uk
Feedback
Addis Admass

Addis Admass

Відкрити в Telegram

የአዲስ አድማስ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ ===== አዲስ አድማስ https://bit.ly/2V1zyZQ ፌስቡክ↠ https://bit.ly/2V0I6jx ትዊተር↠ https://bit.ly/33fDhaP ቴሌግራም↠ https://bit.ly/2JgeCvG ዩቲዩብ ↠ https://bit.ly/3q2hXiv የእርስዎና የቤተሰብዎ

Показати більше

📈 Аналітичний огляд Telegram-каналу Addis Admass

Канал Addis Admass (@adissadmas) у мовному сегменті Амхарська є активним учасником. На даний момент спільнота об'єднує 19 024 підписників, посідаючи 11 828 місце в категорії Новини і ЗМІ та 1 826 місце у регіоні Ефіопія.

📊 Показники аудиторії та динаміка

З моменту свого створення невідомо, проект продемонстрував стрімке зростання, зібравши аудиторію у 19 024 підписників.

За останніми даними від 27 вересня, 2026, канал демонструє стабільну активність. Хоча за останні 30 днів спостерігається зміна кількості учасників на 405, а за останні 24 години на 1, загальне охоплення залишається високим.

  • Статус верифікації: Не верифікований
  • Рівень залученості (ER): Середній показник залученості аудиторії становить 9.52%. Протягом перших 24 годин після публікації контент зазвичай збирає 8.09% реакцій від загальної кількості підписників.
  • Охоплення публікацій: В середньому кожен допис отримує 1 812 переглядів. Протягом першої доби публікація в середньому набирає 1 539 переглядів.
  • Реакції та взаємодія: Аудиторія активно підтримує контент: середня кількість реакцій на один пост – 8.

📝 Опис та контентна політика

Автор описує ресурс як майданчик для висловлення суб'єктивної думки:
“የአዲስ አድማስ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ ===== አዲስ አድማስ https://bit.ly/2V1zyZQ ፌስቡክ↠ https://bit.ly/2V0I6jx ትዊተር↠ https://bit.ly/33fDhaP ቴሌግራም↠ https://bit.ly/2JgeCvG ዩቲዩብ ↠ https://bit.ly/3q2hXiv የእርስዎና የቤተሰብዎ”

Завдяки високій частоті оновлень (останні дані отримано 28 вересня, 2026), канал підтримує актуальність та високий рівень охоплення публікацій. Аналітика показує, що аудиторія активно взаємодіє з контентом, що робить його важливою точкою впливу в категорії Новини і ЗМІ.

19 024
Підписники
+124 години
+1097 днів
+40530 днів
Архів дописів
የመስቀል ደመራ በጎንደር ከተማ
+3
የመስቀል ደመራ በጎንደር ከተማ

photo content

የሮይተርስ የዜና ወኪል የደመራ በዓል አከባበርን አስመልክቶ በሰራው ዘገባ፤ የደመራው እሳት ከተለኮሰ በኋላ የሚወጣው ጢስ የሚያመለክተው አቅጣጫና የደመራው እንጨት ወድቆ የሚያርፍበት ሁኔታ የወደፊት አገራዊና ሃይማኖታዊ ሁኔታዎችን ለመተንበይ በምዕመናኑ ዘንድ እንደሚታመን አብራርቷል። በተጨማሪም የደመራው አመድ አማኞች ግንባራቸው ላይ የመስቀል ምልክት ለማድረግ እንደሚጠቀሙበት በመግለጽ፣ ይህ በዓል ከ1600 ዓመታት በላይ ዘመናትን ተሻግሮ በጥንታዊ ስርዓቱና በሃይማኖታዊ ክብሩ እስከ ዛሬ ድረስ በድምቀት መከበሩ የኢትዮጵያን ጥልቅ የታሪክና የሃይማኖት መሰረት እንደሚያሳይ ዘግቧል። የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ… https://t.me/AdissAdmas

ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ስለ መስቀል ደመራ በዓል ምን አሉ? ቢቢሲ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን ከሚያከብሯቸው ታላላቅ ሃይማኖታዊ በዓላት አንዱ የሆነውን የመስቀል ደመራ በዓል በማስመል
+3
ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ስለ መስቀል ደመራ በዓል ምን አሉ? ቢቢሲ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን ከሚያከብሯቸው ታላላቅ ሃይማኖታዊ በዓላት አንዱ የሆነውን የመስቀል ደመራ በዓል በማስመልከት በሠራው ዘገባ፤ በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ አባቶች፣ መዘምራን እና በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ምዕመናን ነጭ የባህል ልብስ ለብሰው የሚታደሙበት ደመቅ ያለ ሁነቶች የታዩበት መሆኑን ገልጿል። ዘገባው የደመራው እሳት መለኮስ እመቤታችን ንግሥት እሌኒ የእውነተኛውን መስቀል ቦታ ለማግኘት የተጠቀመችበትን የጢስ ምልክት የሚያስታውስ መሆኑን በመጥቀስ፣ በዓሉ ሃይማኖታዊ ይዘቱ እንደተጠበቀ ሆኖ የህዝቦችን እርቅ፣ ይቅርታ እና ማህበራዊ አንድነት የሚያጎለብት ታላቅ ባህላዊ እሴት እንደሆነ አብራርቷል። አልጀዚራ በበኩሉ የመስቀል ደመራ በዓልን በየዓመቱ በመስቀል አደባባይ የሚካሄድ የኢትዮጵያውያን የጽናትና የባህል ማሳያ አድርጎ ያቀረበው ሲሆን፣ በተለይም በዩኔስኮ የማይጨበጥ የሰው ልጅ የዓለም ቅርስ ሆኖ መመዝገቡን አጉልቶ አሳይቷል። በበዓሉ ላይ የሚታዩት በቀለም ያሸበረቁ የካህናት አልባሳት፣ የመዘምራን ዝማሬ እና ግዙፉ የደመራ ክምር ሲለኮስ የሚፈጠረው ድምቀት የበርካታ ዓለም አቀፍ ጎብኚዎችን ቀልብ እንደሚስብ የጠቀሰው ዘገባው፤ በዓሉ በየአካባቢው ያሉ ሰዎችና ከሃገር ውጪ የሚኖሩ ዳያስፖራዎች ወደ ትውልድ ቀያቸው ተመልሰው ከቤተሰቦቻቸው ጋር የሚገናኙበት ታላቅ የማህበራዊ ትስስር አጋጣሚ መሆኑን ገልጿል። ⬇️⬇️

የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን መዘምራን በመስቀል አደባባይ የደመራ በዓል መንፈሳዊ መዝሙሮችን አቀረቡ የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን የመዘምራን ቡድን በመስቀል አደባባይ በተካሄደው የደመራ በ
የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን መዘምራን በመስቀል አደባባይ የደመራ በዓል መንፈሳዊ መዝሙሮችን አቀረቡ የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን የመዘምራን ቡድን በመስቀል አደባባይ በተካሄደው የደመራ በዓል ላይ ተገኝቶ መንፈሳዊ መዝሙሮችን ማቅረቡ በሁለቱ አገራትና አብያተ-ክርስቲያናት መካከል ያለውን ጥልቅ ታሪካዊና መንፈሳዊ ወዳጅነት የሚያጠናክር ክስተት ነው ተብሏል። የመዘምራን ቡድኑ ከስፓሶ-ፕሪኦብራዤንስኪ ሶሎቬትስኪ ስታቭሮፔጂያል ገዳም ተጋብዞ እንደመጣ የስፑትኒክ አፍሪካ ዘጋቢ ገልጿል፡፡ ይህ አይነቱ ሃይማኖታዊና ባህላዊ ልውውጥ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን እና በሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን መካከል ለዘመናት የዘለቀውን የጠበቀ ግንኙነት የበለጠ ያጎለብታል። የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ… https://t.me/AdissAdmas

የደመራ በዓል በደባርቅ
+2
የደመራ በዓል በደባርቅ

ክትፎን የማጣጣም ዕድል ያገኘሁበት የመጀመሪያ አጋጣሚ ክትፎ ከስሙ ውጪ ምን ዓይነት ምግብ እንደሆነ አይቼም አለማወቄ ይገርመኛል። በሚዲያ እንኳን ምን እንደሚመሥል እንዳናይ ደ/ብርሃን ከተማ ብቸኛ የ
ክትፎን የማጣጣም ዕድል ያገኘሁበት የመጀመሪያ አጋጣሚ ክትፎ ከስሙ ውጪ ምን ዓይነት ምግብ እንደሆነ አይቼም አለማወቄ ይገርመኛል። በሚዲያ እንኳን ምን እንደሚመሥል እንዳናይ ደ/ብርሃን ከተማ ብቸኛ የሚዲያ ምንጫችን ሬድዮ ስለነበር እንዲሁም የቴሌቪዥን ሥርጭት ከኢትዮጵያ ከተሞች እጅግ ዘግይቶ በመጀመሩ፤ ቢጀምርም ጥቂት ቤቶች ብቻ የሚገኝ 'ብርቅዬ' በመሆኑ የት እንየው? በከተማዋ ጉራጌዎች በቁጥር ጥቂት ስለነበሩ እና ምግብ ቤትም ስላልከፈቱ የት እንየው? እናማ ጅማ ዩኒቨርሲቲ ሲደርሰኝ አዳዲስ ከተሞችን የማየት ዕድል ማግኘቴ እንደተጠበቀ ሆኖ ክትፎንም በአይኔ የማየት ብቻ ሳይሆን የማጣጣም ዕድል ያገኘሁበት የመጀመሪያ አጋጣሚ ነበር። አገር አቋራጭ አውቶብሶቹ ከአዲስ አበባ ጅማ ወይም ከጅማ አዲስ አበባ ሲጓዙ ለምሳ የሚቆሙት ወልቂጤ ከተማ ስለነበር በእውነቱ የክትፎና የጥብስን ለዛ ያጣጣምኩባት በጥሩ ትዝታ ያስቀመጥኳት ከተማ ናት ወልቂጤ። ያኔ መንገዱ ግማሽ አስፋልት ግማሽ ኮረኮንች ነገር ስለነበር እንዳሁኑ በጊዜ አይ'ገባም። ጉዞው ሙሉ ቀን ይፈጃል። እናም በዚያ አድካሚ ጉዞ መሐል ላይ ወልቂጤ ገጭ ብሎ ምሳ ክትፎ ከጥብስ አማርጦ መመገብ ትልቅ ዓለም ነበር። ብዙ ጉራጌ ወገኖቻችን ለመስቀል ወደየቀዬአቸው እንደሚተሙ ሳስታውስ ትዝ ብሎኝ ነው። 😊 ለክርስትያን ወዳጆቻችን መልካም በዓል ይሁንላችሁ! ሃውለት አህመድ

የመስቀል ደመራ በዓል በደብረ ማርቆስ ከተማ
+2
የመስቀል ደመራ በዓል በደብረ ማርቆስ ከተማ

አርክቴክት ፋሲል ጊዮርጊስ የአሊያንስ ኢትዮ-ፍራንሴዝ ፕሬዚዳንት ሆነው ተሾሙ ታዋቂው የቅርስ ጥበቃ፣ የታሪካዊ ሕንፃዎች እድሳት እና የአርክቴክቸር ባለሙያ አርክቴክት ፋሲል ጊዮርጊስ የአሊያንስ ኢትዮ
አርክቴክት ፋሲል ጊዮርጊስ የአሊያንስ ኢትዮ-ፍራንሴዝ ፕሬዚዳንት ሆነው ተሾሙ ታዋቂው የቅርስ ጥበቃ፣ የታሪካዊ ሕንፃዎች እድሳት እና የአርክቴክቸር ባለሙያ አርክቴክት ፋሲል ጊዮርጊስ የአሊያንስ ኢትዮ-ፍራንሴዝ የአዲስ አበባ ማዕከል ፕሬዚዳንት ሆነው መሾማቸውን ማዕከሉ በይፋ አስታውቋል። አዲሱ ፕሬዚዳንት በዘርፉ ያላቸው ሰፊ ልምድና ግዙፍ አስተዋጽኦ ለማዕከሉ አዲስ እይታና ጥንካሬ ይዞ ይመጣል ተብሎ ይጠበቃል። አሊያንስ ኢትዮ-ፍራንሴዝ በባሕልና ኪነ ጥበብ፣ በቋንቋ ትምህርት እንዲሁም በሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነትና ዲፕሎማሲ ዘርፎች በርካታ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ሥራዎችን በማከናወን የሚታወቅ የረጅም ጊዜ ታሪክ ያለው ተቋም ነው። የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ… https://t.me/AdissAdmas

በግዙፉ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ውስጥ የሚሰራው ኢትዮጵያዊው ኢንጂነር በዓለም አቀፉ የቴክኖሎጂ ግዙፍ ኩባንያ ኤንቪዲያ ውስጥ እንደ ከፍተኛ የጂፒዩ አርክቴክት (Senior GPU Architect) ሆኖ የሚ
በግዙፉ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ውስጥ የሚሰራው ኢትዮጵያዊው ኢንጂነር በዓለም አቀፉ የቴክኖሎጂ ግዙፍ ኩባንያ ኤንቪዲያ ውስጥ እንደ ከፍተኛ የጂፒዩ አርክቴክት (Senior GPU Architect) ሆኖ የሚሰራው ኢትዮጵያዊው ኢንጂነር ኦልያድ ሙሊሳ፣ ለዘመናዊ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) እና ለከፍተኛ ኮምፒውቲንግ ሥርዓቶች የሚያገለግሉ ኃይለኛ ቺፖችን እና አሰራሮችን በመቅረጽ ረገድ ትልቅ ኃላፊነት ያለው ባለሙያ ነው። በዓለም የቴክኖሎጂ መስክ ከሚገኙ ጥቂት አፍሪካውያን የላቁ ባለሙያዎች አንዱ በመሆንም ሀገሩን ያስጠራል። ኢንጂነር ኦልያድ በቅርቡ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን የጎበኘ ሲሆን፤ ኢንስቲትዩቱ በሀገር በቀል ቋንቋዎች፣ በጤና እና በግብርና ዘርፎች ላይ እያከናወናቸውን የቴክኖሎጂ ፈጠራዎች በአካል ተመልክቷል። ሀገሪቱ በኤአይ ቴክኖሎጂ ዘርፍ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ ለመሆን ጠንካራ መሠረት እየጣለች መሆኑንም አድንቋል። ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂው ዘርፍ እያደረገች ያለውን እንቅስቃሴ በማድነቅ ከሀገር ውስጥ ባለሙያዎች ጋር የዕውቀት እና የልምድ ልውውጥ ለማድረግ ፍላጎት እንዳለው አስታውቋል። የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በበኩሉ እንደ ኦልያድ ያሉ ዓለም አቀፍ ባለሙያዎች ድጋፍ የሀገሪቱን የቴክኖሎጂ ጉዞ ይበልጥ እንደሚያፋጥነው ገልጿል። የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ… https://t.me/AdissAdmas

"መስቀል የፀብ ግርግዳ የፈረሰበት የፍቅርና የሰላም መሣሪያ ነው" የመስቀል ደመራ በዓል በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በላዛሪስት ጽዮን ማርያም ቁምስና በድምቀት እ
+2
"መስቀል የፀብ ግርግዳ የፈረሰበት የፍቅርና የሰላም መሣሪያ ነው" የመስቀል ደመራ በዓል በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በላዛሪስት ጽዮን ማርያም ቁምስና በድምቀት እየተከበረ ይገኛል። በበዓሉ ላይ የሀገረ ስብከቱ እንደራሴ አባ ተስፋዬ ወልደ ማርያምን ጨምሮ የቤተ-ክርስቲያኒቷ አባቶች፣ ዘማሪያን እና በርካታ ምዕመናን ተገኝተዋል። በዕለቱ መልዕክት ያስተላለፉት አባ ተስፋዬ ወልደ ማርያም፤ መስቀል ሰማይና ምድር የታረቁበት፣ የፀብ ግርግዳ የፈረሰበት የፍቅርና የሰላም መሣሪያ መሆኑን ገልጸዋል። አያይዘውም መስቀል ትህትናን የሚያስተምር ታላቅ ምሳሌ መሆኑን ተናግረዋል። የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ… https://t.me/AdissAdmas

የመስቀል ደመራ በዓል አከባበር በአዲስ አበባ፤ በ1950ዎቹ መጀመሪያ ታሪክን_ወደኋላ
የመስቀል ደመራ በዓል አከባበር በአዲስ አበባ፤ በ1950ዎቹ መጀመሪያ ታሪክን_ወደኋላ

የሩሲያ ማስጠንቀቂያ በሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት በሰሜን ኢትዮጵያ በትግራይ፣ በአፋር እና በአማራ ክልሎች በመንግሥት ኃይሎችና በታጣቂዎች መካከል ዳግም ውጊያ መጀመሩ የሩሲያ መንግሥት ከፍተኛ ሥጋት እንደ
የሩሲያ ማስጠንቀቂያ በሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት በሰሜን ኢትዮጵያ በትግራይ፣ በአፋር እና በአማራ ክልሎች በመንግሥት ኃይሎችና በታጣቂዎች መካከል ዳግም ውጊያ መጀመሩ የሩሲያ መንግሥት ከፍተኛ ሥጋት እንደፈጠረበት አስታወቀ። የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫ በሰጡት መግለጫ፣ ተፋላሚ አካላት በአፋጣኝ ውጊያ እንዲያቆሙ እና የሰላም ስምምነቶችን እንዲያከብሩ ጥሪ አቅርበዋል። ሞስኮ የኢትዮጵያን አንድነት መጠበቅ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት ብቸኛው መንገድ እንደሆነ ታምናለች። ከዚህም በተጨማሪ ዛካሮቫ ማናቸውም የውጭ ኃይሎች በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ እንዳይገቡ ጥብቅ ማሳሰቢያ አስተላልፈዋል። የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ… https://t.me/AdissAdmas

ጦርነት ደክሞናል! ሳትነግሱ ቢቀር፣ ሳትሾሙ ለወንበር ብላችሁ፣ደም ላይ ከምትቆሙ ሳይበላ ቢቀር በደም የተሰራ በእናቶች እምባ በድሆች መከራ እናንተ የሚታያችሁ ታዋቂ ሆናችሁ ሀገር ሲያጅባችሁ፣ ትንሹ
ጦርነት ደክሞናል! ሳትነግሱ ቢቀር፣ ሳትሾሙ ለወንበር ብላችሁ፣ደም ላይ ከምትቆሙ ሳይበላ ቢቀር በደም የተሰራ በእናቶች እምባ በድሆች መከራ እናንተ የሚታያችሁ ታዋቂ ሆናችሁ ሀገር ሲያጅባችሁ፣ ትንሹ ትልቁ ሲታዘዝላችሁ፣ ገንዘብ ሲዘዋወር በአካውንታችሁ፣ ቆነጃጅት ሴቶች ደጅ ሲጠኗችሁ፣ እንደ ፈቃዳችሁ ሲጋደሙላችሁ። እኛ የሚታየን ስንት እናት አለቀሰች? ስንት ልጅ አባት አጣ? ስንት ሚስት ባሏን ቀበረች? ስንት ቤት ፈረሰ? ስንት ሕልም ከአፈር ተቀላቀለ? ደም ረግጦ የተወጣ ወንበር ላይሰጣችሁ እረፍት ላይሆናችሁ ክብር ምናለ ብትተዉን በሰላም ብንኖር አንድ ቀን ጭብጨባው ይቆማል፣ አጃቢውም ይለያል፣ አካውንቱም ይቀራል፣ ወንበሩም ለሌላ ይሰጣል፤ የፈሰሰው ደም ግን በታሪክ ፊት ይጮኻል። ወንበር ለሰው ቀርቶ፣ ሰው ለወንበር ኖረ፣ “እኔ ልንገሥ”ብሎ ስንቱ ሰዉ ቀበረ። ስልጣን ፈላጊው ብዙ፣ ስንቱን እኛ እናንግሥ? አንዱ ሲሄድ ሌላው፣ በስንቱ እንታኮስ? ባካችሁ ተስማሙ፣ጦርነት መሮናል፤ በደም ጨቅይተናል፣ የእናቶች እንባ፣ሞልቶ ፈሶብናል፣ ደክሞናል! Sofia Shibabaw- የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ… https://t.me/AdissAdmas

ታላቁ የደመራ በዓል በመስቀል አደባባይ ደምቋልታላቁ የደመራ በዓል በመስቀል አደባባይ ደምቋል
+4
ታላቁ የደመራ በዓል በመስቀል አደባባይ ደምቋልታላቁ የደመራ በዓል በመስቀል አደባባይ ደምቋል

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አጭር የመስቀል በዓል መልዕክት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለብርሃነ መስቀሉ በዓል ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ከወትሮው በተለየ አጠር ያለ ነው፡፡
+1
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አጭር የመስቀል በዓል መልዕክት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለብርሃነ መስቀሉ በዓል ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ከወትሮው በተለየ አጠር ያለ ነው፡፡ የመስቀል በዓል ሃይማኖታዊና ባህላዊ ይዘቱን ጠብቆ በመላው ኢትዮጵያ የሚከበር ታላቅ በዓል መሆኑን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ በዓሉ ቤተሰብ የሚገናኝበት፣ ሠፈር የሚሰባሰብበት እና ሕዝቡ ወደ አንድ አደባባይ የሚተምበት ልዩ እሴት ያለው መሆኑን አንስተዋል። ከእንጨት እስከ ደመራ ያለው መሰባሰብ እውነተኛውን የ"መደመር ኃይል" የሚያሳይ ተምሳሌት መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በመልዕክታቸው ጠቁመዋል። በዓሉን ስናከብር የኢትዮጵያን አቅሞች እያሰባሰብንና እየደመርን ታላቅ ሀገራዊ አቅም ለመፍጠር ሁላችንም ጥረት ማድረግ እንዳለብን አሳስበዋል። በየበዓሉ ዘለግ ያለና በተምሳሌት የደመቀ የበዓል መልዕክት በማስተላለፍ የሚታወቁት ጠ/ሚኒስትሩ፣ በዘንድሮው በዓል እጅግ አጭር መልዕክት ማስተላለፋቸው ትኩረት መሳቡ አልቀረም፡፡ የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ… https://t.me/AdissAdmas

በታሪካዊቷ ጎንደር ከተማ የዓለም የቱሪዝም ቀን እየተከበረ ነው የቱሪዝም ሚኒስቴር ከክልል ቢሮ ኃላፊዎች፣ ከግሉ ዘርፍ ተወካዮች እና ከሚዲያ አካላት ጋር በመሆን የዓለም የቱሪዝም ቀንን፣ የቱሪዝም ጉ
+2
በታሪካዊቷ ጎንደር ከተማ የዓለም የቱሪዝም ቀን እየተከበረ ነው የቱሪዝም ሚኒስቴር ከክልል ቢሮ ኃላፊዎች፣ ከግሉ ዘርፍ ተወካዮች እና ከሚዲያ አካላት ጋር በመሆን የዓለም የቱሪዝም ቀንን፣ የቱሪዝም ጉባኤን እና የመስቀል በዓልን በታሪካዊቷ ጎንደር ከተማ በጋራ ማክበር ጀምሯል። በዚህ መድረክ ላይ የቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊ ካሳ እንደገለጹት፤ የቱሪዝም ዘርፍ የሀገርን ኢኮኖሚ ለማጠናከር፣ ማኅበራዊ ትስስርን ለማጎልበት እና ታሪካዊ ቅርሶችን ለትውልድ ለማስተላለፍ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ይገኛል። በዘርፉ ላይ የሚታዩ ችግሮችን በመቅረፍ አዳዲስ ለውጦችን ለማምጣት በመዳረሻ ልማት፣ በፕሮሞሽን፣ በአገልግሎት፣ በአስተዳደር ሪፎርም እና በቴክኖሎጂ አጠቃቀም ዙሪያ በርካታ ሥራዎች መሠራታቸው ተመላክቷል። በተጨማሪም በማይስ ቱሪዝም (MICE Tourism) እየተከናወኑ ያሉ ሥራዎች እና ወደፊት የሚካሄደው የCOP32 ጉባኤ ለሀገሪቱ የቱሪዝም ዘርፍ ትልቅ ዕድል ይዘው እንደመጡ ተጠቁሟል። የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ… https://t.me/AdissAdmas

የመስቀል ደመራ ሥነ ሥርዓት በጅማ ከተማ የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ… https://t.me/AdissAdmas
+4
የመስቀል ደመራ ሥነ ሥርዓት በጅማ ከተማ የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ… https://t.me/AdissAdmas

በመኖሪያ ቤታቸው አደንዛዥ ዕፅ አከማችተው የተገኙ ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር ዋሉ በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 (ገዳም ሰፈር) በመኖሪያ ቤታቸው ውስጥ አደንዛዥ ዕፅ አከማችተው ለሽያጭ ሲያቀርቡ የነበ
+2
በመኖሪያ ቤታቸው አደንዛዥ ዕፅ አከማችተው የተገኙ ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር ዋሉ በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 (ገዳም ሰፈር) በመኖሪያ ቤታቸው ውስጥ አደንዛዥ ዕፅ አከማችተው ለሽያጭ ሲያቀርቡ የነበሩ ሁለት ተጠርጣሪዎች በሕብረተሰቡ ጥቆማ በቁጥጥር ሥር ውለዋል። ወ/ት ኤልሳ ማንደፍሮ እና አቶ ማስረሻ ማንደፍሮ የተባሉት ተጠርጣሪዎች፣ ፖሊስ ከፍርድ ቤት ባወጣው የመበርበሪያ ትዕዛዝ መሠረት በተደረገባቸው ብርበራ ለሽያጭ የተዘጋጁ 75 ጥቅልል አደንዛዥ ዕፆች ከነኤግዚቢሽኑ ተይዘውባቸዋል። ፖሊስ አደንዛዥ ዕፅ ለተለያዩ የወንጀል ድርጊቶች መንስኤ መሆኑን ገልጾ፣ ከሱስ ነፃ የሆነ ትውልድ ለመገንባት ሕብረተሰቡ አሁን እያደረገ ያለው ትብብር የሚመሰገን በመሆኑ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አሳስቧል። ተጠርጣሪዎቹም በቁጥጥር ሥር ውለው አሁን ላይ ጥልቅ ምርመራ እየተደረገባቸው ይገኛል። የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ… https://t.me/AdissAdmas

የመስቀል ደመራ በዓል በመስቀል አደባባይ የመስቀል ደመራ በዓል በመስቀል አደባባይ በተለያዩ ሀይማኖታዊ ሥነ-ሥርዓቶች እየተከበረ ይገኛል። ይህ በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ዘን
+3
የመስቀል ደመራ በዓል በመስቀል አደባባይ የመስቀል ደመራ በዓል በመስቀል አደባባይ በተለያዩ ሀይማኖታዊ ሥነ-ሥርዓቶች እየተከበረ ይገኛል። ይህ በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ዘንድ በየዓመቱ ከሚከበሩ ታላላቅ በዓላት አንዱ ሲሆን፣ በዩኔስኮ የዓለም ቅርስነት መመዝገቡ ይታወቃል። በዚህ በዓል ላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ አቡነ ማቲያስ፣ የሕንድ ማላንካራ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ አቡነ ባስልዮስ ማርቶማ ማቴዎስ ሣልሳዊ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ፣ እንዲሁም የሃይማኖት አባቶች፣ ከፍተኛ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች እና የውጭ አገር የዲፕሎማሲ ማኅበረሰብ አባላት ተገኝተዋል። የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ… https://t.me/AdissAdmasየመስቀል ደመራ በዓል በመስቀል አደባባይ የመስቀል ደመራ በዓል በመስቀል አደባባይ በተለያዩ ሀይማኖታዊ ሥነ-ሥርዓቶች እየተከበረ ይገኛል። ይህ በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ዘንድ በየዓመቱ ከሚከበሩ ታላላቅ በዓላት አንዱ ሲሆን፣ በዩኔስኮ የዓለም ቅርስነት መመዝገቡ ይታወቃል። በዚህ በዓል ላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ አቡነ ማቲያስ፣ የሕንድ ማላንካራ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ አቡነ ባስልዮስ ማርቶማ ማቴዎስ ሣልሳዊ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ፣ እንዲሁም የሃይማኖት አባቶች፣ ከፍተኛ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች እና የውጭ አገር የዲፕሎማሲ ማኅበረሰብ አባላት ተገኝተዋል። የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ… https://t.me/AdissAdmas