uz
Feedback

Firibgarlarga uchmang! Telemetrio bunday kanallarni topadi va belgilaydi 👉 Belgini ko‘rmoqchi bo‘lsangiz, obuna bo‘ling

Addis Admass

Addis Admass

Kanalga Telegram’da o‘tish

የአዲስ አድማስ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ ===== አዲስ አድማስ https://bit.ly/2V1zyZQ ፌስቡክ↠ https://bit.ly/2V0I6jx ትዊተር↠ https://bit.ly/33fDhaP ቴሌግራም↠ https://bit.ly/2JgeCvG ዩቲዩብ ↠ https://bit.ly/3q2hXiv የእርስዎና የቤተሰብዎ

Ko'proq ko'rsatish

📈 Telegram kanali Addis Admass analitikasi

Addis Admass (@adissadmas) Amxar til segmentidagi kanali faol ishtirokchi. Hozirda hamjamiyat 19 635 obunachidan iborat bo'lib, Yangiliklar & Media toifasida 11 720-o'rinni va Efiopiya mintaqasida 1 827-o'rinni egallagan.

📊 Auditoriya ko‘rsatkichlari va dinamika

невідомо sanasidan buyon loyiha tez o‘sib, 19 635 obunachiga ega bo‘ldi.

24 Oktabr, 2026 dagi oxirgi ma’lumotlarga ko‘ra kanal barqaror faollikka ega. Oxirgi 30 kunda obunachilar soni 623 ga, so‘nggi 24 soatda esa 21 ga o‘zgardi va umumiy qamrov yuqori darajada qolmoqda.

  • Tasdiqlash holati: Tasdiqlanmagan
  • Jalb etish (ER): Auditoriya o‘rtacha 11.48% darajada jalb etiladi. Nashrdan keyingi dastlabki 24 soatda kontent odatda umumiy obunachilar sonining 9.09% ini tashkil etuvchi reaksiyalarni to‘playdi.
  • Post qamrovi: Har bir post o‘rtacha 2 253 marta ko‘riladi; birinchi sutkada odatda 1 785 ta ko‘rish yig‘iladi.
  • Reaksiyalar va o‘zaro ta’sir: Auditoriya faol: har bir postga o‘rtacha 10 ta reaksiya keladi.

📝 Tavsif va kontent siyosati

Muallif resursni shaxsiy fikrni ifoda etish maydoni sifatida ta’riflaydi:
“የአዲስ አድማስ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ ===== አዲስ አድማስ https://bit.ly/2V1zyZQ ፌስቡክ↠ https://bit.ly/2V0I6jx ትዊተር↠ https://bit.ly/33fDhaP ቴሌግራም↠ https://bit.ly/2JgeCvG ዩቲዩብ ↠ https://bit.ly/3q2hXiv የእርስዎና የቤተሰብዎ”

Yuqori yangilanish chastotasi (oxirgi ma’lumot 25 Oktabr, 2026 da olingan) sababli kanal doimo dolzarb va katta qamrovli bo‘lib qoladi. Analitika auditoriya kontent bilan faol hamkorlik qilishini, uni Yangiliklar & Media toifasidagi muhim ta’sir nuqtasiga aylantirishini ko‘rsatadi.

19 635
Obunachilar
+2124 soatlar
+747 kun
+62330 kun
Postlar arxiv
ሜላኒያ ትራምፕ በዩክሬን የጦርነት ቀጠና የተኩስ አቁም አሸማገሉ በሩሲያ እና ዩክሬን መካከል በተካሄደው ከባድ ጦርነት በግንባር ቀደምትነት የምትገኘውና በሩሲያ ቁጥጥር ስር የምትገኘው ኦልሽኪ ከተማ
ሜላኒያ ትራምፕ በዩክሬን የጦርነት ቀጠና የተኩስ አቁም አሸማገሉ በሩሲያ እና ዩክሬን መካከል በተካሄደው ከባድ ጦርነት በግንባር ቀደምትነት የምትገኘውና በሩሲያ ቁጥጥር ስር የምትገኘው ኦልሽኪ ከተማ ለከፍተኛ ሰብዓዊ ውድቀት ተዳርጋ ነበር። ያለ ምግብ፣ መድኃኒት እና ንጹህ ውሃ በከፍተኛ አደጋ ውስጥ የነበሩት ነዋሪዎች በሕይወት ለመቆየት አረም እስከመመገብ ደርሰው እንደነበር ተገልጻል። በዚህ አስቸጋሪ ወቅት የአሜሪካዋ ቀዳማዊት እመቤት ሜላኒያ ትራምፕ እና ወኪላቸው ከሁለቱ አገራት መሪዎች ጋር በቀጥታ በመምከር ከአምስት ቀናት በኋላ የሚጀምር የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረስ ማድረጋቸውን ዋይት ሐውስ አስታውቋል። በዚህ ስምምነት መሠረት የሁለቱም አገራት ጦር እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከጥቅምት 27 ጀምሮ ተኩስ የሚያቆሙ ሲሆን፣ የሲቪል መሪዎች በጋራ በመሆን ለነዋሪዎች አስፈላጊውን ሰብዓዊ እርዳታ ለማቅረብ ይሰራሉ። ሜላኒያ ትራምፕ እንደተናገሩት "ያለ እኔ ጣልቃ ገብነት በከተማዋ ሰብዓዊ እርዳታ የማስገባት እድል እና አረጋዊያንን ማስወጣት የማይቻል ነበር" ያሉ ሲሆን፣ ለቅቀው መውጣት ለሚፈልጉ ነዋሪዎችም ወደ ሩሲያ ወይም ዩክሬን የሚያደርጉትን ጉዞ ለመደገፍ ትራንስፖርት እንደሚመቻችላቸው ገልጸዋል። የሩሲያ እና የዩክሬን ባለስልጣናት ስምምነቱን ያረጋገጡ ሲሆን፣ የፕሬዝዳንት ፑቲን ቃል አቀባይ መውጣት የሚፈልጉ ነዋሪዎች መውጣት እንደሚችሉ ተናግረዋል። ከጦርነቱ በፊት 24 ሺህ ነዋሪዎች የነበሯት ይህች ከተማ በአሁኑ ወቅት 200 ሕፃናትን ጨምሮ ስድስት ሺህ ያህል ህዝብ ብቻ እንደሚገኝባት ተገልጿል። የተኩስ አቁሙ ለምን ያህል ጊዜ እንደሚቆይ በዋይት ሐውስ መግለጫ ላይ ባይጠቀስም፣ የታገዱ የሰፈራ እና የሰብዓዊ እርዳታ ስራዎችን እንደገና ለማስጀመር ትልቅ ዕድል ይፈጥራል ተብሏል። bbc- የቴሌግ

"የሰማዕታት ሐውልት የትግራይ ሕዝብ ንብረት ነው" (ነጻ አስተያየት) ለበርካታ ዓመታት የትግራይ የሰማዕታት ሐውልት በሕወሐት እንደ ግል ንብረት ተይዞ እንደ ዋና መሥሪያ ቤት ሲያገለግል ቆይቷል። እን
+2
"የሰማዕታት ሐውልት የትግራይ ሕዝብ ንብረት ነው" (ነጻ አስተያየት) ለበርካታ ዓመታት የትግራይ የሰማዕታት ሐውልት በሕወሐት እንደ ግል ንብረት ተይዞ እንደ ዋና መሥሪያ ቤት ሲያገለግል ቆይቷል። እንደ ብርሃነ ንጉሤ ያሉ የፊልም አዘጋጆች እንኳ ስለ ሰማዕታት የተሠራን ፊልም በቦታው ለማሳየት ተቸግረው ነበር። አሁን ደግሞ ሐውልቱን ለአዲሱ ጊዜያዊ አስተዳደር የሰላምና ጸጥታ ቢሮ መሰጠቱን እየሰማን ነው። ነገር ግን የሰማዕታት ሐውልት የትግራይ ሕዝብ እንጂ የየትኛውም የፖለቲካ ፓርቲ ወይም የከተማ አስተዳደር ንብረት አይደለም። ከፖለቲካና ከአስተዳደር ቁጥጥር ነፃ መሆን አለበት። የሕዝቡን መስዋዕትነትና ታሪክ የሚዘክሩ ቅርሶችን፣ ሰነዶችንና የኪነ-ጥበብ ሥራዎችን የያዘ ሕዝባዊ መታሰቢያና ሙዚየም ሊሆን ይገባል። አንዱን የፖለቲካ አካል በሌላ መተካት ሐውልቱን ለትክክለኛ ባለቤቱ ማለትም ለሕዝቡ አያስረክብም። Getachew Assefaumd- የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ… https://t.me/AdissAdmas

ቱርክ በ5 ዓመት ውስጥ 5 ሚሊዮን ድሮኖችን ለማምረት አቅዳለች ቱርክ በሚቀጥሉት 5 ዓመታት ውስጥ 5 ሚሊዮን፣ በ10 ዓመታት ውስጥ ደግሞ እስከ 10 ሚሊዮን የሚደርሱ ድሮኖችን ለማምረት ማቀዷን የሀገ
ቱርክ በ5 ዓመት ውስጥ 5 ሚሊዮን ድሮኖችን ለማምረት አቅዳለች ቱርክ በሚቀጥሉት 5 ዓመታት ውስጥ 5 ሚሊዮን፣ በ10 ዓመታት ውስጥ ደግሞ እስከ 10 ሚሊዮን የሚደርሱ ድሮኖችን ለማምረት ማቀዷን የሀገሪቱ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ሴልቹክ ባይራክታሮግሉ ገለጹ። ይህ ዕቅድ ቱርክ የወታደራዊ ድሮን ምርቷንና የቴክኖሎጂ አቅሟን በከፍተኛ ደረጃ ለማሳደግ እያደረገች ያለውን ትልቅ እንቅስቃሴ ያሳያል። በቅርቡ በተደረገ የባህር ኃይል ልምምድ ላይ ቱርክ ሰው ያላቸውንና ሰው አልባ የጦር መሣሪያዎችን አጣጥማ የመጠቀም አቅሟን አሳይታለች። በዚህ የቀጥታ ተኩስ ልምምድ ላይ ካልካን የተባሉ ድሮኖች፣ ኤፍፒቪ ድሮኖች እና ፒራና የተባሉ ሰው አልባ የባህር ላይ ተኳሽ ጀልባዎች ሥራ ላይ ውለዋል። እንደ ኤታማዦር ሹሙ ማብራሪያ፣ በቀጥታ ወደ ላይ መነሳትና ወደ ታች ማረፍ የሚችሉ ሰው አልባ ድሮኖች እና ሰው አልባ የውሃ ውስጥ መሣሪያዎች ለቱርክ የባህር ኃይል የወደፊት አቅም በጣም አስፈላጊ ናቸው። በተጨማሪም ሀገሪቱ የጦር መርከቦችን በሀገር ውስጥ የማምረትና የማደስ ሙሉ አቅም እንዳላት ገልጸዋል። የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ… https://t.me/AdissAdmas

የአርሲ ሀገረ ስብከት አጣዳፊ መፍትሔ ጠየቀ በአርሲ ሀገረ ስብከት ሺርካ ወረዳና በአካባቢው በታጠቁ ኃይሎች የሚፈጸመው የክርስቲያኖች ግድያ፣ መፈናቀልና የንብረት ውድመት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየባሰ መምጣ
የአርሲ ሀገረ ስብከት አጣዳፊ መፍትሔ ጠየቀ በአርሲ ሀገረ ስብከት ሺርካ ወረዳና በአካባቢው በታጠቁ ኃይሎች የሚፈጸመው የክርስቲያኖች ግድያ፣ መፈናቀልና የንብረት ውድመት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየባሰ መምጣቱን ሀገረ ስብከቱ ገለጸ። ድርጊቱ ትልቅ ሐዘን እንደፈጠረበት የገለጸው ሀገረ ስብከቱ፣ ችግሩን ለመፍታት ብዙ ጥረቶች ቢደረጉም ዛሬም ድረስ ዘላቂ መፍትሔ ማግኘት አልተቻለም ብሏል። የአርሲ እና የሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ እና የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ ከታች ካሉ የመንግሥት አካላት ጀምሮ እስከ ሰላም ሚኒስቴር ድረስ በተደጋጋሚ በማሳወቅና በመወያየት ትልቅ ጥረት ማድረጋቸው ተጠቁሟል፡፡ ሆኖም እስካሁን ድረስ ምንም ዓይነት መፍትሔ እንዳልተሰጠና ችግሩ እየባሰ መቀጠሉን ሀገረ ስብከቱ አስታውቋል። በአሁኑ ወቅትም በርካታ ክርስቲያኖች እየተገደሉና ከቀዬአቸው እየተፈናቀሉ ይገኛሉ ያለው ሃገረ ስብከቱ፤ ቅዱስ ሲኖዶስ ለጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጥ እንዲሁም የመንግሥት አካላት ለችግሩ እልባት እንዲሰጡ ጥሪ አቅርቧል። Tikvah Ethiopia- የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ… https://t.me/AdissAdmas

ከናይሮቢ የሕንፃ ፍርስራሽ ውስጥ አንድ ሰው በሕይወት ተረፈ *የ31 ሰዎች ደብዛ አሁንም አልተገኘም በኬንያ ናይሮቢ ኢስትሊ (Eastleigh) በተባለ አካባቢ በተደረመሰው ባለ 18 ፎቅ ሕንፃ ፍርስራ
ከናይሮቢ የሕንፃ ፍርስራሽ ውስጥ አንድ ሰው በሕይወት ተረፈ *የ31 ሰዎች ደብዛ አሁንም አልተገኘም በኬንያ ናይሮቢ ኢስትሊ (Eastleigh) በተባለ አካባቢ በተደረመሰው ባለ 18 ፎቅ ሕንፃ ፍርስራሽ ውስጥ ተቀብሮ የነበረ አንድ ሰው በነፍስ አድን ሠራተኞች አማካኝነት በሕይወት መውጣቱን የስፑትኒክ ዘገባ ያመለክታል። በነፍስ አድን ቡድኑ ከፍርስራሹ የወጣው ይህ ግለሰብ በአሁኑ ወቅት በኬንያ ብሔራዊ ሆስፒታል ገብቶ አስፈላጊው የሕክምና ክትትል እየተደረገለት ይገኛል። እንደ ስፑትኒክ ዘገባ ከሆነ፣ በአደጋው ወቅት የጠፉ ሰዎችን የመፈለግ ሥራ ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን፣ እስካሁን የ31 ሰዎች ደብዛ አልተገኘም። ሆኖም ከዚህ ቀደም የጠፉ ተብለው ከተመዘገቡት መካከል ሁለቱ ሰዎች በሰላም ከቤተሰቦቻቸው ጋር መገናኘታቸው ተረጋግጧል። የአደጋ ጊዜ ባለሥልጣናት እንደገለጹት፣ አንዳንድ ሠራተኞች ሕንፃው ከመደርመሱ በፊት ከሥፍራው ወጥተው ሊሆን ስለሚችል የጠፉ ሰዎችን ትክክለኛ ቁጥር ለማረጋገጥ የማጣራት ሥራው ቀጥሏል። የኬንያ ቀይ መስቀል ማኅበር በአደጋው ለተጎዱና ለተጨነቁ ቤተሰቦች የሥነ-ልቦና ድጋፍና የምክር አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል የአደጋ ጊዜ ኦፕሬሽን ማዕከል አቋቁሞ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል። የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ… https://t.me/AdissAdmas

የሆነ ሆኖ ወንዶች ጋር የሚያድጉ የሚበዙት የአገራችን ሴቶች የተሳሳተውን ወንዳወንድነት የሚወርሱበት ጊዜ ብዙ ነው። የወንድና ሴት ድንበሩ የተፋለሰባቸው፣ አጉል ጀግና ጀግና የሚጫወቱ፣ የተጋነነ ኮንፊዲየንስ የሚያሰቃያቸው ወይም የተጋነነ ፍርሃት ውስጥ የሚኖሩ፣ ዝም ብለው ባህሉም ወጉም ማህበረሰቡም ጋር የሚጋጩ፣ የነፃነት ታጋይ፣ ፆታዊ ጉዳይ የተምታታባቸው፣ አባታቸው ጀግና ሌላው ወንድ ደፋሪ ባለጌ ምናምን ሆኖ የሚታያቸው ሆነው ታገኛቸዋላችሁ። (ወንዶች ነፍሳቸው ለጦር የሚፈላለግ ስለሆነ ሰላም ቢመስሉም ውስጣቸው ዝቅ የማለት ተፈጥሮ የለውም፣ ሌላውን የማናናቅ ተፈጥሮ ውስጣቸው አለ አቅም ሲያንሳቸው ራሳቸውን የሚያሳምኑበት መንገድ ነው) ለሴት ለልጆቻቸውም የሚያወርሷቸው በጣም ድብቅ ባህሪ ይህ ነው። ስለዚህ ብዙ አይወራም። ማንም ወዶ በነጠላ ወላጅ አያድግም፤ ግን አጋጥሞ ይነጻጸር ከተባለ፣ እናታቸው ጋር ያደጉ ሴቶች አባታቸው ጋር ካደጉት ሴቶች የተሻለ በሳልና ትክክለኛውን የህይወት ገጽታ መረዳት የሚችሉ፣ ከአጉል ጀብደኝነት የራቁ፣ ሚዛናዊ አስተሳሰብ ያላቸው ናቸው። የእናንተስ ሃሳብ ምንድነው? Alex Abrham- የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ… https://t.me/AdissAdmas

የሴት ልጅ! ከአባቶች ጋር ብቻ ያደጉ ሴቶች --- (የግል ምልከታ እንደወረደ) ​ልጆች ከእናት ጋር ብቻ ማደጋቸው እንደ ስድብ የሚቆጠርበት ጊዜ ነበር። "ነበር" አልኩ እንጂ ከድሮው ቢሻልም አሁንም
የሴት ልጅ! ከአባቶች ጋር ብቻ ያደጉ ሴቶች --- (የግል ምልከታ እንደወረደ) ​ልጆች ከእናት ጋር ብቻ ማደጋቸው እንደ ስድብ የሚቆጠርበት ጊዜ ነበር። "ነበር" አልኩ እንጂ ከድሮው ቢሻልም አሁንም "የሴት ልጅ" የሚለውን አገላለጽ እንደ ስድብ የሚቆጠረው ብዙ ነው። ​የልጅ አስተዳደግ ስኬት ወይም ውድቀት የሚወሰነው በአባቱ ወይም በእናቱ ብቻ ማደግ ላይ ሳይሆን፣ የወላጆች አቅም፣ የፍቅር ስሜት፣ የሞራል እሴቶች እና የሚሰጡት ተገቢ ክትትል ላይ ነው። ​አባቶች ጋር ያደጉ ሴቶች ጠንካራ፣ ራሳቸውን የቻሉ እና በራስ መተማመናቸው የጎላ እንዲሆኑ ይረዳቸዋል፤ በእናቶች ደግሞ ስሜታዊ ጥንካሬን፣ ማህበራዊ ግንኙነትን እና የህይወት መሰረታዊ እሴቶችን በማስተማር ረገድ ትልቅ አስተዋጽኦ አላቸው የሚል "አጠቃላይ" እይታ አለ። ​በአገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ግን "ሁሉም" ከሚል በደፈናው ውጡና ብዙ አባታቸው ጋር ያደጉ ሴቶች ልጆችን ታዘቡ፤ ሲጀመር የልጅ አስተዳደግ ለሴቶች በተተወበት አገር ወንዶች ዱብእዳ ካልሆነባቸው በስተቀር በብቸኝነት ልጅ አያሳድጉም። ሲያሳድጉ እንደሆነ ተዓምር ጀግንነት ነው የሚታየው። ⬇️⬇️

በኬንያ ሁለተኛው የኢቦላ ሞት ተመዘገበ፤ ኢትዮጵያም የወረርሽኙን ስርጭት ለመግታት ጥንቃቄዋን አጠናክራለች በኬንያ ቫይረሱን ወደ ሀገሪቱ ካስገባው የመጀመሪያው ሰለባ ጋር የቅርብ ዘመድና ቀጥተኛ ንክኪ
በኬንያ ሁለተኛው የኢቦላ ሞት ተመዘገበ፤ ኢትዮጵያም የወረርሽኙን ስርጭት ለመግታት ጥንቃቄዋን አጠናክራለች በኬንያ ቫይረሱን ወደ ሀገሪቱ ካስገባው የመጀመሪያው ሰለባ ጋር የቅርብ ዘመድና ቀጥተኛ ንክኪ የነበራት የ65 ዓመት ሴት ህይወቷ ማለፉ ተረጋግጧል። የመጀመሪያው ታማሚ ከኮንጎ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ወደ ኬንያ ከተመለሰ በኋላ በዚህ ወር መጀመሪያ ሕይወቱ ማለፉ ይታወሳል። እስካሁን በሀገሪቱ ከተመዘገቡት 9 የተረጋገጡ የኢቦላ ታማሚዎች መካከል የሁለቱ ህይወት ሲያልፍ፣ ቀሪዎቹ 7 ታማሚዎች በለይቶ ማቆያ ማዕከላት ልዩ ሕክምና እየተደረገላቸው ይገኛል። የኬንያ ባለሥልጣናት ከታማሚዎቹ ጋር ንክኪ የነበራቸውን 135 ሰዎች ለይተው ተገልለው እንዲቆዩ ያደረጉ ሲሆን፣ የሀገሪቱ ጤና ሚኒስቴር በማኅበረሰብ ደረጃ የጎላ የበሽታው ስርጭት ስለመኖሩ እስካሁን ምንም ዓይነት ማስረጃ እንደሌለ አስታውቋል። ይህንን ጎረቤት ሀገር ኬንያ ላይ ያጋጠመውን የኢቦላ ስጋት ተከተሎ፣ ኢትዮጵያ ወረርሽኙ ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገባና የኅብረተሰብ ጤና አደጋ እንዳያስከትል ቀድሞ የመከላከልና የቅድመ-ማስጠንቀቂያ እርምጃዎችን በከፍተኛ ደረጃ አጠናክራለች። የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እና የጤና ሚኒስቴር በድንበር በሮች፣ በኬንያ ወሰን አወሳሰን አካባቢዎች እንዲሁም በቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ጥብቅ የጤና ፍተሻ እና የበሽታ ቅኝት (screening & surveillance) በማካሄድ ላይ ይገኛሉ።

ፕሮፌሰር ሰለሞን ተፈራ ከልብ እናመሰግናለን!!! በኢትዮጵያ የመጀመሪያው በሆነውና በ24 የአእምሮና የስነ ልቦና ሐኪሞች በጋራ በተዘጋጀው "የአእምሮ ጤና መዛባቶች" መፅሐፍ ዙሪያ ዛሬ በዋሊያ መፅሐፍ
+1
ፕሮፌሰር ሰለሞን ተፈራ ከልብ እናመሰግናለን!!! በኢትዮጵያ የመጀመሪያው በሆነውና በ24 የአእምሮና የስነ ልቦና ሐኪሞች በጋራ በተዘጋጀው "የአእምሮ ጤና መዛባቶች" መፅሐፍ ዙሪያ ዛሬ በዋሊያ መፅሐፍት የውይይት ፕሮግራም ተካሄደ:: መጽሐፉ ከስብእና መዛባቶች እስከ ሱስ ሕክምና ድረስ ያሉ ወሳኝ ጉዳዮችን ዳስሷል። በዕለቱ “የአእምሮ ጤና እና የዕለት ተዕለት ሕይወታችን” በሚል ርዕስ ውይይት የመሩት የመጽሐፉ አርታኢና በርካታ ጽሑፎችን ያበረከቱት ፕሮፌሰር ሰለሞን ተፈራ ናቸው። ፕሮፌሰሩ የስብእና መዛባቶች፣ የአንጎል መታወክ፣ የሥርዓተ ጾታ ግንኙነት ችግሮች፣ የስሜት መዛባቶች፣ በልጆችና ወጣቶች ላይ የሚታዩ ችግሮች እንዲሁም ከሱስ ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን በዝርዝር በማቅረብ የኅብረተሰቡን ግንዛቤ የሚያሳድጉ ጠቃሚ ተሞክሮዎችን አጋርተዋል። በመርሐ ግብሩ ማጠናቀቂያ ላይ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የአእምሮ ሕክምና ትምህርት ክፍል ጋር በመተባበር፣ መጽሐፉ ለኪነ ጥበብ ባለሙያዎች፣ ለደራሲያን፣ ለፊልም እና ቲያትር ፀሐፊዎች፣ ለጋዜጠኞች እንዲሁም ለአንባቢያን በስጦታ ተበርክቷል። ለዚህ ስኬት አስተዋጽኦ ያበረከቱት ዶ/ር ሰላም፣ የአርታኢዎች ቦርድ አባላት እና የዲፓርትመንቱ ሠራተኞች ከልብ ተመስግነዋል። ፕሮፌሰር ሰለሞን ተፈራ በሳይካትሪ ሙያቸው ለአገራቸው ከፍተኛ አገልግሎት እያበረከቱ የሚገኙ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ የመጀመሪያው የሱስ እና ተዛማጅ ችግሮች ስፔሻሊስትና ተመራማሪ በመሆን ይታወቃሉ። የ“ሬናሰንት የአዕምሮ ህክምናና ተሃድሶ ማዕከል” መስራችና ዳይሬክተር በመሆንም ኅብረተሰቡን በማገል ላይ ይገኛሉ። Yetebarek Walelegen (መጠነኛ አርትኢት ተድርጎበት የቀረበÿ የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ… https://t.me/AdissAdmas

«ከ3 ቢ. ብር በላይ የተከማቸበት መጋዘን በአድዋ ተገኘ» በትግራይ ክልል አድዋ ከተማ ተደረገ በተባለ አሰሳ፣ ግምታዊ ዋጋው ከ3 ቢሊዮን ብር በላይ የሚሆን የብር ኖት የተከማቸበት መጋዘን መገኘቱን
«ከ3 ቢ. ብር በላይ የተከማቸበት መጋዘን በአድዋ ተገኘ» በትግራይ ክልል አድዋ ከተማ ተደረገ በተባለ አሰሳ፣ ግምታዊ ዋጋው ከ3 ቢሊዮን ብር በላይ የሚሆን የብር ኖት የተከማቸበት መጋዘን መገኘቱን ብዙዎችን አስደንግጧል። ** ምን ማስደንገጥ ብቻ ያሳዝናልም እንጂ፡፡ መረጃው በማህበራዊ ሚዲያ ሲሰራጭ የተገኘ ነው፡፡ የመንግሥት ሰራተኞች ደሞዝ አልተከፈለንም እያሉ በነበረበት ወቅት ህወሃት ግን ይሄን ሁሉ ገንዘብ ደብቆ ማስቀመጡ አጃኢብ ነው፡፡ ባጀት እያለ ሲያላዝንም ነበር፡፡ በጦር መሳሪያው ክምችት ተገርመን ሳናበቃ የገንዘብ ክምችት--ገና ሌላም ማየታችን አይቀርም፡፡ የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ… https://t.me/AdissAdmas

የህወሓት ካድሬዎች በፖሊስ ጣቢያ እንዲመዘገቡ ተጠየቁ የትግራይ የሰላም ኃይል ቃል አቀባይ ኮሎኔል ሰሎሞን ሃይለማሪያም፤ የቀድሞ የህወሓት ካድሬዎች በሙሉ በአካባቢያቸው ወደሚገኙ ፖሊስ ጣቢያዎች ቀርበ
የህወሓት ካድሬዎች በፖሊስ ጣቢያ እንዲመዘገቡ ተጠየቁ የትግራይ የሰላም ኃይል ቃል አቀባይ ኮሎኔል ሰሎሞን ሃይለማሪያም፤ የቀድሞ የህወሓት ካድሬዎች በሙሉ በአካባቢያቸው ወደሚገኙ ፖሊስ ጣቢያዎች ቀርበው እንዲመዘገቡ ጥሪ አቀረቡ። የቀን ገደብ: ከነገ ጥቅምት 15 እስከ ጥቅምት 19 ቀን 2019 ዓ.ም ባሉት ቀናት ውስጥ ሪፖርት ማድረግ ይኖርባቸዋል። ምክንያቱ: ወቅታዊ ሁኔታዎችን እና የትግራይን መጪ ዕጣ ፈንታ ለመነጋገር ታቅዷል። ጥብቅ ማሳሰቢያ: ትዕዛዙን አክብሮ ሪፖርት የማያደርግ አካል ካለ፤ የህወሓት ቡድን ሆኖ የህዝብን ሰላም ለማደፍረስ እንዳቀደ ተቆጥሮ በሌላ መንገድ እንደሚወሰድበት ተነግሯል። የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ… https://t.me/AdissAdmas

የኑሮ ውድነት የቀሰቀሰው ሁከት፡ ፈረንሳይ 70ሺ ፖሊሶችን ልታሰማራ ነው ቢቢሲ እንደዘገበው፤ ፈረንሳይ በመላ አገሪቱ ቅዳሜ ዕለት ሊካሄድ በታቀደው የተቃውሞ ሠልፍ ሁከት እንዳይፈጠር ለመከላከል 70,
የኑሮ ውድነት የቀሰቀሰው ሁከት፡ ፈረንሳይ 70ሺ ፖሊሶችን ልታሰማራ ነው ቢቢሲ እንደዘገበው፤ ፈረንሳይ በመላ አገሪቱ ቅዳሜ ዕለት ሊካሄድ በታቀደው የተቃውሞ ሠልፍ ሁከት እንዳይፈጠር ለመከላከል 70,000 ያህል ፖሊሶችን ልታሰማራ መሆኑን አስታውቃለች። ይህ ጥብቅ ውሳኔ የተላለፈው፣ ባለፈው ሳምንት የኑሮ ውድነትን በመቃወም በተደረጉ ሠልፎች ላይ ከፍተኛ የሆነ የጎዳና ላይ ሁከትና ውድመት ከተከሰተ በኋላ ነው። የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ላውረንት ኑኔዝ አርብ ዕለት እንደተናገሩት፣ ሁከቱን ለመከላከል ከመደበኛ ፖሊሶች በተጨማሪ ልዩ ኮማንዶዎች ይሰማራሉ። የተወሰኑ ቡድኖች በማኅበራዊ ሚዲያ አማካኝነት ለጥቃት ጥሪ ማቅረባቸውን የገለጹት ሚኒስትሩ፤ ማንኛውንም ዓይነት ጥቃት ፈጽሞ እንደማይታገሱ አፅንኦት ሰጥተዋል። ባለፈው ሳምንት በነበረው ሰልፍ ወቅት ፊታቸውን በጭምብል የሸፈኑ የተወሰኑ ግለሰቦች በፓሪስና በሌሎች ከተሞች መኪኖችንና ሕንፃዎችን ሲያቃጥሉ እንዲሁም ሱቆችን ሲዘርፉ መታየታቸው ይታወሳል። ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ባደረጉት አስቸኳይ ስብሰባ ማብቂያ ላይ መንግሥት እጅግ ጥብቅ የጸጥታ እርምጃ ለመውሰድ ዝግጁ መሆኑን መናገራቸው ተዘግቧል። የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ… https://t.me/AdissAdmas

በ81 የሰንበት ገበያ ቸርቻሪ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ ተወሰደ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ቁጥጥር ሃላፊዎች በቅዳሜና እሁድ የሰንበት ገበያዎች ላይ በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ፣ ከተለጠፈው
+1
በ81 የሰንበት ገበያ ቸርቻሪ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ ተወሰደ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ቁጥጥር ሃላፊዎች በቅዳሜና እሁድ የሰንበት ገበያዎች ላይ በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ፣ ከተለጠፈው ዋጋ በላይ ሲሸጡ የነበሩ 81 የሽንኩርትና የቲማቲም ቸርቻሪ ነጋዴዎች ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ ተወስዷል። የቢሮው ኃላፊ ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ፣ ህገ-ወጥ የዋጋ ጭማሪን ለመከላከል የተጀመረው ርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አፅንኦት ሰጥተዋል። በነጋዴዎቹ ላይ የተወሰደው እርምጃ ምን እንደሆነ ግን አልተገለጸም፡፡ የግብይት ስርዓቱን ፍትሃዊነት ከማረጋገጥ አንፃር ሸማቹ ማህበረሰብ የራሱን መብት ማስጠበቅ እንዳለበት የጠቆሙት ኃላፊዋ፤ ህገ-ወጥ አሰራሮችን ሲያጋጥሙ በነፃው ስልክ መስመር 85 88 በመደወል ጥቆማ መስጠት እንደሚገባ አሳስበዋል። አመራሮችና የቁጥጥር ባለሙያዎችም ስራቸውን በጥብቅ ዲሲፕሊን እንዲፈጽሙ ጥሪ ቀርቧል። የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ… https://t.me/AdissAdmas

እነሱ "ከችግሬ አይበልጥም" ብለው ከስብዕና በታች ወርደው የሰበሰቡትን ፎሎወር "ኮላተራል አስይዘው" ቢዝነስ በሰሩ የአንዳንድ ድርጅቶችና ግለሰቦች እነሱን ተፅዕኖ ፈጣሪ ብሎ ለማሞካሸት እና ለመሸለም መራኮት ነው እኔን የሚደንቀኝ። በዚህም በዚያም ብለው ችግርን ያመለጡበትን መንገድ ባደንቅም እነሱስ ቢሆኑ ይህን ያህል "ተፅዕኖ ፈጣሪ" የሚል ስምና ማዕረግ ትከሻቸው እንዴት ችሎ እንደተሸከመው ሳሰበው ይገርመኛል። ዝናና ክብር ማን ይጠላል ለነገሩ ? ደሞ ከሰሞኑ ማን ምን ሠርቶ ተፅዕኖ ፈጣሪ እንደተባለና እንደተሸለመ ሳይ ደግሞ እንደማህበረሰብ ላያችን የሰፈረው የድንቁርና ጥግ እና የገባንበት ዝቅጠት መጠን ነው በጣም ያሳሰበኝ ! አሁን እንደው ማን ይሙት ማህበራዊ ሚዲያ ላይ መኪና፣ ቤት፣ ወርቅ ከሽለማችኋቸው ልጆች የበለጡ ፣ ለህዝብም ለሃገርም በርካታ ቁምነገር የሰሩ ፣ በሙያቸው ተፅዕኖ ፈጥረው አሰተሳሰብ ያስተካከሉ፣ መስመር ያሰመሩ፣ መንገድ የቀየሱ ፣ ህዝብ ለበጎ ነገር ያስተባበሩ፣ በመልካም ሥራ ሀገርን ያስጠሩ፣ ትውልድ የቀረፀ፣ ለማህበራዊ ዕድገትና ለህዝብ መብት የተሟገቱ ሰዎች እዚህ ሃገር ጠፍተው ነው በማርያም ? ወይስ የተፅዕኖ ፈጣሪነት መለኪያዉ የቪው እና የፎሎወር ቊጥር ነዉ? እንደዚያ ከሆነስ "ሶሻል ሚዲያ ላይ ብዙ ተከታይ ማፍራት የቻሉ ብላችሁ በቊጥር ብታወዳድሩ አይሻልም ነበር? መሸለሙን ስፖንሰር እስካገኛችሁና ገንዘብ እስካላችሁ ድረስ ሽልሙ ! ቢዝነስ መስራት መብታችሁ ነው። ግን በኢትዮጰያ ህዝብ ስም እከሌ "በህዝብ ላይ በጐ ተፅዕኖ ፈጥሯል ፣ ህዝብ ጠቅሟል፣ ችግር አቅልሏል ፣ ሃገር አሻግሯል" ምናምን እያላችሁ ባትቀልዱብን ግን ምናለበት ነበር? የነዚህን ልጆች ችግርን የማምለጫ ጥረት እኮ ከልቤ አደንቃለሁ። ትምሮ ሲገግምባቸው ታዲያ ይሙቱ እንዴ? የተዘጋ በር ከማንኳኳት በተገኘው ቴክኖሎጂ በቆረጣ ገብቶ በልቶ ማደር እኮ ፀዴ ነገር ነው። ለኔ ነፈዞቹ ልጆቹ ሳይሆኑ ሸላሚ ነን ብለው ልጆቹ ላይ ከአቅማቸው በላይ ስም የጫኑባቸውና ህዝብ ላይ በህዝብ ስም የሚቆምሩት ድርጅቶች ናቸዉ። ለነገሩ እነሱስ ምን ያድርጉ? . .. መንግስት ራሱ ከነሱ ኋላ ያለውን ሚሊዮናት ግሪሳ ልብ ለመብላት ሲል ልጆቹን ሰብስቦ "የቲክቶክ ተፅዕኖ ፈጣሪ" እያለ በበሸነና ፎግሮ ክልል ለክልል አዙሮ ሃገር ሲያስጐበኛቸው ከረመ አይደል? ኋላ ላይ ግን በነርሱ ኮንቴንት ተፅዕኖ ትውልድ ማህበራዊ ዝቅጠት ሲጀምረዉ ሲያይ ግን "ተወጡት" ብሎ ነው መሰለኝ ላሽ አለ። ድርጅቶቹ ደግሞ ሌጋሲውን ከሱ ተቀበሉና ስፖንሰር እየሰበሰቡ በተፅዕኖ ፈጣሪ ስም እንሸልም ብለው ሽቀላቸውን አጧጧፉ ! የሕዝቡ ንቃተ ህሊና በመሃል ከዳዴ የሚያነሳው አጥቶ እዚያው ይድቆስቆስ ይዟል። ለማንኛውም የዘንድሮ "ተፅዕኖ ፈጣሪዎች" እኛን ደደብ አድርጐ የፈጠረላቸውን ጌታ ያመሰግኑ ! (ይህንንም እንደተለመደው "የምቀኛ ወሬ" ብሎ የሚያለቃቅስ "ጀዝባ" እኮ አይጠፋም 🤔 ባንተ መኖር እነሱ ነገሱ ጀለስ ! ውለታህን ላይቭ ቸክለህ የምታይበት የቲክቶክ አምላክ ይክፈልህ ! Melaku Berhanu- የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ… https://t.me/AdissAdmas

የ"ተፅዕኖ ፈጣሪነት" መለኪያው ግራ ያጋባል ! -የግል ምልከታ እንደወረደ- እኔ እንዳው ይኼ ተፅዕኖ ፈጣሪ፣ ኮንቴንት ክሪኤተር ወዘተ በሚል ርዕሰ የሚዘጋጁ ሽልማቶች ነገር በጣምም ድንቅ እያለኝ ነው
የ"ተፅዕኖ ፈጣሪነት" መለኪያው ግራ ያጋባል ! -የግል ምልከታ እንደወረደ- እኔ እንዳው ይኼ ተፅዕኖ ፈጣሪ፣ ኮንቴንት ክሪኤተር ወዘተ በሚል ርዕሰ የሚዘጋጁ ሽልማቶች ነገር በጣምም ድንቅ እያለኝ ነው ! "ተፅዕኖ" ግን ምን ማለት ነዉ? "ተፅዕኖ ፈጣሪስ" ማነው? ዛሬ ማንም ሰዉ ኮምፒውተርን እንዲህ ሊራቀቅበት ያኔ ኮሌጅ እያለን ወርድ ኤክሴል ምናምን የምንማርበት የኮምፒውተር አኘሊኬሽን የሚባል ትምህርት ነበር። እና አስተማሪው ፈኒ ነገር ነበርና አንድ ቀን ክላስ ገብቶ የሆነች ቀላል ነገር ጠይቆን ዝም ስንል እየሳቀ ምን አለን መሠላችሁ? "እኔን እንጀራ ብላ ሲለኝ እናንተን ደደብ አድርጐ ፈጠረልኝ" አሁን ሳሰበው የሱ አባባል የዛሬ ማንነታችንን ፍንትው አድርጐ የሚገልፅ ምሳሌ ነው ። እኛን ደደብ አድርጐ ፈጥሮን መድረክና ስም ፣ ሽልማትና ክብር የሚገባቸውን ሰዎች በጎን እያለፉ ወደማይገባቸው ሰዎች ሲሄዱ ቆመን ለማየት በቃን። 12 ኛ ክፍል መጨረስ አቅቷቸው ሲንደፋደፉ ድንገት ቲክቶክ የደረሰላቸው ልጆች በጭንቅላታቸው ቆመውም ፣ ዱቄት ላያቸው ደፍተውም ፣ ላይቭ ፖፖ ላይ ተቀምጠውም፣ አፋቸውን ከፍተውም፣ አልቅሰውም፣ ተሳድበውም፣ ህዝብና ዕምነት አዋርደውም ፣ በፊልተር ሃይል ነጥተውም፣ ከወገብ በላይም ከወገብ በታችም ተወዛውዘውም ... ብቻ በልቶ ለማደር አይሆኑ ሆነው የሰበሰቡት ከተቀመጠበት ወንበር መነሳት ያቃተው ግሪሳ "ቪወር" "እንደህዝብ" ተቆጥሮላቸው ተፅዕኖ ፈጣሪ ናቸው ተብሎ ስም ሲሰጣቸው የዕዉነት አያሳዝንም? ⬇️⬇️

ነገ ከንጋቱ 11፡30 ጀምሮ ለተሽከርካሪዎች ዝግ የሚሆኑ መንገዶች ይፋ ሆኑ በነገው ዕለት በኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ አማካኝነት ለተዘጋጀው የጎዳና ላይ ሩጫ ለተሽከርካሪዎች ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን
ነገ ከንጋቱ 11፡30 ጀምሮ ለተሽከርካሪዎች ዝግ የሚሆኑ መንገዶች ይፋ ሆኑ በነገው ዕለት በኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ አማካኝነት ለተዘጋጀው የጎዳና ላይ ሩጫ ለተሽከርካሪዎች ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ ይፋ አድርጓል። ጥቅምት 15 ቀን 2019 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ መነሻና መድረሻውን መስቀል አደባባይ ያደረገ የጎዳና ላይ ሩጫ ይካሄዳል፡፡ የሩጫ ውድድር በስኬት እንዲጠናቀቅ መላው የፀጥታ አካላት ዝግጅታቸውን አጠናቀው ወደ ሥራ መግባታቸውን የገለጸው የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ፤ የሩጫው ተሳታፊዎች ፀጥታው የጋራ ጉዳይ መሆኑን ተገንዝበው ወደ መሮጫ ስፍራው ሲገቡ ለፍተሻ እንዲተባበሩም ጥሪውን አስተላልፏል፡፡ በዚህም መሰረት ሩጫው ተጀምሮ እስኪሚጠናቀቅ ድረስ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች፦ ከቅዱስ ኡራኤል ቤተ-ክርስቲያን ወደ መስቀል አደባባይ ከኦሎምፒያ ወደ መስቀል አደባባይ ከአጎና ሲኒማ ወደ መስቀል አደባባይ በወንጌላዊት ህንፃ ወደ ጎተራ ከቅዱስ ዮሴፍ ቤተ ክርስቲያን ወደ ጎተራ ከጎፋ ቅዱስ ገብርኤል ወደ ጎፋ ማዞሪያ ከሳር ቤት ወደ ጎፋ ማዞሪያ ከአፍሪካ ህብረት ወደ ብልጋሪያ ከትምባሆ ሞኖፖል ወደ ገነት ሆቴል ከጥይት ቤት ወደ ጠማማው ፎቅ ከሜክሲኮ አደባባይ ወደ ለገሃር ከቅድስት ልደታ ቤተ ክርስቲያን ወደ ለገሃር ከሰንጋ ተራ ወደ ለገሃር ከብሔራዊ ቴአትር ወደ ለገሃር ከሐራምቤ ሆቴል ወደ መስቀል ከቤተመንግስት ወደ መስቀል ከካዛንቺስ ሼል ወደ ባምቢስ የሚወስዱ መንገዶች ነገ ከንጋቱ 11፡30 ጀምሮ ውድድሩ እስኪጠናቀቅ ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ፡፡ በውድድሩ መስመር ግራና ቀኝ ለረጅምም ሆነ ለአጭር ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ፍፁም የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

ሚኒስትሮቹ በሙስና ጉዳይ በቴሌቪዥን ቀርበው ከህዝብ ጋር ሊፋጠጡ ነው የማዳጋስካር ፕሬዚዳንት ሚካኤል ራንድሪያኒሪና ሁሉም ሚኒስትሮች በብሔራዊ ቴሌቪዥን ቀርበው ሙስናን እንዴት እየታገሉ እንደሆነ ለህ
ሚኒስትሮቹ በሙስና ጉዳይ በቴሌቪዥን ቀርበው ከህዝብ ጋር ሊፋጠጡ ነው የማዳጋስካር ፕሬዚዳንት ሚካኤል ራንድሪያኒሪና ሁሉም ሚኒስትሮች በብሔራዊ ቴሌቪዥን ቀርበው ሙስናን እንዴት እየታገሉ እንደሆነ ለህዝብ እንዲያስረዱ ትዕዛዝ ሰጥተዋል። ዜጎችም በቀጥታ ስርጭት ጥያቄዎችን እንዲጠይቁ ይደረጋል። ይህ ውሳኔ የተላለፈው በጥቅምት 21 ቀን በተደረገው የሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ ነው። ይህ ትዕዛዝ የመጣው በነሀሴ ወር መጨረሻ ላይ በኦንላይን ማጭበርበር ወንጀል ታስረው የነበሩ 11 ቻይናውያን በህገ-ወጥ መንገድ ከእስር መለቀቃቸውን ተከትሎ በተፈጠረው ትልቅ ቅሌት ነው። ይህንን ተከትሎ የእስር ቤቱ ዳይሬክተር ታግደዋል፤ 15 ሰዎችም በቁጥጥር ስር ውለዋል። የፍትህ ሚኒስትሯ በእስረኞቹ መለቀቅ ላይ እጇ አለበት የሚለውን ውንጀላ ውድቅ አድርጋለች። ‘ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል’ የተባለው ድርጅት ጉዳዩ ከእስር ቤት ሰራተኞች በላይ የሰፋ በመሆኑ ገለልተኛ ምርመራ እንዲደረግ ጠይቋል። ፕሬዚዳንቱ ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተሉት ሲሆን፣ የሚኒስትሮቹ የቴሌቪዥን ቀርበው ማብራራትም በቅርቡ ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል። የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ… https://t.me/AdissAdmas

ስለዚህ ዘላቂ ሰላም የሚመጣው በፖለቲካ ለውጦች ብቻ አይደለም። እውነተኛ ሰላም የሚገነባው ወጣቱ የራሱን ሕይወት ለመገንባት የሚያስችለው የሥራ ዕድል እና የኢኮኖሚ ዋስትና ሲኖረው ብቻ ነው። የወጣቶቻችንን የኢኮኖሚና የኑሮ ጥያቄዎች በቅንነት ሳናስብ እና መፍትሔ ሳናበጅ፣ በአገራችን ሰላምና መረጋጋት ማምጣት ፈጽሞ አይቻልም። Araya Getachew Alayu የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ… https://t.me/AdissAdmas

የኢኮኖሚ ውድቀትና የወጣቱ ተስፋ መቁረጥ ላለፉት ጥቂት ጊዜያት በአገራችን ኢትዮጵያም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ በየቦታው የምናየው አለመረጋጋትና ግጭት ከዕለት ወደ ዕለት እየከፋ መጥቷል። ብዙ ጊዜ እ
የኢኮኖሚ ውድቀትና የወጣቱ ተስፋ መቁረጥ ላለፉት ጥቂት ጊዜያት በአገራችን ኢትዮጵያም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ በየቦታው የምናየው አለመረጋጋትና ግጭት ከዕለት ወደ ዕለት እየከፋ መጥቷል። ብዙ ጊዜ እነዚህን ችግሮች ከፖለቲካ ማዕቀፍ ጋር ብቻ ለማያያዝ እንሞክራለን፤ ነገር ግን ወደ መሬት ወርደን ስናየው የችግሩ ዋና መሠረታዊ መንስኤ የኢኮኖሚ ውድቀት እና የዕለት ተዕለት የኑሮ እውነታ መሆኑ ግልጽ ነው። ዛሬ በየትኛውም ዓለም ቢሆን የኑሮ ውድነት ሰውን እየፈተነ ነው፤ በበለጸጉት አገራት የዋጋ ንረትና የኮርፖሬቶች ጫና ሕዝቡን ሲያቃትት፣ በእኛ አገር ደግሞ የሥራ አጥነት እና የኑሮ ውድነት ወጣቱን ተስፋ ያስቆርጣል። የሰው ልጅ በየቀኑ እየደከመ የዕለት ተዕለት ሕይወቱ ላይ ምንም ዓይነት መሻሻል ሲያጣ በመንግሥታት እና በሥርዓቱ ላይ ያለው እምነት ይሸረሸራል። ይህ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ የስደት ማዕበልን እና አለመረጋጋትን ፈጥሯል። አንድ ወጣት ሥራ አጥቶ፣ ገቢ አጥቶ እና ነገውን የሚያስብበት ዕድል ጠቦት ሲኖር የሚሰማው የውስጥ ቁስል ቀላል አይደለም። በችግር ውስጥ ሆኖ ተስፋ ማጣት ሰብአዊ ክብርን ይነካል፤ ወጣቱ «የማጣው ነገር የለኝም» በሚል ስሜት ውስጥ ሲገባ ደግሞ ለተለያዩ አጥፊ የኃይል አማራጮች እና ግጭቶች በቀላሉ ተጋላጭ ይሆናል። በእኛ አገር ኢትዮጵያ ሁኔታ፣ የፖለቲካ ሰዎች ወይም የፓርቲ እና የመንግሥት መለዋወጥ ብቻውን በቂ መፍትሔ ሊሆን አይችልም። የችግሩ ዋና ሥር የኢኮኖሚ ውድቀት በሆነበት ሁኔታ፣ የፖለቲካ ውሳኔዎች ብቻቸውን ተአምር ሊፈጥሩ አይችሉም። ⬇️⬇️

በመጋዘኖችና በሃይማኖት ተቋማት ግቢ ውስጥ ተደብቀው ሲሸጡ የነበሩ 45 መኪኖች በቁጥጥር ስር ዋሉ የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ቂርቆስ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት፣ ፍትሃዊ የግብር ሥርዓት ለማስፈን እና ህገ
በመጋዘኖችና በሃይማኖት ተቋማት ግቢ ውስጥ ተደብቀው ሲሸጡ የነበሩ 45 መኪኖች በቁጥጥር ስር ዋሉ የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ቂርቆስ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት፣ ፍትሃዊ የግብር ሥርዓት ለማስፈን እና ህገወጥ የታክስ ስወራን ለመከላከል ባደረገው ጥብቅ ክትትል፣ ያለምንም የንግድ ፈቃድና ደረሰኝ በህገወጥ መንገድ ለሽያጭ የቀረቡ ከ45 በላይ መኪኖች ላይ ሕጋዊ እርምጃ መወሰዱን አስታወቀ። ጽሕፈት ቤቱ አንዳንድ መኪና አስመጪዎች ተሽከርካሪዎችን ከመሸጫዎቻቸው አውጥተው በየመንደሩ፣ በመጋዘኖችና በሃይማኖት ተቋማት ግቢ ውስጥ በመደበቅ ሽያጭ እያከናወኑ መሆናቸውን በመለየት ይህንን ርምጃ መውሰዱን ገልጿል። በከተማዋ በህጋዊ መንገድ ለመንቀሳቀስ የንግድ ፈቃድ ማውጣት፣ የክልል ፈቃድን በከተማው ማስጠቀስ፣ ደረሰኝ መለየትና ግብር መክፈል ግዴታ መሆኑ በተደጋጋሚ ማሳሰቢያ ቢሰጥም ሕጉን ወደ ጎን በማለት ህገወጥ እንቅስቃሴ ውስጥ በነበሩ አካላት ላይ የተወሰደው ይህ እርምጃ የከተማ አስተዳደሩ ሊያገኘው የሚገባውን ገቢ በፍትሃዊነት ለመሰብሰብ ትልቅ እገዛ እንዳለው ተገልጿል። የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ፍትሃዊነትን የማስፈን እና ህገወጥነትን የመታገል ሥራውን በቀጣይም አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስጠንቅቋል። የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ… https://t.me/AdissAdmas

Addis Admass - Telegram kanali @adissadmas statistikasi va tahlili