማልማት የውስጥ አቅምን በማሳደግ የምግብ ዋስትናን በራስ አቅም ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል። ኮሌጁ ከመማር ማስተማር ተልዕኮው ባለፈ የበለስ ወንዝን በአግባቡ በመጠቀም የመንግስት ኢኒሸቲቭ የሆኑ የልማት ስራዎችን በመስራት አበረታች ውጤት መገኘቱን አቶ ብሁዓየሁ ተናግረዋል። የመተከል ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ፍቃዱ ደበሎ፤ ኮሌጁ ያሳየው ተነሳሽነት ለሌሎች ተቋማት አርአያ መሆን እንደሚችል ገልፀው ይህ ተግባር ተጠናክሮ እንዲቀጥል ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በቅንጅት መስራት እንደሚገባ ገልፀዋል። በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ግብርና ቢሮ የተፈጥሮ ሀብት ልማት ዘርፍ ምክትል ቢሮ ሃላፊ አቶ አብዱልከሪም ሙሳ፤ ኮሌጁ ያለውን መሬት በአግባቡ በመጠቀም እያለማ ያለው ተግባር ከተቋሙ ሰራተኞች ባለፈ ለከተማዋ ነዋሪዎች በማቅረብ የኑሮ ውድነትን ለመቀነስ ወሳኝ መሆኑን አመላክተዋል። ቢሮው ለዚህ ስኬት የሚያደረገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አቶ አብዱልከሪም አረጋግጠዋል። Via MZC

ዐቢይ አሕመድ አሊ (ዶ/ር) በድጋሜ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ሆነው ተመረጡ::
+1
ዐቢይ አሕመድ አሊ (ዶ/ር) በድጋሜ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ሆነው ተመረጡ::

ሕፃናትን ወደ ትምህርት ቤት መላክ ብቻ ሳይሆን እንዲቆዩ ፤ እንዲማሩ እና በክህሎት እንዲዳብሩ ማድረግ የሁላችንም ሃላፊነት ነው !!

የአመራሮች የስራ ርክክብ መርሀ-ግብር ተካሄደ ---------   -----------    -------------   --------------- (መስከረም 25/2019 ዓ.ም ፤ አሶሳ) አዲሱ የተሾሙ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ  አቶ አመንቴ ገሺ ከቀድሞ የትምህርት ቢሮ ሃላፊ ተመስገን ዲሳሳ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት የስራ ርክክብ አድርገዋል፡፡   በዚህ የስራ ርክክብ ላይ በዕቅድና በትምህርት ፕሮግራሞች ዘርፍ ምክትል ቢሮ ሃላፊ ሆነው በአዲስ የተመደቡ አቶ ለሜሳ ኔኖ ፣ የቀድሞ ምክትል ቢሮ ሃላፊ አቶ በሺር አብዱረሂም እንደሁም በቢሮው የስርዓተ-ትምህርትና የትምህርት ተቋማት ዘርፍ ምክትል ቢሮ ሃላፊ አቶ መሀመድ ኡስማን ፣   የማናጄመንት አበላትና የቢሮው የሪፎርም ቴክኒካል ኮሚቴ አባላት በመርሀ-ግብሩ ላይ ተሳታፊ ሆነዋል፡፡   በ2019 የትምህርት ዘመን በተቋሙ ከፍተኛ ክብደት የተሰጣቸው ተግባራት አስመልክቶ የቢሮው የእቅድና ክትትል ዳሬክተሩ አቶ ቴዎድሮስ አበራ በመርሀ-ግብሩ ለተገኙ አካላት ገለጻ ተደርጓል፡፡ የቀድሞ የቢሮው ሃላፊ ተመስገን ዲሳሳ (ዶ/ር) የተጀመሩና በቀጣይ በአመራሩ የቅርብ ክትትልና ድጋፍ ያሻቸዋል ያሏቸውን ጉዳዮች በዝርዝር አንስተዋል፡፡   አዲስ የተመደቡ የቢሮው ሃላፊ አቶ አመንቴ ገሺ የቀድሞ ቢሮ ሃላፊ ፣ ምክትል ቢሮ ሃላፊዎችና የማናጄመንት አባላት ላደረጉላቸው አቀባበል አመስግነው ፤ ዘርፉ ላይ ውጤት ማምጣት ግዴታችን ነው ፤ የተመደብነውም ለውጥና መሻሻል ለመምጣት እስከሆነ ድረስ የማንጄመንቱ አበላትም በዚሁ ልክ ለጋራ ውጤት መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡   ሃላፊዎቹም ከመርሀ-ግብሩ በኃላ ከቢሮው ሪፎርም ጋር ተያይዞ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን ተዘዋውረው ጎብኚተዋል፡፡ ዘገባው የቢሮው ኮሙኒኬሽን ዳሬክቶሬት ነው፡፡

ትውልዱን በትምህርት ስርዓቱ መሠረት በዕውቀትና በክህሎት ለመቅረጽ ለሚተጉ የግል ተቋማት ቢሮው ያበረታታል ፤ ይደግፋል ፤ አቶ መሀመድ ኡስማን ------------- --------------- ------------ ------------------ (መስከረም 24/2019 ዓ.ም ፤ አሶሳ) የጉለደን የቅድመ አንደኛና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ምርቃትና የወላጆች ቀን ፕሮግራም ላይ የተገኙት በክልሉ ትምህርት ቢሮ የስርዓተ-ትምህርትና የትምህርት ተቋማት ዘርፍ ምክትል ቢሮ ሃላፊ አቶ መሀመድ ኡስማን ትውልዱን በትምህርት ስርዓቱ መሠረት በዕውቀትና በክህሎት ለመቅረጽ ለሚተጉ የግል ተቋማት መንግስት ያበረታታል ፤ ይደግፋል ብለዋል። በመንግሥት የትምህርት ተቋማት ብቻ የተማሪዎች ውጤትና ስነ-ምግባር ማሻሻል እንደማይቻል የሚገልጹት አቶ መሀመድ ወላጆቾ ልጆቻቸውን ከአልባሌ የቴክኖሎጂ አጠቃቀም እንዲታደጉና ከትምህርት ቤቱ ጋር በጥብቅ ቁርኝት እንዲሰሩ አሳስበዋል። የአሶሳ ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ ወ/ሮ ጎጃም አያና የግል ትምህርት ተቋማት በትምህርቱ ዘርፉ ያላቸውን ሚና በሙሉ ሃላፊነት እንዲወጡ አሳስበው ፤ የጉለደን ትምህርት ቤትም በከተማ አስተዳደሩ የተሻለ ተቋም ሆኖ እንዲሰራ አሳስበዋል። የትምህርት ቤቱ ስራ አስኪያጅ በሪሁን ሙጬ (ዶ/ር) እንደገለጹት በክልሉ በዕውቀትና በክህሎት የበቃ ትውልድ ኖሮ የክልሉ ሁለንተናዊ ልማት እንዲሻሻል የነገ ሀገር ተረካቢ በሆኑ ህጻናት ላይ ትምህርት ቤታቸው አበክሮ እንደሚሰሩ ገልፀው ፤ ለትምህርት ቤቱ እዚህ ደረጃ ላይ መድረስ ከክልሉ መንግስት ፣ ትምህርት ቢሮና ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያውን አመስግነዋል። የትምህርት ስራ ሃላፊዎችም የመማሪያ ክፍሎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል። ወላጆች ትምህርት ቤቱ በሚያቀርበው ሪፓርት ዙሪያ ውይይት ያደርጋሉ ፤ በቀጣይም የተሻለ አፈጻጸም እንዲኖረው ምክክር ያደርጋሉ። ትምህርት ቤቱ በተያዘው የትምህርት ዘመን 560 ተማሪዎችን ተቀብሎ በማስተማር ላይ ይገኛል።ዘገባው የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ትምህርት ቢሮ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።

ውጊያችን መሃይምነትን ከማጥፋት በዘለለ ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም የሚገቡ ተማሪዎችን ቁጥር ማሳደግ ነው ፤ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ሃላፊ አቶ አመንቴ ጌሼ ----------- ------------- --------------- -------- (መስከረም 23/2018 ዓ.ም ፤ አሶሳ) ውጊያችን መሃይምነትን ከማጥፋት ባለፈ ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም የሚገቡ ተማሪዎችን ቁጥር ማሳደግ ነው ሲሉ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ሃላፊ አቶ አመንቴ ጌሼ ተናገሩ። ሃላፊው ይህን የገለጹት በክልሉ ከ21 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለተውጣጡ መምህራን ሲሰጥ በቆየውና በማጠቃለያ መድረክ ሲሆን በየደረጃው የሚገኙ ተማሪዎች ውጤት ማሻሻል የተቋሙ የቅድሚያ ተግባር ሆኖም ይሰራል ብለዋል። መምህራን ሚናቸው ከፍተኛ መሆኑን የጠቀሱት አቶ አመንቴ ቢሮው በግብዓትና ሂደት ላይ ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል። በ2018 የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ውጤት ከማሻሻል ረገድ አበረታች ውጤት መመዝገቡን የጠቀሱት የቀድሞ የቢሮው ሃላፊ የአሁኑ የክልሉ ኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ ቢሮ ሃላፊ ተመስገን ዲሳሳ (ዶ/ር) ይህን ውጤት በቀጣይ ይበልጥ ለማሻሻል በጋራ እንሰራለን ብለዋል። በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት የቴክኒክና የተግባር ትምህርት እዲሰጥ መደረጉና ከመ/ቤታቸው ጋር ትስስር እንዲኖረው መልካም አጋጣሚ ሲሆን በቀጣይ በቅርበትና በቅንጅት ከክልሉ ትምህርት ቢሮ ጋር እንሰራለን ያሉት የክልሉ የስራና ክህሎት ቢሮ ሃላፊ አቶ አብዱልሰላም ሸንገል ናቸው። የሙያ ትምህርቶች አሁን ላይ ተፈላጊነታቸው እያደገ መምጣቱን የገለጹት አቶ አብዱልሰላም በቀጣይ በቴክኒክና ሙያ ትምህርት ተማሪዎችን በሻለ ደረጃ መ/ቤታችን ይቀበላል ብለዋል። የተሰጠው ስልጠና በቀጥታ የተማሪዎችን ውጤት በሚያሻሽል የተማሪዎች የመማር ብቃት ማሻሻልን መሠረት አድርጎ ስልጠናው የተሰጠ ሲሆን ከዕውቀት ፣ ከክህሎት ፣ ከአመለካከትና ግላዊ ማድረግ እስከሚያስችል እንደሆነ ታውቋል። ስልጠናው በጄናቫ ግሎባል ድርጅት ድጋፍ የተሰጠ ሲሆን የድርጅቱ የክልሉ ዳሬክተር አቶ ሸምሰዲን መሀመድ በቀጣይ በትኩረት የሚከናወኑ ስራዎችን ለሁሉም ተሳታፊዎች ማብራሪያ ሰጥተዋል። ስልጠና በአሶሳ ዩኒቨርስቲ መምህራን የተሰጠ ሲሆን የሁለተኛ ደረጃ መምህራን ፤ ከክልሉ ስራና ክህሎት ቢሮና ከቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ መምህራንና ባለሙያዎች ተሳታፊ ሆነዋል። ዘገባው የቢሮው ኮሙኒኬሽን ዳሬክቶሬት ነው።

አቶ ለሜሳ ኔኖ በክልሉ ትምህርት ቢሮ የዕቅድና የትምህርት ፕሮግራሞች ዘርፍ ምክትል ቢሮ ሃላፊ ሆነው ተመድበዋል።
አቶ ለሜሳ ኔኖ በክልሉ ትምህርት ቢሮ የዕቅድና የትምህርት ፕሮግራሞች ዘርፍ ምክትል ቢሮ ሃላፊ ሆነው ተመድበዋል።

የተከበሩ አቶ አመንቴ ጌሼ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ሆነው ተመድበዋል። መልካም የስራ ዘመን እንዲሆንላቸው እንመኛለን።
የተከበሩ አቶ አመንቴ ጌሼ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ሆነው ተመድበዋል። መልካም የስራ ዘመን እንዲሆንላቸው እንመኛለን።

የክልሉ ምክር ቤት በርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን የቀረቡ የአስፈጻሚ አካላትን (ካቢኔ) ሹመት አጽድቋል። ** በዚህም መሠረት፦ 1. አቶ ጌታሁን አብዲሳ - ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና የሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ኃላፊ 2. አቶ ኢሳቅ አብዲልቃድር - የከተማ እና መሠረተ ልማት ቢሮ ኃላፊ 3. አቶ ባበክር ኻሊፋ - የግብርና ቢሮ ኃላፊ 4. ተመስገን ዲሳሳ (ዶ/ር) - ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ 5. ወ/ሮ አለምነሽ ይባስ - የክልሉ ሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ 6. አቶ መሐመድ አልማሂ - የንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ 7. አቶ ቃሲም ኢብራሂም - የፕላንና ልማት ቢሮ ኃላፊ 8. አቶ አመንቴ ገሺ - የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ 9. አቶ ቢንያም መንገሻ - የሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ 10. ወ/ሮ ሃጂራ ኢብራሂም - ውሃና ኢነርጂ ሃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ 11. አቶ ወልተጂ በጋሎ - የጤና ቢሮ ኃላፊ 12. ነጻነት ዘለቀ (ዶ/ር) - የሳይንስና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ 13. አቶ አስር ኢብራሂም - የክልሉ ማዕድን ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ 14. አወቀ አይሸሽም - የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ 15. አቶ አብዱሰላም ሸንገል - የሥራ እና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ 16. አቶ ተፈሪ አበበ - የገቢዎች ባለስልጣን ኃላፊ 17. አቶከማል ሀሰን - የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ 18. አቶ ሙክታር አብዱላሂ - የፍትህ ቢሮ ኃላፊ 19. አቶ ዑስማን አህመድ - ቢሮ ኃላፊ የክልሉ መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ 20. አቶ ቱጃኒ አደም - የክልሉ መሬትና ኅብረት ሥራ ማኅበራት ቢሮ ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል። የክልሉ የአስፈጻሚ አካላት ሆነው የተሾሙት በምክር ቤቱ ፊት ቃለ -መሐላ ፈጽመዋል።

📢 ማስታወቂያ በፌዴራል ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች ተወዳድራችሁ ተጠባባቂ ለሆናችሁ ተማሪዎች በሙሉ ትምህርት ሚኒስቴር ለፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የ9ኛ እና 10ኛ ክፍል ተማሪ
📢 ማስታወቂያ በፌዴራል ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች ተወዳድራችሁ ተጠባባቂ ለሆናችሁ ተማሪዎች በሙሉ ትምህርት ሚኒስቴር ለፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የ9ኛ እና 10ኛ ክፍል ተማሪዎችን ለመቀበል ባወጣው ማስታወቂያ መሠረት ፈተና ወስዳችሁ ተጠባባቂ የሆናችሁ ተማሪዎች ከዛሬ ጀምሮ ባሉት ሦስት ተከታታይ ቀናት በተመዘገባችሁበት የምዝገባ ሊንክ በመግባት፣ ስማችሁን እና መለያ ቁጥራችሁን በማስገባት እንድትመዘገቡ ጥሪ እናቀርባለን። 📌የምዝገባ ጊዜ፦ ከዛሬ ጀምሮ ለ3 ተከታታይ ቀናት 🔗 የምዝገባ ሊንክ፦ https://sbs.moe.gov.et/apply ትምህርት ሚኒስቴር

Geneva Global Ethiopian በመተከል ዞን የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ጥራትን ለማሻሻል የሚያስችል የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት ጀመረ ** ​(ግልገል በለስ፡- መስከረም 20 ቀን 2019 ዓ.ም) በመተከል ዞን የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ጥራትን ለማሻሻል እና ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ ተማሪዎችን ቁጥር ከፍ ለማድረግ “Geneva Global Ethiopian” የተባለው ግብረ ሰናይ ድርጅት በትኩረት እየሰራ መሆኑ ገለፀ። ​ድርጅቱ በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታትና የመማር ማስተማር ስርዓቱን ለማጠናከር ያለመ የስራ ላይ የአቅም ግንባታ ስልጠና በግልገል በለስ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ መስጠት ጀምሯል። ስልጠናው በዞኑ ሶስት ወረዳዎች በሚገኙ ተመረጡ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለተወጣጡ መምህራን የተዘጋጀ ነው። ​የስልጠና መርሃ ግብሩን በይፋ ያስጀመሩት የመተከል ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ፍቃዱ ደበሎ እንዳገለጹት፤ ድርጅቱ የመማር ማስተማር ሂደቱን በመደገፍ የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል እያደረገ ያለው እገዛ አበረታች መሆኑን ገልጸው፣ ስራው ተጠናክሮ መቀጠል እንዳበት አሳስበዋል። እንደ ሀገር የተጀመሩ የትምህርት ጥራት የማረጋገጥ ግቦችን ለማሳካት ትምህርት ቤቶችን በቁሳቁስ መደገፍ እና የመምህራንን አቅም ማሳደግ ወሳኝ መሆኑን አቶ ፍቃዱ አመላክተዋል። ​በክልሉ የ“Geneva Global Ethiopian” የክትትልና ድጋፍ ባለሙያ አቶ ዳምጤ ኢተፋ በበኩላቸው፤ ድርጅቱ ባለፉት ሁለት ዓመታት ዝቅተኛ ውጤት የተመዘገበባቸውን 21 ትምህርት ቤቶች በመለየትና በማብቃት ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ ተማሪዎችን ቁጥር ማሳደግ ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል። ​የፕሮግራሙ ዋና ዓላማ የመምህራንን አቅም ማሳደግ፣ የትምህርት ቤት አመራሮችን የመማር ማስተማር ክህሎት ማሻሻል፣ የትምህርት ግብዓቶችን ማሟላት እንዲሁም ወደ ዩኒቨርሲቲ እና ቴክኒክና ሙያ የሚገቡ ወጣት ተማሪዎችን ቁጥርና ውጤት ማሻሻል እንደሆነ አቶ ዳምጤ አክለው ገልጸዋል። ከክልሉ ትምህርት ቢሮ ጋር በመተባበር እየተሰራ ባለው በዚህ ፕሮግራም ላይ ለሴት ተማሪዎች ጭምር ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራ ተመላክቷል። ​ይህ የስልጠና መርሃ ግብር በመተከል ዞን በማንድራ፣ ድባጢ እና ወምበራ ወረዳዎች በሚገኙ ማንዱራ፣ ጋሌሳ፣ በርበር እና ገሰንገሳ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ለሚገኙ መምህራን እየተሰጠ የሚገኝ ሲሆን፤ ስልጠናውም በግልገል በለስ መምህራን ኮሌጅ መምህራን አማካኝነት በመሰጠት ላይ ይገኛል።

Benishangul Gumuz Education Bureau - Telegram kanali @bgeducation statistikasi va tahlili